December 31, 2012

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት መግለጫ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“በትሕትና ዅሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችኹ በፍቅር ታገሡ፤
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” ኤፌ 4:2-3
ታሕሳሥ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
ቁጥር: ኢ/ኦ/ተ/ቤ/እ/ተ/00182005/
ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ
ዋሽንግተን ዲሲ
ለብጹዕ አቡነ ናትናኤል
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እና የአርሲ  ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስ  እና ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል
ቡራኬያችሁ ይድረሰን !
ጉዳዩ:-  እርቀ ሰላምን፣ የቤተክርስቲያንን አንድነትና የምዕመናንን መንፈሳዊ ደህንነትን ከስልጣንና ከሹመት ማስበለጥን ይመለከታል ፦

ላስ ቬጋስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ለቅ/ሲኖዶስ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ


(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 22/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 31/2012/ PDF)፦ በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ከተማ የምትገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ የሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አስመልክቶ የተማጽኖ መግለጫ አወጡ፣ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት እንዲደርስላቸውም ጠየቁ በእርቀ ሰላም የተጀመረውን ወደ አንድነት የመምጣት ጭላንጭል ማክሰም ለሚቀጥሉት የማይታወቁ አያሌ ዘመናት የምእመናንን አንገት የሚያስደፉ ሁኔታዎች እንደሚፈጥር ግልፅ ነው” ያለው መግለጫው ብፁዓን አባቶች ዕርቀ ሰላሙን ከግብ እንዲያደርሱ ጠይቋል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ተመልከቱ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

ከአሥር የማያንሱ ሊቃነ ጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ በመመረጡ አይስማሙም


·            ወጣቶቹ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲህ መስመር የሣተ አቋም የያዙበት ምክንያት ምንድር ነው? አረጋውያኑን በማስፈራራትም፣ በመናቅም የሚገፉት እስከመቼ ነው?
·            አሜሪካ ለዕርቅ የተጓዘው ልዑክ ሪፖረቱን ነገ ማክሰኞ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፤
 (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 22/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 31/2012/ PDF)፦ ከመንግሥት ጋር ቃል እንደተገባቡ የሚነገርላቸው ጥቂት ሊቃነ  ጳጳሳት “ቤተ ከህነቱን ተቆጣጥረናል፣ ከመንገዳችን  የሚገታን አይኖርም” ሲሉ እየተሰሙ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከ10 የማያንስ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የፕትርያርክ መሾሙን እሽቅድምድም እንደማይስማሙበት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ መንግሥትም በበኩሉ የሰላምና የዕርቅ ኮሚቴውን ልዑክ በሚሳዝን ሁኔታ ከሀገር በማባረር በግልጽና በአደባባይ ለዕርቁ እንቅፋት መሆኑን በድርጊቱ አረጋግጧል፡፡ በአንድ በኩል የሃይማኖት ነጻነትን እየሰበኩ በሌላ በኩል ልዑካንን ማሰር ማንገላታት ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

December 30, 2012

ቅዱስ ሲኖዶሱ የማን ነው? የእኛ ነው ወይስ?


(ከመልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ/ PDF)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ አሳውቆናል።  “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንም እንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም።

December 29, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛም አውቀናል

 • የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
 • ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
 • ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
 • የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው

 •     Listen VOA Interview
 •    ዲፖርት አደረጋቸው፤ 
 •     ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
  

December 28, 2012

ለእርቁ እንቅፋት እየሆነ ያለው ማን ነው?

ይድረስ ለደጀ ሰላም፤ መልእክት በእንተ  አቡነ ማትያስ
(ቶላ ገመቺሳ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ READ IN PDF)፦ የደጀ ሰላምን ድረ ገጽ ከሚከታተሉ አንዱ ነኝ፡፡ ጥሩ የመረጃ ምንጭ እየሆነች  በማገልገል ላይ  ስለምትገኝ ሥራዋን አደንቃለሁ፡፡ መረጃ ቁልፍ መሆኑን እንድንረዳ በተግባር አሳይታናለች፡፡ ስለቤተ ክርስቲያናችን  አጠቃላይ ጉዞ  ጥቂት የማይባሉ መረጃዎችን አቀብላናለች፡፡ በዘወትር አንባቢነቴ እድሜ ይስጥልኝ እላለሁ፡፡ ደጀ ሰላም ባትኖር እነ አባ ሰላማ ብቻቸውን ይፈነጩብን ነበር፡፡ ጉዳዩ ሳይደግስ አይጣላ ሆነና  በመናፍቃን “ብሎግ” ተብዮች አንጻር የእውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችንም ድረ ገጽ  እግዚአብሔር  አዘጋጀ፡፡

ከማይቀበሉት ፕትርክና የሚቀበሉት ምንኩስና ይበልጣል!


(ዘሚካኤል ለደጀ ሰላም እንደ ጻፉት/ READ IN PDF)፦ 
ለጊዜው የምኖረው በሰሜን አሜሪካ በመሆኑ እና የቤተክርስቲያንን መለያየት ውጤት የግፍ ቀማሽ ምዕመን በመሆኔ ብዙ ጊዜ የቤተክርስቲያንን ነገር ባሰብኩ ጊዜ እና ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች የጠፉ በመሰለኝ ጊዜ እንደ ምዕመን ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አድርጌ ምን አልባት መፍትሔ ያልመጣው ችግሩን በጥልቀት ካለመመልከት ይሆናል እልና የተሰማኝን ልጽፍ ብዕሬን ከወረቀት አገናኛለሁ፡፡ ነገር ግን እኔ የማልጠቅም ባሪያ ሆኜ ሳለሁ ለአባቶች ጳጳሳት ይህን ማስረዳት ምጥን ለእናት እንደማስተማርም ፤ ያለ አግባብ ወደ ላይ መፍሰስም እየሆነብኝ የጻፍኩትን እቀዳለሁ፡፡ አሁን ግን የምመኘውን የቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት በምንም ዋጋ ቢሆን ልንገዛ የሚገባበት ትልቅ ወቅት በመሆኑ እና ከየአቅጫው የሚሰነዘሩ ምክሮች፣ አስተያየቶች፣ ልመናዎች ወዘተ እንዳለ ሆነው የእየሩሳሌምን ጥፋት እያዩ ከመቀመጥ መጻፍን መረጥኩ፡፡

“በፓትርያርክ ምርጫ ሂደት መንግስት ጣልቃ አልገባም፤ አይገባምም” (መንግስትና ቤተክርስቲያኗ)


(አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2005, Fana Radio/ PDF) የቀደሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እረፍት ተከትሎ ፥ የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣዩን ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመሾም የሚያስችል ደንብ አዘጋጅቶ ሲመክርበት ቆይቷል።

December 27, 2012

የጉባኤ ካህናት ወምዕመናን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ጥሪ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ግልጽ ደብዳቤ 
ታኅሳስ ፲፯ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ዋሽንግተን ዲሲ
ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እና የአርሲ  ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ
ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት - የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
በያላችሁበት
ጉዳዩ: የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ከፍጻሜ ስለማድረስ: 

የታዋቂው ሰባኬ ወንጌል የመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው የዕርቅና የሰላም ጥሪ ለብፁዓን አበው

"ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው። .... በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም  ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን ይሰጣታል። ቤተ ክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች።" የመልእክቱን ሙሉ ቃል ከራሳቸው የጡመራ መድረክ “ቤተ ደጀኔ” ላይ (CLICK HERE) ያንብቡ። ዕድሜ ይስጥልን መ/ሰላም። 
  


December 25, 2012

ከአዲስ አበባ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ የመጣው ልዑክ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን መግለጫ ተቃወመ

 •     አስታራቂ ጉባኤው ይቅርታ ካልጠየቀ በውይይቱ አንሳተፍም ብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 16/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 25/2012/ READ THIS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ከግብ እንዳይደርስ “የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ” ጉዳይ እንዲቀጥል አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን ተቃውሞ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ራሱ ጠንካራ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተለይም አዲስ አበባ ያሉት አባቶች ጉዳዩን በጥሙና እንዲያስቡበት ያሳሰበው ጉባኤው ይህ ሁሉ ልፋት መና እንዳይቀር ተማጽኗል።

የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴው “የተመረጠ” ሳይሆን “የተሰየመ” ነው


(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 16/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 25/2012/ READ THIS IN PDF)፦ 6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ተቋቁሟል የተባለው አስመራጭ ኮሚቴ በጥቆማ ስም ዝርዝራቸው የተበተነ እንጂ ብዙዎቹ ይስማሙበት ወይም አይስማሙበት እንዳልተጠየቁ ምንጮቻችን ገልጸዋልይህንን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ምርጫው እንዲካሄድ በሾርኔ እንደተስማማ ተደርጎ በድረ ገጾች መዘገቡ አጀንዳው ከምርጫው ወደ ማኅበሩ እንዲዞር ለሚሹ ጥሩ አጋጣሚ ከመፍጠሩም በላይ ማኅበሩ ከቅ/ሲኖዶሱ ጋር ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማጠልሸት ለሚፈልጉ ሰዎች አስደሳች አጋጣሚ እንደፈጠረ እየተነገረ ነው።

December 24, 2012

የዴንቨር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን “ከፓትርያርክ ምርጫ ዕርቅ ይቅደም” ሲል ፋና ወጊ መግለጫ አወጣ

 •    ሌሎች አብያተ ክርስቲያንም መግለጫ እንዲያወጡ ጥሪ አድርጓል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 15/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 24/2012/ READ THIS IN PDF)፦ በአባቶች መካከል የተጀመረውን ዕርቅ በሚያደናቅፍ መልኩ በአገር ቤት አባቶች መካከል የተጀመረውን የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ የመቃወሙ እንቅስቃሴ ሥር እየሰደደ በመሔድ ላይ ነው። በአሜሪካን አገር ታዋቂና ታላላቅ ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሆነው የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለምም መግለጫውን በማውጣት ድምፁን አሰምቷል።

“ከፓትርያርክ ምርጫ ዕርቅና ሰላም ይቅደም” ማለት የጀመርንበት የመጀመሪያው እሑድ

 •      አገር ውስጥ እና በውጪ አገር የሚገኙ ሚዲያዎቻችን አንጸባርቀውታል፤
 •     ቅ/ሲኖዶስ በዚህ ሣምንት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፤ ስሕተቱን ያስተካክል ይሆን?
 •      ለምትፈጽሙት ስሕተት ሕዝቡም ታሪክም ይቅር አይላችሁም!!!
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 15/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 24/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በአባቶች መካከል ላለፉት ሁለት አሠርት ዘለቀውን መለያየት ለማጥፋት እና በግራም በቀኝም ያለውን ለማዋሐድ በተጀመረው ዕርቀ ሰላም ላይ የገጠመውን ጋሬጣ ለማንዋት ኦርቶዶክሳውያን የጀመሩት ሥር ነቀል እንቅስቃሴ መልክ እየያዘ ነው። ሚዲያዎች ሐሳቡን ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በማዳረሱ በኩል የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እያደረጉ ሲሆን አዲስ አድማስ ጋዜጣን ጨምሮ በውጪው ዓለም የሚገኙ ሬዲዮኖች “ዕርቁ ይሳካ” ሲሉ ሰንብተዋል። በተለይም የአካባቢ ሬዲዮኖች በሚበዙበት በአሜሪካ መንግሥትን የሚቃሙትም፣ የሚደግፉትም፣ አማካይ ነን የሚሉትም በአንድ ድምጽ ዕርቁ እንዳይሳካ የሚያደርጉትን አካላት ተችተዋል።

December 23, 2012

"ቅድሚያ ለእርቀ ሰላም!" (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ)


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
የተከበራችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን፣ በቅድሚያ ቡራኬያችሁ ይድረሰን። ቤተ ክርስቲያናችን ለሁለት አሥርት ዓመታት በፈተና ውስጥ እንድትቆይ ያደረገውን የልዩነት ግድግዳ አፍርሶ አንድ ሲኖዶስ፣ አንድ ፓትርያርክ፣ አንድ አስተዳደር እንዲኖራት ለማድረግ የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ዓላማ በመደገፍ ልዑካንን በመሰየም የጀመራችሁት ሂደት አስደስቶናል። ነገር ግን የእርቀ ሰላሙ ሂደት ሳይጠናቀቅ ወደ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዞ መጀመሩ በእጅጉ እንድናዝን አድርጎናል።

“ከፓትርያርክ ምርጫ - ዕርቅና አንድነት ይቅደም” ስንል ምን ማለታችን ነው?

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/ PDF)፦ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ተደጋግሞ የተገለጸ ነው ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ማድረግ ነው። ለዚህም “ተስፋ ሰጪ” ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ይህ ዳር እንዲደርስ እናድርግ። ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን አንዱ የመወያያ አጀንዳ ስለሆነ ከዕርቁ በፊት ሌላ እርምጃ አይደረግበት የሚለው ነው። ይህንን በሚጋፋ መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊትና በመንግሥት ተጽዕኖ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል። ሁለቱ አጀንዳዎች የሚገናኙት እዚህ ላይ ነው።

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋሸንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ መግለጫ


የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው። 
(ታኅሳስ 13  2005 ዓ. ም/ PDF):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ መንበረ ፕትርክና ከማግኘቷ በፊት ለ 1600 ዓመታት ከግብጽ በሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ማርቆስ ሥር ስትተዳደር መቆየቷ ይታወሳል ። በእነዚህ ባሳለፈቻችው ዘመናት የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጠበቅ በነበራት ጽኑ አቋም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ችግር በገጠማትም ጊዜ ከግብጽ የሚመጡ አባቶች ሲቀሩባት እንኳን  ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ምስክርነቷን እየሰጠች ፤ በርካታ ሊቃውንትን ፤ በቅድስና የከበሩ አባቶችን  ይዛ ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ስትል ግን ከመንበረ ማርቆስ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲላኩላት ስትማጸን ኖራለች።

December 22, 2012

እሑድ ታኅሣሥ 14/2005 ዓ.ም - ከቅዳሴ በኋላ “ከፓትርያርክ ምርጫ ዕርቅና ሰላም ይቅደም” የምንልበት ቀን ስለማድረግ


(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/ READ IN PDF)፦ ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንድትቆም ያደረጉ ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ለማድረግ ያልቻልነው ለምንድነው? የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው የአባቶች በውግዘት መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን ጉዳይ ነው።

መኳንንት እጆቻችሁን ከቤተ ክርስቲያን አንሡ


“አንስኡ እደዊክሙ መንንት እም ቤተ ክርስቲያን
 (መኑ ከማከ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ READ IN PDF)፦ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአዳም ልጆችን ለሰማያዊ ርስት የምታዘጋጅ መንፈሳዊ ተም ናት፡፡ ባለቤቱ በማዕከለ ምድር ቀራንዮ የተሰቀለበት፣ እር ለጌታዋ ሙሽራ ሆና የምትኖርበት ምክንያት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በእንጨት ፍሬ የወደቀውን የአዳምን ዘር ወደ ቀደመ ክብሩ እና ቦታው መመለስ፡፡ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት ማሸጋገር ነው፡፡ በአርባ እና በሰማንያ ቀን ከተቀበልነው የልጅነት ሥልጣን አንሥቶ እስከ መጨረሻው የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ /ፕትርክና/ ያለው ሥልጣንና ላፊነት ሁሉም አንድ ዲናር ለማግኘት የምንሰራባቸው ናቸው፡፡ አንድ ዲናር አንድ መንግሥት አንድ ክብር በማለት ይተረጎማል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ።


ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።”
      (DEC. 21/2012 ታኅሣስ 12/2005 ዓ/ም/ PDF):- በዚህ ታሪካዊ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተሰይመው የተላኩት ልዑካን በፍጹም መከባበር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት በስፋት ተወያይተዋል።

The EOTC Patriarchate: A Cause for Disunity


(By Teklu Abate EXCLUSIVELY for Deje Selam):- The division of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church (EOTC) into two competing synods has a single cause: the way the most infamous patriarch, the late Abune Paulos, was instated as leader of the church twenty years ago.

December 21, 2012

“Men of God” who made indecency acceptable


(Tamrat Demeke For Deje Selam, Atlatna):- Report has it; men in Addis Ababa Synod are in full steam ahead to elect/select the 6th Patriarch. I am astoundingly ashamed to be an Ethiopian Orthodox Church follower.  After the death of the 5th Patriarch, for anyone with slightest sense of comprehension, it’s a no brainer to take advantage of this golden opportunity to heal so many broken pieces of the church.

ፖለቲካዊ ፓትርያርክነት፤ የዘመናት ጉስቁልና


(ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ/ PDF):- ታሪክ የአስተዋዮች መሠረት ነው፡፡ ትናንትን ቸል ያለ ስለማንነቱ ካለማወቅና የሌሎች ማንነት ላይ ካለው ንቀት ወይም ጥላቻ ጋር የተያያዘ ስህተቶችን ያበዛል፡፡ ስለዚህም የፓትርያርክነትን ዳራ የመረመረ በፓትርያርክ ሹመት ዙሪያ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትን ለመድገም ሲፈልግ ከማንነት ጋር፣ ከፍትሕና ሰብአዊነት ጋር የተያያዘ ስህተቶችን ለመሥራት ወስኖ መሆን አለበት ብሎ መጠርጠር ተገቢ ነው፡፡ ሃይማኖት ሰብአዊነትን ወደ ፈጣሪ ክብር መጥራት እንጂ ሌላ ምንም አይደለምና፤ እንስሳዊም ሳይንሳዊም፣ ፈላስፋዊም አይደለም፤ ሰው ሆኖ በፈጣሪ መፈጠር ብቻ የሚበቃው መጠራት፡፡

December 20, 2012

6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ሩጫ ለማትደግፉ በሙሉ

መፈክራችን - “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚል ነው።

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 20/2012/ PDF)፦ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ተጠናክሮ በመቀጠል አሁን “አስመራጭ ኮሚቴ” በማቋቋም ትልቅ ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ መምረጡ እየተጓዘ ነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)