November 27, 2012

ደጀ ሰላም፦ 6 የአገልግሎት ዓመታት

  •     “የኦርቶዶክሳውያን ጦማርያን ትብብር” እንዲጀመር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 
  •     ደ/ሰላም - “ከምንም በላይ እና ከምንም በፊት የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ትላለች። 
  •     በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተል “ሪፖርት” የሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያን “አለን” እንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

(ደጀ ሰላም ኅዳር 18/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም” እንደሚለው ደጀ ሰላምም ላለፉት ስድስት ዓመታት የቤተ ክርስቲያን ዓይንና ጆሮ በመሆን ስታገለግል ቆይታለች። የተለያዩ ዜናዎችን፣ ማስተዋወቂያዎችን፣ ምልከታዎችን፣ ርእሰ አንቀጾችንና ለቃለ ምልልሶችን እንዲሁም የተለያዩ ኦዲዮና ቪዲዮ ዝግጅቶችን አቅርባለች።


በነዚህ ዝግጅቶች ሕዝበ ክርስቲያኑ ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ትክክለና መረጃ እንዲያገኝ ከማድረጓም በላይ በአባቶችና በሕዝቡ መካከል የነበረውን የመረጃ ገደል ለማጥበብ ችላለች። በርግጥ መረጃዎቹ “ዓይንህን ጨፍን አገር አማን ነው” ወይም “ጅቡ እግርህን እየበላውም ቢሆን ዝም በል” በሚል ቆላቂል የዋህነት የተያዙ ሳይሆኑ “ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን ነው” የሚሉ ደወሎች ናቸው። ከእንቅልፉ መንቃት የማይፈልገውና እንዲነቃበት የማይሻው በጋራ “ያገር ያለህ፣ ያዙልን እሰሩልን” ሲሉ ቢቆዩም ብዙው ክርስቲያን ግን “እስከመቼ እንተኛለን” ሲል ቆይቷል።

አገልግሎታችን ያነቃቃቸው ሰዎች መኖራቸው ሲታወቅ የቤተ ክርስቲያንን ካዝና በመዝረፍ፣ ኑፋቄ በመዝራትና በመቀሰጥ የሚፏልሉት ወገኖች ኃይላቸውን አስተባብረው ደጀ ሰላም በኢትዮጵያ እንዳትከፈት ለማድረግ ችለዋል። ምንም እንኳን የምንሠራው ሃይማኖታዊ ሥራ ቢሆንም መንግሥት ወይም በመንግሥት የሥልጣን ወንበር ላይ የተቀመጡና የኢንተርኔት ቁልፉን የያዙ ወገኖች የደጀ ሰላምን መነበብ ለመከልከል ሞክረዋል። ነገር ግን አሁንም “በጓሮ በሮች” (ፕሮክሲዎች”) እና በማኅበራዊ ድረ ገጾች አማካይነት ተነባቢነቷን ጠብቃ ለመዝለቅ ችላለች።

ቤተ ክርስቲያን  አሁን ያለችበት ሁኔታ “ደጀ ሰላም” ስትጀመር ከነበረው ይለያል። ሙስናና ኑፋቄ መልስ የሚፈልጉ ዐቢይ ችግሮች መሆናቸውን በውስጥም በውጪም ላለው፣ ለወዳጁም ለጠላቱም ግልጽ ሆኗል። መልስ ከመስጠት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ግልጽ ሆኗል። መልስ ለመስጠት ሙከራውም ተጀምሯል። ለዚህም ቅ/ሲኖዶስ ዋነኛውን እንቅስቀሴ በመጀመር የለውጥ ዘመን መጀመሩን አብስሯል። ቤተ ክርስቲያን የኑፋቄና የሙስና ቤት እንድትሆን የተፈቀደበት ዘመን አብቅቷል። ለዚህም ደጀ ሰላም ትልቅ ደስታ ይሰማታል። ደጀ ሰላማውያንም እንዲሁ።

ከዚህም ባሻገር በቤተ ክርስቲያን ላለው አገልግሎት እንቅፋት የነበረው አባቶች መለያየትና መከፋፈል መፍትሔ የሚያገኝበት ዋዜማ ላይ ደርሰናል። በሁለቱም በኩል ያሉት አባቶች ለእርቁ ፈቃደኛ መሆናቸውን ከማሳየትም በላይ ቤጉባኤዎቻቸው በአጀንዳነት በመነጋገር ለፊት-ለፊት ውይይት ቀጠሮ ይዘዋል። ሰሞኑንም በዳላስ ቴክሳስ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትልቅ እመርታ ነው። “ደጀ ሰላም” ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መጠበቅ አቅሟን ያህል እንደመድከሟ ውይይቱን ከዚህ ደረጃ በመድረሱ በእጅጉ ደስተኛ ናት። ነገር ግን ይህንን ሁሉ መንገድ ያቋረጠው ድርድር መክኖ እንዳይቀር ከሕዝበ ክርስቲያኑ ብዙ ይጠበቃል። በሁሉም በኩል ላሉት አባቶች “ወይ አንድ ሁኑ፣ ወይም የፍቅር ቤት በሆነችው ቤተ ክርስቲያን አትነግዱ” የሚል መልእክት ማስተላለፍ ያስፈልጋል። “ደጀ ሰላም” ለዚህ አጀንዳ ትልቅ ትኩርት ትሰጣለች። ከምንም በላይ እና ከምንም በፊት “አንድነት” ትላለች።

እንግዲህ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በጸሎታችሁ እና በምክራችሁ እየታገዝን የአቅማችንን አህል ደክመናል። ከዚህ በኋላ ደግሞ “ባረጀ በሬ” በማረስ አንዘልቅም። ብቻችንን ብቻ ሳይሆን በግራም በቀኝም ያላችሁ ደጀ ሰላማውያን አብራችሁን እንድትሰሩና እንድታገለግሉ የሚያስፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን። ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማል የምትሉትን ማንኛውንም የመረጃ ምንጭ በመሆን፣ ጽሑፎችን በመላክና ቴክኒካዊ እገዛዎች በመስጠት እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

ሰባተኛው ዓመት የውይይት፣ የምክክርና የመፍትሔ ዓመት እንዲሆን እንፈልጋለን። በመጪው ፓትርያርክ ጉዳይ ዙሪያ፣ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ዙሪያ፣ በኑፋቄና ሙስና መፍትሔ ዙሪያ አንባብያን የመፍትሔ ሐሳቦችን በመስጠት እንድትተባበሩ ትጋበዛላችሁ። የኛ ኃላፊነት ደግሞ ጽሑፎቻችሁን ለሕትመት በማመቻቸት እና በማውጣት በኩል ይሆናል። ላለፉት ስድስት ዓመታት ስናደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁን የመረጃና የዜና ምንጭ መሆናችንን እንቀጥላለን።    

ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ከመላው ዓለም አሉ አንባብያን ሲከታተሉን ቆይተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀጥተኛ ተነባቢነታችን በመዘጋቱ በቁጥር ደረጃ ‘እንዲህ ነው” ለማለት አልቻልንም። ከዚህ ውጪ ከአሜሪካ እስከ አውስትራሊያ. ከአውሮፓ እስከ ደቡብ አፍሪካና ኬኒያ፣ ከቻይናና ጃፓን እስከ ደቡብ ኮሪያ አንባብያን መኖራቸውን “ስታቲስቲኩ” ያሳያል። ደጀ ሰላም በዚህ ዓመት ሚሊዮኖች ጊዜ ተከፍታለች። በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያነቧታል። በፌስቡክና ትዊተርም ይከታተሏታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አንባብያን “የኢ-ሜኢል” አድራሻቸውን በማስገባት በኢ-ሜይላቸው መከታተል ይችላሉ። ቁልፉን የያዙት ሰዎች በሩን እስኪከፍቱ ድረስ።

“ደጀ ሰላም” አገልግሎት መስጠት ከጀመረች ወዲህ ብዙ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥብቅና በይፋ ማሳየቱ የቆረቆራቸው ሰዎች በተለይም መናፍቃኑ ብዙ የጡመራ መድረኮችን በመክፈት “ደጀ ሰላምን” ለመዋጋት በመሞከር ላይ ናቸው። በዚህ ደግሞ ደስተኞች ነን። እምነታቸውን በይፋ መግለጻቸው በራሱ ትልቅ ውጤት ነው።

የቀና እምነት ያላቸው ሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም በቅንዓት-መንፈሳዊ መጦመር እየጀመሩ አንዳንዶቹ ሲያቆሙ የተወሰኑት አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው። ካቆሙት የተወሰኑትን ተሐድሶዎቹ “ስማቸውን በመስረቅ” መጠቀም መጀመራቸውን አይተናል። ሌላው ቀርቶ በደጀ ሰላም ስም “ሌላ ደጀ ሰላም” በመጀመር ለማጭበርበር ሞክረውም ነበር፡፤ አልተሳካም እንጂ። አሁን በማገልግል ላይ አሉት ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች በያዙት መቀጠል አለባቸው። ለዚህም ሙያዊ ርዳታ ለሚፈልጉ ጦማርያን ያሉንን መጻሕፍት “በማዋስ”ና ተሞክሮ በማካፈል ለመርዳት ፈቃደኞች ነን። በዚህ አጋጣሚም “የኦርቶዶክሳውያን ጦማርያን ትብብር” እንዲጀመር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። “ትብብሩ” መረጃ በመለዋወጥ፣ ልምድ በመካፈል፣ በመተራረምና በመማማር ደረጃ ብዙ ጥቅም ሊሰጥ ይችላል። ይህንን ለማድረግ “ፈቃደኛ” የሆኑ ደጀ ሰላማውያን በኢ-ሜይል ቢያስታውቁን በደስታ እንቀበላለን።

በሌላውና ርዳታ በምንፈልግበት አንዱ ዘርፍ በየአኅጉሩ/በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተል “ሪፖርት” የሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያን “አለን” እንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እስካሁን በፈቃደኝነት አብረውን ለመሥራት የጠየቁን የአውስትራሊያውን አንድ ደጀ ሰላማዊ ከወዲሁ በማመስገን፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአፍሪካና የተለያዩ አገሮች፣ በአውሮፓና መካከለኛው ምሥራቅ እንዲሁም በአገር ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ያሉ ሰዎች አብረውን እንዲያገለግሉ እነሆ በትህትና እንጠይቃለን።

አስተያየታችሁን እንጠብቃለን።
  
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡


11 comments:

Anonymous said...

በሰመ አብ ወወልድ ውመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ደጀ ሰላም እንክዋን አደረሰሽ መልካም ዜና ነው ::ደጀ ሰላምን በየቀኑ ብቻ ሳይሆን በየሰዓቱ ከምያነቡት ውስጥ የመጀመሪያው መሆኔን በእርግጠኝነት እናገራለሁ :: በዚሁም እቀትላለሁ ብዬ አስባለሁ በማንበብ ብቻ ሳይሆን እንዳላቹት በመራዳት የቻልኩትን ሁሉ ባደርግ ደስተኛ ነን :: ምክንያቱም አስፈላጊ በሆነ ወቅት አስፈላጊ ነገር ነው የምታቀርቡት መቸም ሥራችሁን እዚህ መዘርዘር በቂ ነገር አይገኝለትም ብቻ አምላክ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ ከዚህ በላይም እንድትሠሩ እሱ ይርዳችሁ የአምላክ እናት ከእናንተ ጋር ትሁን ::ባጠቃላይ ነገር ቤተ ክርስቲያናችን ከገባችበት ቀውስና ፈተና ወጥታ የምንፈልጋት እውነተኛ ሆና የምትሄድበትን ጊዜ እንናፍቃለን :: በርቱ በርቱ አንበርታ በያለንበት እግዚአብሔር ይርዳን

Anonymous said...

Nice Openness. God always bless your plan and your work. Warm blessing for you!

Anonymous said...

enkuan adersachihu.... Bertu!

Anonymous said...

እደጉ ተመንደጉ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ::እኔም በአቅሜ የትቻለኘን መረጃ አቀብላለሁ

Anonymous said...

እንኳን አደረሳችሁ፦ ያለምንም ዋጋ እንዲህ ላገለገላችሁን እግዚአብሄር በሰማይ መልካሙን ዋጋ ይክፈላችሁ፥፥

Anonymous said...

I have no problem to read Deje Selam by using www.suresome.com in Ethiopia. so I think it is good to tell to all dejeselamwian to use this proxy. I share to my friends and they told me that they are enjoing ur information.

Anonymous said...

Excellent Job Deje Selam
PLS KEEP IT UP

MAY GOD BE WITH U

ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለችበት ሁኔታ “ደጀ ሰላም” ስትጀመር ከነበረው ይለያል። ሙስናና ኑፋቄ መልስ የሚፈልጉ ዐቢይ ችግሮች መሆናቸውን በውስጥም በውጪም ላለው፣ ለወዳጁም ለጠላቱም ግልጽ ሆኗል። መልስ ከመስጠት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ግልጽ ሆኗል። መልስ ለመስጠት ሙከራውም ተጀምሯል። ለዚህም ቅ/ሲኖዶስ ዋነኛውን እንቅስቀሴ በመጀመር የለውጥ ዘመን መጀመሩን አብስሯል። ቤተ ክርስቲያን የኑፋቄና የሙስና ቤት እንድትሆን የተፈቀደበት ዘመን አብቅቷል። ለዚህም ደጀ ሰላም ትልቅ ደስታ ይሰማታል። ደጀ ሰላማውያንም እንዲሁ።

T/D said...

This is good. Please keep going. And also update your news as you used to do before.

Anonymous said...

AMLAK CHEMRO CHEMRO YABERTACHIHU YEBETEKRSTIYAN AMLAK YTEBKACHIHU

Anonymous said...

እንኳን አደረሳችሁ
እንኳን አደረሳችሁ
እንኳን አደረሳችሁ

Anonymous said...

ውድ የደጀ ሰላም ብሎግ አዘጋጆችእንኳን ለ6ኛው ዓመት የተሳካ አገልግሎት የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አነሳስቶ ያስጀመራችሁ፣ አስጀምሮም በአገልግሎቱ እየደገፈ ለዚህ ያበቃችሁ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ አሜን፡፡ መረጃ ኃይል ነው፡፡ መረጃ እውቀት ነዉ፡፡ መረጃ የሌለዉ ሰዉ ደንቆሮ ብቻ ሳይሆን ልፍስፍስ ጭምር ስለሚሆን ምንም ሥራ መሥራት አይችልም፡፡ ላለፉት 6 ዓመታት ለሚመለከተው ሁሉ አጥጋቢ መረጃዎችን በመስጠታችሁ የሚመለከታቸው ሁሉ ታላቅ መነቃቃትና ለዉጥ የሚያመጡ ወሳኔዎችን እንዲወስኑ አግዛችኋል፡፡ ሁላችንም አካባቢያችንን በንቃት እንድንከታተልና መረጃዎችን ወዴት መላክ እንዳለብን አውቀናል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መከራ ለማቅለል በቁርጠኝነት የሚደክሙና መረጃዎችን በማስረጃ እያስደገፉ የላኩላችሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በሕይወታቸው ወረቃማ ታሪክ አስመዝግበው በማለፋቸዉ እንኳን ደስ አላችሁ በሉልን፡፡ እናንተንም ለበለጠ አገልግሎት ያትጋችሁ፡፡ አምላከ ቅዱሳን መጪውን ዘመን ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ብሩህ ያድርግልን አሜን፡፡

ውድ የደጀ ሰላም ብሎግ አዘጋጆችእንኳን ለ6ኛው ዓመት የተሳካ አገልግሎት የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አነሳስቶ ያስጀመራችሁ፣ አስጀምሮም በአገልግሎቱ እየደገፈ ለዚህ ያበቃችሁ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ አሜን፡፡ መረጃ ኃይል ነው፡፡ መረጃ እውቀት ነዉ፡፡ መረጃ የሌለዉ ሰዉ ደንቆሮ ብቻ ሳይሆን ልፍስፍስ ጭምር ስለሚሆን ምንም ሥራ መሥራት አይችልም፡፡ ላለፉት 6 ዓመታት ለሚመለከተው ሁሉ አጥጋቢ መረጃዎችን በመስጠታችሁ የሚመለከታቸው ሁሉ ታላቅ መነቃቃትና ለዉጥ የሚያመጡ ወሳኔዎችን እንዲወስኑ አግዛችኋል፡፡ ሁላችንም አካባቢያችንን በንቃት እንድንከታተልና መረጃዎችን ወዴት መላክ እንዳለብን አውቀናል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መከራ ለማቅለል በቁርጠኝነት የሚደክሙና መረጃዎችን በማስረጃ እያስደገፉ የላኩላችሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በሕይወታቸው ወረቃማ ታሪክ አስመዝግበው በማለፋቸዉ እንኳን ደስ አላችሁ በሉልን፡፡ እናንተንም ለበለጠ አገልግሎት ያትጋችሁ፡፡ አምላከ ቅዱሳን መጪውን ዘመን ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ብሩህ ያድርግልን አሜን፡፡


ኃይለማርያም

ከደብረ ብርሃን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)