November 4, 2012

አቡነ ቴዎድሮስ፤ 118ኛው የግብጽ ኮፕት ፖፕ ሆኑ

(ደጀ ሰላም ጥቅምት 25/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 4/2012/ READ IN PDF)፦ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ጥቅምት 25 ወይም ኖቬምበር 4 ባደረገችው የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስን 118ኛው ፖፕ እንዲሆኑ ሰይማለች፡፡ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ሥርዓቱ ለመላው ዓለም በተሰራጨበትና ዓይኑን በጨርቅ የተጠቀለለ ሕጻን ዕጣውን ባወጣበት ሥርዓት “አቡነ ቴዎድሮስ” 118ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል። የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ላለፉት 40 ዓመታት የመሩት 117ኛው ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንደነበሩ ይታወሳል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

4 comments:

Anonymous said...

http://www.guardian.co.uk/world/2012/nov/04/egypt-coptic-pope-balancing-act

Unknown said...

ሰላም ለክሙ ኦ ደጀ ሰላማውያን ። ለምን ይሆን ግን ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ጉባኤው ያወጣውን መግለጫ በድረ ገፃችሁ ያላወጣችሁት? በመንግስት በኩል ችግር ይገጥመናል ብላችሁ ይሆን? ስለግብጽ ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ ስትዘግቡ ለምን የራሳችሁ የሆኑትን በግፍ ተሰደው ያሉትን አባቶች ትረሳላችሁ ?ግብጻውያን በምን መመዘኛ ነው የእኛ ወዳጆች የሚሆኑት? በቆዳ ቀለማችን ምክንያት እኮ ነው ኢየሩሳሌም የዴር ሱልጣን ባለቤትነታችንን ለማሳጣት መነኮሳቶቻችንን ሁልጊዜ ሲያጠቁ የሚኖሩት። ዘረኞችና አጭበርባሪዎች መሆናቸውን የማታዉቁ ከሆነ በ325/318 ዓ.ም በኒቂያ ጉባኤ በ318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ መሠረት ኢትዮጵያውያን ከተወላጆቻቸው መካከል ሊቀ ጳጳስ መሾም አይችሉም ብለው ወስነዋል ብለው እኮ ነው ከ1600 ዘመን በላይ በቅኝ ግዛት ቤተ ክርስቲያናችንን የገዟት። (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥ. 50) ኮፕቲኮች በጣም አጭበርባሪዎችና ዘረኞች እንጅ ክርስትናቸው እኛን የሚማርክ አይደለም።

Anonymous said...

Dear Dejeselam editors,
If you are fair and really want our church to stay as one, I would tihink you will put or post an artichle from the synod here in the USA as well. Either you don't acknowlage it or you are just not fair at all. I would suggest for the editors at least give your readers the choice, keep inmind wether you post it or not readers will find it, but to be fair let the readers have a choice. You may not like or agree with the synod here, but that is not for you to decide.

asbet dngl said...

መወቃቀሱን ለግዜው ቆም እናርግና ወደ መልዕክቱ ትኩረት ብናደርግ መልካም ይመስለኛል:: የኢትዩጵያ ኦርተዶክስ በተክርስትያን የ6ኛ ፖትሪያርክ ምርጫ ጉዳይ ለምእመን አልገባ ያለን ይመስለኛል:: ለዚህም ነው በተለያዩ አገሮች ተምሳልነት የምንጠቆም ያለን:: ምርጫው ተፈለገም አልተፈለገ አይቀሪ ከሆነ ባይሆን ይጸለይበትና እንደጐረቤት አገር እንደተደረገው አይኑን በጨርቅ በታሰረ ትንሽ ልጅ ምርጫው በእጣ ይካሄድ ለማለት ነው:: በእጅ ምርጫ የቀበሌ ነው እንጅ የሐዋርያት አባቶቻችን አስተምህሮ የወረደ ተሞክራዌ አገልግሎት አይደለም:: የምርጫው ጐዳይ በእንዴህ አይነት በተረጋጋ ሁኔታ መከናወን ከቻለና በውጭ ሀገር ያለውንም የበተክርስትያን ችግር በአስፈላጌ ሁኔታ አባቶች ሐዋርያዌ ተጋድሎ በማድረግ ለአንዴና ለመጨረሻ መቌጠሪያ ቤያደርጉለት ለኛም የህልና እረፍት ለአባቶችም ትልቅ ከመቃብር በላይ የሜቀር ታሪክ ይሆን ነበር:: ሊላው ይህ በየአገሩ ተቀምጠን የእንተርነት አርበኞች እባካችሁ የምትጽፏትን አወቁ:: መናገርና መስራት ይለያያል:: አልያም በሩቅ ሳይሆን በቅርብ: በብዕር ሳይሆን በተግባር: በማዘዝ ሳይሆን በራስ ቀርቦ በመተግበር ቀረብ በሉና ሞክሩት:: በተለይ ማህበረ ቅዱሳንን ስራቸውን ስንነቅፍ እኛስ በነጻ አለም ተቀምጠን ምን ሰራን ብየ ሳስብ ስብከት ከመስማት ሌላ ምንም ይሆናል መልሱ:: ስለዚህ ዝም እንበል::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)