November 29, 2012

መልአከ ሕይወት ሐረገ ወይን ብርሃኑ ስለ ዕርቅ እና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት
ምንጭ፦ “ግእዝ በመስመር” የጡመራ መድረክ ሲሆን ጦማሪው አዘጋጅተው ስለላኩልን ከልብ እናመሰግናለን።

November 27, 2012

ደጀ ሰላም፦ 6 የአገልግሎት ዓመታት

  •     “የኦርቶዶክሳውያን ጦማርያን ትብብር” እንዲጀመር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 
  •     ደ/ሰላም - “ከምንም በላይ እና ከምንም በፊት የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ትላለች። 
  •     በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተል “ሪፖርት” የሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያን “አለን” እንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

(ደጀ ሰላም ኅዳር 18/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም” እንደሚለው ደጀ ሰላምም ላለፉት ስድስት ዓመታት የቤተ ክርስቲያን ዓይንና ጆሮ በመሆን ስታገለግል ቆይታለች። የተለያዩ ዜናዎችን፣ ማስተዋወቂያዎችን፣ ምልከታዎችን፣ ርእሰ አንቀጾችንና ለቃለ ምልልሶችን እንዲሁም የተለያዩ ኦዲዮና ቪዲዮ ዝግጅቶችን አቅርባለች።

November 25, 2012

Jesus was born years earlier than thought, claims Pope


(TelegraphRome) The entire Christian calendar is based on a miscalculation, the Pope has declared, as he claims in a new book that Jesus was born several years earlier than commonly believed. The 'mistake' was made by a sixth century monk known as Dionysius Exiguus or in English Dennis the Small, the 85-year-old pontiff claims in the book 'Jesus of Nazareth: The Infancy Narratives', published on Wednesday.

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? (እንደገና እንጠይቅ)

  •  ቅዱስነታቸው ስለ ራሳቸው እና ስለ ፕትርክናው ሊናገሩ ይገባቸዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 31/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ ከሆነ እነሆ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ባለው ሥልጣን መሠረት ተተኪው ፓትርያርክ እስከሚሰየም ድረስ አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ” ይሆኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሰይሟል። ቤተ ክርስቲያኒቱ 5ኛውን ፓትርያርኳን በሐዘን እያሰበች ባለችበት በአሁኑ ወቅት “ቀጣዩ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ በስፋት በመጠየቅ ላይ ይገኛል። ድምጻቸው ቀላል ያልሆኑ ኦርቶዶክሳውያንም “እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊሰጥ ዕድል ከፍቶልን ሳለ፣ የቀደሙትን አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ ሲገባ የምን አዲስ ምርጫ ነው?” እያሉ ነው። ለደጀ ሰላም የደረሱ ብዙ መልእክቶችም ይህንን በማበከር ላይ ይገኛሉ። በዚህ አጋጣሚ ደጀ ሰላም” አንድ ሁነኛ ጥያቄ ማቅረብ ትፈልጋለች። የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? ድምጽዎትን ለምን አንሰማም? ሐሳብዎን ለምን አይገልጹም? ከምዕመኖችዎ ጋር በቱርጁማን፣ በስማ በለው፣ በተላላኪ፣ በሦስተኛ ወገን መነጋገር መቼ ነው የሚያበቃው ለማለት እንወዳለን። አንባብያንም ሐሳባችሁን እንድታካፍሉን እንጋብዛለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

November 9, 2012

በጋሻው ደሳለኝና አሰግድ ሣህሉ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 30/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 9/2012, READ THE NEWS IN PDF)፦ ሃይማኖት ጉዳይ በተነሣባቸው ጥያቄ ምእመኑ ዓይናችሁን ላፈር ያላቸው ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በተለይ በበጋሻውና በባልንጀሮቹ ላይ ጠበቅ ያለ አጀንዳ እንደተከፈተባቸው ለረዥም ጊዜ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ጉዳዩ በቅዱስነታቸው እረፍት እና በመከካሉ በመጣው ጊዜ ክፍተት ተረሣ ቢመስልም “ይደር” ተባለ እንጂ “ይዘጋ” ስላልተባለ እነሆ ርዕሳችን አድርገነዋል። በድጋሚ። ከበጋሻው እንጀምር።

November 8, 2012

ለአዲስ አበባ አራት አህጉረ ስብከት ሥ/አስኪያጆች ተሾሙ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የገነገነውን ሙስናና ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያቀረበውን ጥናት የመረመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሀገረ ስብከቱ በአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ እንዲደራጅ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ስለ አከፋፈሉ እና አደረጃጀቱ መነሻ “አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኽት በዝቷልና” በማለት የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ ለጋዜጠኞች ያስረዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በየአካባቢያቸው እንዲስተናገዱ በፓትርያርኩ ጊዜ በአባቶችና ሊቃውንት ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ጉዳይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ቀሲስ በላይ መኰንን ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲንነት ተነሡ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ባለፉት የዜና ዘገባዎቻችን ስንጠቅሳቸው የነበሩትና በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን የነበሩት ቀሲስ በላይ መኰንን ከዚህ ሓላፊነታቸው መነሣታቸው ታውቋል፡፡ የደጀ ሰላም ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰሞኑን በሚደረገው የከፍተኛ ሓላፊዎች ሽግሽግ ቀሲስ በላይ መኰንን የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሓላፊው አማካሪ ኾነው መመደባቸውን እየተነገረ ነው፡፡ በርካታ ዋና ዲኖች በፍጥነት በሚቀያየሩበትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሳይሆን የመቅጫ ቦታ ተደርጎ በሚታሰበው መንፈሳዊ ኮሌጅ ለስድስት ወራት የቆዩት ቀሲስ በላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው የታወቀው “በእድሳትና ለዲግሪ መርሐ ግብር መጀመር ይደረጋል በተባለው ዝግጅት” ሰበብ የመንፈሳዊ ኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ከሁለት ወራት በላይ በተስተጓጎለበት፣ ይህንንም ተከትሎ የደቀ መዛሙርቱ (በተለይም የሰሚናር ኮርሰኞቹ) አቤቱታ ጎልቶ በሚሰማበት ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡

November 4, 2012

አቡነ ቴዎድሮስ፤ 118ኛው የግብጽ ኮፕት ፖፕ ሆኑ

(ደጀ ሰላም ጥቅምት 25/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 4/2012/ READ IN PDF)፦ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ጥቅምት 25 ወይም ኖቬምበር 4 ባደረገችው የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስን 118ኛው ፖፕ እንዲሆኑ ሰይማለች፡፡ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ሥርዓቱ ለመላው ዓለም በተሰራጨበትና ዓይኑን በጨርቅ የተጠቀለለ ሕጻን ዕጣውን ባወጣበት ሥርዓት “አቡነ ቴዎድሮስ” 118ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል። የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ላለፉት 40 ዓመታት የመሩት 117ኛው ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንደነበሩ ይታወሳል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

November 3, 2012

በሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርት ከተቋረጠ ከሁለት ወራት በላይ ኾኖታል


  • ደቀ መዛሙርቱ በዋና ዲኑ ቀሲስ በላይ መኰንን የተዘጋጀውን “የኮሌጅ ደንብና ሥነ ሥርዐት ለማክበር ቃል የሚገባበት ቅጽ” ካልፈረሙ ምዝገባ እንደማይጀመር ተነግሯቸዋል፤ /የቅጹን ተ.ቁ (8) ይመልከቱ/፡፡
  • የስድሳ ዓመት ዕድሜ ባስቆጠረ ሥርዐተ ትምህርት ወደ ኮሌጅ ደረጃ አድጓል የተባለው ተቋሙ “የዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር ዝግጅት አጠናቀናል” ብሏል፤ ደቀ መዛሙርቱ በበኩላቸው “ሥርዐተ ትምህርቱ አልተለወጠም፤ ኮሌጁም አላደገም፤ ቦታው አልሚ አላገኘም” እያሉ ነው፤
  • ደቀ መዛሙርቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው
  • የኮሌጁ ዋና ዲን ቀሲስ በላይ መኰንን ለፕሮቴስታንቱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም÷ “ዘመነ ማቴዎስ የተጠሩበት[ን] ሐዋርያዊ አገልግሎት የበለጠ የሚፈጽሙበትና የሚያስፈጽሙበት ዘመን እንዲኾንልዎ ምኞቴን ስገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፤” በማለት በኮሌጁ የፕሮቶኮል ደብዳቤ የመልካም ምኞት መግለጫ ጽፈውላቸዋል፤ /ሰነዱን ይመልከቱ/፡፡

(ደጀ ሰላም ጥቅምት 24/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 3/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የዘንድሮው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 31 መደበኛ ስብሰባና የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔዎችና የአቋም መግለጫዎች አጽንዖት በሰጠባቸው የሰላም፣ መልካም አስተዳደር፣ የመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ልማት አጀንዳዎች ውስጥ ለተያዙት ዕቅዶች መሳካት የትምህርትና ሥልጠና ተቋሞቻችን፣ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መዋቅሮቻችን ከፍተኛ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)