October 31, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ሐሳቦች

  • READ THIS NEWS IN PDF.
  • የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ ራሱን የሚጠራው” የሚለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ተ.ቁ (2) “እኛንም አላስደሰተንም፤ እንዲስተካከል እናደርጋለን” ሲሉ ሌላው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ደግሞ እንዲህ ያለው ቃል ከጋዜጠኞች በፊት ምልአተ ጉባኤው በተናበበው የመግለጫው ክፍል ላይ እንዳልነበረ ተናግረዋል
  • “ስድስተኛውን ፓትርያርክ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ እየተዘጋጀን ነው ያለነው፤ ሕጉን ካጸደቅን በኋላ ወደ ምርጫው ነው የምንገባው፤ በውጭም ያሉት ተቀብለውን፣ በውስጥም ያለነው ተቀብለናቸው ከእኛው ጋራ ምርጫውን እንዲያካሂዱ ፈቃደኞች ነን፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
  • “ጳጳስ ንብረት የለውም - ጎመን የሚዘራበት፣ ሽንኵርት የሚተክልበት፤ ንብረቶቹ ምእመናን ናቸው፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ የመለሱት/
  • በአዲስ አበባ አራት አህጉረ ስብከት አደረጃጀት ሂደት ከሥራ አስኪያጅነት የሚወገዱት ንቡረእድ ኤልያስ በጸሐፊነት ከያዙት የዕርቀ ሰላሙ ልኡክ አባልነትም እንዲወጡ መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በ2000 ዓ.ም ያጸደቀው “የማዕርገ ክህነት አሰጣጥ፣ ሥርዐተ ምንኵስናን፣ የካህናትና መነኰሳት የማዕርግ አለባበስ ደንብ” አፈጻጸም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግበት ትእዛዝ ሰጠ፡፡ የደንቡን ሙሉ ይዘት እናቀርባለን፡፡
  • የምንኵስና ልብስ ለብሰው ሕዝቡን በማታለልና ሃይማኖታችንን በማስነቀፍ ላይ ከተሰማሩ ምግባረ ብልሹ የስም መነኰሳት ነን ባዮች ሕዝበ ክርስቲያኑ ራሱን ነቅቶ እንዲከላከልና መንግሥትም የሕግ ከለላ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ጠይቋል
  • “ሀገረ ስብከትዎን አያውቁትም” በሚል በምልአተ ጉባኤው የተወቀሱትና የምእመናን አቤቱታ የበረታባቸው ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከድሬዳዋ ሀ/ስብከት ተነሥተው ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ተመድበዋል፤ ብፁዕነታቸው የምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከትን ደርበው ይመራሉ፤ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም የለቀቁት ደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በጋሞጎፋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይመራል፡፡ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የውጭ ግንኙነት መምሪያን በበላይ ሓላፊነት እንደያዙ የካራ መድኃኔዓለም እና አቡነ ገሪማ ገዳም የበላይ ጠባቂ ኾነዋል፡፡
  • የመንበረ ፓትርያርካችን የጋዜጣዊ መግለጫ ዝግጅትና የጋዜጣዊ ጉባኤ ሥነ ሥርዐት የቤተ ክርስቲያናችንን ከፍተኛ አመራር የሚያስከበር መኾን እንደሚገባው ተተችቷል፤
  • የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት የቅዱስ ሲኖዶሱን የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ዘገባ ያስተላለፈበት ሰዓትና አዘጋገብ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተሰማቸውን ቅሬታ በጋዜጠኞች ፊት አሰምተዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ጣቢያው የምልአተ ጉባኤውን መክፈቻ “ሰው ከተኛ በኋላ ምሽት አራት ሰዓት ላይ መተላለፉ ሰዉ እንዳያየው ነው ወይ? የሰማነውስ ነገር እኛ ያልነውን ነገር በትክክል ገልጧል ወይ?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፤ “የብፁዕነታቸው ቅሬታ የሁሉም አባቶች ሐሳብ ነው” ያሉት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በበኩላቸው ቅዱስ ሲኖዶሱ በዘገባውና አዘጋገቡ ላይ የወሰደውን ትዝብትና የተሰማውን ቅሬታ በመደበኛ ኹኔታ ለሚመለከታቸው የጣቢያው የሥራ ሓላፊዎች እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል፡፡

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 21/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 31/2012)፦ አርባ ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለዐሥር ቀናት ሲመክሩበት የሰነበቱበት የጥቅምት 2005 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ ረፋድ ላይ ተጠናቋል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ያዘጋጀው 17 ነጥቦችን የያዘው ጋዜጣዊ መግለጫ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ አማካይነት በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለመግለጫው በተጠሩት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ጋዜጠች ፊት በንባብ ተደምጧል፡፡ ከዚህ በኋላ በተለየ ክፍል በተከናወነው ጋዜጣዊ ጉባኤ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከተወሰኑ ጋዜጠኞች ለተነሡ ጥቂት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጥያቄዎቹ ከመግለጫው አጻጻፍ ጀምሮ በዕርቀ ሰላሙ ሂደት እና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕጣ ፈንታ፤ የፓትርያርክ ምርጫ ሕጉን ሕገ ፓትርያርክን ፓትርያርኩ ሳይኖር ስለምን ለማሻሻል እንደተፈለገ፤ የጳጳሳት ድርብ ዜግነት፣ ንብረት ማፍራትና ውርስ ጉዳይ በሚሻሻለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለሚታይበት ኹኔታ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ስለተወሰነበት ወቅትና ኹኔታ የተመለከቱት ነጥቦች ይገኙባቸዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ለጋዜጣዊ ጉባኤ ካላቸው አዲስነት ጋራ የአነጋገራቸው ለዛና ቀጥተኝነትም የጋዜጠኞችን ቀልብ የሳበ ሲሆን ምላሾቹ ግን ጥቂት የማይባሉትን መኮርኮሩ፣ በአንዳንዶቹም ዘንድ ስጋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡ “ችግር በገጠመ ጊዜ አገርን ለቀቅ አድርጎ ጎረቤት አገር መኖር ይቻላል፤ አገርን ከለቀቁ በኋላ ሲኖዶስ በሚል ማቋቋም፣ ሲኖዶስ የሚለውን ቃል መጠቀም አግባብ አልነበረም፤ ሲኖዶስ አንድ ነው፤ አይከፈልም፤ መንበሩ ያለው እዚህ ነው አይሰደድም፤ እዚያ ያለው ጥገኛ ነው” ያሉት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ ዕርቀ ሰላሙን በተመለከተ “ስንጻጻፍ፣ ሰውም ሲላክ ቆይቷል፤ እግዚአብሔር ባለው ጊዜ ይፈጸማል” ብለዋል፡፡

የዕርቁ ሂደት ከፓትርያርክ ምርጫው ጋራ ስላለው ግንኙነትም “ኻያ ዓመት ሙሉ አምስተኛ ፓትርያርክ እያልን ቆይተን ወደ አራተኛ አንመስም፤ ስድስተኛውን ፓትርያርክ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ በዝግጅት ላይ ነው ያለነው፤ ሕጉን ካጸደቅን በኋላ ወደ ምርጫው ነው የምንገባው፡፡ ቅዱስነታቸው አቡነ መርቆሬዎስ ከፈለጉ እዚሁ እኛው ግቢ ማረፊያ ተሰጥቷቸው፣ ካልፈለጉም በመረጡት ገዳም አስፈላጊው ነገር ተሰጥቷቸው በጸሎት ተወስነው ሊቀመጡ ይችላሉ፤ እዚያ ያሉት እዚህ የተሾሙትን ተቀብለው፣ እዚህ ያለነውም እዚያ የተሾሙትን ተቀብለን ከእኛው ጋራ ምርጫውን ለማካሄድ ፈቃደኞች ነን፡፡”
ብለዋል። “ሃይማኖት እንጂ ሕግ በየጊዜው ወቅቱን ተመልክቶ የሚሻሻል ነው” ያሉት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ለሥራ አመቺ ተርጎ፣ የሚጨመር ካለ ተጨምሮ፣ የማያስኬድ ነገር ካለ እንዲያስኬድ ኾኖ እንደሚሻሻል ገልጸዋል፡፡ ዋና ጸሐፊው አያይዘውም በፍትሐ ነገሥቱ ለሁሉም የራሱ የተደገገለት ተልእኮ (ድርሻ) መኖሩን በማስታወስ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ “ለፓትርያርክ የሚገባው ድርሻ አይነካበትም” ብለዋል፤ የፓትርያርክ ምርጫ ሕጉም ስለ አመራረጡ፣ ስለ አካሄዱ በመኾኑ ፓትርያርኩ አለመኖሩ የሚያሰጠው የተለየ ትርጉም እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ስለ ጳጳሳት ንብረት ማፍራትና ውርስ ጉዳይ ለተነሣው ጥያቄ ብፁዕነታቸው በጥቅሉ “ጳጳስ ንብረት የለውም፤ እርሻ አያርስም፤ ጎመን አይዘራም፤ ሽንኵርት አይተክልም፤ ንብረቶቹ እናንተ ምእመናን ናችኹ” በማለት መልሰዋል፡፡ በአገራችን ሕግ ስለ ድርብ ዜግነት የተደነገገውን በመጥቀስ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ‹ኢትዮጵያውን› ጳጳሳት ስለመኖራቸው ለቀረበላቸው ጥያቄም “አዎ፣ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ጳጳሳት አሉ” ካሉ በኋላ በሚሻሻለው ሕግ ኢትዮጵያዊ ብቻ እንዲኾኑ ከሚያስፈልገው አኳያ ጥያቄውን እንደ ጥቆማ በመውሰድ ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደሚመክርበት አመልክተዋል፡፡

በአጠቃላይ አጋጣሚው ቤተ ክርስቲያናችን የብዙኀን መገናኛዎችን፣ ከቤተ ክህነቱ አስተዳደር ጋራ በተያያዘ የታሪክ እና ፖሊቲካ ተንታኞችን ቀልብ ይዛ ባለችበት ወቅት ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔዎች የሚሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎችና የሚዘጋጁ ጋዜጣዊ ጉባኤዎች መድረኩ የሚፈጥረውን ዕድል ሁሉ አሟጠው የሚጠቀሙ፣ በባለሞያ የታገዘ ከፍተኛ ዝግጅት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ዛሬ የታየው የዜና ሰዎች ትኩረት እና ብዛት ግድ እንደሚለን ሊጤን ይገባል እንላለን፡፡

ተጨማሪ ዝርዝሮችን ይጠብቁ፤
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን

23 comments:

Unknown said...

‎"ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ “በጸሎት ተወስነው በመረጡት ስፍራ ይኑሩ” ሲባል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ለፓትርያርኩ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት÷ በመንበረ ፓትርያርኩ እየተገኙ የቅዱስ ሲኖዶሱን ስብሰባ በርእሰ መንበርነት መምራትና ውሳኔዎቹን ማስፈጸምን፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ኤጲስ ቆጶሳትን፣ የታላላቅ አድባራትና ገዳማት አለቆችንና አበምኔቶች መሾምን፤ በውጭ ግንኙነት ቤተ ክርስቲያንን መወከልን. . . ወዘተ እንደማያካትት ግልጽ ነው ያሉት ምንጮቹ መንበሩን በተመለከተ የሚታየው የምልአተ ጉባኤ አዝማሚያ የቅዱስነታቸውን ፈቃድ በሚያጤን (ባካተተ) አካሄድ ወደ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሹመት መቀጠል መኾኑን አልሸሸጉም፡፡" ''የቅዱስነታቸውን ፈቃድ በማጤን (ባካተተ) አካሄድ ወደ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሹመት መቀጠል..." 'የቅዱስነታቸውን ፈቃድ '' የሚለው ነገር ቅዱስነታቸው እንዴት ለ21 ዓመታት በውጭ አገር በግዞት እንዲኖሩ ያስገደዳቸው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ሳይስተካከል እንዴት አሁን ጥሰቱን እንዲያጸድቁ ፈቃደኛ ይሆናሉ?ለመሆኑ ፈቃደኛ ሁነዋል ? ከሆኑ እኮ ላለፉት 21 ዓመታት በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ላይ ለተደረገው ጥሰትና ጥሰቱን ተከትሎ ለደረሰው ክፍፍል ኃላፊነቱንም ጭምር ተጋሪ ሊሆኑ ነው። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅም ''ጥፋቱ በጋራ የተሠራ ነው'' ብለዋል የሚል በደጀ ሰላም ላይ ተጽፎ አንብቤአለሁ። እረ በወጭም ሆነ ባገር ውስጥ ያላችሁ አባቶች እውነቱን መስክሩ ። በመንግስትና በመካከላችን ባሉ አንዳንድ የጎጠኝነት ስሜት ባላቸው 'አባቶች' ምክንያት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመጣስ ተገደናል ብሎ እውነቱን መመስከር ምንድነው ችግሩ ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው የማይመለሱበት ዋናው ምክንያት በምንግስትና በጥፋት ተባባሪ በሆኑት 'አባቶች ' ተቃውሞ መሆኑን እኛ ምዕመናን አናውቅም መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሁአል። በዚህ ሁኔታ እንኳን እግዜብሔርን ሰውን ማታለል አትችሉም። ፓትርያርኩ እያሉ ለሁለተኛ ጊዜ ሌላ ሁለተኛ ፓትርያርክ ብትሾሙ ታሪክና እግዚአብሔር ይቅር የማይለው ጥፋት እየሰራችሁ መሆኑን መረዳት አለባችሁ። ለመንጋውም መልካም ዓርአያዎች እየሆናችሁ ባለመሆኑ በክርስትናው እምነት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደራችሁ መሆኑን እንደ አንድ ተራ ምዕመን እውነቱን ልነግራችሁ በፊታችሁ ቁሜአለሁ። ለመሆኑ እንደ ዘመነ ሰማዕታት ያለ ሥጋዊ ሞትን በሰይፍ የሚጠይቅ መንግሥት ቢመጣ ምን ልትሆኑ ይሆን ? ይህ ዛሬ ያለው መንግሥት እኮ በቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ልትገባብን አትችልም ብትሉት ሰይፍ መዞ አይስይፋችሁም። እንዴት የኢአማንያንና የጸረ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይሎች መሳለቂያ ታደርጉን አላችሁ ? እናንተ የዛሬዎቹ አባቶች በምትሠሩት ጥፋት እኮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች በመናፍቃን እየተማረኩ ነው። በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ምን ያህል አባላቶቿን ባለፉት 21 ዓመታት ለመናፍቃን እንዳስረከበች ማየት አትችሉም ? እረ ተው ዕለተ ሞታችሁን ኣስቡ !

Anonymous said...

Please remove the picture. That is not representing the October meeting.

Anonymous said...

Dear Deje Selam

"ምልአተ ጉባኤው ያዘጋጀው 17 ነጥቦችን የያዘው ጋዜጣዊ መግለጫ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ አማካይነት በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለመግለጫው በተጠሩት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ጋዜጠኞች ፊት በንባብ ተደምጧል፡፡"

Where can we get it? Could you please post it on your webpage as pdf.

Ameha said...

ከላይ Kebede Bogale የተባሉት ወገኔ የሰጡት አስተያየት የኔም ሃሣብ ነው። እሳቸው በጥሩ አማርኛ የገለጹት በመሆኑ አልደጋግመውም። ቢሆንም፣ አንዳንድ ነገሮችን ማከል እፈልጋለሁ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ሠላም ፈላጊ ሳይሆን አቀጣጣይ ይመስላል። አገር ውስጥ ያሉትም ሆነ ውጭ አገር የምንገኝ ምእመናን እየናፈቅን ያለነው እኮ ሠላምን፣ አንድነትን እና ሕብረትን ነበር። አቡነ መርቆርዮስ የሣሎን ጌጥ ናቸውን? እግርና እጅ አጣጥፎ ለመቀመጥማ ለምን ከዚሁ መንቀሳቀስ አስፈለጋቸው? እሳቸው 4ኛው እያሉ 5ኛውን የመረጣችሁት እናንተ አልነበራችሁም እንዴ? በተጽዕኖም ቢሆን። ስህተትን በማረም ፋንታ እንደገና ስህተታችሁን ትደግሙታላችሁ? “እምቢ ለኃይማኖቴ፣ አሻፈረኝ” ብሎ መስቀሉን መሸከም ምን ያህል መታደል ነበር። እግዚአብሔር ሥራውን ከአናት ጀምሯል፤ በተዋረድ እንደሚያጸዳ አልጠራጠርም። “ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን? አሕዛብንስ የሚገሥጸው፣ ለሰውም እውቀትን የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን? የሰዎች አሳብ ከንቱ እንደሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።” መዝ 93፡9-11

Eshetu Haile said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ለተወደዳችሁ የቤተ ክርስቲያን አባቶች

ከባለፈው ይልቅ የአሁኑ ስህተት የበለጠ እንዳይሆን የታሪክ አደራ የተረከባችሁ አባቶቻችን በአርቆ አሳቢነት ጉዳዩን ታስፈጽሙ ዘንድ ይገባል:: ሐዋርያት አንድት ቤተ ክርስቲያን እንዳስረከቧችሁ ለዚህ ትውልድ አንድት ቤተ ክርስቲያን ልታስረክቡን ይገባል:: ከአሁን በሁዋላ ለሁለት የተከፈለች ቤተ ክርስቲያን ማየት አንፈልግም:: እውነትን መስክሩ የቤተ ክርስቲያንን ህግ ራሳችሁ አክብራችሁ አክብሩ በሉን እንታዘዛለን:: በቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን አስገብተው (እጃችሁን ጠምዝዘው) ውሳኔያችሁን ሊያስቀይር የሚችል ነገር እንኳ ቢኖር እስከ ሰማእትነት ከፍላችሁ ሰማዕትነትን ክፈሉ በሉን::
ስለ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ የሚነገርበት ወቅት አይደለም:: 4ኛው ፓትርያርክ በህይዎት አሉ:: ስርአቱን እያወቃችሁ ለምንድን ነው ስርአት እንድጣስ የምታደርጉት:: ምኑ ነው አሁን ለአድስ ምርጫ እድትባዝኑ ያደረጋችሁ? ከሁሉም በፊት የቤተክርስቲያንን ህልውና ለማስጠበቅ ቅድሚያ ስጡ:: መጀመሪያ እርቀ ሰላሙን ፈጽሙ በመቀጠል 4ኛው ፓትርያርክ ይምጡ እንደራሴ ተመርጦ(ተወክሎ) ስራው ይሰራ:: የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ እግዚአብሄር በፈቀደ ሰአት ይሁን:: ህዝበ ክርስቲያኑን አታሳዝኑት ከጎናችሁ ነውና::

እግዚአብሔር አምላካችን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን

There is one and ONLY one option. Let the 4th Pathriarich assume the position, reunite the church, and let the administrative affairs done by the Holy Synod and the way it is now.

It would be a damn shame if these people at the top of church power echelon continue in this path of destruction. I would never associate myself with EOTC if they opt to miss this great opportunity.

Anonymous said...

አባቶቻችን አሁንም የመንግስትን ተጽዕኖ መመከት የተሳናቸው ይመስለኛል በኔ ግምት :: ወይ ችግራቸውን ወደ ህዝቡ አላወረዱት በቀሚሳቸው ሸፋፍነው ይዘውታል ::አለመታደል ነው ::ምናለበት ሕዝቡን ቢያዳምጡት ? ከእነሱ ይልቅ ህዝቡ ቀኖናውን አውቆት ፓትርያርክ በሕወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ መሾም የለበትም እያለ ነው ::ምንድነው እነሱ ለሹመት ይሄን ያህል ጥድፊያ ? እንክዋንስ አርባ ሚሊዮን ሕዘብ ያለውና እንደ እትዮጵያ ያለ ሰፊ ሀገር ይቅርና ስምንት ሚሊዮን አማኝ ያላት ግብጽ አንኩአን አንድ ፓትርያርክ ለመምረጥ ምን ያሀል ጊዜ ወሰደው አየሰሩበት አንደሆነ መመልከት ያሻል :: ይመስለኛል የእኛ ቤተ ክርስቲያን በሶስት ነገር ተጠምዳለች አሁን... መንግስት ...ራሳቸው ጳጳሳቱ የስልጣን ሽኩቻ ...ዘረኝነት ...በነዚህ ነገሮች ምክንያት ይመስለኛል አቡነ መርቆርዮስ በፓትርያርክነት አንዳይመለሱ አየተደረገ ያለው ::ብቻ ያሳዝናል አግዚአብሔር መልካሙን ያብጅልን አንጂ እንደ እኛ ሥራስ እንጃ .....

Unknown said...

thank you so much !Bogale, Amha & Eshetu. l'm appreciated...

Unknown said...

thank you so much !Bogale, Amha & Eshetu. l'm appreciated...

Anonymous said...

ሁሉም አንድ ናቸው:: እንደ አለማውያኑ ለስልጣን ብቻ የሚጓጉ! ለቤተክርስቲያን ስርአት ደንታ የሌላቸው:: ብጹአን አባቶች ሆይ አንድ ጊዜ ሐጢአት ሰርተናልና በዛው እንቀጥል አይባልም: የድሮውን ሐጢአት ትቶ ወደ ትክክለኛው ወይም ወደ ጽድቅ መንገድ መምጣት ያስፈልጋል እንጂ:: አንድ ጊዜ ቀኖና ስለተጣሰ አሁንም እንጣስ አይባልም:: እንደዛ ከሆነማ ንብረታችን ናችሁ የምትሉን ልጆቻችሁም አንድ ጊዜ ሐጢአት ከሰራን ወይም የእግዚአብሔርን ህግ ካፈረስን አንዴ አፍርሰናልና አሁንም እናፋርስ ብለን ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዳንመለስ እያስተማራችሁን ነው:: ይህንን ነው አሁን ስድስተኛ ፓትርያርክ በመምረጥ ሌላ የቀኖና ጥሰት ደግማችሁ በመፈጸም እያስተማራችሁን ያላችሁት::ቁም ነገሩ የቁጥር ነው? (4ኛ, 5ኛ, ወይም 6ኛ መባሉ) ወይስ ለቀኖና ቤተክርስቲያን መከበር መስራት? ቤተክርስቲያን በእንደራሴ እንዳትተዳደር የሚከልክል ህግ የላትም:: ለሁለተኛ ጊዜ ቀኖና ላለመሻር ሲባል መንበሩ ሳይሾምበት ቢቀመጥ ምንድነው ችግሩ? ቢበዛ እኮ የአቡነ መርቆሬዎስን ስም ቅዳሴ ላይ ማንሳትና ጳጳሳት መሾም ሲያስፈልግ ብቻ እሳቸው እንዲሾሙ ማረግ ነው:: ሌላ ምንም አይነት ተሳትፎ ሳይኖራቸው መንበሩን ማቆየት ይቻላል:: በቅዳሴ ላይ ስማቸው ሲጠራ እኮ "በእንተ ብጹዕ ወቅዱስ አባ መርቆሬዎስ 4ኛው ፓትርያርክ ..." አይባልም:: "በእንተ ብጹዕ ወቅዱስ አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ..." ነው የሚባለው:: ወይም ደግሞ "አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በዘመናችን የሾምካቸውን ብጹዕ አባ እገሌንና ብጹዕ ወቅዱስ 4ኛውን ፓትርያርክ አባ እገሌን ተቀብለናቸዋልና..." አይባልም:: "አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በዘመናችን የሾምካቸውን ብጹዕ አባ እገሌንና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባ እገሌን ተቀብለናችዋልና..." ነው የሚባለው:: ለቤተክርስቲያን ምንም ወደማይጠቅማት ወደ ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እንዲሮጡ የሚያረጋቸው አንድ ሃይል ከጀርባቸው እንዳለ መገመት አያቅትም ነገር ግን ስለቀደሙት ደጋግ አባቶቻችን ሲል እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ያምጣልን! ያለምንም እንከን እርቀሰላሙን በቸርነቱ ያስፈጽምልን::

asbet dngl said...

ከላይ Kebede Bogale የተባሉት ወገኔ የሰጡት አስተያየት የኔም ሃሣብ ነው። እሳቸው በጥሩ አማርኛ የገለጹት በመሆኑ አልደጋግመውም። ቢሆንም፣ አንዳንድ ነገሮችን ማከል እፈልጋለሁ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ሠላም ፈላጊ ሳይሆን አቀጣጣይ ይመስላል። አገር ውስጥ ያሉትም ሆነ ውጭ አገር የምንገኝ ምእመናን እየናፈቅን ያለነው እኮ ሠላምን፣ አንድነትን እና ሕብረትን ነበር። አቡነ መርቆርዮስ የሣሎን ጌጥ ናቸውን? እግርና እጅ አጣጥፎ ለመቀመጥማ ለምን ከዚሁ መንቀሳቀስ አስፈለጋቸው? እሳቸው 4ኛው እያሉ 5ኛውን የመረጣችሁት እናንተ አልነበራችሁም እንዴ? በተጽዕኖም ቢሆን። ስህተትን በማረም ፋንታ እንደገና ስህተታችሁን ትደግሙታላችሁ? “እምቢ ለኃይማኖቴ፣ አሻፈረኝ” ብሎ መስቀሉን መሸከም ምን ያህል መታደል ነበር። እግዚአብሔር ሥራውን ከአናት ጀምሯል፤ በተዋረድ እንደሚያጸዳ አልጠራጠርም። “ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን? አሕዛብንስ የሚገሥጸው፣ ለሰውም እውቀትን የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን? የሰዎች አሳብ ከንቱ እንደሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።” መዝ 93፡9-11

November 1, 2012 6:22 AM

hailu said...

At this point when we Ethiopian Orthodox followers are hopeful about the opportunity of uniting our church,the fathers involved in the peace process should be thoughtful before speaking to the media.

It is amazing that Abune Hizkeal makes such a ridiculous assertion about counting numbers.
He seems that he is concerned about having the 4th Patriarch after having counted 5th for 20 years.

He should have refrained from making such unwelcome comments.

He should have known that the counting also goes 3rd to 4th. Counting 5th jumping 4th was was a spiritual and mathematical anomaly our church has dearly sufferred from for 20 years.

We must fix the original mistake that divided our church rather than a bogus concern about numbering.

If we miss this opportunity and fail to unite our church, God and generations to come shall hold the current so called fathers liable for dividing and weakening the Orthodox faith.

Yes, lets count 4th rightly for the sake of Unity of our church.
6th will be the worst mistake to be committed against the church.

God help us!

Anonymous said...

አሁንስ አስተ ያየታችን ሁሉ የምንሰጠው ሃሳብ ሁሉ ሳናውቀው ወጣ እያል ነው አባቶቻችን በጣም እየተዳፈርን ነው ትንሽ ጠንቀቅ ብን ይሻለናል በብሎጎች የጀመርናቸው በመጻፍ የጀመርናቸው በልብ ያመላለስናቸውን ስለ ሆነ ልብ ደግሞ መልካሙንም ክፉውንም ስለሚያመላልስ ልንጥጠነቀቅ ይገባል ይሄ ሁሉ አንድ ቀን ደግሞ ሊተተገበርም ስለሚችል እስቲ ለእግዚአብሄር ጊዜ እንስጥ እኛ ብቻ አዋቂዎች አንሁን ።

Aregawit said...

Ebakacheu abatoche yemealfewen sowe(mengestene) saeyhone yemayelfewen kristosene frue. lhamanotacheu nuru yetadele sl Kirstos fekre angetune lesefe yesetale almetadele honena sl ewnet yememesker tefa
Getahoye bethene ena hezbchene asbachewe. Amen

Thank you Bogale,Amha & Eshetu. Both of you write my feeling.

Anonymous said...

dበቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በተራ ቁጥር 5 እንደተጠቀሰው ወቅታዊ “የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ” እንዲዘጋጅ መደረጉ ተገቢ ውሳኔ ነው። ነገር ግን ለከባዱ ኃላፊነት የተመደበው ከ 40 ቀን ያነሰ ጊዜ በቂ አይመስልም። ምንም እንኳ በቅድሚያ የተዘጋጀ አንዳንድ ሰነድ ቢኖር፣ ተጨማሪ ምርምር ማድረግ፣ በየገዳማቱና በየአድባራቱ እየተዘዋወሩ ምክር ማዳመጥ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያም ሆነ በውጪው ዓለም ከምእመናን ጭምር የሚገኘውን ገንቢ ሀሳብ ገንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። አጥኚው ኮሚቴ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት ሕጉን አርቅቆ ካቀረበ በኋላም ቢሆን፣ በመግለጫው እንደተገለጸው ወዲያውኑ የአንድ ቀን ስብሰባ አድርጎ ለማጽደቅ ከማሰብ ይልቅ፣ እያንዳንዱ አባል አባት በቂ ጊዜ ተወስኖለት ረቂቁን በዝርዝር እንዲያጠናውና ማሻሻያም ካለው ተዘጋጅቶ በስብሰባው እንዲገኝ ማድረግ ለውጤቱ ስኬታማነት ይበጃል። በቂ ምክንያት የሌለው ችኮላ “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” የሚለውን የአበው ማስጠንቀቂያ እውን ሊያደርገው ይችላል። አዲስ የሚዘጋጀው ሕግ ወደፊት የማይጣስ ሊሆን ይገባል፤ ያለፈው ይበቃል።
ለሃያ ዓመት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም እንዲወረድና የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት እንዲከበር በተለይ ከአቡነ ጳውሎስ ዕልፈት በኋላ በኢትዮጵያም ሆነ በውጪው ዓለም በካህናትና በምእመናን ዘንድ ቅድሚያ የተሰጠው እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ይህንንም እውን ለማደረግ በየቦታው ጸሎትና ልዩ ልዩ ጥረት እየተደረገ ነው። በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ዕርቀ ሰላም ከሰፈነ በኋላ ሌላው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ኃይል በጋራ ይፈታል። ታዲያ ፍቅር፣ ሰላምና ዕርቅ እንደገና ሊመሠረቱ በተቃረቡበት ሰዓት አንዱን ወገን ብቻውን አዲስ ፓትርያርክ ይመረጥ የሚያሰኘው ምን አደጋ ተፈጠረ? ሰላምና ፍቅር ሲኖር መንገዱ ቀና ነው። የሚያመራውም ወደ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መርቆሬዎስ ነው። ስለዚህ ከሁሉም በፊት ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም።

Berhanu Melaku said...

ክርስቶስና ሃዋርያት ዛሬ
===============
ጌታቸን፣ አምላካችንና መድህናቸን እየሱስ ክርስቶስ ሃዋርያትንና የሚከተሉትን ሕዝብ ያስተምራቸው የነበረ በምሳሌ እንደነበር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ምእራፎች ተጠቅሷል።

ታድያ ዛሬ እየሱስ ክስቶስ በዚህች ምድር ላይ ሆኖ ከኦ/ተ/ቤ/ክ/አባቶቻችን ጋር ቢሆን ስለ ጳጳስ ምርጫ ምን ምሳሌ ይሰጥ ይሆን ብለን ለደቂቃ ቆም ብለን እናስብ እስኪ፤ እኔ ምናልባት ሊሆን ይችላል ብየ ማስበው እንዲህ ነው፤

በ፬ ላይ ፩ ስተት ሲደመርበት ፭ ስተቶች ይሆናል፤
በመቀጠልም በ፭ ስተቶች ላይ ፩ ስተት ሲደመርበት ፮ ስተቶች ይሆናል እንጂ ተመልሶ ፬ እውነቶች አይሆንም። ስለዚህ ምርጫችሁ ወደ እውነት ለመሄድ ከሆነ፤ እውነትን ወደ ፭ ስተቶች የቀየረችውን ፩ ስተት ታስወግዳላችሁ እንጂ ሌላ ፩ ስተት በመጨመር ፮ ስተቶች ማድረግ የለባችሁም፤ ያውም አባቴ ባስተካከለው ላይ።

እርስዎስ ምን ገመቱ እውነት ስለ እውነት ስተታችንን እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲደርስ አርሞልናል። ታድያ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን እንባ ሲያብስላት በግልጽ ያሳየንን መረዳት እያቃተን እንዳይሆን፤ እባካችሁ የባሰ ቸነፈር እንዳይወርድብን፤ ለቲንሽ ጊዜ ትግስትን አጥተን ቤተ ክርቲያናችን እንዳትበደልብን።

እኔ በበኩሌ አቡነ መርቆሬዎስ ውጭ አገር ገብተው ሌላ ሴኖዶስ መፍጠራቸውን አልወደድሁላቸውም። ያንን ጥፋት ነው ብለው ካመኑና ጥፋቱን ካስተካከሉ ግን በቀረቻቸው የእድሜ ዘመናቸው በመንበሩ ላይ ተቀምጠው የቤተ ክረስቲያኗን ቀኖና በመጠበቅ የጀመሩትን ሃዋረያዊ ጉዙ እንዲቀጥሉ ይደረግ ዘንድ ብጹአን አባቶቸንና ሁሉንም የኦ/ተ/እምነት ተከታይ እማጸናለሁኝ።

ፈጣሪያችን ለሥጋ ያልሳሳን ለነፍስ የበረታን እንድንሆን የሚያደርግ አንደበትን ያድለን፤ ጭንቅ አማላጇ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እርቀሰላሙን ታማልድልን። አሜን፣ አሜን፣ አሜን፣
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ብርሃኑ መልአኩ ነኝ ከኬንታኪ

Anonymous said...

what is the meaning of abatoch? is any body being bishop can be abataoch? i disagree! abat malet yelijun gibr yeyaze new! ersum yene kerlosin haymanot yanegebe new! ahun yalut asmesaye wenbede bicha new. betekirstianin gin rasu balebetu yitebikal!!!

MelkamKen said...

Answer to who wrote this words‚‘‘አሁንስ አስተ ያየታችን ሁሉ የምንሰጠው ሃሳብ ሁሉ ሳናውቀው ወጣ እያል ነው አባቶቻችን በጣም እየተዳፈርን ነው’’
Do you know why all believers heated on this issue? The reason is ’Our Holy Fathers hate to make as one’. I’m quite sure you know the answer well but may be you are trying to veiled & buried the fact by respect to our fathers! We love them and also we respect too much but when they make wrong as a Christian they should open their heart to know their wrong decision. In the life of Orthodoxy everything is true, how could we endure our fathers preach a lie?! They told to us, Orthodoxy is walking on the rope, yes 100% true but for their case they fearing to stop/oppose the hidden hands and continue their walk. Whether we like or not we should restore the strong Orthodox church and preaching gospel to the world. The question of the believers is not the question of number (four or six)just it is the question of UNITY. As a son of Orthodox, I wish God stop the life of parasites who suck our church blood and always dream the weak Orthodox!
I beg you (our fathers) with the name of Mother Virgin St. Mary that you called every day when you were a student, make us one!!
God help US! Please dear brothers and sisters pray God help our fathers and us too!

Adam said...

Whom ever says what ever if God is willing to do he will do it.let us pray to God spritully and with tear for his willingness.if we do this God will enforce the church leaders to make unity.

let us think back our spritual fathers the recent like "Abune Petros" ,strong spritual father (not only bishops), he decided to be killed on the round about rather than to see the distruction of his country and his church. We can get a leader like him if all the church followers pray to God with one sprit rather than we think and talk like political election.

Pray pray, pray

hailu said...

May God bless those who work relentlessly to unite our church.

For those so called fathers in Ethiopia who are rushing to embark on another sham election of a bogus 6th patriarch while the legitimate 4th Patriarch is still alive, I say don't you have a spritual sense that help you see the grave danger our church has been mired in for the past 20 years?

Because of the division our church has been weakened and become an easy prey to protestants and other groups. It has lost myriads of its followers to protestant groups and non-belief.

Letting the division to continue by talking about a sham election of a bogus 6th patriarch at this time will be yet another grave mistake worse than the one committed 20 years ago.

Let the 4th Patriarch assume the leadership of a united Orthodox Church for the rest of his life. Election shall be considered after that, Not now!

Lets unite our church Now. Lets not fear the influence of a government led by people who don't share our faith. Our church's business if entirely ours. Lets unite our church!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)