October 15, 2012

ዐቃቤ መንበሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት አደረጉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 5/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 15/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ የውይይት መሥመሩን ያመቻቸው በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ነው፡፡ በሁለቱ አባቶች የስልክ ውይይት÷ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ጋራ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፤ ከአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አብረው መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡
የውይይቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም እንደገለጹት÷ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መከበር ላይ ትኩረት በመስጠት ተናግረዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ወደ መንበራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ቢኾኑም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ተቀምጠው ቅዱስ ሲኖዶሱን በርእሰ መንበርነት እየሰበሰቡ አመራር የመስጠት ፍላጎት የላቸውም፡፡ ከዚህ ይልቅ የፕትርክናው መንበር በእንደራሴነት በሚመረጥ ብፁዕ አባት ተጠብቆ ቢቆይ ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መከበር እና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መመለስ አስፈላጊ በመኾኑ በዚሁ መንገድ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት መልካም ፍጻሜ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ፣ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩም የበኩላቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ ማሳሰባቸው ተዘግቧል፡፡

ሓላፊነታቸው መንበሩን መጠበቅ መኾኑን፣ ለዕርቀ ሰላሙ ንግግር ሥምረትም የሚጠበቅባቸውን ሓላፊነት እንደሚወጡ የተናገሩት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅዱስነታቸውን ሐሳብ ለቅዱስ ሲኖዶሱ አቅርበው እንደሚነጋገሩበት ገልጸውላቸዋል፤ በውይይቱም ቅዱስነታቸው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ላቀረቡላቸው ጥያቄም ቅዱስነታቸው ቀሪ ዘመናቸውን በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስኖ መቆየትን እንደሚመርጡ መመለሳቸውን በመግለጽ ምንጮቹ አክለው አስረድተዋል፡፡ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የተካሄደውን የስልክ ውይይት ዐሥራ አምስት አባላት ላሉት ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ሪፖርት ማድረጋቸውን ደጀ ሰላም ያረጋገጠ ሲኾን በመጪው ጥቅምት 12 ቀን ጀምሮ በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአጀንዳነት ቀርቦ ዐቢይ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስበት ተስፋ ተደርጓል፡፡

የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀዳሚ የውይይት አጀንዳዎች እንደሚኾኑ ከሚጠበቁት መካከል፡- በየዘመኑ ለተሾሙት አምስት ፓትርያርኮች አመራረጥ ይዘጋጅ ከነበረው ተለዋዋጭ የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ ይልቅ ቋሚ የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ፤ የሕገ ቤተ ክርስቲያንና የቃለ ዐዋዲው ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ፤ በማሻሻያዎቹ የሚመጣውን ተቋማዊ ለውጥ የሚሸከምና የሚያስፈጽም የተጠናከረ የቅዱስ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መዋቅር የሚሉት ወሳኝ ጉዳዮች የሚኖሩ ሲኾን ከዚህም ጋራ አሁን በመልካም ሂደት ላይ የሚገኘውን የዕርቀ ሰላም ንግግር በአጭር ጊዜ ወደ ፍጻሜ የሚያደርሱ የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡካን ከብቁ እና ተገቢ የሰው ኀይል ጋራ የሚሠየሙበት እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

ነገር ግን÷ እኒህ በየጊዜው እየተሞከሩ በየምክንያቱ ሲደናቀፉ የቆዩና ባለንበት መድረክ ወሳኝ የሰላምና አንድነት፣ የተቋማዊ መሻሻልና መጠናከር አጀንዳዎች የኾኑት የቤተ ክርስቲያናችን ነባር ችግሮች አሁን በሰላምና አንድነት ጉባኤው፣ በቀድሞው ፓትርያርክ፣ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ እና በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ በሚታየው ተስፋ ሰጪ አያያዝ ከመሠረታቸው እንዳይፈቱ ዕንቅፋት የሚፈጥሩ አሉባልታዎች እና ድርጊቶች በቸልታ ሊታዩ አይገባም እንላለን፡፡

የሰላም እና አንድነት ጉባኤው እንደ አካል ይኹን አባላቱም እንደ ግል ለሁለቱ ተወያይ አባቶች በማእከላዊነት ማገልገላቸው መልካም ኾኖ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚሰጠው በሚጠበቀው መግለጫም በወዲያኛውም በወዲያኛውም የተፈጸሙና ቅር ከማሰኘት አልፎ አደናቃፊና ጣልቃ ገብ ተግባራትን የሚገሥጽ፣ ጠቅላላ ሂደቱም በተፋጠነ አኳኋን ወደፊት ተራምዶ በአጭር ጊዜ ወደ ፍጻሜ የሚደርስበትን መንገድ የሚጠቁም እንዲኾን ያስፈልጋል፡፡ ከኻያ ዓመት በኋላ ለሰላም፣ ዕርቅና ፍቅር ከመሥራት አልፈው ጥብቅና መቆም የሚገባቸው ብፁዓን አባቶች አንድነት እንዲፈጥሩ ለማግባባት ምን ያህል ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል?!

በተያያዘ ዜና ይህንኑ አባቶችን እርቅ እና አንድነት በተመለከተ ማኅበረ ቅዱሳን ያዘጋጀው የሁለተኛ ሳምንት የስልክ ውይይት ትናንት እሑድ ተደርጓል። አበው ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን እና የተለያዩ ምሁራን አስተያየታቸውን በሰጡበት በዚህ ዝግጅት ላይ በወቅቱ ለተነሡ የተለያዩ ጥያቄዎች ከማኅበሩ እና በአስረጂነት ከቀረቡት ከ“የሰላምና አንድነት ጉባኤ” አባላት ምላሽ ተሰጥቷል። ተሰብሳቢዎቹ በሰሜን አሜሪካ ያለው የቤተ ክርስቲያን አባቶች ክፍፍል ማብቃት እንዳለበት በጥልቅ መንፈሳዊ ስሜት ሲገልጹ ከመሰማታቸውም በላይ በቀጣይነት ሁሉንም የሚያሳትፍ እና እንቅስቃሴ የጀመረውን ““የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ሊረዳ የሚችል ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
14 comments:

Anonymous said...

emabata sedate yebekane eregine

Anonymous said...

melkame egizihare yirdan!!!!

Anonymous said...

Aristu "Seber Zena" bibal des yilegnal !!!

Anonymous said...

እግዚአብሔር መልካም ነገር አደረገልን ደስም አለን::

Anonymous said...

AMELAKA KIDOSANE EREDANE

Unknown said...

ይትባረክ አምላከ አበዊነ ለዘአስምዐነ ዜና ሠንየ። በጣም ደስ የሚልና ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዜና ነው። የዚች ጥንታዊት ፥ ሐዋርያዊት፥ ወንጌላዊት ፥ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት የሆነው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ20 ዓመታት በልጆቹዋ መካከል ተጋርዶ የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ እንደገና አንድ ሁነን እንድናመልከው በመፍቀዱ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ነውና አሁንም ይመስገን። ''ወሠዐረ እምኔነ መርገመ ፥ ወገብረ ሰላመ ማዕከሌነ''እንዳለው የሶርያው ቅዱስ ኤፍሬም (306-376 AD)በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ፤ አሁንም ይህን የጥል መርገም ሺሮ ሰላሙን በመካከላችን እንዲያሰፍን የሁላችንም ጥረት ይሁን። የሰማነውን ተስፋ ሰጭ ዜና በገቢር እንድናየው ሁላችንም በትጋት የሚጠበቅብንን ክርስቲያናዊ ድርሻ እንወጣ። በያለንበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንም ይህ የርቀ ሰላም ጉዞ መሰናክል ሳይገጥመው ባጭር እንዲጠናቀቅ ጸሎት እናድርግ፣ እንዲደረግም ሁሉም አባቶች ለልጆቻቸው ይህን መመሪያ ቢያስተላልፉ መልካም ነው ። ...ማኅበረ ቅዱሳን እያደረገ ያለውን መልካም ሥራ በግሌ ያለኝን አድናቆት እንድገልጽ የደጀ ሰላምን ፈቃድ እጠይቃለሁ። ይህን ማኅበር መንፈሳዊነቱን ሲጠራጠሩ ከነበሩት ምዕመናን አንዱ እንደነበርኩ መደበቅ አልችልም። ወእምፍሬ ምግባሮሙ ተአምርዎሙ እንዳለው አሁን ግን በሂደት በሚያደርጉት መልካም ሥራ በእውነትም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ደህንነት ከመቆርቆር ሌላ የተደበቀ ሥጋዊ/ዓለማዊ አጀንዳ እንደሌላቸው እየተረዳሁ መጥቻለሁ። ገዳማትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ረዳት በማጣት እንዳይዘጉ የሚያደርጉትን የሞራልና የቁሳቁስ እርዳታ ፣ አዲሱ ትውልድ በሞራልና በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን የሚያደርጉትን ያልተቆጠበ ጥረት ባገር ውስጥ ካሉት የሥጋ ዘመዶቸ ለመረዳት ችያለሁ። ብዙ ካህናት የሥጋ ዘመዶቸ በሰሜን ጎንደር ይኖራሉ። በኩሩ ታላቅ ወንድሜ መሪጌታ ነው። የደብረ ዓባይ መዝገበ ቅዳሴ አስመስክሮኣል። ቅኔ ፥ አቋቋምና ድጓም አዋቂ ነው። 2ቱ ልጆቹንም አስተምሮ ካህናት ሁነዋል። ስለማኅበረ ቅዱሳን በጎ አድራጉት ከነዚህ ቤተሰቦቸም ሳይቀር መረጃ ማግኘት ችያለሁ። ስለዚህ አሁንም በዚህ በአባቶች መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት ማኅበሩ የሚያደርገውን ሥራ በማየት ሁላችንም ልንተባበረው ይገባል። የተደረገውን ጉባዔ ስልክም ተከታትየ አለሁ ፥ ወደፊትም ለመከታተል ወስኛለሁ። እና በርቱ ፥እንበርታ ነው የዛሬው የእኔ አስተያየት ባጭሩ ።

Anonymous said...

Fitsamewon yasamiren.

Anonymous said...

Weyy Endet des yemil zena new. Gosh endih new kirstian, bekena menfes honew yikir sibabalu mayet metadel new. Beka ahun wedefit mehed bicha new yemiyasifeligew, Amlak betibebu lehulachinim yemihon meftihen yamelakiten, Amen!

Anonymous said...

Bewnu le Egziabehare yemisanew neger alen

Anonymous said...

It is very very exciting news , May GOD bless u all.

Deje selam EXCELLENT NEWS KHY

Anonymous said...

Selam Dejeselamoch,
I think you wanted to edit the news about government's preference about "Abune Gorgorios". But it is still in the PDF file. I didn't like such a provocative news. Please update the PDF news ASAP.

From Germany

Anonymous said...

Egziabher yerdan, yesu fekad yehun, betam konjo jemare new!!!

Solomon Berhe said...

ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን፤ ቅን ደገኛ አባት ይስጥልን፡፡

almaz said...

hulachenem eneseley egezabehier yerdan

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)