October 22, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ለዕርቀ ሰላሙ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው አሳሰበ


  • በመዋቅር፣ አደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ አስፈላጊነት ላይ ሲመክር የሰነበተው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ለመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መጠናከር፣ ለኢኮኖሚ አውታሮች መስፋፋት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቷል፡፡
  • ቤተ ክርስቲያን የራሷ ሆስፒታሎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ በርካታ የሁለገብ አገልግሎት መስጫዎች እና የልማት ተቋማት እንዲኖሯት ዕቅድ ተይዟል::
  • ተሻሽሎ የሚጸድቀው ቃለ ዐዋዲ ደንብ በኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይተረጎማል፤ ሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና የአሠራር መመሪያዎች ተጣጥመው እንዲዘጋጁ ተጠይቋል::
  • በ31ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዝግጅት የታየው የአመለካከትና አሠራር ለውጥ ጅማሮ ተሻሽሎና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሰበካ ጉባኤው መምሪያ ገልጧል፡፡
  • የተሰብሳቢዎችን የለውጥ ስሜት ባነቃቁት ጥናታዊ ጽሑፎችና የቡድን ውይይቶች ካለፉት ጉባኤያት የተለየ አካሄድ ለነበረው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሥምረት የሰበካ ጉባኤ መምሪያ፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ምስጋናና አድናቆት ተቸሯቸዋል፡፡
  • READ THIS NEWS IN PDF.

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012)፦ ለስድስት ተከታታይ የሥራ ቀናት የተሳታፊዎችን ትኩረት በሚስብ አኳኋን ሲካሄድ የቆየው 31ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ትናንት፣ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ቀትር ላይ ሠላሳ ነጥቦች ያሉት ውሳኔና የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ ጉባኤው በአቋም መግለጫው ‹‹ስለ ሰላሙ ኹኔታ ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥበት›› በማለት ዛሬ፣ በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚካሄድ ጸሎት የሚከፈተውን የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አሳስቧል፡፡

ሰበካ ጉባኤ ‹‹ዐጸደ ወይን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አብባ አስካለ ወይን ያፈራችበት የ21ው መቶ ክፍለ ዘመን ገባሬ ተኣምር ነው›› ያለው መግለጫው በቀረቡት የ2004 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን ሪፖርቶች እና ጥናታዊ ጽሑፎች፣ በተካሄዱት የቡድን ውይይቶች÷ በዕቅድ መመራትን፣ ዘመናዊ የፋይናንስ ሲስተምን፣ መልካም አስተዳደርን፣ የገዳማትና ቅርስ አጠባበቅን፣ የአብነት ት/ቤትን እና ሰንበት ት/ቤቶችን፣ ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ የተደረሰባቸው የተቋማዊ አደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ውሳኔዎች ‹‹የወረቀት ላይ አበባ›› ኾነው እንዳይቀሩበትም አደራ ብሏል፡፡

ዝርዝሩን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡ 

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)