October 13, 2012

በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማኅበረ ቅዱሳን ጠየቀ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 3/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 14/2012/ READ IN PDF):- የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራርና የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤያት መስከረም 30 ቀን 2005 .. በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ በአስተዳደርና በተወሰኑ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን አተረጓጎም ልዩነት ምክንያት ለሁለት አሠርት ዓመታት ተለያይተው በቆዩ አባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት እስከ መጨረሻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ ማቅረባቸውን የማኅበሩ ድረ ገጽ ዘገበ፡፡

ድረ ገጹ (Linkየማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ / ሙሉጌታ ኀይለ ማርያምን ጠቅሶ እንዳለውበአገር ውስጥና በውጪ አገር በሚገኙ አባቶች መካከል የተጀመረው ውይይት ከሁሉም ጉዳዮች በፊት ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሠራና እንዲፈጸም የማኅበሩ ፍላጎት” መሆኑ ተገልጿል

ዋና ጸሐፊው ለመካነ ድሩ በሰጡት መግለጫየማኅበሩ አባላትም ሆኑ ሌሎቹም ምእመናን የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ተግተው መጸለይ ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሰላሙንና የዕርቁን ሁኔታ ሊያደናቅፉ የሚችሉ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱም አንድነቷ ተመልሶ የምትሠራበት ሁኔታ ይፈጠር ዘንድ ማኅበሩ የሚጠበቅበትን አገልግሎት ለመፈጸም ዝግጁ ነው፡፡ ስለሆነም የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መምህራን ጭምር የማኅበሩን አቋም የማስታወቅ ሓላፊነት አለባቸውብለዋል፡፡

እርቁ እንዴት ይሁን? እንዴት ይፈጸም የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጣቸው በሁለቱም ቦታዎች በሚገኙ አባቶችና በአስታሪቂ ሽማግሌዎች መሆኑን በመገንዘብ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት መተው እንደሚገባ / ሙሉጌታ ማስታወቃቸውን የጠቀሰው ድረ ገጹ “የተጀመረው እርቅ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግና እግዚአብሔርንም በጸሎት እንዲማጸን አሳስበዋል” ብሏል።

ዋና ጸሐፊው በማጠቃለያ መልእክታቸው “ፍቅር ሰላምና አንድነት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ስምረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁል ጊዜ ለፍቅር ለመግባባትና አብሮ ለመሥራት በሰላም ለመኖር ሁሉም መጣር ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ ከዚህ የሚያደናቅፍ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡ አንድነትን የሚጠላ ፍቅርን የሚጠላ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡ ስለዚህ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ለዚህ ጉዳይ መትጋት ይኖርባቸዋል” ማለታቸውን ዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜና ይህንን የአባቶችን እርቅ አስመልክቶ ማኅበረ ቅዱሳን ካሉት የውጪ አገር ማዕከላት አንዱ የሆነው የአሜሪካ ማዕከል ያዘጋጀው የቴሌኮንፍረንስ ውይይት ባለፈው እሑድ መካሄዱ ታውቋል። ዕርቀ ሰላሙን በተመለከተ የተለያየ ሐሳብ ያላቸው ክርስቲያኖች ከተለያዩ የአሜሪካ እና የካናድ ከተሞች በተሳተፉበት በተባለው በዚህ ውይይት የተለያዩ ሐሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን በሚቀጥለው እሑድ ጥቅምት 4/2005 ዓ.ም/ ኦክቶበር 14/2012 ከሰዓት በኋላ እንዲቀጥል ቀጠሮ ተይዞለታል። 

አዘጋጅ ክፍሉ እንዳለው ውይይቱን ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ በሚከተለው መግለጫ መሠረት መጠቀም ይችላሉ።

የኮንፈረንስ ቁጥር፦ 1-559-726-1200/ መግቢያ ኮድ፦ 24-81-12
ቀን፦ እሑድ  ጥቅምት 4  ቀን 2005 ዓ/ም (October  14, 2012 )
ሰዓት፦ 6:00 PM - 8:00 pm በዲሲ ሰዓት (EST) / 3:00 pm - 5:00 PM ካሊፎርኒያ ሰዓት (PST)

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

1 comment:

Anonymous said...

በኢትዮጵያና በውጪው ዓለም ባሉት አባቶች መካከል ሃያ ዓመት ሙሉ የኖረው መለያየት ተወግዶና ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት እንደገና እንዲታነጽ፣ ትምህርቷም ተጠናክሮ እንዲስፋፋ፣ የጥፋት ተልእኮ ካላቸው ከጥቂቶች በቀር፣ የመላው ምእመናን የዘወትር ፍላጎት፣ ጥያቄና ጸሎት ነው። የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ቅድሚያ ተሰጥቶት በመልካም ውጤት እንዲቋጭ ማኅበረ ቅዱሳን በይፋ ለባቶች ያቀረበው ማሳሰቢያ በውስጥም በውጭም የምንኖረውን የቤተ ክርስቲያኗን ምእመናን ጥያቄ የሚያስተጋባና የሚያጠናክር ወቅታዊ መልእክት ነው። በአሁኑ ሠዓት ፍቅርን፣ ዕረቀ ሰላምንና የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት ሊያደናቅፍ የሚችል ምንም ምድራዊ ምክንያት ሊኖር አይገባም። ልዑል እግዚአብሔር መንገዱን ጠርጎልናል። ምስጋና ይግባው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)