October 31, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ሐሳቦች


 • READ THIS NEWS IN PDF.
 • የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ ራሱን የሚጠራው” የሚለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ተ.ቁ (2) “እኛንም አላስደሰተንም፤ እንዲስተካከል እናደርጋለን” ሲሉ ሌላው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ደግሞ እንዲህ ያለው ቃል ከጋዜጠኞች በፊት ምልአተ ጉባኤው በተናበበው የመግለጫው ክፍል ላይ እንዳልነበረ ተናግረዋል
 • “ስድስተኛውን ፓትርያርክ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ እየተዘጋጀን ነው ያለነው፤ ሕጉን ካጸደቅን በኋላ ወደ ምርጫው ነው የምንገባው፤ በውጭም ያሉት ተቀብለውን፣ በውስጥም ያለነው ተቀብለናቸው ከእኛው ጋራ ምርጫውን እንዲያካሂዱ ፈቃደኞች ነን፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
 • “ጳጳስ ንብረት የለውም - ጎመን የሚዘራበት፣ ሽንኵርት የሚተክልበት፤ ንብረቶቹ ምእመናን ናቸው፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ የመለሱት/
 • በአዲስ አበባ አራት አህጉረ ስብከት አደረጃጀት ሂደት ከሥራ አስኪያጅነት የሚወገዱት ንቡረእድ ኤልያስ በጸሐፊነት ከያዙት የዕርቀ ሰላሙ ልኡክ አባልነትም እንዲወጡ መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ መግለጫም በማውጣት ተጠናቀቀ


 • ምልአተ ጉባኤው የዕርቀ ሰላሙን አምስት የመነጋገሪያ ነጥቦች ለይቷል፤
 • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባን፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ይመራሉ፤
 • “የመነኰሳት መተዳደሪያ ደንብ” ይወጣል፤ የገዳማት ተወካዮች በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤
 • ለአኵስም ጽዮን ማርያም አዲስ ንቡረእድ ይሾማል፤
 • ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች (ብር 10 ሚልዮን+) እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን በላይ በጀት ተመድቧል፤

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 21/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 31/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሥራ ላይ የቆየው የጥቅምት 2005 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ፣ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ላይ መግለጫ ተጠናቀቀ፡፡ በ“ልዩ ልዩ ጉዳዮች” አጀንዳዎች ሥር በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰውና የበጀት ምደባን ጨምሮ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቀደም ሲል ውሳኔ ያሳለፈባቸውን የመነጋገሪያ ነጥቦች ዳግመኛ በጥልቀት ሲመለከት የቆየው ምልአተ ጉባኤው÷ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡክ መነጋገሪያ (መደራደሪያ?) የሚያደርጋቸውን አምስት ነጥቦች መለየቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም የሚገልጡ ናቸው የተባሉት አምስቱ ነጥቦች “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ላቀረባቸው ሰባት ጥያቄዎች በተሰጡ መልሶች ላይ በመመሥረት የተዘጋጁ መኾናቸውን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አስረድተዋል፡፡

October 29, 2012

የቅ/ሲኖዶስ የቅዳሜ ውሎና ውሳኔዎች፤ ስብሰባው አልተጠናቀቀም


 • READ THIS NEWS IN PDF.
 • ቤተ ክህነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጭር እና የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፤
 • ለአዳሪ እና አብነት ት/ቤቶች ማጠናከርያ 10 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧል፤
 • የካህናት ማሠልጠኛዎች በየክልሉ ይቋቋማሉ፤ በየቋንቋዎቹ የመጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመት ይጀመራል፤
 • የሥርዐተ ምንኵስና አፈጻጸም በየገዳማቱ ሕግ መሠረት ጠብቆ “ልማት እንዲጠናከርባቸው” ይደረጋል፤
 • የጋዜጠኛ መ/ር ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር “ብፁዓን እነማን ናቸው?” መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብበት ተወስኗል፤
 • የአቡነ ጳውሎስ “ንብረት” ተሰብስቦ ወደ ሙዝየም እንዲገባ ተወስኗል፡፡ ሐውልታቸውስ?
 • ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል  የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ጸሐፊ የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን ከሥልጣነ ክህነት በማገድ የወሰዱት ርምጃ “በግል ጥላቻ የተገፋ ነው” ያለው ምልአተ ጉባኤው ካህኑም ሊቀ ጳጳሱም ለዕርቀ ሰላሙ በሚያመሩት ብፁዓን አባቶች አቀራራቢነት ተነጋግረው መፍትሔ እንዲሹ ትእዛዝ ሰጠ
 • በሕገ ወጡ የዋሽግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ላይ አስቀድሞ የተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ “የጽ/ቤቱ ባለሙሉ ሥልጣን” በሚል በአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ተሹሞ የነበረው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከተሰጠው ሓላፊነት ተወግዶ በቃለ ዐዋዲው መሠረት አዲስ ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ተወስኗል
 • የአቡነ መቃርዮስ የኤርትራ ጉብኝት እንደማይወክላቸው በስደት የሚገኙት አባቶች ገለጹ፤
 • በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የሀ/ስብከቱን የአስተዳደር ችግር የሚያጠራው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ልኡክ ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

October 27, 2012

የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል


አርእስተ ጉዳይ፡- 
 • READ THIS ARTICLE IN PDF
 • የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
 • በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
 • ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከት ያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
 • ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
 • ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤

October 26, 2012

የቅ/ሲኖዶስ የሰሞኑ ውሎ ሪፖርታዥ


 • በግብጹ የፓትርያርክ ምርጫ ቤተ ክርስቲያናችን በአምስት ብፁዓን አባቶች ትወከላለች
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ሰጠ::
 • የውጭ ግንኙነት መምሪያ በክፍለ አህጉር ዴስኮች ይደራጃል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳስስ መጽሔት በእንግሊዝኛ ቋንቋ  ይጀምራል::
 • “አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መከፈሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ይቀርፋል፡፡” /የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/
 • ሢመተ ፓትርያርክ በምርጫ ወይስ በዕጣ? ከግብጽ ምን እንማራለን?

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 26/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 25 ቀን 2005 (እ.አ.አ ኖምበር 4 ቀን 2012) በሚካሄደው የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118 ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚገኙ አምስት ብፁዓን አባቶችን በልኡክነት መሠየሙን የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ አስታወቀ፡፡

October 25, 2012

የዕርቀ ሰላሙ ውይይት በመጪው ኅዳር ወር ይቀጥላል


 • ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ወሰነ
 • እስከ መጪው ግንቦት ወር የአራቱን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ይቆያል
 • የአራት ኪሎውን መንትዮች ሕንጻ ጨምሮ 283 ቤቶችንና ሕንጻዎችን ማስመለስ በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ከከተማው ከንቲባ ጋራ ውይይት ተካሄደ

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 15/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 25/2012/ READ NEWS IN PDF)፦ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተመጀረው የዕርቀ ሰላም ውይይት በመጪው ኅዳር ወር መጨረሻ እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ለሚቀጥለው ውይይት ምልአተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማን በልኡክነት የሠየመ ሲኾን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በልኡካን ቡድኑ ጸሐፊነት ብቻ እንዲያገለግሉ ተወስኗል፡፡

October 24, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባጸደቃቸው በ20 አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው


 • ዕርቀ ሰላሙ የምልአተ ጉባኤው ግንባር ቀደም አጀንዳ ነው::
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ላይ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል::
 • ንቡረእድ ኤልያስ ኣብርሃ ከሓላፊነታቸው ሊነሡ ይችላሉ::
 • በአቡነ ጳውሎስ ዕረፍት የታሸገው መንበረ ፓትርያርክ ጉዳይ ውሳኔ ያገኛል::

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 24/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት የተጀመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ 20 የመወያያ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

October 23, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ


 • የሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ:: 

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የ2005 ዓ.ም ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ትናንት ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ አምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም የሚጀምረው ምልአተ ጉባኤው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት አስቸኳይ ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ኹኔታ፣ በፓትርያርክ አመራረጥ ሕግ ረቂቅ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ካለፈው ምልአተ ጉባኤ በተላለፉ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

October 22, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ለዕርቀ ሰላሙ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው አሳሰበ


 • በመዋቅር፣ አደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ አስፈላጊነት ላይ ሲመክር የሰነበተው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ለመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መጠናከር፣ ለኢኮኖሚ አውታሮች መስፋፋት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቷል፡፡
 • ቤተ ክርስቲያን የራሷ ሆስፒታሎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ በርካታ የሁለገብ አገልግሎት መስጫዎች እና የልማት ተቋማት እንዲኖሯት ዕቅድ ተይዟል::
 • ተሻሽሎ የሚጸድቀው ቃለ ዐዋዲ ደንብ በኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይተረጎማል፤ ሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና የአሠራር መመሪያዎች ተጣጥመው እንዲዘጋጁ ተጠይቋል::
 • በ31ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዝግጅት የታየው የአመለካከትና አሠራር ለውጥ ጅማሮ ተሻሽሎና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሰበካ ጉባኤው መምሪያ ገልጧል፡፡
 • የተሰብሳቢዎችን የለውጥ ስሜት ባነቃቁት ጥናታዊ ጽሑፎችና የቡድን ውይይቶች ካለፉት ጉባኤያት የተለየ አካሄድ ለነበረው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሥምረት የሰበካ ጉባኤ መምሪያ፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ምስጋናና አድናቆት ተቸሯቸዋል፡፡
 • READ THIS NEWS IN PDF.

የአባቶችን እርቅና ሰላም የሚደግፉ መግለጫዎች ወጡ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ተለያይተው የቆዩትን አባቶች ለማስታረቅ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለመጠበቅ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን እንደሚደግፉ በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዓለም አቀፍ ማኅበር አስታወቁ፡፡ የሁለቱን ተቋማት መግለጫዎች ለማንበብ ይህንን ይጫኑ (መግለጫ 1 እና መግለጫ ሁለት)። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይም ገለልተኛ ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ሊታይ የሚገባው የድጋፍ ምልክት አሁንም በጉጉት እየተጠበቀ ነው። በተለይም በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙት ታላለቅ ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት አሁን የተጀመረው የእቅርና የሰላም እንቅስቃሴ መሠረት እንዲይዝና ችግሩ ለአንዴም ለመጨረሻውም መፍትሔ ያገኝ ዘንድ በጎ አስተዋጽዖዋቸውን በይፋ ማበርከት እንዲሚጀምሩ እየተጠበቀ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን፡፡
October 18, 2012

Mentioning God's name is funny in Ethiopian Parliament?

31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

 • ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል
 • በሪፖርት የተካተተው የዋልድባ ጉዳይ በንባብ መዘለሉ ጥያቄ አሥነስቷል
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 7/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 31መደበኛ ስብሰባ፣ ትናንት፣ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ በመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከአራረ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ አመራር በሚሰጣቸው የተሐድሶ መናፍቃን ግንባር ቀደም መሪዎች የተደራጁ ጥቅመኛ ቡድኖች የሽግግር ወቅት አጋጣሚውን ተጠቅመው ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል፡፡

October 16, 2012

የየራሳቸውን “ፓትርያርክ ለመሾም” ሙከራ የሚያደርጉ …


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 6/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 16/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንድነት አስፈላጊነት ከምንም በላይ በሁሉም ዘንድ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ነው። በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም “አንድነት፣ እርቅ” የሚሉት ቃላት ተደጋግመው በመሰማት ላይ ናቸው። የቀጣዩ ፓትርያርኩ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ አሁን መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት አላቸው የተለያዩ አካላት፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና ስብስቦች በይፋ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ከመንግሥት እንጀምር።

October 15, 2012

ዐቃቤ መንበሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት አደረጉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 5/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 15/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ የውይይት መሥመሩን ያመቻቸው በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ነው፡፡ በሁለቱ አባቶች የስልክ ውይይት÷ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ጋራ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፤ ከአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አብረው መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

October 13, 2012

በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማኅበረ ቅዱሳን ጠየቀ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 3/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 14/2012/ READ IN PDF):- የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራርና የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤያት መስከረም 30 ቀን 2005 .. በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ በአስተዳደርና በተወሰኑ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን አተረጓጎም ልዩነት ምክንያት ለሁለት አሠርት ዓመታት ተለያይተው በቆዩ አባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት እስከ መጨረሻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ ማቅረባቸውን የማኅበሩ ድረ ገጽ ዘገበ፡፡

October 11, 2012

ቅ/ሲኖዶስ የድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቋመ


 •    በቅ/ሲኖዶሱ አቋም የተደሰቱት የደብሩ ካህናት፣ ምእመናንና የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አባላት አጣሪ ኮሚቴውን ለማገዝ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል።
 •    ኮሚቴው ማጣራቱን እስኪያጠናቅቅ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ሥ/አስኪያጅ እና የደብሩ አስተዳዳሪ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ታግደው እንዲቆዩ ተወስኗል።
 •      ጉድለቱ ከብር 1.8 ሚልዮን አሁን ከብር 5.6 ሚልዮን በላይ ደርሷል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 1/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 11/2012/ READ IN PDF)፦ ከቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያዎች፣ በዕርቀ ሰላም እና በቀጣዩ ፓትርያርክ ሹመት የቅድመ ዝግጅት ምዕራፎች ላይ አበክሮ እየሠራ የሚገኘው ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው ፀረ - ሙስና አቋም ያላቸውን አገልጋዮች ለበለጠ ተጋድሎ የሚያነሣሣ፣ ምእመኑም በአመራሩ ላይ ያለው እምነት ይጠናከር ዘንድ ታላቅ ተስፋ የሚሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

October 9, 2012

“መሰናዘሪያ” የተባለ ጋዜጣ “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል መዘገቡ ለዕርቁ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላል ተባለ

“አቡነ መቃርዮስ”

(ደጀ ሰላም መስከረም 28/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 8/2012; READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሜላቢን ፕሮሞሽን ሓላ/የተ/የግ ማኅበር የሚታተመው “መሰናዘሪያ” የተሰኘ ሳምንታዊ ጋዜጣ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል በዜና ገጹ ላይ የተሣሣተ ዘገባ ማውጣቱ ለተጀመረው ዕርቅ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ጋዜጣው በስደት ላይ የሚገኙት አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ኤርትራ አምርተው ለቀናት ጉብኝት እንዳደረጉ፣ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋራ አብረው እንደሚሠሩና ጉብኝታቸው ከዚሁ ጋራ የተያያዘ መኾኑን በመጥቀስ ያቀረበው ዘገባ “ትግራይ ኦንላይን” የተባለውን ድረ ገጽ በምንጭነት በመጥቀስ ነው። ድረ ገጹ “Why was Abune Mekariossent to Eritrea by Ginbot-7 after Prime Minister Meles died? በሚል ርእስ ሴምቴፐር 27/ 2012 ባወጣው ዘገባው ኤርትራን ጎበኙ ሲል የጠቀሳቸው “አቡነ መቃርዮስ”ን ነው፡፡ 

October 7, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በውግዘት ስለተለያዩት አባቶች ዕርቅ ጉዳይ የስልክ ውይይት አዘጋጀ


(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 25/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 6/2012/ READ IN PDF):- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በውግዘት የተለያዩት አባቶች በዕርቅ አንድ በሚሆኑበት እና መለያየ በእግዚአብሔር ቸርነት ተወግዶ የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ስለሚጠበቅበት አስተዳደሯ ተጠናክሮ ስለሚቀጥልበት ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልጅነት መንፈስ በጋራ መወያየትና ሳብ መለዋወጥ አስፈላጊነቱን በማመን ምዕመናን ሁሉ የሚሳተፉበት የመጀመሪያ ዙር የስልክ ውይይት” ለእሑድ መስከረም ቀን 27 2005 ዓ/ም (October 7 2012) ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

አቡነ ገሪማ ከሥራ አስኪያጃቸው ጋር እንዲቀርቡ ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ አዘዘ

 • በጠ/ቤ/ክህነቱ ኦዲት የተረጋገጠውን የ1.8 ሚሊዮን ብር ጉድለት ሲያጣጥሉ የቆዩት ሥ/አስኪያጁ ጉድለቱን አምነዋል፤
 • ሥራ አስኪያጁ ሙሰኝነትን በተቃወሙ ሰባት የደብር አለቆች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፈዋል፤
 • ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ የነበረው ደብሩ በቋቱ የቀረው ከብር 70,000 አይበልጥም፤
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 25/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 6/2012/ READ IN PDF):- የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ በስምንት ተጨማሪ ብፁዓን አባቶች እንዲጠናከር የተደረገውና ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩን ጨምሮ ዐሥራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በአባልነት የያዘው ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት፣ መስከረም 25 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው÷ የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምእመናን ተወካዮች በሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ጉዳይ በደብሩ አስተዳዳሪ፣ በሕንጻ አሠሪው ኮሚቴ ሊቀ መንበር፣ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ በየደረጃው ስለቀረቡት አቤቱታዎች እንዲያስረዱ ከጠራቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጋር መወያየቱ ተሰምቷል፡፡

October 5, 2012

የድሬዳዋ ሳባ ደ/ኀ/ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ


 • የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀ/ስብከታቸውን እንቅስቃሴ በቅርበት ተገኝተው ለመከታተል ባለመቻላቸው ምእመናኑ መራራ አቤቱታ አቀረቡባቸው፣ ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ብፁዕነታቸውን ለጥያቄ ጠርቷል፤
 • አስተዳዳሪውና የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ ተጠይቋል፤
 • ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደሚያሳልፍበት ይጠበቃል፤

(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 24/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 5/2012/ READ IN PDF):- የድሬዳዋ ሳባ ደ/ኃ/ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ያለውን ውዝግብ በዝርዝር ከማቅረባችን በፊት በዚህ ውስጥ ስማቸው ተደጋግሞ የሚነሣውንና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ለበርካታ ዓመታት የፓትርያርኩ መጋቤ ሥርዐት (የፕሮቶኮል ሹም) ኾነው የሠሩትን መጋቤ ሥርዐት ሙሉጌታ በቀለን እናስተዋውቃችሁ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)