September 28, 2012

ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያንና ለአንድነቷ

(ከቀስቶ ወተረ አትላንታ ጆርጂያ/ READ THIS ARTICLE IN PDF)
1.   ከታሪክ ምን እንማራለን
በዚህ ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ያሳለፈችውን ችግርና መፍትሔዋን ከጠቅላላው አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ተመክሮ አሁን እኛ ያለብን ችግር መነሻውና ለመፍሔው ምን ማድረግ እንዳለብን የሚገልጥ ጽሑፍ ይሆናል። ጽሑፉ ማንም ለመንካት ተብሎ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም። በጽሞና ከተነበበ ለአንድነቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ብቻ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው። አንባቢዎችም ከዚህ አንጻር እንዲያነቡት ይጠየቃሉ።
ታሪካዊ መረጃና ትምህርት
ከታሪክንደምንረዳው ቤተ ክርስቲያን ብዙ ዓይነት የተላያዩ ችግሮች  ስተጋፈጥ ኑራለች የችግሮቹ መነሻም የዓለም ፖለቲካ ተጠቀሚዎች በክርስትናው ወስጥ ረዳት መስለው መግባታቸው ነበር[i]።  ቤተክረስቲያ የዓለማውያን ነሥታት ጣልቃገብነት ሰለባ የሆነቸውም በቆሰጠንጢኖስ ዘመን በተወሰደው እርምጃ ነበር[ii]። ያ እርምጃ ብዙ የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ አባቶችን እንዳሳደደ እንዳሣሠረና  እዳንገላታ[iii] ብዙ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ሰነዶች ይህን እውነት  ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ።

አሁን በአለንበት ዘመንም እኛ የተደቀነብን ችግር ቀደም ባሉት ዘናት በዓለም በአሉ አብተ ክርስቲያናት ሁሉ የተከሰተ ችግር ነው  የችግሩ መነሻም የዓለም ፖለቲካ መሆኑ   በዚህ ዙራያ ጥናቶች  አረጋግጠዋል ለምሳሌ የምናቀርባቸው የከቶሊክ ቤተ ክረስቲያን፤የራሽያ  ኦረቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፤የአንጾኪያ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያንና የአርመን ኦረቶዶክስ ቤተ ክረስቲያን በዚሁ በፖለቲካ ምክንያት በተፈጠረው የችግር መንገድ አልፈዋል[iv] አንዳንዶቹም እሰካሁን በዚሁ ችግር ውሰጥ አሉ የፖለቲካውን ችግር ማዕበል ተቋቁመው ከችግሩ የወጡት ካቶሊክ እና ራሽያዎች  ናቸው የራሽያዎቹ የችግር መነሻና   ከችግር  እንዴት እንደወጡ እደሚከተለው እንመለከታለን ችግራቸውን ከማየታችን በፊት የሩሲያ ቤት ክርስቲያንን ታሪክ ምንነት መጠነኟ ገለጻ ስለሚያስፈልግ መጠነኛ ማብራሪያ እንመልከት

የራሽያ ኦረቶዶክስ ቤተክሰርሰቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች  የታሪክ ሒደታቸውን በአምስት የታሪክ ጊዜ ምድቦች ይመድቧቸዋል[v] የመጀመሪያው የሞንጎሎያን  ጊዜ የሚባል ሲሆን የአዲሱ ክርስትና እምነት በሩሲያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ ከፍተኛ  እንቅስቃሴ የታየበትና የመጀሪያው የክረስትና መንፈስ ዘመን ይባላል። ሁለተኛው የታሪክ ጊዜ ይኸው የመኖጎሎያን ዘመን ሲሆን1238-1480 ዓም ነው። ይህ ዘመን በሩሲያ የክርስትና ዘመን ውስጥ የሞንጎሎያን ነገሥታት ጭቆና ዘመን የተባለው እና የአዲሲቷ የራሻ ዋና ከተማ የሞስኮ እደገት የታየበት ዘመን ነበር።

 ሦስተኛውየታሪክ ክፍለ ጊዜ የራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከቁስጠንጥንያ ቤተ ክርስቲያን ተለይታ  ራሷን የቻለችበት ዘመን ሲሆን የነጻነት ዘመን በመባልም ይታወቃል። አራተኛው የታሪክ ክፍለ ገዜ የራሽያ ኦርቶዶክስ  ቤተ ክርስቲያን ከስቢል አስተዳድር ጋር የገጠመችበት ዘመን ይባላል አምስተኛው የፓትርያርክን ስልጣን ማደላደልና ቀጣዩ የኮሚኒሰት ክፍለ ጊዜ የተባለው ነው በዚህ ጊዜ ውስጥ የራሽያኦርቶዶክ ቤተ ክረስቲያን በመንግሥት ተቀባይነት መንግሥት ያደራጃት  ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጥን  በአገሪቱ የተከሰተው መልካምም ክፍፉም አጋጣሚዎች ገጥመዋታል።


ዋናውና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የምትመሳሰልበት ግን በኮሚስት ዘመን የገጠማት ችግር ነው  የመጀመሪያው ችግር እንደ እንደኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ቤተ ከርሰቲያኒቱ የመንግረስት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን የነጉሠ ነገሥቱ መንግስት ሲያከትም ጥቅሟና መከበሯ አብሮ አከተመ ከዚያም  የአምላክ የለሹ ኮሚኒስት መርህ ያለየሌለ ኃይሉን ጣለባት በቤተ ክርስቲያኒቱ ወስጥ ከሚያገለግሉት  ከጳጳሳት መካከል ግማሾቹ የኮሚኒስቱን መርህ ደጋፊዎች ሁነው  በመገኘታቸው ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሦስት ተከፈለች።

አንደኛዋ  መንግስቱን የምደገፍ የኮምኒሰት ደጋፊ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ሌላኛዋ እውነተኛዋ የራሻ ኦርቶዶክስ በመባል ግብበመድር ወይም ካታኮፕ ቤተ ክርስቲያን በመሆን ራሷን የቻለች ቤተ ክርስቲያን ሆነች  ሌለዋ ሦስተኛዋ ደግሞ ዓለም አቀፋዊዋ በመባል የመትታወቅ ቤተ ክርስቲያን በማለት ራሷን ሰይማ የምትንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያን ሆነች[vi] ይህ ሁኔታ ከራሻ ውጭ ያሉት ሀገረ ሰብከቶችን በሙሉ  እንዲሁ ከሦስት  ከፈላቸው እንደ ሀገር ውስጡ ሁሉ  አንደኛው የመንግሥትን መጠነኛ ፈቃድ አግኝቶ በአገር ውጥ በሞስኮ ፓትርያርክ ስር ሚንቀሳቀስ  ሌላኛው በውጭ አገሩ ስር በመሆን የጥንቱ ራሽያ የሚባልውን ስም የያዘ ሆነ ሦስተኛ ምደብ የጥንት ራሽያ በመሆን  የውጭቹም በተመሳሳይ መንገድ ተከፈሉ ይህ ሂደት ሁሉም እንደኛው ሌላውን በማውገዝ ለረዥም ጊዜ ከቆዩ በላኋ  አንደነበረው ወደ አንድነት ለመመለስ ብዙ ዋጋ ጊዜና ጉልበት ፈጅተዋል ሆኖም አሁን ውገዘቱም ተፈቶ ተስማምተው በተለያየ አተዳደር በሁሉም ያለች አንዲት ሐዋርያዊት ቤክርሰቲያን የሚለውን ቀኖናዊ መርህ ተከትለው ቀጥለዋል

ለአንድነቱ መምጣት የረዷቸው ግን  ሦስት ምክንያቶች አሏቸው የመጀመሪያው የችግሩን መነሻ የሚሆነውን ዐቢይ ጉዳይ በመመርመር እውነት በሆነው ጉዳይ ላይ መስማማት የችግሩን ምንጭ መረዳትና የችግሩ ፈጣሪና ተጠያቂ ማን እንደሆነ አውቆ አጥፊውን ለተጠያቂነት ማሳመን።[vii]

ሁለት በችግሩ ውስጥ ያሉትን የችግር መነሻ ናቸው የተባሉትን ቅደም ተከተል አወጥቶ ቀላልና ከባድ የሆኑትን ለብቻ በመለየት በችግሩ ውስጥ ሁለቱን ተደረዳደሪዎች አንድ የሚያደረጋቸውን ችግሮች ማውጣትና ለመፍትሔቸውም እንደ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አካሐድ በዚያ በክብደቱ መጠን ተራቸውን ጠብቆ ጥናት ማድረግ[viii] ሲሆን በጥናታቸው መሠረት  የችገራቸው መነሻ የነበረውኮሚንስት መንግሥት መሆኑ በሁሉም ስምምነት ተደረሰ።አርሱም ስለ ነበር የኮምኒስት መውወደቅ ለአንድነቱ ከፍተኛ አስታጽኦ አድረጓል[ix]።ለእኛ ቤተ ክረስቲያን አንድነት ጠንቅ የሆነውና የችግሩ እንብርት የሆነው አሁን ያለው የመንግሥት ፖለቲካ ጣልቃ ገበነት ነው [x]ስለሆነም የችግሩ ዓይነትም መታየት ያለበት በዚህ ከመንግሥት ፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ከሆነ በዚህ ሒደት የቤተ ክረስቲያንን ቀኖና ማሰጠበቅ ይቻላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ነው መመለስ ይኖርበታል።

ለራሽያዎቹ  አንድነት  ላቅ ጠቀሚታ የነበረው  ተጨማሪ ኃይል  የአሚሪካዋ ኦርቶዶክስ  ቤተክረሰቲያን መጠንከር ነበር[xi]። የአሜሪካዋ ኦርቶዶክሳዊት  ቤተ ክርስቲያን መጠንከር ራሷን የቻለች ቤተከርሰቲያን እንትሆን እድል ከመስጠቱም በላይ በዓለም ላሉት ኦረቶዶክሳውያን የትምህርት ማዕክል መሆኗ የሰደተኞቹን ኃይል አበራቶታል። ከዚህ ላይ እኛን ከነሱ የሚለየን ትልቁ ነገር  እነርሱ  ሕግ አክባሪዎች መሆናቸውና ለቀኖና ቤተ ክርስቲያ በለጠ ታቀማኝ መሆናቸው  ነው

የመጨረሻውና ዋናው ነገር ግን የኢኪዮሚኒካል ዓለማቀፋዊ የሆነው የሁሉም ኦርቶዶከስ የአነድነት ፓትርያርክ መኖርም ለተከፋፈሉት አንድነት ጠቀሜታ ነበረው አሁን በዓለንበት ዘመንና አገር የምስራቁ ኦርቶዶክስ በሁሉም  ያለች አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በማለት በዓለሙ ፓትርያርክ ስር የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት[xii]

ሁሉም ራሱን የቻለ ሆኖ ግን የአስታንቡሉን ፓትርያርክ የበላይ አባትነት በመቀበል ሐዋርያዊ ትውፊትንና ኦርቶዶክሳዊ ሥርአተ አምልኮን መሠረት ያደረገ አንድነት ነው። ያላቸው ይህም አንዱ የእድገት ምልክት ነው 

የካቶሊክ ቤተክረስቲያን ሁለት ትልልቅ ችገሮች ነበሩባት አንደኛው የፈረንሳይ ነገሥታት ገሚስ አውሮፓን ይገዙ በነበረበት ወቅት ነጉሡ ከፖፑ ጋር በአለ መግባባቱ መክንያት ለተወሰነ ጊዜ ከአንገላታው በኋላ አስገድዶ አቪዣን ወደተባለች የፈረነሳይ አጎራባች የደንቨር  ከታማ ወሰደው[xiii] ከዚያ ለቀጣይዎቹ ስድሳ ስምንት አመታት በተከታታይ ፈረነሳይ ተወላጁችን እያሾመ ከሮማው የበለጠ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ገንብተው ኑረዋል[xiv] በኋላ በአንዲት መናኝ ቅድስት አማካኝነት ወደ ሮም እንደ ተመለሰ ታሪካቸው ያሰረዳል[xv]

ዘመኑ 1309-1387 እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ሲሆን በዚሁ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ካቶሊክ ሌላ ቸግር ገጠማት 1387 የተመረጠው ፖፕ ዩርባን ስደስተኛ  የለውጥ  አራማጅ በመሆኑ የፈረንሳይ ተወላጆች ጳጳሳት ለውጡ ስለ አስደነገጣቸው  ፖፑን ሳያወርዱም ሳያወግዙም ከአስራሁለት በላይ የሚሆኑ ጳጳሳት ሌላ ፖፕ  ቀለሚንጦስ የተባለ ፖፕ  መርጠው ቀለሚንጦስ  ሰባትኛ ብለው ይሾማሉ።

እነዚህ ሁለት ፖፖች እያንዳንዳቸው አውነተኛው እኔ ነኝ በማለት ተወጋገዙ ይህ ጊዜ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትልቁ ክፍፍል በመባል የታወቃል[xvi] ይህ ብዙም ሳይቆይ የቆንስጣንጢን የሰላም ጉባኤ በማለት የሆለቱን  ጳጳሳት ችግር ሊፈታ ያስበ  አንድ የሰላም ጉባኤ ተቋቋመ  ይህ ጉባኤም ሳይቆይ ሁለቱን ፖፖች ትቶ ሊላ ሦስተኛ ፖፕ መረጠና አለክሳንደር አምሰተኛ ብሎ በመሾም የካቶሊክን ቤተክርሰቲያን የሦስት ፖፖች ባለቤት አደረጋት።[xvii]

በዚህ ሁሉ ግን አበዛኛዎቹ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ይህ ሁኔታና ጊዜም  ቢሆን ካቶሊክ ሦስት ፖፖች አልነበሩዋትም። ቤተ ክርስቲያን አንድ ሰለ ሆነች አንድ እውነተኛ ፖፕ ሁለት የሐሰት ፖፖች ነበሩ  ብለው ይተርካሉ ምክንያትቀኖናው ለአንድ መነበር አንድ ፖፖ ብቻ ስለሚፈቅድ ነው በነገራችን ላይ እነዚህ ፖፖች ሁሉ ቦታችሁን ለቀቃቹ ብሎ የወቀሳች የለም በሕገወጥ በመሾማች እንጅ አሁንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ  ቤተ ክርስቲያን  የተከሰተው ችገር ይህ  ዓይነቱ ነው። መተያት ያለበትም ቀኖናው አንዴት ይከበር የሚለው ጥያቄ  ነው ትክከለኛውየቤተ ክርስቲያንን ትክክለኛ አቅጣጫ መስያዝ የሚቻለውም ይህጥያቄ መለስ ማግኘት ሲችል መሆን  አለበት ይህ መልስ ሲመለስ በመንም አይነት የገለሰቦችን  ጥቅምና ጉዳት ማይታይት የለም መታየት ያለበት ትውፊተ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጠብቀው ቀኖና ነው።

የካቶሊኮቹም  ችግር መጨረሻ  የተቃለለው  ሁለቱ የሐሰት ፖፖች በግዴታ ውዴታ በፈቃደቸው ሥልጣናቸውን ሲለቁ በሕጋዊ መንገድ ተመርጦ ስልጣን የያዘው እውነተኛው ፖፖ ግን እስከ ጊዜ ሞቱ አገልግሎ አርፏል። ከዚያም በምተኩ እየተመረጠ እስከ አሁን የቀጠለ ሥርአት አላቸው ይህንንም መደርግ ያለበት አንደኛውና ዋነኛው ቀኖናዊ መንገድ ነው።

የኦርቶዶክሶቹ ግን ከዚህተለየ ነው የተከተሉት መርህ  የተመሠረቱበትን አለማቀፋዊ ቀኖና መሠረት በማድረግ ሲሆን ግማሾቹ አስተዳደራቸው ራሳቸውን እንደቻሉ ሁነው  በአስተዳደራዊ አንድነት ሳይሆን ቀኖናው በሚያዘው መሠረት ሐዋርያዊ ቀጣይነትን የአምለኮ ሥርዓትን የዓለሙን ፓተርየርክና  እውነተኛውን እምነት ከተቀበለ በዓሉበት ሆነው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት የክረስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት የሚለውን የሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንን  መርህ በመቀበል አቃለውታል[xviii]

እስከ አሁንም ችርግሩ  ያለተቃለለላቸው አሉ  በኦርቶዶክሱ ዓለም  አሁንም  ይህን የሚከታተል ኮሚቴ አለ ይህ ኮሚቴ ልዩነቱ ሲፈጠር ቀኖና ቤተ ክረስቲያን እንዳይጣስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል ጥንቃቄው እነሱ የተቀበሏቸው ጉባኤያት በተቀነኑ ቀኖናዎች መሠረት መሔዳቸውን ማረጋገጥ ነው የእኛ ጉዳይም መታየት ያለበትዚህ አንጻር ነው  የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክረስቲያን አሁንም ችግራቸው እንዳለ ይሁን እንጅ በአሁኑ ጊዜ ያሉት  ሦሰት ፓትርያርኮች[xix]  ይህም ሦስቱም ራሳቸውን የቻሉ ፓትርያርኮች ይሁኑ እንጅ በእመነት አንድ ስለሆኑ ሳይወጋገዙ እያንዳደንዱ ፓትርያርክ የተቀበለው ሕዝብ አባት ሁኖ በሌላኛው ፓትርያርክ እውቅና በማግኘት ሥራቸውን እየሠሩ ነው[xx]።ይህ ማለት በአሁኑ ጊዜ በአርመኒያ አንዲት በሦስት ፓትርያርኮች ይምተዳደር የአርመን አርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አለች ማለት ነው

እነዚህ ሁሉችገራቸውን በማቃለል ላይ ናቸው ይህ ሁኔታ ግን እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብዙ ትግስትን አርቆ ማየትና የኔነትና ጥቅም የሚሉትን ሁሉ እንዲተው ያደርጋል የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን በችግር ምክንያት ጠቅላይ ጸህፈት ቤቷን ወደ ችጋጎ አዛውራ ሥራዋን እየሠራች ትገኛለች። እነዚህን ሁሉ ችግር ያለብን ችግሮ ስንመለከት  የትኛውን ይመስላል ከሚለው ጥያቄ ለማፈላለግ  ወደፈት ለምናደርገው ውይይት መጠነኛ እገዛ እናገኛለን ችግሩ አንድ ዓይነት ላይሆን ይችል ይሆናል  ለመፍትሔው ማፈላለጊያ  ግን ያስተመረናል በችግር እያለፈን ያለነው  እኛ ብቻ እንዳልሆን ከአወቅን አሁንምን ወደፊትም ለሚደርስብን ችግር ለመፍትሔ አንቸገርም።

ይህም ትግስትን ቅንነትን እውነተኝነትን የሚጠይቅ ሥራ ነው  ከእነዚህ ውጭ እሠራለሁ ማለት ሕዝብ ከማሳዝን ራስንም ከማታለል ቤተ ክርስቲያንን ከማዳከም ያለፈ ፋይዳ የለም በዚህም ምክንያት ወይ ፖለቲከኞች መሆን አልተቻለ ወይ ሃይማኖተኛ መሆን ካልተቻሰለ ከሁሉም ሳንሆን በክንቱ መደክም ይሆናል ይህን ከላይ ለምሳሌ የገለጥነውን መሠረት አድርገን መሆን የአለበትን ቁምን ነገር ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ነጥብ እንመለክት

ችግራችንና መፍትሔው ሰጭ ውይይት የኢትዮጵአ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ ክረስቲያን ችግር  በጥቅሉ ሲታይ ከጠቅላላው ትውፊታዊ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከቤተ ክርስቲያኒቷ ታሪክና ሥርዓት ጋር መጋጨት ከታሪካችን መረዳት እንችላለን ከዚህ ተነስተን ስለኢትዮጵያ ቤተክረስቲያን ችግር ስናጠና የምንጀምረው ከአመሠራረቷ ነው በብዙ የታሪክ ሰነዶች እንደ ተገለጠው ክርስትና በኢትዮጵያ በነገሥታት አነሣሽነት ስለተጀመረና ተይዞ ስለኖረ እንደ አገርም እንደ አገር አንድነት አስተባቂም ሆኖ ኖሯል[xxi]።ቤተ ክርስቲያን ራሷን ስትችል ንጉሠ ነገስቱ የተጫወቱትን ሚናና የግብጽን ቤተ ክርስቲያን አጻፋ ስንመለከት የእነ ቅዱስ አረቤን የእነአጼ ተዎድሮስን ታሪክ ስንመለከት የቤተ ክርስቲያኒቱ  የበላይ ጠቂና መሪዎች ነገሥታቱ  መሆናቸውን በርግጠኝነት ማወቅ ይቻላል ይህ ከሆነ ደግሞ በሀገር የሚመጣ ማንኛውም ፖለቲካዊና ሕዝባዊ ጥቅምም ሆነ ጉዳት ቤተክርቲያኒቱን በቀጥታ ይመለከታታል

በዚህም ምክንያት በአገር ችግር ሲመጣ ችግሩ የሚመለከተው አገርን ብቻ አይደለም    በችግሩ በመካፈልም ሆነ ችግሩን በማቃለል ደረጃ  ቤተ ክርስቲያቱ ትልቅ ሚና ነበራት[xxii]  በዚህም መሠረት  የክርስትናውን ሃይማኖት ለማስጠበቅ ይደረግ የነበረው ጥንቃቄ የአገርን ለማስጠበቅም እንደሚደረገውና ለአገር አንድነት የሚጠይቀው የጥበቃ ሥራ ጋር አንድና ተመሳሳይ ነበር የአጼ ምን ይልክን የጦር አዋጅና የካህናቱ ታቦት ይዘው መዝመት ቤተክረስቲያኒቱ ስለ አገር የነበራት ሚና የሚሳየው  ነጸብራቅ ነው።

የቤተ ክረቲያን ቀኖና ጥስት አጀማመርይህ የመንግሥት ከለላና ጥበቃ ሲቀር በሌሎቹ መነግሥት ይደገፋቸው በነበሩ  አብያተ ክርስቲያናት እንደሆነው ሁሉ ሃይማኖቱን የሚመሩት ነገሥታት ችግር  ሲገጥማቸው የተከሰተው ችግር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ነክርስቲያንም ቸግር በተመሳሳይ መጠንና መልክ ተከሰተ  ቤተ ክርስቲያኒቱ አገራዊ አንደመሆኗ  መጠን የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር የሚከሰተው በአገር ላይ ችግር በተፈጠረ ጊዜ ነው።

በመሆኑም የቤተ ከርስቲያናችን የቀኖና ጥሰት ችገር  የተጀመረው በአገሪቱ የኢጣልያ ወረራ በተካሓደበት  ወቅት ነበር።ይህ ማለት የአገር ወረራ የቤተከተርስቲያን ወራራ ጭምር ነበር ማለት ነው ይህን ለማረጋገጥ በነበሩት ሊቀጳጳስና  በኢጣልያ ፖለቲከኞች መካከል በነበረው አለመግባባት የተፈጠረው ችግር ሊቀ ጳጳሱ እንዲሰደዱ ማድረጉ ነበር። የዚያ ውጤትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በሕገወጥ መንገድ ጳጳሳትን መሾሟና ያን ተከትሎ የመጣው የኢሕጋዊነት  ችግር አሁንም ላለንበት ችግርም መጠነ ሰፊ አስተወጽኦ አድርጓል ።

ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ  ሁኔታው የተከናወነው  የንጉሠ ነገሥቱ መሰደድን ተከተሎ የመጣ ነበር[xxiii] ያን የቀኖና ጥሰት ተከትሎ የተወሰደው እርምጃ ቤተ ክርስቲያንን ትዝብት ላይ የጣለ ውሳኔ ነበር በዚህ ቦታ ላይ በሰፊው መግለጥ አዳጋች ቢሆንም በመጠኑ ግን ማብራራት ወሳኝነት አለው ።

ኢጣልያ ኢትዮጵያን ከመውረራ በፊት ከግብጽ የመጡ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ የበላይ የነበሩበት በግብጻየውያን ሥር የነበረ አንድ ሊቀ ጳጳስ አምስት ኤጲስቆጶሳት አባለት የነበሩበት ሲኖዶስ ነበር ኢጣልያ  አገሪቱን ስትወርና   ነጉሠ ነገሥቱ ሲሰደዱ ግን ሊቀጳጳሱም አብረው ተሰደዱ በዚህም ጊዜ ሁለቱ ጳጳሳት አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል በግፈኛው ጠላት በግፍ በሰማዕትነት ራሳቸውን መስጠታቸው ይታወሳል  የግብጻዊው ሊቀ ጳጳስ መሰደድ  ምክንያት ግን  ሁለት ግልጽ ሁኔታዎች ነበሩ አንደኛ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ  ጳጳስ ወደ ለኢትዮጵያ ሲመደብ ቃለ መሐላ የሚፈጽመው ለንጉሠ ነገሥቱና ለመንግሠታቸው ታማኝና ጠባቂ እንዲሆን ስለነር ንጉሡ ሲሰደዱ ጳጳሱ ብቻቸውን መቀመጥ አስፈላጊም ሕጋዊም አልነበረም[xxiv]

ምክንየቱም አንዱ የንጉሥነት ሥልጣን  ይገባኛል ባይ  ጳጳሱን አስገድዶ ንጉሥ ሊሆን ይችልና የወደፊት በንሡና በግብጽ ቤተ ክርሰቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያሻክር ይችላልና ነው። ሁለተኛው ግብጽን በመትገዛው በእንግሊዝና ኢትዮጵያን በወረረቸው ኢጣሊያ  ያለው የፖለቲካ አለመግባባት የመጣው ተጽዕኖ ነው በዚህ ምክንት ቤተ ክርስቲያንን አሁን ለአለው ችግር  መሠርት  የሆነ  አሉታዊ ተጽእኖ አመጥቷል[xxv]  የችግሩን መነሻ ኢትዮጵያውያን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎችም ችገሩን አንጠረው ማውጣት አልቻሉም እንደዋና አንኳር አድርገው የሚገልጹት የጳጳሱን መሸሽ እንጅ  የችግሩ መንጭ የሆነውን  በእንግሊዝና በኢጣሊያ መካከል የነበረው የፖለቲካ ልዩነት ተጠያቂ አላደረጉትም።[xxvi]

ዋና መሠረቱ የሆነው ችግር  የኢጣልያው ወራሪ ኃይል የግብጽ ቤተክረስቲያን የመደበቻቸውን ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ እናት ቤተ ክረስቲያን ለይተው ራሷን የቻለች ቤተ ክርስቲያን ያደረጉና አርሰዎ ፓትርያርክ ይሁኑ እንጅ ከግብጽ ጋር ያስተዳድር ሕብረት የማይቻል ነው የሚለው የኢጣሊያ  የፖለቲካ መርህ ነበር  ሊቀ ጳጳሱን ወደሮማ ለይግባኝ እንዲጓዙ የአደረጋቸው ገሪማ ታፈረ የወቅቱን ሁኔታ እንዲህ ነው ያሠፈሩት”ሊቀ ጳጳሱን አባ ቄርሎስን የሐበሻ ቤተ ክርስቲያን ከግብፅ የሚያስተሣስራቸውን ማሠሪያ ለመፍታትና አርነት ለማውጣት የእሽታ ፈቃዳቸውን ቢጠይቅ እንቢ ቢሉትና በፁዕ ፓትርያርኩንም አልክድ ከላካቸውም የመንፈሳዊ ልቅና አልወጣም ብለው በመመለሳቸው ነው” [xxvii]። ይላሉ ገሪማ ታፈረ ይህ አባባል የጳጳሱን ጥንካሪ እንጅ ክህደትን አያሳይም

ይህ አቤቱታ  አልሳካ ሲል ነው ሁለቱን የበላዮች ማለትም የቤተ ክርስቲያኔቱ የበላይ የሆኑትን ንጉሠ ነገሥቱንና የክህነት የበላይ የሆኑትን የግብጹን ፓትርያርክ ከመካድ ይልቅ የተሻለ አሟራጭ የሆነው  ወደላከቻቸው እናት ቤተ ክርስቲያን ወደግብጽ መሔዱ ነው[xxviii] ይህም አገራቸውንና  ጦራቸውን ጥለው ወደ አንግሊዝ ከተሰደዱት ንጉሥ የበለጠ ከህደት ነው ሊያሰኝ አይችልም[xxix]  ሆኖም ይሕ ሒደት በሕገወጥ መንገድ ስልጣን ለያዙና እንሱን ለሚደግፉ ወገኖች አንደመረጃ  አድርገው ስለ ሚጠቀሙበት በመጥፎ ጎኑ ተጽእኖ አደርጓል ይህን ሐሳብ እንደትልቅ ነጻነት አድርገው ከአሞግሱት ኢትዮጰያውያን አንዱ መምህር ገብር ዮሐንስ ገብረ ማያም የኢትይጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ክፍል ሁለት በተሰኘች ትንሽ መጻፍ ላይ ሐሰባቸውን ገልጠዋል መምህር ዮሐንስ የግብጽን ክፋት አብራርተዋል ከዚያም በኢጣልያ ቀስቃሽነት የተሾሙትን አወድሰዋል የሕገ ወጦችን ተሿሚች መሻር ግን እንዲህ ያስነብቡናል”የስራሁለት ጳጳሳት መኖር የተሟላሲኖዶስ እንዲኖር ያደርጋልታሪክ መሥመሩን ስቶ ከተመዘገበ ውድቅ የሚሆንበት አይቀርም።የአፄ ኃይለ ሥላሴ ከስደት መመለስ ተጠናክሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሲኖዶስ እንዲፈረስ አደረገ”[xxx]የመምህር  ዮሐንስ አባባል ርስበርሱ ይጋጫል በአንድ በኩል የተዛባ ታሪክ አውነት ሲመጣ ከአውነት ጋር መቆም አይችልም ይላል በሌላ በኩል የተጠናከረው የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ይላል ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን ቀኖናን ከተንኩልና ከበድል ጋር ማዛመድ የለባቸውም የምንለው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ተንኮል መታየት ያለበት በታሪክና ያም ታሪክ ራሱን ችሎ ስሕተት ይባላል ግን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መታየት ያለበት ቤተ ክርስቲያኒቱ ያከበረችው ሕግ ነው።   

መምህር ሉሌ መላኩም ከዚሁ ከዚሁ አካሐድ  አላመለጡም  የኛ ጸሐፍያን የግብጽን ቤተ ክርስቲያን ደክመትና ተንኮል ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመጣስ መግቢያ መንገድ አድርገው ተመልክተዉታል[xxxi]  በመሆኑም ሁኔታውን ለማስጨበጥ  መጠነኛ ገንዘቤ እንዲኖረን ከዚህ ላይ መጠነኛ ማብራሪያ ያስፈልጋል ሊቀ ጳጳሱ ወደ ሮማ ለይግባኝ  ሲሔዱ አቡነ አብርሃም የተባሉትን ጳጳስ ወከለው ነበር የሄዱት።

የወከሏቸው አቡነ አብርሃም የወክልናውን ቦታ ወደሊቀ ጳጳስነት ከፍ አደጉት ገሪማ ለዚህ ሐሳብም የሚሉት አላቸው “ሊቀ ጳጳሱ የሮማ ወሪ ሲጠባበቅ የሃበሻ ሊቃውንት ተሰብበስበው ወደግርማዊ የኢጣልያ መንግሥት እንደራሴ በኦክቶበር ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፯ ዓ ም የአበሻ ቤተ ክርስቲያን ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንድትለያይና በአርነት አካሐድ እንድኖር እንፈልጋለን ስለዚህ ብፁዕ ፓትርያርኩ የቀቡዋቸው አባ አብርሃም ለሐበሻ ሊቀጳጳስ ይሁኑልን አሉ ተብሎ የግርማዊ የኢጣልያ መንግሠት እንደራሴም ፈቀዱለቸው የሚል ጋዜጣ ወጥቶ ተነቧል ሲሉ  ከአዲስ አበባና ከሮማ የተላለፉት ቴሌግራሞች በዲሲምበር ሦስት ቀን ፲፱፻፴፯ ዓም አስታወቁ” [xxxii]በማለት ያስነብቡናል።

 በዚሁ መሠረት ሁኔታው በዚያም ሳያበቃ የሊቀ ጵጵስናነው መአረግ  የፓትርያርክነት ቦታ ሰጡት ገሪማ ይህ ሁኔታ በግብፁ ቆነስላ በኩል ለግብፁ ፓትርያርክ እንደተነገራቸው  አርሳቸው በሁኔታው እንዳልተሰማሙ ይገልጻሉ  አቡነ አብርሃም ግን ሳይፈቀድላቸው   ሥልጣን ይዘው የተወሰኑ ጳጳሳት ሹመው  ማገልገለል እንደ ጀመሩ በዙም ሳይቆዩ ሞቱ በሳቸው የተተኩት አቡነ ዮሐንስ ባስልዮስ ሚካል ቴዎፍሎስ ጢሞቴዎስ ያዕቆብ ይስሐቅ  ጴጥሮስ ሳዊሮስና አበርሃም የተባሉ ጳጳሳት ሹመው ቤተ ክርስቲያንን ከገብጽ የመንፈሳዊ ቀኝ አገዛዝ ነጻ ወጣች በማለት አወጁ።

ሁኖም  ነጻ ቤተ ክርስቲያን ናት በማለት አውጁ እንጅ  አዋጁ  ግን በግብጽ ቤተ ክረስቲያን መወገዝን ሲያሰከትል በኢትየጵያውያን አረበኞችም ጥሩ ስሜትን አልፈጠረም*[xxxiii] ከዚህ የተነሣ አባ ዘካርያስ የተባሉ ጳጳስ ለኢየሩሳም ተሹመው በሰደተኛው ተቀባይነት በማጣታቸው በዙ ሲጉላሉ ቀይተው ወደ አገራቸው አንደተመሰሉ መምሀር ዮሐንስ ገልጸዋል።

 ይህ በዚህ እንዳለ ነጉሠ ነገሥቱ ከስደት ተመለሱ በዚህ ጊዜ ካለይ ስማቸው የተጠቀሰው ጳጳሳት በሙሉ ተሽረው ወደ ገዳም አስተዳዳሪነት ዝቅ ብለው ሲመደቡ አንዱ ብቻ ለፖለቲካ ሲባል  ሹመታው አንዳለ ቀርቶላቸው ነበር[xxxiv] ሌሎቹ  ግን በኋላ እንደገና ጵጵስና ለሁለተኛ ጊዜ  እነደተሾሙ ይነገራል ይህ ሁሉ ከቀኖና ቤተ ክረስቲያን አንጻር ሲታይ ሰሕተትነበር በየትኛው ተውፊታዊ ቀኖና ተደጋፊነት የለውም  የሚደረገው ለፖለተካ ጥቅም ሲባል ስለሆነ የቤተ ክርስቲያናችን የሚታየው ችግር አሁንም ያን ገዜም ፖለቲከኞች ለስልጣናቸው ሲሉ የሚያደረጉት ስህተት መሆኑን መረዳት ይቻላል[xxxv]።  

  በኢጣልያ ግፊት የተሾሙትን ጳጳሳት ልዩነት ፈጥሮ አንዱን ሽሮ ሌላውን መተው ከቀኖና ቤተክርሰቲያንም ሆነ ከዜግነት አንጻር ሊወገዝ የሚገባው ነበር[xxxvi] ከዚህ ያለፈው ሕገ ወጥነት ደግሞ  የተሻሩትን ጳጳሳት ድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ የጵጵስና ሥልጣን መሰጠቱ ከሚስጥረ ክህነት እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ሲታይ  የከፋው እርምጃ ነበር  ይህ ስሕተት ከተፈጸመ በኋላ  ነጻነት ሲመለስ እንደ ንጉሠ ነገሥቱ ሁሉ ከክህነት ሹመት ቦታቸው ተሰደው ወደአገራቸው ሒደው የነበሩት ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ ወደመንበራቸው ተመልሰው  እሲኪሞቱ ደረስ ከአገለገሉ በኃላ  በመንፈሳዊ ጉባኤ ቀስቃሽነትና በንጉሠ ነገሥቱ ጥረት ቀኖና ጥሰቱ ተሰተካክሎ ቤተ ክርስቲያን ራሷን የቻለች ነጻ ቤተ ክርስቲያን ሆነች*[xxxvii]

ሆኖም ግን  የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሲወድቅ ያው የፖለቲካው ተጸዕኖ በሌሎቹ አገሮች እንደሆነው ሁሉ  በእኛም የተለመደው ችግር ተፈጠረና የቤተ ክርስቲያን ችግር ተከሰተ[xxxviii]።ዛሪ የአቡነ መርቆሬዎስን ሁኔታ ከዚህ መን ይለየዋል ነው  መሆን ካለበት ፓትርያርኩ በሕይወት እያለ ሌለ ፓትረያረክ መሾም የለበትም ከሆነ እንግዲህ በተደራቢ የተሾሙት ቅድሚያ ከሞቱ እንግዲያ ሕጋዊ ለ ነው ቀኖነው ሕጋዊነት የሚሰጠው  አሁንም መታያት የለበትሁኔታው የገለሰብ ተደደርጎ አይደለም አንደግለሰብ አይደለም የቤተ ከርስቲያኒቱን ሕልውና የማስጠበቀውን የተቋም ሕግ ነው እንጅ

በሰደት ያሉት ወገኖች በአሁኑ ጊዜ እየያቀቡት ያለው መረጃ በይበልጥ ለአዲስ አበቦቹ የኃላፊነት ከበደት እየሰጠ ይገኛል የመረጀው ፍስትም የአቡኑ መውረድ በመንግሥት ተጽእኖ መሆኑ  በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ ታምራት ላይኔ  ተረጋግጧል[xxxix]  የሚለው አባባል ሚዛን እየደፋነው እነዚህን ሁሉ ሒደቶች ስንመለከታቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ጥሰት መነሻውም መድረሻውምፖለቲካ ተእኖ  መሆኑ ታሪካዊ ሐቅ እየሆነ  ነው  ከታሪካችን እንደ ምንረዳው  የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከአገር ጋር የተያያዘ በመሆኑ አገሪቱን የሚመለከት ጉዳይ በሙሉ ቤተ ክርስቲያኒቱንም  ስለ ሚመለከት የችግሯ  ዋና መሠረትም በሀገሪቱ የሚከሰተው  የፖለቲካ ሁኔታ የበጎም የከፍም  ተጽዕኖ አለው።

ቢሆንም ሌሎቹ የዚህ ዓይነት ችግር አግጥሟቸው የነበሩ እብያተ ክርስቲያናት ችግራቸውን  የተወጡት  ከሰማይ በወረደ ተአምር ሳይሆን እውቀትን ገንዘብንና ሐሳብን  በእውነተኛ ጥናት ላይ በማዋል ነው ጥናታቸውም ዳግም በቤተ ክርስቲያን ችገር እንዳይነሳ ቤነሣም እንኳን እንዴት መቃለል እንዳለበት መፍትሔ በማስቀመጥ ነበር[xl]

 ለምሳሌ የራሻንና  የአርመኒያንን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲአናትን ስንመለከት ከፍተኛ ጥናት  በማድረጋቸው ነው  ኮሚኒስቱ መንግሥት  ሲወድቅ መልሶ እንድ ለመሆን ጊዜ ያልወሰደባቸው[xli] በእኛ ቤተ ክረስቲያንም መሆን ያለበት  ለሰደትና ለክፍፍል የበቃነው ሕጋዊ ቀኖና መጣሱ ስለሆነ  ሁሉም ጊዜውን ማጥፋት ያለበት ያን የተጣሰ ሕግ ተረባርቦ በማሰከበር ላይ ነው።

ከዚህ አውነት ላይ ሲነሣ ለአንድነቱ እስከምን መሔድ አለብን የሚለውን መሠረታዊ ጥያቂ ይዞ  የራሷን የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ አውነት መሠረት ማድረግ አለበት  እንጅ ከወጭ የራሳቸውን ፖለቲካ መሥራት አቅቷቸው በሕዝብ ከተጠሉ ፖለቲከኞች እረዳታ መፈለግ የለበትም ቀኖናው የተጣሰው የት ላይና እንዴት ነው የሚለውን በማጥናት

ይህ ስህተት ሲፈጸም የነበረው ሲኖዶስ የሠራውን  ስሕተት ማጥናትና መመርመር ነው ያለበት ከዚህ ላይም መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖረን ቀኖናዊ ማበራሪያ ያስፈልጋል ስለሆነም እንደሚከተለው አንመልከት

በወቅቱ የነበረው ሲኖዶስ በሐዋርያት ቀኖና መሠረት ከሁለት ጳጳሳት የተገኙበት ጉባኤ  የከርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን የሚወክል ሲኖዶሳዊ ምእላተ ጉባኤ ይሆናል ስለሚል ቀኖናዊነቱን በመቀበል በወቅቱ የወሰነውን ውሳኔ በመርህ ደረጃ እንቀበለው እንበል[xlii]። ማለት ትውፊታዊ ሲኖዶስ መሆን ይችላሉ የሚለው ትውፊታዊ ቀኖና የሚያሟላ ስለሆነ እንዲሲኖዶስ መቀብል አለብን  እንበልእና ሕጋዊ ነው እንበለው።የሐዋርያት ቀኖና የሚያዘውን  ትእዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ  ቀኖናዊ ነው ማለት እንችላለን።ሆኖም ግን በወቅቱ የነበረው ሲኖዶስ ቢያንስ ሦስት ትልልቅ ስሕተቶችን ሥርቷል  የመጀመሪያውያው አውነትን ክዷል  በመንግሥት ተጽእኖ  ምክንያት የሠራተኛው ደመውና የቤተ ከህነቱ የሥራ ማስኪያጃ በጀት ለማሰለቀቅ በስምምነት ሳይታመሙ ታመዋል ብለን መንግስት የያዘውን በጀት ካስለቀቅን በኋላ የፓትርየርኩ ከመንግሥት ጋር ያለውን ጉዳይ  በቀጣይ ለመመልከት የተሰወንውን  መንግሥት ያለውን ጉዳይ ለማስፈጸም ብለው አባታቸውን ክደው ምንም ዓይነት የቀኖና ድጋፍ ሳይኖር ወርደዋል ማለታቸው ክህደት ነው።

 ሁለተኛው  በደል  የቤ ከርስቲያኒቱን አባት መካድ ሲሆን ይህም  አልበቃ በሎ  ቤተ ክርስቲያን ትሠራው የነበረውን ሰብአዊ መብትን የማስጠበቅ ሥራ  የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ አባት እንደ አባት ከአለማስከበሩም በላይ  እንደ  አንድ ዜጋ ሰብአዊ መብታቸውን ማስክበር አለመቻሉ ትልቅ ክህደት ነው  ይህን የሰብኣዊ መብት ጥበቃ  የቤተ ክረስቲያን ራስ  በሆኑት    አባት ቢለማመደው ለማንኛውም ዜጋ ያደርገው  ነበር ይህ  በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ከአደጋ መጠበቅ  አለመቻል ሲሆን በሌላ በኩል ሲኖዶሱ ለሰው ልጅ መብት ሊጠበቅ  ይገባው የነበረውን ኃላፊነት የተወጣ በአለሆኑ ስሐተትም ሠርቷል በደልም በድሏል

ሦስተተኛው  ዋሽቷል ተብሎ ታምቷል ቅዱስነታቸው አለመታመማቸው እየታወቀ በውሽት  ሰብዓዊ መ መብታቸውን ገፎ ታመዋል ማለቱ የሐሰት በድል ነው  ይህ በዳይነቱም ወነወጀለኛ ያደርገዋል እንጅ የሕጋዊነት መብት ስለማይጠው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ትዕዛዝ መሠረት የሚሰጠው ብይን ሁሉ ተአማኒነት የለውም ሰውን እንደሰው ማክበር ማለትም የቅዱስ ፓትረያርኩ ጉዳይ የተወሰነው አርሳቸው በሰውነታችው ተጠይቀው የሆኑትን ተናግረው ሳይሆን አርሳቸው ያለሆኑትን ሁነዋል ተብሎ በተፈጠረ  የእረሳቸው ባልሆነ ስሕተት መሆኑ የተባለው የውሸት ቸግር    በእረሳቸው በመለጠፉ ነው።

 ይህም የውሸት በደልም ፓትርያርኩ  ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ  ሰጥተዋል በማለት የተነገረው  ነው ይኸው ወሸት ፓትርያርኩን ሐላፊነታቸውን እንዳልወጡ አደርጎ ከማሳየቱም በላይ በክደት ፓትርያኩን በመበደል ሐላፊነቱን በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ለሚገባው ሲኖዶስ  ሌላ ስሕተት ውስጥ ለመግባት መንገድ ጠራጌ ሁኖ ተመቻቸለት እንጅ አውነተኛ ሲኖዶስ ሆኖ የቤተ ክርስቲያንን እውነተኛ ችግር ፈች ነው ሊያሰብለውና እንደሲኖዶስ ሊያስቆጥረው አይችልም። የሚለውን ክስ በቅቱ የነበው ሲኖዶስ በቂ መለስ አልሰጠም ወይም የለውም 

ስለዚህ ይህ ሲኖዶስ እንደ ሕጋዊ ሲኖዶስ ሁኖ የሚሠራው ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል ስለሆነ ተቀባይነት ኖሮት በፓትርያርኩ ላይ ወሰኖኩት ያለው ሁሉ እንደ  ቅዱስ ሲኖዶስ ተቆጥሮ በውሳኒነት ሊጸድቅ አይቸልም የሚለው ሕጋዊነት ያለውን ጥያቄ ስናነስ የጉዳዩን አውነተኝነት የሚያስተባበል በቂ መለስ ማግኘት ያዳግታል።

ስለዚህ አንደኛ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሕጋዊ የፓትርያርከነት ሥላጣን በአዲስ አበባው ሲኖዶስም  ሊካድ የማይችል እውነት ሆኖ መቀረቡ አውነት ነው ይህ አውነት የማይከደበት ምክንያት  የፓትርያርኩ መውረድ በተነሣው የፖለቲካ ለውጥ እንጅ እርሳቸውን ከሥልጣን የሚያውረድ ምክንያት እስአሁን ተጨባጭ መረጃ የለም ስልጣንን ለፖለቲካ ደጋፊዎች ለመስጠት የተወሰደ አርምጃ ነው ከሚያሰኘው በቀር

ይህም ሊታወቅ በአለፈው ለሁለትኛ ጊዜ ለድርድር በቀረቡ ቅዱስ ጳትርያርኩ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠበቂ ይሁኑ  ማለታቸው   የአቡነ መርቆሬዎስን የፓትርያርክነት  መቀበላቸውን የሚያመለከትነው ይህ አንግዲህ የአዲስ አበባውወ ከመሞታቸው በፊት ነበር አሁን ሁለት የሚለው ስልሌለ   የፐትርያረትክነተቸውን ሥልጣን እስከተቀበሉ ደርስ የአስተዳደሩ ሁኔታ በምክክር የሚሆን ጉዳይ ነው  የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ የሚለው አባባል በአቶሰሶፎሎስ ቤተ ክርስቲያ መርህ መሠረት የቤተ ከርስቲያኔቱ ፓትርያርክ አስተዳደሩን የሚሠራው ሳይሆን የመንፈሳዊው የበላይ ጠባቂ የሆነው ነው[xliii]  ይህም አሁን በአለንበት ዘመን  የኦርቶዶክሱ ዓለም ፓትርያርክ የመንፈሳዊው ሥላጣን የበላይ የሆነው የአስተዳደር ስልጣን የለውም።

ያ ማለት እኛን ጨምሮ  የጥንት ቤተ ክርስቲያን አሠራር እንደዚሁ ነበር  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክረስቲያን ለአንድ ሽኸ ስድት መቶ አመት የኖረቸው የግብጹ ፓትርያርክ ያስተዳደሩን ሥራ እየሠራ አይደለም ግን የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ነበር እርሱ የሾመው ሊቀ ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስን ወክሎ ነው ማለት ነው ስለ ዚህ ስደተኛው ሲኖዶስና ፓትርያርኩ ይህን በቀኖናዊ መልክ ይዞ መቅርብና ማሳመን ነው የሚኖርው ስደተኛው ሲኖድሰም ይህን አጀንዳ  የመሟገቻ ሐሳብ ሊያቅብ ቢችል ቀኖናውን ያጠነክራን አንጅ ለአንድነቱ የሚያመጣው ጉዳት አይኖርም። ምክንያቱም ቀኖና ያልሻራቸውን ፓትርያርክ አባትነት አባት የማድረግ ሕገ ቤተ ክረስቲያን ግድ ይላልና

ለዚህ ችገር በዚህ የታሪክ ሒደት ያለፈቸው የአረመኒያን ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን ተምሳሌትን ማየት ምን አልባት ለጌዚያዊ መፍትሔነት እንደአማራጭ ማየት ይቻል ይሆናል[xliv]። ይህ ሲደረግ ግን በተራ አሉባልታ የሚነዱ ጥቅማቸውን ለማሰጠበቅ ሲሉ ቤተ ክርስቲያንን ተጠግተው የሚጎዱ በፖለቲካ የተሸፈነ ራስ ወዳድ ግለ ሰቦችና እነሱ የሚነግዱባቸው እልህ አምላኪ አባቶችን ሐሳብ ይዞ አይደለም።

ክፍፍሉ የወለደው ክፍፍል ከላይ ከፍ ተብሎ እንደተጠቀሰው በቤተ ክረስቲያን ሕግ ላይ ተመሥርቶ  ሕጋዊ ጥናት በማጥናት አንጅ ይህን መሠረታዊ ጥናት  ለማጥናትና ለቤተ ክረስቲያን ችገር መፍትሔ ለማምጣት  ግን ይህው ክፍፍል ከፍተኛ እንቅፋት ሆኖ ይታያል  አንድነቱን ለማምጣትም  የጉሮሮ አጥንት የሆነውም  በሦስተኝነት ተገልሎ ከሁሉም አይደለሁም እያለ የአስቸገረው ከፍልም አለ።ኦርቶዶክሳዊነት የሚጠይቀው መመዘኛ በስሙ ከመጠራት ያለፈ ተግባርን  ቀኖናዊ ትውፊት ማሟላትን ነው  አሁን ያለው  አካድ ግን  በሁሉም መንገድ ቀኖናዊ  አለመሆኑ መታወቅ አለበት ቀኖናዊ ካልሆነ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ ነው ማለት ያደጋታል። ኦረቶዶክሳዊነት የሚያሰኘው አንዱና የመጀመሪያው ትውፊታዊ ቆኖናን መጠበቅና ማስጥበቅ ሲቻል ብቻ ነውና የጥንት አባቶች ለዚህ ነው ይህን የሚጥስ ሲኖዶስ ያወግዘዋል የሚለውን የቆኖና ማሰሪያ ያበጁት[xlv]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ ቤተ ክርስቲያንን ችግር ከሌላው የሚለየውና ውሰብስብም የሚያደርገው ትፊታዊ  የቀኖና ድጋፍ ሳይኖረው ያለ ሕጋዊ ክህነት ውክልና በደፍረትና በክህደት ቤተ ክረስቲያን ነኝ የሚሉ ወገኖች መገኘታቸውና አንዲሁም ሐጋዊነትን ለግል ስሜትና አላማ መዋል ነው። ይህ አላማም  በተወሰነም ቢሆን በሕዝብ ተቀባይነት ማግኘቱ  ለአንደነቱ ከባድሆኖ እየታየ ነው።

ይህ የሕዝብ አለመጠርጠርና በህዝብም መጠነኛ ቅባሎት ማግኘት ደግሞ ወደፊትቤተ ክርስቲያን ከፈተኛ አደጋ ላይ መሆኗ አሁን የምናየው አካሐድ የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው ይኸውም በአንድ በኩል ቤተ ከርስቲያቀንን የመገንጠል አዝማሚያ ይታያል በሌላ በኩል  በእደግፋለሁ ባይነት  ቤተ ክርስቲያንን አውቀትም አምነትም ለሌለቸው ጨካኞች ለማስያዝ  የሚደረገውን ጥርት ለቤተ ክርስቲያናችን እደገትና ሰላም ከፍተኛ ችግር ሰጭነቱ  በትግባር እየታየ ነው።

ይህን የሚያራመዱ አባቶችም ሆነ  ምእመናን ከጥንት ቀኖና ጋር ፊትለፊት እየተጋጩ ይገኛሉ ለእለት ጥቅምና ከንቱ ውዳሴ ብሎ መእመናንን በማያሰገባቸው  የከህነት አገልግሎት ውስጥ አስገብቶ ቤተ ክርስቲያንን ማመስ የተወገዘ፤ የተጠላ፤ መጨረሻውም የማያምር ነው በቤተ ክርስቲያን ልጆችና በተለይም ትውፊትናን ቀኖን  የተረዱ ሰዎች በሦስት ክፍለ መከፈሉ  ለቢተ ክርስቲያን ከመሥራት ይልቅ የራሳን ስሚት ያማዳመጥ ሒደት  እንደ ሚካሀድ ነው የሚታመነው ነው ሦስቱም ወገኖች ማለት ሕጋዊ፤ ሕገ ወጥና ገለልተኛ  በመባል የሚታወቁት ከፍሎች ቤተ ክርስቲያንን የራስ መጠቀሚያ ለማድረግ አንዱ አንዱን በዓይነ ቁራኛ እተመለከተ በእሸቅድምድም ላይ ይገኛሉ። አሁን ግን ይብቃ ሊባሉ ይገባቸዋል ለዚህ አባቶች ቆኖናዊ አላማ ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው ለዚህ ወሳኝ ጊዜ አቡነ መርቆሬዎስም ቀላል የማይባል ለአንድነት የመሥራት ኃላፊነት ወድቆባቸዋል የእርሳቸው የአባትንት ሥልጣን የሚነሣውን ቀኖናዊ ጥያቄ  ያለስህተት መመለስ አለበት።

ሔደቱም እነዚህን ሲመለከት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ ያከበረቻቸውንኖናዊ ሒደቶች ማየትና ከቀኖና ጋር ተስማሚ መሆን ይኖርበታል  ።ለዚህ  ምሳሌ የሚሆነውን  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነጻነቷን ያገኘችበት ሒደትን ማስረጃ ማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው[xlvi] የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ነጸነቱን የገኘችው  በሕጋዊ መንገድ ቀኖናን ጠብቃ መሆኑ የታመነና ታሪካዊ እውነት ነው ከሆነ አሁን ለምን ሕግ  በሥራ ላይ አይውልም የሚለው ጥያቂ መልስ ማግኘት አለበት ማረጋገጫውም ቤተ ክርስቲያንን  የራስን መቻል ስልጣን  የአገኘቸው ትውፊታዊ ቀኖናን ተከትላና አክብራ መሆኑ ሲታወቅ ነው ይህም አውነት ከፍ ብሎ ለዚሁ በተሰጠው ቦታ ላይ መጠነኛ ገለጻ መደረጉን እናስታውሳለን።

ስለዚህ አካሐዳችን ይህንን ቀኖናዊ እውነት መሠረት ማድርግ አለበት እንጅ የኢኮኖሚ ስደተኛ ይመሰል  ከስልጣን ክፍፍል መድረስ የለበትም ጥያቂው የስልጣን ክፍፍል ጉዳይ አይደለም ጥያቂው መሠረታዊ የነገረ ቤተክርሰቲያን ሕግ ተሽሯል ነው ውጤቱ ማጠንጠን ያለበት በዚህ ዙሪያ ነው።

ገለልተኝነትም ለሰላም ምንደን ነው ለዚህ ገለልተኛና ድጋፍ ሰጭ እያለ ለሚያውከው ክወፍል የሚቀርብለት ጥያቄ ምንድን ነህ በየትኛው ቀኖና ሕግ ነው ለእንደዚህ  ዓይነት ክፍል ቤተ ክርስቲያንን የመምራት ሥልጣን የሚፈቅደው  በየትኛው ጉባኤ ነው የተወሰነው እንዲህ ዓይነቱ መብት? በተለይም “ገለልተኛ”  ምድብ ላይ ለሚገኘው ክፈል የሚጠየቀው ጥያቄ የመተጠቀሙበት ቀኖና በየተኛው ጉባኤ የተወሰነ ነው  የምትቀበሉትስ ጉባኤ የትኛው ነው  የኒቅያን ቁጥንጥንያን እንዳይባል እነዚህ ጉባኤያት የወሰኑትን ሕጋዊ የክህነት ውክልና የሚያዘውን ቀኖና  መቀበል ካልተቻለ የሚቀድሰው ቅዳሴ እንኳን እንዴት እንደሚካድ መመልከት በቂ ነው።

እነዚህን ጉባኤያት መቀበል ማለት ያስቀመጡትን ትውፊት እምነትና ሥርአት መቀብል ብቻ አይደለም[xlvii] እመነቱን ማመንና  እምነቱንም ማስጠበቅን በእምነቱ መኖርንም  የሚያካትት ኃላፊነት ነው[xlviii] በሥርአተ ቅዳሴያችን  የምንጸልየውን ጸሎት ፍትሐ ዘወልድን የሚያነብ ካህን ህጋዊ የክህነት ውክልና ወይም ከትውፊታዊ ሲኖዶስ አመራር ተለይቶ ክህነት አለኝ ብሎ መናገር እንዴት ይችላል[xlix] የጸሎቱ ምንባብ በሥሉስ ቅዱስ ከማመን ጀምሮ በነቢያትና በሐዋርያት ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን በሰብዐ ሁለቱ  አርድዕት የነአትናቴዎስ የነዮሐንስ አፈወርቅ የእነ ቄረሎስ ምስከርነት የሦስት መቶ አሥራስምንቱ  የመቶ ሐመሳው የሁለት መቶው አበው ጉባኤ የእመነት ጥበቃን ያጠቃለልው ጸሎት ተያይዞ መጥቶ የሚደመድመው አሁን በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓተርያርክነትና የክፍል ሊቀ ጳጳስ  ትተከታይነት ዘርዝሮ ከራሱ የክህነት ሥልጣን ይደርሳል።

ይህን የቅዳሴ ሥርዐት  የሚያከናውን ካህን የቁርባንን ሥርዓት ለመፈጸም ሥልጣኑ  በራስ ፈቃድና አነሳሽነት የሚወስነው ሳይሆን የቤተክረስቲያን ሐብት ነው  ስልጣኑንም መጠቀም ያለበት በቤተ ክረስቲያን ፈቃድ ነው[l] ይህን የማይቀበል ሰው በስልጣኑ ሊጠቀም ቢል እንኳን በድፍረት ከማድረግ ያለፈ እውነተኛ  እምነት ነው ብሎ ማመን አይቻልም።በዚህ መልክ የሐዋርያት ሥልጣን ቀጣይነትትን ሳይየዙ የሚቀጥሉ ክፍሎች እንዲሰነሡ ያደረገው  የቤተ ከርስቲአኔቱን መከፍል ምክንያት በማድረግ ነው ይህን ሕዝብ እንዲያውቀወ በድፍረት መናገር መመስከር ያሰፈልጋል[li]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤክርስቲያንን ችግር ይህን የጠራ ጉዳይ ለሕዝብ አለማሳወቅ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አሁን እንደ ሚታየው ሕጉን የምንገለገልበት  ለግል ክብር ይሰጠናል  የሚመስለንን ብቻ  እየመሰለ መጥቷል በስደተኛው የቅዱስ ሲኖዶስ  ይህ እያታየ መጥቷል የአሁኑ ክስተት ይህ ሳይስፋፋና ለሌላ መከፋፍል መንገድ ሳይከፍትመፋጥን ይኖርባታል በሌላው ዓለም የሚኖሩ ኦርቶደክሳውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤክርስቲያንን የሚበልጡት ቀኖናዊ ሕጉን መጠበቅና ማክበራቸው ነው[lii]

ስደት ለምን ከዚህ ላይ ሲኖዶስ አይሠደድም የሚል ከቀኖና ይልቅ ስም ማጥፋት የሚቀድማቸው ሰዎች ስለ አሉ እንዚህንም ሳናወግዝ እውነቱን ማሳወቅ  ግን  አሰፈላጌ ነው  የምናነሳው ጥያቄም ሊክዱት ከማይችሉት እውነት ላይ ነው። ሲኖዶስ አይሰደድም ለሚሉ ሰዎች  በሐሳባቸው ብንሰማማ የማያሰኬድ ነግር ግን ከፊታችን ይደቀናል ይህም  ቤተክረስቲያን ሒዳችሁ ታስቀድሳላችሁ ወይ  የሚለው ጥያቄ ነው መልሱ አዎ ከሆነ ወደ ሁለተኛው  ከባድ ጥያቄ የውስደናል ቅዳሴ የሚቀድሰው ቄስ ከየት መጣ ወደሚለው  ከኢትዮጵያ ከሆነ የት ሆኖ ቀደሰ? ከኢትዮጵ ውጭ  እንዴት ሆኖ ተሰዶ ወይ አስፈቅዶ ሁሉም  አገር ለቆ ነው መልሱ  የካህን ክህነት ውጭ አገር ከሠራ እንግዲያውስ የከህነቱ ባለቤቶች የሆኑት ጳጳሳት የጵጵስና ሥልጣናቸው  በሌላ ቃሉ ሲኖዶስ  የትም ቦታ ሆኖ ይሠራል አንላለን[liii]

የክርስትናን መስፋፋት ታሪካዊ ሒደት ማቅረብ ምን አልባትም አእምሯቸው ከእውነት ጋር ለተጋጨባቸው መልስ ይሆናል ብልን እናስባለን በታሪክ ሒደት ክረስትና ሲስፋፋ ሐዋርያት ወንጌል ሰበኪዎቸን ፓትርያርኮች ሲሰደዱ በተሰደዱበት ያመኑትን እምነት በተቀበሉት ክህነት ሲያካሒዱ ነው የኖሩት  ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ሲደርስ ያነን ቀኖና ማን ሻረው ክህነትና አምነት ቦታ ላይ ሳይሆን በሰው ላይ ነው ከፍልስጥኤም ተነሥተው መላ አውሮፓን በማካለል ወነጌልን ሲያዳርሱ ማን ነው ሐዋርያ አይሰደደም ወንጊልም ቦታ አይለቀም ብሎ ያልተቀበለ[liv] ያ ባይሆንስ ኑሮ  ክርስትና እንዴት ይሰፋፋል ብሎ ማሰብ የቻላል  ስለዚህ ሲኖዶስ ቦታ አይለቀም የሚለው አባባል  የአውነተኝነት ሚዛን አይደፋም።

ከዚህ ይልቅ የተሰደዱት ሰዎች ሕጉን በአግባቡ እየተጠቀሙበት ነውን? የሚለውን መጠየቁ ይመረጣል ሲኖዶስ አይሰደደም ከሚለው የአሉባልታ ሐሳብ ይልቅ የስደተኛው ሲኖዶስ አባልት አካሐድቸው ትክክል ነውን የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት ይህን ጥየቄም ስንመልስ ቀኖናን መሠረት አድረገን የተሳሳቱበትን የስህተት አካሓድ  እንጅ የቆሙበትን አላማ አንኮነነውም ምክንያቱም ስሕተቱ መሰደዳቸው አይደለምና ቀኖና ተጣሰ ብሎ መሰደድ ትክክለነኛና ቀኖናዊም ነው[lv] በስደት ክህነት የማይሠራ ከሆነ አባ ጳወሎስና አባ ማትያስም ጵጵስናቸው ይሠራል ተብሎ ሲያገለግሉ ነበር ያውም አባ ማትያ ተወግዘው አባ ጳውሎስም ሲኖዶስን ክደው ይህ ሲባል ግን የእነሱ ስሕተት ስለሆነ እኛም እንሳሳት እያልን መሆን የለበትም የእነሱ ስሕተት ድፍረት ነው  ክህደታቸው ነው

ስለዚህ   ክፍል የውይይቱን አቅጣጫ ማየት ያለበት መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ጥሰትተካሕደው የፖለተካ ተጸኖ ቢሆንም የዞ የተነሣው ግን የቀኖና ጥሰት  ዓላማ ይዞ ከሆነ  በዚሁ ዓላማ ላይ የተመሠረተ የውይይት መድርክ መክፍት ነው[lvi] ይህ የውይይት መደርክ ብቻ አይደለም መሆን ያለበት  የወደፊት የቤተ ክርስቲያንን እድልም ወሳኝነት ያለው መሆኑን ጥብቅ ትኩረት  ያስፈልገዋል ምክንያቱም ይህ ሁኔታ ካልተሰተካከለ የፖለቲካ ነጻነት እንኳን ቢመጣ  የጠራ ቀኖናዊ ዓላማ አይኖርም  ይህን አደራ ካልተወጣ ሕጋዊ ነኝ ማለቱ ብቻውን ሕግ ሊሆን አይቸልም ሕጋዊ መሆን ትልቁ እድል በልበ ሙሉነት መሠራት ማስቻሉ ነው የሕገ ወጥነት ችግር ደግሞ የተጣሰው ሕግ አላሠራ ስለሚል  ያለሕግ በመመራት ከሚያለማው ይልቅ የሚያጠፋው በልጦ መገኘቱ ነው።

ስለ ዚህ ድርድሩ በሦስት ረደፍ ያሉትን ቡድኖች አንድ የሚያዸረግ ሁሉም ደግሞ ሕገ ቤተ ክረስቲያንን የተከተለ መሆን ይኖርበታል በተለይ ሕጋዊ ነኝ የሚለው ክፍል በዚህ ተመርኮዞ ካልሠራ መውደቂያ ቀዳደው ብዙ ነው ምክንያቱም በሁለቱም ያሉት ክፍሎች  የሚገፉት ይህንኑ ነው ሆኖም ግን አሁን እንደምናው በዚህ በኩል ያሉ ከስልጣን ውጭ ህልም በሌላቸው በሕዝብ ዘንድ የተተፉ ክሱራን ፖለቲከኞች የሚገፉ አባቶች ይህን የተረዱ አይመስልም[lvii]

አንድነቱ መታየት  ያለበት ከግል ሥልጣንና ከእለት ጥቅም ያለፈ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና የሚዳስስና ዳግም በቤተ ክርስቲያን ችግር እንዳያስነሣ መሠረት የጣለ መሆን ይኖረበታል[lviii] ለራስ ስሜት ከተስማማ የቤተ ክረስቲያን ጉዳይ  የተሟላ የሚመስላቸው ግለሰቦች የሰላሙን ሒደት ከእነሱ ስሜት ጋር ማያያዝ የለባቸም ክፍ ብሎ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለተሰጠው ክፍል ላይ በተገቤው መልኩ እንደተገለጠው የነአትናቴዎስ የነዮሐንስ አፈውርቅ የነ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ስደትና መንገላት ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል[lix] የእነሱ ስደት ቤተ ክርስቲያን  በእመነቷና በሥረአቷ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ጥንካሬዋ ከፍተኛ  ቦታ እንዳለው ከማሳየቱም በላይ ቤተ ክርስቲያን በጠላቶቿና  ላይ የበላይነት እንዲኖራትና በምላትና በጥብአት በአሸናፊነት አልፋ እንድትታይ አድረጓታል።

አንድነቷንም አጠናከሯል አሁን እኛ ለመረጃ የምናቀርበው ቀኖናዊ ሰነድም የነዚያ አባቶች  የስደትና የመከራ ውጤት ነው ይህንን ካላስከበርን ግን የአባቶቻችን አደራ አልተወጣንም ማለት ስለሚሆን ተጠያቂነታችን በአለፈውም በአሁኑም ትውልድ ይሆናል  ከዚህ ለመዳን የውይይቱ አቅጣጫ  ምን መሆን እንዳለበት ስለ ውይይቱ  ሒደትና ጠቋሚ ሐሳቦችን በሚለው ነጥብላይ  በቀጣዩ  ምናባብ አንገናኝ እስከዚያው ችር ይግጠመን
ቀስቶ ወተረ (ከቀስቶ ወተረ አትላንታ ጆርጂያ/ qesto1010@gmail.com/):-  
[i]Timothy D. Barnes,Athanasius and Constantiud theology and politics in the constantian Empire,19-32
[ii] Ibid J.stevenson, Creeds, councils and controversies Documents illustratimg the hitoryof the chuch AD337-461,1-42.hohn Meyendorff Imperial Unity and Christian Divisions,39.
[iii] Creeds, councils and controversies Documents illustratimg the hitoryof the chuch
[iv] Steven Ozment, The Age of Refotm 1250-1550 in intellectual and religious history of late medeivla and reformation Europe, 135-175.
[v] Dimitry Pospielovsky,the  orthodox Church in the history of Russia,15-35.Neicolas Zernvo,the Russians  and their Ccurch  frome,18-114 በዚህ መጽሐፍ የሩሲያንን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክን አሟልቶ የያዘ ስለሆነ ስለ ቤተከርስቲያኒቱ  መሠረታዊ አውቀት ለማቅ የሚፈልግ ሰው እንዲያነበው ነው ለመረጃነት የቀረበው
[vi]Eastern Chrianiny and politics in the twentieth Cenry, Edited by  pedro Ramet,61-135 ይህ ክፍል ጠቅላላ ቤተ ከርስቲያኒቱን በአጭር መልክ የሚያሳይ  የጥናታዊ ጽሑፍ ሰብስበ መጽሐፍ ነው በዚሁ መጽሐፍ የጠቅላላው በኮሚኒስት ሥር ያሉ ኦርቶዶክሳዉያን ተሪክ ባጫር ባጭሩ  ተገልጾዋል
[vii] Erockson, the challinge of our past 97.
[viii]John Meyendorff, Vision of unity,74-75.
[ix] Erockson Orthodox Christians in America,85-108
[x]  የማይገለጥ የተከደነ የለም  ሕጋዊው  ቅዱስ ሲኖዶስ  ለሕገ ወጡ የወያኔ ሲኖዶስ የተሰጠ መልስ  በሚል የጠዘጋጀ መጽሐፍበመጀመሪያው ክፍል ከገጽ 10-30 በዚህ ዙሪያ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠቷል
[xi] Erockson Orthodox Christians in America,94-108
[xii] Olvier Clement,Conversation with Ecumenical Patriarch Bartholomew I, Tr frome the French by paul meyendorff,21-54
[xiii] Steven Ozment The Age of Refotm 1250-1550 in intellectual and religious history of late medeivla and reformation Europe,157.

[xiv] Hans Kung, Christianity Essence, History, and Future, 461.
[xv] Ibid Steven Ozment, 175.
[xvi] Steven Ozment, 155.
[xvii] Hans Kung, 467. Steven Ozmen,159
[xviii] Erickson, the Challengine of our past,110.Orthodox Christian in Ammerica,89.

[xix]Armenian Apostolic Church, Armenian Church, Holy See of Cilicia, The Armenian Apostolic Orthodox Church

[xx] Arch BISHOP Trian Nersoyan Armenian church Historical studies matters of Doctrine and Admininstration,177.
[xxi]አባጎርጎኢረዮስ ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መቅድሙን ይመልከቱ
[xxii]  ገሪማ ታፈረ ጎንደሬ በጋሻው ገጽ83-84
[xxiii] ጎደሪ በጋሻው ገጽ 93-100 በዚህ መጽሐፍ ከኢጣልያ መንግሥት ጋር የተያያዘ በአለሰላሳ ስድት አንቀጽ የቤተ ከርስቲአን ደንብ ወጥቶ በሥራ ላይ ውሎ ነበር 
[xxiv] የኢትዮጵያ ኦረቶዶ ቤተ ክርሰቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት
[xxv] ሉሌ መላኩ የቤተ ከርስቲያን ታሪክ ገጽ 137
[xxvi] ሉሊ መላኩ የኢትዮጵያ የቤተ ከ ታሪክ ገጽ 170
[xxvii] ገሪማ ታፈረ  ጎነደሬ በጋሻው ገጽ 89
[xxviii] ሉሊ መላኩ የኢትዮጵያ የቤተ ከ ታሪክ ገጽ 173
[xxix] ሉሌ መላኩ የቤተ ከርስቲያነ ታሪክ 136።
[xxx]  ገብረ፡ዮሐንስ ገበረ ማርያም የኢኢዮጵያ ቤተ ክረስረቲያን ታሪክ  ገጽ 82
[xxxi] ሉሊ መላኩ የኢትዮጵያ የቤተ ከ ታሪክ ገጽ172
[xxxii]  ገሪማ ታፈረ ጎነደሬ በጋሻው 89።
*በገሪማ ታፈረ የበተዘገጀው  ጎንደሬ በጋሻው የሚለው መጸሐፍ ላይ ሁለተኛ የሊቀ ጵጵስና ሹመት የተሾሙት አቡነ  ዮሐንስ ሲሾሙ አብወሮ የቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብም የወጣ መሀኑን የሚገልጸው በዚሁ ጊዜ ነውሕጉ በአዋጅ ከወጣ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ በፊርማ አረጋግጠው ለጳጳሳቱና ለካህናቱ የማጽደቂያ ድበዳቤ ጽፈዋል ገጽ 102
[xxxiv] ሉሌ መላኩ የቤተ ክርስቲአን ታሪክ 138።
[xxxv] ሉሌ መላኩ የኢትዮጵያ ክርስቲአን ታሪክ 173
[xxxvi] ገብረ፡ዮሐንስ ገበረ ማርያም የኢኢዮጵያ ቤተ ክረስረቲያን ታሪክ  ገጽ 84
[xxxvii]ይህን ታሪክ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ  የጻ ፉ ሁሉ አስፈረውታል ገብረ ዮሐንስ  የኢትዮጵያ ቤተ ከርስቲያን ታሪክ ገጽ 80-85 ሉሌ መላኩ የኢትየጵያ ቤተ ከርስቲያ ኦርቶዶክስ  ተወህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ173-174አባ ጎርጎርዮ የሽዋ ሊቀጳጳስ  የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያ ታሪክ ገጽ 80-882
[xxxviii] Erickson Orthodox Christians in America  A short  History ,5-9
[xxxix] የአቶ ታማርት ለይኔን መለስ ስንድ በመጽሐፉ መጭረሻ በሚቀመጠው መረጃ ይመልከቱ
[xl]Meyendorff, Vision of unity, 98.
[xli]Amrmenian Church Historical studies,Matter  Doctrine and Adminstration,231-300 በዚህ መጽሐፍ የአርመን ኦርቶዶክስ አስተዳደራዊ ችግር የተገለጠ ሲሆን አምዴት ያን ሁሉ ችገር እንዳለፉትም ጠቋሚ ሐሳብ ይሰጣል ለዚህ ነው በመጽሐፉ ሰፊ ክፍል የተሰጠውም  
[xlii]The Apostolic Canon canon II
[xliii] John Meyendorff ,Voisin of unity.101
[xliv] Amrmenian Church Historical studies,Matter  Doctrine and Adminstration,231-300
[xlv] ፍትህ መንፍሳዊ አነቀጽ አራት ቁጥር  አርባአ ሁለት
[xlvi] የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክረስቲያን እመነትና ሥረዐት ራስን የመቻልታሪክ ከፍል አንድና ሁለት
[xlvii]  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲአን ቅዳሴ  ፍትሐ ዘወልድ
[xlviii]  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ የእመነት መግለጫ
[xlix]  ፍትህ መንፍሳዊ አንቀጽ አንድ
[l] አንቀጽ ስድት  ሁለት መቶሃያ ሰባት ፍትህ መንፈሳዊ ገጽ 75
[li]Adolf Von Harnack John Owen  Sourcs of the  Apostolic Canons.29-35
[lii]John  H Erickson the challenge of  Our Past.73-74
[liii]  Creeds/councils and controversies.5-8
[liv] Barnes, Athanasius and constantius .87
[lv] ፍትህ መንፍሳዊ
[lvi]ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አራት ገጽ 35 ቀጥር 70
[lvii]  ለምሳሌ ድጋፍ ስጭ ኮሚቴን መመለክት ይቻለል
[lviii]Creeds/councils and controversies.5-8
[lix] Ibid and barnaes, Athanasius and constanntius.94-99

5 comments:

Anonymous said...

Excellent analysis, but difficult to read since it is full of typo errors.
Please, take this article off and first fix all those spelling errors.

Anonymous said...

ወይ ጉድ በቀባጣሪዎች የቆሰለች ነፍሴን አጥንት በሚያለመልም እውነት እንዴት አድርገው ፈዎሷት፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ፡፡ ይህ ብዕር ደጀ ሰላሞችንም ሳይቆጠቁጣቸው አይቀርም ችለውት ነው እንጅ፡፡ በእርግድ ሁሉንም የምንችልበት ከራስ ፍላጎት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም የምናስቀድምበት ጊዜ ነው፡፡ ይገባል፡፡ ገለልተኞች የት ጠፋችሁ ከሚሉ አድማ ጠሪዎች ይሰውረን፡፡ ከቅን ልቦና በሚፈልቁ ሀሳቦች እየተማርን በየአካባቢያችን የምዕመናን የውይይት መድረክ ማዘጋጀት ይገባናል፡፡ አምላከ ቅዱሳን አንድነታችን ይመልስልን፡፡ አሜን፡፡

Anonymous said...


The kind of unbiased article I expect to read on Deje Selam.

Kebede Bogale said...

በይዘቱ በጣም ጥሩ ሐሳብ ያለው ጽሑፍ ነው። በቅርጽ ደረጃ ግን አረፍተ ነገሮቹ ያለ ልጓም ፥ ማለት ያለ አራት ነጥብ ዝም ብለው ያለ ማሰሪያ አንቀጽ ስለሚጋልቡ ትንሽ የጽሑፉን ውበት አሳጥቶታል። በጣምም ባይረዝም ጥሩ ነበር። ዋናው መልክት ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ችግር ላይ እንደወደቀችና በነማን ጣልቃ ገብነት ቀኖናዋ እንደተጣሰ በቂ መረጃዎችን ጸሓፊው አቅርበዋል ፣ መፍትሔውንም ጠቁመዋል። በተለይ ''ገለልተኞች ነን ''ስልሚሉትና ''ሲኖዶስ አይስደድም'' ስለሚሉት ወገኖች የሰጡት ትችት እኔን አርክቶኛል። ...ሌላው ነገር ገን ከስደተኞቹ አባቶች ስለጉዳይ ምንም የምንሰማው ነገር ስለሌለ ስለሁኔታው ያላቸውን አቋም ለማወቅ ብዙዎቻችን ተቸግረናልና ምን ላይ እንዳሉ ቢያሳውቁን መልካም ነው ብየ አምናለሁ። እስቲ ለሁሉም ሁሉን ማድረግ ለሚችለው፥ የሁላችን ፈጣሪና አምላክ ለሆነው በግልም ሆነ በማኅበር ሁነን ተግተን እንጸልይ። ዛሬ ያጣነው አብርሓሞችን ነው እንጅ የአብርሐም አምላክማ የፍጥረቱ ሁሉ አምላክ ሰለሆነ ትላንት በነአብርሐም ዘመን እንደነበረው ዛሬም አለ ፥ ወደፊትም ዓለሙን ሁሉ አሳልፎ ለዘለዓለም ይኖራልና፥ አብርሐምን ሁነን ከተገኝን ለጸሎታችን አፋጣኝ መልስ ይሠጠናል። የተጣላነው እንታረቃለን ። የተለያየነው አንድ እንሆናለን ። የተሰደድነው ወደቅድስት አገራችን እንመለሳለን። በአሓቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፥ በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክና በአንድ ቅዱስ ሲኖዲስ መንፈሳዊ አመራር ሥር ሆነን አንድ አምላክን እናመልካለን። ስለዚህ አይሆንም ማለትን ትተን በእምነት ይሆናል ብለን ለመፍትሄ እንነሳ !

Anonymous said...

የቤተ ክርስቲያኗን እምንትና ቀኖና ለሚያውቁ (ወይም ሊያውቁ ለሚገባቸው) ካህናት፣ ምሁራንና ምእመናን ይህ ሐረግ መዝዞ ሁኔታውን በዝርዝር የሚያስረዳ ጽሑፍ ራስን በጽሞና ለመመርመርና ትክክለኛውን መንግድ ለመያዝ የሚረዳ ብዙ ቁም ነገር ያዘለ ሰነድ ነው። ከባዱ ችግር እውነቱን ባለማውቅ ወይም የሚማሩበት መድረክ በማጣት፣ በስሜት እየተነሳሱ የእገሌ ወገን ነኝ፤ የእገሌ ተቃዋሚ ነኝ ወይም ገለልተኛ ነኝ የሚሉት ምእመናን ቁጥር እያደገ፣ ጊዜውም እየረዘመ በመሄዱ የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት ከባድ አደጋ ላይ መውደቁ እሙን ነው። ስለዚህ አሁን የቀረበውንና ሌሎችንም ገንቢ ሰነዶች መነሻ በማድረግ አንኳር የሆኑት ሀሳቦች በማይከበድ አጻጻፍ/አነጋገር በኢትዮጵያ በተለይም በውጭው ዓለም ላሉት የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች በመገናኛ ብዙሐን (በራዶዮና በቲቭ ጭምር)ቶሎ ቢሰራጩ በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑም ትምህርት ቢሰጥባቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ እውነቱን ይበልጥ ተረድቶ አስተማማኝ የመፍትሔው አካል ሊሆን ይችላል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)