September 6, 2012

ጥቂት ማብራሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስላወጀው የምሕላ ጸሎት


(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 1/2004 ዓ.ም፤ September 6/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ደጋግመን እንደዘገብነው እና ቀጥሎም ሙሉ ደብዳቤውን እንዳስነበብነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሁለት ሱባኤ ማለትም የ14 ቀናት የጸሎት አዋጅ አውጇል። ይሁን እንጂ “ሱባኤ” የሚለው ቃል የተለያየ ትርጉም ያለው ከመሆኑ አንጻር ፣በርግጥ የራሱን አዋጅ የማብራራት ሕጋዊ መብት ያለው አዋጁን ያወጣው አካል ቢሆንም፣ የደብዳቤውን እና የአዋጁን መንፈስ ማብራራቱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።


መግለጫው የሚለው “ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተናዊ ዕድገት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት (ፓትርያርክ) ለቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙት አህጉረ ስብከት፣ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ከጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል” ነው። ስለዚህ የታዘዘው በተሰበረ ልቡና፣ በሰቂለ ኅሊና ሆነን ጸሎታችንን ወደ አምላካችን እንድናደርስ ነው። መጪው አዲስ ዓመት እና ተያያዥ በዓላት መሆናቸው ግልጽ ከመሆኑ ጋር አንዳንድ ደጀ ሰላማውያን እንደጠየቃችሁን “በዓሉን በጾም እንድናሳልፍ” የሚጠይቅ ውሳኔ ሳይሆን ለዚሁ ታላቅ ጉዳይ ብቻ በአንድ መንፈስ ጸሎታችንን እንድናደረግ ብቻ ነው።

በዚህ የጸሎተ ምሕላ ሱባኤ ልዑል እግዚአብሔር ለአገራችን ኢትዮጵያ የሚበጃትን ርእሰ መንግሥት እንዲሰጣት፣ ለቤተ ክርስቲያናችንም አንድነቷን እንዲመልስና ለመንጋው የሚራራ ደገኛ ርእሰ አበው እንዲሰጣት ጸሎት ይደረጋል፡፡ በሊቁ አለቃ አያሌው አገላለጽ “ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የማትለይ÷ መቃድ ያልነካት፣ ስፌት ያልዞረባት የክርስቶስ ሥረ ወጥ ልብሱና መቅደሱ” ናትና ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በያሉበት በዚህ የሁለት ሳምንት የጸሎተ ምሕላ ሱባኤ  ስለውዲቱ አገራቸውና ስለ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው መንፈሳቸውን ያስተባብራሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡

በአገር ውስጥ ከገዳማቱ ጀምሮ እስከ አድባራቱ ድረስ ከምእመኖቻቸው ጋር ምሕላውን እንደሚያደርጉ ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም በውጪው ዓለም በተለያየ ዓይነት ኑሮው ውስጥ ያሉ ምእመናን በአካባቢያቸው አብያተ ክርስቲያናት ካሉ በየአብያተ ክርስቲያናቱ፣ ከሌሎ ደግሞ በግላቸውም ሆነ በጋራ በመሰባሰብ ይህንን የጸሎት ግዳጅ ሊፈጽሙ ይገባቸዋል ብለን እናምናለን። ከዚህ በፊት “ቅዱስ ፓትርያርኩን አንቀበልም፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ግን እንቀበላለን” የሚሉትና በተለምዶ ገለልተኛ የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት በዚህ በኩል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። 

በዚህ መግለጫው ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን ለረዥም ጊዜ ሲያነሡት የነበረውን ትልቁን ጥያቄ መልሷል። ይኸውም ችግር በመጣ ጊዜ “ኧረ ጸሎት እናድርግ፣ ጸሎተ ምሕላ ይታወጅ” ለሚሉት ምላሹን ሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያናችን በአዲስ ጎዳና ላይ መገኘቷንም አመላክቷል። ለችግሮቻችን አማናዊውን ምላሽ የምናገኘው ከአምላካችን መሆኑን በአንድ ልብ ተቀብለን ወደ እርሱ እንድንጸልይ የሚመራ እና የሚያተጋ ሆኗል። ለዚህም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶቻችንን ከልባችን ልናመሰግናቸው እና “አይዟችሁ እኛም ከእናንተው ጋር ነን፣ በአቅማችን ለመርዳት ዝግጁዎች ነን፣ መመሪያችሁን ተቀብለን እናስፈጽማለን” እንላቸዋለን። እግዚአብሔር ይርዳን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡


15 comments:

አልፎ አይቼው said...

አይዟችሁ እኛም ከእናንተው ጋር ነን፣ በአቅማችን ለመርዳት ዝግጁዎች ነን፣ መመሪያችሁን ተቀብለን እናስፈጽማለን። አምላካችን የለመንነውን ሰጥቶናልና።

Anonymous said...

“ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የማትለይ÷ መቃድ ያልነካት፣ ስፌት ያልዞረባት የክርስቶስ ሥረ ወጥ ልብሱና መቅደሱ” ናትና

Anonymous said...

atelayane AMELAKACHEN

ተስፋ ዘኢትዮጵያ said...

እግዚአብሔር ይመስገን

አቤቱ ጌታ ሆይ

ያልከውን ቃል ልታደርስል እንደሆነ እና የተባለው ትንቢታዊ ቃል እነሆ መጀመሩ ይሆን?

አባቶች ሆይ!
በርቱልን ለተኩላ አሳልፋችሁ እንዳትሰጡን! እኛም ከእናንተ ጋር ነን

ቸር ወሬ ያሰማን፣ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ጠላቶች ማስወገድ እንደጀመረ ይጨርስልን!

ሰላም አዲስ ዓመት ያምጣልን፣ ደጉን የአገር መሪ እና የቤተክርስቲያን አባት ይስጠን፣ ሁላችንንም ያበርታን፣

አሜን!

Anonymous said...

አይዟችሁ እኛም ከእናንተው ጋር ነን፣ በአቅማችን ለመርዳት ዝግጁዎች ነን፣ መመሪያችሁን ተቀብለን እናስፈጽማለን። አምላካችን የለመንነውን ሰጥቶናልና

Anonymous said...

I am attending in one of the Geleletegna church and they already start 2 ro 3 weeks ago having mehela during their Qidase.
Bezawu meqetelem newu.

Anonymous said...

Deje Selam Bertu Melkam Neger Astemiru Hulachihum Yehayimanot sewoch Mehonachihun Awkalehu
Bezih Gize Mahibere Kidusanm Mebertat alebet Melkam abat lebete kirsityanachin endiseten Ketechale Abune Merkorewos Bigebu -Kalhone Gash Taye Yetebalut Memihir Bimeretu-weyim Kegedam sew Bifeleg

Anonymous said...

Dear Deje-Selam,

What would be a highly significant and useful contribution from you would be to present an in dpeth report about the issue as to whether Abune Merqorios, the current "legal" EOTC Patriarch is entitled to such a claim or not in accordance with the church's bylaws, especially the one issued in 1991 EC. I do hope that you will not be fearful to address this timely and important subject!

ከካርቱም ሱዳን said...

ጸሎተ ምህላው መታወጁ በጣም ጥሩ ነው፡፡ አሁን የማስተላልፈው መልእክት በጐረቤት አገር ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መረጃውን ካለማግኘት ይመስለኛል በቤተ ክርስቲያኑ ጸሎቱ አልተጀመረም እና ውድ ደጀሰላሞች እባካችሁ ደብዳቤውን ፋክስ ማድረግ ስለሚቻል መልእክቱ እንዲተላለፍ ብታደርጉልን፡፡ እናመሰግናለን፡፡

Anonymous said...

Ewnet new:: debdabew lehulu betekristian kethiopia wich yalu betechristian bicha sayhone ethiopia wistm yalu betechristian medaresun eterateralhu mikniyatum, ethiopia wist yalu guadegoche enkuan tselot metawejun alawekumena zaren altseleyum silezih lehulum mimenan beteleyaye megenagna mesaria bemetekem meliktun betekihnetu madares alebet elalehu:: Egziabher yirdan.

Anonymous said...

እግዚአብሔር በተክርስቲያንን አስባት

Anonymous said...

እግዚአብሔር ሆይ ቤተክርስቲያንን አስባት

Anonymous said...

መልካም ጅምር ነው፥፥ አባቶቻችንም ከኣሁን በውሁኣላ ማንም ባለ ጠብ መንጃ ወይም ማንም በፈለገው ተመክቶ ቢመጣ በአምላካቸን ፍጹም ተማምነው የቤተክርስትያንን ጥቅም ኣሳልፈው ላለመስጠት የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረስ ኣለባቸው፥፥ እስከሞት የታመንክ ሁን

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያኗ በአባቶች ተከፋፍላ ባለችበት ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያሉት አባቶች ባልታረቁበት ሁኔታ ስለተተኪ ፓትርያርክ መጸለይ ምን ትርጉም አለው? ቃሉ፣«እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ። አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤ እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።»

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያኗ በአባቶች ተከፋፍላ ባለችበት ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያሉት አባቶች ባልታረቁበት ሁኔታ ስለተተኪ ፓትርያርክ መጸለይ ምን ትርጉም አለው? ቃሉ፣«እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ። አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤ እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።»

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)