September 3, 2012

ስንክሳርንና ግብረ ሕማማትን ወደ አማርኛ የተረጎሙት ሊቅ ዐረፉ


(MKWebsiteነሐሴ 28/2004 ዓ.ም/ August 3/2012/ በእንዳለ ደምስስ/ PDF):- ስንክሳርንና ግብረ ሕማማትን እንዲሁም ሌሎችን መጻሕፍት ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙት ታላቁ የመጻሕፍት ሊቅ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. በሞተ ስጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በአርሲ ክፍለ ሀገር በጢዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ጨቢ አቦ በተባለ አካባቢ ከአባታቸው መምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተ ሩፋኤል ብስራት ነሐሴ 16 ቀን 1915 ዓ. ም. ተወለዱ፡፡

ከአባታቸው ከመምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ ንባብ፤ ውዳሴ ማርያም ንባብና ዜማ ፤መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ዲቁና በመማር ለስልጣነ ክህነት ከበቁ በኋላ በአካባቢያቸው በሚገኘው ዱግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ገና በለጋ እድሜያቸው ትምህርትን ፍለጋ ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር ላስታ ገረገራ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመሔድ ከመምህር ሰይፉ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጓሜ ፤ ከሌሎችም ታዋቂ መምህራን ድጓንና ጾመ ድጓን ተምረዋል፡፡ ወደ ጎንደር በማቅናት ዙር አምባ ገዳም ከታላቁ መምህር ቀለመወርቅ ዝማሬ መዋሥዕት በመማር አጠናቀዋል፡፡ ወደ ደብረ ታቦር በመሔድም የተክሌ አቋቋም ሊቅ ከሆኑት መምህር ቀለመወርቅ ዘንድ ገብተው አስመስክረዋል፡፡ ጎንደር አደባባይ ኢየሱስ ከታዋቂው የቅኔ መምህር በቅጽል ስማቸው የቅኔው ማዕበል መምህር ፈንቴ ቅኔ አስመስክረዋል፡፡ በዋሸራ ከሚገኙት የቅዳሴ መምህር አባ አላምረው ዘንድ የደብረ ዓባይ የመዝገብ ቅዳሴ ተምረዋል፡፡ ሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ደግሞ  ከመልአከ ገነት ጥሩነህ ለተማሪዎቻቸው ዝማሬ መዋሥዕትን እያስቀጸሉ  ከእሳቸው የአቋቋም ስልቶችን በሚገባ አጣርተው ለማስመስከር በቅተዋል፡፡

ወደ መምህርነት ከገቡ በኋላ ብዛት ያላቸው ደቀመዛሙርትን ያፈሩ ሲሆን የተክሌ የአቋቋም በቀላሉ ለመማር የሚያስችል ምልክት ፈጥረው ለደቀ መዛሙርቶቻቸው አስተምረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን፤ በታእካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤ በደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ፤ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያናት እየተዘዋወሩ በርካታ ደቀመዛሙርትን አፍርተዋል፡፡

ወደ ትውልድ ሀገራቸው አሰላ በመመለስም በአሰላ መንበረ ጵጵስና ደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሪ ጌትነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፤ ከ1971 ዓ.ም.  እስከ 1998 ዓ.ም. በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡

በጎንደርና ጎጃም የትምህርትና የመምህርነት ዘመናቸው ላበረከቱት አገልግሎት ከደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅሎ ከነኮርቻው ተሸልመዋል፡፡

ባበረከቱት ፍጹም ቅንነት የተሞላበት አገልግሎታቸው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከቀድሞው ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቀሚስና ጥንግ ድርብ ከነካባው አልብሰዋቸው፤ የእጅ የወርቅ መስቀል በመሸለም ሊቀ መዘምራን የሚል የክብር ስምም ሰጥተዋቸዋል፡፡

መጻሕፍትን በማንበብና በመተርጎም ለቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ውለታ የዋሉ አባት ሲሆኑ የዓመቱን መጽሐፈ ስንክሳር ከግእዝ ወደ አማርኛ ለመተርጎም ሰባት ዓመታትን ፈጅቶባቸው አስመራ ለሕትመት በተላከበት ወቅት ጠፍቷል፡፡ ተስፋ ሳይቆርጡ በድጋሚ በሁለት ዓመታት ውስጥ በድጋሚ ተርጉመው ለሕትመት አብቅተዋል፡፡ እንዲሁም ግብረ ሕማማትንና ገድለ ዜና ማርቆስን ከግእዝ ወደ አማርኛ በመተርጎም ለሕትመት አብቅተው ቤተ ክርስቲያን እየተጠቀመችባቸው ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ገድለ ሓዋርያት፤ ተአምረ ኢየሱስ፤ ገድለ ቂርቆስ ፤ ገድለ ነአኩቶ ለአብ ፤ ገድለ ሊባኖስ፤ ገድለ ማርያም መግደላዊት፤ ድርሳነ ሐና ፤ ገድለ ዮሐንስ መጥምቅና ሌሎችም በርካታ መጻሕፍት ከግእዝ ወደ አማርኛ በመተርጎም ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡

ሊቀ መዘምራን ላዕከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በአንድ ወቅት መጻሕፍትን ለመተርጎም የተነሳሱበትን ምክንያት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ "በመኪና አደጋ እግሬ ተሰብሮ በነበረበት ወቅት ቁጭ ከምል ለምን መጻሕፍትን አልተረጉምም በሚል እግዚአብሔር አሳስቦኝ ተነሳሳሁ፡፡ ስንክሳርንና ሌሎችን አሥራ ሦስት መጻሕፍትን የተረጎምኩት ያኔ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ ችሮታ ነው ያደረገልኝ፡፡ እግሬ ባይሰበር ኖሮ እነዚህን መጻሕፍት መተርጎም አልችልም ነበር፡፡ እግዚአብሔር የጎዳ መስሎ ይጠቅማል፡፡ የእግሬ መሰበር ትልቅ ጥቅም ለኔም ለቤተ ክርስቲያንም አስገኝቶልኛል፡፡" ብለው ነበር፡፡

በቅርቡም በጠና ታመው ሕመማቸው ፋታ በሰጣቸው ስዓት ለደብረ ሊባኖስ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ይተረጉሙት የነበረው ዜና ሥላሴ የተሰኘው መጽሐፍ አብዛኛውን ክፍል ተርጉመው ያገባደዱት ሲሆን ሳይፈጽሙት ሞት ቀድሟቸዋል፡፡

በእርግና ምክንያት ጡረታ ከወጡ በኋላ ለቤተ ክርስቲያን ባበረከቱት ከፍተኛ ትጋትና አገልግሎት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሙሉ ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው አድርገዋል፡፡

ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በ1946 ዓ.ም. ከወ/ሮ ምሕረት በትዕዛዙ ጋር በስርዓተ ተክሊል ጋብቻ የፈጸሙ ሲሆን ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆችን አፍርተው ሠላሳ አንድ የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል፡፡ ዝግጅት ክፍላችን ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመድ ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡


Share

25 comments:

Anonymous said...

bereketachew yideribin!

Anonymous said...

Selam Alemu
sirachew hiyaw new...............nefisachewin begent yanurileine
7 minutes ago · Like

Blake Ayana
Nefs yimarilin
7 minutes ago via mobile · Like

Fekadu Woldesenbet
መንግስቱን ያውርስልን
5 minutes ago · Like

Ezra Woldetsadik

Rest in peace.
5 minutes ago · Like

Miki Mehari
Nefsachewen begent yanurelen.AMEN AMEN AMEN!!!

Anonymous said...

berketachwen ye
derben

Anonymous said...

ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያምን በአካል አገልግሎታቸውን በሚገባ አውቀዋለሁ:: በተለይ ማህሌት ሲቆሙ የመላእክትን ዝማሬ እንጂ ከሰው አንደበት የሚወጣ ዝማሬን የምንሰማ አይመስልም:: ማህሌት ላይ አንድ ጊዜ እንኳን እረፍት ሳያረጉ አድረው ቅዳሴውንም እንደዛው እንደቆሙ ነበር የሚፈጽሙት:: በጣም ደግሞ የማይረሳኝ ከልጅነቴ ጀምሮ የማስታውሰው በአመት አንድ ጊዜ አስተርእዮ ማርያምን ዝዋይ ደብረጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም ነበር የሚያሳልፉትና: እሳቸው መጡ ከተባለ የአካባቢው ሰው በሚገባ ስለሚያውቃቸው ከዋዜማው ጀምሮ ከማህሌታቸው ለመሳተፍ ቃለ እግዚአብሔሩን (ግእዙን) የሚያውቀውም የማያውቀውም ወደ ቤተክርስቲያን ይጎርፍ ነበር:: እሳቸው ከመጡ ቤተክርስትያን ውስጥ ቦታ ስለማይገኝ ሰው በጊዜ ነበር የሚሄደው:: አንድን ነገር ማስረዳት ከጀመሩ ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ እንዲሉ ከስር ከመሰረቱ ጀምረው በጣም በግልጽና ለማንም ሊገባው በሚችል መልክ ነው የሚያስረዱት:: እሳቸውን አንድ ነገር ጠይቆ አልገባኝም የሚል አላየሁም:: በጣም ሲበዛ ደግሞ ቅን ናቸው:: ቤተክርስቲያን በእውነት በጣም ትልቅ አባት ነው ያጣችው::
ለሁላችንም መጽናናቱን ይስጠን: የአባታችን በረከት በሁላችን ይደርብን::

Anonymous said...

Nebse Yemarelen! Bereketachew Yedereben!

Anonymous said...

ነፍሳቸውን ይማርልን፤ በቀኙ ያሳርፍልን፤
የዘላለም ህይወት ስጥቶ በገነት ያርግልን።
ስላሴ ቤ/ክርስቲያን መቀበር ያለባቸው፤
እንደ እኚህ ያሉ አባት ናቸው።
እስቲ ዝም ብለን እንይ የት እንደሚያደርጉዋቸው፤
ሃዘናችን ቢከፋ ቢጠና አሁን ነው ።
እንዲህ ያለ ጠቢብ ከየት ሊመጣ ለናገኝስ ነው።
በሉ ቀጥሉበት ተማርን የምትሉ፤
የሳቸውን መንገድ የምትከተሉ።
ምነው ዝም በዛ ጸጥ አለ ዌብ ሳይቱ
በእውነት ሲሰሩ እውቅትን በጽሁፍ ሲያሰፍሩ ለሞቱ።
እኔን ያርገኘ ኢትዮጵያዊ ያርገኝ ድንቄም ክርስቲያን፡
ታዘብዃችሁ ተገነዘብኩዋችሁ ያልሆነ ቦት ስታፈሱ ስትረጩ እንባችሁን።
እኔስ ተጠራጠርኩ አልሞቱም እሳቸው፤
ሊመሰክሩ ነው ስለ ፓትሪያርኩ ስለ ፕሬዚደንቱ በቅርቡ ላለፈው፤
ካሰፈሩት ነገር ከመጵሀፋቸው።

የዳንኤል ገፅ said...

ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያምን በአካል በሚገባ አውቃቸዋለሁ። በአሰላ ደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያ ሰንበት ትምህርት ቤት በማገለግልበት ሰአት። እጅግ በጣም ትሁት፣ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ ኣባት ነበሩ። ለእረፍት ሀገርቤት በነበርኩበት ሰዐት 05/2012 በኣካል ፪ ጊዜ አግንቻቸ ነበር:: ዜና እርፍታቸን ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት። በእውነት ቤተ ክርስቲያ አንድ ታላቅ ሰው አጣች። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በቀኙ ያሳርፍልን። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

የዳንኤል ገፅ said...

ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያምን በአካል በሚገባ አውቃቸዋለሁ። በአሰላ መንበረ ጵጵስና ደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያ ሰንበት ትምህርት ቤት በማገለግልበት ሰአት። እጅግ በጣም ትሁት፣ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ ኣባት ነበሩ። ለእረፍት ሀገርቤት በነበርኩበት ሰዐት 05/2012 በኣካል ፪ ጊዜ አግንቻቸ ነበር:: ዜና እርፍታቸን ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት። በእውነት ቤተ ክርስቲያ አንድ ታላቅ ሰው አጣች። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በቀኙ ያሳርፍልን። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

Anonymous said...

Egna min eyeseran new esachewin yemesel abat endisexen bertiten entseliy.

Anonymous said...

nafesachwen. yemare
egame laBatekirestane bakemachen yamenagalagel yadergane

MN IRRAA said...

Sim kemigbar, maa-ireg kemuya gar astebabirewu yeyazu bete matsahift. lubbu isaani jannat nuuf hakaa'uu.

Anonymous said...

BEREKETACHEW YIDERIBIN. AMEN.

boots said...

RIP..

hailu said...

May God bless his soul.

The loss of such great teachers is huge and hard to replace. Such is a loss that hurts our church and we should mourn. May God give the strength to some one to step in his feet.

Anonymous said...

Nefis Yimar! Esachew sertew alefu.

Anonymous said...

E/r nafisachaw yemailin

Anonymous said...

Bereketachew yideribin Amen

Anonymous said...

ሠላም ዸጀ ሠላሞች የእንዸምን ከረማችሁ ሠላምታዬ ካላችሁበት ቦታ በአግዚአብሔር ሥም ይድረሳችሁ ። ሥለ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ እየሱስ እረፍተ ዜና ስሰማ እጅግ አዘንኩ አባታችንን የማውቃቸዉ አሰላ መድሐኒአለም በአገልግሎት ላያ እያሉ ነበር። ከብዙ በጥቂቱ ያሉኝ መንፈሳዊ ትውስታዎቻቸዉ በፉልሰታ ፆኦም የእመቤታችንን ቅዻሤ ሲቀድሡ ዜማዉን በዜማ ንባብን በንባብ ሲቀድሡ ሣይቸኩሉ በእርጋታ ከድምፃቸው ጠአምና ሌዛጋ ተደማምሮ እጹብ ድንቅ ነበር በተለይማ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ልዩ ፍቅር ላለዉ ሠዉ በዚያች ሠአት ሕሊናዉ ተነጥቆ የአርያሟን ንግስት ፍለጋ ይሔዳል አባ ሕርያቆሥ እንዳለዉ። ሌላዉ ደግም የኪዳን ምሥጋና ጠዋት ሢያቀርቡ ቆባቸውን አዉልቀዉ እምንጣፉ ላይ አስምጠዉ መሥቀሉን ይዘዉ ቅድሥ ሲሉ ምሥጋናዉን ግእዙን በአማረኛ ሲያነቡት ሕሊናን የመመሰጥ ታላቅ ፀጋ የነበራቸዉ አባት ነበሩ ። እግዚአብሔር ነፍሳቸዉን በአብርሐምና በይሳሐቅ አጠገብ ያኑርልንን አሜን። መሥፉን0፬

Orthodoxawi said...

Bereketachew be ewnet yiderbin!

Anonymous said...

Tewahdo lost Laibrery.I very sad for this.
R.I.P

Anonymous said...

I have a doubt who is going to replace such great spiritual knowledge at this century. GOD Bless Ethiopia. Nebsachawin begenet yanurilin Amen.

Anonymous said...

mengestesemayten yawerseln !

Anonymous said...

bereketachew yedressen

Anonymous said...

Nefisachewin begenet yanurileine

Anonymous said...

Nefisachewin begenet yanurileine

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)