September 21, 2012

ወቅታዊ ጉዳይን በሚመለከት ከኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መ/ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ

(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 11/2004 ዓ.ም፤ ምቴፕር 21/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፡- ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ወቅታዊ ጉዳዮች” አስመልክቶ ሁለት መግለጫዎችን እንዳወጣ ታወቀ። በመምሪያ ኃላፊው በአቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ ኃ/ማርያም ስም ይፋ የተደረጉት ሁለቱ መግለጫዎች በአገሪቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ም/ጠ/ሚኒስትር ሹመት እና ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

በተለይም በአዲስ ፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዝ ጉዳዮችን የሚያትተው መግለጫ “የሽግግር ወቅት ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዳይራመድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥና ዙሪያ የተሸሸጉ አንዳንድ ጥቅመኞችና የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላማዊ አካሄድ የማይዋጥላቸው ግለሰቦች ያላቸው “ከሚነዙት መሠረተ ቢስ አሉባልታ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል”። አክሎም “‹የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫና መሰል ጉዳዮች በጥቅምቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ይወሰናል” ብሏል። በአገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሒደትና የአዲስ ጠ/ሚኒስትር መሾምን በሚመለከት የሚያትተው ሌላውም መግለጫ “ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም እንደ ጥንቱ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ለልማትና ለሰላም ቅድሚያ ሰጥታ ትንቀሳቀሳለች” ብሏል።

የመግለጫዎቹን ሙሉ ይዘት ከዚህ (መግለጫዎች) ላይ ይመልከቱ።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

16 comments:

Anonymous said...

I am really sorry. Why Eskindir? Where are our Fathers? What is going on in the church? I didn't read the second letter but I think it is just to say congratulations for the New Prime Minister and Deputy PM. That is ok but it should have been signed by Abune Philipos (sira askiyaj) or Abune Nathnael. The first letter is completely wrong. We don't need this kind of letter from the church. We need up dated information about the discussion between the two H. Synods.

But the letter has some other meaning. This letter means they don't need to discuss with our fathers in exile. This is a good indication that there is pressure from the Government side to elect new Patriarch before the discussion.
If the government is going take this kind of action, it will be very bad for the country. The worst will come for the country. It will be good if government officials don't involve in this issue.

Anonymous said...

ሁላችንም ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መኖር የምንጨነቅ ሁሉ ነፍሳችንን እስከመስጠት ለሚደርስ መስዋእትነት ዝግጁ እንሁን:: በቤተክርስቲያኒቱ ስም የሚወጣ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ አምኖበት መሆን አለበት:: መውጣት ያለበትም በዋናው ስራ አስኪያጅ ወይም በአቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ፊርማ መሆን አለበት:: አቶ እስክንድር ምንም አያገባውም በቤተክርስትያን ጉዳይ ላይ:: መንግስት ከቤተክርስቲያን ላይ እጁን ቢያነሳ መልካም ነበር ግን አላነሳም:: ስለዚህ ወገኖቼ ኢትዮጵያ ላይ ዝምታ ትርጉም አላመጣም:: ሁሉ ነገር በስርአት እንዲፈጽም ትስፋ ማድረግ አልሰራም:: ስለዚህ በመካከላችን አስታራቂ ሳንፈልግ በአሜሪካው ሲኖዶስ ስርና በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ያለን ሁሉ በአንድነት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስንል ለቤተክርስቲያኒቱ ህልውና እንቁም:: መንግስት እጁን ከቤተክርስቲያን እንዲያነሳ እንታገል:: የቤተክርስቲያን ቀኖና እንዲከበር እንታገል::

Anonymous said...

yakedosane amelake eredane

Anonymous said...

Horrible! Horrible! Horrible!!

The God of Abraham and of Yishaq and of Yakob and of Yosef and of Musie and of Aron and of Dawit and of Makada and of the Prophets and of the Apostles and of Abune Selama and of Kidus Kaleb and of Kidus Yared and of Kidus Lalibela and of Abune Basllios and of Aleqa Ayalew ... come down and protect us, for we are weak and powerless.

Anonymous said...

i don't think there is any congratulations for the New Prime Minister and Deputy PM in the letter

Anonymous said...

እንዴት ነው ይህ ነገር? በዕውን ይህ መግለጫ ከሃይማኖት ድርጅት ነው የወጣው ወይንስ ከፓለቲካ ድርጅት? ከመውጣቱ በፊትስ ለመሆኑ አባቶች አንብበውትና አጽድቀውትስ ነው ወይ የወጣው? በጣሙን ነው የሚያስገርመው። ሁለቱም መግለጫዎች ተጀምረው እስክያልቁ ድረስ ስለመንፈሳዊና ዘላለማዊ ህይወት አያወራም፡፡ በሚያስገርም አኳሃን የሚናገረው በአብዛኛው ዓለማዊው ስለሆነውና ስለልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት ነው። ለመሆኑ ዘላለማዊው ህይወት የሚገኝበት መንፈሳዊው ስራ ለማን ተሰጥቶ ነው? የቤተክርስትያችን ተቀዳሚ ስራ ምድራዊ ሆነ እንዴ? ትንሽ ተቆይቶ ቤተክርስትያናችን የልማቱን ስራ በሰፊው ለማካሄድ ፓለቲካው ምርጫው ውስጥ ራሷን በእጩነት እንዳትቀርብና ከፓለቲከኞች ጋር እንዳትወዳደር ነው የሚያስፈራው። ምነው ሰው እንኳን ባይፈራ እግዚአብሄር አይፈራም እንዴ? ትንሽ አልበዛም እንዴ? አዲስ ለተመረጡ መሪዎቻችን የደስታ መግለጫ መላክና እግዚአብሄር ደግ ደጉን አሳይቷቸው ህዝባችንን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ መመኘትና ለዚህም ጸሎት ማድረግ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ጭልጥ ብሎ ዘወትር የሰለቸን የካድሬ መልእክት ማስተላለፍ ግን ሌላ ነው።

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል:: ማነው እስክንድር ገብረክርስቶስ? ለምን እስክንድር? ቤተ ክርስቲያን "አቶ" የቤተክርስቲያን መሪ እንዲሆንና በቤተክርስቲያን ስም መግለጫ እንዲሰጥ አልመደበችም:: ቤተክርስቲያን በሚገባ አስተምራ የሾመቻቸው አባቶች አሏት:: የ"አቶው" መግለጫ ግን በየትኛውም መስፈርት የቤተክርስቲያን መግለጫ ሊሆን አይችልም አይገባውምም:: በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመናን የምንፈልገው የፓትርያርክ ምርጫ አይደለም በሁለት የተከፈሉትን የአባቶችን እርቅ ብቻ ነው:: "አቶዎች" ቤተክርስቲያንን ማገልገል ከፈለግን በአቅማችን ብቻ እናገልግል:: አባቶች መስራት የሚገባቸውን ስራ ያለቦታችን በመግባት አንዘባርቅ:: በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለአቅማችን እየተንጠራራን ሽብር አንፍጠር:: እኛ እርቁን በአስቸኳይ እንዲከናወን እየጠበቅን ባለንበት ሰአት ይህ መግለጫ መውጣቱ በጣም አሳዝኖናል:: በጥቅምት ወር ስለፓትርያርክ ምርጫ እንዲወያዮ 'አቶው' ቃለ ጉባኤውን እሱ ሊቀርጽላቸው ፈልጓል ማለት ነው? አባቶቻችን የመወያያ ነጥቦችን ለማውጣትም ችግር የለባቸውም:: እባካችሁ አድር ባዮች ባባቶቻችን በስራቸው አትግቡባቸው:: አባቶቻችን እንኳን ለቤተክርስቲያን ጉዳይ ቀርቶ አለምን ለማስተዳደር ከበቂ በላይ አቅም አላቸው:: አትንኳቸው:: የፈለጉትን ይወስኑ ያድርጉ::

ዘሐመረ ኖህ said...

እኛ ጠግቦ እንደተኛ አሳማ ለጥ ብለን እስከተኛን ድረስ ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን መንግስት ቤተክርስቲያናችንን ሊያጠፋ ቆርጦ ከተነሳ ዓመታት ተቆጥረዋል አኛ ደግሞ ቆርጠን ተኝተናል መንግስት ከጫካ ጀምሮ ቤተክርስቲያናችንን እያጠፋ እንደ መጣ በዚሁ በደጀ ሰላም ብሎግ የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ የገበያ ግርግር ይሆናል በሚል ርዕስ ስር ከነማስረጃው አንብበናል ግን የወሰድነው እርምጃ የለም ለምን? ምን እስከምንሆን እየጠበቅን ነው? ስለ ሃይማኖታችን መሰዋት ካቃተን በቁማችን የሞትን ነን አሕዛብ ከኛ መማር ሲገባቸው እኛ ከነሱ መማር አቃተን ለስንፈታችን ምክንያት አሕዛብ በባለስልጣኖቻቸው ተመክተው ይቃወማሉ እንላለን እኛ ግን በሰራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሔር ተመክተን ቤተክርስቲያናችንን አትኩብን ብለን መነሳት ያቃተን አሳፋሪ የተዋህዶ ልጅ ብጤዎች ነን የአቶ ገረመን እንዴ ገና ሼኩ ገብቶ መግለጫ ይሰጥብናል ምክንያቱም የሚንቀሳቀስ እሬሳ ነንና የዋልድባ ገዳም አባቶች የሚከፍሉትን መስዋእትነት በተግባር እያሳዩን እንኳን ከቁም እንቅልፋችን መባነን አልቻልንም እግዚኦ ከኛ የባሰ አሳዛኝም አሳፋሪም ትውልድ የሚፈጠር አይመስለኝም ከተፈጠረም ወይ የሚሰልም አለያም ጣዖት አምላኪ ይሆናል እኛ ያላስረከብነውን ሃይማኖት ከወዴት ሊያመጣው? ብዙ ማለት እፈልግ ነበር ግን መቀጠል አልቻልኩም

Unknown said...

'ድመት መንኩሳ አመልዋን አትረሳ!' ብዙ ማለት እፈልግ ነበር ግን ደጀ ሰላም ካሁን በፊት የጻፍኳቸውን አስተያየቶች ስላላወጣቸው ከንቱ ድካም ይሆናል።

Unknown said...

መግለጫው ከቤተክነት ነው ወይስ ከኢሕአዴግ ምክር ቤት የተሰጠው???
የሚያገለግሉትስ ማንን ነው?

Unknown said...

መግለጫው ከማነው የተሰጠው? ከቤተክህነት ወይስ ከኢሕአዴግ ፅህፈት ቤት???

Unknown said...

በአቶ እስክንድር የተሰጠው ማስጠንቀቂያ የሚያመለክተው ነገር ምንድን ነው ? የቤተ ክርስቲያን ችግር መሠረቱ ድሮስ ማን ነው ? ዓለማዊ የሆነው መንግሥት በምድር የሰማያዊው መንግሥት ተወካይ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን የራሱ መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም በሃይል አስሮ ስለያዛት እኮ ነው ሁልጊዜ ስትታመስ የምትኖረው። ድሮም ነገሥታቱ እነሱ ከተወገዱ በኋላም እንሱን ያስወገዱት ማርክሲስቶቹና ሌኒንስቶቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን ነጥቀው መሳሪያ አድርገው እየተጠቀሙባት ነው። ደርግም ሆነ ወያኔዎቹ መሠረታዊ የርእዮታቸው ምንጭ 'አልቦ እግዜአብሔር' የሚለው ማርክሳዊውና ሌሊንናዊው ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከነዚህ ዓለማውያን ሃይሎች በማያሻማ ሁኔታ በቃላት ብቻም ሳይሆን በተግባር የሚታይ ነፃነቷን እስካልተጎናጸፈች ድርስ የራሷን የውስጥ ችግር ፈትታ የክርስቶስ ሙሽራ ሁና መቀጠል አትችልም። አሁንም በእነዚህ ዓለማውያን ሃይሎች ጣልቃ ገብነት የዛሬ 21 ዓመት በአባቶች መካከል የተፈጠረው ክፍፍል ተፈትቶ በአንድ ሲኖዶስ የምትመራ አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ልትኖረን ነው ብለን ተስፋ ጥለንበት የነበረውን ነገር ሁሉ እንደገና እንዲጨልም የሚያደርግ መግለጫ ነው በአቶ እስክንድር ፊርማ ይፋ የተደረገው ። ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም እንደተባለው ስለሆነ ፥ ደጀ ሰላም ለአንባብያን ያብቃው ወይም አያውጣው ዋስትና ስለሌለ ይብቃኝ።

Anonymous said...

Dear Zehamero , you are writing what i felt may GOD bless u.

ዘሐመረ ኖህ said...
እኛ ጠግቦ እንደተኛ አሳማ ለጥ ብለን እስከተኛን ድረስ ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን መንግስት ቤተክርስቲያናችንን ሊያጠፋ ቆርጦ ከተነሳ ዓመታት ተቆጥረዋል አኛ ደግሞ ቆርጠን ተኝተናል መንግስት ከጫካ ጀምሮ ቤተክርስቲያናችንን እያጠፋ እንደ መጣ በዚሁ በደጀ ሰላም ብሎግ የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ የገበያ ግርግር ይሆናል በሚል ርዕስ ስር ከነማስረጃው አንብበናል ግን የወሰድነው እርምጃ የለም ለምን? ምን እስከምንሆን እየጠበቅን ነው? ስለ ሃይማኖታችን መሰዋት ካቃተን በቁማችን የሞትን ነን አሕዛብ ከኛ መማር ሲገባቸው እኛ ከነሱ መማር አቃተን ለስንፈታችን ምክንያት አሕዛብ በባለስልጣኖቻቸው ተመክተው ይቃወማሉ እንላለን እኛ ግን በሰራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሔር ተመክተን ቤተክርስቲያናችንን አትኩብን ብለን መነሳት ያቃተን አሳፋሪ የተዋህዶ ልጅ ብጤዎች ነን የአቶ ገረመን እንዴ ገና ሼኩ ገብቶ መግለጫ ይሰጥብናል ምክንያቱም የሚንቀሳቀስ እሬሳ ነንና የዋልድባ ገዳም አባቶች የሚከፍሉትን መስዋእትነት በተግባር እያሳዩን እንኳን ከቁም እንቅልፋችን መባነን አልቻልንም እግዚኦ ከኛ የባሰ አሳዛኝም አሳፋሪም ትውልድ የሚፈጠር አይመስለኝም ከተፈጠረም ወይ የሚሰልም አለያም ጣዖት አምላኪ ይሆናል እኛ ያላስረከብነውን ሃይማኖት ከወዴት ሊያመጣው? ብዙ ማለት እፈልግ ነበር ግን መቀጠል አልቻልኩም

Anonymous said...

STOP ATO ESKINDER ,LET OUR HOLY FATHERS TO DECIDE WHAT IS BEST FOR OUR CHURCH NOT FOR EPRDF OR TPLF. OTHERWISE IS GOING TO BE A BIG , BIG MESS...... THAT IS TO MUCH, YOU ARE GOING TO FAR , YOU CAN NOT TELL THEM WHAT TO DO , THERE IS NO, NO, NO, ELECTION , WE ARE DESERVE TO GET PEACE AND UNITY !!!

Anonymous said...

WHO IS ATO ESKINDER ?????????????????? IS HE A GOVERNMENTAL / TPLF / AGENT OR WHAT ???? WE GOT TO WEAK-UP ETHIOPIAN ORTHODOX BLIVERS, WE HAVE TO RAISE OUR VOICE NOW , NOW, NOW , TELL TO OUR HOLY FATHERS TO DO THE JOB WHAT WE WANT NOW , PEACE, PEACE , PEACE , UNITY , UNITY , UNITY !!!!!!!!!!1

hailu said...

The worst form of letter that can come out of a spritual organization.

This is rather a letter by a TPLF/EPRDF cadre inbeded in the church.

May God remove such tugs from the premises of our church so that our church unite.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)