September 7, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ


(Mahibere Kidusan Website፤ ጳጉሜን 1/2004 ዓ.ም፤ September 6/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ በሬዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ተጀምሯል፡፡


በዋዜማው ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የማኅበሩ አባላት ከምሽቱ 12፤00 ስዓት ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ ባዘጋጀው ትራንስፖርት ከማኅበሩ ዋናው ማእከል አቧሬ ወደሚገኘው አቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በመጓዝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅ፤  ሕጽበተ እግርና የእራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠዋት የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ በመመራት በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በተጋበዙ ቀሳውስትና ካህናት ጸሎተ ወንጌል የተካሄደ ሲሆን በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተከፍቷል፡፡


የማኅበረ ቅዱሳን የሁለት ዓመት የአገልግሎት ክንውን ሪፖርት በማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም አማካይነት የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱም በሚዲያ አገልግሎት በግቢ ጉባኤያት፤ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት፤ በቅዱሳት መካናትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የተሠሩ ከፍተኛና አነስተኛ ፕሮጀክቶች፤ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የተደረጉ የጥናትና ምርምር ሥራዎች፤ የቤተ ክርስቲያንና የምእመናን ማኅበራዊ አገልግሎት፤ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃትና የተወሰዱ እርምጃዎች፤ ወዘተ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በተያዘው መርሐ ግብር የኦዲት ሪፖርት ቀርበዋል፡፡ የማኅበሩ ሒሳብ የ2003 ሪፓርት የውጪ ኦዲተር ሀብተ ወልድ መንክርና ጓደኞቹ በቻርተር የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች የኦዲት ሪፖርቶች ቀርበዋል፡፡ በዚህም ሂሳቡ ትክክለኛ እና የማኅበሩን ገጽታ የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በቀረበው የማኅበሩ የሁለት ዓመታት ክንውን እንዲሁም አጠቃላይ አስተያየት እንዲሰጡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መልካም ፈቃድ ከብፁዐን ሊቃ ነጳጳሳት ተጋብዘዋል፡፡ በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ከበጎ አድራጊ ምእመናን፤ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር፤ ከፀረ ተሐድሶ ጥምረት የተወከሉ እንግዶች በማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አስተያየታቸውን ከሰጡ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳዊ የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “በገሊላ አውራጃ ጌታ አሥራሁለት ሐዋርያትን እንደ መረጠ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም በምሳሌነት ይህች ቤተ ክርስቲያን የተማረ የሰው ኀይል ያስፈልጋታል በማለት 12 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ይዘው ነው በዝዋይ ሥራ የጀመሩት፡፡ ማኅበሩ ማኅበራችን ነው” በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን አመሠራረት አስታውሰዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አስተያት “ማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ምሁራንና አዋቂዎች የተሰባሰቡበት ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ተጠሪ ነው” በማለት ነበር የገለጹት፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “ማኅበረ ቅዱሳን በ20 ዓመት ውስጥ ያከናወነው አገልግሎት እኛ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎች ብቻ ሳንሆን ተቃራኒዎችም የሚመሰክሩት ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡

ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም አስተዳዳሪና የካሊፎርኒያ  አካባቢ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በሰጡት አስተያየት ”ከማኅበሩ ጋር በግጭትም፤ በፍቅርም ተገናኝተናል፡፡ ማኅበሩን ከማወቄ በፊት የተቀበልኩት በበጎ መንፈስ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ እኔን የሚያሳምኑ ነገሮች የተፈጠሩት ውስጣችን ገብተህ አገልግሎታችንን ተመልክተህ ፍረድ የሚል ጥያቄ አቀረቡልኝ፡፡ አላቅማማሁም ገባሁ፡፡ የማኅበሩን ማንነት ውስጡን ሕይወቱን ለማየት በምሞክርበት ጊዜ በትክክል የቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ለማወቅ እድል አገኘሁ” በማለት ከማኅበሩ ጋር ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል፡፡

የጠዋቱ መርሐ ግብር በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና በአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተጠናቋል፡፡

ከስዓት በኋላ በነበረው መርሐ ግብር የማኅበሩ ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ሓላፊ ዲ/ን ንጋቱ ባልቻ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም የማኅበሩ ስልታዊ ዕቅድ አፈጻጸም፤ የማኅበሩ ሥራ አመራር አፈጻጸም፤ የጠቅላላ ጉባኤያት ውሳኔ በተመለከተ ያልተተገበሩ፤ የሂሳብ ሪፖርት ላይ ታይተዋል ያሏቸውን ክፍተቶች አቅርበዋል፡፡በተጨማሪም የጠቅላላ ጉበኤ ውሳኔ ወይም አቅጣጫ የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው ጠቅላላ ጉባኤው ቀጣዩን ስልታዊ እቅድ እና የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ሲከለስ እንዲካተቱ ትኩረት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡ በኦዲትና ኢንስፔክሽን በቀረበው ሪፖርት ላይና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም ከአባላት በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማኅበሩን ወደ ፊት ሊጠቅሙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም የሚቀጥሉትን አራት ዓመታት ማኅበሩን የሚመሩ የሥራ አመራር አባላትን የሚያስመርጥ 5 አባላትን ያቀፈ አስመራጭ ኮሚቴ ለመምረጥ አስተያየት ከተሰጠባቸው በኋላ በብፁዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምና አቡነ ዘበሰማያትን በማድረስ አምስቱን አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን በእጣ እንዲለዩ ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሠረት የዕለቱ መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ዮናስ ቡራኬ ተጠናቋል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤው እስከ አርብ ጳጉሜ 2 ቀን የሚቀጥል ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበትና ለቀጣዩ አራት ዓመትት ማኅበሩን የሚመለከት ስልታዊ ዕቅድ ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል


16 comments:

Anonymous said...

tamasegan

Anonymous said...

Egziabhere Yetemesegene yehune Esikezihe yaderesene amilaki yemesigene.

Anonymous said...

Egziabher Legna Yalaregew neger min Ale? MK is a gift to EOTC from GOD

hailu said...

I have known MK since the time of Mahiber Michael in the Bilate Kespans. I can be a witness that it has contributed greatly to the EOTC although it also had some unintentional damages.

Its utmost challenge at this time, I believe, must be to contribute in a historic way in the effort towards restoring the unity of our church.
Failure to resolve the division in the church will remain as a black mark in the history of the generation of this time including MK.

May God help us achieve the unity our Orthodox Church. Amen.

Anonymous said...

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዛሬ ለስብሰባው የመጀመሪያቸው እንደሆነና በመጀመሪያ የካህናት መሰባሰብ ተገቢና ወቅታዊ እንደሆነ፣ እስከ አሁንም መቆየታችው ጥሩ እንዳልነበረ ገልጸው መጀመሪያ ግን ወደ መሠረታዊ ሐሳቡ ከመግባታችን በፊት “እኛ (ስብስቡ) ማን ነን?” የሚለውን ጥያቄ ጠይቀዋል። ቀጥለውም “ዋስትናችንስ ምንድን ነው?” ብለዋል። ይህንንም አባ ወልደ ሰማዕት ሲያብራሩ “ዋስትናችን አንድነታችን ነው” ብለው መልሰዋል። ከዚያም “እኛ ማን ነን?” ሲሉ ለጠየቁት ራሳቸው ሊቀ ክህናት ሲመልሱ “መተዳደሪያ ደንብ ይኑረን፣ አወቃቀራችን ከቃለ አዋዲው ውጭ ስለሆነ የራሳችንን ህልውና ማረጋገጥ ስለላለብን ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረን ያስፈልጋል” ብለዋል። ማብራሪያ ሐሳቡን ሌሎቹ ተሰብሳቢዎቹም ተቀብለውታል።

ስያሜ ምን መሆን እንዳለበት ቅድሚያውን የወሰዱት ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ሲያብራሩም “ማኅበረ ካህናት ብንለውና ደንብ ቢኖረን ጥሩ ነው” ብለዋል። አንዳንዶቹ ተሰብሳቢዎች “ይህ ስብስብ ከሀገረ ስብከት የተለየ ማኅበር ስለሆነ ደንብ ቢኖረን፣ የተቀረጹትን አጀንዳዎች ብንወያይበት ጥሩ ነው” ብለው ጥያቄ አቅርበዋል። ሰብሳቢውም የሊቀ ካህናት ጥያቄ ጥሩ እንደሆነና እኛን ሀገረ ስብከቱ ቢቀበለን የሚል ሃሳብ አቅርበው አጭሩ መንገድም በሀገረ ስብከቱ ስር መቋቋም እንደሆነ ጠቁመው አልፈዋል። ከተሰብሳቢዎቹም መካከል በኩረ ትጉሃን አቡሃይ “ለመሆኑ ይህንን ስብስብ ሊቀ ጳጳሱ ያውቃሉ ወይ?” ብለው ጠይቀው ሰብሳቢውም ሲመልሱ ለሊቀ ጳጳሱ ነግረናቸው ተቀብለውት በርቱ ብለውናል” በማለት ገልጸዋል።

ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ሃሳብ መሠረት ጉባኤው የመተዳደሪያ ደንቡን የሚያረቅቁ ሰዎች እንዲመርጥ ተስማምተው የሚከተሉት ሰዎች ተመርጠዋል።
1. መልአከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ፣
2. ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ፣
3. ሊቀ መዘምራን ክነፈ ርግብ ሐጎስ፣
4. በኩረ ትጉሃን አቡሃይ ፈንቴ እና
5. መጋቤ ምሥጢር በቃሉ ከሃሊ።

Anonymous said...

Good Job MK! Our public institutions has got a lot to learn from you. For sure, the coming time will be both challenging and rewarding. God always be with you and us your supporters!

Anonymous said...

"በሬዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች " የሚባለው ነገር ሲያስጠላኝ ይቅርታ ይደረግልኝና ምንም መንፈሳዊነት የሌላቸው የኢሀዴግ ተወካይ መሆናቸው ነው? ምናልባትም በዋልድባ ላይ ከወሰኑት ባለከረባቶቹ ይመስሉኛል የኔ ነገር ሬዴራል ፖሊስ እና ሬዴራል ጉዳዮች የሀይማኖት ሬዴራል ፖሊስ ማለት ይመስለኛል:: ታዲያ መንግስት ከሀይማኖት ጋር ግንኙነት ከሌለው ፌደራል የሚሉት ነገር ከቤተክርስቲያናችን እንዴት ሊገባ ቻለ? ግእዝ አይሉት እዝል ወይም አራራይ ፌደራል ብሎ ነገር ሲያስጠላኝ!!!!!

tesfaye said...

egziabher zewetir kenante gar yihun

Anonymous said...

AWo gena bezu yetbekbachwalena kezeh yebelete meserate techlalache be betkerstyanachen bezu yemetskaklu gudayoche aluna bete .

Anonymous said...

የፌዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች ለምን ተገኙ? ከመቼ ወዲህ ነው በማህበረ ቅዱሳን መደበኛ ጉባኤ ላይ መገኘት የጀመሩት? በያንዳንዱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ፕሮግራሞች ላይ ሊገኙም እቅድ አላቸው ማለት ነው? በየቅዳሴው ፕሮግራምም ለመገኘት እቅድ አላቸው? ወይስ ማህበሩ ጋብዟቸው ነው? ማህበሩ ጋብዟቸው ከሆነ ቅሬታ የለኝም:: እራሳቸው መገኘት ፈልገው ከሆነ የተገኙት ከዚህ በፊት ያልሰማነውና ያልነበረ ነገር በመሆኑ ምክንያታቸውን ብናውቀው አይከፋም:: በመካፈላቸው ግን ምንም ቅሬታ የለኝም አዲስ ስለሆነብኝ ብቻ ጠየቅሁ እንጂ በሁሉም የቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች ላይ እየተገኙ ከቤተክርስቲያን ስርአትን ቢማሩ መልካም ነው:: እንደመንግስት ተወካይ ሆነው ተገኝተው ግን የቤተክርስቲያኒቱ ፕሮግራሞችና ስርአቷ ላይ እንዲህ ብታደርጉ እንዲያ ብታደርጉ የሚል ማንኛውንም ትእዛዝም ሆነ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው:: ቤተክርስቲያን የስርአት ባለቤት ናትና:: ቤተክርስቲያንን ያለምንም ጫና ነጻ አድርገዋት ቢተዉአት እንኳን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ቀርቶ አለምን ከየተኛውም ብቁ ተብሎ ከሚታወቅ መሪ በተሻለ ማስተዳደር ትችላለችና:: አባቶቻችን በዚህ ምንም ችግር የለባቸውም:: እነሱ (የአለሙ መሪዎቻችን) እንደሚያስቡት አባቶቻችን ያልተማሩ አይደሉም:: የቤተክርስቲያንን የአብነት ትምህርት አንዱን እንኳን ያስኬደ ወይም ያጠናቀቀ የቤተክርስቲያን ሰው በዘመናዊው ትምህርት ባችለር (B.Sc/B.A equivalent Bachelor degree) plus ማስተርስ (M.Sc/M.A or equivalent) እና ዶክትሬት (PhD) ጨርሶ እስከ ፕሮፌሰርነት ከደረሰ በጣም ጎበዝ ከሚባል ሳይንቲስት (Scientist) እጅግ የበለጠ ነው:: አባቶቻችን ደግሞ ብዙዎቹ ከአንድ በላይ የአብነት ትምህርት አጠናቀዋል::

ስለዚህ ፌደራሎቹ የተገኛችሁት ስርአት ለመማርና ቤተክርስቲያን የምትሰራውን ለማየት ከሆነ ጥሩ ነው ቀጥሉበት:: ሌላ አላማ ኖሯችሁ ከሆነ ግን ቆም ብላችሁ አስቡ::

Anonymous said...

"በሬዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች " የሚባለው ነገር ሲያስጠላኝ ይቅርታ ይደረግልኝና ምንም መንፈሳዊነት የሌላቸው የኢሀዴግ ተወካይ መሆናቸው ነው? ምናልባትም በዋልድባ ላይ ከወሰኑት ባለከረባቶቹ ይመስሉኛል የኔ ነገር ሬዴራል ፖሊስ እና ሬዴራል ጉዳዮች የሀይማኖት ሬዴራል ፖሊስ ማለት ይመስለኛል:: ታዲያ መንግስት ከሀይማኖት ጋር ግንኙነት ከሌለው ፌደራል የሚሉት ነገር ከቤተክርስቲያናችን እንዴት ሊገባ ቻለ? ግእዝ አይሉት እዝል ወይም አራራይ ፌደራል ብሎ ነገር ሲያስጠላኝ!!!!!

Anonymous said...

ፌደራል ብሎ ነገር ሲያስጠላኝ!!!!!

Anonymous said...

"በሬዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች " የሚባለው ነገር ሲያስጠላኝ ይቅርታ ይደረግልኝና ምንም መንፈሳዊነት የሌላቸው የኢሀዴግ ተወካይ መሆናቸው ነው? ምናልባትም በዋልድባ ላይ ከወሰኑት ባለከረባቶቹ ይመስሉኛል የኔ ነገር ሬዴራል ፖሊስ እና ሬዴራል ጉዳዮች የሀይማኖት ሬዴራል ፖሊስ ማለት ይመስለኛል:: ታዲያ መንግስት ከሀይማኖት ጋር ግንኙነት ከሌለው ፌደራል የሚሉት ነገር ከቤተክርስቲያናችን እንዴት ሊገባ ቻለ? ግእዝ አይሉት እዝል ወይም አራራይ ፌደራል ብሎ ነገር ሲያስጠላኝ!!!!!

Anonymous said...

Wow Excellent news
Long live for Mahebere Kidusan

May GOD bless u all members and supporter of Mahebere Kidusan.

Anonymous said...

ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም አስተዳዳሪና የካሊፎርኒያ አካባቢ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በሰጡት አስተያየት ”ከማኅበሩ ጋር በግጭትም፤ በፍቅርም ተገናኝተናል፡፡ ማኅበሩን ከማወቄ በፊት የተቀበልኩት በበጎ መንፈስ አልነበረም፡፡???
*****2. ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ፣****
"በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ እየተካሄደ ነው"http://www.dejeselam.org/2012/08/blog-post.html
betam yemigerm new selamaheberu yeteradut sebsaba laye new wayes kedam belaw bedanb selamahebaru sera teradtawetal...

Anonymous said...

እግዚአብሔር አምላካችን የተመሠገነ ይሁን። ለእኔ ማህበረ ቅዱሳን ማለት ለእውነተኛይቱ እና ጥንታዊቱ በስውርም ሆነ በግልፅ ብዙ በረከት እና የሰማይ ቤት ሀብት ለምታሰጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልዩ ጠባቂ ፖሊስ እና ጠበቃ ሆነው አዲስ ከመጣው የመናፍቃን ወረርሽኝ ሃይማኖቷን የጠበቁ ልዩ አርበኞች ናቸው። ልብ አድርጉ ባለፍንባቸው የተዝረከረከ የቤተክርስቲያኗ አመራር ሂደት ግንባታና ሥራቸውን እየሠሩ ስንት ነገር እንደ ልዩ ፖሊስ አጋልጠው ከእንቅልፋችን በማንቃት መሐላችን የገቡ መናፍቃንን እንድናይና እንድንጠነቀቅ እንዳደረጉ!የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ብዙ የተሰወሩ እና የተገለፁ የእግዚአብሔር ሥራዎች ስላሉ ማመን ተግባሩ ነው። ይህ ማኅበረ ቅዱሳን ግን የተኩላዎቹ መምጫ ዘመን ነው ሁሉንም አትመኑ መርምሩ የሚለውን ቃል ያስታወሰን እና ያሳየን ማኅበር ነውና አባልም ባልሆን ለማህበሩ ትልቅ አክብሮት አለኝ። ለወደፊትም እግዚአብሔር በዚሁ ያበርታቸው እያንዳንዱንም ይባርክ ብዬ እለምናለሁ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)