September 30, 2012

የመስቀል በዓል “ግዙፍነት ከሌላቸው የዓለም መንፈሳውያን ሀብቶች” ተርታ ሊመዘገብ ይችላል


 • ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል
 • የአ/ /ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡት ትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማ እንደነበረው ተጋልጧል
 • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላት ላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞ ገጥሞታል፤ 
 • የአቶ መለስ ዜናዊ 40 ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ//ክህነት ይደረጋል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓል አከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረትበመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርም ኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓል የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

September 28, 2012

ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያንና ለአንድነቷ

(ከቀስቶ ወተረ አትላንታ ጆርጂያ/ READ THIS ARTICLE IN PDF)
1.   ከታሪክ ምን እንማራለን
በዚህ ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ያሳለፈችውን ችግርና መፍትሔዋን ከጠቅላላው አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ተመክሮ አሁን እኛ ያለብን ችግር መነሻውና ለመፍሔው ምን ማድረግ እንዳለብን የሚገልጥ ጽሑፍ ይሆናል። ጽሑፉ ማንም ለመንካት ተብሎ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም። በጽሞና ከተነበበ ለአንድነቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ብቻ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው። አንባቢዎችም ከዚህ አንጻር እንዲያነቡት ይጠየቃሉ።

መጪውን ጊዜ በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” መዋጀት

(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ 20ኛ ዓመት ቁጥር 1/ 2005 ዓ.ም/ PDF):- ጊዜ ይመጣል ጊዜ ይሄዳል፡፡ ጊዜ መጥቶ ሲሄድ ግን እንደው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ የጊዜውን አሻራ አሳርፎ ነው፡፡ አሻራው ግን አዎንታዊም አሉታዊም ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ምርጫው በጊዜ መጠነ ክበብ ውስጥ ያለው የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ በጊዜያት ውስጥ የረቀቀና የገዘፈ ዓለም ባለቤት ሆኖ የተፈጠረና ጊዜ የማይቆጠሩላቸው የሥሉስ ቅዱስ ፍጡር ነው፡፡ በሕያውነቱ ረቂቁን ዓለም- ዓለመ ነፍስን መስሎና ሆኖ ሲኖር፤ በምድራዊነቱ ግዙፉን ዓለም- ዓለመ ሥጋን በተዋሕዶ ነፍስ መስሎና ሆኖ ይኖራል፡፡ በዚህም የሁለት ዓለም ባለቤት ነው፡፡ የሰማያዊና ምድራዊ ወይም የመንፈሳዊና ዓለማዊ፡፡

“መለስ አልሞተም፤ እውነት መለስ ነው” (ሙገሳ እና ስብከት ስለ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ)

Separation of Church and State in Jeopardy

September 24, 2012

በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ቤተ ክርስቲያን ሰፊ የብዙኀን መገናኛ ሽፋን እንደምታገኝ ይጠበቃል

 • በሰንበት ት/ቤቶች ዐውደ ትርኢት የዕርቀ ሰላምና አንድነት ጥያቄው ትኩረት ተሰጥቶታል::
 • ግማደ መስቀለ ክርስቶስ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት የተቀጸል ጽጌ በዓል ተከብሯል::
 • ተቀጸል ጽጌ ናትናኤል ሊቀ ጳጳሳት” (የአዲስ ዓለም ጽዮን ማርያም ገዳም ሊቃውንት)::
 • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርባኛ ቀን መታሰቢያ ዛሬ መስከረም 14 ቀን ይዘከራል::
DEMERA (Courtesy of Teddy Haile)
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- ሃይማኖታዊ መሠረትና ብሔራዊ ገጽታ ካላቸው በዓላት አንዱና ዋነኛው የመስቀል በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በዓለ መስቀልን ከጌታችን ዘጠኝ ንዑሳን በዓላት አስገብታ በመወሰን ታከብራለች፡፡ ሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ “መስቀል መልዕልተ ኵሉ ነገር ያድኅነነ እምፀር” በማለት መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ እንደኾነና ከሥጋዊ (ዓለማዊ) ጠላትም ኾነ ከመንፈስ ጠላታችን ዲያብሎስ እንደሚያድነን እንዳስተማረን÷ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀል ጽንዓታችን፣ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን ነውና እናከብረዋለን፤ እናገነዋለን፤ በመባረክና በማማተብ ረቂቃን አጋንንትን እናርቅበታለን፤ በመታሸት ከደዌ ሥጋ፣ ከደዌ ነፍስ እንፈወስበታለን፤ በሰውነታችን በመነቀስና በተለያየ ኪነ ቅርጽ ማዕተብ አድርገን ክርስትናችንና በመስቀሉ ማመናችንን እንገልጽበታለን፡፡

September 22, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዠን መርሐ ግብር ሊጀምር ነው(MahibereKidusan Websiteመስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም./ በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ/ PDF):- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡

September 21, 2012

ወቅታዊ ጉዳይን በሚመለከት ከኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መ/ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ

(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 11/2004 ዓ.ም፤ ምቴፕር 21/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፡- ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ወቅታዊ ጉዳዮች” አስመልክቶ ሁለት መግለጫዎችን እንዳወጣ ታወቀ። በመምሪያ ኃላፊው በአቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ ኃ/ማርያም ስም ይፋ የተደረጉት ሁለቱ መግለጫዎች በአገሪቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ም/ጠ/ሚኒስትር ሹመት እና ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

September 19, 2012

ቀጣዩን ፓትርያርክ በተመለከተ …


(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 9/2004 ዓ.ም፤ ምቴፕር 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፡- ከአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማለፍ በኋላ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቀመጥ የሚገባውን ቀጣይ አባት ከመሾም አስቀድሞ የአራተኛውን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ዕጣ ፈንታ መወሰን፣ ከዚህም ጋራ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት እንዲሁም የመዋቅር ማሻሻያ የሚመለከቱ ርምጃዎች መውሰድ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ኾኖ ወጥቷል፡፡ በአሜሪካው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ከተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት በተጨማሪ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሓቅ የሚመራውና ከዐሥር ያላነሱ ልሂቃንን የያዘው የአገር ሽማግሌዎች ቡድን ሰሞኑን ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ጋራ በመወያየት በቅርቡ ቡድኑ በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ የሚነጋገርበት ኹኔታ እንዲመቻች መደረጉ ተዘግቧል፡፡

September 14, 2012

በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን

 (ደጀ ሰላም፤ መስከረም 4/2004 ዓ.ም፤ September 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ ያደረሱን “ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ” የተሰኙ ፀሐፊ ሲሆኑ የደጀ ሰላም ዝግጅት ክፍል ጽሑፉ የያዘው ቁምነገር ለደጀ ሰላማውያን ቢደርስ ሊኖረው የሚችለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።
 ፍቅር፣ ሰላም እና ይቅርታ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት!
(ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ፈርጀ ብዙ ፈተናዎች እና ችግሮች ስትጋፈጥ ኖራለች ። ቢሆንም ቅሉ በእግዚአብሔር አጋዥነት ሁሉንም እያለፈች ከዛሬው ዘመን ደርሳለች ። ፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማረፋቸውን ተከትሎ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ባሳተፈ መንገድ የወደፊት ጉዞዋን አሳምራ፥ መጠበቅ ያለበትን አየጠበቀች ፥ መስተካከል የሚገባውን እያስተካከለች ፥ አደራዋን ጠብቃ ፥ ቀጥ ያለውን አቋሟን እንዳከበረች ያለማወላወል እንደምትቀጥል ይታመናል። ለዚህም ያመች ዘንድ መሠረታዊ የሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት ወሳኝ ሥራዎችን መሥራት ጊዜው የሚጠይቀው ዐቢይ ጉዳይ ነው።

September 12, 2012

"የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" ቅ/ሲኖዶስ አስታወቀ

 • “የሃይማኖት መሪዎች ጊዜ ሳያልፍ አንድነታቸውን እንዲያጠነክሩ ጸሎቴ ነው” /ፕ/ር ኤፍሬም ይሥሐቅ/
 • ከመጪው ግንቦት በፊት የሚፈጸም የፓትርያርክ ሹመት እንደማይኖር እየተነገረ ነው::
 • ማኅበረ ቅዱሳን ስለዕርቀ ሰላሙ ያለውን አቋም በግልጽ ዐውጆ ሂደቱን እንዲያግዝ ተጠይቋል::
 • “በአሐቲ ቤተ ክርስቲያን መርሕ የቤተ ክርስቲያን ፍጹም አንድነትና ሰላም እንዲጠበቅ እንሠራለን” /የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር/::
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 2/2004 ዓ.ም፤ September 12/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅርቡ በመንግሥት በኩል ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው የአመራር ሽግግርና የሚተካው ርእሰ መንግሥት ከተለወጠው ዘመንና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኅልፈት ጋራ ተያይዞ ከታየው የሕዝብ ጨዋነት፣ ይቅር ባይነትና ርኅራኄ አኳያ የሚመጥኑ ተፈላጊ ለውጦችን ለማምጣት የሚያስችል እንዲኾን እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክህነቱም በኩል ከቀጣዩ ርእሰ አበው ሹመት አስቀድሞ መከናወን ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ እየተገለጸ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ ኅልፈት ተገቢውን ሰው መተካትና የተፈጠረውን ክፍተት ማሟላት ሕገ መንግሥታዊ እና ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ በግዴታው አፈጻጸም ሂደት የሚታየው የመንግሥት ይኹን የቤተ ክህነት ባሕርይና ብቃት ለየራሱ ከጎሰኛነትና ጥቅመኛነት በላይ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን በማስቀደም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡

September 9, 2012

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን አቃቤ መንበረ ፓትርያርክየአዲስ ዓመት መልእክት አስተላለፉ


(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 4/2004 ዓ.ም፤ September 9/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ አዲሱ የቤተ ክርስቲያናችን አቃቤ መንበር እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አዲሱን ዓመት አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉት መልእክት ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ሰፍሯል። ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
Ø    በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
Ø    የሀገርን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
Ø    በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራባ ተይዛችሁ በየሆስፒታሉ የምትገኙ፣
Ø    የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚአ ቤት ያላችሁ፣
Ø    በተለያየ ምክንያት ከሀገራችሁ ከኢትዮጵያ ወጥታችሁ በዓለሙ ሁሉ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤

September 8, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ምርጫ አካሄደ


(Mahibere Kidusan Website፤ ጳጉሜን 2/2004 ዓ.ም፤ September 7/ 2012/ PDF)፦ ከነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠዋት በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ “በማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ጉዞ የአባላት ተሳትፎና የወደፊት ሁኔታ” በተመለከተ ጥናት የቀረበ ሲሆን በአባላት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከሰዓት በኋላ በቀጠለው ስብሰባም “ስልታዊ ለውጥ ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት ከማኅበረ ቅዱሳን ተልእኮና አቅም አንጻር” በሚል በዲ/ን ያረጋል አበጋዝና ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በአባላት ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመጨረሻም የጽ/ቤት ግንባታ ሪፓርት ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጸሜ ሆኗል፡፡

September 7, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ


(Mahibere Kidusan Website፤ ጳጉሜን 1/2004 ዓ.ም፤ September 6/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ በሬዴራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮች ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ተጀምሯል፡፡

September 6, 2012

ጥቂት ማብራሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስላወጀው የምሕላ ጸሎት


(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 1/2004 ዓ.ም፤ September 6/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ደጋግመን እንደዘገብነው እና ቀጥሎም ሙሉ ደብዳቤውን እንዳስነበብነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሁለት ሱባኤ ማለትም የ14 ቀናት የጸሎት አዋጅ አውጇል። ይሁን እንጂ “ሱባኤ” የሚለው ቃል የተለያየ ትርጉም ያለው ከመሆኑ አንጻር ፣በርግጥ የራሱን አዋጅ የማብራራት ሕጋዊ መብት ያለው አዋጁን ያወጣው አካል ቢሆንም፣ የደብዳቤውን እና የአዋጁን መንፈስ ማብራራቱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

September 5, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው የሁለት ሱባኤ የምሕላ ጸሎት


ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው የሁለት ሱባኤ የምሕላ ጸሎት


 • ለአገራችን መልካም መሪ ለቤተ ክርስቲያናችንም ደገኛ አባት እንዲሰጥ ጸሎት ይደረጋል::
 • የተቀጸል ጽጌና መስቀል ደመራ በዓላት አከባበር ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ ተሰጥቷል::
 • የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በዕርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ ይወያያል::
 • ነገ ከሚጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን ዐሥረኛ ጠቅላላ ጉባኤስ ምን እንጠብቅ?
 (ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 29/2004 ዓ.ም፤ September 4/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት ታውጆ የሰነበተውና ሀገሪቱን ማቅ ያለበሳት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ካበቃና ሐዘኑን በተለያየ መንገድና በተለያየ መንገድ ሲገልጽ ለቆየው የተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል  ወደ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴው እንዲመለስ ከተጠየቀ፣ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ የቆየው ሰንደቅ ዓላማ ወደ መደበኛ ከፍታው ከተመለሰ በኋላ ለሁለት ሱባኤ ያህል (ዐሥራ ሦስት ቀናት) የቆየው ብሔራዊ ሐዘን ማብቃቱ ከወደ ቤተ መንግሥት በተገለጸበት ዕለት የሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ ደግሞ ከቤተ ክህነት በኩል ታውጇል፡፡ ለሁለት ሱባኤ ማለትም ለዐሥራ አራት ቀናት የሚዘልቀው የጸሎተ ምሕላ ሱባኤ ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም በዘመነ ዮሐንስ ተጀምሮ መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም በዘመነ ማቴዎስ የሚፈጸም ነው፡፡ የጸሎተ ምሕላው ሱባኤ የታወጀው በትናትናው ዕለት ተጀምሮ ዛሬም ቀጥሎ በዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ነው፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)