- የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ነሐሴ 17 ቀን በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፤
- የቅዱስነታቸው አስከሬን ነሐሴ 16 ቀን ወደ ካቴድራሉ የሚያመራው መንግሥት በሚመድበው ሠረገላ ነው፤
- የመንግሥት፣ የአኀት አብያተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ይገኛሉ፣
“ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የእገሌ ወእገሌ አይደሉም፤ የሁሉም አባት ናቸው” ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የቀድሞው ፓትርያርክ አስከሬን ሲቀድሱ ባደጉበት፣ ከእስር ከተፈቱም በኋላ ባገለገሉበት፣ ማዕርገ ጵጵስናም ፕትርክናም በተሾሙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጎን በተዘጋጀለት ሥፍራ እንደሚያርፍ አስታውቋል፡፡
ስለ ሥርዐተ ቀብሩ አፈጻጸም በወጣው መርሐ ግብርም ነሐሴ 16 ቀን
2004 ዓ.ም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስከሬን አሁን ከሚገኝበትና
እስከ ቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ከሚቆይበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተወስዶ ጸሎት ይደርሳል፤ ጸሎተ
ቅዳሴም ይቀደሳል፡፡ ከዚያም በዕለቱ ከቀኑ በ7፡00 ላይ መንግሥት በሚመድበው ሠረገላ ተጭኖ፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታጅቦ በክብር
ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያመራል፤ በካቴድራሉም ጸሎተ ፍትሐት ሲደረግለት አድሮ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም
ማለዳ በ12፡00 ሰዓት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ጸሎተ ቅዳሴው ይከናወናል፡፡
ይህም ጠዋት 3፡00 ላይ እንደተጠናቀቀ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብሩ
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት፣ የአኀት አብያተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የሌሎች
አብያተ እምነት እንግዶች በተገኙበት ሥነ ሥርዐቱ ይቀጥላል፤ የሐዘን መግለጫዎችም ይሰማሉ፡፡
የዐውደ ምሕረት ሽኝት መርሐ ግብር ቀትር 6፡00 ላይ ከተካሄደ
በኋላ የቅዱስነታቸው አስከሬን ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መካነ መቃብር ጎን በተዘጋጀለት ሥፍራ በክብር እንዲያርፍ
ተደርጎ የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ፍጻሜ ይኾናል፡፡
ከግማሽ በላይ ብፁዓን አባቶች የተገኙበትን የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ
ጉባኤ የመሩት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው የብፁዕ ወቅዱስ
ፓትርያርኩ ሥርዐተ ቀብር ተፈጽሞ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ የያዙት ሓላፊነት እንደተጠበቀ
ኾኖ የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስን ስብሰባዎች በመምራት በሓላፊነት እንደሚቆዩ ተገልጧል፡፡
ይህም በ1991 ዓ.ም ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምዕራፍ 3 አንቀጽ
11 ንኡስ አንቀጽ (2) መሠረት የተደነገገ ነው፡፡ “የቋሚ ሲኖዶስ
ሰብሳቢው ፓትርያርኩ ነው፤ ፓትርያርኩ በማይኖርበት ጊዜ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተወክሎ ሰብሳቢ ይኾናል፡፡ አባላቱም በቅዱስ ሲኖዶስ
ምልዓተ ጉባኤ የተመረጡ አራት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ኤጲስ ቆጶሳት ይኾናል፡፡››
በአሁኑ ወቅት ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስና የቅዱስ
ሲኖዶስ ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ጋራ የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በመኾን የሚሠሩት ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ
ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

1 comment:
Yekidusane amelake kedegagochu abatoche mehakel yadergelen yehe neger lega mekrna tegsatse yehone zend tederege yasazenale egame wed fetna endanegeba tegetene enseleye
Post a Comment