November 25, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? (እንደገና እንጠይቅ)

  •  ቅዱስነታቸው ስለ ራሳቸው እና ስለ ፕትርክናው ሊናገሩ ይገባቸዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 31/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ ከሆነ እነሆ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ባለው ሥልጣን መሠረት ተተኪው ፓትርያርክ እስከሚሰየም ድረስ አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ” ይሆኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሰይሟል። ቤተ ክርስቲያኒቱ 5ኛውን ፓትርያርኳን በሐዘን እያሰበች ባለችበት በአሁኑ ወቅት “ቀጣዩ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ በስፋት በመጠየቅ ላይ ይገኛል። ድምጻቸው ቀላል ያልሆኑ ኦርቶዶክሳውያንም “እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊሰጥ ዕድል ከፍቶልን ሳለ፣ የቀደሙትን አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ ሲገባ የምን አዲስ ምርጫ ነው?” እያሉ ነው። ለደጀ ሰላም የደረሱ ብዙ መልእክቶችም ይህንን በማበከር ላይ ይገኛሉ። በዚህ አጋጣሚ ደጀ ሰላም” አንድ ሁነኛ ጥያቄ ማቅረብ ትፈልጋለች። የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? ድምጽዎትን ለምን አንሰማም? ሐሳብዎን ለምን አይገልጹም? ከምዕመኖችዎ ጋር በቱርጁማን፣ በስማ በለው፣ በተላላኪ፣ በሦስተኛ ወገን መነጋገር መቼ ነው የሚያበቃው ለማለት እንወዳለን። አንባብያንም ሐሳባችሁን እንድታካፍሉን እንጋብዛለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

93 comments:

Dn Haile Michael said...

Yes it is a good opportunity for church unity if His Holiness Patriarch Marchorewos comes.And I see no other option. Government should leave the Church to exercise Her right.

Anonymous said...

Betam asakegnim asazenegnim.
Yasakegn. Dimstachewenima ayenew minun enisemalen. Le Haimanot Yemotu nachew yibal neber neger gin besirachew YeBEtekirstianin Meleyet wededu. Lehudamoch Medirek kefetu. Leleboch tilik dimist setu. Poletikegnoch endeiyakenekinubat mikiniat honu. KEzih belay dimst ale?


Yasazenegn demo. Zarem lay sew yeminamelik Yehen hulu tefat yaderesew besachew mikniat kehone, minew amlikotachenin gira agabanew? Ay dejeselam bilachehu demo Merkoriosin promote madireg fekedachehu?

Anonymous said...

አግባብ ያለው ጥያቄ ነው፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ድምጽ መስማት እጅግ እንፈልጋልን::ቅዱስነታቸውም ለቤ/ያን አንድነት ሲሉ መከፈል የሚገባውን መስዋአትነት ከፍለው አንድ እንዲያድርጉን በያዙት ስልጣን እግርዎ ስር ወድቄ እለት እለት እለምንዎታለሁ:: እባክዎ በቤ/ያን መከፍል ምክንያት የተጎዳውን ሁልንተናችንን ይጠግኑልን:: በዚህ እንኳ የ20 አመት ሃዘናችን እንዲበቃ ያድርጉልን::

Anonymous said...

እግዚአብሄር አምላካችን የቤተክርስትያንን አንድነት ይጠብቅልን ዘንድ ለልጅልጅ ስርአቱ ተጠብቆ ይተላለፍ ዘንድ አቡነመርቆሪዎስ ወደ መንበራቸዉ ይመለሱ፤ ቀኑ ሃላፊ ነዉ፡ ህዝቡም ጳጳሳቱም በአንድነት ስለቤተክርስቲያን አንድነት በጋራ ሊነሳ ይገባዋል። እዉነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ቃሉ እንደሚለዉ ፡ስለቤተክርስትያን አንድነት ነዉ መጨነቅ ያለብን፤አምላካችን ይርዳን

Anonymous said...

selam to all ethiopia ortohdox tewhedo familly,1st of all patriarrch merchorios is not our leader,he is a leader of group of pops and some blinds ethiopans, even if he wants go back home, he has to go debrelebanos gedam to pray for what he did and also he has to ask mercy ethiopian people, ethiopian church,and ethiopian sinod
selam to ethiopian by ethiopian sinod
adnew

Anonymous said...

Do you think that makes difference?
Whether he says a word or not EPRDF is gonna put some body who can work with them smoothly. Putting back the former patriarch would be swallowing the spit for the government& on top of that some bishops could be targeting the chair from inside & some doesn`t like the idea of unfication from the outside because of personal benefits. So brothers the best thing to would be pray, pray & pray for our church unification & peace & stability for our country

Anonymous said...

Abune Mekorios is in Atlanta.

Anonymous said...

It it very very very important to bring back "abune Merkoriyos", to our beloved holy church unity.
"God bless our church and our country"

Demile yalew said...

Before what he want to do we ask abune Merkerewos why first the synodos try to make agreement with all fathers ( erke-selam comite) b/c in that agrement the needs of thes father can simply official. May God spirit can told thes what must do for this first better give priority for peace!

Anonymous said...

laBatekirestane andenate enasebe.....
Senodose anode hono. charo Madehaneyalame yasayane.
Amen Amen Amen

Anonymous said...

I have been asking this question for long period of time. I have been also discussing this will my friends a lot of times. We need the father to go out and speak so that we can understand situation better. If he won't, I think we all practically couldn't be able to consider his existence in the coming spiritual leader selection process. God bless him and all of us! Thanks Dejeselam for being me and my friends voice!

Anonymous said...

መንበሩ ከእሳቸው አልፋለች ለዚህ ነው ዝምታ የመረጡት እሳቸው ሌሎቹ የጥቅም ጩህት ነው

Anonymous said...

በቀጥታ ማግኜት የሚችሉት በድህረ ገጽ ሳይሆን ቀጠሮ ይዛችሁ የት እንዳሉ ስለምታውቁ ማግኔት ይቻላል የሳቸው ነገር በጣም ወሳኝ መሆኑን ትክክለኛ የእግዚያብሄር ሰው የሆነ ሁሉ ያውቀዋል::

Anonymous said...

The right question at the right time for the right father. I and my friends have been discussing the same question a lot of times though we couldn't be able to answer. I hope God help him to do so. God bless him and all of us! Thanks Dejeselam for being the voice me and my friends.

እግዚኦ መሃረነ said...

ደጀሰላም አግባብ ያለው ጥያቄ ነው::

የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት ለመመለስ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ ወደ መንበራቸው መመለስ ግድ ይላል::
በዚህም ብሎ በዛ አባቶቻችን ይህን ችግር ፈተው ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት ከመለሷት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲመሰገኑ ይኖራሉ::

ይህ ችግር ሳይፈታ ግን አዲስ ፓትርያርክ ተመርጦ የውጭ የውስጥ የሚባለው ነገር ካልቀረ በሰው ሰውኛ በቼም አንድነት ሊመጣ አይችልም::

Anonymous said...

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው::

Anonymous said...

እውነተኛ ሃሳብ ግዜውንም የጠበቀ ነው ሁሌም በሃሳባችንም የሚመላለስ ነው ብዙውን ጊዜ መግለጫም የሚሰጡት አባ መልከጼዲቅ ብቻ ናቸው ለምን?

Nabutee said...

His Holyness Abuna Merekoriose great spiritual leader, he was strongly praying continuously , he is rearly speak to any one. he his not that much bothered but the power of the church even though he is the legal Patriarch of ethiopian orthodox church. but dejeselam why you need his voice for he is not street politician has big mouth and talk nonsense. his well educated in the church theology traditionally, he believes nothing powerful and stronger than prayer to God. God will do every thing in his behalf, do not be paranoid.

Anonymous said...

The question is appropriate. But the right response is No No and No to abune Merkorious return. The reason is clear. He is the man who divided the church. How can we expect him to make unity. He is the leader of rival groups. We can't allow them to further divide the church. Who is behind the dividing game is Tehadiso. Tehadiso groups can't lead our church. EOTC is ours and our fathers should take the leadership. GBU

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያንን የከፋፈላት ሰው እንዴት አንድ ሊያደርጋት ይችላል? እኛ የሚሰደድ ወይም የተሰደደ ሲኖዶስ የለንም ሊኖረንም አይችልም:: ቤተ ክርስቲያናችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጂ ፓትርያርክ አታመልክም!!!

temesgen ke London said...

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ላይ በድፍረት የምትናገሩ ሰዎች ብታስተውሉ ለ እናንተ መልካም ነው እላለው::

እሳቸው ምርጥ ኢትዮጵያዊ፣ የጸሎት አባት፣ የቤተ ክርስቲያናችን መሪ(ፓትርያርክ) ናቸው::

የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅ የተሰወረ የለም እንዳለው ወንጌሉ ከጥቂት አመታት በፊት እውነት ውሸት መስሎ የኖረበት ነበር ግን እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆነና ይኸው እውነት ውጥታ ታየች::

የድንግል ልጅ መድኃኔዓለም ከ እሳቸው እና ከቤተ ክርስቲያናችን ጋር ነው::

Meron from Norway said...

Bitsue wekidus Abune Merkorios higawiw Patriarik mehonachew yetaweke new ena esachew wede menberachew memeles alebachew::

EGZIABHER SELAMUN , FIKRUN, ANDINETUN yawurdlin!

Anonymous said...

አግባብ ያለው ጥያቄ ነው። የመዳን ቀን አሁን ነው ብል ቤተክርስቲያን ዕለት ዕለት እንደምታስተምረን፤ ዛሬ የቤተክርስቲያን አንድነት ልናረጋግጥ የምንችልበት ጥሩ አጋጣሚ ነውና "የእርቀ ሰላሙን ጉዳይ" አጽንዎት መሰጠት አለበት። ዳግም በታሪክም በስርዓትም ተወቃሽ እንዳንሆን የቻልነውን ያክለ እንስራ።

ተስፋዪ said...

መቼም አባታችን ወደ መንበራቸዉ ቢመለሱ ለሁለት የተከፈለችዉን ቤተክርስትያን ሉታደጓት ይችሉ ነበር::ነገር ግን ኦሳቸዉ ወደ መንበሩ የሚመለሱ ከሆነ በስራቸዉ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የመሰረቱትን ሲኖዶስ /ጳጳሳት/እንዲየት ያድርጉ ?ለዚህም ምላሽ ያሰፈልገዋል::ለማንኛዉም መድሀኒያለም በጎቹን የማይበትን:ጥሎ የማይሸሽ፡ በጎቼ ከሚበሉ እኔ የሚል :አባት እሱ ይስጠን እኛም በጸሎት እንትጋ::

Anonymous said...

Thank you- I agree!

ቤተ ክርስቲያንን የከፋፈላት ሰው እንዴት አንድ ሊያደርጋት ይችላል? እኛ የሚሰደድ ወይም የተሰደደ ሲኖዶስ የለንም ሊኖረንም አይችልም:: ቤተ ክርስቲያናችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጂ ፓትርያርክ አታመልክም!!!

Anonymous said...

I can't say it is not a proper question to ask. I said the same thing when I heard Abune Paulos's death.But if you think about it in depth, there are many things that needs to be done before that. For example if he (abune Merkorios)comes to Ethiopia and took the place, will he agree to avoid the using of organ(piano)in the church? B/c his voice (abune Melketsedek) supports the use of piano and there are churchs under sidetegnaw synod and use piano. I believe it is very easy for fathers in Ethiopia to forgive and take back these fathers(Abune Merkorios and papasat appointed by him)but will they agree to stop their distorted teachings about Ethiopian Orthodox church? Will aba Weldetensae (Menafik,who said....many wrong things about Dingil Mariam and our church cannons), confess for his deeds? I think that is the hardest part of dealing with Abune Merkorios and his followers in US (since most of them have minfikina and just follow abbe Merkorios for some benefit and for being papas one day. So we need to think about all these things before just saying abune Merkorios have to take the chair for our mother church peace.

Anonymous said...

Agibab yalew tiyakie new @ dejeselamawuyan. Sile betechirstian andinet hulachinim linasib yigebal,Egziabher yirdan. Amen!

Anonymous said...

DS have u seen this
https://docs.google.com/file/d/0B93cKtII07NHdGdLc2Nrdi1WblU/edit?pli=1
don't post it this is for your information

anonymous said...

where is Abune Merkorios?He was in Eritrea 2-3 days ago visiting armed Ethiopian oppositions and missing a church visit!!!.Abune paulos was politically aligned to the ruling party,EPRDF,no question as abune merkorios is to the DERG.I am no one to tell you this but,Please all Abunes leave politics to the politicians.YOU are supposed to be involved in your religious duties.is that not what Jesus preached?

yoseph said...

ደጀ ሰላሞችህ የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳቹና ቅዱስ ፓትሪያርክ የመምረጡን ነገር ለምን ለቅዱስ ሲኖዶስ አንተዉለትም ? እርቅ እና ሰላም ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ነው ያለው እግዚአብሄር ፍጻሜውን ያሳምርልን: ነገር ግን ''ድምጻቸው ቀላል ያልሆኑ ኦርቶዶክሳውያንም “እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊሰጥ ዕድል ከፍቶልን ሳለ፣ የቀደሙትን አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ ሲገባ የምን አዲስ ምርጫ ነው?” እያሉ ነው'' ላላቹት ማንም አላለም ከጥቂት እኛ ያልነው ካልሆነ ከሚሉ ሰዎች በስተቀር : እኛ እያልን ያለነው የማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት እጅ ሳይገባበት:እንዲመረጥና እግዚአብሔር እሱ የወደደዉን እና ለኛ የሚበጀንን አባት ይሹምልን ነው እያልን ያለነው: የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ደግሞ እርቁ በሰላም ተጠናቆ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትሪያርክ ይሁኑ ካለ ማንም አያግደዉም : ሁሉ ይቻለዋልና :ግን አሁንም ከላይ ያቀረባቹት ሃሳብ የሰዉን ልብ የሚከፋፍል እንጂ አንድ የሚያደርግ አይደለምና ፍጹም መንፈሳዊነት በተሞላ(ወገንተኝነት ባልተሞላ) አቀራረብ ብታቀርቡት የተሻለ ነው ባይ ነኝ: አሁንም ግን ከምንም በላይ ሃይማኖታችንም ሆነች ሃገራችን የሁላችንንም ጸሎት የምትሻበት ሰዓት መይስለኛል::

yoseph said...

ደጀ ሰላሞችህ የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳቹና ቅዱስ ፓትሪያርክ የመምረጡን ነገር ለምን ለቅዱስ ሲኖዶስ አንተዉለትም ? እርቅ እና ሰላም ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ነው ያለው እግዚአብሄር ፍጻሜውን ያሳምርልን: ነገር ግን ''ድምጻቸው ቀላል ያልሆኑ ኦርቶዶክሳውያንም “እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊሰጥ ዕድል ከፍቶልን ሳለ፣ የቀደሙትን አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ ሲገባ የምን አዲስ ምርጫ ነው?” እያሉ ነው'' ላላቹት ማንም አላለም ከጥቂት እኛ ያልነው ካልሆነ ከሚሉ ሰዎች በስተቀር : እኛ እያልን ያለነው የማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት እጅ ሳይገባበት:እንዲመረጥና እግዚአብሔር እሱ የወደደዉን እና ለኛ የሚበጀንን አባት ይሹምልን ነው እያልን ያለነው: የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ደግሞ እርቁ በሰላም ተጠናቆ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትሪያርክ ይሁኑ ካለ ማንም አያግደዉም : ሁሉ ይቻለዋልና :ግን አሁንም ከላይ ያቀረባቹት ሃሳብ የሰዉን ልብ የሚከፋፍል እንጂ አንድ የሚያደርግ አይደለምና ፍጹም መንፈሳዊነት በተሞላ(ወገንተኝነት ባልተሞላ) አቀራረብ ብታቀርቡት የተሻለ ነው ባይ ነኝ: አሁንም ግን ከምንም በላይ ሃይማኖታችንም ሆነች ሃገራችን የሁላችንንም ጸሎት የምትሻበት ሰዓት መይስለኛል::

Anonymous said...

In the name of father, Jesus Christ and the holly spirit Amen
Dear all Dejeselam brings the best issues for all to pray and to discuse each others and our father why others you are the only person that knows the reality በዚህ አጋጣሚ “ደጀ ሰላም” አንድ ሁነኛ ጥያቄ ማቅረብ ትፈልጋለች። የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? ድምጽዎትን ለምን አንሰማም? ሐሳብዎን ለምን አይገልጹም? ከምዕመኖችዎ ጋር በቱርጁማን፣ በስማ በለው፣ በተላላኪ፣ በሦስተኛ ወገን መነጋገር መቼ ነው የሚያበቃው ለማለት እንወዳለን። thank you dj

Anonymous said...

Given the current official statment of the fathers in exile (https://www.quatero.net/pdf/sle_Abune_poulos%5b1%5d.pdf), I am optimistic about a postive peace aggrement soon between fathers soon. So, let us keep encouraging that.We hope we will hear our father will speak when it is appropriate. I don't even see the point to open tee discussion on how and why His Holiness left the Seat as we already heard enough the arguments, which practically has neither spritual nor logical sense in either side. Let us go forward and look for reconcilation rather. May God help our fathers to resolve this issue wisely and let us see all fathers and children of the church pray together.

Anonymous said...

where is Abune Merkorios ?He was in Eritrea 2-3 days ago,visiting the armed oppositions and missing a church visit there!!!.Abune Paulos was aligned to the EPRDF,no question as Abune Merkorios is to the DERG.I am no one to tell you this,but please Abunes you are supposed to do your religious duties and defend the church from external influences.Leave politics to the politicians.Is that not what Jesus preached.You are supposed to preach love,forgiveness,tolerance and reconciliation ,not to be the source of dispute,hatred and division. LET GOD HELP US ALL.

Anonymous said...

Please hold your fire. Let him speak his mind as requested, which has been long overdue and we need to pray for reconciliation of our fathers whether he becomes the Patriarch or not. This division has hurt Orthodox Chiristians(especially in the Diaspora) to their bones. Let's always look at the Greater picture and wish that our church becomes unified again.

We need to put pressure on our fathers to bring this division into a halt. A new Patriarch might emerge with the blessing of bishops at home and in the diaspora or Abune merkorios could lead the church again for a couple of years until his death. Whatever the outcome, this is time for reconciliation and unity.

Anonymous said...

where is abune merkorios ?He was in Eritrea 2-3 days ago,visiting armed opposition groups and missing a church visit there !!!.abune paulos was aligned to EPRDF,no question,as as abune merkorios is to the DERG.I am no one to tell you this,but please abunes,you are supposed to do your religious duties and defend the church from external influences and leave politics to the politicians.Is that not what Jesus taught?.You are supposed to preach love,tolerance,reconciliation not to be the source of division and hatred .MAY GOD HELP US ALL.

Anonymous said...

ቀዱስ ሲኖዶስ እንደተፈለገ የሚወጡበትና የሚገቡበት ሆቴል ቤት አይደለም። ቤተ ክርስትያንን ሁለት ከፍሎ ቤተክርስትያን አብሮን ተሰዷል ያለ ሰው እንኳን ሕጋዊ የሞራል መብትም የለው።

Unknown said...

የደጀ ሰላም ጥያቄ አይከፋም ፣ ነገር ግን የአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሃሳብ ግን እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው። ገዳም ይግቡ፥ የኢትዮጵያን ሕዝብና ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ይጠይቁ የሚሉት አስተያየቶች ምንጫቸው የት ይሆን ? የበደለ ነው ወይስ የተበደለ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባው ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መሳሪያ ታጥቀው ከጫካ በመጡ ሃይሎች ከግዑዙ መንበራቸው ፥ ማለት መስሪያ ቤታቸው በሃይል እንደተወገዱ ራሱ ሥራውን የሠራው አቶ ታምራት ላይኔ ዛሬ እራሱ የምስክርነት ቃሉን እየሰጠ ባለበት ሁኔታ እንደ በደለኛ ይቅርታ ይጠይቁ መባሉ በእውነት ከክርስቲያኖች አእምሮ የሚፈልቅ ሃሳብ ነው ብለን ልንቀበለው ይገባል ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበረ ሥልጣናቸው አልተወገዱም። የተወገዱት ሰው ሰራሺ ከሆነው መስሪያ ቤት ነው። ምክንያቱም የፓትርያርክነት ሥልጣኑ መንፈሳዊ ስለሆነ ቦታና ጊዜ የሚሺረው ሥጋዊ ሥልጣን አይደለም። በሕይዎተ ሥጋ እስካሉ ድረስ የትም ሁነው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባት ናቸው። መንበር የሚባለው መንፈሳዊው ሥልጣን እንጅ አደራሹ ወይም ኦፊሱ አይደለም። ሥልጣነ ፓትርያርክነት ከኢትዮጵያ ውጭ አይሰራም ከተባለ እኮ ከኢትዮጵያ ውጭ የምንኖረው ካህናትና ምዕመናንም ክህነታችንና ክርስትናችን ከኛ ጋር ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው ። ቋንቋችንና ዜግነታችንን የማይጋሩ ቅብጦች እኮ ናቸው በተጭበረበረ የኒቂያ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ተወላጆች ጳጳስ ሊሾሙ አይገባም የሚል የውሸት ምክንያት አስቀምጠው ከ330 እስከ 1951 ዓ.ም. መርተውናል። ታድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር መንበሩ ? እንኳን መንበሩ ሰዎቹ ራሳቸው ኢትዮጵያውያን አልነበሩም። ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሆን መጣር ያለብን በሃይል የተጣሰው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተስተካክሎና ታርሞ፥ ሕጋዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባት ወደትውልድ አገራቸው ገብተው ቤተ ክርስቲያኒቱን አንድ አድርገው እንዲመሩና በዓለማውያኑ መካከል ያለው የፖለቲካ መለያየትም በብሔራዊ እርቅና መግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ከቅዱስ ሲኖዶሱና ካህናት ጋር ሁነው የሰላምና መረጋጋት ሥራቸውን እንዲሰሩ ያለው መንግሥት ትብብሩን እንዲሠጥ ነው መጠየቅ ያለብን። እንደ ማኅበረ ቅዱሳን የመሳሰሉት መንፈሳውያን ማኅበራትና እንደ ደጀ ሰላም የመሳሰሉ ድኅረ ገፆችም የሚጠበቅባቸው መንፈሳዊና ሃገራዊ ሃላፊነትም ይህ ነው። እግዚአብሔር ጨለማውን ያብራልን ። ለእውነትና ለሥርአተ ቤተ ክርስቲያን እንጅ ለግል ጥቅም ከመቆም እንጠበቅ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ዓሜን።

Anonymous said...

To Anony. @August 31, 2012 8:48 PM

"Where is Abune Merkorios? He was in Eritrea 2-3 days ago visiting armed Ethiopian " ... This is wrong information. His Holiness never been shown in any political stage as long as I know. The news you refered was about "Aba Mekarios" (one of the newly appointed bishops- not H.H.Abune Merkorios)

Anonymous said...

Kebede Bogale የተባሉት አስተያየት በጣም አስደስቶኛል የልቤን ነው የተናገሩልኝ!!!

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው እውን የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም እና አንድነትን ከሁሉም በፊት የምንናፍቅ ከሆነ!

እግዚአብሔር እየፈረደ ነው ይፈርዳልም!

Anonymous said...

Benegerachin lay tsehafiw betam ye abune paulos adnaki or degafi yimeselal.Lemehonu Likane Papas Abune Merkorios Ayitahachew takeleh. Ene ke 1dim sost gize yemayet agatami neberegn..Yihewum Bitsuwe Abune Zena Markos yemotu gize new. Normally, he doesn't speak. He is so humble but he sings really really great. Always when he come to Gebriel in Seattle, he sings including current Mezimurs. He has amazing voice. Otherwise, he never speak in public and it is Bitsuwe Abune MelkeTsedek who speaks for him. This is the way he is. He is so humble with amazing voice for songs as well as Kidase. I m blessed that I attended his Kidase. So for your question, the patriarich is like that and you will never hear him speak but when he sings or do kidase.

Anonymous said...

For one of the commentors, it is not Patriarich Abune Merkorios (መርቆሪዮስ) who is in Eritrea. It is Abune Mekarios(መቃሪዮስ) who went to Eriteria By the way, you are definitely woyane and tiraz netek. you dont even different the two names. Above all,yes God is a fighter. Bible is history of war, where God helps his people to be freed like from Egypt. There is no any contradiction if Abune Mekarios went to armed forces who are trying to liberate the country from the woyanes.

Anonymous said...

This is a good quesiton we need to pray&pray!!! together for our church

Anonymous said...

እዚህ ላይ ፕትርክና ማለት ለብዙ ሰው የገባው አይመስለኝም:: ፕትርክና በራሱ ክህነት አይደለም:: ብዙ ሰዎች ግን ክህነት አድርገው ስለሚያስቡ ወደ ተሳሳተ አስተያየት ይሄዳሉ:: መጀመሪያ ይህንን ማስተዋል ያስገፈልጋል::

Anonymous said...

We need a strong prayer. I hope God will answer our prayer. It is very difficult time. our spritual fathers aren't doing the right thing. I amn't accusing any side ,but generally their heart isn't ready for negotation. It sad ,but that is what it is.I strongely believe God will anoint a very good spritual leader to watch after his children. May God bless everybody.

Anonymous said...

የቤተክርስቲያን ህልውናና አንድነት በአንድ ሰው መውጣትና መግባት ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይገባም:: ቀድሞ እንደነበረው አይነት "የጎንደር ምንቸት ተመልሰህ ግባ..." የሚባልበት ዘመን አልፎአል:: ከቤተ ክርስቲያን የተሰደዱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ እንጂ ከስልጣን የተሰደዱ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ማድረግ የክርስትና ዓላማ አይደለም!!!

Anonymous said...

በእውነቱ አፋችሁን ሞልታችሁ ይመለሱ የምትሉ ልታፍሩ ይገባል:: በአሁኑ ሰዓት በእርሳቸው ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የማንም መፈንጫ ሲሆኑ እያየን ነው:: በእውነቱ አባ መርቆርዮስ እነዚህን በጣት የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን እንክዋን በአግባቡ ያልመሩ በምን መስፈርት ነው የሚመለሱት?

Anonymous said...

Abune Samuel is one of the new bred of abunes who is dedicated and can be a good leader.

hailu said...

May God bless Dejeselamawuyan for opening this extremely important discussion.

The division in our church for the past 20 years has brought an extraordinary damage. Some may not appreciate the gravity of the problem for various reasons. But for me it has been one thing that has been worrying me the most.

Such division may have delighted Satan and strengthened the enemies of our Orthodox Church; however, it has indeed weakened our church significantly. We need to end this once and for all. We need to stop saying 'yen entina betekirstian'. We must stop the bickering and stand united in defense of our mother church from real enemies who want to destroy her.

The division 20 years ago came into existence when the Church's canon law was disregarded Patriarch Merkorios was unjustly forced out of his office. Any other reason including ill health etc is discredited. We have now 20 years of experience how the government justifies the wrong it does by orchestrating drama like testimonies, court trials etc. One can read the wikileaks diplomatic document from the US embassy detailing the then PM Tamirat Layne confessing how the government caused the church's division.

The main thing now is how we can restore unity in our Church? Regardless of what we feel about one another, we must correct the wrong that led to the division of our church two decades ago. This can be achieved by returning Patriarch Merkorios to his 'menber'. We must do this for sake of uniting our church.

About Abune Merkorios: although many may have views based on emotions and without facts, he is a very humble human being, real monk, man of prayer, full of a lot of patience, graceful father and melkam kahn.

May God give wisdom to our fathers from either side to resolve our church's division.

May God help us and guide us in uniting our church.

Anonymous said...


Lets do this for the sake of uniting our church.

Lets not repeat the same mistake by electing another fake 'patriarch' while a legitimate one is alive and without fault.

May God Help Us.

Anonymous said...

Dear Dejeselamawiyan, tiyakew agibab yalew new..lenegeru enante kidus abatachin yet endalu tefetuachihu ayidelem...gin le hizbu meweyaya endihon yimeselegnal bemehonum endalachihut eskemeche be wekil siyanageru yinoralu wede adebabayi bik yibelu ena yinageru.....Ene bebekule Kidus abatachinin bagegnehut agatami lemanager mokere nebere..lemanager sil endew bagegnhut agatami sawerachew new enji bezih gudayi ansichelachew ayidelem...selezih selesachew tinesh yemawekatin linager....yagegnehuachew ene balehubet betekerstiyan le agelgelot metew hulete 3 wer koyetew hedewal ena keza bemenesat new hasaben yemisetew
1. Kidus abatachin beken 1 geze 6pm layi becha gimash enjera ayinu befetete ater kik wet yibelalu (beken 1 becha)
2. 1 kubaya tea (shayi) yalesekuar yitetalu keza banana (muz) yiwedalu beka yihew new kelebachew
3. Keza wechi sirachew tselot becha new (be agatami kesachew gar yemagelgelu huneta selenebere min yahil menfesawi abat endehonu bayine ayichalehu)
Keza wechi agerachew megibat betam yifeligalu endewim esachew siltanun minim ayifeligum Ethiopia gebetew gedamawi hiwot menor new yemifelgut gin kezih betach yastewalkutin chiger temelkichalehu
1. Besimachew yalewin Sinodos yemiyankesakisew " Abune Melke tsedek" tebeyew Like papas new, Seweyew betam adegegna ena kebad yehone le hager le wegen sayihon lerasu ena letikit giletseboch yekome new 9Melke tsedeku)..Kidus abatachin besimachew yemiserawin kuch belew kemayet yezelele minim ayinagerum yehe esachew bemimerut sinodos yetaweke new, enehu seweye 9Melke tsedeku) yalut yihonal yalalut ayihonim lesachew yaltegeza ayihonim becha esu ena tikiet geleseboch nachew sinodosun yemiyankesakisut
2. Kidus abatachin enkuan be sinodosu liyazubet lerasachew enkuan kuami bet yelachewim...tikit abiyatekerstiyanat becha nachew lesachew yemihon genzeb enkuan yemiyawatut (le elet elet nurochew
3. Besirachew alu yemibalut papasat begilachew yemiyastedadiruchew yerasachew betekerstiyan yalechew lelelaw gid yelelechew ena silatanu ke siga felagotachew gar yetemechache silehone ahun yebetekerstiyanuan selam yifeligalu beye ene alasibim...ene balehubet akababi 2 papasat esachew yeshomuchew alu..lisgachew enji le betekerstiyan minim gid yeleleachew yehe and ken bemereja gezew sideres yemikeirb yihonal gin abezagnaw hulum bayihonim yaw nachew....
Becha bezu malet bechalkugne bezu neger weste ale bachiru Egziabher yemifekid bihon yeselam nigigeru esachewinim yechemere bihon emenugne selam beketita yinmetal betarik esachew le siltan asibew ayawikum gin ene Melketsedek ena tikit sewech alu ahun sim megeletse bayasifeligim enantem tawekuchewalachu ena betechale wegentegna sanihon enihin talak abat kenezih lesigachew kaderu bezuriyachew ketekolekolu kemagna please lemalakek gezew ahun new...egna endeminasibew esachew lesiltan ayimetum ....becha asfelegai kehone techemai mereja lemestet mengedu kale zigeju negne ena hasabachihu tiru enem Kidus abatachin ebakewot zimetaw yibekal bayi negne.

Anonymous said...

የቤተ ክርስቲያንን መከፋፈል ምክንያት ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ያስፈልጋል:: አቡነ መርቆርዮስ የደረሰባቸው ችግር ከሀገር እንዲሰደዱ አድርጎዋቸዋል:: ከሀገር ከተሰደዱ በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያንን ሳይፋፍሉ /ሌላ "ሲኖዶስ"/ ሳይመሰርቱ መቆየት ይችሉ ነበር:: ስለዚህ መሰረታዊው ችግር የመሰደድ ጉዳይ ብቻ አይደለም:: በዚህ በምዕራቡ አለም የምንኖር ሁሉንም አሳምረን እናውቀዋለን:: የጥቅም የስልጣን የፓለቲካና የምንፍቅና ጥምረት ነው የመከፋፈሉ መንስዔ:: ያረጁ(Expired) ፓለቲከኞች መጠጊያ የተሰደደው 'ሲኖዶሳቸው' ነው:: ለቤተክርስቲያናችን የሚሆን አባት ግን እግዚአብሔር እንዲሰጠን ሁላችን እንጸልይ::

Anonymous said...

Who is the "legitimate" patriarch and who is the "fake" patriarch? Is Aba Merkorios, who left his children alone to seek his comfort, a 'legitimate' patriarch? እውነተኛ እረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል እንጂ ጥሎ አይኮበልልም:: Okay, he left us alone. We tolerated that. Why he organizes and catalyzes a 'fake' synod. A patriarch is assigned by a synod but can't establish a synod by himself.

Anonymous said...

WHY YOU GUYS AREGUING FOR NOTHING,WHY DON'T YOU PRAY TO OUR LORD JESUS CHIRST. WE CAN GET ANSWER FROM HIM, I HAVE A STRONG FATH WETHER YOU LIKE IT OR NOT HIS HOLYNESS ABUNE MERKORIOS WILL BACK HIS CHAIR SOON,THIS IS THE TRUTH AND FACT. JUST KEEP PRAYING...PRAYING...PRAYING...
GOD BLESS OUR CHURCH & OUR COUNTRY.

Anonymous said...

"99ኙን በጎች ኢትዮጵያ በትነው የጠፋውን አንዱን በግ (ስልጣን) ለመፈለግ ወደ ምዕራቡ አለም የሄዱት" አባ መርቆርዮስ እርሶም ነገ የሞት ፅዋ ተካፋይ ከመሆንዎ በፊት እባክዎን በዚች ቤተክርስቲያን ላይ የፈጠሩትን ችግር ያስተካክሉ::

Anonymous said...

The question is do we want our church to continue being like our politics or not. Should a monk who is supposed to be dead on earth leave his church, only because new politicians came to power? What was he afraid of? His life? Where is the church divided? The church is divided due to the former patriarch outside Ethiopia. Let us all pray to have a genuine church leader that will not be influenced or threatened by government.

B said...

የቤተክርስቲያን ህልውናና አንድነት በአንድ ሰው መውጣትና መግባት ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይገባም:: ቀድሞ እንደነበረው አይነት "የጎንደር ምንቸት ተመልሰህ ግባ..." የሚባልበት ዘመን አልፎአል:: ከቤተ ክርስቲያን የተሰደዱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ እንጂ ከስልጣን የተሰደዱ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ማድረግ የክርስትና ዓላማ አይደለም!!!

Anonymous said...

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በሀበ እግዚአብሔር! ክርያላይሶን

Anonymous said...

Thank you Dejeselam to post this message. I saw some friends who wrote Abune Merkoriwos must not come again? Why not? Please, be logical for what you have written blindly. Is Abune Merkoriwos responsible for the division? You are totally mistaken. It is the Woyane together with Aba Paulos divided and weakened the church. The only remedy is restoring the unity of the church. This is possible by keeping the rules and regulations of the church and implementing accordingly.Resolving the problem with the two synods is the basis to maintain church unity. Those who want the church to remain divided are not supporting the coming of Aba Merkoriwos. We Ethiopian Tewahido members know what has to be done.We hopefully give our voice to His Holiness Aba Merkowiwos. እባካችሁ ፖለቲከኞች ለቀቅ አድርጉን የምንሰራውን ጠንቅቅን እናውቃለንና የቤተክርስቲያንን ችግር እንፍታበት::

Anonymous said...

አቡነ መርቆርስ ለምንድነዉ የማይገሩት ?እሳቸዉ ዝም በማለታቸዉ ቦታቸዉን የተለያዩ ሰዎች ወክለዉ ይናገራሉና:ይህ ደግሞ ዛሬ ቤተክርስትያናችን ለደረሰባት መለያዬት ትልቁ አሰተዋጸዎ ካደረጉት ምክንያት አንዱ ነዉ::አሁንም ቢሆን ዝም ማለታቸዉ ቤተክርስትያናችን ወደ አንድነት የምታረገዉን ጉዞ የሚገታት ስለሆነ::ለቤተክርስትያን ጠላትቶች በርም ከፉች ስለሆነ::ስለስልጣን ስይጨነቁ ስለእግዝአብር መንግስት በመጨነቅ ቤተክርስትያንዋን ቢታደጓዋት ይሻላል::

Teklesilasie said...

Emotions aside, Let’s do this for the sake of uniting our church- have only one Patriarch at a time.

To some who comment above accusing Abune Merkorios,

Are you with your right minds to think that he was the reason for the church's division because of coming of late Aba Paulos?
This is 'woyaneyawi firde gemdilnet'.

The reason for the mess our church finds itself now was the transgression of our church's cannon law by the TPLF/EPRDF to assign their loyal fellow ethnic person.

For those who say Abune Mekrorios should not have gone into exile, I say going into exile is not new. The bible and history tell us spiritual leaders including Jesus had gone to exile.

For those who say Patriarch Mekorios should have died in Ethiopia, what is there to be gained by a purposeless death? What did we gain when the derg killed the patriarch before Abune Teklehaimanot?

May God give wisdom to our fathers inside and outside of Ethiopia to unite our church.

yemelaku bariya said...

መልሳቸው እዚህ ዋሺንግቶን ዲሲ ነዋ:: ነገር ግን ከመናገራቸው በፊት የአቡነ መልከጼደቅን ፈቃድ ማግኘት ስላለባቸው ለጊዜው መልስ ላይሰጡ ይችላሉ:: ቅዱስነታቸውን ያለ አቡነ መለከጼደቅ ማግኘት ቀላል የሚሆን አይመስለኝም:: አላግባብ ከመንበራቸው የተነሱት እሳቸው እንደመሆናቸው መመለስ እንደሚገባቸውና መመላሳቸውም ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ልዩ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ምንም ጥያቄ የለውም:: ነገር ግን ችግር የሚሆኑት በሕጸጽና በሌላም ከቤተ ክርስቲያን የተለዩት የተለያየ ምክንያት እየደረደሩ ቅዱስነታቸውን ከመግባት እንዳያግቷቸው እፈራለሁ:: የስደተኛው ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳ የአቡነ መልከጼደቅ መሪነት የጎላ እንደሆነና ቅዱስነታቸው እንደተሰብሳቢ እጃቸውን አውጥተው ሲናገሩ ያስተዋልንበት ጊዜ ሁሉ አለ:: እናም የአቡነ መልከጼደቅ መልካምፈቃድ መጨመር ሳይኖርበት አይቀርም::

Anonymous said...

መሰደዳቸው መች ከፋ፡ ቤተክርስትያን አብሮኝ ተሰዷል ብለው በቤተክርስቲያናችን ያልነበረ መከፋፈል መፍጠራቸው እንጂ። እንደወጡ መቅረታቸውን አውቀው አርፈው ይቀመጡ። ባለቀ እድሜ አጉል ተስፋ ምንም አይበጃቸው።

Anonymous said...

FAKADEHE YEHONE

Anonymous said...

No Christian would say no to peace! Please think about what you say before you say it! Action speaks louder yelalu..egziabeher libonawin yesten

Unknown said...

I think His holiness is in Asmara, Eritrea. The last place his eminence is expected. Instead of working for peace and uniting the church, his holiness abune Mekarios chose to travel to the butcher Isayas` country and encourage the mercenaries in Eritrea inflict more damage and bloodshed in Ethiopia. May his holiness reconcile himself and the "synod in exile" with the Ethiopian people.

Anonymous said...

If I am not mistaken the pop who went to asmara as you have said it called abune Mekarios not Bitsu wekidus abune merkorios.

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን ቅዱስ አባታችንን ወደ መንበራቸው መመለስ ነው መፍትሄው:: ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን አዲስ ፓትሪያሪክ ቢመረጥ ቤተ ክርስቲያናችን ከሁለትና ከሶስት ተከፍላ ትቀራለች::ሌላው ማወቅ የሚገባን ውጭ ያሉትም ወደፊት ቦታው ክፍት ሲሆን የራሳቸውን ፓትሪያሪክ ከመሾም ወደ ኋላ አይሉም:: ያ ማለት ደግሞ ተለያይተን ቀረን::

Anonymous said...

በተቀባው አባት በአቡነ መርቆርዮስ ላይ ትፈርዱ ዘንድ እናንተ እነማናችሁ? እሱ ባለፈበት አልፋችኋልን? እሱ የደረሰበት ደርሶባችሁ ታግሳችኋልን? እራሳችሁን በእርሱ ቦታ አድርጋችሁ ተመልከቱት ግብዝ አትሁኑ ደግሞም ይህ አባት የተጓዘው ጉዞ የእግዚአብሄር ፍቃድ ይሁን የሱ ፍቃድ መናገር የሚቻለው ማነው? ሃይማኖት የፖለቲካ እሰጣገባ አይደለም እባላችሁ ወገኖቼ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ትተን የቄሳርን ለቄሳር እንስራ እግዚአብሔር የኛ እርዳታ አያስፈልገውም::

Anonymous said...

በተቀባው አባት በአቡነ መርቆርዮስ ላይ ትፈርዱ ዘንድ እናንተ እነማናችሁ? እሱ ባለፈበት አልፋችኋልን? እሱ የደረሰበት ደርሶባችሁ ታግሳችኋልን? እራሳችሁን በእርሱ ቦታ አድርጋችሁ ተመልከቱት ግብዝ አትሁኑ ደግሞም ይህ አባት የተጓዘው ጉዞ የእግዚአብሄር ፍቃድ ይሁን የሱ ፍቃድ መናገር የሚቻለው ማነው? ሃይማኖት የፖለቲካ እሰጣገባ አይደለም እባላችሁ ወገኖቼ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ትተን የቄሳርን ለቄሳር እንስራ እግዚአብሔር የኛ እርዳታ አያስፈልገውም::

Anonymous said...

Daniel checkul selehone abune mekarios yetebalewune le abune merkorios seteto sehetet lay wodeke. Pleease know what you right about before you comment on a very delicate matter. This is really nonsense.

Anonymous said...

Daniel , you rush to comment. It is nonsense. please know about what you want to comment before you react and fail in to a big fault.

hailu said...

To Daniel tarikh and some above,

If you knowingly said the Patriarch went to Eritrea , I say you are not honest and you need to reconcile with yourself.

The Patriarch is His Holiness Abune MeRKOrios NOT MeKArios.

His Holiness DID NOT go to Eritrea as you falsely wrote above.

Tekle said...

To those who try to saw a seed of animosity between fathers,

I think we should refrain in wrong accusations and attempts to cause division between Abune Merkoriwos and Aba Melketsedek. This does not help resolve our church's problem. They are brothers in faith in good and bad times.

I also don't think Abune Merkorios should make a speech. For one thing he is not a man of opportunism who wants to grab attention just because a fellow human being has died.

No speeches from any side are necessary other than the expression of determined will to negotiations in solving the church's two decade old problem, the division.

The best venue will be through the EOTC Peace and Reconciliation Committee and it should be they who need to update us on the progress.

Anonymous said...


ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ የተራው የወቅቱ ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትም የለኝም:: ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

Anonymous said...

HAYLE በእውነት አቡነ መርቆርዎስ ተመልሰወ ቢቀመጡ ምንም ማለት አይደለም ነገር ግን እነ አባ ወልደ ትንሳኤን የመሰሉ የተሃድሶ ሰባኪያን እነ አቡነመልከጼዴቅ አይነቶቹን በኦርጋን የሚቀድሱትንና የቤተክርስቲያንን ስርአት ለማፉለስ የተዘጋጁትን ምን አድርገን ነው ይህንን ሀሳብ የምናነሳው? ወይስ ገብተው በኦርጋን እንዲቀድሱና አሳማ ብሉ የሚለውን ትምህርታቸውን እንዲያስፋፉ ነው? ደግሞስ ለሰላምና ለአንድነት ቢያስቡ ኖሮ አቡነ መቃርዮስ ወይም ወደ ኤርትራ እንዲሄዱና ጦሩን እንዲያበረታቱ ያደረጉት ይገርማል። ወደ ገዳም ሄደው ጸሎት ማድረጋቸው ነው? እንዲህ ልብ ካላቸው እዛው አይታገሉም ነበር ? ወይንስ እንደ መለስ ታግዬ ያገኘሁት ስለሆነ እኔ ነኝ ፖትርያርክ መሆን ያለብኝ ለማለት? አልገባኝም አላማቸው። በበኩሌ በጣም ነው ያፈርኩት። እርግጠኛ ነኝ አቡነ መርቆሪዎስ ይህንን ነገር አይደግፉትም። ወታደር ወይስ ጳጳስ? ስለዚህ ኢትዮጵያ ቢገቡና ስልጣን ቢይዙ ምን እንደሚሆን እናስብ። በአቡነ መርቆሪዎስ ስም ለመነገድ ስለሚፈልጉ ነው? እንደምንሰማው ግን እሳቸው በጣም ጸሎተኛ እንደሆኑ ነው:: እሳቸውም ቢሆን ገዳም እገባለሁ ከፈለጋችሁ ግደሉኝ ከሀገሬ አልወጣም ማለት ነበረባቸው::

Anonymous said...

ደጀ-ሰላም ሆይ! መሪያችሁ አባ-ገ/መድህን የሉም።በመፈንቅለ-ፓትርያርክ ለ 21 አመት በስልጣን ላይ የማይገባ ስራ ሲሰሩ ኖረው ሄደዋል። በሃይል ከመንበራቸው የተባረሩትን ብጹዕ ወቅዱስ ፖትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን በሃይማኖታቸው ስለ-ሃይማኖታቸው መሰደዳቸውን ግፈኛው ታምራት ላይኔ የመሰከረላቸው መሆኑን እንደ አዲስ አይነገራችሁም።መሰደዳቸውን ደግሞ ወልደ-እግዚአብሄር ኢየሱስክርስቶስም እንደ መለሰ ዜናዊ ግፈኛ በነበረው ሄሮድስ ዘመን ተስዷል።ሁሉንም ለእግዚአብሄር ብለው በጸሎት ስለተጉ ለምን እንካ-ሰላንቲያ አልገጠሙም ብላችሁ ብትባዝኑ ብፁእ አባታችን የሚሰሟችሁ አይመስለኝም አትድከሙ!

Anonymous said...

ለሃይማኖታቸው; አልተሰደዱም; ለጥቅማቸው ;ነው ምን; ተጎዱ ;ዘር ;ማንዘራቸውን; አውጥተዋል; ታዲያ; ቢመለሱስ?

Anonymous said...

please don"t fight brothers ,just pray .pray.pray ...GOD is only the problem solver,so give every thing to him. he is working, you will see what's going to happen soon....
GOD BLESS US AND OUR CHURCH.

Anonymous said...

please don"t fight brothers ,just pray .pray.pray ...GOD is only the problem solver,so give every thing to him. he is working, you will see what's going to happen soon....
GOD BLESS US AND OUR CHURCH.

Anonymous said...

Shame on you, menafik leba. Esachew ye haimanot abat engi yemengist balesiltan alneberum, bedergim gizea siltan alneberachewim

Anonymous said...

I share this comment.

የደጀ ሰላም ጥያቄ አይከፋም ፣ ነገር ግን የአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሃሳብ ግን እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው። ገዳም ይግቡ፥ የኢትዮጵያን ሕዝብና ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ይጠይቁ የሚሉት አስተያየቶች ምንጫቸው የት ይሆን ? የበደለ ነው ወይስ የተበደለ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባው ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መሳሪያ ታጥቀው ከጫካ በመጡ ሃይሎች ከግዑዙ መንበራቸው ፥ ማለት መስሪያ ቤታቸው በሃይል እንደተወገዱ ራሱ ሥራውን የሠራው አቶ ታምራት ላይኔ ዛሬ እራሱ የምስክርነት ቃሉን እየሰጠ ባለበት ሁኔታ እንደ በደለኛ ይቅርታ ይጠይቁ መባሉ በእውነት ከክርስቲያኖች አእምሮ የሚፈልቅ ሃሳብ ነው ብለን ልንቀበለው ይገባል ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበረ ሥልጣናቸው አልተወገዱም። የተወገዱት ሰው ሰራሺ ከሆነው መስሪያ ቤት ነው። ምክንያቱም የፓትርያርክነት ሥልጣኑ መንፈሳዊ ስለሆነ ቦታና ጊዜ የሚሺረው ሥጋዊ ሥልጣን አይደለም። በሕይዎተ ሥጋ እስካሉ ድረስ የትም ሁነው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባት ናቸው። መንበር የሚባለው መንፈሳዊው ሥልጣን እንጅ አደራሹ ወይም ኦፊሱ አይደለም። ሥልጣነ ፓትርያርክነት ከኢትዮጵያ ውጭ አይሰራም ከተባለ እኮ ከኢትዮጵያ ውጭ የምንኖረው ካህናትና ምዕመናንም ክህነታችንና ክርስትናችን ከኛ ጋር ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው ። ቋንቋችንና ዜግነታችንን የማይጋሩ ቅብጦች እኮ ናቸው በተጭበረበረ የኒቂያ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ተወላጆች ጳጳስ ሊሾሙ አይገባም የሚል የውሸት ምክንያት አስቀምጠው ከ330 እስከ 1951 ዓ.ም. መርተውናል። ታድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር መንበሩ ? እንኳን መንበሩ ሰዎቹ ራሳቸው ኢትዮጵያውያን አልነበሩም። ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሆን መጣር ያለብን በሃይል የተጣሰው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተስተካክሎና ታርሞ፥ ሕጋዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባት ወደትውልድ አገራቸው ገብተው ቤተ ክርስቲያኒቱን አንድ አድርገው እንዲመሩና በዓለማውያኑ መካከል ያለው የፖለቲካ መለያየትም በብሔራዊ እርቅና መግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ከቅዱስ ሲኖዶሱና ካህናት ጋር ሁነው የሰላምና መረጋጋት ሥራቸውን እንዲሰሩ ያለው መንግሥት ትብብሩን እንዲሠጥ ነው መጠየቅ ያለብን። እንደ ማኅበረ ቅዱሳን የመሳሰሉት መንፈሳውያን ማኅበራትና እንደ ደጀ ሰላም የመሳሰሉ ድኅረ ገፆችም የሚጠበቅባቸው መንፈሳዊና ሃገራዊ ሃላፊነትም ይህ ነው። እግዚአብሔር ጨለማውን ያብራልን ። ለእውነትና ለሥርአተ ቤተ ክርስቲያን እንጅ ለግል ጥቅም ከመቆም እንጠበቅ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ዓሜን።

Anonymous said...

"99ኙን በጎች ኢትዮጵያ በትነው የጠፋውን አንዱን በግ (ስልጣን) ለመፈለግ ወደ ምዕራቡ አለም የሄዱት" አባ መርቆርዮስ እርሶም ነገ የሞት ፅዋ ተካፋይ ከመሆንዎ በፊት እባክዎን በዚች ቤተክርስቲያን ላይ የፈጠሩትን ችግር ያስተካክሉ::

Anonymous said...

ለሃይማኖታቸው; አልተሰደዱም; ለጥቅማቸው ;ነው ምን; ተጎዱ ;ዘር ;ማንዘራቸውን; አውጥተዋል; ታዲያ; ቢመለሱስ?

Anonymous said...

ቀዱስ ሲኖዶስ እንደተፈለገ የሚወጡበትና የሚገቡበት ሆቴል ቤት አይደለም። ቤተ ክርስትያንን ሁለት ከፍሎ ቤተክርስትያን አብሮን ተሰዷል ያለ ሰው እንኳን ሕጋዊ የሞራል መብትም የለው።

dl said...

God has spoken for him.

Anonymous said...

በስደቱ ዓለም ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ሌሎች አባቶች እንዲሁም አማካሪዎቻቸው የሆኑ ካህናትና ምእመናን ቤተ ክርስቲያኗ በአቡነ ጳውሎስ እልፈት ተጠቅማ ወደ አንድነቷ ዛሬ ባትመለስ ሊደርስ የሚችለውን ለዘለቄታው የመለያየት አደጋ እንደሚገነዘቡት ይታመናል። ከአሁን በኋላ ለብዙ ዓመታት ቀርቶ ለወራትም ቢሆን ተወጋግዞና ተከፋፍሎ ከዕርቅ፣ ከፍቅርና ከሰላም ተለይቶ ለመኖር መሞከር በቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነትና አንድነት ላይ መፍረድ ይሆናል።
ከሃምሳ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በስደቱ ዓለም ሆኖ መምራትና ማገልገል እንደማይቻል የታወቀ ነው። በውጭው ዓለም የሚኖሩትን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩትን ምእመናን ከኢትዮጵያ መምራትና ለወደፊቱም የቤተ ክርስቲያኗን ትምህርት ማስፋፋት ግን ይቻላል። በፊትም ለዘመናት ተደርጎ ነበር። ዕርቀ ሰላም ወርዶ አንድነቷ ካልተረጋገጠ ቤተ ክርስቲያኗ ከአሁን በኋላ ለዘለቄታው ሳትከፋፈል የውስጥና የውጭ በሚባል ስያሜና አመራር አንድነቷ ተጠብቆ ልትተዳደር አትችልም። ውጭ ያሉት ምእመናንም ቢሆኑ ከኢትዮጵያ ሊርቁና ተደማጭ ሰብሳቢ ሊያጡ ስለሚችሉ በየአጥቢያው ተበታትነውና ተዳክመው ይቀራሉ። ዛሬም ቢሆን በውጭው ዓለም ብዙ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖች በየራሳቸው የውስጥ ደንብ ብቻ መተዳደራቸውና የአመራሩ መሰላል በሚገባ አለመጠበቁ እጅግ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው።
ስለዚህ ዛሬ ልዑል እግዚአብሔር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ለዕረቀ ሰላሙ የበላይ አባትና መልካም አርአያ እንዲሆኑ ስለመረጣቸው ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነትና አንድነት የሚበጀውን የተቀደሰ ውሳኔ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በራሳቸው አንደበት በቅርቡ እንዲያበሥሩና ለዕርቀ ሰላም ቡራኬ እንዲሰጡ እንማጸናቸዋልን። የቤተ ክርስቲያኗን ሕግጋት ማክበርና ማስከበር የሚቻለው በሰላም፣ በፈቅርና በዕርቅ ነው። ስለዚህ ዕርቀ ሰላም ይቅደም።
1050

Anonymous said...

It is nice so many people want to see Unity and are sick of the division. I hope people would appreciate and respect the fact that going on mass media OR talking to interviewers is not necessarily the right way to communicate with the people and specially for Spiritual fathers. The committee working on getting the two groups together is talking to both groups. We should respect Abune Merkorios's way of not engaging in interview OR dialogue that is usually taken out of context and also not appropriate to his level. Let him work with the committee and the mass media is not the appropriate place for him at this moment.

I hopt it is God's will and time for unity and we should focus on praying and also not damaging the process, also push our individual churches and the committee to work faster and better in the negotitation. We should stop pressuring him to come to mass media.

Tesf

hailu said...

Dejeselam,

I suggest that you post your article with a recent picture of His Holiness Patriarch Merkorios instead of an old picture that does not show his current persona and grace. You can easily get it in the web,please visit http://eotcholysynod.info/home/.

May God help us unite our church. Amen.

Anonymous said...


Deje Selam & Readers,

I happen to be very close to His Holiness and get to see him every Sunday when he is in town (mostly his stay is my hometown)

His Holiness is the man of God who prefers praying/fasting than talking and politicking. I, as individual, believe what has been transpired has a lot to do with his personality.

While I am disgusted by most of our fathers (I said most, cause I know there are few Men of God) and lost faith in them; both here abroad and in Addis.

He never utters any conversation that leads up to his future. NEVER.

I have no doubt, in the end; things will have a better ending to the church.

Deje Selamoch;

I know all the discussions about why His Holiness should return or why he shouldn’t return and all the arguments. It's true that one could take my comment as a biased feeling to His Holiness. I can attest to everyone for a matter of fact that His Holiness cares NOT about power or position. He does not. His handless might. Actually they do care about power and position than anything. But His Holiness DOES NOT.

This is beyond power or anything. FOR THE SAKE OF THE CHURCH UNITY, ADVOCATE FOR THE RETURN OF HIS HOLINESS AND REUNITE THE CHURCH. He is an aged man of God and electing another patriarch will for ever and ever damage the church. If a new patriarch is elected while His Holiness is alive, who is to say those here abroad won't elect another Patriarch if/when His Holiness passes away? It will be historical suicide for the church. We can NOT afford to miss this opportunity.

I hate to say this and may God forgive me for saying this but I realized the EOTC is led by 85% wolfs and 15% men of God. The numbers are not scientific but I personally know many who are just plain men who fall for money, power, and worldly things rather than serve the Lord.

This unification will serve as a healing the wounds and close doors to those heretics who are using this leadership gap as a way to spread their venom.

Anonymous said...

Deje Selam & Readers,

I happen to be very close to His Holiness and get to see him every Sunday when he is in town (mostly his stay is my hometown)

His Holiness is the man of God who prefers praying/fasting than talking and politicking. I, as individual, believe what has been transpired has a lot to do with his personality.

While I am disgusted by most of our fathers (I said most, cause I know there are few Men of God) and lost faith in them; both here abroad and in Addis.

He never utters any conversation that leads up to his future. NEVER.

I have no doubt, in the end; things will have a better ending to the church.

Deje Selamoch;

I know all the discussions about why His Holiness should return or why he shouldn’t return and all the arguments. It's true that one could take my comment as a biased feeling to His Holiness. I can attest to everyone for a matter of fact that His Holiness cares NOT about power or position. He does not. His handless might. Actually they do care about power and position than anything. But His Holiness DOES NOT.

This is beyond power or anything. FOR THE SAKE OF THE CHURCH UNITY, ADVOCATE FOR THE RETURN OF HIS HOLINESS AND REUNITE THE CHURCH. He is an aged man of God and electing another patriarch will for ever and ever damage the church. If a new patriarch is elected while His Holiness is alive, who is to say those here abroad won't elect another Patriarch if/when His Holiness passes away? It will be historical suicide for the church. We can NOT afford to miss this opportunity.

I hate to say this and may God forgive me for saying this but I realized the EOTC is led by 85% wolfs and 15% men of God. The numbers are not scientific but I personally know many who are just plain men who fall for money, power, and worldly things rather than serve the Lord.

This unification will serve as a healing the wounds and close doors to those heretics who are using this leadership gap as a way to spread their venom.

Anonymous said...

"ቀዱስ ሲኖዶስ እንደተፈለገ የሚወጡበትና የሚገቡበት ሆቴል ቤት አይደለም። ቤተ ክርስትያንን ሁለት ከፍሎ ቤተክርስትያን አብሮን ተሰዷል ያለ ሰው እንኳን ሕጋዊ የሞራል መብትም የለው።"

May God forgive you, for not know what you are saying.

All I can say while tears on my eyes.

Clover said...

This is really a great read for me. Thank you for publishing articles having a great insight stimulates me to check more often for new write ups. Keep posting!

Clover
www.n8fan.net

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)