August 28, 2012

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል

  • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
  • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

በወረዳው የጸጥታ ኀይሎች “ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ፤ ታጋይ ገድላችሁ እናንተ በሰላም አትኖሩም፤” እየተባሉ መደብደባቸውን የተናገሩት የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት÷ በተለይም ከነሐሴ 18 ቀን 2004 ዓ.ም በሚፈጸምባቸው ድብደባ በርካታ አባቶች መጎዳታቸውን፣ ከተሰደዱት ስድስት መነኰሳት መካከልም አባ ገብረ ማርያም ጎንዴ እና አባ ገብረ ጊዮርጊስ የተባሉ አባቶች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ማኅበረ መነኰሳቱ ከሰኔ 21 ቀን እስከ ኅዳር 8 ድረስ በሚዘልቀው የሱባኤ ወቅት ላይ ይገኛሉ፤ የመንግሥት ሓላፊዎችም በተለመደው አነጋገር “ዳዊታቸውን እንደ ዘቀዘቁ ናቸው፤ መቅሠፍቱም ይቀጥላል” ብለዋል በሚል የገባው በማይወጣበት፣ የወጣው በማይገባበት ይህን የሱባኤያቸውን ወቅት እንኳ ሳይታገሡ ነው ድብደባውንና እንግልቱን የሚፈጽሙት፡፡

በአቶ መለስ መሐንዲስነት እንደተቀየሰ በተነገረው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የአንዱስትሪ ልማት ዘርፍ አካል ከሆኑት ዐሥር ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎች አንዱ የኾነው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት÷ በገዳሙ ህልውናና ክብር ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋና ታሳቢ ስጋቶች የተነሣ ሐዘናቸውን ወደ እግዚአብሔር በማመልከት የቆዩት አበው መነኰሳት የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር አባላት ናቸው፡፡

ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡40÷ በሚኒስትሮች ም/ቤት መለጫ መሠረት ድንገት በተከሠተ ኢንፌክሽን÷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመምና ኅልፈት “የመነኰሳቱ እንባና ሐዘን ወደ እግዚአብሔር ከመድረሱ የተነሣ የመጣብን ተግሣጽ ነው” ብለው የሚያምኑ ወገኖች ቁጥር በቀላሉ የሚገመት እንዳልሆነ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚታዩ የመረጃ ልውውጦች እና ከኅልፈታቸው ጋራ ተያዘው የሚደመጡ ፈርጀ ብዙ ትርክቶች እያጠየቁ ናቸው፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

25 comments:

Anonymous said...

“የመነኰሳቱ እንባና ሐዘን ወደ እግዚአብሔር ከመድረሱ የተነሣ የመጣብን ተግሣጽ ነው” ብለው የሚያምኑ ወገኖች ቁጥር በቀላሉ የሚገመት እንዳልሆነ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚታዩ የመረጃ ልውውጦች እና ከኅልፈታቸው ጋራ ተያይዘው የሚደመጡ ፈርጀ ብዙ ትርክቶች እያጠየቁ ናቸው፡፡

Anonymous said...

“ዳዊታቸውን እንደ ዘቀዘቁ ናቸው፤ መቅሠፍቱም ይቀጥላል”

hailu said...


Meche yihon yihe giff yemiabekaw?

Lemins balesilatanochu libachewun ende Feron adenedenut?

Sew behageru, emnetun tebiko,hulun tito begedam menor ayichilim?

Gifachewun eskeketelu dires Egziabher seifun yizeregal.

They keep messing with Waldiba, the Woyanes will follow suit with Aba Paulos, Meles, etc.

Anonymous said...

Abetu Amkak Hoy Tebake Melakhen lakelegn ale Kidus Dawit on the last Psalm.

Abetu Amlak Hoy YekerBelen!!! Abetu Amlak Hoy begochehen tebek ebakeh.

Kebede Bogale said...

ኦሪት ዘጸአት ላይ ተጽፎ ያለውን የፈርዖንና የሙሴን ታሪክ አየደጋገምኩ እንዳነበው ይህ በዋልድባ ገዳም መነኮሳትና በወያኔ /ኢሐደግ መካከል ያለው ሁኔታ አስገደደኝ። በቤተ ፈርዖን ስንት አይነት መቅሰፍቶች ነበረ የተላኩበት ? መጨረሻስ በ1270 ከክርስቶስ ልደት በፊት በማን አሸናፊነት ድርጊቱ ተፈፀመ ?

Anonymous said...

I always ask what happened to us (Tewahedo Christian believers)? When are we getting mad and rise up for our right and our true faith? How long we just keep on reading this kind of story and do nothing about it except just feel sorry?

Oh God! Please give us strength and help us to stand for our church. Amen!

Anonymous said...

Ene yemilew? Egzer endi miketa bihon weym mot mkchaw bihon engdia egna zelalemawyan nena!Tewu poleticanina haymanotin atkeytu. Lemehonu ezaw gedamu wust ersbers slslew rejim gize yekoye kififilna ersbers dibdib takalachu? Engdia Egzer endet yhin zim ale? Antenna enens bezihulu hatyatachin endet tagesen? Ene bebekule maninim altelam. beteley kemotu behuwala sile PMu yesemahuwachew negeroch betam germewgnal. Tewu keEgzer wenber enwred? Bebekule mekseft kale yemejemeryaw mekseft yemigebagn ene negn.Enantes yedejeselam azegajochina anbabiwoch, tsadkanina yaltekesefachut kemotut wegenoch silemitshalu yhon? Lib ysten.

Anonymous said...

Ye mimeka be Egziabeher yemeka. Enezihe aheyoch begulbetachew temeketewal. God is going to judge on that, which is already known that He decided and there time is up. Years ago there was a vision seen that meles and his groups going up in the sky like a rocket going to the moon, but fall like a winter tree to the ground on it's own with out nobody touching it. Actually that is what happned the past few days. Thanks to the great God of the poor and oppresed. No worries the Waldibas are Semaetat.

Anonymous said...

"Ene yemilew?" yalkew wendeme/ehete esti nigeregn. Koy enezih menekosat letedebedebut, leteseqayut mene hazenete satasay ledebdabiwochu mazeneh meen yebablal? Yehe neew Cristiyanawi feqer malet? Le Dawit sayhon Le Goliyad mazen?

Anonymous said...

Kadrewoch Ke Egziabher gar megedaderu bibekachewu min ale!? Ere betekirstianin lekek adrguat. Yekirstos bet titilalechi enji befisum atwodkm.

hailu said...

It looks the chief financier of the controversial sugar factory around Waldiba, Sheik Al Moudi, has died. Ethiopian review has announced it as breaking news.

If this is true, God is speaking in plain terms. Joro Yalew Yisma.
Leave Waldiba and the monks alone!!!


Pattern recognition:

Meles who loved to be in control of everything and showing up for every meeting was nowhere to be found when rumor was rampant about him being dead. Woyanes resisted at first claiming that he was well and still in charge but eventually admitted that he was dead.

If Al moudi was well or alive, there would not be any way that he would be absent among the mourners. Woyanes are showing pictures of anyone seemingly mourning but Al moudi is nowhere to be seen. Come on, he would be among the first to praise the dictator. It is most likely true that he is either dead or incapacitated.

God's judgment on those who desecrate his holy places!

Anonymous said...

እንዴት ነው እኒህን ሕዝቦች የሚያደርጋቸው፤ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንደተባለው።
የገዳም መነኰሳት እንደ አቶ ኦሳማ ቢላደን በመንግስት ላይ የአጥፍቶ መጥፋት አዋጅ አላወጁም፤ መንግስት ነው እንጅ አጽም እየቆፈረ እያወጣ እግዚአህሔርን ያስቆጣውና እግዚአብሔር የጥፋት መአት ያወረደብን።
ይህ የብሔርተኝነት ትእቢት ከእግዚአብሔር ጋር ግብግብ መያያዝ ከፈለገ እግዚአብሔር እንደ መንግስቱ ኃይል ማርያም ወደ ሲኦል የሚሮጥ አይደልም ወደ ሲኦል ያስሮጣል እንጂ።
አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጅ ናቸው፤ ጉዳቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ይህ ትክክል አይደለም የትግራይ ብቻ ልጅ ናቸው የሚል ካለ፥ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንደማዎጅ ነው። የዘረኝነት መንፈስ ከሁለቱም አባቶቻችን ጋር አብሮ መቀበር አለበት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ "ዘረኝነት በቃኝ!!!" ብሎ በ አንድነት መነሳት አለበት።

Anonymous said...

ኧረ ስለ ጉልበታችሁ አምላክ አባቶቻችንን ተዉልን!!!!!!!!!!!!!! ስለምን ልባችሁን እንዲህ አደነደናችሁ? ፈርኦን ሆይ ልብህን ለእግዚአብሔር እስካላስገዛህ ድረስ መጥፊያህን ታበዛለህ፣ ቁጣውን በላይህ ታነዳለህ። አባቶቻችንን ተዉልን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! እሺ ወደ የት እንሂድ???

Anonymous said...

የእዚአብሄር ቃል በ ፩ ሣሙኤል ምእራፍ ፪ ቁጥር ፲ እንደሚነግረን፣ "ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።"

hailu said...

Dear my orthodox sisters and brothers,

Let not cry bitterly. God has heeded the voice of the monks who chose to live monastic life but are being harassed and tortured by the Woyane cadres.

We should pray for guidance from God. We must also do our part. Remember, if it were not for those fathers of ours who chose to die in defense of Orthodox when Atse Susinios decreed Catholicism as the national religion, our Orthodox faith would have been history. However, Christians of the time died in defense of the Orthodox Church. By their action with the help of God, they were able to restore Orthodox faith pass it onto generations including ours.

We must rise up in defense of our monasteries. Should we sit by and watch as the monks are being forced to abandon their monastery? When will we say enough is enough?

By our inaction to defend it, we seem to have made the sacrifice of our fathers look like was for nothing.

Compared to our fathers we have become coward generation who choose to talk about history made by our fathers but do nothing while such history and great assets of our church are being desecrated and destroyed.

Anonymous said...

Ye abatochache amlak le'ule EGZIABIHER hoye bedelachenen yikir belen yalante meshesham meketam yelen. Amnalehu ye Ethiopia Orthodox TewahidoBetekiristiyan hulem bekindochih endemititebek. Manim tunchawun biyaferetim, serawit biyasemara liyanawutsat indemayichel.

Lelijochuam kin lebonan, andinetinina fikrin tiseten zend inleminhalen.

Ketselot lela min mesariya alen!!

Anonymous said...

Here is wisdom stop abusing our fathers and mothers.If the government must not stop, the second phase is very dangerous. pLease be advised back off now. Very dangerous phase is coming !!! Nobboday will not stop it!!! We will not call international communities they are already nailless, boneless and teethless tiger and lion. The God of Israel ELOHIM angels are stand by please be advised 1, 2, 3, 4, 5, 5, 6, 7 " please please. We are not a member of any political parties leave the EOTC alone now!!!
When Ethiopia calls ELOHIM LISTEN HER

Anonymous said...

YALETADALO BALASELETANE....NESEHA GEBO

Anonymous said...

DAGEMAWE FAREONE YASAZENALE

Anonymous said...

abatoche besadadeo basega nawe wayawe laenaneta....

Anonymous said...

EGZIOOOOOOOOOOOO....

Anonymous said...

YAKEDOSANE AMELAKE EREDANE,,,,,,,,,,,,

Anonymous said...

መቼም ሰዉ ድርሻዉን መስራት ሲገባዉ በተለያዩ ዓለማዊ ሞክንያቶች ሊሰራ ባለመቻሉ እና ለሀይማኖቱ ደንታ ቢስ በመሆኑ :እግዚአብሔር ደግሞ በቤቱና በቅጥሩ:በቅዱሳኑ ሲመጡበት ዝምም አይልም::ቅዱሳን አባቶቻችን ዓለም አልተገባችንም :በዚች ዓለም ከመኖር ከአ ምላካችን ጋር መኖር ይሻለናል ብለዉ ገዳም የገቡትን መነኮሳት ሴጣን በሰዎች ላይ አድሮመኖርያቸዉን ሊያተራምስ:ቅዱሳኑን ሊበትን የክተት አዋጅ አወጀ ::ዓምላካቺን ለቅዱሳኑ የሰጠዉን የቃልኪዳን መንፈሳዊ ገዳም ሲጣን ለስኳር እርሻ ተመኘዉ ::ተመኝቶም አልተወም:መነኮሳቱን አሳደደ አሰረ :ገዳሙን አፈረሰ ::መነኮሳቱ ሁሉን ቻይ ወደሆነዉ አምላካቸዉ በምድር መፍትሄ ሰላላገኙ የእንባቸዉን ዘለለ ወደ ሰማይ ረጩ ::እንባቸዉ በከንቱ አልቀረም በሚያስገርም መልኩ ሀያላል ነን ያሉትን አዋረድ:ፍርዱ አላለቀም :: ነገርግን የአምላክን ፍርድ ተቃዉሞ ጥቁር ለብሶ በአደባባይ
ወቶ ነፍስን የወሰድክ አምላክ ልክ አይደለህም ቢሉት ለበለጠ ሀዘን አሳልፍ ይሰጣል::ሞች ነገርግን ክርስትያን ከሆነ በሚያመክበትየአምልኮ ቦታ ወስዶ ፀሎተ ፍትሀት ማድረግ እስላም ከነበሮ እዝያዉ በመስጊዱ ምንም ዉስጥ ከሌለ የወሴፍ :ከዚያ በተረፈ ሌላዉ በአለም ታይቶ የማይታወቅ ሴጣንም አይቶትም ሰምቶትም የማያዉቀዉ የቀጠሮ ለቅሶ ነዉ

Anonymous said...

abatu yenezihe kedusane telote sema ,endehatiyatachene bezate atasebene Egizizbehar amlake selekedusanu zeme ayeleme3

Anonymous said...

ጥሪ ማድረጉ ባልከፋ::
ምን ይበሉ ነው ጉትጎታው? እንዲሉ የምንፈልገውን እንዲሉን ነው? ወይስ ማለት ያለባቸውን እንዲሉ? የት ይመልሱት ጥያቄውን? ከነዚህ ሁሉ ጋር መልሱን ቢያደርሱንም ባያደርሱንም:: እንደ እኔ ሦስት ነገሮች ጥንቃቄ ይፈልጋሉ እላለሁ አራተኛ ጥቆማዬን አክላለሁ

የመጀመሪያው ድምጻቸውን የሚያሰሙት አረጋዊ አባት ዝምታን የመረጡት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል:: ያለዚያ ማለቂያ ወደሌለው የማይረባ ትንተና እንገባለን:: ሌላ የመለያየት ምክንያትም እንመዛለን:: ስለዚ ለዝምታቸው የራሳችንን ትርጉም ያለመስጠት ጥንቃቄ ያስፈልገናል:: ይህ ማለት ዝምታ መብታቸው ነው አይደለም::

ሁለተኛው ላሰሙት ድምጽ የሚኖረን ምላሽ ነው:: ምንም ይበሉ ትልቁ ነገር ይሆናል አይሆንም? ያዋጣል አያዋጣም በሚል ሚዛን የሚመዘን ሊሆን አይገባም:: የተሻለ የሚሉትን ምርጫ መርጠው ይህን የመለያየት የታሪክ ምእራፍ እስክንዘጋ በልዩ ልዩ መንገዶች ሊገደዱ/ሊገፉ/ ይገባል:: መልሳቸው የራሳቸው ብቻ ሊሆን አይችልም ማለት ነው:: ሊጠበቁ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል:: ወደድንም ጠላንም የቤተ ክርስቲያን ናቸው:: ስንቸኩል እንዳንስት ጥንቃቄ ያሻናል::

ሦስተኛው በአቡኑ ዙሪያ አካባቢና ከአቡኑ ጋር ያሉ ተያያዥ ጉዳዮች ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል:: በዙሪያቸው ፖለቲከኞች ዘረኞች ጥቅመኞች ጥገኞች /ምን አለፋቹ ብዙ ኞች አሉ::/ . . . መኖራቸው አሌ አይባልም:: ስለዚ በቀላሉ ብቻቸውን ድምጾትን አሰሙ: ኑ: ያን አድርጉ ያን ፍጠሩ ልንላቸው የምንላቸው አደሉም:: በጥንቃቄ ይታሰቡ መታሰባቸው ከዝንጋኤው አይከፋምና:: አካባቢያቸው ያለበት ሁኔታም አለ ቤተ ክርስቲያን ተከፍላ በወገን የምትጠራ ሁናለች:: ይህም ጥንቃቄ ያሻዋል:: ድምጻቸውን ሲያሰሙ በጥንቃቄ ሊታሰቡ ይገባል:: ሌሎቹ ከሳቸው ጋር የሚነሱ ነገሮች ናቸው:: አቡነ መርቆርዮስ ሲባል ትውስ የሚለን ነገር አለ:: በምንም ምክንያት ይሁን ሲጀመር መንጋ ነው በትነው የሄዱት:: ካገር ሲወጡም ትልቁን የታሪክ ስህተት ፈጽመዋል:: መንበር ተሰደደ ብለው ለመከፋፈል ምክንያት ሁነዋል:: እንደ አባት ገዳም ስንጠብቃቸው ነው አሳይለም ሲከር መሆናቸውን የሰማነው:: እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ታሪካዊ ስህተቶችን ፈጽመዋል:: ድምጻቸውን ቢያሰሙም ባያሰሙም እነዚህን ትዝታዎቻችንን በጥንቃቄ የማየትን አስፈላጊነት ልጠቁም እወዳለሁ::

አራተኛ የግሌን አሳብ ለመስጠት በሪሞት እንዲመሩን በፍጹም አልመኝም:: እንደ ደከሙ እርግና እንደተጫናቸው አስባለሁ:: በግድ ካላሉ በቀር አሁን ያለችውን ቤተክርስቲያን ለመምራት ሕሊናዊ ዝግጅት ይኖራቸዋል ብዬ አልገምትም:: ከብዙ ውጥንቅጡ ጋር:: አሁን ከተቻለ ቤተ ክርስቲያን ራሷን በብዙ መንገድ የምታይበት ውስጧን የምታጠራበት ወቅት ነው:: በመሆኑም ዋናው መሪነታቸው አይመስለኝ:: የመለያየት የመጣላት የመወጋገዝ አባዜው ቀርቶ በመረጡት ገዳም ተቀምጠው በጸሎታቸው ቢራዱን:: አባትነታቸው የኢትዮጵያ ምእመናን በመሆኑ ለሕልውናቸው ከለላ ካደረጉዋቸው ጥቅመኞች ይልቅ እንዲያደሉልን መልእክቴ ነው:: መደራደሪያ ያደረጉዋቸው ሌሎች ናቸው:: ለምን መጠቀሚያ ይሆናሉ? የዛፎቹ ዓይነት እጀታ ሁነው እያስገደሉን ነው:: በፖለቲካ መጥረቢያ መች እንመታ ነበር? አባታችን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም እድል መስጠት ይችላሉና ያዘንነውን ያስደስቱን የተከፋነውን ያጽናኑን:: ማኅበራት አባቶችና ሌሎች የምትችሉ ሁሉ በተለይ በቅርበት የምታውቋቸው ግፊት በመፍጠር ብንተጋገዝ ሥጋዊ አሳብ ነው ብዬ አልገምትም:: ድርሻ ድርሻ አለንና ::

ከደሴ መድኃኒዓለም ወልድ ዋህድ ሰ/ትቤት

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)