August 27, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥርዐተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል


(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  ነሐሴ 15 ቀን 2004 . ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ... ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር፣ እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 . በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡ 

የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት በፌዴሬሽን /ቤት በሰጠው መግለጫ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2004 .ም፣ ከቀኑ 1100 - ምሽት 100 ድረስ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው መርሐ ግብር የተለያዩ አብያተ እምነት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ሥነ ሥርዐት መዘጋጀቱን የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ አባላት ለዜና ሰዎች የሰጡት መረጃ አመልክቷል፡፡

እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 . በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚፈጸመው ሥርዐተ ቀብርም እስከ አሁን ድረስ 20 ያላነሱ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እንደሚገኙ ማረጋገጡን የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ ገልጧል፡፡ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት እየከተከናወነ በሚገኘው የሐዘን መግለጽ ሥነ ሥርዐት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ቀናት እየተገኙ ጸሎት በማድረግ አጽናንተዋል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ፤
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

13 comments:

Gebre Z Cape said...

If Meles Zenawi would know all such plans. I think he could have wrote on his wills saying please not a single person (specially from church) to mourn my death. Anyways, minale bayakabidu ena asikirenun betolo bekeberut.

Anonymous said...

ሰላም ደጀ ሰላም
ከ ባለፈው የፓትራርኩ ቀብር ስነ ስራዐት ቀብሩ ያማረ እንዲሆን ቤተ ክህነቱ ጥረት ማድርግ አለበት። መረሀግብሩ እትዮጵያዊን እና አለም ሁሉ የሚየው በመሆኑ ጥንቃቄ መደርግ አለበት። የሚከተሉት ነገሮች ላይ ትኩረት ቢደርግ፡
1. ከጸሎት ፍታት በተጨማሪ የሚቀርቡት ወርቦች ትርጉም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ተተርጉሞ ለ እቲቪ ዘጋቢ እና መረሀ ግብሩን ከመድርክ ለሚመራ ቢሰጥ...ወርቡ እየቀርበ በማሀል ምን እያሉ እንደሆነ መልክት ያሰተላልፋሉ
2. መድርኩ በተቻለ አቅም ሰፊ ቦታ ቢኖረው = መድርኩ ላይ የሚሆኑት የተወሰኑ ብቻ ቢሆኑ - ሚዲያዎች በሌላው አግር እንደሚደርገው አንድ ስፍራ ብቻ ቢስጣቸው - የተቻልውን ተክንሎጂ ከ እርቀት ሆኖ ተጠቅሞ ቢከረጽ - ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ የውጭ እንግዶች፣ የ መለስ ቤተሰቦች ብቻ እና ወርብ የሚያቀርቡት በቻ መድርኩ ላይ ቢሆኑ መልካም ነው እላለሁ። አስበውት ዪሆናል እንዲያው ለመተንፈስ ነው


3.

Anonymous said...

Endetewadedu
teterartewu hedu!

Tazabi said...

He is not even christian EKO! Take his body to Tigray we don't need him

Anonymous said...

እንዴ ሰውየው ክርስቲያን ነበሩ? ታዲያ ምነው ቤተክርስቲያናችንን ሲያምሶት ኖሩ?! እኔ ግን አይመስለኝም። ያፈሩት መራራ ፍሬያቸው ስለሁሉም ይናገር የለ እንዴ። ነው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከእምነቱ ውጭ የሆነ ሁሉ መቀበሪያ ነው? እኔ ሳውቅ ዩሴፍ የሁሉም መቀበሪያ መሆኑን ነው።
አንድ ጥያቄ ለደጅ ሰላሞች፤ ከምር ፓትሪያሪኩ ከነሙሉ ልብሳቸው ነው የተቀበሩ? ከሆነስ ደንብ ነው? እስኪ አንድ በሉኝ። ከምስጋና ጋር።

Anonymous said...

ወይ ጉድ ፣ይህ ዓርዮስ አንዴት ስላሴ ይቀብራል ፧
ስላሴ አኮ የሃገር ሞራል የለለው ሰው ዓይቀበርም ነበር። ዓይ ጊዜ ሰላም በፀሎት ዓይመጣም የሚል ዓገር ያጠፋ ፣ህዝብ የገደለ፣ ከሃዲ አንዴት ስላሴ ይቀበር ከቶ

Anonymous said...

Komew balawekut ena ligedluat basabu'at Betekirstian liqeberu new:: Nefsachewn yimar!

Anonymous said...

So!!!!!!!! Sorry!!!!!!!! the selfish Ethiopians. You were running everywhere; White house, embassies, State Department and all over to condemn Meles and Abba Paulos. You said Abebe Gela.... Now Obama, Opposition groups and individual did nothing to him or them, but The Almighty GOD gave his decision and took them both almost at the same time for ever out of this world. That was your wish. On the contrary, I heard all your comments including most activists and church people and many more said I felt sorry on their death. So with this situation, are you all now quarreling with God? Because He took them away forever up on your cry and request??????You think you are being nice? You think you are going to haven with this "I felt sorry" Comment?
Look!!!! God never makes mistakes don't forget he is pure. These two guys are criminals and got what they deserved. His followers, who lied to the people and want to continue his did are criminals too who are going quick same way as them, because God do not like their evil activity.

Listen either be hot or cold, if you are luck warm I will spit you out of my mouth said GOD. Believe it or not those of you who tried to be on both sides, know what is going to happen to you. What blinded you to forget about all the the 20 and 21 years of going into poverity and facists style administration? Even though I have a lot to say, let me cut it short here and leave you to think a little bit better. I can not say thank you at all.

hailu said...


The two people who were at the helm of power created havoc to our church for the past two decades.

God has taken them away.May God bless their soul. May God bring peace to EOTC and Ethiopia.

Anonymous said...

well said brother"atfred yefrdbhale"

Anonymous said...

ሁለተኛ ላይ አስተያየት የሰጠኸው ወንድሜ ወይም እህቴ:-
ቤተክርስቲያን ፍትሀት የምታደርሰው በTV እንዲታይላት ሳይሆን ነፍሱ በሰራው ሃጢአት ምክንያት ወደ ሲኦል እንዳትገባና አምላክ በቸርነቱ ወደ ገነት እንዲከታት ወደ አምላክ ለመማጸን ነው:: ቤተክርስቲያን አላማዋ የምታደርሰውን ጸሎት አለም እንዲያይላት አይደለም:: ቢቻል እንደውም ባይቀረጽ ይመረጣል:: ስርአት ላልከው ቤተክርስቲያን ሁሌም የስርአት ባለቤት ናት:: ህዝበ ክርስቲያኑም ሁሌም ስርአት ያለው ነው:: በጉልበታቸው የሚመኩት አቶ መለስና ተከታዮቹ ናቸው በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ስርአት ልበኝነትን እያስፋፉብን ያሉት:: በተለይም ላለፉት 21 አመታት በቤተክርስቲያን በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ስርአት አልበኝነት በነአቶ መለስ አማካይነት ሰፍኖባት ቆይቶአል:: ቤተክርስቲያን ስርአትን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአለም ማስተማር የምትችል ናት:: የምትናገሩትን ነገር አስባችሁ ተናገሩ::

Anonymous said...

My dad and Abune Pawelose were friends before Abune entered Enda Aba Girma Monastery ....no doubt, He is 76.

Anonymous said...

የደጀ ሰላም ጽሑፍ አቡነ ጳውሎስን ለመተካት የሚደረገው ምርጫ ጊዜ ይሰጠው፣ መምሪያም ይውጣ ብሎ ይመክራል። የሚያቀርበው ምክንያት ምርጫው ከተጣደፈ እንዳለፈው ጊዜ አሁንም ወያኔ ለጥቅሙ የሚበጀውን ወገኑን ያስመርጣል/ይሾማል የሚል ነው። መጠንቀቁና አለመጣደፉ በመሠረቱ የሚደገፍ ነው። ግን ለችግሩ በቂ መፍትሔ አይደለም። በሚራዘመው ጊዜ ውስጥ በቅደም ተከተል የሚፈጸመው ሥራ ምንድነው? በተባለው መምሪያ ውስጥ የሚካተቱትስ ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድናቸው? ለነገሩ መምሪያ መቼ ጠፋ መፈጸሙና ማስፈጸሙ እንጂ?! ጊዜው ቢራዘምስ ወያኔ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣልን? እርሱስ በረጅሙ ጊዜ አይጠቀምበትምን? ከሁሉም ይበልጥ የሚያዋጣው የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ ጠባቂ የሆኑ አባቶች ሁሉ በዘር፣ በጎጥ፣ በጥቅምና በመሳሰለው ሁኔታ እንዳይከፋፈሉ፣ ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሲሉ ሰላም፣ ፍቅርና ሐቀኝነት አስፍነው አንድነታቸውንና የቤተ ክርስቲያኗን ደኅንነትና አንድነት ተግተው እንዲጠብቁ መርዳት፣ ማግባባት፣ መከታተልና ሥርዓት አክብረው እንዲያስከብሩ ሁኔታውን ሁሉ ማመቻቸት ነው። የቤተ ክርስቲያኗ ሕግና ሥርዓት ይከበር ሲባልም በሀገር ቤትም ሆነ በውጭው ዓለም ያሉትን አባቶች ያካትታል። አቡነ ጳውሎስ ከተለዩ አቡነ መርቆሬዎስ መንበራቸውን ሊይዙ ይገባል የሚል ዜና ከተሰደዱት አባቶች ይደመጣል። ይህ ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነትና አንድነት ሲባል ከጠቅላላው የእርቅ፣ የሰላምና የፍቅር መሠረት ጋር አብሮ የሚታይ ወቅታዊና እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ለአፈጻጸሙ በቂ ጊዜ መውሰድ ተገቢነው፤ ነገር ግን ከብዙ መከራ በኋላ ቸሩ እግዚአብሐር ለቤተ ክርስቲያኗ የሰጣት ዕድል እንደገና እንዳይባክን ኃላፊነትን በወቅቱ መወጣት ያስፈልጋል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)