August 19, 2012

የቅዱስነታቸውን ዕረፍት አስመልክቶ የኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ


ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ 115፥6)
የአምስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስን ዕረፍት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ። 
ነሐሴ 11/2004 ዓ/ም Aug 17/2012 (READ IN PDF)

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
እንዲሁም በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለሚኖሩ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን በሙሉ።
          በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በአምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማውን ከፍተኛና ትልቅ ኃዘን ይገልጻል። እንደሚታወቀው ቅዱስነታቸው ለቤተ ክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻል፣ መጠናከርና መስፋፋት የሚጠቅሙ በርካታ መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑ  ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን አባትና  የሥራ ሰው ነበሩ። በመሆኑም ቅዱስነታቸው በአገልግሎት ዘመናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ሐዋርያዊ ተግባራት ምን ጊዜም ሕያውነታቸውን ሲያስታውሱ ይኖራሉ። ቅዱስነታቸው ብሔራዊውን የአብነት ትምህርትና ዘመናዊውን ዕውቀት አገናዝበው የተማሩ ታላቅ ሊቅ ስለነበሩ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ቅዱስ አባት ነበሩ፤ ይልቁንም ባለንበት ዘመን ቤተ ክርስቲያናችንን በዓለም መድረክ ወክለው ያከናወኗቸው ብዙ ሥራዎች ዘወትር ሲታሰቡ ይኖራሉ። ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን እኒህን ታላቅ አባት በድንገት በማጣቷ ልባዊ ኃዘናችንን በድጋሚ እንገልጻለን። በእውነቱ የቅዱስነታቸው  ድንገተኛ ዜና ዕረፍት ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ  ኃዘን ነው።
          ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በቅዱስነታቸው አባታዊ ቡራኬና በቅዱስነታቸው በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ ሦስተኛውን ዙር የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሳለ ይህንን ቤተ ክርስቲያንን አንድ የሚያደርግ ታሪካዊ ሒደት ለፍጻሜ ሳይበቃ የቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት መስማቱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳዝኖታል፤ ሊያስከትል የሚችለው ውጣ ውረድም ከወዲሁ አሳስቦታል። ቅዱስነታቸው የጀመሩትን የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጥረት የመጨረሻ ፍሬ ሳያዩ በድንገት በማለፋቸው ኃዘናችን ወሰን የለውም። የሰላምና አንድነት ጉባኤው በቅዱስነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የጉባኤውን የኃዘን መግለጫ የሚያደርሱ ልዑካንን  ሰይሞ ለመላክ በአንድነት ወስኗል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን አሁን ካለችበት አሳሳቢ የልዩነት ፈተና ይበልጥ ወደ ባሰና ወደ ከፋ ችግር እንዳትሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ተቀዳሚ ሥራው በማድረግ ለዘመናት በአንድነቷ ጽንታ የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ታሪኳን ለመመለስና ለማደስ ተገቢውን ሥራ በአንድነት እንዲሠራና እስካሁን ድረስ የቆየው የልዩነት ምዕራፍ እንዲዘጋ፣ በቅዱስነታቸውና በቅዱስ ሲኖዶስ በጎ ፈቃድ የተጀመረውን የሰላምና አንድነት ሒደትም ለፍሬ ያበቃው ዘንድ ጉባኤው ከታላቅ አደራ ጋር ይማጸናል።
በመሆኑም የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መላው ካህናትና ምእመናን ወምእመናት ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ያስተላልፋል።
1ኛ/ በቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማንን ጽኑ ኃዘን እየገለጽን ከምንም በላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዋነኛውና አንገብጋቢው ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ማድረግ መሆኑን በአጽንኦት እንገልጻለን፤  እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ባለፈው ሐምሌ ወር ሦስተኛውን ጉባኤ አበው ለማካሄድ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነበር። ይሁን እንጂ በግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የላክነው ደብዳቤና ባለ ሰባት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳቦች በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም የሚገኙት አባቶቻችን በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመገኘት ሙሉ ፈቃዳቸው መሆኑን ገልጸውልን ነበር። በዚህ መካከል ግን በአዲስ አበባ በኩል በሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረቡትን ሰባቱን የመፍትሔ ሐሳቦች አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በወርኃ ሐምሌ መግቢያ ላይ ተነገጋሮባቸው በአፋጣኝ መልስ እንደሚሰጠን በደብዳቤ ተገልጦልን ነበር። ያንን መልካም ዜና በጉጉት እየተጠባበቅን ሳለን ይህ ድንገተኛ ኃዘን ቤተ ክርስቲያንን ገጠማት፤ አሁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሦስተኛውን የዕርቀ ሰላም ውይይት በወርኃ ጥቅምት ከሚካሔደው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በፊት ለማካሔድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። በመሆኑም በመላው ዓለም የተበተነችውን ቤተ ክርስቲያን አንድ ለማድረግ፣ በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ የሚገኙት አባቶችም በቅርቡ በሚዘጋጀው የሰላምና አንድነት መድረክ ተገናኝተው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ተነጋግረው፣ ችግሩን በውይይት በመፍታት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ያደርጓት ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል።  

2ኛ/ ቤተ ክርስቲያን ለወደፊቱ ተለያይታ እንዳትቀር በሀገር ውጭና ከሀገር ውስጥ ባሉት አባቶች መካከል ያለው ልዩነት በአንድነት ሳይፈታ ሌላ ፓትርያርክ የመተካቱን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወዲሁ በከፍተኛ አትኩሮት እንዲያስብበት፤ ይልቁንም የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት በማጽት የቀድሞውን የአንድነት ታሪክ ይመልሱት ዘንድ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ስም ከልብ ይማጸናል።
3ኛ/ በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትም ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠበቅበትን የበኩሉን አስተዋጽኦ በአግባቡ እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን።
4ኛ/ በመላው ዓለም ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ማኅበረ ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን አንድ በማድረጉ ታሪካዊ ሒደት ላይ በጾም፣ በጸሎትና በሚያስፈልገው ማናቸውም ነገሮች ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ይሠሩ ዘንድ በትሕትና እንማጸናለን።
 በመጨረሻም አምላከ አበው እግዚአብሔር የቅዱስነታቸውን ነፍስ ከማኅበረ አበው ኄራን እንዲደምርልንና ለመላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለቅዱስነታቸው ቤተ ሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን።
የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ያሳየን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ።


25 comments:

Anonymous said...

GIRUM MELIKIT WEKETAWINA NEGEROCHIN YAGENAZEBE BETIBEB YETEMOLA MEGELECHA...AMEN AMEN AMEN!!!!

Anonymous said...

ለዚህች ቤ/ክርቲያን መድሃኒቷ እውነት እና እግዚአብሄር ናቸው። እውነትን እንናገር፤ አንሸነጋገል። ቀኑን ሙሉ እኛ ተራ ምህመናንን ካህናት የሚሉንና የሚሰብኩን እኮ በአውደምህረት አንድ ነገር ነው፤ አጥአት ከሰራቸውሁ ሲኦል ትወርዳላችሁ ነው። ይህ እኮ ለነርሱም ይሰራል። እውነትን እንንናገር። አ ቡነ ጳውሎሶ መቀመቅ ይወርዳሉ ብለው የሚሉ ወንድም እና እህቶች ዛሬ ደግሞ ባህል ሆነና ፤ “ ከቅዱሳን ጎን ያኑርልን”፤ “ነብሳቸውን ይማርልን” ብላ ብላ ብላ ። የሆዳቸሁን ተናገሩ። አትሸንግሉን። ይበቃል። ማንን ነው የምንፈራው። አስር ብር የሰረቀ የመንገድ ሌባ’ ሲኦል ይግባልን እያልን፤ ቅዱስ ቤ/ክርስቲያንን ለበተኑ፤ ነፍስ ላጠፉ፤ ወጣቶችን ለአውሬው ወያኔ አሳልፈው ለሰጡ፤ ጉበኛ አባት; “ ከቅዱሳን ጎን ያኑርልን” የምንለው። እኔ የሽማግሌ አላዋቂ አያናደኝም፤ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን፤ ወጣቶች ስንፍዙ አልወድም፤ አቡነ ጳውሎስ፤ ስ ኦል እንዲወርዱ ጸልያለሁ። እኔ 16 ሰአት የምሰራ፤ 16 ዘመድ የምቀልብ አማኝ፤ ይጸለይልኝ፤ ስራዬ አያጸድቀኝምና፤ ብዙ ብሆንም።፡22 ሚሊዮን ዶላር የከመሩት ጳውሎስ፤ ስ ኦል ይወርዱልን፡፤ ስ ኦል ለዚህ እኮ ነው የተሰራዎ፤ ካመንበት፤ ደደብ አትሁኑ፤ ከአህያ አንነስ።

Anonymous said...

ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

Hailu said...

Thanks to the EOTC Peace and Unity Committee.

Aba Paulos is called by his creator, may God bless his soul. Judgment is for God.

I am sure we all agree in saying the division of our church is a shameful history. The division of the church happened due to the assignment of a second "patriarch" while Patriarch Merkoriwos is still alive.

Ending this division and uniting our beloved church must be the most important thing to do.

Another fake election against the canon law of our church will guarantee the perpetuation of the grave mistake that shook our church to the core for the past 20 years.

The wise and courageous thing to do is to restore Patriarch Merkoriwos and heal the wound of our church once and for all.

This is the only best way we should advocate for the sake of our church. I am sure there are opposing views and emotions, but we must think beyond our emotions and do the right thing to unite our church.

May God bless our Orthodox Church. May God give our fathers the wisdom to put our church before their personal wishes. May God help us, Orthodox Christians, to do our part to unite our church. Amen.

Anonymous said...

Who are these atalay Kahinat. Degmo eko “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ 115፥6)
Bilew Metsafachew new. Tiksun lemenger endehone Egnam enawukewalen. Yalawekiyt gin leman metsaf endalebet new...

Anonymous said...

"ሌለ ፓትርያርክ ከመሾሙ በፊት" የሚለው የአሜሪካውን "አቡን" ለመመለስ ታስቦ ከሆነ ቅድሚያ መንግስቱ ሃይለማርያምን (ደርግን) መመለስ ግድ ያስፈልጋል እላለሁ::

Anonymous said...

Restoring Aba Merkorios can't be an alternative solution. His exile is totally political, not religious. The presence of Abune Paulos was not the cause of the exile. We must not think 20 years back. We have to think for the future. Other ways creating unit should rather be considered. We need young, educated and dynamic patriarch. God Bless you.

Anonymous said...

ለነፍስ ያደሩ አባቶች ያድርግልን(እዚህ ውጭ ከእኛው ጋር ያሉትን)፤ አሁንም የፓትሪያርክ ወንበር እንደፖለቲካው መደራደሪያ መሆን ለምን?።
ሌላው፤ እውነት "የሰላምና አንድነት.." ሸምጋይ መስሎ ይህ ካልሆነ የሚል ከሆነ ምኑን ከምን አረገው?? አባቶቻችንና ቤተ ክርስቲያን በሃዘን ላይ እያሉ ይህን አይነት የተጨማለቀ (ምላሴን ቆንጠጥ) መግለጫ?። ሌላው ቢቀር "አፈር እስኪለብስ"ን ማን አስረሳቸው?።
ደፋርነት ነው(ምላሴ ይቆንጠጥ)።
መቼስ ሀገር ያሉ አባቶችም ይህ ይጠፋቸዋል ብዬ አይደለም።
... ለሞቱ አባታችን ነፍስ ይማር
ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም

ቴክሳስ

ዘሐመረ ኖህ said...

አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም ወደ ገላትያ 6፥ 7
ይሄ የሸምጋዮች ነው ወይስ የሸንጋዮች መግለጫ አባ ጳውሎስ ያልሆኑትን ሆኑ። ያልሰሩትን ሰሩ። ማለት በሰውም በእግዚአብሔርም መቀለድ አይደለም ወይ፤ ክፉ ባህል ሆኖ ማንኛውም ሰው ሲሞት ክፉውን ደግ፤ ቂመኛውን ይቅር ባይ፤ ተንኮለኛውና መሰሪውን የዋህ፤ ለውድቀት ምክንያት የነበረውን የእድገት ምሳሌ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረውን ቅዱስ እያልን ማወደስ የምንተወው መቼ ነው፤ ቢያንስ የሃይማኖት መሪ የነበረን ሰው ባልሰራው ሰራ፤ ባላደረገው አደረገ እያልን በሰውና በእግዚአብሔር መዘበትን ብናስቀር ምን አለበት። እርቀ ሰላም እንዳይፈጠር ዋነኛው እንቅፋት ሆነው መኖራቸውን የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ሳለ ...ቅዱስነታቸው የጀመሩት የቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጥረት የመጨረሻ ፍሬ ሳያዩ መሞታቸው... ማለት በእግዚአብሔርም በሰውም መዘበት ነው እውነት የኢ/ ኦ/ ተ/ ቤ/ክ በአባ ጳውሎስ ዘምን አደገች ወይስ ለሁለት ተከፍላ ቁልቁል ወረደች፤ አጽራረ ቤተክርስቲያን የበለጠ የተመቻቸው ሙስና፣ ዘረኝነት፣ የመንፈሳዊና ቁሳዊ ክስረት፣ ዝቅጠትና ምዝበራ የሰፈነበት ስንት ገዳማትና አድባራት ተርበውና ታርዘው አባ ጳውሎስ ግን በውድ ልብስ ተሽቆጥቁጠው ጥይት በማይበሳው መኪና የተሸራሸሩበት፤ መንግስት ነኝ የሚል ባለበት ገዳማትና፣ አብያተክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ ካህናትና ምእመናን የታረዱበት፣ሕዝበ ክርስቲያኑ እንደ ጧፍ ነደው እንደ ሻማ ቀልጠው አቤት ባይ ያጡበት፤ መንግስት ሆነ ብሎ የዋልድባን ገዳም ለማጥፋት የዘመተበት ወዘተ ዘመንን ነው አባ ጳውሎስ ... ለቤተክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻል፣ መጠናከርና መስፋፋት የሚጠቅሙ በርካታ መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑ ... የተባለላቸው። በጣም ያሳዝናል አባ ጳውሎስን ወደ ንስሃ ካልመራቸው ምክንያቶች መካከል ይሄ ሁሉ ውዳሴ ከንቱና የማእረግ ድሪቶ ስለተቆለለባቸው ይመስላል ልባቸውን ለንስሃ ማቅናት የተሳናቸው። አባ ጳውሎስ በውጭም ለምእራባውያኖቹ ስለተመቿቸው የማእረግ ብዛት ቆለሉባቸው በሃገር ቤት ያሉት እነ ኤልዛቤልና መሰሎቿ ... የዋህ፣ ቅን፣ ሩህሩህ፣ ደግ፣ ይቅር ባይ፣ ሐሰት በአንደበታቸው የማይዞር ቅዱስ አባት... በማለት ሃውልት አስቀርጸው በማቆም ወደ ማመለክ አቀረቧቸው። በቂመኛነታቸው ብፁአን አባቶችን በስውር ያስገድሉ፣ ያስደበድቡ፣ የቤተክርስቲያኗን ሊቃወንትን ሙልጭ አርገው አባርረው ለችግርና ለሞት ከዳረጉ በኋላ በተሃድሶ መናፍቃን፣ በዘርና በጉቦ የተኩትን ፓትርያርክ ደግ የዋህና እሩህሩህ አሏቸው። በንፉግነታቸው ብዛት አያሌ ሊቃውንት ተማሪዎቻቸውን በትነው ወንበራቸውን አጥፈው በችጋር እንዲሰደዱ አደረጓቸው። አያሌ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጧፈ መግዢያ አጥተው ካሀናቱ የ50 ብር ደሞዝ አሮባቸው አብያተ ክርስቲያናቱ እንዲነጥፉ ያአደረጓቸውን ፓትርያርክ ሩህሩህ አሏቸው።የሰው ደም ያለባአውን አባት እንዴት ቅዱስ እንላቸዋለን ። ኧረ ለመሆኑ የአባ ጳውሎስ ግፍና ጥፋት ተዘርዝሮ ያልቃል ? አያልቅም። ምን አለበት ትንሽም ብትሆን የሰሯትን ጥሩ ስራ ካለች እሷኑ ጠቀሶ ማመሰገን ቢቻልና በእግዚአብሔርና በሰው ላይ ባንዘብት ። 20 አመት ሙሉ በተቃጠለና በቆሰለ አንጀታችን ላይ ጨው መነስነስ ግፍ አይሆንባችሆም እናንተ እንደምትሉት ...ቅዱስነታቸው በአገልግሎት ዘመናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ሐዋርያዊ ተግባራት ምን ጊዜም ሕያውነታቸውን ሲያስታውሱ ይኖራሉ።... ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ ጥለውት የሄዱት ጠባሳ ምንግዜም የሃይማኖታችንን ታሪክ እንዳጠቆረ ይቀራል ያውም እያመረቀዘ ካላስቸገረ በስተቀር። ደግሞ ... ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ቅዱስ አባት ነበሩ፤ ... ማለታችሁ አቤት ውሸት! የቤተክርስቲያናችን ነቀርሳ cancer ነበሩ ብንል ማጋነን አይሆንም። ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር መዝ 115፥6 እያላችሁ በድፍረት በእግዚአብሔር ላይ አትዘብቱ ይህ ቃል ለአቡነ ጳውሎስ ፈጽሞ አይገባም። አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል ገላትያ 6፥7 ። ሲጀመርም አባ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለኢሕአዴግ እጅግ አስፈላጊ አባት ነበሩ የቤተክርስቲያን አባት ሆነው አያውቁም። ለ20 ዓመት የኢሕአዴግ አባት ነበሩ። 20 ዓመት ሙሉ የኢሕአዴግን ፖሊስ ሲፈጽሙና ሲያስፈፅሙ ነበሩ። ለዚህም ነው አባ ጳውሎስ ትምክህታቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን በኢሕአዴግ በተለይም በጠ ሚ መለሰ ዜናዊ ላይ እንደነበረ ከራሳቸው ከአባ ጳውሎስ አንደበት ስንሰማው የኖረ ነው። የኢሕአዴግ መንግስት ደግሞ ከጫካ ጀምሮ 17 ዓመት በበረሃ፣ 21 ዓመት በስልጣን ወይም በመንግሥትነት በሃገራችንና በቤተክርስቲያናችን ላይ ግፉን የሰራብንና እየሰራብን ያለው ። እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ገለጻ ከአብዮቱ በኋላ የትግራይ ሕዝቦች ነጻ አውጪ ግንባር ሕወሐት ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ መካከል ያላትን ሚና እና አብዮቱን ከሚቃወሙ ኃይሎች ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት ተረዳ። ግንባሩ በሚያደርገው ትግል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከመንገዱ ላይ እንደተደነቀረች እና በጥንቃቄ ሊይዛት እንደሚገባ አወቀ። ቤተ ክርስቲያኒቱን የትግሉ አካል እና ደጋፊ ማድረግ እንደሚገባው ተገነዘበ። ስለዚህም ሊያዳክሟትና እና ለዓላማው መሳካት እንድትቆም ሊያደርጉ የሚችሉ ተከታታይ ሥራዎችን ሠራ ። ለበለጠ መረጃ Agust 18,2012 ደጀ ሰላም ላይ የተጻፈውን ያንብቡ።
አባቱ ዳኛ ልጁ ..... !!!
ስለዚህ እንደ እናንተ ማለትም የሰላምና አንድነት ጉባዔው እንደተባላችሁት ውዳሴ ከንቱ ሽምግልና ሳይሆን በእግዚአብሔ ቸርነት በድንግል ማርያም አማላጅነት በእውነተኞቹ አባቶቻችን ጸሎት እርቅ፣ ሰላምና አንድነት ተስፋ እናደርጋለን ። የሕዝበ ክርስቲያኑ፣ የአባቶች በተለይም የዋልድባ አባቶች እንባና ጸሎት ገና ብዙ ተዓምር ያሳየናል።
ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የምንጸልይበት፣ ካለፈው ስህተትና ጥፋት የምንማርበት ጊዜአዊና ዘመነ አመጣሽ ልዪነቶች አስወግደን ለአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን በአንድነት የምንቆምበትና የመንሰዋበት ጊዜ አሁን ነው። አሁን ጌዜአችንንና አእምሮአችንን አሰባስበን ከፊት ለፊታችን ለተደቀነው ትልቅ ሥራ ለሚጠይቀውም መስዋእትነት በአንድነት እንነሳ::
ዘሐመረ ኖህ
ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

Amelaka Kedosane yeredane
Eliza behare kaenaneta gara yehone

Anonymous said...

TSOME. YETAWAJE

Ahadu said...

"Restoring Aba Merkorios can't be an alternative solution. His exile is totally political, not religious. The presence of Abune Paulos was not the cause of the exile. We must not think 20 years back. We have to think for the future. Other ways creating unit should rather be considered. We need young, educated and dynamic patriarch. God Bless you."

ይህን ጽሁፍ የጻፍከው Anonymous ወይ የምታወራውን አታውቅም፣ ወይም አንተ እራስህ ቀንደኛ ዘረኛ ፖለቲከኛ ነህ ወይንም ደግሞ አቡነ ጳውሎስ ከሾሟቸው ቤተ ክህነትን ካንቋሸሹት "ጳጳሳት" አንዱ እንዲሆንልህ እና ቤተ ክርስቲያኗን ለመዝረፍ እንዲያመችህ ነው!
ወጣትነቱን ያልጨረሰ ደግሞ ፓትርያሪክ ሆኖ ካሳለፍነው 20 አመት በላይ ቤተ ክርስቲያና ትጎዳ እንዴ ?

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ወንበራቸው ይመለሱ:: የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትን የምትፈልጉ ከሆናችሁ!!!

ብላቴናዋ ከጀርመን said...

ሰላም ደጄሰላሞች በቅድሚያ ለታላቁባል ለደብረ ታቦር እንኩዋን በሰላም አደረሳችሁ በመቀጠል ግን ልሰጠው የምፍልገው አስተያየት ቢኖር የፓትርያርኩን እረፍትአስመልክቶ የሰላምና ኣንድነት ጉባኤ ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ በተራ ቁጥር 2ላይ አስተያየት የሰጠውን ሰውየ በተመለከተ የምለው አለኝ በመጀመሪያ የምጋራው ሀሳብ ቢኖረኝ ለዚች ቤተክርስቲያን መድሀኒ የሚሆናትበትትክክልም እውነትና እርሱ ባለቤቱ መድሀኒአለም ነው ነገርግን እስከመጨረሻው ድረስ መራርለመሆንና በክርስቶስ ፍርድ ወይም ስልጣን ገብተን ሲኦል መግባት አለባቸው ማለት ግን ከክርስቲያንነት አንጻር መልካም አይደለም ባይሆንስእኒህሰውየ ሄዱበቃ ላይመለሱ ፍርዱን ለርሱ እንተወው በአውደምህረት ላይ የሚሰብኩን ላልከውግን በትክክልም ለኔም ግራይገባኛል ለምሳሌ መታዘዝ ከመስዋእትነት ይበልጣል ለበላዮቻችሁ ታዘዙእያሉ እያስተማሩን እነርሱግን መታዘዝ አቅቶአቸው ሲኖደሱን እንቀበላለን የፓትርያሪኩን ስምግን እንጠራም ብለው ተለይተው ቤተክርስቲያን በሁለት ሲኖዶስ መከፈልዋ ሳያንስእንደገና ለሶስት ተከፍላ አንገታችችንን እንድናቀረቅር ሆንን አሁን ግን ሰውየው ሲሞቱ በቅዳሴግዜ የፓትርያርኩን ያቡነፓውሎስን ነፍስ ገነት መንግስተ ሰማያትን እንዲያወርሳቸው በተደጋጋሚ ሲመኙላቸው ስሰማ በጣም ነው የተገረምኩት መልካም ምኞቱ ባይከፋም ግን ማንንነው የምናታልለው ልብናኩላሊት ያመላለሰውን የሚያውቀውን አምላክ ምንአለበት ለቆምንበት አላማ ሁሌም ጽናት ቢኖረን ለዚህለዚህ መከፈሉን ምንአመጣው ነው ያው የተለመደው የበሻ ጠባያችን አይሎብን ሰው ከሞተ በሁዋላ ደግነቱንና የማንነቱን ሀተታ ቀለምቀብተን ማየት ስለሚቀናን ለማንኛውም እነርሱ ሲያደርጉት የራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸውም እንደኔ እንደኔ ግን በሂወት እያሉ ስማቸውን እየጠሩ ላለባቸው ህጸጽና ጥፋት እንዲመለሱ ጸልየውላቸው ቢሆን እንዴት መልካምነው ብየ አምናለሁኝ ለማንኛውም ከላይ እንደገለጽኩ አስተያየት ሰጭም እንደማንኛችንም ሀሳብ ያይደል የሚገባቸውን እርሱያውቀዋልና እንደቸርነትህ ብለን እንተወው ለሁላችንም ማስተዋልN ይስጠን አሜን

mk from gteece said...

የሠላም አምላክ በእኛ ላይ እንዲሳራ በአዋጅ ፆም ቢታወጅ መልካም ነው እላለሁ ፡፡ 1 ሣምንት ያለ መሪ የተቀመጠች አገር ኢትዮጵያ ልብ ይሏል/ኢአጌግ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት ያንዣበበውን እልቂት፣ 97 ዓ/ም ምርጫ ማግስት የተጀመረውን የእልቂት ጅምር በሰኔ ልደታ ዕለት የዘነበው ዝናብ እግዚአብሔር ከሕዝቦቿ ጋር መሆኑን ያስተውሏል፡፡ ስለዚህ ለዚች አገር አገራዊ/ብሔራዊ/ ኃላፊነት ያለባት ቤ/ክ ሰላም ማጣት የሁሉንም ደጅ ያንኳኳልና አባቶቻችን የአዋጅ ጾም ቢያውጁ መልካም ነው ፡፡ የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኔዓለም ይርዳን አሜን፡፡/ማሽ ከግሪክ

Anonymous said...

በኔ እምነት ፓትሪያክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ከዚህ በኋላ ፓትሪያክ ካልሆንኩ ብለው የሚከራከሩ ሰው አይመስሉኝም ቢሉም የኢሕአዴግ መንግስት እሺ የሚል ስላልሆነ እንደተባለው አዲስ የፓትሪያክ ምርጫ ዘግይቶ በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ያለው ልዩነት ተፈቶ ሁሉም ወደ ሐገር ቤት ገብተው ሁሉንም የሚወክል ፓትሪያክ ቢመረጥና ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ሐገር ቤት ተመልሰው ቀሪውን እድሜያቸውን በሰላም ቢያሳልፉ ለወደፊቱ ለቤተክርስቲያን አንድነት መልካም ነው በተረፈ ይህንን አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ካልተጠቀምንበት ለወደፊቱ ቤተክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ከባድ የሚያደርገው ይመስለኛል።

Anonymous said...

Ante wedaje abnePawlos siol endigebu yeferedik lerasih fired bitibal firdih mindinew? kesachew yeteshale tsidk alegn bileh taminaleh? Tsadkanko hule rasachewn kealem hulu yekefa hatiyategna argew new miyasbut na miyamnit. Endiyam eyalu yekerewn hatyat siyateru new wedefitsuminet yederesut. Ant miskin esachew siol bigebu ante min tagegnaleh. Abet yesew neger! Geta akimachinin wisn maregu endet cher new? 22 million? yet ayeh. Tew wederasih temeliket yesew hatyat atkuter lezawim ergitegna satiho satay! Abet yekunene yaleh limena.Wedaje ahun esachew yelum.Biyans besga teleytewnal.Rasachinin besew kemefred enalakina ene kesew hulu yemans hatiyategna, chingaf! enbel rasachinin. Cherku enkuwan yemifewsew hawaryaw kidus Pawlos endeza new yalew bezahulu tsidiku, Ylik nisha giba kezich seat behuwala silalew gize minim atak. Balesamint ante lithon tichilaleh. Ersachews kenun mech awekut. Endeleba bedinget metabachew enji. Neg benae new wedaje. Bemot na betsidkachin anmeka. Ylikis lerasachinim lelelochim entsely. Amen.

yemelaku bariya said...

ሰላም ደጀ ሰላሞች:: በቅድሚያ ያለውን እውነታ ለሰዎች ቢመቻቸውም ባይመቻቸውም ስላሳወቃችሁን መመስገን ይገባችኋል:: ብዙ አስተያየቶችን ሳያቸው ቢነገረን መከራ ባናውቀው መከራ አይነት ማኅበረሰቦች ነን:: በደጀ ሰላም ላይ ውሸት እስካልተጻፈ ድረስ እውነቱን እንደወረደ መቀበል ግድ ነው:: ለኛ የቸገረን የምንመኘውና በተግባር ያለው እውነት አለመጣጣማቸው ይመስለኛል ልንቀበለው የሚከብደን::ይልቁንስ ለወደፊቱ በአሁኑ የአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ያስተዋልናቸውን ክፍተቶች እና የተዝረከረኩ አካሄዶች እንዳይደገሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ከምርጫ በፊት የቤተ ክርስቲያናችንን አሰራር ግልጽና ተጠያቂነትን የተሞላ የሚያደርግ ህግጋትን እንዲያዘጋጁ ቢጠቆም መልካም ነው::
ሌላው ብዙ ሰው ስለ፬ኛው ፓትርያርክ ስለ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መመለስ አስተያየት ሲሰጥና ይህን ዓለም የተሰናበቱት አባት የቤተ ክርስቲያንን ለሁለት መከፈል የሳቸው እንደሆነ የሚያስነብቡን ብዙ ናቸው በመሆኑም ደጀ ሰላም ከናንተ የምንጠብቀው ለኛ ቢስማማንም ባይስማማንም
፩ኛ ለቤተ ክርስቲያን መከፈል ተጠያቂው ማነው?
፪ኛ በስደት ያለውን ሲኖዶስ የመሰረቱት አባቶች በውነት ከሀገር የተሰደዱት በፓትርያርኩ ላይ ተፈጸመ ባሉት ያላግባብ መነሳት ነውን? ከሆነስ ያንን ለመቃወም ምን ያክል ጊዜ ወሰደባቸው:: ተቃውሟቸውስ ከራሳቸው ጥቅም ጋር ያልተያያዘ ነወይ?
፫ኛ በውጭ ያለው ሲኖዶስ እንደምናስተውለው ኃይማኖታቸው በጥርጣሬ የተሞላ እና ከተዋኅዶ ጋር የሚቃረን አስተምሮን የሚከተሉ በመሆናቸው፣ ፓትርያርኩ በኃይማኖት ላዋጮች ላይ ቁርጠኛ አቋም ካልወሰዱና ይህንንም ሕዝብ እንዲያውቀው ካላደረጉ ልዩነትን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ብቻ ዘው ብለው መግባት አለባቸውን?
፬ኛ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስልጣናቸውን በተመለከተ ከሕዝብ ጥያቄን ያለማንም ረዳት ራሳቸው ብቻ ለመቀበል ፈቃደኛ እንዲሆኑ መጠየቅ የሚቻልበት መንገድስ ይኖራልን::
ይህንን ብታደርጉና የውይይቱን መድረክ ሰፋ ብታደርጉልን ይቻላችኋልን:: እባካችሁ የሚቻል ከሆነ ሞክሩ:: እግዚአብሔር ከናንተ ጋ ይሁን በየእለቱ የእውነት መንገድ ይከበራልና እውነትን መናገራችሁን ግፉበት ሰው ባይወዳችሁ የእውነት አምላክ ግን አይጠላችሁም::
ተጠምቀ መድኅን ነኝ ከሀገረ አሜሪካ

Anonymous said...

Egziabhear Yerdachu.. Sile Honewm Silemihonewm Egziabhear Yemesgen; Abatoch Ye Tsom/Tselot Gize Biyawjuna Gudayu Mejemeria Lemimeleketew Nigus Kirstos Eyesus Feqad Be And Lib Biniteyqew Yemigeba Yemeslegnal.... Be Kirstos Wendim ena Ehitoche Yehonachu Ye Betekirstean Lijoch Ahun Enkuan Sile Tilant Mansat ena Metalun Titen Sile Zare/Nege Eyteweyayen Egziabhearm Sirawn Endisera Ke Mengedu Zor Enbel, Wenz Yemayashagir Simetina Wegentegnetachinin Tewet Adrgen Eyanegesnew Yalewn Telat Diabilos Enikadew...Hasab Sinset QUM NEGERU Bicha Bota Yenurew(Menga Lemimeslu Aqetatayochu ena Tekulawochu Egziabhear Yewagachewal Yale Ersum Ewnetegna Feraj Yelem) Egziabhear Le Betekrstean Yeqomutin Tibebina Tsegawn Yabzalachew

Anonymous said...

Selam letewedeachihu wendimochina ehitoch. YeGreecu wendim endalut Cheru Egziabher Hagerachenena Haymanotachinen yetebikiln. Betechristan besew sayhon Bemenfes Kidus enditmerana hayluana gulbetua EGZIABHER endihone Be-TSOMINA BE-SELOT enberta. Kewistachen and begeta ytemerete ynoralna. YESADIK SEW TSELOT HAYLIN TADERGALCH teblual Bekidus mesihaf EGZIABHER YERDAN.

Anonymous said...

እንደኔ እንደኔ የተጻፈው መግለጫ በጣም ጥሩና በጣም በጥንቃቄ የተጻፈ መግለጫ ነው። ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚደክሙትን ወንድሞች እግዜር ይርደቸው። በመካካላቸው ያለውን ልበሰፊነት እና ይህን ውስብስ ችግር ለመፍታት ያላቸውን የአስተሳሰብ ታላቅነት እኔ ከመግለጫቸው ተገንዝቤአለሁ። እንደ ተባለው ቤተ ክርስቲያንን አንድ የማድረግ ሥራው በስፋት ሊሰራ ይገባዋል። አባቶችንም ከክፉ አስተሳሰብ የመጠበቅ በልጅነታችንi ኃላፊነት አለብብን። እዳው ነገ የእኛ ነውና። ይህልዩነት ባለበት ሁኔታ እኔ ፓትርያርክ ልሁን የሚል አባት ካለ ያ ለፓትርያርክነት ቀርቶ ለምንም የማይሆን የቤ/ክ ዕዳ የማይከብደው ሰው መሆን አለበት።

ደረጀ ነኝ ዳላስ

Anonymous said...

Egziabhear Ke Enante Gar Yehun.. Abatochachn Ye Tsom/Tselot Gize..? Wendim ena Ehtoche Ezih ena Ezia Sanil Sile Zare/Nege Enweyay ..QUM Negerun...(Tekula ena Aqetatayoch Egziabhear Yewagachhu) Geta Kehulachn
Gar Yehun Amen

Anonymous said...

አስካሁን ድርስ ገለልተኛ ነኝ ሲል የነበረው ዳላስ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ አባላት ለ አቡነ ጳውሎስ ቀብር መለክተኛ ለመላክ መእመኑ ሳይሰማ በድብቅና አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ አሰደቁ።

Anonymous said...

Andet betekirstian atinafikachihumin??? ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን! yemilew ayinafkachihumin???????
Thank you ደረጀ ከዳላስ. Allow me to post your ideas once again.
እንደኔ እንደኔ የተጻፈው መግለጫ በጣም ጥሩና በጣም በጥንቃቄ የተጻፈ መግለጫ ነው። ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚደክሙትን ወንድሞች እግዜር ይርደቸው። በመካካላቸው ያለውን ልበሰፊነት እና ይህን ውስብስ ችግር ለመፍታት ያላቸውን የአስተሳሰብ ታላቅነት እኔ ከመግለጫቸው ተገንዝቤአለሁ። እንደ ተባለው ቤተ ክርስቲያንን አንድ የማድረግ ሥራው በስፋት ሊሰራ ይገባዋል። አባቶችንም ከክፉ አስተሳሰብ የመጠበቅ በልጅነታችን ኃላፊነት አለብን። እዳው ነገ የእኛ ነውና።
Others who are commenting negatively about the condolence/report of the Council of Peace and Unity - Felit yigibachehu enji wegenoche! We only want one church again and again and forever! If we are committed for the unity of the church, let us compromise our differences and don't take extreme positions and run to criticize harshly the wise walk of the Council. Please refrain from flaming the issue. Let us first prioritize the unification by putting aside whatever of our positions. Kindly let us be POSITIVE and flourish only positive and constructive ideas for the UNIFICATION. UNIFICATION! UNIFICATION! UNIFICATION!
For dejeselam, please be aware to post only constructive views that could contribute for the unification of our beloved church. For the time being, I wish you could halt extreme views just for the sake of our church. Please, please..............
እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ያሳየን!
የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የምናፍቅ ታናሽ ወንድማችሁ ከጀርመን

Anonymous said...

በኔ እምነት ፓትሪያክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ከዚህ በኋላ ፓትሪያክ ካልሆንኩ ብለው የሚከራከሩ ሰው አይመስሉኝም ቢሉም የኢሕአዴግ መንግስት እሺ የሚል ስላልሆነ እንደተባለው አዲስ የፓትሪያክ ምርጫ ዘግይቶ በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ያለው ልዩነት ተፈቶ ሁሉም ወደ ሐገር ቤት ገብተው ሁሉንም የሚወክል ፓትሪያክ ቢመረጥና ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ሐገር ቤት ተመልሰው ቀሪውን እድሜያቸውን በሰላም ቢያሳልፉ ለወደፊቱ ለቤተክርስቲያን አንድነት መልካም ነው በተረፈ ይህንን አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ካልተጠቀምንበት ለወደፊቱ ቤተክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ከባድ የሚያደርገው ይመስለኛል።

በኔ እምነት ፓትሪያክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ከዚህ በኋላ ፓትሪያክ ካልሆንኩ ብለው የሚከራከሩ ሰው አይመስሉኝም ቢሉም የኢሕአዴግ መንግስት እሺ የሚል ስላልሆነ እንደተባለው አዲስ የፓትሪያክ ምርጫ ዘግይቶ በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ያለው ልዩነት ተፈቶ ሁሉም ወደ ሐገር ቤት ገብተው ሁሉንም የሚወክል ፓትሪያክ ቢመረጥና ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ሐገር ቤት ተመልሰው ቀሪውን እድሜያቸውን በሰላም ቢያሳልፉ ለወደፊቱ ለቤተክርስቲያን አንድነት መልካም ነው በተረፈ ይህንን አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ካልተጠቀምንበት ለወደፊቱ ቤተክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ከባድ የሚያደርገው ይመስለኛል።

Anonymous said...

ክላይ ያነበብኴቸው ጽሁፎች በጧም ያሳዝናሉ፣ ማንኛውም ቤተክርስቲያን ስለሞቱት አባት ነፍስ ይማር ማለት ስርአቷ ነው፣ ክፋ ነገር ቢፈጽሙም እግዚአብሔር ስለሃጥአን ወደዚህ አለም አልመጧም እንዴ? ታዲያ ቤተክርስቲያን ስለ ነፍሰ ገዳይ እንኳን ነፍስ ይማር ማለት ግዴታዋ ነው ፣ እንኳንስ ለሃይማኖት አባት። ስለዚህ ነፍሳቸውን ይማር በማለት ጸሎት ያላደረጕትን ቤተክርስቲያኖች መንቀፍ ነው እንጂ ነፍስ ይማር ብለው ጸሎት ያደረጉትን ቤተክርስቲያን የሚቃወም ራሱ ሀይማኖት የሌለው ሰው ነው። እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጳጳስ ይቅርና ለግብጹ ጳጳስ እንዃን ነፍስ ይማር በማለት አብዛኛውን ቤተክርስቲያን ጸሎት ተደርጔል ፣ስለዚህ ለአቡነ ጳውሎስ ጸሎት ያደረጉ ቤተክርስቲያኖች እንደ ሀጥያት የተጻፈባቸው አግባብ የሌለው ጽሁፍ ነው ባይ ነኝ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)