August 17, 2012

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል

“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።

በአዲሱ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የራሳቸው “ጥቅም” እና ፍላጎት ያላቸው አካላት፣ ግለሰቦች እና ቡድኖች መኖራቸው እሙን ሲሆን ከነዚህ ሁሉ ኃይለኛው እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ እና ሥልት ያለው ግን መንበረ መንግሥቱን የተቆናጠጠው የኢሕአዴግ አስተዳደር ነው። በበረሃ ወታደራዊውን መንግሥት ሲታገል ከነበረበት ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ስልት ነድፎ ሲንቀሳቀስ ከመቆየቱም በላይ በመንግሥትነት በቆየባቸው ዓመታትም ይህንኑ ቀጥሎ ሲያከናውን ቆይቷል። ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ቢያንስ የ38 ዓመት ዕቅድና ተሞክሮ አለው ማለት ነው። 17 ዓመት በበረሃ፣ 21 ዓመት በመንግሥትነት።

ስለዚህም ከአቡነ ጳውሎስ ሕልፈት በኋላ ማን ሊተካ እንደሚችል ከማንም የበለጠ ቀድሞ እንደሚያስብ የታወቀ ነው። በርግጥም ይህንን ሐሳቡን አሁን በፍጥነት፣ በግርግር፣ በዚህ ሁሉ ትርምስ መካከል የሚያደርገው ከሆነ ቤተ ክርስቲያናችን ባለፉት 20 ዓመታት ካሳለፈችው አሳዛኝ ሁኔታ የበለጠ አዘቅት ውስጥ ልትወድቅ እንደምትችል ለመገመት የአቡነ ጳውሎስን ዘመን ማስታወስ ብቻ ይበቃል። የሚቀጥለው ጊዜ እንዲያውም ከእርሳቸው ዘመን የከፋና “ጳውሎስ ማረኝ” የሚያሰኝ ሊሆን ይችላል። በታሪክ እንደምናውቀው ከክፉ መሪዎች ሕልፈት በኋላ የሚመጡ መሪዎች የበለጠ ክፉ የሚሆኑበት ብዙ አጋጣሚ አለ። የቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴን ዘመን “አስከፊ ነው” ያለው ወታደራዊ መንግሥት “ጃንሆይ ማሩኝ” አሰኝቶን እንዳለፈው ማለት ነው።

የኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተው “ፖለቲካዊ ትንታኔ” ገና ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ፈር በያዘ መልክ የተጠናና አቋም የተያዘበት እንደሆነ የህወሐት መሥራች አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባደረጉት የምርምር ሥራቸው (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia/ Amsterdam 2008) ላይ ጽፈውልናል። የፓርቲው ሃይማኖትን በተመለከተ የያዘው ይህ አቋም በተለይም ነባሮቹን የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና እስልምናን የተመለከተ መሆኑን፣ ኮሚኒስታዊ ፓርቲዎች ሁሉ ባላቸው “የጨቋኝ - ተጨቋኝ” ትንታኔ መሠረትም እነዚህ ሁለቱ ቤተ እምነቶች በተለያየ ጎራ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን፣ ክርስትና ጨቋኝ፣ እስልምናም ተጨቋኝ ተብሎ መፈረጁን አንብበናል።

ዶ/ር አረጋዊ ባብራሩት የኢሕአዴግ ትንታኔ መሠረት “ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞቹ መንግሥታት ጋር “በነበራት ቁርኝት” ከገዢው መደብ ጋር የተሰናሰለ የጥቅም እና የጨቋኝነት ግንኙነት ነበራት። በነዚህ ረዥም የጭቆና ዓመታት ከተጨቆኑት መካከል ደግሞ ሙስሊሞች” ይገኙበታል፤ ስለዚህም ኢሕአዴግ ይኼንን የጭቆና ቀንበር “ለመስበር” እና እኩልነትን ለማስፈን የተከተለው ፖሊሲ፣ “ቤተ ክርስቲያንን ማምከን/ፍሬ ቢስ ማድረግ” እና “ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ” ("neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) ነው። (ገጽ. 300)

እንደ ዶ/ር አረጋዊ ገለጻ ከሆነ “በኢህአዴግ እና በቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት ከመጀመሪያው ጀምሮም ችግር ያልተለየው” ነበር። የትግሉ ማዕከል ከነበረው ከትግራይ ስንነሣ በሕዝቡ መካከል የሚደረገው ማንኛውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በአገልጋይ ካህናቷ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነው። ሰርጉ፣ ክርስትናው (የሕጻናት ጥምቀቱ)፣ ቀብሩ እና በጎረቤቶች አለመግባባት ወቅት ያለው ሽምግልናውና እርቁ በሙሉ የሚፈጸመው በቤተ ክርስቲያን በኩል ነው። ያንንም ለማከናወን ደግሞ በቂ ካህናት አሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ቤተሰብ ሕይወቱን የሚከታተሉ አባቶች (የነፍስ አባቶች) በነፍስ ወከፍ አለው። ስለዚህም በያንዳንዱ አካባቢ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሕዝቡ ሕይወት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አላት።

በሁለተኛ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ እና በመንግሥታት መካከል ድልድይ ሆና ትሠራለች። ዶ/ር አረጋዊ እንዳሉት “ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁልጊዜም ካለፉት ነገሥታት ጋር አብራ ቆማለች፤ መንግሥታቱም ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትኖር፣ እንድትስፋፋ እና አንድነቷ እንዲጠበቅ” ረድተዋታል። ቤተ ክርስቲያን ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ድረስ ተቋሟን ከመዘርጋቷም በላይ በመንግሥትና በተቀናቃኞች መካከል ለሚፈጠር ቅራኔ በአስታራቂነት እስከመግባት ትደርሳለች። ምእመናኗም ለመንግሥታቸው እንዲገዙ ታስተምራለች፣ አገራዊ ብሔርተኝነት እንዲዳብርም በማዕከልነት አገልግላለች። ባንዲራን የመሳሰሉ አገራዊ ምልክቶችን በበዓላቷ ሳይቀር ከፍ አድርጋ በማውለብለብ ብሔራዊ ማንነትን (national consciousness) ገንብታለች። የቤተ ክርስቲያን በዓላት ካለ ሰንደቅ ዓላማ በጭራሽ አለመከበራቸውን ልብ ይሏል።

በሦስተኛ ደረጃ በየዘመኑ የነገሡ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን እስካልተቀቡ ድረስ ንግሥናቸው ተቀባይነት አልነበረውም። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን የነገሥታቱ ሥልጣን አረጋጋጭ እና ወሳኝ ሆና አገልግላለች። በአኩሱም ጽዮን ለሚፈጸመው ለዚህ ቅብዓ መንግሥት ነገሥታቱ በበኩላቸው ርስት እና ጉልት በመሥጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጠቅመዋል። አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው፣ የአጥቢያው ምእመንም እንዲንከባበከባቸው፣ አገልጋይ ካህናቱም የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ የአጼዎቹ አስተዳደር ጠቅሟቸዋል።

“አጼያዊው አስተዳደር ከወደቀና ቤተ ክርስቲያን ርስት ጉልቷን ሁሉ ካጣች በኋላ በወታደራዊው መንግሥት እና በሰሜን በሚዋጉ ተቃዋሚዎች መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገባች” ይላሉ አረጋዊ በርኸ። “ኢ.ዲ.ዩን በመሳሰሉ ፓርቲዎች ላይ ተስፋ አሳድራ ብትቆይም ሳይሳካ” ቀርቷል።

እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ገለጻ ከአብዮቱ በኋላ የትግራይ ሕዝቦች ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሐት) ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ መካከል ያላትን ሚና እና አብዮቱን ከሚቃወሙ ኃይሎች ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት ተረዳ። ግንባሩ በሚያደርገው ትግል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከመንገዱ ላይ እንደተደነቀረች እና በጥንቃቄ ሊይዛት እንደሚገባ አወቀ። ቤተ ክርስቲያኒቱን የትግሉ አካል እና ደጋፊ ማድረግ እንደሚገባው ተገነዘበ። ስለዚህም ሊያዳክሟትና እና ለዓላማው መሳካት እንድትቆም ሊያደርጉ የሚችሉ ተከታታይ ሥራዎችን ሠራ -  ይላሉ።

ግንባሩ በመጀመሪያ የወሰደው ርምጃ ወታደራዊው መንግሥት ያወጀውን “የመሬት ላራሹ” አዋጅ ባለመቀልበስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብቷ፣ ንብረቷ፣ መሬቷ እንዳይመለስላት ማድረግ፣ በዚህም ጉልበቷን ማዳከም እና ለሺዎች ዓመታት የነበራትን አቅም በመስበር ከአማኞቿ ጋር አዲስ ውል እና ቃል ኪዳን እንድትገባ ማስገደድ (በምእመናን ምጽዋት ላይ እንድትደገፍ ማድረግ)፣ ልትረዳቸው የምትችላቸውን የተቃውሞ ኃይሎች እንዳትረዳ ደካማ ማድረግ ነው። ቤተ ክርስቲያን የነበራትን መሬት ራሱ ፓርቲው በመውረስ ለሕዝቡ ለማከፋፈል ከመሞከሩም በላይ የቤተ ክርስቲያንን መሬት ለመጠቀምና ለማከፋፈል ፍላጎት በሌለባቸው አካባቢዎችም ፓርቲው ራሱ በመቆጣጠር ተሰሚነቱን ከፍ ለማድረጊያነት ተጠቀመበት።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ተጽዕኖ በማዳከሙ በኩል ፓርቲው በሁለተኛ ደረጃ የወሰደው ርምጃ በማንኛውም የዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ማለትም (ሰርጉ፣ ክርስትናው (የሕጻናት ጥምቀቱ)፣ ቀብሩ እና በጎረቤቶች አለመግባባት ወቅት ያለው ሽምግልናውና እርቁ) ሕዝቡ ዓይኑን ከቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲያነሣ እና ፓርቲው በሚያቋቁማቸው ተቋማት ላይ እንዲያደርግ በዚህም ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነቷ ዝቅ እንዲል ማድረግ ነው። እንደታሰበውም ቤተ ክርስቲያን የሸምጋይነት ተግባሯን እንዲሁም ቦታዋን አጣች።         

በሦስተኛ ደረጃ ፓርቲው ያደረገው ነገር ተከታታይ ሴሚናሮችን ለተመረጡ ካህናት ማካሔድ ነበር። ይህ እ.ኤ.አ በ1979 የተካሔደው ሴሚናር ዓላማ በትግራይ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ከመላው አገሪቱ ካለው መዋቅራዊ አሠራር በመለየት እና በመነጠል፣ የትግራይ ብሔርተኝነትን በማጠናከር ፓርቲው ለተነሣለት ዓላማ እንዲጠቅሙ ማድረግ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን ተጽዕኖ ለመቋቋም ትግራዋይነትን እና የትግራይ ብሔርተኝነትን መቀስቀሱና ማራገቡ ትልቅ አስተዋጽዖ ሊያደርግ ቻለ። በወረዳ ደረጃ የነበረው የትግራይ ካህናት ተከታታይ ሴሚናር የተከናወነው “በአንደበተ ርቱዑ የቲዮሎጂ ምሩቅ በገብረ ኪዳን ደስታ” ሲሆን የውይይቱ ርዕሰ ጉዳይም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅትን ዓላማ በተቀበሉ እና “ትግራዋይነትን እና የትግራይ ግዛትን በሚያስፋፉ ካህናት” መተካት ነበር።

(ማስታወሻ የነዚህ ሴሚናሮች እና ቀረጻዎች ውጤቶች የሆኑ አያሌ ካህናት፣ መነኮሳት እና ጥቁር ራሶች ዛሬ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ መዋቅሮች ላይ ተቀምጠዋል። ብዙዎቹም ቤተ ክርስቲያን የምትፈልግባቸውን በማድረግ እና ፓርቲያቸውን በመታዘዝ መካከል ተወጥረው የሚኖሩ ሆነዋል። የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎትም በፓርቲ መነጽር ብቻ የሚመለከቱ ናቸው።)

ይህ እንቅስቃሴ “የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትን እና ተርታ ምእመናንን በማንቀሳቀስ እና በማነቃቃት” የተከናወነ ሲሆን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር በመነጠል እና በመገንጠል፣ ዋናዋን እናት ቤተ ክርስቲያን በማዳከም ላይ ያተኮረ ነበር። በአቶ ስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ መዋቅር የተደራጀ ሲሆን የፓርቲውን ሰላዮች በመነኮሳት እና በካህናት ስም ደብረ ዳሞን በመሳሰሉ ዋና ዋና ገዳማት በማስገባት እና ቤተ ክርስቲያኒቱን በመቆጣጠር ላይ ሥራ ተሠርቷል። እ.አ.አ በ1979 የተጀመረው የካህናት ተከታታይ ሴሚናር አድጎ በ1987 እና በ1989 ክልላዊ እና አገር አቀፋዊ የካህናት ጉባኤዎች ‘ነጻ በወጡ መሬቶች ላይ” ሊካሔዱ ችለዋል። ዓላማውም የቲ.ፒ.ኤል.ኤፍን ዓላማ የተቀበለች ቤተ ክርስቲያን በትግራይ መመሥረት ነበር። በውጤቱም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ልትከፈል ችላለች፣ አንደኛው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር፤ ሌላኛውና ሁለተኛው ደግሞ በፓርቲው ሥር ያለ አስተዳደር። ሁለቱም አስተዳደሮች ፓርቲው መቐለን እስከተቆጣጠረበት እስከ 1990 ድረስ በትግራይ ውስጥ በትይዩ ሲሠሩ ቆዩ። መቐለ “ነጻ ሲወጣ” አንደኛው አስተዳደር አበቃለት፣ በፓርቲው አስተዳደር ተተካ ሲሉ ያትታሉ።

በ1983 ዓ.ም ግንቦት ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በወታደራዊው መንግሥት ጸረ እምነት አቋም እና በአጠቃላይ የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ የተነዋወጸው ቤተ ክህነት ተከፋፍሎ ለበለጠ መለያየት ተመቻችቶ ነው የቆየው። በኢሠፓነት የተከሰሱት ብፁዕ ወቅዱስ አበኑነ መርቆርዮስ “በፈቃዳቸው” መንበራቸውን ለቅቀው ብፁዕ አቡነ ዜማ ማርቆስ “ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ” ሆነው ተመረጡ። በአንድ ጽሑፋችን እንዳልነው በዘረኝነት በሽታ በጽኑዕ የታመመው ቤተ ክህነት በሌላ የዘረኝነት ወረርሽኝ ተመታ። በአንድ ጽሑፋችን እንዳልነው፦ “የጎንደር ምንቸት ወጣ፣ የትግሬ ምንቸት ገባ”። ዘረኝነቱ ቀጠለ። መንግሥትም ቀጥተኛም ቀጥተኛ ባልሆነም መንገድ ቤተ ክህነቱን ይዘውረው ገባ።

ቤተ ክህነቱ በየትኛው ዘመን ፍፁማዊ ነጻነት ነበረው ለማለት ባይቻልም እንደ አሁኑ ደግሞ “ዳዊት ባልደገመ አፋቸው፣ አቡነ ዘበሰማያት በማያውቅ አንደበታቸው” ቤተ ክህነቱን እንወክላለን የሚሉ፣ በእምነታቸው ኢ-ኦርቶዶክሳዊነት የሚታወቁ፣ በገንዘብ ዘረፋ የተሰማሩ፣ በይፋ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን እና ኢትዮጵያዊ ባህልን የሚያጎድፉ ሰዎች ተሰግስገውበት አያውቁም። ይህ 20 ዓመት ሥርዓተ ምንኩስና፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ አሠረ ክህነት፣ ፕትርክና እና የተከበረ አባትነት፣ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ አለመሆን ወዘተ የተንኮታኮተበት ዘመን ነው።

በአጠቃላይ በዚህ ሁሉ ግርግር መካከል፣ ባልተረጋጋ መንፈስ፣ ጤነኛው ከቀማኛው፣ እውነተኛ እረኛው ከነጣቂው ባልተለየበት እና ትክክለኛ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ለመስጠት ቤተ ክህነቱ መዋቅራዊ ጤንነቱ ባልተጠበቀበት ሁኔታ፣ ሕግጋቱ እና አሠራሮቹ ሳይስተካከሉ፣ ቅዱስ ሲኖዶስም የማይነቃነቅ ሉዓላዊ የበላይነቱን እንደገና ከእጁ ሳያስገባ አዲስ ፓትርያርክ መምረጥ ከዘመነ አቡነ ጳውሎስ ለባሰ ችግር ሊያጋልጠን ይችላል።

በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 13፡5 ላይ እንደተጠቀሰው በፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚሳተፉትየቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የየመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የጥንታውያን ገዳማት አበምኔቶች የአድባራት አስዳዳሪዎች ከየሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤያት በዕድሜ ከሠላሳ ዓመት ያላነሱ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች እንዲሁም ዕድሜያቸው 22 አስከ 30 ዓመት የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ሲሆኑ በጠቅላላው በሰበካ ጉባኤው የሚወከሉት ከአንድ ሀገረ ስብከት አሥራ ሁለት ሆነው በሥጋወደሙ የተወሰኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የጸኑ መሆን አለባቸው” ይላል።

በዚህ መሠረት ባለፉት ዓመታት በተለያየ ምክንያት በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ የተሾሙ፣ በምግባራቸውም በእምነታቸውም አስነቃፊነት በተለያዩ ጊዜያት የምዕመናን ቅሬታ፣ ዕንባና ሐዘን የወረደባቸው ሰዎች ዞረው “ፓትርያርክ መራጮች” ሆነው ይመጣሉ ማለት ነው። በርግጥ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ “የምርጫው አፈጻጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል” ቢልም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውጤቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።

የምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ውክልናም በተመለከተ ምዕመናን እና ወጣቶቹ በቅጡ ሊመክሩበት ይገባል። የምንመርጠው ፓትርያርክ እንጂ የቀበሌ ሊቀ መንበር አይደለም። ከየአህጉረ ስብከቱ የሚወከሉ ሰዎች በቢሮ-ለቢሮ የደብዳቤ ልውውጥ እና በድርጅታዊ አሠራር የሚላኩ መሆን የለባቸውም። ለዚህም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ኃላፊነት አለባቸው።

ከዚህ አንጻር ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል። ከ40 እስከ 80 ቀናት በቂ አይደሉም። አሳማኝም አይሆንም። ቅ/ሲኖዶስ የምርጫ ደንብ ለማውጣት ጊዜ ያስፈልገዋል እንላለን። ጊዜ፣ ጊዜ፣ ጊዜ። መመሪያ፣ መመሪያ፣ መመሪያ። ደንብ፣ ደንብ፣ ደንብ። መንግሥትም አጁን ሰብሰብ ሊያደርግ ይገባዋል። ብፁዓን አባቶችም ኃላፊነታቸውን በቅጡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

36 comments:

Anonymous said...

+++
Wel-said! KaleHiwot Yasemalin

Anonymous said...

አይን የሚገልጥ (ለተገለጠላቸው ደግሞ ቦግ የሚያደርግ ነው)። መንግስት እጁን ያነሳል የሚል ካለ የዋህ ሳይሆን ሞኝ ነው። ነገር ግን አባቶቻችን በርትተው ሊቋቋሙት ይገባል።

ለሁሉም ግን መፍትሔው ላይ የሰው ድርሻ ቢያስፈልግም፣ ዋናው ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው እና ሁላችን እንጸልይ። በየገዳሙ ለወደቁ አባቶቻችንም የተሻለ እንዲያመጣልን እንዲጸልዩልን ሁሉም ያስታውስ።

ጊዜው ከምንም በላይ የጸሎት ነው።

Anonymous said...

እኔ አንደ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቀርቋሪ አማኝ የምለው አራተኛው ፓትርያርክ በሕይዎት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ መሾም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ከፋ ችግር ያስገባታል፤ ለዘለዓላምም ታሪኳን አጥቁሮት ይቀራል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ለዚህ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ቤተ ክርስቲያናችንን የምንዎድ ወጣቶችም ተባብረን መንግሥትም በጎ ፈቃዱ ሆኖ ይህንን ታሪክ ብናርመው ለወደፊት የቤተ ክርስቲያን ክቡር ታሪክና አንድነት መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ባየ አምናለሁ። እባካችሁ ቤተ ክርስቲያንን የምትወዱ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ ለጊዜአዊ ጥቅምና በሚል ሌላ ፓትርያርክ እንዲመረጥ ብናደርግ ቤ/ክንን በእጅጉ እንጎዳታለን፤ መፍትሄው አራተኛውን ፓትርያርክ ወደመንበራቸው መልሶ ቤ/ክ በቅዱስ ሲኖዶስ እንድትመራ ማድረግ ይመስለኛል፤ ስለዚህ አበው ሊቃነጳጳሳት እና የቤተ ክርስቲያን ሰወች ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲሉ ታሪካችንን ያስተካክሉት። ቤ/ክ ተከፋፍላ አትቅር እላለሁ።
አመሰግናለሁ
ተስፋ ሥላሴ ከአሜሪካ

Anonymous said...

yibel yibel new!

Anonymous said...

yegonder menchet yemelse

Anonymous said...

አሁን በኢትዮጵያ የሚኖሩት አባቶቻችን ሌላ አባት እንሹም ብለው ከተነሱ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ መፍትሔ ቢሰጥም አንስማማም የማለትን ያክል ከባድ በደል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይcveማሉ ብለ አስባለሁ፤ ግን መንፈስ ቅዱስ ጠርሶ ካልተለየን ይህንን በደል ቅዱስ ሲኖድ ደግሞ የሚሰራው አይመስለኝም። ለማንም ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ሲባል የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ እባካችሁ ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ። አባቶቻችን በእውነት ታሪክ ስሩ አንተን እንሶምሃለን አንተን እንሶምህአለን በሚል አታላይ ቃል እንዳትታለሉ። ያከበረቻችሁን የቤተ ክርስቲያንን ክብርና አንድነት አስቀድሙ፤ በፓትርይርክ ላይ ፓትርይርክ መሶሙ በየትኛውም የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ አያገንም፤ ስለዚህ የአሩትን አረጋዊ አባት እግዚአብሔር እስኪሰበሰብ ድረስ ዕድል ስጡት አትቸኩሉ። መጣቶችም በእውነት ለእኛም ለልጆቻችንም ስንል እናልቅስ። ያቅማችንንም ለቤ/ክ ክብርና አንድነት እንስራ። ያንጊዜ መናፍቃንም ተንባላትም አጋንትም ድል ይነሳሉ።
ኃይለ መለኮት ነኝ ከአሜሪካ

Hailu said...

DejeSelamoch and dear Ethiopian Orthodox Christians,


This is a momentous time to correct the grave mistake that was committed some 20 years ago and left our beloved church splintered. Look, unless we do the right thing now, it is saddening to see a divided and weakened Orthodox Church we will pass to the generation to come.We need to step back and think before we start beating the drum of electing another fake patriarch. We must not repeat the very mistake that caused us so much trouble. Remember, how the deceased, came to power 20 years ago. It was orchestrated by TPLF to control and weaken the church. If there is any one out there who believes Patriarch Merkoriwos relinquished his position due to ill health, I would say he/she must not have been observing what the TPLF has been doing to justify every atrocity it committed against our church and Ethiopia in the past two decades. Read the diplomatic cable released by wikileaks on what the then PM Tamirat Layne, now menafik, told to the US Embassy about how they caused the division of our church.


The damage the late Aba Gerbremedihin aka Aba Paulos has caused is enumerable. Look how we are responding to the death of a person whom we would otherwise have mourned had he assumed the position legitimately according to canon law, had he done the right things to the church, and had he been on our side.


However, the most glaring damage of all, I think, is the DIVISION he has brought to the Ethiopian Orthodox Church, and his complacence while the age old monastery, Waldiba, is being desecrated.

He is now gone. God is the judge here. It is a relief for the church that he is gone.


Now, the most important question should be how we can restore unity, dignity, and holy leadership going forward. This is the time to think how to solve our Church's most pressing problem, the division. It is time for soul searching and praying to God for guidance, and not a time to simply vent our emotions.

I consider three possible scenarios about the leadership of our church following the passing of Aba Gebremedihin.

1. We acknowledge Patriarch Merkorios as the head of the church for his life span, however long that may be, and eliminate the very reason that led to the division in our beloved church, which is appointing a patriarch while a living patriarch exists. This scenario must be entertained courageously just for the sake of uniting our church regardless of the bickering from either side.

2. TPLF will orchestrate a fake election and assign another cadre and try to maintain the status quo leading to a continued suffering of our beloved church and its followers.

3. A seemingly free election may be held by the synod in Addis and the fathers choose one amongst themselves. This will still be assigning another patriarch against the cannon low of the church while a legitimate one is still alive. This will guarantee the perpetuation of the very problem that divided our church for the past 20 years.


We are fed up of the division, trivialization of our values, corruption in the church, desecration of our holly places, etc. We are tired of the weeping, the heart aching and helplessly murmuring as we witness ill being done to our Orthodox Church.

I pray to God to give the fathers of the church to use this opportunity to heal the division the late Aba Gebremedihin caused to the church. For the purpose of mending the splinter in the church, restoring the legitimate Patriarch, Abune Merkorios, is the best scenario. Unless God does his divine intervention, such a wise idea to solve the church's most significant problem is less likely. TPLF may likely assign another cadre. This is what we fear as human beings, but God's plan and work is supreme as we are witnessing these days. Our church may at last be united or remain divided. We shall see.


May God bless our church and Ethiopia! Nefis Yimar Lemotut.

Anonymous said...

It bothers me when young people think like uneducated, archaic idots. Not spiritual ones, just down right useless old retards.
What do you expect from Ethiopian government. "Yemengst Fekad hono" Idiot. what government. Woyane. Woyane will only allow to have a faher appointed who will fulfuill thier interest to repress people, creat choas, ensue division and destroy the church. All woyane want is what is not good for its people. IF the appointment of the church will unite you, woyane will want a father like paulos who will devide. It is sad young people are waiting for this myopic junta to do right. I don't know who thought you. It embarasses me that we share citizen ship. young people the only way is to question authority, including old, draconian, blotted so called kesis and abunas. Their did stinks. They are not our fathers they are just piece of human waste that go around eat our food, drink our TELLA , east our foo, rob our money and send us to hell. they are nothing but diablos himself in long robs, long beard and a fancy hut. Empty drobs devoded of spirtuality and fatherly guidancy.

Anonymous said...

The almighty God thyself created an opportunity for this church to repair its broken order. As a faithful member of the Ethiopian Orthodox church, I suggest not to repeat the same mistake that brought our church to its knees. Whether its from Gonder or Tigray or Wolega, we are one in the kingdom of heaven. We should also learn what the Egyptians do when their government arrested the head of the church and demanded to elect one. But, the faithful refused to comply. Finaly the government came to its sense and restored the churches order.
During the take over of EPRDF, a grave mistake was made not just by the government but also by us - the faithful. We should have been refused to elect new Patriarch unles he is departed by death or fair justice for he has been disecrating the church. But, none of these conditions has been met. We jumped with EPRDF's bandwagon and seriously injured our church.
For whatever weakneses he may have (the 4th patriarch Abuna Merkorios) he is the legitmate head of the church who shall be reinstated to his place. To be frank, I had been one of the displeases when he was working as the head of the church for the reason that some of his relatives from Gonder has been interfereing in the churches affairs. But, we have to recognize that, the past 21 years has been a great lesson for him to remorse on the past failures. Moreover, he is a true monk who has not been spoiled by the worldly enticement unlike Abuna Paulos.
We have to learn one more lesson also from our muslim brothers who refused to buy what government tries to impose on them. This is the right time to claim back the glory of our church. Rise Christians up! and say our church's diginty shall be respected! Our Churche's order must be reinstated!

Anonymous said...

The almighty God thyself created an opportunity for this church to repair its broken order. As a faithful member of the Ethiopian Orthodox church, I suggest not to repeat the same mistake that brought our church to its knees. Whether its from Gonder or Tigray or Wolega, we are one in the kingdom of heaven. We should also learn what the Egyptians do when their government arrested the head of the church and demanded to elect one. But, the faithful refused to comply. Finaly the government came to its sense and restored the churches order.
During the take over of EPRDF, a grave mistake was made not just by the government but also by us - the faithful. We should have been refused to elect new Patriarch unles he is departed by death or fair justice for he has been disecrating the church. But, none of these conditions has been met. We jumped with EPRDF's bandwagon and seriously injured our church.
For whatever weakneses he may have (the 4th patriarch Abuna Merkorios) he is the legitmate head of the church who shall be reinstated to his place. To be frank, I had been one of the displeases when he was working as the head of the church for the reason that some of his relatives from Gonder has been interfereing in the churches affairs. But, we have to recognize that, the past 21 years has been a great lesson for him to remorse on the past failures. Moreover, he is a true monk who has not been spoiled by the worldly enticement unlike Abuna Paulos.
We have to learn one more lesson also from our muslim brothers who refused to buy what government tries to impose on them. This is the right time to claim back the glory of our church. Rise Christians up! and say our church's diginty shall be respected! Our Churche's order must be reinstated!
From Japan

Anonymous said...

እስቲ በርትተን እንፀልይ ወይም ወደሚፀልዩት ጋር እንዲፀልዩ እንማጠን። ደጀ ሰላማውይያንን ግን ሳላመሰግን አላልፍም እነኝህን በሳል ጽሁፎች ሳነብ የጸሃፊዎቹንም በሳልና ምሁርነት፤ መንፈሳዊነት አደንቃለሁ።

ተስፋማርያም ዘስላሴ said...

ፈጣሪ ደጉን ዘመን ከደግ አባት ጋር ያምጣልን

ሁላችንም በርትተን እንጸልይ

Anonymous said...

PLEASE TRY ALL OF US LETS PRAY AND FAST TO GET A GOOD FATHER FROM GOD HE CAN GIVE FOR US A GOOD ONE IF WE ARE GOOD.PRAY PRAY PRAY

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

This Gebrekidan mentioned in Berhe's thesis is an ignorant individual who always tried to stir ethinic strifes between trigrians and the other people. Look at the book - Ye Tigray Hizeb-Ena Ye Temekehetgnoch Syera.

tad said...

Please lets fight first for the canon of the church, not for the best father we can find.
20yrs ago we compromised on our canon law and fantasized with the best educated phd patriarch.
It is not only to blame tplf. It is more to blame the psychy of EOC bishops,priests, deacons and faithfuls. When it comes to canon laws it is not only up the patriatch or bishops... to defend it. "It takes the village to raise a child'.
Lets learn from our mistakes, heal history and sanctify the future of our spiritaulity. Lets grow up and learn from copts that they refused to appoint new patriarch when Sadat house arrested Abune Shenouda. The past 20 yrs bishops were wrong, MK was wrong, sunday schools were wrong, clergies were wrong, ...we all were wrong. But we can make tomorrow and the day after tomorrow right. Our churche's future is in our hands, ofcourse with the help of Almighty.
Lets not go for kilil, as it happend 20 yrs ago. Lets get strong and say we have one and only one patriarch once and for all.I know there are alot of emotions, misgivings,misunderstanding....But we can do it.
This is a moment for MK to play a national role.

Anonymous said...

አሁን ባሉት ፓትርያርክ ዙሪያ ያሉት ሊቃነጳጳሳት እና ሌሎች ሰዎች ብዙ ምድራዊ የሆነና የፖለቲካ አላማ ስላላቸዉ ችግሩን ለመፍታት እንዲህ ቀላል አይሆንም:: ለዚህም ሰሞኑን ለኢሳት ቃለ መጠይቅ የሰጡት አባት ወይንም በሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አበበ ገላዉ ያደረገዉን ንግግርና የጳጳሱን ንግግር በማዬት/http://www.youtube.com/watch?v=m2IQi46jFhA/ በፓትርያኩ ዙሪያ ያሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማዬት ይቻላል:: እዉነት እንነጋገር ከተባለ አብዝሃኛዉቹም አሁን ያለፉት ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ጳዉሎስ ሲሾሙ ይደልዎ ሲሉ የነበሩና አብረዉ የመረጡ እንዲሁም የደስታ መልዕክት የላኩ አባቶች አሉበት:: ስለዚህ ሁለት ጽንፍ የያዘ አስተሳሰብ ትተን የነበረዉ ዉይይት ቢቀጥልና ኢትዮጳያ ያሉት አባቶቻችን ሳይቸኩሉ የግብጽን ቤተክርስቲያን አርአያ መከተል ቢችሉ መልካም ኑዉ ብዬ አምናለሁ:: እኛም በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ ያሉት ተሃድሶ መናፍቃንና በዘርም ሆነ በጊዜያዊ ጥቅም የተሳሰሩ ወገኖች የሚያሰራጩትን አሉባልታ ወደ ጎን ትተን ለቤተክርስቲያናችን አንድነት መቆም አለብን

Anonymous said...

God bless those who are devotedly working for Deje selam. Lets keep on praying to see the hand of God. Beware that those who fight with God will scrumble forever. Long live Tewahdo!

Anonymous said...

መንግሥትን ጨምሮ የራሳቸው ጥቅም እና ፍላጎት ያላቸው አካላት፣ ግለሰቦች እና ቡድኖች እንደ ማኅበረ ቅዱሳን እና ተሐድሶ አጁን ሰብሰብ ሊያደርግ ይገባዋል።

እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን አንድት መፍትሔ ይሰጥ ጊዜውም የጸሎት ነው።

Anonymous said...

Anony..

The man who sent the last message, you don't even what the difference b/n Mahibere kidusan and tehadeso you are just pasting ur message, I don't think so u are able to comment.
Pls read read read read more more more.

Anonymous said...

Dejeselam alamaw alemawi new weys menfesawi? Enih abat ene ergtun balakim kifu nachew (ykr ybelegnna) sibal kereme. Ahun motu. Ere sileEgziabher enasarfachew. Wedeewnet bota hedewal. Libin mimeremir cher amlak geta medhanialem endechernetu beAbreham ekf yanur nebsachewin. Bikefam bilemam bejachew ye fetarin bereket tekeblenal. Sgawedemun kejachew beltenal.Bezalay ewnetegnawin menfesawi hiywetachewn mermro lemawek yemichil kegna wst manew? Motko yesew birtatna dikam adelem yefetari ekid enji. Are wedelibonachin enmeles gobez! Yemiketilewn Patriark geta endimertilin metseley yshalal bay negn. Yetsadik sew tselotko besrawa ejig hylin tadergalech. Are enmen.Metseleyna mamen biyakiten bemerzama bier yemotutn alastegna aln. Enmen entsely. Bemot leteleyun abatim entsely. Menberu yegeta new. Midrawi baleslitan kekrstos belto yegetan menber keto aywesdim. Minalbat hatiyatachin kekefa gin lekifu asalifo endayseten entenkek. Yam hone ya gin menberu yegeta new. Eyandandachin zeregnochina kifuwoch adelenim. Banhon endet yeleloch kifatna zeregnanet tayen? Awo hatie hule yaynun miseso aymeleketim yesew aynin gudf enji. Ya new beyandandachin yemintsebarekew zare. Ere ybkanina aynachinin kesew enansa. Wedelay enangat. Yane geta wedegna ymeleketal. Bahun kifatachin gin geta bimeleketewm anayewm. Ena melkam kewstachin yseweral. Yegetanim sira mastewal yakitenal. Ahun hulun titen entsely bakachu. Silehulum neger entsely. Geta kemdrawyan alkoch ybeltal enmen. lenesum bihonko botawn yesetew esuw Medhanialem new. Sewma min akim alew? Gdyelachihum enmenina bertiten entsely. Geta bemebetachin amalajinet ytadegen. Amen.

Anonymous said...

Dear Brother and Sisters,
I don't think that the solution would be to return the former Patriarch Abune Merkorios to power, in my opnion and as your report stated, 1st he was also involved in racism, like "Gondere" and "Gojame" in power and so on, 2nd he resigned from power himself not kicked out as many thought and he replaced Abune Zena Markos. However history has repeated itself, Abune Paulos came and replaced everybody around with "Tigrayans", this was the second committed mace. In my opinion the Chruch should have a very clear and good Patriarch who is away from the politics and racism. I don't think that Abune Merkorios and his assistants think or worry too much for this church, they are exactly the other side of a coin, I mean Abune Paulos in one side and Abune Merkorios in the other, on one of them worried for the chruch,instead just for their power and fame. Even if Abune Merkorios is invited to come back to power , I don't think that he is going to accept it, now he is fine but the situation will not be easy for him to handle. In my opinion the Chruch needs a Patriarch who "believes in God's power" not his power, this will adjust the chruch of course, in short words one like Abune TekleHaymanot, who on body so far has raised his name for bad, he just devoted himself for his faith and his chruch, served God and his sons and passed away, whoelse do you need? I don't think this is going to be easy as the actual Bishops are all involved in politics, corrupted and other ugly things. "wogenoch" it is time to pray - don't blame any one of those - just pray , pray and pray for our Church, it is in a very critical condition now, could also be time to have a new era - ONLY God knows. Mihiret yawuredelen AMEN

መላኩ said...

እንደምን ከረምን፤ ወገኖች!

አባ ጳውሎስን ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

ውጭ አሉ የሚባሉትም አባት ከኃላፊነታቸው ወርደው ወደ ገዳም ቢገቡ ክፍፍሉ ሁሉ ሊወገድ ይችላል።
ውጭ ያሉት አገር ለቀው መውጣታቸው ትክክል አይደለም። ውጭ ያሉት የክርስቶስን መልዕክት በመካድ ለእስላሞች ጂሃድ ድጋፍ ማድረጋቸውም እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። ለፓትርያርክነት ብቃት የሚኖራቸው ከአገራቸው ያልወጡ አባቶች ብቻ ናቸው። እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያናችንን፤አገራችንን በገዳም ፈንታ፡ በኃብታሙ የውጭ አገር ለመኖር ከወሰኑትና በጣም ከተሳሳቱት አባቶች ይጠብቅልን!

Anonymous said...

It is great to read all of the comments and I am very impresed with the depth of our conversation. God is great and I am so very relieved that he passed away, but I am also very sadened. Meantime, the processes that we are going to follow to elect his successor , as many already said it,is very crutial. I have no doubt that TPLF and their junta are already ready to do all their best to put some one alike aba paulos. I have no also doubt that they will put some one they want to use the church as their political machien. This shouldnt be a question at all. The question need to be how much do we love our church? How far can we go to keep our holly, unique church rules and dogma? Will be ready to pay sacrify our selves for the church? If we are true ethiopian orthodox church believers, we need to be ready to pay any price to keep the true rules of the church so that we become united. WHO EVER COMES TO POWER, WE DONT NEED TO INVOLVE, WE HAVE OUR FATHERS TO DO IT. But we need to follow each step so that if any government body interfer, we need to get to the street and die for our church. I would rather chose to die than see TPLF play on my church again. Dont even disccus wethater TPLF will interfer or not. YES they are ready and they will. We need to unite adn unite , no more divission in our church. However, we shouldnt start to name names as a potential successor; the church has its own rules in accomplishing the task. Let that be done by our holly fathers. When it comes to Abune merkorios, I think he should die there before he flee the country and in my opinion he dont need to be considered as a successor. But he needs to be encouraged to go there and be a part of the election and if not elected, he can serve as a hager sibket appas. PLEASE DONT BE FOOLS ANY MORE, BE READY.
Thank you

Anonymous said...

በጣም ልብ የሚነካ እና በሳል ጽሑፍ ነው፡፡ በርቱ የቤተክርስቲያን ልጆች፡፡ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚለን ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ሰንበት ተማሪዎች ፣ ምዕመናን ፣ ማዕበራት፣ አንድነት ጎባኤዎች ወዘተ የሕይወት መስዋትነት ለመክፈል እና ቤተ ክርስቲያን ከጨለማው ዘመን ወጥታ እንድታበራ የምናደርግበት የቁርጥ ሰዓት ነው፡፡ http://awdemehret.org/?page_id=137 ድረ ገጽ ድምጽ በመስጠት ምን መደረግ እንዳለበት እንወያይ
አውደ ምሕረት

Anonymous said...

በጣም ልብ የሚነካ እና በሳል ጽሑፍ ነው፡፡ በርቱ የቤተክርስቲያን ልጆች፡፡ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚለን ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ሰንበት ተማሪዎች ፣ ምዕመናን ፣ ማዕበራት፣ አንድነት ጎባኤዎች ወዘተ የሕይወት መስዋትነት ለመክፈል እና ቤተ ክርስቲያን ከጨለማው ዘመን ወጥታ እንድታበራ የምናደርግበት የቁርጥ ሰዓት ነው፡፡ http://awdemehret.org/?page_id=137 ድረ ገጽ ድምጽ በመስጠት ምን መደረግ እንዳለበት እንወያይ
አውደ ምሕረት

Anonymous said...

I think this is the time for us to follow everything and play our role to have our speritual father. If any thing goes wrong we need to be ready to fight it! Lets pray for God to bless us with a good father!

Anonymous said...

LALENIBET ZEMEN MEWAJAW BE ENBA YETEMOLA TSOM TSELOT BICHA NEW. AMLAK YITAREKEN ZEND ENTSELY. DINGIL BEMILJAWA ATLEYEN. MELKAMUN EREGNA GETA YISETEN ZEND MELKAM FEKADU YIHUN.

Anonymous said...

ለፓትርያርክነት ብቃት የሚኖራቸው ከአገራቸው ያልወጡ አባቶች ብቻ ናቸው። አቡነ መርቆሬወስ አገር ለቀው መውጣታቸው ትክክል አይደለም። ሞት ፈርተው ነው እንጂ ወደ ገዳም ከመግባት ይልቅ ወደ ዓለማዊት አሜሪካ የገቡ፤ ማንም አላሰደዳቸው" ስልጣናቸውን አላግባብ ተቀምተዋል? አዎ በዚያ እንስማማለን። ይሁን እንጂ ወደ አሜሪካ ሄደው ሌላ ሴኖዶስ በሃይማኖታችን ላይ መመስረታቸው ትልቅ ስተት ነው። አገራችን እንኳን አቡነ መርቆሬወስን ወንበዴ የሚያስጠጋ ገዳሞች ሞልቷታል። ከ45ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የኦ.ተ.ምእመን ከጉዳይ ሳይጥፉ "የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በስደት ላይነች" እያሉ ሀይማኖታችንን ከሁለት ከመክፈል ለምን በገዳም ሁነው ለሕዝባቸው አቤት አላሉም። የመረጡት ይህችን አለም ነው፤ እንደ ምርጫቸውም እየኖሩባት ነው። ዛሬ ግን አንበሳው እስኪሄድለት እንደሚጠብቅ ጅብ በአሜሪካ ዋሻ ተደብቀው ኖረው ቀን የወጣ ሲመስላቸው ብቅ ሊሉ ከፈለጉ፤ በዚህ እግዚአብሔርን እና የ ኦ.ተ ምዕመንን ደስ ሊያስኙት የሚችሉ አይመስለኝም። ክርስትናችን ተጠብቃ የኖረችውኮ ስንቶች ጻድቃን አንገታቸውን ለሰይፍ፥ ስጋቸውን ለእሳአና ለአውሬ እየሰጡ ነው፤ ታድያ ገዳም ገብቶ ከመታገል ይልቅ አሜሪካ ገብቶ ዶላር መሰብሰብ???
ነገር ግን፤ በአቡነ መርቆሬወስ ስር ሆነው የኢትዮጵያ ኦ.ተ.ቤ. ክርስቲያንን የሚያገለግሉትን ጳጳሳትና ቄሳውስት የቀጣዩ ፓትርያርክና ቅዱስ ሴኖዶስ እንዲቀበላቸው ምኞቴን ልገልጽ እወዳለሁ።

Unknown said...

http://www.ethiotube.net/video/15661/ESAT-Special--Human-Rights-in-Ethiopia
watch this how his holiness Abune Merqorewos forcefully removed by the Government in 1991.

Aregawi said...


http://harep.org/ifaapr/7219.pdf

you can get Aregawis book from this site for free

Anonymous said...

አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ማሳወቅ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው መንግሥት ደጋፊ አለመሆኔን ነው።

ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ የተመራው ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትም የለኝም:: ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

Anonymous said...

Well written. Let's pray for our beloved church. God has answer for our question.

Anonymous said...

The article is based on one person thesis. He is already a looser what ever he says is not credible. His comments and views were always distractive.Instead of relaying on him it would have been better if you refer other sources.
As a Christain, i want to see one Patriarch and one synodoes. it is heartbreaking....
God is in control of everything. He knows who deserves this post. Nothing is not happened without His will and it won't in the future too.

Anonymous said...

አቡነ ጳውሎስን በትግሬነታቸው መውቀስ አግባብ አይደለም። አንዳንዶች በአስተያየት መስጫው ላይ ተጎንደርና ጎጃም ካልሆነ የሚሉ ይመስላል። የአቡነ ጳውሎስ ስሕተት ለጥሪአቸውና ከአባትነታቸው ጋር ከማይስማማ ሁኔታ ጋር መተባበራቸው ነው። ከኢሕአዴግ ጋር መተባበራቸው እንኳ በራሱ እንደ አዲስ ነገር ሊያስወቅሳቸው አይገባም። የቀደሙት አባቶችስ ከአጼዎቹ ጋር አልነበሩም? እውነት እንነጋገር ካልን ግን እንደ አባታችን ተክለሃይማኖት ማንም አይገኝም። ለነፍሳቸው ያደሩ ለማንም ያልተበገሩ። ባጭሩ ትግሬና አማራነቱ ላይ አይደለም ነገሩ ማለት ነው። እውጭ ያሉት አባት አገር ጥለው መውጣታቸው ለአገራዊ አባትነት እንዳይበቁ አደራውንና ክብሩን ቀንሶባቸዋል ባይ ነኝ። በሌላ አንጻር የጎሣን ነገር አጥብቀን ስናነሳ፣ ከኦሮሞና ከደቡብ ወዘተ ያሉትን አማኞች ስለሚያገልላቸው ይበልጥ የሚያቃቅርና የሚገፋ ይሆናል። ለእስልምና መስፋፋት ይረዳል።

Anonymous said...

ቤተክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አመታት በመንግስት ጣልቃ ገብነትለሁለት ከተከፈለች 20 አመት ሞልቱአታል ይሁን እንጅ ምቀኝነት፡ ዘረኝነት፤ አድመኝነት በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠሉ እንደመሆናቸው ዉድ የተዋህዶ ልጆች እና በዉጭም ሆነ በአገር ዉስጥ ያላቸሁ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እባካቺሁ ሰዉ የዘራዉን ያጭዳልና ዛሬ በዚህ ዘመን የተከላችሁት የልዮነት እዳ አሁን በቁም ካልፈታችሁት ለልጅልጅ ይተርፋል። መንግስትእንኩዋን ቢያዋክባችሁ ስለ ክርስቶስ መከራን ብትቀበሉ ለፅድቅ ይሆንላችሐል።
እርስ በርስ ይቅር መባባል ካቃታቸው፣ እርስ በርስ መዋደድ ካልሆነላቸው፣ ልዩነቶቻቸውን በማጥበብና እርቅም በማውረድ
አንድ መሆን ከተሳናቸው እንጸልይ/ጸልዩ ማለት ምን ማለት ነው? ሰላም: እርቅ: ፍቅርና: አንድነት ካልተፈለገ ጸሎት ለምን አስፈለገ?
“ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን
ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።” (የማቴዎስ ወንጌል 6:14, 15)
“ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች
ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። (የማርቆስ ወንጌል 11:25)
ማሳሰቢያ፡ አናዳንድ የቤተክርስቲያናችን ሰላም የማይፈልጉ የፖለቲካ ቁማር ስለሚጫወቱ አማኞች ልንነቃ ይገባል።

Anonymous said...

deje selam lemtadergut keftegna tigel betam amesegenalehu. aned teyake alegne min meselachehu kechalachehu ye lekane papasatun phone number ebakachehu post aderegulen ena hulachenem endewelelachew .please please

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)