(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ
ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው
ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ
በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት
ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡
እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ
መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ
መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን የተዘገበ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና
መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች
ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ደጀ ሰላም ዜናውን እየተከታተለች ማቅረቧን
ትቀጥላለች።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

22 comments:
May the God of Abraham give His Holiness eternal peace and rest.
May the Virgin Mary intercede him to God.
Amen.
Egziabher ende kidusan abatochachen nefsachewin be genet yanurlin!! AMEN!!!
The crying of the Waldiba Fathers is claiming many:
1. The president (a bit of scratch)
2. The PM
3. The Patriarch
Fathers of pure heart and soul, please pray for us - God may forgive us. You have the power to change an age into a different one - not expected.
ዘመናዊዋ መነኩሴ ከሌላ ጎራ
የት ሊገቡ ነው ሆነባቸው ጋራ፤
አስፉት የቀብር ጉድጓዱን
አባት ሚገቡበትን።
http://www.dejeselam.org/2011/05/blog-post_5236.html
Patriarch Dr. Abune Paulos (born 3 November 1935) was Abuna and Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (1992 - incumbent). For the last 20 years
Abune Paulos
Enthroned 1992
Reign ended Incumbent
Predecessor Merkorios
Personal details
Birth name Gebre Medhin Wolde Yohannes
Born 3 November 1935 (age 76)
Adwa, Tigray, Ethiopia
Residence Addis Ababa, Ethiopia
Alma mater Theological College of the Holy Trinity
Saint Vladimir's Orthodox Theological Seminary
Princeton Theological Seminary
ነፍስይማር ብያለሁ አሁንነው መጠንቀቅ ምክንያቱም ጅብበቀደደው ውሻ ይገባልና ለሚቀጥለው ምርጫ እንደግብጾች ቢቻል ሁሉንም የቤተክርስቲያንልጆችን የሚያሳትይፍ ቢሆን ያምባይሆንእንኩዋን የተመረጡ ምእመናንንና ማህበራትን የሚያሳትፍ ቢሆን መልካምው እላለሁኝ መቸም ቸኮልሽ እንደማትሉኝ እርግጠኛነኝ ምክንያቱም ካሁኑ መታሰብ ያለበት ጉዳይነው ደግሞ ሌላ 20 አመታትትን የመከራ ቀንበር ቤተክርስትያናችን እምታስተናግድበት አቅሙያላት አይመስለኝም ቢቻል ለምርጫ የሚቀርቡት አባቶች የሂወት ታሪካቸው እነሱ በሚሉት ሳይሆን የሚያስተዳድሩት ምእመን ሀሳብ በሚሰጠው ተገምግመው መሆን አለበት ብየ አምናለሁኝለማንኛውም በጥልቀት መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆኑና ቢቻል የአዋጅ ጸሎት ቢደረግና ሁሉምምእመናን ለቤተክርስቲያናችን የሚቆረቆርና መንጋውን በትህትና የሚመራ አባት እንዲሰጠን ወደ ቤተክርቲያን አናትና መሰረትወደሆነው ወደቸሩ መድሀኒአላም ምህላ ማድረግ ይገባናል ቸርያሰማን አሜን
እርቃናችንን ወደዚህ አለም መጥተን እርቃናችንን ወደመጣንበት እንዲሁ እንመለሳለን። ነብሳቸውን አምላከ ቅዱሳን ከአብርሃም ከይሰሃቅ ጋር ያኑርል። በዚህም ላዘንን ሁሉ አፅናኝ መንፈስ ቅዱስን ይላክልን።
ማርያም አዘነችና ከምር
የልጇ ስም እንዲከብር፤
ጠራች እንግዳ ለሰርጉ
ሁሉም ለፍቅሯ እንዲጓጉ፤
ሆኖ ይሆን የእንግዳው ስለቱ
በፍልሰቷ የተጠራ ወደ ቤቱ?
ምን ሊመልስ ነው አንደበቱ
ልጅ ሲጠይቀው ስለ እናቱ?
ምን ልትመልስ ነው ነፍሱ
ሲጠየቅ ስለራሱ ?
nefes yimar.
Egzabher amlak yewdedewn neger aderege. ye amlakachen semu lezelalm yetemesegene yehun.ye dengele mariam amalagenet le zelalem ytemesegene yehune.
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር። ሐውልት ከመስራት ድነናል። ከቦሌ ተነስቶ መቃብራቸው ላይ ይቁምልን።
ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም በቃችሁ እያለ ነው፡፡ ቆመናል ማንም አይነቀንቀንም ለሚሉት ግልጽ የእግዚአብሔር መልዕክት፡፡
እጃችሁን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ አንሱ፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ በክፉ አድራጊዎች ላይ ዘወትር አያንቀላፋም፡፡ ከደሙ ለመንጻት የክፋት ካባችሁን አውልቁና ጣሉ፡፡
እግዚአብሔር ያቡነ ጳውሎስንም የአቶ መለስንም ነብስ ይማር፡፡
Believe it or not the worst is coming we have to repent from our sin.
የአቡነ ዻውሎስን ነፍስ ይማር። የተተኪውን አባት ምርጫ ለእግዚአብሔር እንተው።ከአባቶቻችን የነበረ አምላክ ከኛ ጋር እንዲሆን በይሁዳ ምትክ ቅዱስ ማትያስ እንደተካ አንተ ምረጥ እንበለው። ይህ ሲሆን ታሪክ ይሰራል በጣት
ቅሰራ ከሆነ" የአቡነ ጳውሎስ 2ተኛ ምዕራፍ ይቀጥላል
ዲሚስኪ ከአትላንታ
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያሊክ ከዚህ አለም በሞት በስጋ በመለየታቸው እጅግ በጣም አዝነናል። ሆኖም ግን እውነተኛ
የጌታ ሐዋርያ ፣ የሐይማኖታችን አርበኛ፣ በትእግስት የሚገባውን ሩጫ ፈፅሞ ወደ ጌታው በመሄዱ ደግሞ ፍፁም ክርስቲያናዊ ደስታና ሃሴት
ተሰምቶናል። ሰው የማያውቀውን የድል አክሊል የሚያውቀው አምላኩ እግዚአብሔር እንደሚያቀዳጀውም በምሥሉ ልብ እናምናለን።
እኛም ክርስቲያኖች ከብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፤ ፈተናንና መከራን በትእግስት ማሳለፍን ተምረናል። እግዚአብሔር አምላካችን ከቅዱስነታቸው ረድኤትና በረከት ያካፍለን እንላለን፣ አሜን፣ አሜን፣ አሜን።
የመነኩሴው፡ነብስ፡ጮሃ፡ተፈረደላት።የገብረ፡መድኅን፡ሞት፡ ካስጨፈጨፋቸው፡ኢትዮጵያውያን፡ነብስ፡ጋራ፡ለምመጣጠን፡ ባማይችል፡መሞቱ፡ለቅድስት፡ተዋኅዶ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ትልልቅ፡ ግልግል፡ነው።ነብሱ፡የሥራዋን፡ይስጣት።
Nefisachewun Yimarlin. Egnanim Yikir yiblem. bizu simachewun atifitenachewal. motachewun nafikenal. Betam enasazinalen.Egiziabher Yiker Yibelem.
“የጫንክብኝን አውርድልኝ
ያመጣሀውን ውሰድልኝ”
ብየ እንጂ የተማጸንኩት
ግደል አትግደል መች አልኩት
‘እሱ’ ም ሚስጥሩን አልገለጠ
የሚሻለውን መረጠ
አሁንም….ተዘጋጅ ባለተራ
ስምህ እስከሚጠራ
dejeselamoch congratulations! Motulachehu! Gedelachewachew!
egzabher yewededewn aderge nefse yemar
two down (thew PM and the patriarch) , who is next ? what a cleansing !these two people were watching when thousands of innocent people got killed. i cry for those not for these.
May God let to Rest His soul in peace. We all have to pray for the unity of our church and fathers . We all should repent from our sin to please God. Pray for our church fathers to give them wisdom so that they can lead us and be the perfect example to all Christians. God have mercy!!!
Post a Comment