August 16, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ

  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል፤ መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክሩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ታሽጓል፤
  • ጥቂት ብፁዓን አበው ወደ ባልቻ ሆስፒታል ሄደዋል፤ አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
    ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
  • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል:: (ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
  • “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን” ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
  • በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/READ THIS NEWS IN PDF) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ንጋት ላይ በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡


ፓትርያርኩ ከትናንት በስቲያ፣ ነሐሴ 8 ቀን 2004 ዓ.ም ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ገብተው ሕመማቸውን ለረጅም ጊዜ ሲከታተሉላቸው በቆዩት የሆስፒታሉ ዶክተሮች ሕክምና ቢደረግላቸውም በቆየባቸው በሽታ ዛሬ ንጋት 11፡00 ላይ መሞታቸውና አስከሬናቸውም በዚያው እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የምንገኝበትን የፍልሰታ ለማርያም ጾም በድሬዳዋ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ወቅድስት አርሴማ የሴቶች ገዳም የማሳለፍ ልማድ ቢኖራቸውም በዘንድሮው ሱባኤ ግን መሰንበቻቸውን ያደረጉት የፕትርክናው መንበር በሚገኝበት በአዲስ አበባ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ነበር፡፡

በቀደሙ ዘገባዎቻችን እንደገለጽነውና በሰሞኑ የሱባኤው ቅዳሴ ውሎዎች እንደተረጋገጠው÷ አቡነ ጳውሎስ የጀመሩትን ጸሎተ ቅዳሴ ለመጨረስ ተስኗቸው ቅዳሴው ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት /እነ ብፁዕ አቡነ ገሪማ/ እየተተኩ እንዲጠናቀቅ ሲደረግ ነበር፡፡ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት÷ ፓትርያርኩ በጸሎተ ቅዳሴው መካከል በወንበር ላይ እንደተቀመጡ ሁለት እግራቸውን ፊት ለፊታቸው በሚገኝ ሌላ ወንበር ላይ ሰቅለው ታይተዋል፤ ወደ መኖሪያቸው ሲወጡም ይኹን ሲገቡ ዙሪያቸውን በረዳቶቻቸው ተደግፈው ነው፡፡ ከቆየባቸው የስኳር በሽታና ሌሎችም ሕመሞቻቸው መወሳሰብ ጋራ በተያያዘ ሁለቱም እግሮቻቸው ከአውራ ጣታቸው ጀምሮ እስከ ጉልበታቸው ድረስ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል፡፡ እግራቸው እንዲቆረጥ ጤናቸውን በሚከታተሉላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ሐኪሞች ሲነገራቸውን ቢቆይም ፓትርያርኩ የሐኪሞቹን ምክርና ማሳሰቢያ ችላ ብለው በውጭ ምንዛሬ በሚገዟቸውና በመርፌ በሚወስዷቸው መድኃኒቶች ራሳቸውን ሲያስታምሙ ቆይተዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ከትናንት በስቲያ ወደ ሆስፒታል የገቡት ታዲያ በዚሁ እግራቸው ላይ በከፍተኛ ጥዝጣዜ እየተሠቃዩ በነበረበት ኹኔታ ነበር፡፡


በኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው አከባበርና ከዚያም ወዲህ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚካሄዱት ስብሰባዎች ጥልቅ የመቀዘዝ ስሜት ይታይባቸው የነበሩት አባ ጳውሎስ÷ ትምክህታቸውን በሚገልጹባቸውና እንደ አለኝታም በሚቆጥሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በጽኑ መታመም ክፉኛ መደናገጣቸውና ግራ መጋባታቸው፤ በግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤም በሃይማኖት ሕጸጽ ከተጠየቁ ወዲህ [በመጽሐፍ መልክ ባሳተሙት የዶክትሬት ጥናታቸው ሕጸጹ የተገለጸባቸውን አንቀጾችና ዐረፍተ ነገሮች አላካተቱም] በአያሌው መጨነቃቸው፤ ከወርኀ ግንቦት ጀምሮ ከቅዱስ ሲኖዶሱ በላይ አመራር ሰጪ ለመኾን ሕገ ወጥ ቡድኖችን በማደራጀት ያደረጓቸው ጥረቶች መክሸፋቸው፤ ከዚህም ሁሉ ጋራ ቀደም ሲል በሄዱበት እርሳቸውን አክብረው የሚከተሏቸው በርካታ ጳጳሳት የሸሽዋቸው መኾኑ እዚህም እዚያም ከሚሰማው የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ምእመናንና ወዳጆች ሐዘንና ጸሎት ጋራ ተደማምሮ የፈጠረባቸው አካላዊና መንፈሳዊ መጎሳቆል ለተመልካች በጉልሕ የሚረዳ እንደ ነበር የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡

ሐምሌ 5 ቀን 1984 ዓ.ም የተሾሙትና ለኻያ ዓመታት በፕትርክና የቆዩትን የአቡነ ጳውሎስን የቀብር ሥነ ሥርዐት ለማስፈጸም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ ጠዋት ከመከሩበት በኋላ “የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ” መቋቋሙ ተዘግቧል፡፡ የፓትርያርኩ የሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤትና ፕሮቶኮል ሓላፊዎችም በየአህጉረ ስብከቱ ስልክ በመደወል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳማትና አድባራት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በርካታ አባቶች፣ አገልጋዮችና ምእመናን በመንበረ ፓትርያርኩ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመገኘት ኀዘናቸውን እየገለጹ ሲኾን ስለ ጸሎተ ፍትሐቱ እና የቀብር አፈጻጸም መርሐ ግብሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚያወጣው መግለጫ እየተጠበቀ ነው፡፡

የአቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በመጀመሪያ የደጀ ሰላም ዜና መገለጹን ተከትሎ በርካታ ወገኖች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዓለማዊው አገራዊው ኹኔታ አኳያ በወሳኝ ኹኔታ ላይ እንደምትገኝ፣ በሹመታቸው ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት የከፈሉት አቡነ ጳውሎስ በሞታቸውም እንደይከፋፍሉን ይልቁንም ቀጣይ ርምጃዎች ያለፉትን ስሕተቶች የሚያርሙና እንዳይደገሙ የሚያደርጉ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሁለንታዊ አገልግሎት መጠናከርም የሚያግዙና ብሔራዊ ክብሯን የሚመልሱ በመኾናቸው ላይ የተረጋጋና ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ እንዲሠራ እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

በፓትርያርኩ ሞት ሰበብ ዘመዶቻቸውና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንዳያሸሹ ማሳሰቢያ እየተሰጠም ይገኛል፡፡ በተለይም የ”አቡነ ጳውሎስ ቁም ተዝካር” በተባለው ኻያኛው በዓለ ሢመት አከባበር ላይ የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ የነበሩት ውሉደ ጳውሎስ (እነ እጅጋየሁ በየነ) በአቡነ ጳውሎስ ስም የሚጠራ “ጳውሎስ ፋውንዴሽን” እናቋቁማለን በሚል እየተሯሯጡ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

ለ‹ፋውንዴሽኑ› መቋቋም ያስፈልጋል የተባለውን ገንዘብም እንደተለመደው ከአድባራትና ገዳማት እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ኢኮኖሚያዊ ምንጮች ለመሰብሰብ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን የገለጸው ምንጩ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነን፣ መልአከ ፀሐይ በቀለ ተሰማ (ቤቴል ቅዱስ ሚካኤል)፣ ሰሎሞን በቀለን (ቦሌ መድኃኔዓለም)፣ ቀሲስ ግሩም መልአክ ታዬ (ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል (ጠቅላይ ቤተ ክህነት) በዋና አደራጅነት ጠቅሰዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ ጠንካራ ክትትል በማድረግ የወይዘሮዋንና ሌሎች አካላትን ችግር ፈጣሪነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማቆም እየሠራ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡

በአቡነ ጳውሎስ እምቢተኛነት ሳይካሄድ በቀረውና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተለይም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከእምባ ጋራ “የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፈረድ” በሚል ሐዘናቸውን ከገለጹበት የሐምሌው ልዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በኋላ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ሦስት አባላት የሚገኙበትና በብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሚመራ ኮሚቴ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባቶች ጋራ የሚካሄደው የሰላምና ዕርቅ ንግግር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለአስታራቂ ኮሚቴው ምላሽ የሚሰጥ ጽሑፍ በመዘጋጀት ላይ እንደነበርም ተነግሯል፡፡ የሰላምና ዕርቅ ንግግሩ እንዳይቀጥል ዕንቅፋት ሲፈጥሩ የቆዩት አቡነ ጳውሎስ ሞታቸው በሂደቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ገና የሚታይ ይኾናል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

በ1991 ዓ.ም የወጣውና በሥራ ላይ የሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያን
ፓትርያርክ ድኅረ ዕረፍት ወይም ከሥልጣን መውረድ (አንቀጽ 16) ኹኔታዎች
በአንቀጽ 17 ንኡስ አንቀጽ 1 – 3 የሚከተለውን ይላል፡፡

አንቀጽ 17 - ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ
1.          ፓትርያርኩ በሞት ሲለይ ወይም በዚህ ሕግ አንቀጽ 16 መሠረት ከሥልጣኑ ሲወርድ ቅዱስ ሲኖዶስ በሹመት ቀደምትነት ካላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በዕለቱ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ መርጦ ይሾማል፡፡ የተተኪው ፓትርያርክ ምርጨም ይካሄዳል፡፡
2.         የተተኪው ፓትርያርክ ምርጫ አፈጻጸም እንደጊዜውና እንደ ሥራው ኹኔታ እየታየ ከ40 እስከ 80 ቀን ባለው ጊዜ ይኾናል፡፡
3.         የዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ተግባር፡-
ሀ) ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ጊዜያዊ ጉዳዮችን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋራ እየመከረ ያከናውናል፡፡
ለ) በፓትርያርኩ ምርጫ ጊዜም የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ኾኖ ምርጫውን ያስፈጽማል፤ እርሱ ግን ከምርጫው አይገባም፡፡

ቀጣይ ዜናዎችን ይከታተሉ

15 comments:

Genene said...

አሁን ያ ቦሌ መድሀኒአለም የቆመውን ድንጋይ ማፍረስ ልጀምር

Anonymous said...

Dear DS, Ahun ahun min ayinet tilacha endalachihu le Patriaricu eyegebagn hede. Lik ende agerachin weg bahil, bemejemeriya nefsachew yimar mebal sigebachihu gena ke'ahun mewkes mejemer tizibt lay yitilachuhal enji esachew ande arifewal. Yemikonin yemiyatsedk egziabher new, Egziabher firdun yisetachewal. Gin be'ewunet yebetekiristiyan lij kehonachihu, muwut ayiwekesim new yemibal ena lezih subae enquan yesachewin kifu neger bich eyanesachihu mewkes bititewu tiru yimesilegnal. Yenantem nefs be'ejachihu ayidelechim. Be'Egziabher enji. Egziabher amlak nefsache begent yanur lenatem libona yistachihu.

Anonymous said...

Dear DS, Ahun ahun min ayinet tilacha endalachihu le Patriaricu eyegebagn hede. Lik ende agerachin weg bahil, bemejemeriya nefsachew yimar mebal sigebachihu gena ke'ahun mewkes mejemer tizibt lay yitilachuhal enji esachew ande arifewal. Yemikonin yemiyatsedk egziabher new, Egziabher firdun yisetachewal. Gin be'ewunet yebetekiristiyan lij kehonachihu, muwut ayiwekesim new yemibal ena lezih subae enquan yesachewin kifu neger bich eyanesachihu mewkes bititewu tiru yimesilegnal. Yenantem nefs be'ejachihu ayidelechim. Be'Egziabher enji. Egziabher amlak nefsache begent yanur lenatem libona yistachihu.

Anonymous said...

wey nefes yemar ABUN FANUEL gdachew fela abun fanuel engedi men yhonu ayeee sew yetdgfut sew wedeq erso ahun neshu aygbum

ዘሐመረ ኖህ said...

...ቀጣይ ርምጃዎች ያለፉትን ስሕተቶች የሚያርሙና እንዳይደገሙ የሚያደርጉ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሁለንታዊ አገልግሎት መጠናከርም የሚያግዙና ብሔራዊ ክብሯን የሚመልሱ በመኾናቸው ላይ የተረጋጋና ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ....
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያናችንን እና የሃገራችንን መከራ በቃችሁ ሊለን ይሆን የባሰ እንዳይመጣ የበለጠ መጠንቀቅ ይኖርብናል
በቀደመው ዜና ላይ በተሰጠው አስተያየት መሠረት በርግጥ የተተኪውን አባት ምርጫ በጸሎትና በምህላ ለእግዚአብሔር በመስጠት በይሁዳ ምትክ ቅዱስ ማቲዎስ እንደተተካ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ ሰውም የራሱን ድርሻ መወጣት እንደሚኖርበት ብላቴናዋ ከጀርመን እንዲህ ብለው የሰጡት አስተያየት ሚዛን የሚደፋ ነው
ብላቴናዋ ከጀርመን said...
ነፍስይማር ብያለሁ አሁን ነው መጠንቀቅ ምክንያቱም ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባልና ለሚቀጥለው ምርጫ እንደግብጾች ቢቻል ሁሉንም የቤተክርስቲያን ልጆችን የሚያሳትይፍ ቢሆን ያም ባይሆን እንኩዋን የተመረጡ ምእመናንንና ማህበራትን የሚያሳትፍ ቢሆን መልካም ነው እላለሁኝ መቸም ቸኮልሽ እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ካሁኑ መታሰብ ያለበት ጉዳይነው ደግሞ ሌላ 20 አመታትትን የመከራ ቀንበር ቤተክርስትያናችን እምታስተናግድበት አቅሙያላት አይመስለኝም ቢቻል ለምርጫ የሚቀርቡት አባቶች የሕይወት ታሪካቸው እነሱ በሚሉት ሳይሆን የሚያስተዳድሩት ምእመን ሀሳብ በሚሰጠው ተገምግመው መሆን አለበት ብየ አምናለሁኝ ለማንኛውም በጥልቀት መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆኑና ቢቻል የአዋጅ ጸሎት ቢደረግና ሁሉም ምእመናን ለቤተክርስቲያናችን የሚቆረቆርና መንጋውን በትህትና የሚመራ አባት እንዲሰጠን ወደ ቤተክርቲያን አናትና መሰረት ወደሆነው ወደ ቸሩ መድሀኒአላም ምህላ ማድረግ ይገባናል ቸር ያሰማን አሜን
እኔም እዚህ ላይ ይምጨምረው የለኝም አሜን
ቸር ያሰማን
ዘሐመረ ኖህ

Anonymous said...

Deje Selam Ahun Masawek-Mezegeb Yalebachuin Neger Mawk Alebachihu Abune Pawlos Arefu- Hedu -Motu
Kezih Behala Bizu Menageru Sewn Masenakel Endayihon Asibo Wedefit Sile Mitekaw Patiryarik Maseb Yishalal Tishalin Sedij Tibisin Ametsahu Endayihon Negeru
Abune Merkorewos Temelsew Bigebu Selam Yemimetsa Kehone Or Menfesaw Sew Ketegege Addis Memretsi Yemshal Kehone Menegageru Yibejal Enj Fayilu Ketezega Behala Yemoten Mewkes Mekefafeln Yabezal Asibubet

Anonymous said...

ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ አረፉ:: ቤተ ክርስቲያንም አረፈች:: እስኪ ለራስ ክብር ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት መፋጠን የሚጨነቅ አባት ይሰጠን ዘንድ ጠንክረን እንጸልይ::

Anonymous said...

አምላክ ዋናውን ገላገለን ስንል ስራስሮቹ ነፍስ እንዳይዘሩ ሁላችን በትጋት ልንጸልይና ልንሰራ ይገባል!

አምላከ ተክለ ሃይማኖት ትጉህ እረኛ ይሹምልን

Anonymous said...

are you happy now?

Abel said...

የዚህ ጽሑፍ አላማ ዛሬ በሞት የተለዩን አባታችን ላይ ለመሳለቅ አይደለም። ይልቁንም ምን ያህል የመንፈስ ክስረት እንዳጋጠመኝ እንድትረዱልኝ ነው። በተጨማሪም ቀጣዩ አባታችን፤ ከእንዲህ አይነቱ የመንፈስ ክስረት እኔንና መሰሎቸን እንዲያወጡን ለመማጸን፤ ያለፉትን እኒህ አባት ስህተት እንዳይደግሙ ለማሳሰብ ነው። ዜና እረፍታቸውን ስሰማ ልክ ከፍተኛ የሆነ የማስታገሻ መድሃኒት እንደወሰደ ሰው አንዳች ነገር ከላዬ ሲቀልና ሲወርድ ተሰማኝ። ውስጤን ደስታ ቢጤ ኮረኮረው። ግን ለምን? እኔ እኮ ክርስቲያን ነኝ። ይህ ስሜት እንኳንስ ከአንድ በክርስቶስ ከሚያምን ክርስቲያን ፤ከማያምን ነገር ግን ሰው ከሚባል ፍጡር መውጣት የለትም። ምን ያህል የመረረ ጥላቻ ቢያድርብኝ ይሆን? እኒህ አባት በግል ያደረሱብኝ ምንም አይነት በደል የለም። ነገር ግን በጎቼን ጠብቁ ብሎ ባዘዘው መንበር ላይ ተቀምጠው የሚሰሩትን ግፍ ከተለያዩ ሚዲያዎች ሰምቻለሁ፤ አንብቤአለሁ፤ እንዲሁም በተግባር የሰሯቸውን ስህተቶች ተመልክቻለሁ። ለበጎ ነገር ይቁሙ፤ ይተው ሲባሉ እልህ እንደተናነቃቸው ያለፉ አባት ናቸው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ብዙ በዙሪያቸው ያሉ አባቶችን አስለቅሰዋል፤ አሳዝነዋል። ዛሬ ወደ ማይቀረው መቃብር ወረዱ። እንዲህ ለማይቀረው ነገር ለምን ይሆን መልካም ነገር መስራት ያቃተን? በተለይ የክርስቶስን መንገድ እየተከተሉ በምዕመናን አናት ላይ መፈንጨት ምን የሚሉት አባዜ ይሆን? ስንቶች አሁን በሕይወት የሃይማኖት አባቶች ከዚህ አይነት መቅዘፍት ይማሩ ይሆን? አንዱ ወገን ለገዢው ሌላው ወገን ለተቀዋሚው ወግኖ ድፍን የኢትዬጵያን ክርስቲያን በዚህ የአሰላለፍ ስልቻ ውስጥ ለመክተት የተሰናዱ የቤተክርስቲያናችንን አባቶች ቤት ይቁጠራቸው። ገዢው መንግስት ውሸተኛ በሙሉ ተቀዋሚው እውነተኛ እንደ ሆነ ለመመስከር የሚዳዳቸው አባቶች በአውደ ምረቷ ላይ አልጠፉም።

አሁን በሕይወት ያሉ አባቶቻችን ከፓለቲካው መዘውር ውስጥ ወጣ ብለው እንዲያስቡ ወሳኙ መዕራፍ ላይ ያሉ ይመስለኛል። በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗ የሐይማኖት ገበሬ አንጅ በሬ አትፈልግም። ይህ ካልሆነ በጎቹ ይበተናሉ፤ መንበሩን ብቻውን ይቀራል። በምዕራቡ አለም የምናዬው የመንፈሳዊ ሕይወት ክስረት ወደ አገራችን ለመግባት ሰፊ በር ይከፍታል። በድህነታችን ላይ መንፈሳዊ ኪሳራ ሲታከልበት ልንቋቋመው ወደማንችለው አዘቅት ውስጥ ልነገባ እንችላለን። ስለዚህም በክርስቶስ የተጠመቅን ምዕመናን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ቀናኢ አባቶች ከማንኛውም ሊደርስባቸው ከሚችለው ስጋዊ አደጋ ጠብቀን፤ ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመሯት የሁላችንም ድርሻ መሆን አለበት።

እግዚአብሔር የመንፈስ ልጆቹን ይጠብቅ።

Anonymous said...

endet des alegn meselachehu?

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ የመለሰ ዜናዊን መታመም ሰምተው ለማጥመቅ መስቀላቸውን ይዘው መለሰ ዜናዊ ካለበት ክፍል ይደርሳሉ።
ልክ እንደ ደረሱ:-
መቼም አንተ እምነት የለህም። ላጥምቅህና ከዳንክ ታምናለህ ይሉታል።
መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- በጣም ተጨንቋልና ኧረ አሁንም አምናለሁ አጥምቁኝ ይላቸዋል።
አባ ጳውሎስም:- መስቀላቸውን አንስተው ማየ ጸሎቱን ከባረኩ በኋላ አጠምቀከ በስመ ሕወሃት፤አጠምቀከ በስመ ብአዴን፤አጠምቀከ በስመ ኦሕዴድ ሲሉት ይጮህ ጀመረ።
አባ ጳውሎስ:- ማነህ ልቀቅ ? ሲሉት
መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- አልለቅም አበበ ገላው ነኝ፤ አልለቅም አበበ ገላው ነኝ ፤ አልለቅም አበበ ገላው ነኝ ፤አልለቅም አበበ ገላው ነኝ፤ አልለቅም አበበ ገላው ነኝ እያለ melese zenawi is Dicator, melese zenawi is Dicator, melese zenawi is Dicator Free Iskinder Nega and all political prisnors! We need freedom! Food is nothing without freedom! እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲያንጎደጉድባቸው።
አባ ጳውሎስም:- መጮህህን ትተህ ትለቃለህ አትለቅም? ሲሉት
መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- ሳልገድል አልለቅም ይላል።
አባ ጳውሎስም:- እንባ እየተናነቃቸው እባክህ ልቀቀው ይሉታል።
መለስ ላይ ያለው አጅሬ:- እለቃለሁኝ ግን እሱን ከለቀቅኩኝ ወደ አንተ ተዛውሬ አንተን ነው የምገድልህ ይላል።
አባ ጳውሎስም:- አይ በቃ ተው። እዛው እንደ ጀመርክ ጨርስ። እኔ ትንሽ ልሰንብትበት ብለው ማጥመቁን ትተው ወደ ቤታቸው ሄደው አልጋ ላይ ሰነበቱ።
ትንሽ ልሰንብት እንዳሉ ላይመለሱ ሄዱ።
ነፍሳቸውን በመለስና በሕወሃት አጠገብ ያሳርፍልን። አሜን!!!!!!

Anonymous said...

you guys are nonsense! why you are dancing about our father death?

Hailu said...

May God bless his soul. He is gone now.

The damage the late Aba Gerbremedihin has caused is enumerable. Look how we are responding to the death of a person who we would have mourned otherwise had he assumed the position legitimately according to canon law, had he done the right things and had he been on our side.

However, the most glaring damage of all, I think, is the division he has brought to the Ethiopian Orthodox Church and his complacence while the age old monastery, Waldiba, is being desecrated.

Any ways, God is the judge here. It is a relief for the church that he is gone now.

Now the most important question should be how we can restore dignity, unity and holy leadership going forward.

Possible scenarios that may follow after the passing of Aba Gebremedihin are the following.

1. Acknowledging Patriarch Merkorios for his life span and help close the reason for the division in our beloved church.

2. TPLF will orchestrate a fake election and assign another person of their own and try to continue the status quo leading to a continued suffering of our beloved church and its followers.

3. An unhealthy free election be held by the synod in Addis and the fathers choose one amongst themselves. This will still be assigning another patriarch while a legitimate one is still alive. The problem that shook the country for the past 20 years will continue with this scenario as well.

We are fed up of the division, trivialization of our values, corruption, desecration of our holly places, etc. We are tired of the weeping, the heart aching and helplessly murmurring as we see ill being done to our Orthodox Church.

I pray to God to give the fathers of the church to use this opportunity to heal the division the late Aba Gebremedihin caused to the church. For the purpose of mending the splinter in the church, restoring the legitimate Patriarch, Abune Merkorios, is the best scenario. Unless God does his divine intervention, such a wise idea to solve the church's most significant problem may be put to the side.

May God bless our church and Ethiopia! Nefis Yimar Lemotut.

Anonymous said...

የዚህ ጽሑፍ አላማ ዛሬ በሞት
የተለዩን አባታችን ላይ
ለመሳለቅ አይደለም።
ይልቁንም ምን ያህል
የመንፈስ ክስረት
እንዳጋጠመኝ እንድትረዱልኝ
ነው። በተጨማሪም ቀጣዩ
አባታችን፤ ከእንዲህ አይነቱ
የመንፈስ ክስረት እኔንና
መሰሎቸን እንዲያወጡን
ለመማጸን፤ ያለፉትን እኒህ
አባት ስህተት እንዳይደግሙ
ለማሳሰብ ነው። ዜና
እረፍታቸውን ስሰማ ልክ
ከፍተኛ የሆነ የማስታገሻ
መድሃኒት እንደወሰደ ሰው
አንዳች ነገር ከላዬ ሲቀልና
ሲወርድ ተሰማኝ። ውስጤን
ደስታ ቢጤ ኮረኮረው። ግን
ለምን? እኔ እኮ ክርስቲያን
ነኝ። ይህ ስሜት እንኳንስ
ከአንድ በክርስቶስ ከሚያምን
ክርስቲያን ፤ከማያምን ነገር
ግን ሰው ከሚባል ፍጡር
መውጣት የለትም። ምን
ያህል የመረረ ጥላቻ
ቢያድርብኝ ይሆን? እኒህ አባት
በግል ያደረሱብኝ ምንም
አይነት በደል የለም። ነገር
ግን በጎቼን ጠብቁ ብሎ
ባዘዘው መንበር ላይ
ተቀምጠው የሚሰሩትን ግፍ
ከተለያዩ ሚዲያዎች
ሰምቻለሁ፤ አንብቤአለሁ፤
እንዲሁም በተግባር
የሰሯቸውን ስህተቶች
ተመልክቻለሁ። ለበጎ ነገር
ይቁሙ፤ ይተው ሲባሉ እልህ
እንደተናነቃቸው ያለፉ አባት
ናቸው ብል ማጋነን
አይሆንብኝም። ብዙ
በዙሪያቸው ያሉ አባቶችን
አስለቅሰዋል፤ አሳዝነዋል።
ዛሬ ወደ ማይቀረው መቃብር
ወረዱ። እንዲህ ለማይቀረው
ነገር ለምን ይሆን መልካም
ነገር መስራት ያቃተን?
በተለይ የክርስቶስን መንገድ
እየተከተሉ በምዕመናን አናት
ላይ መፈንጨት ምን የሚሉት
አባዜ ይሆን? ስንቶች አሁን
በሕይወት የሃይማኖት አባቶች
ከዚህ አይነት መቅዘፍት
ይማሩ ይሆን? አንዱ ወገን
ለገዢው ሌላው ወገን
ለተቀዋሚው ወግኖ ድፍን
የኢትዬጵያን ክርስቲያን በዚህ
የአሰላለፍ ስልቻ ውስጥ
ለመክተት የተሰናዱ
የቤተክርስቲያናችንን አባቶች
ቤት ይቁጠራቸው። ገዢው
መንግስት ውሸተኛ በሙሉ
ተቀዋሚው እውነተኛ እንደ
ሆነ ለመመስከር የሚዳዳቸው
አባቶች በአውደ ምረቷ ላይ
አልጠፉም።
አሁን በሕይወት ያሉ
አባቶቻችን ከፓለቲካው
መዘውር ውስጥ ወጣ ብለው
እንዲያስቡ ወሳኙ መዕራፍ ላይ
ያሉ ይመስለኛል። በአጠቃላይ
ቤተክርስቲያኗ የሐይማኖት
ገበሬ አንጅ በሬ አትፈልግም።
ይህ ካልሆነ በጎቹ ይበተናሉ፤
መንበሩን ብቻውን ይቀራል።
በምዕራቡ አለም የምናዬው
የመንፈሳዊ ሕይወት ክስረት
ወደ አገራችን ለመግባት ሰፊ
በር ይከፍታል። በድህነታችን
ላይ መንፈሳዊ ኪሳራ
ሲታከልበት ልንቋቋመው
ወደማንችለው አዘቅት ውስጥ
ልነገባ እንችላለን። ስለዚህም
በክርስቶስ የተጠመቅን
ምዕመናን በሙሉ
የቤተክርስቲያናችን ቀናኢ
አባቶች ከማንኛውም
ሊደርስባቸው ከሚችለው
ስጋዊ አደጋ ጠብቀን፤
ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመሯት
የሁላችንም ድርሻ መሆን
አለበት።
እግዚአብሔር የመንፈስ
ልጆቹን ይጠብቅ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)