August 14, 2012

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል


. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደ ነበሩ የተናገሩት የዜናው ምንጮች÷ የፓትርያርኩን አጣዳፊ ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡ ይኹንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን ተነግሯል፤ ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አባ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ጤናቸውን ለመከታተል የሚያደርጉት ሳምንታዊ ወጪ ከስድሳ ሺሕ ብር በላይ ማሻቀቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡


53 comments:

Anonymous said...

ሰው የዘራውን ያጭዳል
ካድሬው ጳውሎስ አሁን ንስሃ ገብተህ ካምላክህ ጋር ታረቅ እግዚአብሄር አምላክ መሃሪ ነው በስሙ ነግደሃል ሰርቀሃል እና ይቅርታውን እሻ >>>

Anonymous said...

Egiyabhare Bemihretu ygobgnachew!! Kifu memegnet tiru aydelem...Betkristiyanchinin Egziyabhare ytebikal enji sew aytebikatim...enam Ebakachuhn bezi filiseta tsom kifu kal aywtan!!

Unknown said...

Manew "Kefu Yetemegnew"? Yaltestafewen neew yemetenagerew. Zenawen report madreg degmo gedetachen neew.

Anonymous said...

Amlak mihretun yilakilachew!

Anonymous said...

chere were yasman haymanoyachen kemtfat danche egyzabher berasu siltan lehymanotum lehageryun yemaysfelguten yateral behaylu

Anonymous said...

Man yawuqal Tewahedo selam litagegn yihonal

Anonymous said...

I heard that he was busy celebrating his 20th celebration cermony coming to power. May be he is tired of the whole 15 days celebration. To your surprise I thaught he will celebrate the occasion with the poor but he was dining & wining with thw rich in Sher-aton. I saw it in TV windows.

Ayi yichi kentu alem sintun gud tasayinaleshi!!

Egiziabher Ethiopian asibaat ebakih

Anonymous said...

Dear Deje selam

Thanks a lot for the latest news and working hard to get such latest news about our beloved church.

May GOD bless u all

Anonymous said...

Enante zenawen mawtatchuh melkam new...enae lemalet yefelekut asteyayet lemisetu wendimocha/Ehitocha new!!

Anonymous said...

Dear Deje Selam. You are okay for reporting the news.May the mercy of Lord be with Abune Poulos. I think Anonym 11:55pm is responding to Anonym 10:52 pm.

Anonymous said...

My almighty God give him his marcy. We all have to pray through this hard time even if we have problems with his leadership. Special during this feliseta tsome God will answer our question.

Anonymous said...

zenaw sayhon kifuw neger asteyayetu yemeslegnal bete kristian lekifum ledegum titselyalech beyans b edme silemibeltun antu enbel.

Anonymous said...

even though, so many times, I pray his death, let God Give him His Mercy.

Anonymous said...

"ሕግ፡ተላላፊዎችን፡ጠላሁ፡፡"
መዝ.100 ቁ. 3

የዋልድባ፡አምላክ፡ፍርዱን፡እያሳየን፡ነው።

በሕገ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ላይ፡ዓመፃ፡የሚፈጽሙ፡
ሁሉ፡ጠባቸው፡ከምድኃኔ፡ዓለም፡ጋር፡ነው።"አባ"
"ጳውሎስ"ለምድራዊ፡"ክብር"፡የተሸነፉና፡ተዋ
ሕዶ-ኢትዮጵያን፡ያስመረሩ፣ያስለቀሱ፣ያጠቁና፡
ያስጠቁ፡ናቸው።

በታሪካችን፡እንዲህ፡ያለ፡የጥፋት፡ሰው፡በቤተ፡ክር
ስቲያናችን፡ታይቶም፡ተሰምቶም፡አያውቅ!ከፀረ-ማርያምነት፡እስከ፡የእራሳቸውን፡ጣዖት፡በማቆም፡
ከመድኃኔ፡ዓለም፡ጋር፡እንደ፡ወዳጃቸው፡እንደ፡ሳጥ
ና፡ተገዳድረዋል!

ዓለምን፡መርጠዋል።ዋልድባን፡የማጥፋቱ፡ተባባሪ፡
ናቸው።ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ለማጥፋት፡የሚደረ
ገው፡ዓመፃ፡ዋነኛ፡መሪ፡ናቸው።የቅዱሳን፡ለቅሶ፡በ
ላያቸው፡ነው!የኤል፡ሻዳይ፡ፍርድም፡በመገለጽ፡ላ
ይ፡ስለሆነ፡ክብርና፡ምስጋና፡ፍርዱ፡ለማይቀር፡ፈጣ
ሪያችን።

"ከቶ፡አይቀርም፡ሞቱ፣ከቶ፡አይቀርም፡ሞቱ፣
ከቶ፡አይቀርም፡ሞቱ፣ምንም፡ቢታክቱ..."

"ክፉውን፡የተመኙት"እና፡ክፉውን፡ሁሉ፡በቤተ፡ክ
ርስቲያናችን፡ላይ፡እና፡ውስጧ፡የፈጸሙት፡እና፡ያስ
ፈጸሙት፡"አባ" "ጳውሎስ" ናቸው!እኛማ፡ወደ፡
እግዚአብሔር፡ከማልቀስ፡ሌላ፡በጠመንጃ፡የተደገፈ፡
ሥልጣናቸውን፡እንዲያበቃው፡ለማድረግ፡ምን፡አቅም፡አለን?!

እግዚአብሔር፡ግን፡ለቅሶአችንን፡እና፡ተማጽኗችን
ን፡አይቶና፡ስምቶ፡መቅደስ፡የገባውን፡የዘራፊዎች፡
ሥርዓት፡ጠራርጎ፡ሊያስወግድልን፡ሥራውን፡እንደ
ጀመረ፡እናስተውል።

የመድኃኔ፡ዓለምን፡ጠላት፡ያልጠላ (እንደ፡እያሱ
ና፡እንደ፡ካሌብ)፡ፍርዱን፡(አይሁድ፡እንዳገኙት)
ከመድኃኔ፡ዓለም፡ሳይውል፡ሳያድር፡ያገኘዋል!

"በኃጢአተኛ፡ብዙ፡መቅሰፍት፡አለበት፤
በእግዚአብሔር፡የሚታመነውን፡ግን፡
ምሕረት፡የከበዋል" መዝ. 31 ቁ.10

"ጽዋ፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ነውና፤
ያልተቀላቀለ፡የወይን፡ጠጅ፡ሞላበት፤
ከዚህ፡ወደዚያ፡አገላበጠው፥
ነገር፡ግን፡አተላው፡አልፈሰሰም፤
የምድር፡ኃጢአተኞች፡ሁሉ፡ይጠጡታል።
...
የኅጣንን፡ቀንዶች፡እሰብራለሁ፤
የጻድቃን፡ቀንዶች፡ግን፡ከፍ፡ከፍ፡ይላሉ።"
መዝ. 74 ከቁ. 8-10

"...ለእያንዳንዱም፡እንደ፡ሥራው፡መጠን፡እከ
ፍል፡ዘንድ፡ዋጋዬ፡ከእኔ፡ጋር፡አለ።"
ራዕየ፡ዮሐንስ ምዕ. 22 ቁ. 12

በየወህኒው፡ተጥለው፡ከሚንገላቱት፡የዋልድባ፡አባ
ቶች፡ጋር፡አብረን፡እጃችንን፡በመዘርጋት፡መድኃኔ፡
ዓለምን፡በልቅሶና፡በዋይታ፡በተሰበረ፡አንገትም፡ም
ሕረቱን፡ለተዋሕዶ-ኢትዮጵያ፡እንዲያድለን፡እን
ጸልያለን።ይህ፡ነው፡የፍልሰታ፡ስባኤያችን!!!

አቤቱ፡አምላካችን፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ሆይ፡
ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ማረን!ከወረረን፡የጥፋት፡ኃ
ይል፡አድነን፤ታደገን፤ጠብቀን።አሜን።

እመ፡ብርሃን፡ኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡አስቢን!


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

ሁላችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጣችን አለቀሰ ምነው እግዚአብሔር ዝም አለ አልን ነገር ግን.".. እሥራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋም" ቢዘገይም የሚቀድመው የለምሰ...ሰለ ባርያው ስለ ዳዊት ሲል እሥራኤልን የታደገ አምላክ ዛሬም ከቅዱሳኖቹ ጋር ነው።በጸሎት እንትጋ በንስሀ እንመለስ ሌላውን በትእግሥት እንጠብቅ "...ከኛ ጋራ ያሉት ከእነርሱ ጋራ ካሉት ይበልጣሉና" ..ግዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ተብሏልና

Anonymous said...

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።
I don't think you have the basic teaching of Christianity which says Love your Enemy let alone a fellow brother or Father in this case.

May Lord be with our Father?

Girmachew

Berhanu Melaku said...

*** የአባቴ ቃል ***
=============
ደክሞኝ አቧራ ላይ ተኝቸ፥
ውኃ የሚያጠጣኝ አጥቸ፤
ስገላበጥ ስላዎስ እንደ ትል፥
ሳረምም ራይ ዮሐንስን ስከተል፤
አየሁ ገዳሙ በሳት ሲቃጠል፥
አንደበቴ ሊያጠፋው ሲታገል፤
አባ የት አሉ ይርዱኝ እናጥፋው፥
ብየ ስጣራ በትትና እንዳይክፋው፤
ለካስ ነበረ እጁ ከባንዲራው፥
ከፋብሪካው ክብሪቱን ከሰራው፤
አላምን ብየ የአባን ድርጊቱን፥
እሳቱ ግሎ እርሱ መጥፋቱ፤
ሳወጣ ሳወርድ ሙሉ ቀን ውየ፥
ስልክ ደዎልኩኝ ወደ ቪኦኤ፤
ለእርዳታ ብጮህ ለእሳት አደጋ፥
አባቴ ላከኝ ለእስር ቤት መንጋ፤
እስር ቤት ሆኘም ስራ አልፈታሁም፥
አዎ ገዳሜ እንዲነድ አልተስማማሁም፤
አንዱ ጻድቅ እሳት ሊያጠፋ በተራራ ሲኳትን፥
ሌላው ጻድቅ ሲያበላና ሲያጠጣ በሸራተን፤
ከበደኝ በዛብኝ ማየቱና መስማቱ፥
የእግዚአብሔር ልጅ ለሥጋ መሞቱ፤
ከአምላክ ጽፈት ቤት ፋይል ከፈትኩኝ፥
ናናናና ቶሎ ብለህ ዳኘን እያልኩኝ፤
ጥላቻ ይቅር ሰላም እንመኝ ለእያንዳንዳችን፥
መፍትሄ ሰጭው እሱ ብቻ ነው ቸሩ አምላካችን።
እግዚአብሔር ይማር።

Anonymous said...

Aba Dabilos, his hellness Satanic Aba of the TPLF junta, please don't come back alive from D/Balcha Hospital. God please conclude his life and let EOTC be free of TPLF. Let the monasteries, churches and believers be at peace.

I condemn you to death in the Name of Jesus.

Anonymous said...

እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር ይማራቸው....እንደ እኔ እሰይ ስለቴ ሰመረ እልልልልልልልልል...አንጀቴን ሲያበግኑት ሰንብተው አይ ጉድ

Anonymous said...

Dear Girmachew,
All the points stated by Samuel the Asebot are correct. He is not wishing death for Aba Paulos rather stating what is happening.

Mr. Girmachew, you also said 'May Lord be with our Father'. Of course amen, but he is not the father of Ethiopian Orthodox Church and christians.

We don't have a father who works in contrast to the teachings of our church.

የቤተክርስቲያንን ህልውና የሚያቃውስ በምንም ተአምር የቤተክርስቲያን አባት ሊሆን ኣይችልም:: የቤተክርስቲያንን ህልውና ብቻ ሳይሆን አቡነ ጳውሎስ እምነቷንም አይቀበሉም:: ለዚህም ጥሩ ማስረጃ በዶክትሬት ዲግሪ መመረቂያ ጽሁፋቸው ላይ ቤተክርስቲያናችን ከምታምነው በተቃራኒ እመቤታችንን ጥንተ አብሶ አለባት ብለው መጻፋቸው ነው:: ከዚህም በተጨማሪ የተሐድሶ እምነት አራማጆችን ያበረታታሉ በጣምም ይደግፏቸዋል::

በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ተንኮል የሚሸርቡ ሁሉ ይጠፋሉ ወይም የማንም መጭረሻ ይሆናሉ:: ለዚህ ኢጣሊያ ጥሩ ምሳሌ ናት:: በርሊን ላይ በተካሄደው የአውሮፓ መንግስታት ስብሰባ ላይ አፍሪካን እንደ ቅርጫ ለመከፋፈል (በቅኝ ግዛት ለመግዛት) እጣ ሲጣጣሉ ለኢጣልያ ሲፈርድባት ሐገረ እግዚአብሔር የሆነችው ኢትዮጵያ ደረሳት:: ኢትዮጵያን ቀጥቅጬ እገዛለሁ ብላ ኢጣልያ ያላትንና በዘመኑ የነበሩ ታላላቅና እጅግ ዘመናዊ መሳርያዎችን ታጥቃ ኢትዮጵያ ላይ ዘመተች:: አባቶቻችን ግን ምንም እንኳን መሳርያ ባይኖራቸውም ከነገስታት ሁሉ በላይ የሆነውን የነገስታት ንጉስ እግዚአብሔርን አምነውና ይዘው ነውና የተነሱት በፈረሰኛው በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የተሰየመውን ታቦተ እግዚአብሔርን ይዘው ዘመቱ:: በመሳርያቸው የተመኩትን ኢጣልያንን አባቶቻችን በእግዚአብሔር ሃይል ድል
አደረጉ:: ሌሎቹ አውሮፓውያን የአፍሪካን ሃገሮች ሲገዙ ኢጣልያን ግን አፍራ ተመለሰች::ኢጣልያ ሐገረ እግዚአብሔርን ከመድፈሯ የተነሳ ዛሬም ድረስ ከአውሮፓ ድሃዋ ሃገር እንደሆነች አለች::

አባ ጳውሎስም ከእግዚአብሔር ጋር ተገዳድረዋል:: ሁሉን ሲያደርጉ እግዚአብሔር ዝም አለ አሁን ግን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ህልውና መፈታተን ስለጀመሩ (በተለይም የዋልድባ ጉዳይ) እግዚአብሔር አይታገሳቸውም::
እኛ ግን ፍላጎታችን እግዚአብሔር ከስጋ ደዌ ፈውሷቸው ንስሃ ገብተው ማናችንም ወደማይቀርልን ወደዛኛው አለም እንዲሄዱ ነው:: በምድር መቆየታቸው ለሐገርም አይጠቅሙም ግን ንስሐ ገብተው እንዲሄዱ ንስሐ የሚገቡ ከሆነ ቢምራቸው ጽኑ ፍላጎታችን ነው::

H. Mar

Anonymous said...

The price of sin is death...... One who touches that is not permitted for him will pay the price ... Stay alive stay away from Waldeba .....

Anonymous said...

I don't understand about Abuna Phawlose 15 days celearation.
But what can we say about there sickness. Let us say God bless them as a christian.

Anonymous said...

ለእኛስ፡እግዜር፡አለን፡ይብላኝ፡ለሌላቸው
ይግባኙን፡ልከናልናል፡ይመጣል፡መልሳቸው

Diabilos said...

For the wages of sin is death

Romans 6:23

Anonymous said...

Deje Selam Ahun Min Yibalal ? Patiryarikun Tamemu Bilo Medeset Kirisitina New ?Yasazinal subae -Agelgilot Yelebachihum Bitamemu Sertew New -Norew New- Agelgilew New Enante Gena Yale edimeyachihu titamemalachihu Menafikan Nachihu End ?Atimesulgim

Anonymous said...

the passing of abune paulos is only good for the church. Don't get confused, I am not the judge for his behavior and distruction. GOD is. I am only human.

Watch! woyane is manuvearing to bring in either activist politician like paulos or a rabber stamp patriarch. Nothing different for you people. Rely only on your own activitsm and GOD. Participate in your church affaris and contnue to sift out greedy fathers from your churchs and organize and think. stop blinly following. That is salvation for your church. Not the passing of Paulos. Passing paulos is like passing of Meles. Meles will be replaced by another WOyane and Paulos will be replaced by another Woyane or any of other puppet organizations they created.

Anonymous said...

Thank you Samuel ZeAsebot. Belibe lay yalewun new yalkew. Betekiristianachinin lezih yadereswat, tiru abatochachinin anget yasdefu, lemenafiqan gulbet yesetu ersachew nachew. Egziabher ytagesal enji firdu aykerim. YeWaldba abatoch ena yebizu nitsuhan abatoch dem ena enba yifaredal.

natan said...

bergit sew ye zerawin yachidal...Egiziyabiher becherinetu yasibachew......hagerachinin Gedamatin hulu yetebikiline

Anonymous said...

አይ ሳሙኤል.ዘአሰቦት የቤተክርስቲያን ለ፳ አመታት ገዳሞቿ ሲደፈሩ፥ ሲቃጠሉ፥አማኞቿ በጸሎት ላይ እያሉ" በአክራሪ እስላሞች" በእሳት ሲቃጠሉ፥በገጀሞ ሲፈለጡ፤ሃይማኖቷ በገዛ ዓውደ ምሕረቷ ሏይ በመናፋቃን ሲሰደብ ፤ብፁአን አባቶች ሲደበደቡ የአብነት ት/ቤቶቿ ተማሪዎች የሚበሉት ጥራጥሬ አጥተው ሲበተኑና ሲዘጉ እያዩና እየሰሙ " ዦሮ ዳባ ልበስ" ብለው በሸራተን ሆቴል ከቤተክርስቲያን ጠላቶቿ ጋር በሰረቋት ብር እየበሉና እየጠጡ መልሰው ሲገዟትና ሲሸጧት...ወዘተ እያለቀሰች ዘወትር በቅዳሴዋና በጸሎቷ በእንተ አቡነ....ብላ መጸለዩዋን ረሳኸው ወይስ የጥቅስ እንጂ ቅዳሴው ላይ የለህም? ወንድሜ እኔ ያልኩት ክፉ ተግባራቸውን እንጂ

Anonymous said...

Girmachew,

You are proceeding from a wrong
understanding, if you have really paid attention to what was written! You may have your reasons to "love" "abba" "paulos". I can tell you straight away that we Orthodox Christians are not followers of a "teaching" which says "love those who destroy your Churches and Monasteris"!

If our ancestors had followed your simplistic logic; they would have had to "love"Gragn Mehammed and other intruders who wanted to destroy our Tewahedo Church and replace it with their false teachings!

When I think of Waldiba,Agaro, of Zqwala, of Asebot Gedam, of Siltie, and many other centers of our Faith which have been left defenceless by the man you "love",
I can only wail and ask the Good Lord for Our Redemption!

Your wrong understanding of "love" would even bring you to sympathize with "abba" "Fanuel" and his supporters who are destroying Our Church in North America, just as they tried to do it in Awassa! That is the consequence of a wrong understanding of the biblical teachings of the EOTC. Haven't we observed that in the spoutings of Menafiqans?!

The EOTC has been damaged and betrayed by "abba" "paulos" in whose defence you chosen to stand.
This is a man who was excommunicated by our heroic and
unfortgetable father Aleqa Ayalew
Tamiru.

As far as where I stand, I don't have to prove anything to you, more than the words I have written,against which you have chosen to stand.

If you knew the bible, and have followed the teachings of Our Church, you would have gone beyond the catch-word "love your enemy" and reflected about the the role of Judas among the Apostles, and his betrayal of Our Lord Jesus Christ.

I don't love the enemies of Jesus Christ and His Tewahedo Church! I LOVE our Waldiba Fathers who have
been betrayed by "abba" "paulos" and are now languishing in prisons simply because they wanted to preserve Waldiba and it's heritage!
The teachings of Aleqa Ayalew Tamiru are very significantnow more than ever in the light of the
multiple damages being done by this excommunicated man against the
EOTC.

Unless you correct it, through learning, the simplistic nature of your understanding of "love" would
lead you even to love the devil himself!

Before you jump into questioning my stand as a Tewahedo Christian and my understing of the teachings
of The Bible and Our Church, I would recommend that You would do yourself a great service by reading again what I had written in the light of the sufferings of Our Church at the hands of of "abba" "paulos" and his supporters!

You might learn something. It might even dawn to you that you ought to start learning humbly and not be a victim of your own false claim and misunderstandings.

Please copy the link below, paste it on your browzer, and read Aleqa Ayalew Tamiru's excommunication of the man you defend, a man who should have been long thrown out of our church a long time ago:

http://www.aleqayalewtamiru.org/excommunication.html

በየወህኒው፡ተጥለው፡ከሚንገላቱት፡የዋልድባ፡አባ
ቶች፡ጋር፡አብረን፡እጃችንን፡በመዘርጋት፡መድኃኔ፡
ዓለምን፡በልቅሶና፡በዋይታ፡በተሰበረ፡አንገትም፡ም
ሕረቱን፡ለተዋሕዶ-ኢትዮጵያ፡እንዲያድለን፡እን
ጸልያለን።ይህ፡ነው፡የፍልሰታ፡ሱባኤያችን!!!

አቤቱ፡አምላካችን፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ሆይ፡
ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ማረን!ከወረረን፡የጥፋት፡ኃ
ይል፡አድነን፤ታደገን፤ጠብቀን።አሜን።

እመ፡ብርሃን፡ኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡አስቢን!


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።Anonymous said...

የአለቃ፡አያሌው፡ታምሩ፡ውግዘቶችና፡መግለጫዎች
http://www.aleqayalewtamiru.org/news_mebruk%2827-10-88%29.html

http://www.aleqayalewtamiru.org/news_maebel%2811-01-89%29.html

http://www.aleqayalewtamiru.org/news_tomar%2814-05-89%29.html

http://www.aleqayalewtamiru.org/news_maebel%2814-06-90%29.html

http://www.aleqayalewtamiru.org/news_itop%2812-05-96%29.html

http://www.aleqayalewtamiru.org/news_maebel%2807-03-98%29.html

Anonymous said...

ይህ ሰው ከታመመ እግዚኣብሄርን አና የበደለውን ህዝብ ይቅርታ የመጠየቅ አድል ተሰጠው ማለት ነው፥፥
ለሌሎቹም ማስጠንቀቂያ ነው፥፥ ህይወት ኣላፊ ነች፥፥ ለሃቁ ቆሞ ሞትን በጸጋ መጠበቅ ይበልጣል፥፥ ጆሮ ያለው ይስማ

Anonymous said...

ይበል! ለ፟ ሳሙኤል ዘአሰቦት

ውድ ግርማቸው፡

በጥሩም ሆነ በጥሩ ባልሆነ የሰውን ልጅ ምግባር መግለፅ “ጠላትን ከመውደድ ወይ ከመጥላት” ጋር ምን እያያዘው? ያውም በጠራራ ፀሓይ ላይ ተሰጥቶም ሆነ ተሰቅሎ ያለውን ምግባር!
መበቀል ሌላ፤ በለቅሶ ወደ ፈጣሪ ቀና ማለት ግን .....
መፍረድ ሌላ፤ ፍፁም ዝምታን መምረጥ ደግሞ ከእንስሳትም እንዳንወርድ፤
ለአባታችን መልካም ጤንነት!

ወ ሳሙኤል
አቡነ ተ/ሃ ወአቡነ አረጋዊ / ዳላስ-ቴክሳስ

Anonymous said...

የጥፋት ርኩሰት ዘረኛው ነፍሰ ገዳዩ ና በ እግዚአብሄር ላይ የተሳለቀ መንጋውን የበተነ በ ታቦተ ጽዮን ላይ የተጫነ ዳጎን ። የቅዱሳን እንባ ይፋረድህ

Anonymous said...

ይበል! ለ፟ ሳሙኤል ዘአሰቦት

ውድ ግርማቸው፡

በጥሩም ሆነ በጥሩ ባልሆነ የሰውን ልጅ ምግባር መግለፅ “ጠላትን ከመውደድ ወይ ከመጥላት” ጋር ምን እያያዘው? ያውም በጠራራ ፀሓይ ላይ ተሰጥቶም ሆነ ተሰቅሎ ያለውን ምግባር!
መበቀል ሌላ፤ በለቅሶ ወደ ፈጣሪ ቀና ማለት ግን .....
መፍረድ ሌላ፤ ፍፁም ዝምታን መምረጥ ደግሞ ከእንስሳትም እንዳንወርድ፤
ለአባታችን መልካም ጤንነት!

ወ ሳሙኤል
አቡነ ተ/ሃ ወአቡነ አረጋዊ / ዳላስ-ቴክሳስ

Anonymous said...

Unholy Tirnity: The Father Satan the Son Abune Paulos the UNholy sprit TPLF will destroyed sooner or later.
We fear the second death and we do not have silent tounge. I know I am the worldest top first sinner but my sin caused only myself For my sin I am responsible. My sin only causes just only mine. I will not cause friends, societies or country because I fear the second dangerous death. Thses guys are hurting friends up to country now.

Anonymous said...

hulume yezerawn yachedal

Anonymous said...


hulume yezerawn yachedal

ድሉ ዘእግዚአብሔር said...

አንዳንዶቻችሁ አባ ጳውሎስ ለንስሐ በቅተው ቢሞቱ መልካም ምኞታችሁን ተመኝታችኋል። ግን ንስሐ የሚገባ እኮ እምነተ እግዚአብሔር ያለው ነው። እምነተ እግዚአብሔር ያለው ሰው ፈሪሃ እግዚአብሔር አለው። የሚመካውም ከሁሉ በላይ በሆነው በፈጣሪው በእግዚአብሔር እንጅ ጠመንጃ ባነገቡ ፥ ድሀዎችን ቀጥቅጠውና ረግጠው በሚገዙ ፥ ገዳማውያንን በሚያስለቅሱ የሥጋ ወገኖቹ አይመካም። አባ ጳውሎስ በጠመንጃ ሃይል መንበረ ፓትርያርኩን ከሕጋዊው ፓትርያርክ ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ''ብፁእ ወቅዱስ ''በሚል ቅጽል ሲጠሩ እንጅ አንድም ቀን የተቀደሰ ሥራ ሠርተው አሳይተውን አያውቁም። ባጠቃላይ እምነተ እግዚእብሄርም ሆነ ይሉኝታ የተባለው ኢትዮጵያዊ ባህል ሳያንጸባርቁ ነው የኖሩት። ሰውንም ፥ ፈጣሪያቸውንም ንቀው በስማቸው ጣዖት አቁመው ነው ያሳዩን። እንዲፈርስ ቅዱስ ሲኖዶሱም ቢወስን ውሳኔውን ሺረው ጣዖቱ በሴት ወይዘሮ ድጋፍ እስካሁን እንደቆመ ነው። ስለዚህ እምነት ስለሌላቸው ለንስሐ ሊበቁ የሚችሉ ሰው አይደሉምና ከንቱ ምኞት አንመኝላቸው ነው የምለው። ''ሞቱ ለኃጥእ ጸዋግ ወእቱ''ያለውን አምርሳ !

Anonymous said...

Follow ESAT radio. They made an interview

Anonymous said...


Aba paulos had long time to repent and put the church on the right track. He did not use his time. In stead he continued on his evil deeds. Like his master who is also on bed, he thinks that no one can touch him when he ebezeled the property of the church with corrupt individuals like Elizabel. Now the hands of God came to him to either teach or take him. Aba paulos's hands are not clean to deliver the flesh and blood of Jesus to the christains during this holy season, hence he has to spend this time on bed or go for good. Does he realy believe on this fasting season of our Virgin Mary ? Look, he has been enjoying with the reach and cursed politicians of that land celeberating his " anointement by the politicians". He run short of time time to finish the celebeartion because this fasting days were approaching. God is not some one to be cheated by people like him. I tell my heart has been bleeding. Because of not him but because of the evil and anti church things he has been doing. To be honest, most of us have been feeling the same way. Now we say let's pray for him. My brothers and sisters, I have many things to pray for. Do you thing that God is wrong for what he did to him ? Do you think that his sickness came because of tempetaion from devil ? no no no. Do you think that you are more kind than God ? Please let's be honest. I support the cancer cell has to be removed. I do not pray to God to leave the cancer cell. Be honest to your selves do not pretend you are holier than God. He is right for every thing he does. If you realy pray, pray for many topics that deserve prayer.

Brotherly

yemelaku bariya said...

እኔን የጠሉኝን ልወድ ማመኔ ግድ ይለኛል:: የጽድቅ መንገድን ለምታስተምር የእግዚአብሔርን መንግሥት ለምትሰብክ ቤተ ክርስቲያንን የጠላ ልወድ ይገባኛልን? እርሷን የሚጠላ የሰው ያልሆነ የሰይጣን ነው ሰይጣንንና የርሱ የሆነውን ግን መውደድ አይጠበቅብኝም:: አቡኑም በዉኑ የእግዚአብሔር ከነበሩና ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋት ከሆነ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል ይህ ካልሆነና እንዳሰብኩት በተቃራኒው ቆመው ከሆነ እንደስራቸው ይከፍላቸዋል:: እግዚአብሔር ፍርድ ስለማያጓድል የማይገባቸውን እንደማያገኙ አምናለሁ:: እንደመሃሪነቱ ብዙ የተሻሻለ እንደሚያደርግላቸውም ሳልዘነጋ ነው:: ምንም ይሁን ምንም ሁሉም እንደስራው ማግኘቱ አይቀርም:: ይልቅስ ለራሳችን ዛሬውኑ ለፍርድ ቀን የሚሆን ትንሽ ስንቅ እንያዝ::

Anonymous said...

edema laneseha nawe

yemelaku bariya said...

እኔ የምፈራው የሳቸውም ሞት ወንዛቸው ልጅ እነ እንደ ፖለቲካ አጋራቸው ድብቅ እንዳይሆን ነውና እባካችሁ ያሉበትን ሁኔታ እያጣራችሁ ንገሩን:: እነዛ ክፉ ደቀመዛሙርቶቻቸው ከገንዘብ ሌላ ዘመድ የላቸውምና በጸሎት ላያስቧቸው ይችላሉና ነፍስ ይማር እንዳናስቀርባቸው አደራ ተከታትላችሁ ንገሩን:: ለህመማቸው እንኳ ከሳቸው በፊት የታመመ ልማታዊ ባለስልጣን ስላለ ለሱ ጸሎት እያደረግን ነው እሱ እንደተሻለው ለሳቸውም እንቀጥላለን:: እስከዛው ካልተሻላቸውን አኩርፈው ከሄዱ ግን እንደምንቀየማቸው ንገሩልን:: የሃገራችንና የቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች ከፊታችሁ እየሆ ነ ያለውን አስተውሉ በዋልድባ የምታሳርሰው አባይ ጸሃየ ቀጣዩ ያንተ ተራ እንዳይሆን አስብ ዋልድባን ልቀቅና ወደጡረታ ከዛም ወደንስሃ ይሻልሃል:: እነዛ ያደፈ የለበሱ በባዶ እግራቸው የሚሄዱት በአይንህ ሙሉእንኳ የማይሆኑት በጸሎታቸው ብዙ ያደርጋሉ እንባቸው እንደ እሳት ይፋጃል:: እናም እወቅበት::
ሌላው በቤተ ክርስቲያናችን ያላችሁ አባቶች መልካሙን እንድትሰሩ እግዚአብሔር እንድረዳችሁ ከቀደመው አብልጣችሁ ጸልዩ አደራችሁን እንድትወጡ እንድረዳችሁ::

Anonymous said...

BATAME YEGAREMALE ABATE ENA LEJE

Anonymous said...

yehane eyo ena lealochachohe neseha gebo

Anonymous said...

I am one of those who pray for the death of Aba Paulos. which is wrong perception. wishing death to Abune paulos is an indication that we are unable to bring peace to our church with our struggle. We always need change in killing somebody. It is an indication that we are powerless, having no capacity

DAN said...

አሳሳቢው ከአባ ጳውሎስ በኃዋላ የቤተ ክርስቲን አመራር እንዴት ይሆን

ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን የምንማረው አለ

መለስና አባ ጳውሎስ ወደ መቃብር አብረው ሲወርዱ
ቀሪዎቻችን አገርንና ቤተ ክርስቲያንን እንደነሱ
ለሆነ ወይስ
ሕግና ስርዐት የሚያከብር መሪ ለሀገር
ወንጌል ተከትሎ ለደሀ ለቤተክርስቲያን የምሚያገለግል መሪ ይስጠን

Anonymous said...

አሳሳቢው ከአባ ጳውሎስ በኃዋላ የቤተ ክርስቲን አመራር እንዴት ይሆን

ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን የምንማረው አለ

መለስና አባ ጳውሎስ ወደ መቃብር አብረው ሲወርዱ
ቀሪዎቻችን አገርንና ቤተ ክርስቲያንን እንደነሱ
ለሆነ ወይስ
ሕግና ስርዐት የሚያከብር መሪ ለሀገር
ወንጌል ተከትሎ ለደሀ ለቤተክርስቲያን የምሚያገለግል መሪ ይስጠን

Anonymous said...

If this site is preaching the gospel, didn't you read the word of God " Love your enemies"? you should be praying for his health, all Christians should pray for him specially on this fasting month tsome Filseta!

Anonymous said...

Rest in Peace Abune Paulos and Prime Minester Meles, Thank you for all your dedications. Hope your family and friends will find comfort through these difficult days.
As of those who write hatefull messages, I hope and pray that some how you will find it in yourself that it doesn't worth it. We all are a guest in this land, we all going to die we are just waiting our turn, it doesn't worth it to wish death and mysery to others. That is not what we learned in our religion for those of us who knows our religion and values our upbringing. I hope and pray that this transition will go as smooth as it can to Ethiopia and our Orthodox church through out these difficult days ahead.

Anonymous said...

Love your enemies and thy neighbors, we can't wish death or mysery to those who do us wrong. Yes, we are human beings and we want revenge at times, but that is not who we are as Orthodox belivers or christians. We need to find a way to work with each other instead of anagonizing each other and create conflict all over, we left the country for some reason. Can we try to find some way to reunite and help each other while we are here abroad and raise up healthy children who are going to love and serve God?

Anonymous said...

Remember it does say that "be aware of those who will mislead you they will have long sleeve but beacarefull---toward the end of the world" There are so many of our own priests who are mislead, because they are also human beings but we don't need to follow them and cooperate to split our church. What is done is done, we need to find a way to work together to be under one Patriarch even those of us who are not in Ethiopia. If not I am afraid we are going to be lost and allow others to destroy us and take over our Orthodox Church. We are also told that He is the only one who can judge the head of the churches not us, we don't have any power to do so. I hope and wish that those who serve on the board on every church have clear understanding of the basic of the religion, instead of making it a place to shine and destroy our churches all over.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)