August 28, 2012

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል

 • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
 • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡

August 27, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥርዐተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል


(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  ነሐሴ 15 ቀን 2004 . ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ... ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር፣ እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 . በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡ 

August 25, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ሥርዐተ ቀብር ሪፖርታዥ


 • READ THIS NEWS IN PDF.
 • መንግሥት - የፓትርያርኩ አብሮ የመኖርና መቻቻል እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል::
 • የውጭ እንግዶች - ፓትርያርኩ ለኢኩሜኒዝም ዓላማ የተጉ (Committed Ecumenist) እንደነበሩ ተናግረዋል::
 • በዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር መቀመጫ ያላገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮችና ዲፕሎማቶች ነበሩ - መድረክ ዝግጅት አይዋጣልንም?
 • በቤተሰቦች ለቀረበው ቅሬታ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ “ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያን ናቸው” ሲሉ ምላሽ:: ሰጥተዋል፤ የቤተሰቡ አባላት ሥርዐተ ቀብሩ በአጭር ቀንና ጉዞ እንዲጠናቀቅ መደረጉ “ጥላቻና ተንኰል ነው” በማለት ይከሳሉ፡፡
 • ስለ አቡነ ጳውሎስ ዕድሜ የተጣረሱ መረጃዎች ቀርበዋል::
 • ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ገብረ እግዚአብሔር በተሰኘው የክርስትና ስማቸው ተዘክረዋል::

August 24, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግብዓተ መሬት ተፈጸመ


 • ሥርዐተ ቀብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ተላልፏል። (READ IN PDF)

 (ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 17/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 23/ 2012)፦  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም የተወከሉ የእምነት አባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ ሥርዓተ ቀብሩ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ተላልፏል። ዝርዝር ሐተታውን እንደደረሰልን እናቀርባለን። (Picture: Courtesy of MK Website
የቅዱስነታቸውን ነፍስ በአብርሃምና በይስሐቅ እቅፍ ያኑርልን። አሜን። 

August 23, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሥርዐተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል


 • የኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ይገኛሉ።
 • አቶ መለስ ዜናዊ (ገብረ እግዚአብሔርበጸሎተ ቅዳሴው ታስበዋል።
 • ጊዜያዊ ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ይገኛሉ።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 17/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 23/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሥርዐተ ቀብር ዛሬ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡ ትናንት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴ ተከናውኗል፡፡ በዚህ ወቅት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እንደተናገሩት÷ “የቤተ ክህነቱም የቤተ መንግሥቱም መሪዎቻችን በአንድ ቦታ እንገናኝ ብለው የተቃጠሩ ይመስል በአንድ ወቅት ተጠርተው ሄደዋል፡፡ ሁለቱንም መሪዎች ተራ በተራ እንሸኛቸዋለን፤ ተራ በተራ ነው የምንሸኛቸው፤” ብለዋል፡፡

August 22, 2012

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ “አርፈዋል” መባሉን ምንጮቻችን አስተባበሉ


(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 22/ 2012)፦  ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ “አርፈዋል” እየተባለ በመሠራጨት ላይ ያለው ዜና ትክክለኛ አለመሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታወቁ። ብፁዕነታቸው ለረዥም ጊዜ በሕመም ምክንያት ከሰው ዓይን ተለይተው እንዳሉ ያስታወሱት እነዚሁ ምንጮቻችን “ሞተዋል” መባሉን በማስተባበል ብፁዕተናቸው “ደህና መሆናቸውን ነው የምናውቀው” ብለዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን።


የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ሽኝት


 • ግርግሩ መልክ ይያዝ::
 • ሥርዐተ ቀብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስከሬን፣ ተጠብቆ ከቆየበት ሃያት ሆስፒታል ዛሬ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም፣ 5፡00 ላይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ደርሷል፡፡

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ኾነው ተመረጡ

 • ቋሚ ሲኖዶሱን የሚያጠናክሩ ብፁዓን አባቶች ተመርጠዋል::
 • ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያር ምን ይላል? (ከዜናው መጨረሻ ላይ ያንብቡት)
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 14/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 20/ 2012/ PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በፊት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አድርጎ መርጧል፡፡ ስለዚህም ጉዳይ ዛሬ በ9፡00 ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ለመሠየም ምልአተ ጉባኤው ባካሄደው ምርጫ ሦስት ዕጩዎች ቀርበው እንደነበር የጉባኤው ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17 መሠረት ለምርጫ የቀረቡትና በሹመት ቀደምትነት ያላቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

August 21, 2012

(Breaking News) Prime Minister Meles Zenawi Dies

(Deje Selam, August 21/2012):- ETV confirmed today that PM Meles Zenawi has died. The long lasting discussion of his whereabouts are rested now. Ethiopia lost two of its powerful leaders: the premier and the patriarch. It is amazing time. May God rest their souls. Amen.
(BBC):- Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi has died at the age of 57, state media say, after weeks of speculation about his health.

ቅ/ሲኖዶስ የቀብር ቀን እንዲቀየር የቀረበውን ጥያቄ አልተቀበለውም

 • የፓትርያርኩ ቤተሰቦች “በሕግ እንጠይቃለን” እያሉ ነው፤ ፓትርያርኩ የቤተሰቦቻቸው ወይስ የቤተ ክርስቲያን?
 • የሰላም እና አንድነት ጉባኤ ልኡካን አዲስ አበባ ይገባሉ፤ ጉባኤው ልዩነት በአንድነት ሳይፈታ ሌላ ፓትርያርክ የመሾሙን ጉዳይ ቅ/ሲኖዶስ እንዲያስብበት ተማፅኗል፤ የመንግሥትንም እገዛ ጠይቋል።
 • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለፓትርያርኩ ሥርዐተ ቀብር አፈጻጸም ዝግጅት እያደረገ ነው።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 15/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 21/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት ከተሰማበት ቀን አንሥቶ አጠያያቂ ከኾኑት ጉዳዮች መካከል ሐዘናቸውን በሚገልጹ አንዳንድ ወገኖችና ብዙኀን መገናኛ ዘንድ የሚሰማው “ቤተሰቦቻቸው” የሚለው ቃል ነው፡፡

August 19, 2012

የቅዱስነታቸውን ዕረፍት አስመልክቶ የኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ


ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ 115፥6)
የአምስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስን ዕረፍት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ። 
ነሐሴ 11/2004 ዓ/ም Aug 17/2012 (READ IN PDF)

August 17, 2012

ስለ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ቀብር ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር

·  የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ነሐሴ 17 ቀን በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል::
·        የቅዱስነታቸው አስከሬን ነሐሴ 16 ቀን ወደ ካቴድራሉ የሚያመራው መንግሥት በሚመድበው ሠረገላ ነው::
·        የመንግሥት፣ የአኀት አብያተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ይገኛሉ::
·        ከሥርዓተ ቀብሩ በኋላ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል::
·        ኅብረትን አጠንክሮ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራት ጸሎትን የሚጠይቅ ነው፤ ምእመናንን አንበትንም፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
 (ደጀ ሰላም ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/2012/ READ IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቀብር ሥነ ሥርዓት÷ ኀሙስ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ወሰነ፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መቃብር ጎን ያርፋል

 • የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ነሐሴ 17 ቀን በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል
 • የቅዱስነታቸው አስከሬን ነሐሴ 16 ቀን ወደ ካቴድራሉ የሚያመራው መንግሥት በሚመድበው ሠረገላ ነው
 • የመንግሥት፣ የአኀት አብያተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ይገኛሉ
 (ደጀ ሰላም ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቀብር ሥነ ሥርዐት÷ ኀሙስ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም (August 23/2012) ከቀኑ በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ወሰነ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ይካሄዳል፤ መግለጫም ይሰጣል


 • የፓትርያርኩን ቀብር የማስፈጸም ጉዳይ ቅድሚያ ጉዳይ ይሰጠዋል፤
 • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ እስኪመረጥ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተወክለው ይሠራሉ፤
 • የአቡነ ጳውሎስ አስከሬን ከተገነዘ በኋላ ግንዛቱ ተፈቶ ዳግመኛ ምርመራ ተካሂዷል፤

(ደጀ ሰላም ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/2012/ READ THIS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ፣ ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት፣ 3፡00 ጀምሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፤ ጋዜጣዊ መግለጫም ይሰጣል፡፡ ለአስቸኳይ ጉባኤው በርካታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ሲኾን በተገኙት አባቶች የፓትርያርኩ ሥርዐተ ቀብር አፈጻጸም በቀዳሚ አጀንዳነት እንደሚታይ ተነግሯል፡፡

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል

“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።

August 16, 2012

(UPDATED) የአቡነ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት ጉዳይ ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር

 •  READ THIS UPDATED NEWS IN PDF
 • በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ በፓትርያሪኩ የተለያዩ ዘመዶች ስም ከ22 ሚልዮን ብር በላይ መከማቸቱ ተጠቁሟል፤
 • የተወሰኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስከሬናቸው ባለበት በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ተገኝተው ሥርዐተ ግንዘቱን አከናውነዋል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች፤
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአህጉረ ስብከት ሓላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል፤

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ

 • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል፤ መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክሩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ታሽጓል፤
 • ጥቂት ብፁዓን አበው ወደ ባልቻ ሆስፒታል ሄደዋል፤ አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
 • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::

(ሰበር ዜና) ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

Breaking News: Abune Paulos passed away


(Deje Selam, August 16/2012):- Deje Selam sources say  Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is dead. Stay Tuned for the detail.
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

August 14, 2012

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል


. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡

August 11, 2012

ቅ/ሲኖዶስ የ”ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮቹን እንቅስቃሴ “ተቀባይነት የሌለው ነው” በሚል እንዲታገድ ወሰነ


 • በመሥራችነት ከተጠቀሱት ግለሰቦች መካከል ስለ እንቅስቃሴው ምንም የማያውቁና በፓትርያርኩ ስም አስገዳጅነት የተሰባሰቡ ይገኙበታል።
 • እንቅስቃሴው ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ብሎጎች ጋራ ያለውን ግንኙነት ይፋ አድርጓል።

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 5/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 11/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት መጽናትና ለአስተዳደራዊ አንድነቷ መጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ውሳኔዎች መጠናቀቁን ተከትሎ÷ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነናዊ አሠራር ለማጠናከርና ቡድናዊ ጥቅሞቹን ለማሳካት ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ፈቃድ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ በመጥራት ኅቡእ እንቀስቃሴ ሲያካሂድ የቆየው ቡድን በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ታገደ፡፡

Virgin Mary 'crosses the finish line' with Olympic gold runner


Meseret Defar of Ethiopia holds up a picture at the London 2012 Olympic Games on August 10, 2012 in London, England. Credit: Alexander Hassens/Getty Images Sport/Getty Images
.- Ethiopian athlete Meseret Defar provided one of the most emotional moments of the London 2012 Summer Olympic Games when she crossed the finish line in the 5000 meter race to win the gold.

August 10, 2012

"Save Waldebba" Conference


መንፈሳዊ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
“. . . በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ . . .” ሉቃስ ፲፫ ፥ ፳፬
በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ለምትኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ፥
ጉዳዩ: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ እየተከሰተ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ለመነጋገር እና ለመወያየት፤

August 1, 2012

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ እየተካሄደ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለ ወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ ነው። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴን ከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)