July 19, 2012

For Your Information


2 comments:

Anonymous said...

በጣም ጥሩ ማስታውሻ ነው። ሰዉየዉንም በትክክል የሚገልጠዉ ይህ ፎቶግራፍ ነው። ግን ጽዋው ሞልቶአል? ወይስ ገና ጥቂት ይቀረዋል???

ፊንሐስ

Anonymous said...

የጎላው ሰለሞን! መቼም ስም ቀይሮ ሀሜት ትችላላችሁ:: የጎላ ልጆች ስትባሉ ግን ከአገልግሎት ይልቅ ዘለፋ ሥራችሁ ሆነ እንዴ:: ከታላላቆቻችሁ የወረሳችሁት ይህ እኩይ ተግባር ግን የት እንደሚያደርሳችሁ በቅርብ የምናየው ይሆናል:: ለጎላ ምን ሰርታችሁ ይሆን ይሄ ሁሉ መንቦጣረር? የተሞሉትን ከመተንፈስ በፊት ጎላዎች ሁለቴ አስቡ:: ለምጠይቃችሁ ምላሽ ይኖራችሁ ይሆን? የሚያማምሩ ጨርቆችን እየለወጣችሁ ስትለብሱ ከመዝሙር ያለፈ አስተዋጽዋችሁ ምን ነበር? ጎደለ ለማለት የሚቻለው የራስን ካዋጡ በኋላ አይደለ እንዴ? ቅዱስነታቸው ምንም አልሰሩም ብሎስ መከራከር ይቻላል? ስኬት የምትሉት እናንተ ምን ጠብቃችሁ ነው? እስኪ የቤት ሥራ ልስጥዎ በቀላሉ አምስቱን ፓትርያርኮች ብቻ ያወዳድሩና ስኬት ምን መሆኑንም ያሳዩን? ከተወቀሱም ለምን ብቻቸውን? በየአገረ ስብከቶቻቸው በግልና በጋራ በሲኖዶስ ሌሎቹስ ምንአደረጉ? አባባሎ በዘመነ ደርግ ጠፍቷል ለምንለው ሁሉ ተጠያቂው ፕሬዝዳንቱ ብቻ ነው እንደማለት አይቆጠርም? በአገር ደረጃስ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሙግቱን ያቀረበ አቡን የታለ? ትናንትም ዛሬም? ከዚህ ይልቅ ለማናችንም ጠቃሚው ለነገ ያስፈልጋል የምንለውን አይነት መሪ ሰንበት ት/ቤታችሁም ሆነ ማንም በማዘጋጀት የተጋን እንደሆነ ነው:: እውነት ለመናገር በዚህ መንገድ መጠቀሚያ እንጂ አትራፊ ትሆናላችሁ ብዬ አልገምትም:: አቶ ሰሎሞን በዚህ ተግባሮ የሚያስደስቱት ይበዛ ይሆናል ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን ጠላቶችም ተደምረው የሚስቁበት ተግባር በመሆኑ:: ጥቂትም ብንሆን የሚያሳዝኑን የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኖራችንን መዘንጋት አልነበረቦትም:: ወደፊትም እንዲህ አይነቱ ተግባር የከናንን ርግማን የሚጠራ በመሆኑ ተማክራችሁ ልታስወግዱት ይገባል:: የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና ጠንቀቅ ማለት ሳያሻን አይቀርም::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)