July 31, 2012

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ


  • READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳት ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋልበዶንዶሮቃ 50 በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስ ተፈትሿል
  • ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
  • የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩ ናቸው
  • 49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
  • ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› /የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 23/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 30/ 2012)ምሽቱን ወደ ገዳሙ በገቡት ዐሥር ያህል የማይ ፀብሪ ፖሊሶችና ታጣቂዎች የተወሰዱት ሁለት መነኰሳት አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም፣ አባ ገብረ ማርያም ጎንዴ ከማይ ለበጣ (የማኅበረ መነኰሳቱ ሰፊው የአትክልት ቦታ) ናቸው፡፡ ሁለቱ አበው መነኰሳት በፖሊሶቹ ተይዘው ከመወሰዳቸው አስቀድሞ በኣቶቻቸው በፖሊሶቹ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተገልጧል፡፡ ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት መኾኗ የወረዳው አስተዳደር ለገዳሙ ትውፊታዊ ሥርዐትና ክብር መጠበቅ ያለውን የወረደ ግንዛቤ የሚያሳይ ነው፡፡

ትናንት ምሽት በገዳሙ ውስጥ ከተካሄደው ፍተሻ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ዓርብ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2004 .ም፣ ከጠዋት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በዋልድባ ዶንዶሮቃ ገዳም የሚገኙ ከኀምሳ ያላነሱ መነኰሳትና መነኰሳዪያት ቤት ቁልፎች በኀይል እየተሠበሩ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተመልክቷል፡፡

ኻያ ስምንት ያህል የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት የሁለቱን አባቶች መወሰድ በመቃወም ወደ ማይ ፀብሪ ተጉዘው አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ወረዳ ከተማው ከሚወስደው ፅርጊያ መንገድ ሲደርሱ በፖሊሶቹ የኀይል ርምጃ መገታቱ ተነግሯል፡፡ የጉዟቸው መገታት ብቻ ሳይኾን ‹‹መመለሳቸውም አሳሳቢ ነው ብለዋል›› ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የተናገሩ አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ መጠነ ሰፊ ፍተሻ እና እስር ምክንያት በተለይ ከቆላ ወገራ የመጡ ናቸው በተባሉ አርሶ አደሮች ድንገተኛ ርምጃ እንዲሁም በጅብ መንጋና በእባብ በፕሮጀክቱ የጥበቃ ኀይል አባላት እና ሠራተኞች የሕይወት እና አካላዊ ደኅንነት ላይ ደርሷል የተባለው ጉዳት ነው፡፡

አስገራሚው ጉዳይ ግን በሽታቸው ይኹን የወቅቱ መገኛቸው አነጋጋሪ ስለኾነው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመም የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች በመነኰሳቱ ላይ የተናገሩት ቃል ነው - ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡››

በተደጋጋሚ በወረዳው ፖሊስ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተጋልጠው ከሚገኙት የዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ መነኰሳት መካከል ‹‹ፕሮጀክቱን እንቃወማለን፤ ለገዳማችን ክብር እና ህልውናም እንሰየፋለን›› በሚል ግልጽ ተቃውሞ ያሳዩ 49 መነኰሳት ስም ዝርዝራቸው ተይዞ በፖሊስ እየተፈለጉ መኾኑን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል፡፡ ፖሊሶቹ በየጊዜው እየመጡ መነኰሳቱን እየለዩ ለሚያደርሱት እንግልትና እስር ከዋልድባ ቤተ ሚናስ መነኰሳት ጋራ የአስተምህሮ ልዩነት ያላቸው የዋልድባ ቤተ ጣዕማ መነኰሳት ‹‹ተባባሪዎች ናቸው›› ተብሏል፡፡ ሐምሌ 13 ቀን 2004 . ከዋልድባ አብረንታንት ገዳም በማይ ፀብሪ ፖሊስ ተወስደው የታሰሩት መነኮስ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ አሁንም ያልተለቀቁ መኾናቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተለይም ከሰኔ ወር ጀምሮ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና የዛሬማ ወንዝ ግድብ በዋልድባ ገዳም ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋ እና ታሳቢ ስጋቶች ጋራ ተያይዞ በፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊስ በማኅበረ መነኰሳቱ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ እስርና እንግልት ተባብሶ ስለ መቀጠሉ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ማይ ፀብሪ ፖሊሶች እንደተናገሩት ለገዳማቸው ክብርና ህልውና መጠበቅ የቆሙት ጽኑዐኑ የዋልድባ ማኅበረ መነኮሳትምታታሞችባይኾኑም÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ የተያዙበትን ጽኑ ሕመም እንደ እግዚአብሔር ተግሣጽ (እንደ መቅሠፍት) የሚቆጥሩ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጥቂት እንዳልኾኑ በሕመማቸው ዙሪያ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚተላለፉ መልእክቶች ያስረዳሉ - ‹‹ደዌ ዘመቅሠፍት›› እንዲሉ፡፡

በርግጥም ሰው ኾኖ መታመም የሚያነጋግር ባይሆንም የታላቁ ገዳም መነኰሳትና ባሕታውያን አባቶች የዘወትር ሐዘንና ልቅሶ÷ በተለይም በዚህ የሱባኤያቸው ወቅት÷ ግዳጁን አይፈጽምም ለማለት አይቻልም፡፡

31 comments:

Anonymous said...

"ሀገርን ያለጠባቂ አይተዋትም" የኢትዮጵያ አምላክ አሁንም የቅዱሳኑን ጸሎት ይሰማል:: ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደሞቱ የተረጋገጠ መረጃ እየተሰጠ ነው::

ወይ ፈጣሪ! እሳቸውም የማይነካውን የቅዱሳንን ቦታ ነኩ!! ጉድ ነው ጭራሽ ለዚህም ደረሱ?

ነፍስ ይማር!! ወገኔ አየህ ሞት ለማንም አይቀርም::

Anonymous said...

የእኛ አባቶችስ በየትም ቦታ ያሉት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብለው ነው እሚለምኑት። እኳን በዋልድባ የበቁ አባቶች ባሉበት በሁሉም ቦታ ያለች ቤተክርስቲያናችን
ሁሌም በየቀኑ ለገዥዎች መልካም ልቦናና ጥሩ አስተዳደር እንዲኖራቸው ነው የምትፀልየው ሰዎች እንዲታመሙና እንዲሞቱ ሳይሆን ለንስሃ እንዲበቁ ነው የምትለምነው።

Anonymous said...

kentu yekentu kentu gena mene ayetewe enesu lezihe ande ethiopianena betekirstiyanenen lematefate letenesa yecheneqalu endea!!!

gena mene ayetew...egiziabehere teamere yasayenale

egiziabehere ethiopianena betekirstiyanene yetebeqelene

Anonymous said...

መዝሙር 149

1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፤ ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።

2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።

3 ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።

4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና።

5 ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፤ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።

6 የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥

7 በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፤

8 ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፤

9 የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ !ሃሌ ሉያ!ሃሌ ሉያ!

Anonymous said...

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ!?
መዝሙር 149

1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፤ ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።

2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።

3 ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።

4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና።

5 ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፤ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።

6 የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥

7 በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፤

8 ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፤

9 የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ !ሃሌ ሉያ !ሃሌ ሉያ።

Anonymous said...

የሰውዬውን ሚስት መልስ

ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ።

ሰዉየው/አብርሀም ቤተ ክርስቲያን ናት ቤተ አብርሀም ትባላለችና

ሚስት ዋልድባ ናት በግፍ ተናጥቀዋታልና

ንጉሡ አቢሜሌክ ጠቅላይ ሚንስትራችን ነው

ሐተታ
እንደንጉሱ አበስኩ ገበርኩ ካለ በንስሀ ከተመለሰ ይድናል:: ሚስት ዋልድባንም ለባለቤትዋ ቢመልስ እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል:: << ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም።>>
ቤተ ክርስቲያንንም እንድህ ብትላት <>

ትጸልይልሀለች::የሟችን ሞት አትወድምና
<> እንዲል ትፈወሳለህ:: /ዘፍ.20/::

Anonymous said...

Des ylal amelkaket betam

Anonymous said...

አቤቱ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅ፣ እኛንም ወደ ልቦናችን መልሰህ ለንስሐ እድሜ ሰጠህ የመንግስቱ ወራሾች እንድንሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አሜን፡፡

Anonymous said...

He used to be terribly and unbelievably one of the leading and innate opponent (i.e. enemy) & destructor of Ethiopia, Ethiopianizm, Ethiopian, Ethiopian History and Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Biblical Quote “You shall reap what you saw…”Lemanem Amelakachen Medhanialem Kirstose Nefesun Yemarew.

Anonymous said...

ሲያዝዝ፡ ያቅነዘንዝ!
ሟች ሊሞት ሲል፣ ሞት ሞት ሲለው፣ ሞት ሲሸተው፣
አፉን ከፍቶ፣ ቀና ብሎ፣ የግፉን ጽዋ ሊጋተው፣
በጎ መሥራት፣ ጥሩ መሥራት፣ አልሆንለት ሲል፣ ሲያዳግተው፣
ያ! ክፉ ሥራው፣ የተካነው፣ ወደ ኋላ ሲጎትው፣
አረፋ ሲያስደፍቀው፣ ሲጥለው ሲደብተው፣
ትንሽ ቆይቶ፣ ቀና ብሎ፣
የተሰጠውን፣ ጊዜ አቃጥሎ፣
ባንድ የነበረን፣ አነጣጥሎ፣
ኗሪውን አፈናቅሎ፣ ፈቃድ የሌለው አስመስሎ፣
በውስጡ ቂም አርግዞ፣ ሐረግ መዝዞ ተበቅሎ፣
ሀገሪቱን አመሳቅሎ! አመሳቅሎ! አመሳቅሎ!
በዚህም ሳያበቃ፣
ብዙ ነገር ሲጎረጉር፣ በስላቅ በሰበቃ፣
የማይደፈር ነገር ደፍሮ፣ ዋልድባ ገብቶ ለሰረቃ፣
ሲያንኳኳ ሲቆረቁር፣ የቤተክርስቲያን ሳንቃ፣
ቢመከርም፣ ቢዘከርም፣ ስላልባነነ ሰላልነቃ፣
አይሆንም ቢሉት፣ ይሁን ብሎ፣ እንዳልሆነ ሆነ በቃ።
አይ ሲያዝዝ! ሲያቅነዘንዝ!
በስልጣኑ ተመክቶ፣
የማይነካ ነገር ነክቶ፣
ሙታንን ሲቀሰቅስ፣ ከሙታን ከተማ ገብቶ፣
አንድ መንፈስ፣ ሳይታሰብ፣ ተናገረ አሰምቶ።
አፅመ ቅዱሳን እንደሆነ፣ አልተረዳህም ከቶ!
አንተ ማን ነህ? ምን አመጣህ? በማለት ተቆጥቶ፣
ወደላይ ተመልክቶ፣ ለሙታኑም አመልክቶ፣
አስቸጋሪውን አሳሪውን፣ ሳያስበው እንደዋዛ፣ አሰረው አስገብቶ።
ከእንግዲህ ማን ያስፈታል? ተከራክሮና ተሟግቶ፣
ይግባኝ የለ! ሰበር የለ! የሚፈርድ የለ! ተሳስቶ።
አይ ሲያዝዝ ሲያቅነዘንዝ!
ዱርዬው እንደ ድሮው፣ ከዱር ገብቶ፣ ሐረግ ሲመዝዝ፣
ዛፍ ቅርንጫፉን፣ ሲያወዛወዝ፣
የቻለውን፣ ስቦ ስቦ፣
እሱም ወደዚያው፣ ተሰብስቦ፣
ድንገት ሐረጉ፣ ተበጥሶ፣
በጀርባው፣ ወደቀበት፣ ወደኋላ ተመልሶ፣
ምን ዋጋ አለው! ምን ይጠቅማል! ከውድቀት በኋላ ለቅሶ!
እኔንም አሳዘነኝ፣ የፈራሁት በእሱ ደርሶ።
ቤተሰቡም በሁኔታው፣ እጅግ በጣም ተተራምሶ፣
ያልተጎዳ አስመስሎ፣ ይናገራል አደበስብሶ።
ከእንግዲህማ ምን ዋጋ አለው? በሙታን ጥርስ ተነክሶ!
ሁለተኛ ላይመለስ፣ ርቆ ሄዷል ገስግሶ።
ማን ይኖራል በዚህ ምድር? ቤተመቅደሱን አፍርሶ።
አይ ሲያዝዝ ሲያቅነዘንዝ!
በገዳም የሚኖሩት እነማን ናቸው? ምኖች ናቸው?
ለመሆኑ አወቅሀቸው?
ዓለምን ንቀው ቢሰደዱ ለመንፈሳዊው አላማቸው፣
ሊገናኙ ካምላካቸው፣ የእሱ ፍቅር በልጦባቸው፣
አንተ ዘምነህ ይህን ንቀህ እንደጅል ቆጠርሀቸው!
ታሰሩ፣ ተገረፉ፣ ተደፈረ ገዳማቸው፣
ወንዛቸው ተገደበ ታረሰባቸው እርሻቸው፣
ተሰረቀ ንብረታቸው፣ እጅግ በዛ ፈተናቸው፣
በቃ ተኮሱ አነጣጥረው ታርጌት መታ ጸሎታቸው።
========//========
ከወዳጄ አያሌው

Anonymous said...

መንግሥት ወይም የመንግሥት ባለሥልጣን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎቹ የዋልድባ መነኮሳት ናቸው ቢል ኖሮ ነበር እንጂ አንዳንድ ተራና ያልተማሩ ወገኖች የሚናገሩትን ይዞ እንደትልቅ ዜና አድርጎ ማቅረብ እናንተን ጸሐፊዎቹን መደዴና ያልተማራችሁ/"ማይሞች" አድርጎ ያስገምታችኋል ። አስተያየት ሰጪዎችም ብትሆኑ በዚህ ሰዓት ስለ ሀገር ሰላም ስለ ሕዝብ ደኅንነት መጸለይ እንጂ ስለ አንድ ሰው መታመም/መሞት እያጋነኑ "ቅኔ መቀኘት" የሃይማኖት ሰዎች ነን ከሚሉ ወገኖች የሚጠበቅ አይመስለኝም ። ሁሉንም በልባችን ብንጠብቀው አይሻልም? እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ሕዝቧንም ይጠብቅ ፤ አሜን ።

Anonymous said...

really egezhaber qane alew zeme ayelem pm melese endemoteme anmeyletem egezaber lebona yesetawe yechristanochen bedele ayto yeferdale

Anonymous said...

አቶ ሲሳይ መረሳ
"የማይ ጸብሪ አስተዳዳሪ"
በፈጠረህ አምላክ አበሳህን አታብዛው ከንጉሱና ከደርግ ባለስልጣናት ተማር ይህም ያልፋልና በሰፈሩበት ቁና መሰፈር አይቀሬ ነው::

Anonymous said...

አናኖመስ ተጋዳላይ
"መንግሥት ወይም የመንግሥት ባለሥልጣን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎቹ የዋልድባ መነኮሳት ናቸው ቢል ኖሮ ነበር እንጂ"
የምትለው ለነገሩ እንደናንተ አይነቶች ሆድ አምላኩ እያላችሁ ምን ሰላም ይገኛል ለማንኛውም ዘገባው የሚለው "የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመም የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች በመነኰሳቱ ላይ የተናገሩት ቃል ነው - ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡›› የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች የመንግስት ባለስልጣን ነፍጠኞች ናቸው:: አንተ ባለስልጣን የምትላቸው ምናልባት አዲሳባ ያሉትን ከሆነ በቦታ ልዩነት እንጂ በወያኔነት ያው አንድ ናቸው::
እባካችሁ የተዋህዶ ልጆች በአንድነት ስለቅድስት ቤተክርስቲያን እንነሳ ወያኔም ሰላዮቹም ይፈሩ አሪወሳዊያን

lamelame europe said...

eske lagame tsaleyolen abatoche

galela said...

TASEFA ALANE EUROPEIAN...

Anonymous said...

Oh God, they dare to the extent to
give a censor about the content of
our prayers
እንግዲህ ደግሞ ምን ብለን መፀለይ እንዳለብን
ከቤተ-መንግስት አቅጣጫ እስከሚሰጠን ድረስ
'ፀሎት ተስታጎለ ላትሉን' ቃል ግቡልንና.......

Anonymous said...

I was follower of ur blog. I appreciate it so far. Today is my first time to give you negative comment. i did not believe in the openion what the police say about PM.
We have to prey for him as he is the leader of the country which God Give him. Weather he use it for distruction or not you guys, as a Christian, should not worry. The only thing what you should do is prey for him.

Anonymous said...

የእኛ አባቶችስ በየትም ቦታ ያሉት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብለው ነው እሚለምኑት። እኳን በዋልድባ የበቁ አባቶች ባሉበት በሁሉም ቦታ ያለች ቤተክርስቲያናችን
ሁሌም በየቀኑ ለገዥዎች መልካም ልቦናና ጥሩ አስተዳደር እንዲኖራቸው ነው የምትፀልየው ሰዎች እንዲታመሙና እንዲሞቱ ሳይሆን ለንስሃ እንዲበቁ ነው የምትለምነው።
ጠቅላይ ምንስቲሩንም ሆነ ሌሎችን ለንስሃ ያብቃልን

July 31, 2012 10:48 AM

lele said...

mekarawe mekarawe embe kala makara yemekarawe
LEBE YALAWE LEBE YEBALE kamane gare nawe eyatagalen yalanawe????????????????????????????????????????????????????????????????????????

Anonymous said...

gana bezo enayalane
edema lanetseha nawe.
embe kaleneme........

Anonymous said...

AYETE MOTONE SETESHA HEDA TASHATALACHE YADEMATE AFENECHA aloo

asbet dngl said...

ቀኑ ተቃረበና እኔም ምን አላችሁ እያልኩ የሰማሁትን በጥያቄ ድግግሞሽ እያዳመጥኩ ነው :: ይገርማል! አዎ! ሃቅ ነው:: ሁሉም በግዜው የሜከለክለው ነገር የለም “ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ” ምን አዲስ ነገር አለ:: ይልቅስ የሜያሳዝነው የአሁኑ የሰላም አምባሳደር የአባታችን ህልፈት ነው:: አይሞቱም ነገር ግን ከውሻ በአነሰ ክብራቸው ዝቅ ብሉ በስደት ሄወታቸውን ሴመሩ ልናይ ነው:: በጣም ይቅርታ የሐይማኖት አባት ምንያህል መከበር እንዳለበት ባልዘነጋም የሁኔታው መግለጫ የተሰጠኝ ይኽው ስለሆነ ነው:: በተቻለኝ መልዕክቴን በአገኘሁት አጋጣሜ ለመጻፍ ሞክሪ አለሁ:: እባካችሁ ምእመን በያላችሁበት ሁናችሁ ህልናን ሰብሰብ በማድረግ ለመጸለይ እንሞክር :: እኛም የመጸለይ የመልእክት ግዲታ አለብን: በተለይ የማህበረ ቅዱሳን አባሎች በውጭ በውስጥ ያላችሁ::
የድንግል ማርያም ልጅ ኢትዩጵያንና ሕዝቡዋን ይጠብቅ:: አሜን!!!

Anonymous said...

Some people mix up things wrongly. The respected spiritually devoted monks and clergy stood firmly to defend the sanctity of the holy worship places against the Pharaoh (Ferreoon). It was not for their personal gains or individual narrow desires that they faced harassment and punishment, arbitrary arrests, evictions and physical assaults. Cursing the Pharaoh and praying to God to punish him in order to protect his holy places is just and legitimate. If the Pharaoh died it is because he is like Satan and Judea who refused to regret their sins and misdeeds by seeking God's forgiveness and his redemption. When Moses told the Egyptian Pharaoh to release the Israelites, he refused and suffered 11 rounds of punishments. God ordained those curses and punishments to liberate the Israelites from their centuries of bondage and servitude.
Furthermore, Jesus himself got extremely angry with the merchants and moneychangers when he saw that they converted His Father’s house into a marketplace. He used every measure to cleanse the temple. So we Ortodoxawiyan Christians need to show holy emotions and righteous anger against heretics and Pharaohs to defend the sanctity of Worship places and houses of prayers where we celebrate and glorify our God.

Anonymous said...

I wish this monster pagan Zenawi dies and burn in hell!

Anonymous said...

It will keep going unless you bunch of Pro Atheist stop abusing our fathers and mothers.
Abune Paulos be ready our heart is sick our soul also sadened. Death angel and terrior is coming. Leave our church. Repent and remove vatican Statu right now with out precondtions. It is not biblical to put Statu. Remove your image Now.Those Black dress clothed armed body Guard will not save you. Be prepared terrior is infront of your door. Ask forgive God's people.
You must stop harrasing our fathers unless God's work will keep going. God is Great all the enemy of our church inside and out side will dry like grass soon

Anonymous said...

እግዚአብሔር ቤቱን ሊያጸዳ ፈለገ።

"... የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት።" ዮሐ. ፪ ፥፲፮
" ...stop making My Father's house a place of business." John 2:16

ባጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦ. ተ. ክርስቲያኖች ብዙ ታምር እናያለን። የአባቶቻችን አምላክ ልጆቹን ተመለከተ።

Anonymous said...

yekedusane amlake haymanotachenene yetebeke yekeduanume fetena lekeber yehunelachew.

Anonymous said...

yekedusane amlake haymanotachenene yetebeke yekeduanume fetena lekeber yehunelachew.

Ethioman said...

Stop speculation, we know that this website is Kinget and Ginbot 7 website, racist people

Ethioman said...

Stop speculation, we know that this website is Kinget and Ginbot 7 website, racist people

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)