July 26, 2012

የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት - በሼራተን አዲስ

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 19/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 26/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF) የአቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሐምሌ አምስት ቀን 2004 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተከብሯል፡፡ ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ ከ500 ያላነሱ ሰዎች የታደሙበት የራት ግብዣ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እና “ራእይ ለትውልድ” በተባለ አካል የተዘጋጀ መኾኑ ተገልጧል፡፡


 ለበዓለ ሢመቱ የኅትመቶች፣ ቲ- ሸርት፣ ፖስተሮች፣ ራት ግብዣ ዝግጅቶች ፓትርያሪኩን ጨምሮ ግለሰቦች ከስፖንሰር ሽፕ እና በዚሁ ሰበብ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከሚሰበሰበው ገንዘብ ሕገ ወጥ ጥቅም እያጋበሱበት መኾኑ የበዓሉን ምንነትና ፋይዳ አደናጋሪ መልክ አስይዞታል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋራ በተገናኘ አቡነ ጳውሎስ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በማይታወቀው የልዩ ጽ/ቤታቸው መዋቅር፣ በእጅጋየሁ በየነ እና እንደ ዶ/ር አግደው ረዴ /ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር/፣ ቀሲስ ግሩም መልአክ ታዬ /ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት/፣ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ /አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/ እና ተመስገን ዮሐንስ /አ.አ.ዩ/ በመሳሰሉት ግለሰቦች አማካይነት “ራእይ ለትውልድ” /Vision For Generation/ ከተባለው አካል ጋራ ፈጥረውት የቆዩት፣ በዚሁ በዓል አከባበርም ገሃድ የኾነው እውነታ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

በዚሁ ዝግጅት ላይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝ እና ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖም የራት ምሽቱ የክብር እንግዶች የነበሩ ሲሆን በአቡነ ጳውሎስ ስም የተሰየመ የኤድስ፣ ቲቢ እና ካንሰር ሕሙማን ማገገሚያ ማእከል በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚገነባና የግንባታ ሥፍራውን የማፈላለግ ሥራ እየተሠራ መኾኑ ተገልጧል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ የማእከሉን ግንባታ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ አቡነ ጳውሎስ ሾመዋቸዋል። የአቡነ ጳውሎስን ሥራዎች ይዘክራል የተባለ የኻያ አምስት ደቂቃ ሥዕላዊ ፊልምም ታይቷል።

ክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝ “ክቡርነታቸው [ቅዱስነታቸው] በሀገራችን የልማት ጉዳይ ከመንግሥት ጋራ እየሠሩ መኾኑን እንገልጻለን፤ . . . የአክራሪነትን አደጋ በተመለከተ መንግሥታችን እዚህ ከተገኙትም ካልተገኙትም የሃይማኖት ተቋማት ጋራ አብሮ ይሠራል” ማለታቸውም ተዘግቧል።
ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የመጡት ቄስ ደረጀ ጀንበሩ በበኩላቸው “የሃይማኖት አባቶች ተመካክረው እንዲሠሩ ጥረት አድርገዋል፤ ቤተ ክርስቲያናችን የእርስዎን ታላቅ አባትነት ያከብራል” ሲሉ “እንዳዛሬው ደክመው በሚታዩበት ኹኔታ ሳይሆን ቀድሞ በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ለማስገኘት አብረን ሠርተናል፤ ቅዱስነታቸው ዘወትር ሲናገሩ አንድን ሃይማኖት ሳይሆን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ በመወከል ነው” ያሉት ደግሞ ሼኽ ኤልያስ ሬድዋን ናቸው።

በተያያዘ ዜና ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዝግጅቱ ላይ የተወከሉት አባ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልም “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባልዎት የሊቀ መንበርነት ሓላፊነት ለሰላም አብረን መሥራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። የ“ራእይ ለትውልድ” የተሰኘው ተቋም ተወካይም “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን አባት ናቸው፤ በስማቸው የኤድስ፣ ካንሰር እና ቲቢ ማገገሚያ ማእከል ለመገንባት የዲዛየን ሥራው ተጠናቋል” ካሉ በኋላ በ200 ሚልዮን ብር ማእከሉን እንደሚገነባና ለመሠረት ሥራው ብቻ አምስት መቶ ሺሕ እንደሚያስፈልግ ሲገልጹ ማዕከሉን እንዲመሩ በፓትርያርኩ የተሾሙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም “የተሰጠኝን ሓላፊነት አልቀበልም አልልም፣ እቀበላለኹ፤ ከራእይ ለትውልድ ጋራ አብሬ እሠራለኹ፡፡” ብለዋል።

ማዕከሉን አስመልክቶ አቡነ ጳውሎስ ሲናገሩ “በስማችን የተሰየመው ማእከል ለመገንባት መነሣቱ የሚመሰገን ነው፤ ማእከሉን ሁላችንም እንደምንጠቀምበት ማሰብ አለብን፤ እግዚአብሔር አምላክ ለመልካም ሥራ ሁሉ እንድንተባበር አዞናል፤ በስሜ ለተሰየመው ማእከል ግንባታ የበላይ ተቆጣጣሪ እንዲኾኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተሾመዋል” ብለዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

11 comments:

Anonymous said...

kikikiki leba hula..hayemanote yeleshe ,acheberebari...

egiziabehere ayenachewene yaberawe

galela said...

yalettadalo abate

Anonymous said...

Betam Des Yemil New Abatachen Edemena Tena Yestelen Egziabher yitebkelen betkresteyanachen wedeseletanew aem eyegebach new be aatachen zemen bezu lewetochen ayetenal Egziabher yitebekilen amen

Anonymous said...

ደርግ በሕዝብ ንብረት የ 10ኛውን የአብዮት በዓል በእጅግ ከፍተኛ ዋጋ ድግስ ደግሶ ሲያከብር ወገን በድርቅና በረሃብ ይረግፍ ነበር

ዛሬም ተጋዳላይ ገ/መድህን / አባ ጳውሎስ/ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በኑሮ ውድነት በሚቆራመዱበት በአሁኑ ወቅት፤ በፆም በጸሎት ምህላ ይዘው የምህረት ዘመን እንዲመጣልን በመማጸን ፋንታ፣ ፆም የሚያድሩትን ወገኖቻችንን የዕለት እንጀራ በመዘከር ፋንታ፣ በምስኪን ምዕመናን ገንዘብ፣ በሼኩ የቅንጦት ሆቴል እነ ሆድ አምላኩን ሰብስበው ቀበጡበት???

አቤቱ ጌታ ሆይ! መቸ ይሆን? የአንተን ትዕዛዝ አክብሮ የሚያስከብር፣ የምድራዊውን የሥጋ ዓለም ንቆ የአንተን መንግሥት የሚናፍቀውን፣ ከጎሰኝነት እና ከፖለቲካ የፀዳ፣ እውነተኛ መካሪ እና የመንፈስ አባት የምትሰጠን መቼ ይሆን???

እውነት ኢትዮጵያችን እንደራሄል የምታነባላት እናት የላትም???

ጌታ ሆይ! ለኢትዮጵያስ የገባህላትን ቃል ኪዳን ምነው አዘገየኸው???

ኧረ እባክህ በቃችሁ በለን!!!

Anonymous said...

ደርግ በሕዝብ ንብረት የ 10ኛውን የአብዮት በዓል በእጅግ ከፍተኛ ዋጋ ድግስ ደግሶ ሲያከብር ወገን በድርቅና በረሃብ ይረግፍ ነበር
ዛሬም ተጋዳላይ ገ/መድህን / አባ ጳውሎስ/ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በኑሮ ውድነት በሚቆራመዱበት በአሁኑ ወቅት፤ በፆም በጸሎት ምህላ ይዘው የምህረት ዘመን እንዲመጣልን በመማጸን ፋንታ፣ ፆም የሚያድሩትን ወገኖቻችንን የዕለት እንጀራ በመዘከር ፋንታ፣ በምስኪን ምዕመናን ገንዘብ፣ በሼኩ የቅንጦት ሆቴል እነ ሆድ አምላኩን ሰብስበው ቀበጡበት???

አቤቱ ጌታ ሆይ! መቸ ይሆን? የአንተን ትዕዛዝ አክብሮ የሚያስከብር፣ የምድራዊውን የሥጋ ዓለም ንቆ የአንተን መንግሥት የሚናፍቀውን፣ ከጎሰኝነት እና ከፖለቲካ የፀዳ፣ እውነተኛ መካሪ እና የመንፈስ አባት የምትሰጠን መቼ ይሆን???

እውነት ኢትዮጵያችን እንደራሄል የምታነባላት እናት የላትም???
ጌታ ሆይ! ለኢትዮጵያስ የገባህላትን ቃል ኪዳን ምነው አዘገየኸው???

ኧረ እባክህ በቃችሁ በለን!!!

Anonymous said...

dear dejeselam.......egziabher ye ewunet amlak new.......! Sile ewunet yiferdal.......! Ye betekrstiyan genzeb ena nibret betemeretu abatochi simezeber,sizeref mayet be ejigu yasaznal...... Egziabher ye kedemutn abatoch zemen yamtaln amen.

Anonymous said...

behiwot zemenu yemitekim sera yalsera sew moto yemiastawesew selemainor bekumu hawelt yaseral beden hawelt lebeden seraw mlet new
20 yezeregnenet, yezerefa, yehaset yeambagenenenet ametat melkam ledet enbelachew kidusenetachewen.
Mechem dena sitata yemelemelal gobata aydel yemibalew!

Anonymous said...

Hodachew amlakachew kibrachew benorachew"
Min yigermal menfesawi sira bisera new yemigermew. Yiheko manim mafiya betekrstian mewaqir lay biqemet yemiseraw sira new. Sewuyewu bemengist tibeqa yemidergilet yemafiya budin meri new. Endetebalewu yihin be'al mikniyat bemadreg yeterabu wegenoch bitasebu, meba latu abiyatekirstiyanat digaf bidereg sint tiqim neberew. Lenegeru enzihin sirawoch mahibere qidusan yiseral. sewuyewu ktebabariwochu gar hono yemafiya sira yisra.

Yegeremegn hailemariyam manin new " akrari" yalew ?. Yegedel mamito.

Anonymous said...

Hmmmmmmmmmmm.!

Anonymous said...

""We Ethiopian Orthodox Churches will not negotiated about Paulos and the government evil strategy""!!!
The God of Daniel is Great and so great we will see you fly Vatican with your statue soon.

God is counting your time now. We strongly refuse the sate must not associate/use our churches.
King Paulos we hate your work we hate your act unGodly behave. We worship God who suffer inpalce of us the Lord Almighty jesus Christ

DANIEL5:1
King Belshazzar gave a great banquet for a thousand of his nobles and drank wine with them. 2 While Belshazzar was drinking his wine, he gave orders to bring in the gold and silver goblets that Nebuchadnezzar his father[a] had taken from the temple in Jerusalem, so that the king and his nobles, his wives and his concubines might drink from them. 3 So they brought in the gold goblets that had been taken from the temple of God in Jerusalem, and the king and his nobles, his wives and his concubines drank from them. 4 As they drank the wine, they praised the gods of gold and silver, of bronze, iron, wood and stone.
5 Suddenly the fingers of a human hand appeared and wrote on the plaster of the wall, near the lampstand in the royal palace. The king watched the hand as it wrote. 6 His face turned pale and he was so frightened that his legs became weak and his knees were knocking.
7 The king summoned the enchanters, astrologers[b] and diviners. Then he said to these wise men of Babylon, “Whoever reads this writing and tells me what it means will be clothed in purple and have a gold chain placed around his neck, and he will be made the third highest ruler in the kingdom.”
8 Then all the king’s wise men came in, but they could not read the writing or tell the king what it meant. 9 So King Belshazzar became even more terrified and his face grew more pale. His nobles were baffled.

10 The queen,[c] hearing the voices of the king and his nobles, came into the banquet hall. “May the king live forever!” she said. “Don’t be alarmed! Don’t look so pale! 11 There is a man in your kingdom who has the spirit of the holy gods in him. In the time of your father he was found to have insight and intelligence and wisdom like that of the gods. Your father, King Nebuchadnezzar, appointed him chief of the magicians, enchanters, astrologers and diviners. 12 He did this because Daniel, whom the king called Belteshazzar, was found to have a keen mind and knowledge and understanding, and also the ability to interpret dreams, explain riddles and solve difficult problems. Call for Daniel, and he will tell you what the writing means. ”

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

ማነዉ ባለ ሳምንት?
ርዕሰ ብሔሩ ሳያገገሙ እርግናም ተጭኗቸዉ እንደተኙ ድማጻቸዉ ጠፋ። ሰዉ የታጣ ይመስል አሊያም ደግሞ ካልሞትኩ እስኪ ወንበሩን ንክች ታደርጉና ያሉ ይመስል እርሳቸዉ( አባባ ግርማ) በቁም አሸልበዉ መንበራቸዉን በሪሞት እየተቆጣጠሩ ምስኪኗን ኢትዮጵያ መሩ። ሞቱ ወይስ አሉ እያልን ሸኝተናቸዉ እነሆ ሌላኛዉን ልናስተናግድ ደፋ ቀና እያልን ነዉ። ኢትዮጵያ መሪ አይብቀልብሽ ተብሎ የተረገመ ይመስል አስጨናቂዎቿ በተለይ በሃያ አንደኛዉ ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ከገጠር እስከ ከተማ በረከቱ። የምትታወቅበትን የሀይማኖት ተቋማቶቿን የሚበዘብሩ፣ ዓለም የተደነቀበትን ታሪኳን የሚሠርዙ፣ የዋሁን ሀገር ወዳዱን ኢትዮጵያዊ ሀገሩን የሚያስክዱ ከሀዲዎች በረከቱ። ታዲያ ርዕሰ ብሐሩ በቁም ሲያሸልቡ ጠቅላይ ሚኒስቲሩ ለሪሞቱ መሪ ባትሪ እየሞሉ ሲመሩን ሰነበቱና ዛሬ ደግሞ ተራዉ ደርሷቸዉ በቁም አሸለቡ። በሽታቸዉ አንዴ ካስተኛ የማይመልስ ሲሆን ደግሞ በግፋቸዉ የሚታወቁ የሌለኞቹ መሪዎቻችን ጉዳይ አሳሰበኝ። እንዴት ነዉ?፣ በፊት ያሞት ነበር ? ተብለዉ ለመጠየቅ እንኳ እድል ሳያገኙ አንደበታቸዉ መዘጋቱ ምን ይባላል? ወገን እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ሲባል መስማትኮ መታደል ነዉ። ተስፋ ሰንቆ ለመሄድ ። በሰማይ ቦታ ባገኝ እንደማለት……. ለአልባኒያ ሳይንስ በሰማይ ቦታ ባለመኖሩ የገደለን ሞት ይብላዉ ይበቃል።
እስኪ ማነዉ ባለ ሳምንት ? ለመልሱ ብቸገርም ለአልባኒያዉ ሳይንስ ቡራኬ የሰጡት አባት ቢሆኑስ? መቼም ልጃቸዉ ሲሄድ እርሳቸዉ ለመከታላቸዉ የሸራተን አዲስ ድግስ ቋሚ ምሥክር ነዉ::፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉ የሉም? ሲባል የሰነበተዉ አሰልቺ ወሬ 21 ዓመት በገደሏት ሀገር የደረሱበት ጉዳይ መቀበሩ ቢሞቱ እንጂ ቢኖሩ አያስብልም። በቃ ሞተዋል እንስማማ። አቶ መለስ በሕይወት እያሉ ዝም አይሉም ። እንዴት አስችሏቸዉ። ቤተ መንግሥቱ የለመደዉ ጉዳይ ስለሆነ እየተንገዳገዱም ቢሆን የተንገዳገደችዉን ሃገር ይመሯታል እንጂ። ጉዳዩ የእርሳቸዉ መሞት ሳይሆን የተከሉት መርዛማ ሰንኮፍ የሚነቀልበት መላ ነዉ። ሰዉየዉ እንደሚሞቱ ቀድመዉ እንዳወቁ የጭከና ሥራቸዉ ምስክር ነዉ። ለመገደልና ለማሰር የማይተጠፍ ክንድ ተስፋ ከመቁረጥ ማህጸን እንደተወለደ እዉነት ነዉ።የእርሳቸዉ መሞት ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሆናት የድርግላቸዉ። የግፋቸዉ ብዛት ጣር አብዝቶባቸዉ ከሆነ ቶሎ ለአፈር አብቃቸዉ ነዉ ምርቃቱ። ተቆርጦ እንደወደቀ የእንሽላሊት ጅራት ሞተዉ የሚላወሱ ከሆነ መቼም ደፍሮ ወደ ወንበራቸዉ የሚጠጋ ኃይል የሚኖሩ አይመስልም። ቢመለሱስ ያሰጋልና። ለ21 ዓመታት በደቦ የገደሏት የአቶ መለስ የመድረክ ተዋናዮች ለሙት ሽፋን ከመስጠት ለእድሜ ማቆያ እንክብል እንዲሆናቸዉ የሞተን ቀብረዉ “ማነዉ ባለሣምንት” የሚለዉን የደወል ድምጽ ቢያደምጡ የተሻለ ይሆናል። ማነዉ ባለ ሳምንት ሲባል መስቀል ወይስ ሾተል ነዉ የያዘዉ እየተባለ የሚታማዉ የአባ ጳዉሎስስ እጅ ከደም እንዴት ይጠራ ይሆን?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)