June 22, 2012

በጀርመን የቅ/ሚካኤል በዓለ ንግሥ በመናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ


(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ሆን ብለው ከረፈደ በቦታው በተገኙት መናፍቁ «ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ። በሀገረ ጀርመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኑፋቄያቸው ምክንያት በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቁጣን እያስነሱ ያሉት መናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ “ከልካይ የለኝም” በሚል መንፈስ በአካባቢያቸው የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን በአውቶብስ ጭነው ከአካባቢያቸው ወጥተው በአገልግሎት እንዳይስተፉ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የጣሉባቸውን እግድ በመተላለፍ እሑድ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።


ገዳሙ ከግብር አበሮቻቸው ጋር
በጀርመን በአራቱም አቅጣጫ ካሉት የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናት በኮሎኝ ከተማ የሚከበረውን ዓመታዊውን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን የንግሥ በዓል ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ ቁጥር ተገኝተው የነበሩት ምእመናን በዓሉን በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ሳሉ ግለሰቡ እሑድ ጠዋት ግብር አበሮቻቸውን ይዘው በአገልግሎት ላይ ያሉ በሚመስል መልኩ ፈረጅያቸውን ለብሰው፤ ቆባቸውን አጥልቀው በቤተ ክርስቲያኑቱ የተገኙ ሲሆን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ፤ ዑደቱ አብቅቶ፤ ምእመናኑ ቃለ ምእዳን የሚሰጥበት ቦታ በመሰባሰብ ላይ ሳሉ እኚሁ ግለሰብ ከካህናቱ ጋር ለመቆም ወደፊት ለመቅረብ በሚሞክሩበት ጊዜ በግለሰቡ በቦታው መገኘት በተለይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በግለሰቡ ላይ የጣሉት የእንቅስቃሴ እግድ አለመከበሩ ያቃጠላቸው ምእመናን በንዴት “፤ወደ ታቦተ ሕጉ አይቀርቡም አልተፈቀዶለትም” ብለው መንገድ ዘግተውባቸዋል። በዚህ ጊዜ በዋነኝነት መንገዱን ዘግተው ወደፊት አይሄዱም ብለው ከፊታቸው የከለከልዋቸውን ጎበዝ ምእመን ገፍትረው ለመሄድ በመሞከራቸው ረብሻ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።

ምንም እንኳን ግለሰቡ በበዓሉ በመገኘታቸው ምክንያት ከሚፈጠረው ግርግር እተርፋለው ብለው ያሰቡ ቢሆንም እንዳሰቡት ሳይሆን በተቃራኒው አጋጣሚውአብዛኛውን ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ ያለውን ቀናዒነት፤ ተቆርቋሪነት እና የመንፈስ አንድነት አሳይቶ አልፏል። ግለሰቡ ግርግሩን ካስነሱ በኋላ ተጎጂ በመምሰል ፖሊስ ለመጥራት ቢሞክሩም በቦታው የተገኙት ፖሊሶች ሁኔታውን በአግባቡ አገናዝበው ምእመኑም በግለሰቡ ላይ ለምን ቁጣ እንዳነሳ ተነግሯቸው ምንም የከፋ ነገር ሳይፈጠር ተመልሰዋል። ይልቁንም “ወደ ታቦተ ሕጉ አይቀርቡም” ብለው የከለከሏቸውን  ምእመን ከግለሰቡ ግብረ አበሮች መካከል አንዱ “ደምሽን ነው የማፈሰው” የሚል ዛቻ በመናገሩ ፖሊሶቹ በግለሰቡ ላይ ክስ መመሥረት የሚቻል መሆኑን አሳውቀዋል። 

አባ ብርሃነመስቀል ምእመኑን ሲያረጋጉ
በአጠቃላይ በተፈጠረው ክስተት እጅግ የተቆጣውን አብዛኛውን ምእመን ደጉ የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አባት አባ ብርሃነመስቀል ተድላ ከመካከላቸው በመገኘት ያረጋጉ ሲሆን የምእመናኑን ጥያቄ እንደሚረዱ፤ ከሌሎች አባቶችም ጋር ጉዳዩን እየተመለከቱት መሆኑን፤ ምላሹንም በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳውቁ በመግልጽ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ አድርገዋል።

በዓሉ ከመከበሩ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ በነበረው የካህናት ስብሰባ እና በዋዜማው ጸሎት ላይ ያልተገኙት የቪዝባደኑ አለቃ እሑድ ረፋድ ላይ ማኅሌቱ አብቅቶ “አሐዱ አብ” ተብሎ ቅዳሴ ከተጀመረ በኋላ፤ መልእክታት ሲነበቡ ለመግባት ያመቸኛል ባሉበት፤ ምእመናንም በሰቂለ ኅሊና በነቂሐ ልቡና የቅዳሴውን ተሰጥዖ በመከታተል ላይ ሳሉ ድንገት ብቅ ቢሉም፤ ምእመናኑ ቅዳሴ ከተጀመረ በኋላ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ጭቅጭቅ መፍጠሩ ተገቢ አለመሆኑን በመረዳት ወደውጭ እስኪወጡ ድረስ ጠብቀው አግባብ ነው ያሉትን ነገር አድርገዋል። የግለሰቡ አመጣጥ በእርግጥም ረብሻ እና ግርግር ለማስነሳት እንደሆነ ግልጽ የሚያደርገው በካህናት ስብሰባው እና በዋዜማ ጸሎቱ ላይ ሳይገኙ እሑድ ዘግይተው መገኘታቸው ሲሆን የጸሎቱን ሥነ ሥርዓት ከግማሽ ለመካፈል ከቪዝባደን ድረስ አውቶብስ ተኮናትሮ ከረፈደ የሚያስመጣ ሌላ ምን ምክንያት አለ ያሰኛል።  

ፓሊስ በምእመኗ ላይ የዛተውን ግለሰብ ሲያነጋገሩ
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የግለሰቡን ብልጣብልጥነት ያላስተዋሉ ይልቁንም በየዋህነታቸው መጠቀሚያው የሆኑ አንዳንድ የቪዝባደን እና የፍራንክፈርት ምእመናን ጉዳዩን ከሃይማኖት አኳያ ማየት አለመቻላቸው ብዙዎችን አሳዝኗል። ገና ነገሩ እዚህ ደረጃ ሳይደርስ “ግለሰቡ እውነተኛ ማንነታቸውን በካባቸው ሸፍነው የገቡ መናፍቅ ናቸው” እየተባለ ከዓመታት በፊት በምእመናኑ በኩል አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ ወገባቸውን ይዘው ለግለሰቡ ኦርቶዶክሳዊነት ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች፤ እንደውም የቀኝ እጃቸው ናቸው እስክመባል የደረሱ ዛሬ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናቸው ፈጽሞ የሉም። ያሉት በመናፍቃን አዳራሽ ነው። ለዚህም እንደ ማሳያ በዋነኛነት ከሚጠቀሱት ምእመናን መካከል አንዷ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ፈለቀ ናቸው። እኚህ ወይዘሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን በቪዝባደን ካቋቋሙ ግለሰቦች መካከል  አንዷ ሲሆኑ በሰበካ ጉባኤ አባልነትም በአጥቢያው ያገለገሉ፣ ንዋያተ ቅድሳትን ከራሳቸው ገንዘብ እያወጡ ሳይቀር ሲያሟሉ የነበሩ ቅን ወይዘሮ ነበሩ። ወ/ሮ ጥሩወርቅ ዛሬ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበሉባት በነበረችው በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናቸው የሉም። በእልቅና ካባ ከመቅደሳችን በገቡት መናፍቅ ምክንያት የመናፍቃኑን ጎራ ተቀላቅለዋል። ትናንትና ግለሰቡን “ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ነው” እያሉ እንዳልተከራከሩላቸው ዛሬ እሳቸው ራሳቸው የግለሰቡን እውነተኛ ማንነት በግልጽ በሚያሳይ መልኩ የሃይማኖት ቤታቸውን ጥለው ወጥተዋል። እዚህ ጋር አንባቢዎች ልብ እንዲሉ የሚገባው እኚሁ ወይዘሮ በራሳቸው ቃል “ሃይማኖትን ያስተማረኝ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያስተዋወቀኝ ቄስ ገዳሙ ነው” ብለው በመድረክ መናገር ብቻ አይደለም በቪዝባደን ከተማ በጀርመንኛ በሚታተም የአካባቢው ጋዜጣ ምስክርነት የሰጡ መሆናቸውንም ጭምር ነው።

ወሮ ጥሩወርቅ ከ«ቄስ» ገዳሙ ጋር
የወይዘሮ ጥሩወርቅ መውጣት በጀርመን ትልቅ መነጋገሪያ መሆኑና በእኩይ ሥራቸውም ላይ የፈጠረውን ተጽእኖ የተረዱት የቪዝባደኑ አለቃ፤ በመጀመሪያ “አንድ ግለሰብ ከቤተ ክርስቲያን ወጣ እና ምን ይፈጠር?” ሲሉ ከቆዩ በኋላ ጫናው ሲበረታባቸው ወይዘሮዋን ጎትጉተው አምና የደብረዘይት ዕለት “ወደ ቤተ ክርስቲያኔ ተመልሻለሁ” እንዲሉ ያደርጋሉ። በዕለቱም ድግስ ተደግሶ ወይዘሮዋ ንግግር እንዲያደርጉ ነገር ግን ማንም ጥያቄ እንዳያነሳ ለአስተያየት ብቻ ግን በአካባቢው ለሚታወቁ እና ለግለሰቡ ባላቸው ድጋፍ ታማኝ ለሆኑ ሰዎች እድሉ ተሰጥቶ “ቄስ” ገዳሙም “ወደ ቤቷ እንደምትመለስ ቀድሞ ራእይ ታይቶን ነበር” ብለው ነገሩን አደባብሰው ያልፋሉ። ብዙ አልቆየም፤ እንደ መምህራቸው ከልብ ያልሆነው መመለስ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ ስለነበር፤ ወይዘሮዋ ደግመው ወደ መናፍቃኑ አዳራሽ ከመሄዳቸውም ባሻገር ሌሎችን ወደዚሁ ስብስብ ጋባዥ ሆነዋል።

ታዲያ በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ በዚህ ዓይነት ቀልድ አይሉት ድራማ በሚመስል ሁኔታ ሲሳለቁበት “በአጥቢያው ያሉት ምእመናን ምነው መንቃት አቃታቸው?” ያሰኛል። እንደ አንድ ምሳሌ እኚህ ወይዘሮ ተጠቀሱ እንጂ ሌሎች በርካታ የግለሰቡ የቅርብ ወዳጆች የሆኑ ግለሰቡን “በባህል እና በአሮጌ ልማድ ከተተበተበች ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ያወጣን ታላቅ ወንጌላዊ ነው፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆኖ የሚሠራው ሥራ ቀላል አይደለም” እያሉ የሚያሞካሹ ቤተ ክርስቲያናቸውን ክደው የወጡ ጥቂቶች አይደሉም። የግለሰቡ ደጋፊዎች የሆኑቱ ይህን ሁላ እየተመለከቱ፤ ጌታም በወንጌሉ “ሐሰተኛ መምህራንን ከፍሬአቸው ታውቁአቸዋላችሁ” ብሎ እንደተናገረው እዛው ከመካከላቸው ለ«ቄስ» ገዳሙ በጣም ቅርብ የሆኑ፤ “መጽሐፍ ቅዱስን ከሳቸው ተማርን” የሚሉ፤ የሐሰተኛ መምህራቸው የገዳሙ ደምሳሽ ፍሬ የሆኑትን ሰዎች አንድ በአንድ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሲወጡ እያዩ፤ ማስተዋል በጎደለው መልኩ ለግለሰቡ ጥብቅና መቆማቸው በእውነትም ብዙዎችን አሳዝኗል።

በሌላ በኩል በጀርመን የሚገኘው የምእመናን ኅብረት ከቀደመው ጊዜ በተለየ መልኩ በመጠናከር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ እያሳወቀ ሲሆን በቅርቡ በጉዳዩ ዙሪያ ጠንካራ ይዘት ያለው ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መላኩ ታውቋል። የዚህኑ ደብዳቤ ግልባጭም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት አንስቶ በጀርመን ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች በሙሉ ልኳል። “ጠባቂ እረኛችን ይሆኑ ዘንድ በላያችን የተሾሙ ካህናት በጎቻቸው የምንሆን ምእመናን ለቀሳጢ ተኩላ ተላልፈን ስንሰጥ እስከመቼ ይሆን ዝም የሚሉት? ከበቂ በላይ ማስረጃ የተያዘባቸው ግለሰብ እውነተኛ ማንነታቸውን ጮኸው የሚናገሩ መጻሕፍቶቻቸውን በአደባባይ እየቸረቸሩ፤ ሐሰተኛ ትምህርታቸውን ምንም በማያውቁ በየዋህነት በተሰበሰቡ ምእመናን ላይ ሲረጩ፤ በቀን ፀሐይ በጎቻቸውን ከመንጋቸው እየነጠቁ ሲወስዱ ለምን ይሆን በዝምታ የሚታለፉት? በእውነት ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ሲል ለሊቀ ጳጳሱ ያሳሰበው ኅብረቱ “ትእግስታችንም ተሟጦ አልቆ የራሳችንን እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ለችግራችን የበኩልዎን አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጡን ዘንድ ለመጨረሻ ጊዜ አንድ በምታደርገን፣ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም በልጅነት መንፈስ እና በታላቅ አክብሮት እንጠይቅዎታለን” በማለት ለመጨረሻ ጊዜ ነው ያለውን ጥያቄውን አቅርቧል።

ከዚህ በተጨማሪም በጀርመን የሚገኙ ኦርቶዳክሳዊ ምእመናንን በጠንካራ ሁኔታ እያስተባበረ ሲሆን ምእመናኑም ጉዳዩን በሚገባ ተገንዝበው የማያወላዳ አቋም እንዲይዙ፤ ቤተ ክርስቲያናቸውንም የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሰብ በራሪ ወረቀት በጀርመን በሚገኙ አድባራት አሰራጭቷል፤ የኅብረቱን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችም እንዲከታተሉ የሚረዳ Yememenan Hibret የሚል የፌስቡክ ገጽ በመክፈት መረጃዎችን እያስተላለፈ ይገኛል።

ለብፁዕ አቡነ እንጦንስ የተላከውን ደብዳቤ እና በራሪ ወረቀቱን ለመመልከት እዚህ ጋር ይጫኑ። 

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

17 comments:

Anonymous said...

dear Dejeselamawyan, I know Gedamu Demsash when he was living around Genete Iyesys church, Ferensay, Addis Ababa. He rented a room from a decent woman who was struggling to raise her children. By then, there were three churches Genete Iyesus, Woybila Mariam and AnQestse Mihret Qidus Michael under one administration and most of the time the most educated fathers go to Genete Iyesus. knowing this, Gedamu was frequenting Michael church and preaches. The knowledgeable fathers
attend Michael church whenever it is St. Michael, St. Gabriel and other major commemoration days on which Gedamu never appear there. During the major christian holidays like Lidet, Tinsae, Timket,.. he goes to 4 kilo Trinity. I remember on one Tinsae eve he asked the landlord to take her son to Trinity with him and she answered 'we have three churches here at our doorsteps and why he needs to go all the way to 4 kilo'. So, we (those who were in the same area) know from early 1980s that Gedamu and co- are protestants. Finally, we heard that he was married to a girl named Ethiopia and left the country after a while. Therefore, Gedamu has been protestant before he left the country and I am surprised that he got the current status in our church. With all the evidence you mentioned, he is still continuing with his attachment with our church means there are big names in the church hierarchy helping the protestant movement. We need to clear our house and let the Almighty help us to do so.

Anonymous said...

ayeee tekula yebg lemd lebesh metashene???? wey dejeselam(mahebre kidusan) mann lematalel new ahun yihen yahel weshet metkejew enem ezaw nebreku ye 100 aleka berihun mist dibedb anseta alhonelat ye Germen mahebre kidusan abedachehu zendero kes gedamu wengel selesebeku gena yisebekal tebeku weshet atetsafu ok enem botaw neberku 10 sew yizachehu ye Germen me emen telalachehu dinkem kkkkkkk

Anonymous said...

Selame dejselamoche bezu geze yehe neger be dejselame laye enanbealen ewente enate betkerstyane lezeh meftehs mesteat aketwate new weys eza hager yalte menkosatena kahenate benger amenwebet neber zem belew eskahun yalute ? weys endet new bewenat memenaneu eko teschalu awo yeche emenetachen besetu tedfer enkwane enante ategbe yalachute egame beruke bezu yesemanale belu amelake kidusane betkerstyanache yetbeke amen.

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይባርካቹ ውድ ምእመናን።
ክርስቶስ ያልተከለው ዛፍ ይነቀላል።
ማን አለብኝ የሚል ባለ ስልጣንም ነገ ተራ ሰው መሆን እንዳለም አይርሳ።
በተለይ በጀርመን ቤተክርስቲያን ዙርያ ትልቅ አስተዋጸኦ ያደረጉት ዶ ር መርሃዊ ተበጀም ሰው እንደወደዳቸው፤ እናዳከበራቸው ሁሉ ነገ ሌላ ሳይመጣ ከመናፍቁ ጎን ከመቆም ይልቅ ለቤተክርስቲያኑ ቢቆሙ የተሻለ ነው።

ለነገሩ ከዚህ በፊት ከካቶሊክ እና ከሌሎች መናፍቃን ጋር በጥምቀት አንድ ነን ብለው መፈረማችው ይታወሳል።

ምእመናን በርቱ!!!!

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

ለነገሩ፡እሱም፡ቢሆን፡የልብ፡ልብ፡እየተሰማው፡የሚበጠብጠው፡አስተዳዳሪው፡ሊቀ፡ካህናት፡መርአዊ፡ተበጀ፡ስለሚፈቅዱለት፡አይደል፡እንዴ፡፡እሳቸውም፡ምክንያት፡አላቸው፡ይህውም፡የሱ፡ችግር፡እስካልተፈታ፡ድረስ፡የሳቸውን፡ጉዳይ፡ ማንም፡አያነሳውም፡የሚል፡ግምት፡አላቸው፡፡የሳቸውም፡ጉዳይ፡ቢሆን፡ከሱ፡ያላነሰ፡ስለሆነ፡መረሳት፡የለበትም፡፡ሁለቱም፡የክህደት፡ተግባር፡ፈጽመዋልና፡፡የሱን፡ጉዳይ፡ለመፍታት፡መጀመሪያ፡ከሊቀ፡ካህናት፡መርአዊ፡የሚያገኘውን፡ድጋፍ፡ማስቆም፡አለብን፡፡
አምላካችን፡ይርዳን!!!
የእመቤታችን፡ጸሎት፡አይለየን!

ብላቴናዋ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች ስላቀረባችሁት ዘገባበጣምእናመሰግናለን ግን ምነው የነገሩን ጠንሳሽ ዋናውን እረሳችሁዋቸው ሊቀካህናት ተብየውን አህያውን ፈርቶ ዳውላውን አይሁን የናንተም አካሄድ እዚህ እንዳለነው ምእመናን ይሄን ያልኩበት ምክንያት ሲጀመር የቄስመራዊ ምንፍቅና ጠፍቶን ነው ጀሌዎቻቸውላይ የምናፈጠው ለዚያውስ ቢሆን መችፈርተው እርሳቸው እሁድ እለትም ቢሆን ሰውየውን እርሳቸው መክረው ና ባይሉት መች ይመጣነበር ችግሩም ከተፈጠረ በሁዋላም ቢሆን ካህናቱን ትተው በሰውየው ተላለኪ ባቶያሬድ ተጠርተው ከመናፍቁና ካጃቢወቹጋር አውቶብሳቸው ውስጥ ገብተው ተማክረው መናፍቁ ቄስ እጃቸውንየጋጠጣቸው መስቀላቸው እንደሆነ ሲናገሩ እንዳልሰማናቸው ሁሉ ምእመኑዋ እንደሙዋጨረቻቸው ተደርጎ ፖሊስ እንዲጠራ መክረው ምንምእንደማያውቅ ከካህናቱጋር ምሳለመብላት እንደገቡ ስንከታተላቸው የነበርን ታዛቢዎች እናውቃለን ፖሊስ ከመጣበሁዋላም ሚስታቸው ለመናፍቁቄስና ላጃቢዎቻቸው ምሳ አገልግል ሰርተው በነገሩ የተናደዱ ምእመናን እየተሳደቡና እያመናጨቁ መውሰዳቸው ሳያንስ ቄስመራዊ ሰየውንና ተናዳፊምላስያላቸውን ሴቶቻቸውን ለመሸኘት ባውቶብሱ ተሳፍረው ትንሽ መንገድ ሄደው መመለሳቸውሳያንስ ስለቤተክርስቲያናቸው በቁጭት የሚቃጠሉትን ምእመናን ግን መለስ ብለው ሳያናገርዋቸው ቀሩ ለነገሩማ የዋዜማው እለት ቅዳሜ ማደሪያ ያጣው ምእመን ሳታት የሚቆሙልን አባት ፈልገን ስንጸልይ እንደር ልጆቻችንን ይዘን የት እንድረስ ያልዋቸውን ምእመናን የማውቀው ነገር የለኝም የትስ ብትሄዱ ወጡልኝ ብለው ሲዘጉባቸው የተገረመ አንድወጣት ይሄን ቤተክርስቲያ ለመግዛት ገንዘብ አዋጡተብለን አዋጥተን እንዴት ያባርሩናል ቢላቸው የመለሱለት መልስያሳፍር ነበር ለዚያውስ ቤተክርስቲያኑ በስጦታ እንደተሰጠን ሆዳችን እያወቀ እናም ደጀሰላሞች መረጃችሁ የተሙዋላ ለመድረግ ያህል ነው እንጅ የጀርመኑ ጉድ በዚህ የሚያልቅ ሆኖ አይደለም ይቆየን ቸር ያሰማን አሜን

Anonymous said...

pastor gedamu is not an aleqa. he is a protestant pastor who has the permission to preach in our Orthodox Church by dr.merawi tebeje who is supported by and is a loyal friend of the german protestant church. We had heard that dr. merawi had brought to ethiopia his protestant supporters after abba paulos became patriarch and introduced them to abba paulos.
dr. merawi tebeje, from what have heard does not speak good german.
how did he then get his"dr"title? who wrote or translated for him his "dissertation" which is gedle tekle haimanot itself?

Anonymous said...

For me the problem is not mainly of Gedamu but L/K Merawi, who is said to be the head of EOT Churches in Germany, but who strongly and fanatically covers Gedamu. How come that L/K Merawi embraces such a heretic person who wrote an anti orthodox book, unless he (L/K Merawi) himself is taken by heresy like Gedamu? Everybody knows that Gedamu's book was all about protestantism. There is a very simple logic - had he (Gedamu) repented and came back heartily to our church, he should have wrote at first place an official response book to his earlier protestant publications. And never L/K Merawi urged him to write such a book. Neither had we asked such an assurance book. While his books are still sold out to the innocent sheep, L/K Merawi on the contrary defends Gedamu. Is that because of 'yewenz lijenet' or is Merawi also taken by heresy. My conclusion is besides 'yewenz lijinet' L/K himself is already exercising the same belief with Gedamu.' Ye Assa Gimatu Ke antu' endilu abatoch. So, let us first raise a question about L/K Merawi, and Gedamu's secondar and at least we know this person at the outset.

Amen said...

መንገዱን ዘግቶብን ቆሟል መኪናው:
ወይ አዲስ አልገዛን በሽታ የሌለው:
ተበላሽቶ ቆየ መተላለፊያው፡
እባካችሁ ግፉ እናስወግደው።

Anonymous said...

Hallo Deje selamwech selam nacheu ye Germen guday bezeh yemabeka aydelem wanaw Dr. Merawi yemebal sewy selehwne yemebetebetew ebakacheu Deje Selamwch Dr.Merawi bezu yemasazen yeserut neger selale betechalacheu meten yesachewen gud awtulen

Anonymous said...

Ene Be Germany Yemiagelegilu Abatoche Kahinaten Yemiteyekew 1
Tiake Aleng.
Eskemeche new Yehenen Menafik Beguyachihu Wist Debikachihu Yemitinorut.Yehen Hulu Ewnet Eyayachihu Zim Yalachihubet Miknyatu Mindenew?
Eskemeche new Ye Hizbe Christianunes Abetuta,Chuhet,Lekiso
Ende alayachihu,endalsemachihu honachihu yemitasalifut?

Anonymous said...

Hallo sewoch,
ine izi german lerejim ametat sinor, wede bete christian yemihedbet gize betam betat yikoteralu. Balebete besint mekera wede Cologne inhid ina Michaeln inakbir sitlegn, esti zare lihid biye kerejim ametat behula lemejemeria gize metahu. Be'alu betam asdestogn sale bestemecheresha indezi aynet neger bemayete azenkugn. lemangnawim ine kesochun alawkachewim, gin 1 kes pente (menafik) hono temelese sibal, indemedeset lemin bete christianuan tibetebtuatalachu! Yetefaw lij Misale tawkutalachu? bitawkut indezi baladeregachu neber. inante yaye new iko wede protestant yemihonew. christianoch honachu, BE'TABOT fitlefit indezi aynet difret, sew kalmetahugn yibalal? indesemahut kehone degmo, yihichi setyo KORBALECH!!! ye christosin sigana dem wesdalech!!! ..iwnet yihe ye christian sira new??? indanebebkut kehone ye Cologne kesoch nachew ye wiesbadenun kes yegabezut aydel? ..inesu a getachinin melkit new yaderegut, yebedele kalem yimaral, yetefaw beg kehonem bedesta yikebelutal. Misaleyawi sira new yefetsemut, silezi please be'iwnet inante lehaymanotachu yemitkorekoru kehone lemenegager mokru kehulum sewoch gar. kalhone gin yetekerewim protestant yihonulachual. irmen biye wede igziabher bet bimeta, beagul haymanotegnoch tedenabre wede bete temeleskugn. ahunm igre tiseber bimeta...

Anonymous said...

ደጀ ሰላም አዝጋጆች ምነው በሓማኖት የውሽት አስተላላፊዎች መሆን መረጣችሁ? በአውነት እናንተ ሃይማኖተኞች ናችሁ?

Anonymous said...

እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ !!!!!! ወዮልህ መራዊ ፤ወዮልህ ሲራክ ወዮልህ ገዳሙ እናንተ መናፍቃን በ የመለኮት ሥጋ እንደሚፈተትበት እና የ እመቤታችን የአማላጃችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስም የሚጠራበት መሆኑን አትርሱ ዋዋዋ ትግስቱ አልቆ የመጣ ቀን ቁጣው ከ ከለን ተነስቶ...ቪዝባደን ..... ፍራንክፈርት.... እሩቅ ደግሞ አደለም አንተ መናፍቅ ዋልህ እመቤታችንን መሳደብህ ሳያንስ ኦነ አውስናመ ብለህ ማንም ማንም ቢሆን ብለህ የቅዱስንን ክበር አዋርደህ በካስል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያስተማርከው ምንፍቅና እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥልንንና ዶክተር ዲ/ን ሔኖክ ጥሩ መልስ ሰጥቶበት አንጀታችንን አርክቶታል እነ መራዊ እና ጳጳስ ተብዬው እንጦንስ ቁጭ ብለው መልስ ሰጪው ዲያቆኑ ነበር እግዚኦ አምላክ ሆይ እንከመቼ ይሆን ዝምታህ???

Anonymous said...

እኔ ውደ ኮለን ሚካኤል ቤተክርስትያን አልፎ አልፎ እሄዳለው ፡፡ ይህን የተፈፀመው ድርጊት በቦታው እና በጊዜው የተደረገ ትክክለኛ ድርጊት ነው ብዬ አላምንም ፡፡ ግን ሁሉ በርሱ ሆነ በዬ ተቀብዬዋለው ፡፡
ከላይ አንድ ወንድሜ ለመጀመርያ ጊዜ ኮለን ቤተክርስትያን መጥቶ ይህን ሁሉ አስተያየት በመስጠቱ ገርሞኝ ነው እኔም የፃፍኩት፡፡ እንዴት በአንድ ቀን ጋባዥ ማን እንደሆን መጋበዙስ ትክክል እነደሆነ፣ የተጋባዥ ምንነቱስ እውነት በዚህ ሁኔታ ተጋብዞ እንደሆነ ፣ ግብዣውንስ አክብሮ በስአቱ እንደመጣ እና በተሰጠው ቦታ ላይ እንደተገኘ፣ ድርጊቱን የፈፀመችው ማንንት (ቆራቢ ናት ማለትህ ፤ ልምን እንደጠቀስከው ባይገባኝም)፣ እንዲሁም ትክክለኛነቱን አረጋግጠህ በመፃፍህ አሳዝነህኛል፡፡ እንዴት በአንድ ቀን ይህን ሁሉ አጣርተህ አወቅህ? በወሬ? እስቲ ቆም ብለህ እራስህን መርምር፡፡ ነገሩ ስለ እግዝአብሔር ነውና ፡፡ ወደ ቤተክርስትያን ከአሁን በኋላ አልሄድም ከማለት በፊት ለምን ወደ እግዝአብሔር ቤት እሄዳለው ?የሚለውን ለማወቅ ሞክር፡፡ ለወሬ ወይስ እራስን ለማዳን? ስለዚህ በምጀመርያ ከባለቤትህ ጋር እግዝአብሔር የሰጠህን ጊዜ ተጠቅመህ ቡዙ ጊዜ ና ፤ በፀሎት ጠይቅ ፤ ትምህርቱን ተማር ፤ ነገሮችን በመንፈስ መርምር ፤ አራስህን ለንስሃ አብቃ ፡፡ ከዛ በኋላ የምትሰጠው ሙሉ እና ታማኝነት ያለው ይሆናል፡፡

Anonymous said...

yikrtahin wendime, ezih lay yetetsafutin komentoch benmb adrigeh bitanebew hulunim ine yetsafkuachewin information tagegnachew neber. bete christianu gar tebetino yeneberew berari wereketim anb'bewalehu. sile setyewa mekureb degmo, iza yeneberut sewoch sinageru neber. "yekorebech nat ina atas'chenkuat" silu neber. yihen yetekeskubet mikniat, ager bet iyalehu yekorebut sewoch indet indeneberu silemawq new min yahel feriha igziabher indalebachew! lelaw lilih yemifelge degmo, ine huletegna wede bete christian alhedim aydelem lemalet yefelegkut, ke indezi aynet christianoch gar hogne ye igziabher sim mawedes alfelgim. bete christian ye fikir nat inji ye til aydelechim, bezih amnalehu. getachin iyesus kristos ke'andem hulete soste yetetelutin, yetenakutin, hatiategnochin sewoch kelibachew yikir belen silalut bicha mihretin indiyagegnu adrgo mengiste semay indigebu adirgoachewal. igna man feraj adrgon new indezi aynet neger yeminadergew?? yihe begziabher sira megbat new indene amelekaket ina yihe yemigeba aydelem lemalet new yefelegut.

Anonymous said...

yihe yemikeraker sew tsihuf yeman endehone megemet ayakitim. kehuletu gazetegnoch ayafim.enesu nachew yichin ababal yemidegagimuat.Bemejemeria dereja be eletu yetefetsemewun girigir endinesasa yaderegut Gedamuna gbr aberochachew nachew.Sewoch atqeldu!1 sew siemeles des aylachihum, minanin eyalachihu atqeldu. Sewyew altemelesem, yememelesim hasab endelelew bemetsihafochuna besiraw asaytoal.Beyesamintu Pente yemihonut dekemezamurtun atqotrum ende?Kezih belay yemiaskota neger alle ende?Endiawum alasfelagi tigist beza bay negn ene.
Meemenan tenkek bellu lemanigawum.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)