June 6, 2012

በደብረ ይድራስ ቅ/ጊዮርጊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን የተሰማራው ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ይዞ ቤተ መቅደስ ገባ


·        በአስለቃሽ ጢሱ ጸሎተ ቅዳሴው ታጉሏል፤ ሕፃናት፣ ምእመናንና አገልጋዮች ታፍነዋል::
·        ለውዝግቡ መፍትሔ ያፈላልጋል የተባለ ጥምር ኮሚቴ ተቋቁሟል::
·        ከ70 - 80 የሚደርሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን እንደታሰሩ ናቸው::
·        ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሊቀ ጳጳሱን በስልክ አነጋግረዋል::

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 29/2004 ዓ.ም፤ ጁን 6/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ትናንት፣ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ ስድስት ፖሊሶችና በርካታ ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ብዙዎቹን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላትንና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ በቁጥር ከ70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣት እና አዛውንት ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡


ግጭቱ እየቀጠለ በነበረበት ኹኔታ ለጸሎተ ቅዳሴ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመበተን በሚል ፖሊስ ወደ ቤተ መቅደሱ ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተመልክቷል፤ በዚህም በመካሄድ ላይ የነበረው ጸሎተ ቅዳሴ ታጉሏል፤ ለቍርባን የተዘጋጁ ሕፃናት፣ ሌሎች ምእመናንና አገልጋዮችም በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሕን ቤተ ክርስቲያኑ በሮችና መስኰቶች መንሥኤው ለጊዜው ባልታወቀ ኹኔታ የተበሳሱና የተሰባበሩ ሲሆን የደብሩ አስተዳደር ቢሮዎች፣ የጥምቀተ ክርስትና ቤትና ሌሎችም በሮች “የተደበቁ ሰዎችን ለማሰስ” በሚል መዝጊያዎቻቸው እየተሰበረ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ተገልጧል፡፡

ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ‹የፓትርያሪኩ ልዩ ሀገረ ስብከት› በሚል ከሚታወቀው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የረዳት ሊቀ ጵጵስና ሓላፊነታቸው እየለቀቁ ያሉት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በጉዳዩ ላይ በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል፤ በግጭቱ አንድ ፖሊስ መሞቱንና ሌሎች ስድስት አባላት መቁሰላቸውን የተናገሩት ከንቲባ ኩማ የታሰሩት ምእመናን እንዲፈቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉ ተሰምቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የደብሩ የክብረ በዓል (ንግሥ) እና መስቀል ደመራ ፍራ የነበረውን ይዞታ የቀበሌ 06 ጽ/ቤት (የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ) ለመከለል የጀመረው ሂደት እንዲቆም ተደርጎ ውዝግቡን የሚያጣራ ኮሚቴ መቋቋሙ ተነግሯል፡፡ ኮሚቴው ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ ከአጥቢያው ምእመናን፣ ከክፍለ ከተማው አስተዳደርና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የተውጣጡ አባላት የሚገኙበት ነው፡፡
ግጭቱ ትናንት ጠዋት ከመቀስቀሱ ቀደም ብሎ የአጥቢያው አስተዳደር፣ አገልጋዮችና ምእመናን በፖሊስ ታጅቦ የመጣውን ግብረ ኀይል በባንዲራው እያሉ ሲማፀኑ ነበር፤ እነርሱ ራሳቸው ይዞታቸውን ለማስከበር በተደጋጋሚ ሲያመለክቱበት የቆዩበትና አሁንም ከፓትርያኩ ጋራ እየተነጋገሩበት በመኾኑ ግብረ ኀይሉ ወደ ርምጃ ከመግባቱ አስቀድሞ ሁለት ቀናት እንዲሰጣቸው ሲጠይቁም እንደ ነበር ተዘግቧል፡፡

ምእመናኑ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ለሚያቀርቡት ተማኖ ቦታ ያልሰጠው ግብረ ኀይሉ ግን አጥሩን ወደ ማፈራረስና ችካል ወደ መቸከል ተግባር በመግባቱ ምእመናኑ ርምጃውን ድንጋይ በመወርወር ሲከላከሉ የአድማ ብተና ፖሊስ ደግሞ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ ምእመናኑን ለመበተን መሰማራቱ ተገልጧል፤ ጥይትም ተተኩሷል፡፡ የችካል ምልክቱ የሚያርፍበት ቦታ ከዐውደ ምሕረቱ ያለው ርቀት ከኀምሳ ሜትር እንደማይበልጥ የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የደብሩ አስተዳደር በዚህ ይዞታው ላይ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታና በሌሎችም ትልሞች የራሱን የራስ አገዝ ልማት ዕቅዶች ለማካሄድ ሲንቀሳቀስ እንደ ነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ በርካታ አድባራትና ገዳማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዳገኙ ተዘግቧል፡፡ በአንዳንዶቹም÷ ለአብነት ያህል በኮተቤ ደብረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል÷ የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ለግለሰብ ጥቅመኞችና ለፕሮቴስንታቶች በመሰጠቱ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የየካ ክፍለ ከተማ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በጉዳዩ እንዲያስብበት ያቀረበው ጥያቄ ይገኝበታል፡፡

በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንም የትናንቱ ችግር በተዘገበው ደረጃ እንዲባባስ ያደረገው አሁን እስከ ዐውደ ምሕረቱ የዘለቀው የይዞታ ነጠቃ ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ጽ/ቤት ቀደም ብሎ የደብሩ ካህናት መኖሪያ ቤት ተሠርቶበት የነበረውን ቦታ በመውሰድ ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ጽ/ቤት ሲሠራበት በዝምታ በመታለፉ መሆኑን አስተየየታቸውን ለዜና ሰዎች የሰጡ የሰበካው ምእመናን ገልጸዋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ (ከፍተኛ 24 ቀበሌ 14 59 ቁጥር ማዞርያ) አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከ23 ዓመት በፊት፣ በ1981 ዓ.ም የተመሠረተ ደብር ነው፡፡
ይድራስ የዱድያኖስ ጭፍሮች የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ዐፅም አቃጥለውና ፈጭተው የበተኑበት ተራራ ስም እንደ ኾነ ይታወቃል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን


15 comments:

Gofa Geberal said...

weyew medhanialem, ere gude newe meche newe dege negere sele betkerstianachene yemensemawe. Bewenete ye medhanialm kuta ahunesse alberde beluale. ye kuta betrue betam kebeobenal. ye zekala esate segermene waldeba, ye waldeba sedenkene, ye debereyderase. Every day new mekerana hazene betekerstayanachene aschenekate. ahunese yemyasfelegew hulachnem neseha megebate ena essu endetarkene we de amanuel mechohe newe. Enatu kene lejewa, ye mehrete fetewane temelselene. Ye betkerstaynachenene tefatena mekera beyekenu ke mesemate yadenene.

Gofa Geberal said...

weyew medhanialem, ere gude newe meche newe dege negere sele betkerstianachene yemensemawe. Bewenete ye medhanialm kuta ahunesse alberde beluale. ye kuta betrue betam kebeobenal. ye zekala esate segermene waldeba, ye waldeba sedenkene, ye debereyderase. Every day new mekerana hazene betekerstayanachene aschenekate. ahunese yemyasfelegew hulachnem neseha megebate ena essu endetarkene we de amanuel mechohe newe. Enatu kene lejewa, ye mehrete fetewane temelselene. Ye betkerstaynachenene tefatena mekera beyekenu ke mesemate yadenene.

lamelame europe said...

Egezeoooooooooooooooooooooooooooooooooooo

Anonymous said...

አሁን በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጥቃት ከመቶ ዓመት በፊት የቅኝ ገዥዎች በአፍሪካውያን ወገኖቻችን ላይ ያደረሱት ጥቃት ተቀጢያ ነው። በወቅቱ ወላጆቻችን ባደረጉት የጀግንነት ተጋድሎ ህዝባችንን፣ሃይማኖታችንና ባህላችንን አስጠብቀውና አስከብረው ለሌላ አፍሪካውያን ወገኖቻችንና በአጠቃላይ ለጥቁር ህዝብ ኩራትና የጀግንነት ምሳሌ እንድንሆን አድርገውን አልፈዋል። እነኚህ የባዕድ ሃይሎች በጊዜው በወላጆቻችን ቆራጥ ተጋድሎ ያሰቡትን መፈጸም ቢያቅታቸውም በጣም በረቀቀ መንገድ እንደነሱ እንድናስብና ዓለምንም እነሱ በሚያዩት መነጽር እንድናይ ማለትም “እነሱ የሰለጠኑ: እኛ ግን ያልሰለጠን፣እንደውም ከስብዕና ዝቅ ያልንና ህግና ስርዓት የማናውቅ፣ ሃይማኖት፣ታሪክና ወግ እንዲሁም ስልጣኔ የሌለን በመሆኑ፣ እነሱ ክርስትና አንሰተውን ወግና ስርዓት ካላስያዙን እንደእውሬ እርስ በርስ የምንበላላ ህዝብ እንደሆን) አድርገው ዘመናዊ ትምህርት በሚባለው አእምሮ አደንዛዥ አደንዝዘውንና አሳምነውን ህዝባችንን እንድናዋርድና ሃይማኖታችንን፣ ባህላችን፣ ታሪካችንና በአጠቃላይ የእኛ የሆነውን እንድንንቅና የባእድና የነሱ የሆነውን ግን እንድናደንቅና እንደውም እንድናመልከ አድርገውን የአሁኑ አይነት ጥቃት በህዝባችን ላይ እንድናደርስ አስደርገውናል። ጥቃት እየተካሄደብን ያለው እነሱ ባሰለጠናቸው ወገኖቻችን መሆኑ በጣሙን የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ ነው። ባለፈው በአፍሪካውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃትና በአሁኑ ሰዓት በህዝባችን ላይ አየደረሰ ያለው ጥቃት ልዩነቱ ያለፈው ጥቃት ቀጥታ ወረራ በማድረግ የተከናወነ መሆኑና ያሁኑ ጥቃት ግን እነሱ ባሰለጠኖቻቸው የራሳችን ወገኖቸ መደረጉ ነው። በይዘት ሁለቱም አንድ ናቸው። ሁለቱም በስልጣኔና የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚል ስም ነው። ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ባህሉና ወጉ የተናቀ ህዝብ በራሱ ላይ እምነትና ኩራት ሊኖረው ስለማይችል አገር ማልማት ቀርቶ ህልውናውንም ማስከበር የማይችል አንገቱን የደፋ ህዝብ ነው የሚሆነው። አስተዋዩና ትግስተኛ ህዝባችን ያኔም እንዳደረገው ይህን በባእድ አጅ በሰለጠኑ ወገኖቹ የሚደርስበትን ጥቃት ከእግዚአብሄር ጋር ይቃቃማል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።

Anonymous said...

yebelen.... endi beye atbiaw torun yazmet enji..... zimetaw endehon tesmamtotal...yaltebabere kind wagaw yehew new...tinant le waldeba alchohenem.. ahunem demo lezih betekrstian lelaw debar aychohem.. ande be ande yatefun enji menager endehone alhonelen!! lemehonu ethiopia lemadeg betekrstian metefat alebat ende??? yehe lemat yemibal neger eko yeemnet tser hone!!!

Anonymous said...

ፖለቲካ ውስጥ ካሉ አስነዋሪ ድርጊቶች መከከል አንዱ ይህ ነው::

ሕዝብ አመራሩን በቅርበት እንዳይመለከተውና ለአደጋ እንዳይጋለጥ የሚፈልጉ አንባገነን መሪዎች የሚጠቀሙበት ራስን የመደበቅ ስልት አለላችሁ:: /Agenda divret/ ወይም ጉዳይ መቀየር ይሉታል:: እኛ ምናልባትም በወሬያችን መካከል ርእስ መቀየር የምንላት ዓይነት ናት::

የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዝቡ ትኩረት ሳቢ ጉዳይ ሃይማኖት መሆኑን በሚገባ ያውቃል:: በዚህ ምክንያት በርካታ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች በተለያዩ ወቅቶች ለአጀንዳ መቀየሪያነት ውለዋል:: በተደጋጋሚ አሁንም ድረስ የሚጠቀምበት የይዞታን ማስከበር ጉዳይን በምሳሌነት ብናነሳ:: መቼም የትም ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይቀሰቀስ የሚፈልግ መንግሥት ጉዳዩን እዚህም እዚያም ሁከት የሚፈጥር: ሕዝብን እርስ በርስ የሚያጋጭ ሆኖ ሲያገኘው: በራሱም ላይ ጥላቻን የሚፈጥር መሆኑን እያወቀ:: እንዲህ ያሉ ጉዳዮች እንዲህ ባለ ሁኔታ ይፈቱ ብሎ አፈጻጸሙን መወሰን አቅቶ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ተለይቶስ አከራካሪ የሚሆነው የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ብቻ ነውን? ጉዳዩ ግን ሃይማኖታዊነውና ለአጀንዳነት ያገለግላ:: ከይዞታ ወደ ሌላኛው ማሳያ ልለፍ ቃጠሎ የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ላይ ያተኮረው ግራኝ ዳግም ተወልዶ ነው ወይ አያስብልም? ወይስ በተለየ ሁኔታ ታሪካዊ ገዳማትና አድባራትን ያጠቃው እሳት ከሰማይ ወርዶ ነው? በቀላሉ ደጀ ሰላም የዘገበቻቸውን የቃጠሎ ዜናዎች ብቻ በሁለት ዓመት የት እንደደረሱ ቁጠሩዋቸው:: ለአጀንዳ መቀየሪያነት ስንቱ ሀብት እንደባከነ አገር ይቁጠረው:: የሚገርመው ጉዳይ በየቤተ እምነቱ ያሉ ትኩሳቶች ደግሞ አሉ:: በኢትዮጵያ ከመንግሥት ምክር ቤት ስብሰባ ይልቅ የሲኖዶስ ስብሰባ የሚዲያውን ከፍተኛ ሽፋን ይወስዳል ብል አልዋሸሁም:: በበጎ መልኩ ቢሆን መልካም ነበረ:: ነገር ግን መንግሥት ሆን ብሎ ከጀርባ በሚሠራቸው ፊልሞች የአንድ ወቅት መነጋገሪያ ያደርጋቸዋል:: በነዚህ ወቅቶች ሕዝብ የኑሮ ውድነትን: የመንግሥትን ለውጥ: የፖለቲካ መሪዎችን መግለጫ: ወዘተ የሚሰማበት ጆሮ የሚያወራበት ጊዜ የለውም:: በዚህ ምክንያት አዳዲስ ሃይማኖታዊ አጀንዳዎችን እንደ አየር ጠባይ እየቀያየረ ወደ ፊት ገጽ ያመጣቸዋል:: እስኪ አስተውሉ አገራችን እውነት ለእድገቷ የምንተጋ ሕዝቦቿ ነን ምቀኛ ሆነን ለምን ፋብሪካ ተተከለ የምንለው? የአባይ ፕሮጀክት የት ደረሰ? ስንት ተሰበሰበ? እያልክ ስትወያይ ከምትውል:: የአምስት ዓመቱን የእቅድ መርሐ ግብር ስኬታማነት ከምትገመግም:: . . . በምትወደው ነገር ይፈትንሀል:: ላሳርገው መንግሥታችን መፍትሄ የሚሰጠን ስለሚያስፈልገን አደለም:: ለነርሱ ጠቃሚ የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው:: ትኩረት የሚስብለት ጉዳይ ካገኝ ባለመፍታት በማጉላላትና በማጋጨትም ጭምር ይጠቀማል:: ስለዚህ ሁል ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን የሚገጥሙ ክስተቶችን ብቻቸውን ሳይሆን ጀርባቸውንና ፍጻሜያቸውንም ጭምር ማወቅና መከታተል ያስፈልገናል:: እላለሁ እናንተስ ምን ትላላችሁ ደጀሰላማውያን?

Anonymous said...

አሁን በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጥቃት ከመቶ ዓመት በፊት የቅኝ ገዥዎች በአፍሪካውያን ወገኖቻችን ላይ ያደረሱት ጥቃት ተቀጢያ ነው። በወቅቱ ወላጆቻችን ባደረጉት የጀግንነት ተጋድሎ ህዝባችንን፣ሃይማኖታችንና ባህላችንን አስጠብቀውና አስከብረው ለሌላ አፍሪካውያን ወገኖቻችንና በአጠቃላይ ለጥቁር ህዝብ ኩራትና የጀግንነት ምሳሌ እንድንሆን አድርገውን አልፈዋል። እነኚህ የባዕድ ሃይሎች በጊዜው በወላጆቻችን ቆራጥ ተጋድሎ ያሰቡትን መፈጸም ቢያቅታቸውም በጣም በረቀቀ መንገድ እንደነሱ እንድናስብና ዓለምንም እነሱ በሚያዩት መነጽር እንድናይ ማለትም “እነሱ የሰለጠኑ: እኛ ግን ያልሰለጠን፣እንደውም ከስብዕና ዝቅ ያልንና ህግና ስርዓት የማናውቅ፣ ሃይማኖት፣ታሪክና ወግ እንዲሁም ስልጣኔ የሌለን በመሆኑ፣ እነሱ ክርስትና አንሰተውን ወግና ስርዓት ካላስያዙን እንደእውሬ እርስ በርስ የምንበላላ ህዝብ እንደሆን) አድርገው ዘመናዊ ትምህርት በሚባለው አእምሮ አደንዛዥ አደንዝዘውንና አሳምነውን ህዝባችንን እንድናዋርድና ሃይማኖታችንን፣ ባህላችን፣ ታሪካችንና በአጠቃላይ የእኛ የሆነውን እንድንንቅና የባእድና የነሱ የሆነውን ግን እንድናደንቅና እንደውም እንድናመልከ አድርገውን የአሁኑ አይነት ጥቃት በህዝባችን ላይ እንድናደርስ አስደርገውናል። ጥቃት እየተካሄደብን ያለው እነሱ ባሰለጠናቸው ወገኖቻችን መሆኑ በጣሙን የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ ነው። ባለፈው በአፍሪካውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃትና በአሁኑ ሰዓት በህዝባችን ላይ አየደረሰ ያለው ጥቃት ልዩነቱ ያለፈው ጥቃት ቀጥታ ወረራ በማድረግ የተከናወነ መሆኑና ያሁኑ ጥቃት ግን እነሱ ባሰለጠኖቻቸው የራሳችን ወገኖቸ መደረጉ ነው። በይዘት ሁለቱም አንድ ናቸው። ሁለቱም በስልጣኔና የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚል ስም ነው። ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ባህሉና ወጉ የተናቀ ህዝብ በራሱ ላይ እምነትና ኩራት ሊኖረው ስለማይችል አገር ማልማት ቀርቶ ህልውናውንም ማስከበር የማይችል አንገቱን የደፋ ህዝብ ነው የሚሆነው። አስተዋዩና ትግስተኛ ህዝባችን ያኔም እንዳደረገው ይህን በባእድ አጅ በሰለጠኑ ወገኖቹ የሚደርስበትን ጥቃት ከእግዚአብሄር ጋር ይቃቃማል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ

Anonymous said...

Wegenoch ebakachu wede Medaniyalem enchuh...Wektum yestome silehone le Tselot, Egziota yimechal...Yemisebesiben abat binatam begilachinm bihone Wede Bete mekdes hiden Medaniyalemin enimatsen...Amlak fitun endiyazoriln be enbachin tatiben enleminew. Esu deg Amlak new chuhetachinin yesemal...entseliye entseliye, enseliye.

galela said...

yasazenale .........

Anonymous said...

Amlak hoy gin silemin tewiken...ebakh fithin wedegna melis...telatachin begna lay endiseletin atifikedilet....Geta hoy tsegah erkonal...frihat wereren, desta erakan, selam atan, terabin, teteman, melkamun mayet ena mesmat akaten...Geta hoy Hatiyatachin minigna yekefa bihon yihon...ante yeraken. Amlkhoy Yikir belen ena Temeles wedegna Get Hoy Ebakhi Temeles wedegna...Weladite Amlak Ebakish Lijshin temastegnilin Askeyimenewal ena Astarkin...Anchin yizen Anafirm Eme Amlak....ooooooo

Anonymous said...

betam tikekel new yemazenagat sera eyetesera new.

123... said...

Comment Alsetm. Miknyatum mefthewn hulum slemiyawqew. Tyaqew bete khnet engba weys betemengst? new. Bete megst stgeba bete khnetun tagegnewaleh. yih degmo bewere ayhonm bemesrat new. Ye Tewahdo lijoch muslimun eyut wede 4 killo eyegesegese new.Bete chrstiann lemadan betemengstun meyaz yasfelgal. Behulu mesk tetsno fetari mehon yashal. Waldban yedefere mengst weyrasefern mn endiaderg entebkalen?

lelr said...

what is next?

ክፍለ ከጀርመን said...

እንዴ እኒህ ሰዎች መካሪ የላቸውም እንዴ ለምንድር ነው በማይመጣው እየመጡ የሚፈታተኑን? ስንቴ ቤተመቅደሳችንን ይደፍራሉ? ስንቴ ቅዳሴ ያስታጉላሉ? ስንቴ ካህናቶቻችንን ይገርፋሉ? ስንቴ ምእመናንን ያስራሉ? ሁሉን እኮ ተውንላቸው ምናለበት ሃይማኖታችንን ቢተዉልን ወደከፋ ምሬት ባያደርሱን! እባካችሁ የምትሰሙ ካላችሁ ምሬታችንን ንገሩልን በእሳት አትጫወቱ በሉልን፤ አምላክ ሆይ እንደይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን በእኛ ኃጢአት በደምህ የዋጀሀትን ቤተክርስቲያንህን ለሚጣሉአትና ለአሳዳጆች አሳልፈህ አትስታት፤ በግፍ የሚታሠሩና የሚገረፉ የአገልጋዮችህን መገፋት ተመልከት ማስተዋል ከተሳናቸው ዕቡያን መሪዎች ታደጋት! ደግሞም የሚያከብራት የሚያስከብራት አባት ስጣት።

Anonymous said...

ይሄ ወሮ በላ መንግሥት ሰፊ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን በነጻ አስረከበ ዝም አልን! በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር የኢትዮጵያ ለም መሬት ለሳውዲ ለማሌዚያ ለቻይናና ለህንድ ባለሃብቶች ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ ዝም አልን! በርካታ ሄክታር የኦሮሚያ ለምለም ደን በእሳት ተቃጥሎ ተመንጥሮ ለውጭ ኢንቬስተሮች ሻይ ቅጠል መትከያነት ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ ዝም አልን! ለምቶ እህል ልንበላበት ከልመና ልንወጣበት የሚያስቸል በርካታ ሄክታር መሬት ለጠገቡ ፈረንጆች አበባ ማብቀያ እንዲሆን ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ የአበባው መሬትም ሌላ የእህል ዘር እንዳያበቅል ሆኖ በአሲድ እየተቃጠለ እያየን ዝም አልን! ወደ ዋልድባ ገዳም ሄዶ የእምነት ቦታውን በጉልበቱ ነጥቆ የቅዱሳንን አጽም እየፈነቀለ ሲጥል አቅም የሌላቸው መነኮሳትን እያሳደደ ሲያስር እያየን ዝም አልን! አሁን ደግሞ በሃገሪቱ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ቀስ በቀስ ይዞታቸውን እየሸጠ ገንዘቡን ኪሱ መክተት ጀመረ ዝም አልን !በዚህ ጉዳይ ማንም እንዳይቃወመው በቤተክርስቲያን ካድሬዎችን ከዲያቆን እስከ ፓትርያርክ አስቀመጠ በመስጊድ ካድሬዎቹን ከደረሳ እስከ ኢማና የመጅሊስ መሪ ጭምር አስቀመጠ! ደጋፌዎቹ አህባሾችንም ሰገሰገ! ወገኖቼ በሂደት ሃገራችንን እያጣናት እኛም ለባርነት እየተሸጥን ነውና በእግዚአብሔር ወይም በአላህ ሥም ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ !ሃገረ የሌለው የተዋረደ ስደተኛ ሆነን ከምንቀር ሃገር ያለው ለሃገሩ በክብር የሞተ ሰው ብንሆን ይሻለናልና በአንድነት እንቁም

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)