(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።
ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን
እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው
ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና
ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት
ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ
ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል።
በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦ 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ
ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት
የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን
ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ
ይህንን ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን


20 comments:
Endih New Enji Jegninet... Enat eko lijochuwan yemititebikibet gize new
Great Vegas,that how it should be done.Everyone should learn from vegas.
ይበል የሚያሰኝ ነዉ ቬጋሶች እንዲያ ነዉ እንጂ!
ለሌሎች አራአያነት ያለዉ ሥራ ነዉ የሠራችሁት ሌሎችም የናንተኑ ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነዉ። በተለይ ስም በመጥራት (ከመረቁ አዉጡልኝ ... አይነት) ላይ ያሉትም እንዲሁ ሊያደርጉ ይገባቸዋል። ደጋፊዎች አሉኝ እያሉ እዚያ አገር ቤት የሚያወሩትና የሚያስወሩትም ለዚሁ ይመስላል። አቡነ ፋኑኤልን ባዶአቸዉን የምናስቀርበት ጊዜ አሁን ነዉ።
አቡነ ፋኑኤል እና አቡነ ጳዉሎስ ከነ ግብር አበሮቻቸዉ የቤተ ክርስቲያናችንን እድገት ሳይሆን ዉድቀትዋን ለማየት የሚናፍቁ ናቸዉና በተለይ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል።
መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያያቸዉ እንደማይፈልግ ስለሚያዉቁ ከዚህ በኅላ ወደ አገር ቤት ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር አይሄዱም: እዚያዉ እንደለመደባቸዉ የራሳቸዉን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክስቲያን ይዘዉ ቁጭ እንዲሉ ማድረግ ነዉ ::
Great job. All what they pointed out are acceptable.
I have been suggesting this for a long time. This is the only way to deal with Abune Paulos and his political and ethinic coronies. It is time believers fought back against, church gear clad so called fathers. It is enought they abuse poor church goers in Ethiopia, they shouldn;t be allowed to ran amock in a place we sought refugee from thier brutality. God bless
ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ውሳኔ። እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ።
ሁላችንም የነሡን ፈለግ በመከተል በየአብያተ ክርስቲያኑ ያሉ መናፍቃንን ጥፋት እንከላከል።
Thank God! and thanks vegas here you go the real orthodox followers and keep it up.we expect more jobs like this clearing the unclean. the God of our fathers be with you.God for the sake of your mother and our holly fathers please protect our church.amen
እናታችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን ጐበዝ ቨጋስ ጠንካራ ክርስትያን ያለበት ብዙ ፈተና ያሳለፉ ወንድሞችና እህቶች ያሉበት ነው አሁንም ከነዚህ በተክርስትያንን ከምጠሉ ጋር ህብርት ያለው ማንም ይሁን ማን በጥንቃቄ እንድታዩት አደራ እናንተ ውስጥ እርም የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠ አለና
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን
Thanks Dejeselam....
Dn Seyoum Asfaw Teklearegay teblo Yistekakel
Dn seyoum w/agetay yemilew sihtet new
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን
seattel is next
ጎበዝ!ሁላችንም እንቃ ለሰዎች ሳይሆን ለቤተክርስተያናችን ዘብ እንቁም የሚያጠፉ ሰዎች ጥፋታቸውን እንንገራቸው ለእነሱም ይጠቅማልና፡፡
ጎበዝ!ሁላችንም እንቃ ለሰዎች ሳይሆን ለቤተክርስተያናችን ዘብ እንቁም የሚያጠፉ ሰዎች ጥፋታቸውን እንንገራቸው ለእነሱም ይጠቅማልና፡፡
dejaselam u are thadeso u r not ortodok
seyoum tekle aregay teblo Yistekakel
+++
የሐዋርያት ሥራ 20:27_30 የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
በርቱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን::
ጸረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና አቋም ያለው ስው እንዴት ብፁዕ ተብሎ ይጠራል?
So Vegas's, do you think you are protecting the churchs cannon by not accepting and refuse the Arcbishop instead of dis-respect the word ofholly sinod. I thought you are under EOTC, so what can you say after this, half-half, or neutral, or so.Even if you belive the Arcbishop is not write the way you experess is not write too. you can fix "seheteten be sehetet". Think twice, huwala yemiasafer wesane endayehone !
DRAR DEJESELAMAWEUAN,YOU DID A GOOD JOB VEGAS. I PROUD OF YOU. THIS IS WHAT WE SHOULD DO.
Post a Comment