June 16, 2012

ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ

·         መናፍቃ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም
·         የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ
·         መናፍቃ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ
·         ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል
·         ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
·         “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡

ድርጅቶቹ እና ግለሰቦቹ የተወገዙት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት የተለየ የኑፋቄ ትምህርት በመጽሐፋቸው፣ በመጽሔታቸው፣ በመጣጥፎቻቸውና በኤሌክትሮኒክስ የኅትመት ውጤቶቻቸው ሲያሰራጩ በመገኘታቸውና ይህም በማስረጃ በመረጋገጡ መኾኑን የገለጸው ቃለ ውግዘቱ÷ ውሳኔው በይፋ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ድርጅቶቹ እና ግለሰቦቹ በቤተ ክርስቲያኒቱ መርሐ ግብር በማንኛውም መድረክ እንዳይሳተፉ፤ እስከ አሁን ሲጠሩበት በነበረው የክህነት እና የክብር የማዕርግ ስም እንዳይጠሩበት ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አሳስቧል፡፡ ለውሳኔው መሠረት የኾነው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የሊቃውንት ጉባኤ ጥምር ኮሚቴ ሰነድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ዐዋቂዎች እና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከተመረመረ በኋላ ድርጅቶቹ እና ግለሰቦቹ የቤተ ክርስቲያኒቷን የከበረ ስሟን በማጉደፍ፣ ታሪኳን፣ ክብሯን በመዳፈር ላደረሱት በደል በሕግ እንደሚጠይቁ የውሳኔ ቃለ ጉባኤው አስታውቋል፡፡

መናፍቃን ድርጅቶቹና ግለሰቦቹ ላሰራጯቸው ጽሑፎች የማስተባባያ ምላሽ እንደሚዘጋጅና ዝግጅቱም በመጽሔት ጥራዝ መልክ ተዘጋጅቶ እንደሚወጣ የውሳኔው ማጠቃለያ አመልክቷል፡፡ በይቀጥላልም ጽሑፉን የማዘጋጀት ሓላፊነት የተጣለበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል የሚሰነዘረውን ሃይማኖትን የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ተከታትሎ በጊዜው በቂ የኾነ ምላሽ ለመስጠት በሚያስችለው ስፋት እና ጥራት እንደሚጠናከር አብሥሯል፡፡

በቃለ ውግዘቱ የተካተቱት ድርጅቶችና ግለሰቦች በበደላቸው ተጸጽተው የይቅርታ ደብዳቤ ጽፈው ይቅርታ ከጠየቁ የይቅርታ ጥያቄውን ለመመርመር እና ይቅርታ ጠያቂዎችን ለመቀበል ዝግጁ መኾኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጧል፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኒቂያና በቁስጥንጥንያ፣ እንዲሁም በአምስተኛው መቶ ዓመት በኤፌሶን በተደረጉ ጉባኤያት የተወሰኑትን ተቀብላ፣ አጽንታ በመያዝ የምታስተምር መኾኗን የገለጸው የውሳኔው መግቢያ÷ በዓለማችን በትምህርተ ሃይማኖት ሂደት ብዙ አስደንጋጭ፣ አስፈሪና አሳፋሪ ብዙ ክሥተቶች በየጊዜው በተለያየ ስምና ጠባይ መፈጠራቸውን አስታውሷል፡፡ ነቢያት በትንቢት፣ ሐዋርያት በስብከት፣ ሊቃውንት በትምህርት የተባበሩበት ትምህርተ ሃይማኖት ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገ፣ ከነገ ወዲያው ያልተለወጠው፣ የማይለወጠው የጸና፣ የቀና እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚኖር በመኾኑ መናፍቃን ድርጅቶቹንና ግለሰቦቹን ማውገዙን አስታውቋል፡፡

ቃለ ውግዘትን ፈርቶ በተወገዙበት ጉዳይ ከልብ ተጸጽቶና ቃለ ካህንን አክብሮ ይቅርታ መጠየቅ፣ ራስን ከተሳሳተ ትምህርትና ከምግባረ ብልሹነት መጠበቅ አብዝቶ ይጠቅማል፡፡ እንደ መፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች ክህነትንና ግዝትን ንቆና ተደፋፍሮ ሌላውን ማደፋፈር ደግሞ ድርብ ጥፋት ነው፡፡ በሰማይ እና በምድር ሁሉን በተገባ ለማሰርና ለመፍታት ሥልጣን የተሰጣቸው ቅዱሳን ሐዋርያት መንበር ወራሽ የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በክህነታዊ ሥልጣኑ ያስተላለፈውን ውግዘት መናቅ በምንም መንገድ መንፈሳዊነት ሊኾን አይችልምና፡፡

ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል “አንቀጸ ብርሃን”  በሚል ስያሜ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚያጭበረበረው ድርጅት መሥራች አሸናፊ መኰንን ይባላል፡፡ በእጅጋየሁ በየነ አስተዋዋቂነት በመንበረ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት “የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት” የተሰኙ ጽሑፎችን እስከማዘጋጀት መድረሱ ይነገርለታል፡፡ ወደ ልዩ ጽ/ቤቱ ከመቅረቡ በፊትም ይኹን በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የቅዱስ ሲኖዶስን ቃለ ጉባኤ ከሚይዝ አንድ ግለሰብና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና መዝገብ ቤት ሓላፊ ከኾነችው ወ/ሮ ዐጸደ ግርማይ ጋራ ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው ተገልጧል፡፡

ኑፋቄን፣ ስድብንና ሽንገላን፣ ሽሙጥንና ትችትን፣ ክሕደትን የተመሉ ስድስት መጻሕፍቱ፣ 10 መጽሔቶቹ እና ሌሎችም መጣጥፎቹ ተመርምረው ዳንኤል ተሾመ ከተባለ ሌላ ግብረ አበሩ ጋራ እነርሱም፣ ድርጅታቸውም ጽሑፎቻቸውም በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘው አሸናፊ÷ ገና ጉዳዩ ለምልአተ ጉባኤው ቀርቦ በመታየት ላይ ሳለ በወይዘሮዋና በፓትርያርኩ ተጽዕኖ ውሳኔውን ለማስቀየር ያደረገው ብልጠት ሳይሠራለት ቀርቷል፡፡

አሸናፊ ግን ቁርጡን ዐውቆ በህልውና ሥላሴ፣ በጌታችን አምላካዊ ክብር፣ በሃይማኖታችንና በኢትዮጵያዊ ወኔያችን ላይ ሲዳክርበት የኖረውን ጥፋቱን አላመነም፡፡ የመጨረሻ ነገር ግን አሳፋሪ ሙከራ አደረገ፡፡ ለዚህም የቅዱስ ሲኖዶስን ቃለ ጉባኤ ከሚይዙት የጽ/ቤት ሠራተኞች የአንዱን÷ በአንዳንድ ምንጮች ጥቆማ ግለሰቡ የ”አንቀጸ ብርሃን” የቆየ አባል እንደ ኾነም ተጠቁሟል÷ (ስሙን ብናውቅም ከመጥቀስ ተቆጥበናል) ሸፍጥ ይጠቀማል፡፡

የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች እንደሚያስረዱት ይኸው የአሸናፊ ሸፍጠኛ የቅዱስ ሲኖዶሱ የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ተተይቦና ተባዝቶ በሚጠረዝበት ወቅት÷ በገጽ 38 ላይ በስም ተራ ቁጥር ከሚዘረዝራቸው 16 ውጉዝ ግለሰቦች መካከል÷ በተራ ቁጥር 16 ላይ የተጠቀሰው የአሸናፊ መኰንን ስም አብሮት ከተወገዘውና በተራ ቁጥር 4 ላይ ከተጠቀሰው ዳንኤል ተሾመ በመነጠል በመጨረሻ ላይ እንዲሰፍርና እንዲገደፍ በማድረግ የ15 ሰዎችን ስም ዝርዝር ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቅርቧል፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ የመረመሩት ብፁዕ ዋና ጸሐፊውም ግለሰቦቹ 16 መኾናቸውንና የአሸናፊ መኰንን ስም አለመካተቱን በመጥቀስ ቀልቡን ይገፉታል፡፡

በቤተ ክህነቱ የቆየ ሠራተኛ ለዚያውም የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባልደረባ በመኾኑ ጓደኛው አሸናፊ ከክፉ ግብሩ ተመልሶ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሊመክረው ሲገባ ቅሠጣው የተጋለጠበት ቀሣጢው ግለሰብም በድንጋጤ ነው ቢሉ፣ ለሌላ ተንኰል እንዲያመቸውም ነው ቢሉ የተቀሠጠው (የጎደለው፣ የጎመደው) የአሸናፊ መኰንን ስም በተራ ቁጥር 16 ላይ በእጅ ጽሑፍ እንዲገባ ያደርጋል (ገጽ 38 ይመልከቱ)፡፡ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው አቡነ ሕዝቅኤል ግን ውሳኔው ከተላለፈ ወዲህ እንኳ ስሕተቱን አምኖ በተከፈተለት የይቅርታ በር ከመጠቀም ይልቅ በጓሮ በር በሽምግልና ጭምር ሲያስቸግር የሰነበተው የአሸናፊ መኰንን ስም እጅ ጽሑፉ ብቻ ሳይኾን በታይፕም ተጽፎ (ገጽ 39 ይመልከቱ) በሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዳግመኛ እንዲፈረምበት በማድረግ ያከሸፉትን ቅሠጣ ለታሪክ እንዲተላለፍ አድርገዋል፡፡ በተ.ቁ (7) ላይ ስብሐት ለአብ በሚል በአባቱ ስም ብቻ የተገለጸው ቀንደኛው መናፍቅና የ”ማኅበረ በኵር” መሥራች መሠረት ስብሐት ለአብ ስምስ በምን ተንኰል በዚህ መልኩ እንደታለፈ አያጠያይቅም ለማለት አይቻልም፡፡

ይህ የከሸፈ የእነአሸናፊ ሸፋጮች ሙከራ ግን የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄው ትግል ቀጣይ የተጋድሎ ዐውድማ በሚኾነው በቤተ ክህነቱ ቢሮክራሲ ውስጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በግልጽ የሚያመለክት እንደኾነ የጉዳዩ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ቤተ ክህነቱን ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቅጥረኞች እና የእነርሱ መተላለፊያ ወደብ (harbor) ከኾኑት ሙሰኞችና ዘረኞች ለማጽዳት በይቀጥላል የሚደረገው ቢሮክራሲያዊ ትግል እስከአሁን ከተካሄደው የበለጠ ውስብስብ እንደሚኾን ከታሪካዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ደማቅ ውሳኔዎች ማግስት አባ ጳውሎስ እንደ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ካሉ አጋፋሪዎቻቸው ጋራ በእልክና በበቀል ጥማት የሚያሳዩት መወራጨት ምስክር ነው - የመጨረሻው ምሽግ መላላጥ (the last ditch effort) ይኾን?

ግሪኮች “ከዐዩ የወገን ድል በፊት ጠላት የሚያውጃቸው ትንንሽ ድሎች አሉ” ይላሉ፡፡ አባ ጳውሎስና እነኀይለ ጊዮርጊስ መንግሥትን ጭምር ሊያጨበረብሩበት የተዘጋጁበትና ከፈተናው በፊት ቀረር የሚያሰሙበት ሰሞናዊው “ጉባኤያቸው” የት ያደርሳቸው ይኾን? ብዙ እየተናገሩ ነው፤ እርስበስ ለማናተፍ ይረዳናል፤ ያሸማቅቅልናል ያሏቸውንና ከምናባቸው በቀር በዕውን የሌለ የጭቃ ጅራፋቸውንም በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎቻቸው እያጮኹ ነው፡፡ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ግልጽ ሊኾንላቸው የሚገባው ግን ብፁዕ አቡነ አብርሃም ትናንት፣ ሰኔ 8 ቀን 2004 ዓ.ም እንደተናገሩት “በሽተኛ እና ጤነኛ በአንድ ቤት ማደር እንደማይችል” ነው፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰባቱ መናፍቅ ድርጅቶች እና 16 ግለሰቦች ላይ ስላሳለፈው የውግዘት ውሳኔ÷ ትናንት፣ ሰኔ 8 ቀን 2004 ዓ.ም በሐረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በተጠራው የሀ/ስብከቱና የስድስት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያን ጥምረት አባላት በተገኙበት ጉባኤ ላይ “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ የግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ልበሱ” (ኤፌ.6÷11) በሚል ርእስ ትምህርት ሰጥተዋል፤ በውሳኔው አተገባበር ላይም አባታዊ ሪያና ምክር አስተላልፈዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተሐድሶ ጭፍሮች ዝናራቸውን ጨርሰው የቅዱሳኑንና የትጉሃን አገልጋዮቹን ስም ወደ ማጥፋት መዝቀጣቸውን ተናግረዋል፡፡ “ድርጅቶቹንና ግለሰቦቹን ያወገዝናቸው በሰውነታቸው ስለጠላናቸው ሳይኾን በሃይማኖት ስለ ካዱ ነው” ያሉት ብፁዕነታቸው ሰውን ለማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖታዊ ክሕደቱ እንዳልኾነ አስረድተዋል፡፡

በመኾኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በውሳኔው “የኑፋቄ ትምህርት አስተላላፊዎች እና ፀረ - ኦርቶዶክስ አቋም ያላቸው መናፍቃን” ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በተወገዙበት ማግስት ለውሳኔው መሠረት የኾኑ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ በማቅረብ እልክ አስጨራሽ ተጋድሎ ያደረጉትን በሙሉ÷ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳንን÷ ለማዳከም ከተሳካላቸውም ለማፈራረስ፣ ውሳኔው በተገቢው መንገድ ተጠንቶና ተመርምሮ ታላቅ ፍጻሜ ላይ የደረሰበትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን የአባ ጳውሎስን ሥልጣን በሚያጠናክር አኳኋን ለመለወጥና የቅዱስ ሲኖዶሱን ሥልጣን ለመፃረር፣ ከመወሰን እስከ ማስፈጸም ድረስ በየደረጃው ሓላፊነት የተጣለባቸውን ብፁዓን አባቶች፣ የሥራ ሓላፊዎች፣ ካህናት፣ መምህራንና ሰባክያነ ወንጌል ለመድፈቅ እየተራወጠ የሚገኘውን ስብስብ (የዐመፅ ቡድን) ተግዳሮቱ በሚጠይቀው መጠን በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ገጥሞ ለማስወገድ አንድነታችንን እንድናጠነክር ደጀ ሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

የክህነትና የክብር ማዕርጋቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
በሰማይና በምድር የተወገዙት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ዝርዝር
የሚከተለው ነው፤
ሰባቱ ድርጅቶች፡-
1. ከሣቴ ብርሃን
2. ማኅበረ ሰላማ
3. የምሥራች አገልግሎት
4. የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር
5. አንቀጸ ብርሃን (ከድርጅቱ ጋራ አሸናፊ መኰንንና ዳንኤል ተሾመ)*
6. የእውነት ቃል አገልግሎት
7. ማኅበር በኵር
8. የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት/ኢመተኅ/ - (ተጨማሪ ማጣራት የሚደረግበት)

16ቱ ግለሰቦች፡-
1. ‹አባ› ወልደ ትንሣኤ አስገዶም
2. አቶ መስፍን
3. አጥናፉ መኰንን
4. ዳንኤል ተሾመ
5. ግርማ በቀለ
6. ሥዩም ያሚ
7. መሠረት ስብሐት ለአብ
8. ሰሎሞን መኰንን
9. ጽጌ ስጦታው
10. ደረጀ ገዙ
11. በዛ ሰፈርህ
12. አግዛቸው ተፈራ (አሁን የጮራ መጽሔት አዘጋጅ)*
13. ተስፋ ተገኝ
14. ብሥራት ጌታቸው
15. መ/ር ተስፋ ዓለም
16. አሸናፊ መኰንን

ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ጽሑፍ “ትምህርተ ውግዘት” በሚል ርእስ ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ ከጻፉት የተወሰደ ነው፡፡ ስለ ውግዘት አጠቃላይ ግንዛቤ በሚሰጥ መልኩ እንደሚከተለው በአጭሩ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
 ቸር ወሬ ያሰማን!!!!! አሜን
ውግዘት ምንድን ነው?
ማውገዝ በዘይቤ፣ በአገባብ ይኹን በምስጢር ብዙ ፍችዎች አሉት፡፡ ማውገዝ መለየት፣ መካድ፣ መርገም፣ መፍረድ፣ ማሰር፣ መወሰንና ሥርዐት መሥራት ማለት ነው፡፡ ኢአማንያንን፣ መናፍቃንንና ክፉዎችን ከምእመናን፣ ከቤተ ክርስቲያን፣ ከጉባኤ እግዚአብሔር እና ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ማለትም ከቅዱስ ቍርባንና ከመሳሰለው ሁሉ የሚለይ መንፈሳዊ መቍረጫ ውግዘት ነው፤ “የሚያውኳችኹ ይቆረጡ” እንዲል (ገላ.5÷11)፡፡

ውግዘት መንፈሳዊ ሰይፍ ነውና ኢአማንያንን ከአማንያን ይለያቸዋል፡፡ ማውገዝ ሰይጣንን በሃይማኖትና በሥራ መካድ ነው፡፡ “ዘይፈቅድ ይጠመቅ ይምሀርዎ ያውግዝ ሰይጣነ ወይእመን በክርስቶስ - ሊጠመቅ የፈቀደውን ሰው ሰይጣንን እንዲክድና በክርስቶስ እንዲያምን ያስተምሩት፤” እንዲል (ዲድስቅልያ 34) ፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ልዩ ልዩ የክሕደት ትምህርት አንቅተው ያስተማሩ መናፍቃን ላይ የቤተ ክርስቲያን ርምጃ “ታወግዞሙ፤ ወትረግሞሙ፤ ትፈልጦሙ፤ ወትመትሮሙ” በሚሉ ኀይለ ቃላት በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ላይ ተገልጾ እናገኛዋለን፤ ፍቺውም ቤተ ክርስቲያን ታወግዛቸዋለች፤ ትረግማቸዋለች፤ ቆርጣ ትለያቸዋለች ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ማውገዝ መርገም ነው፤ መወገዝ መረገም ነው፡፡

ማውገዝ መፍረድ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም እስከ ኅልፈተ ዓለም ድረስ የሚሠራ እንጂ በእነርሱ ብቻ ተወስኖ የቀረ አይደለም፡፡ “እውነት እላችኋለኹ፤ እናንተስ የተከተላችኹኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችኹ፤” ብሏቸዋል፡፡ (ማቴ.19÷28) ስለዚህ ሐዋርያት በምድር የፈረዱት ፍርድ በሰማይ አይገሠሥባቸውም፤ ማለትም በሥልጣነ ክህነታቸው በምድር ላይ የሠሩት ማንኛውም ዐይነት ሥራ፣ ውሳኔና ፍርድ በዳግም ምጽአት ይጸናል ማለት ነው፡፡ ይህም “በምድር ያሰራችኹት በሰማይ የታሰረ ይኾናል፤ በምድር የፈታችኹት በሰማይ የተፈታ ይኾናል፤” (ማቴ. 16÷19) በማለት ፈጣሪ ከሰጣቸው የማሰርና የመፍታት (የማውገዝ) ቃል ኪዳን ጋራ የሚዛመድ ነው፡፡

ማውገዝ መወሰን፣ ማሰር፣ ሥርዐት መሥራት ነው፡፡ የተሳሳተ እምነትንና ትምህርትን ይህ ሐሰት ነው ብሎ “ማሰር”ይህ ደግሞ እውነት ብሎ “መፍታት” የማውገዝ ሥልጣንን የሚያሳይ ነው፡፡ ሰይጣንንና ሠራዊቱን ኀይል ማሳጣትና ማሰርም የማውገዝን ሥልጣን ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ማውገዝ አጥፊውን ሰው በሥጋውና በነፍሱ ማሰር፣ መንፈሱን መግታት፣ ትምህርቱንና መጻሕፍቱን መከልከል ነው፡፡ እንዲህ ባለ ክፉ ሰው ላይ አድሮ የሚሠራውንም ርኵስ መንፈስ መቃወምና ማድከም፣ ሐሳቡና ዕቅዱ፣ የሰውዬውም ጠማማ እምነት ፍሬ ቢስ እንዲኾን ማድረግ ነው፡፡ ሰውዬው ቢሞት እንኳ ያደረበት መንፈስ የሚሞት አይደለምና የዘራው ክፉ ዘር እንዳያፈራ ማገድ የውግዘት ዓላማ ነው፡፡ ሰው ይኹን ተቋም እምነቱ፣ ድርጊቱ ተመርምሮ ሲደረስበት ክፉ ኾኖ ከተገኘ÷ ከሞተ በኋላም እንደ ግለሰብ ይኹን እንደ ሥርዐት (ተቋም) ሊወገዝ ይችላል፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ አርጌንስ ከሞተ ከ294 ዓመታት በኋላ ከነመጻሕፍቱ ባልተወገዘ ነበር፡፡ (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፤ ገጽ 86)

ውግዘትን የሚያስከትለው እምነትና ተግባር
አንድ ሰው በውግዘት የሚለየው በህልውና እግዚአብሔር ያላመነ ሲኾን ብቻ አይደለም፡፡ በገዛ ፈቃዱ ሥርዐትን ያፈረሰ ሰው በውግዘት ሊለይ ይችላል፡፡ አለመታዘዝ ያስወግዛል፤ “ወእመ ኢተአዘዘ ይትወገዝ መኑሂ በሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ የማይታዘዝ ማንም ቢኾን በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ይወገዛል” (ተግሣጽ ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ቁጥር 4)፡፡ ሥርዐት የማያከብር ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ሐዋርያት በመልእክታቸው ጽፈዋል፡፡ ቃሉም “ወንድሞች ሆይ÷ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይኾን ያለሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን፤” የሚል ነው፡፡

ሰው በምግባር ሕጸጽ ይኹን በሃይማኖት ክሕደት ሊወገዝ ይችላል፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ መማለጃ የሚቀበሉትንና ዕቍባት ያሏቸውን ሰዎች ዕቍባቶቻቸውን እንዲተዉ፣ ክፉ ልምዳቸውን ያርቅ ዘንድ ገዝቷል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ንግሥት አውዶክስያን ደኃን ስለበደለች ስለ ክፉ ምግባሯ ገዝቷታል፡፡ (ስንክ ዘታኅ 6፤ ድርሳነ ዮሐንስ የታሪክ ዓምድ)፡፡ ይኹን እንጂ ቶሎ ርምጃ የሚወሰደው ጥፋቱ የሃይማኖት ኾኖ ሲገኝ ነው፡፡ ስለዚህም ጌታችንና ቅዱሳን ሐዋርያት ካስተማሩን ውጭ “ልዩ ትምህርት” የሚያመጣ ሁሉ የተወገዘ ነው፡፡ ከቀድሞው ሌላ መሠረት መሥርቷልና፤ በአበው ትምህርት፣ ወግና ምሳሌነት የማይሄድ ሥርዐት አፍራሽ ነውና፡፡ (2ተሰ.3÷6)፡፡

“ጌታችንን የማይወደው” ሁሉ የተወገዘ ነው፡፡ “ጌታችንን የማይወደው” ማለት ምግባር ያጎደለ ማለት ነው፡፡ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ.19÷15) ስለተባለ ያልወደደ አይታዘዝምና ምግባር ሊኖረው አይችልም፡፡ የሰው አስተሳሰቡም ኾነ ሥራው ውስብስብና እንደጊዜው የሚለዋወጥ ረቂቅ ነው፡፡ ስለሆነም የሚያስወግዙ ክፉ ተግባራትን ሁሉ በተናጠል በመዘርዘር ወስኖ ማስቀመጥ አይቻልም፤ ነገር ግን በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ከተዘረዘሩት

የማውገዝ ሥልጣን
ማውገዝ ለእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ “ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትኹን” (ዘፍጥ.3÷17)፤ “ብንክደው እርሱ ደግሞ ይክደናል” (2ጢሞ.2÷13)፤ “በሰው ፊት የሚክደኝን እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለኹ” (ማቴ.10÷33)፡፡ ስለኾነም ሥርዐተ ውግዘትን የሠራ፣ የወሰነ፣ ያሰረ፣ የታሰረውንም የሚፈታ፣ የሚዘጋ፣ የሚከፍት እግዚአብሔር ነው፡፡ (ራእ.3÷7፤ 5÷9)፡፡

ለእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ የኾነው እግዚአብሔር በገንዘቡ የወደደውን ለማድረግ ሥልጣን አለውና በቸርነቱ ይህን ሥልጣን ለአባቶቻችን ካህናት በጸጋ ሰጥቷቸዋል፡፡ (ማቴ.20÷15) “በዘአእመረ መንፈስ ቅዱስ” እንዲሉ “እርሱ መንፈስ ቅዱስ ባወቀው” ይህን ታላቅ ሥልጣን ለካህናት የሰጣቸው ሕገ ወጥ የኾኑ ሰዎችን ሕገ ወጥ የኾኑ ሰዎች ምእመናንን እንዳያናውጧቸው ለምእመናን ድኅነትና ዕረፍት አስቦ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የሚያስሩበትንና የሚፈቱበትን ሥልጣነ ክህነት የተቀበሉት ጌታችን እፍ ብሎባቸው “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ይቀርላቸዋል፤ የያዝችኹባቸው ተይዞባቸዋል፤” (ዮሐ.20÷22) ባላቸው ጊዜ ነው፡፡

ይህ የክህነት ሥልጣን በሐዋርያት ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ በእግረ ሐዋርያት እየተተኩ፣ የእነርሱን አሰረ ፍኖት ተከትለው እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ ለሚነሡና ብቁ ኾነው ለሚገኙ ሁሉ ይህ የሥልጣነ ክህነት ቃል ኪዳን ተነግሯል፡፡ ይህም “እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ” (ማቴ.28÷20) በማለት በተናገረው ቃል ታውቋል፡፡ ሌላውም ምንጭ “ከመለኰትህ ገናንነት ምስጢር ለደቀ መዛሙርትህ እንዳልሰወርኽ እነርሱም ከእኛ የሰወሩት የለም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ሊቀ ጳጳስ፣ ኤጲስ ቆጶስ፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት አድርገው ሾሙን እንጂ” በማለት ለቅዱሳን ሐዋርያት የተሰጣቸው የክህነት ሥልጣን ለሐዋርያውያን አበውና ለሊቃውንት መተላለፉን ያስረዳል፡፡ (ቅዳሴ አትናቴዎስ ቁ.1)፡፡

ከአሕዛብ ይልቅ መናፍቃንን፣ ከመናፍቃን ይልቅ ደግሞ የተወገዙ ሰዎችን መጠንቀቅ ይገባል
በአግባቡ ለተወገዙ ሰዎች ያለአግባብ መቆርቆር የአጋንንት ወዳጅ ከመኾን አይዘልም፤ በእግዚአብሔር ሥራ የማይደሰቱ፣ ሰይጣንና ግብረ አበሮቹን የማያወግዙ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ ናቸውና፡፡ በሃይማኖትና በምግባር ከተወገዙ ሰዎች መራቅ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበለው ወግ ሳይኾን ያለሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን” በማለት በግልጽ ተናግሯል፡፡ (2ተሰ.3÷6)፡፡ ይህ ቃል ቁርጥ ትእዛዝ እንጂ ምክር አይደለም፤ “እናዛችኋለን” ይላልና፡፡ ከትእዛዝም ጥብቅ ትእዛዝ መኾኑን ደግሞ “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም” የሚለው ሐረግ ምስክር ነው፡፡ ይህ የሐዋርያው የብቻው ትእዛዝ ሳይኾን በዘመኑና ከእርሱ በኋላ የሚነሡ ቅዱሳን አበው ሁሉ ትእዛዝ ነው፡፡ “እናዛችኋለን” ይላል እንጂ “አዛችኋለኹ” አይልምና፡፡

ምግባር እና ሃይማኖታቸው ከከፋ ከኀጥአን፣ ከቀራጮችና ከአረመኔዎች ጋራ እንዳንተባበር መጽሐፍ ቅዱስ አስጠንቅቆናል፡፡ 1ቆሮ.5÷9፤ 15÷33፤ 2ዮሐ. ቁ.10 እና 11፤ 2ቆሮ.6÷14-16፡፡ ከክፉ ሥራችን አንመለስም ብለው በውግዘት የተለዩ ሰዎች ደግሞ ምድባቸው ከአሕዛብ፣ ከአረማውያን፣ ከኀጢአተኞች፣ ከዐመፀኞችና ከመናፍቃን ጋራ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችን “ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት እንደ አረመኔ እንደ ቀራጭ ይኹንልህ” የሚለው እንደእነዚህ ያሉትን ነውና፡፡ (ማቴ.8÷17) ፡፡ ሥራቸውና ክፋታቸው በግልጽ ከሚታወቅ ከአሕዛብና መመለክያነ ጣዖታት ይልቅ መጠንቀቅና አለመተባበር የሚገባው መናፍቃንን ነው፡፡ ከመናፍቃን በላይ ደግሞ ከተወገዙ ሰዎች መጠንቀቅ ይገባል፤ ምክንያቱም ከአሕዛብ ይልቅ መናፍቃን፣ ከመናፍቃን ይልቅ ደግሞ የተወገዙ ሰዎች ተመሳስሎ የመኖር ሰፊ ዕድል ስላላቸው ነው፡፡ ተመሳስለው ከኖሩ ደግሞ ሌሎችን በቀላሉ ወደራሳቸው የጥፋት ጎዳና ይስባሉ፡፡

ምንጭ፡- ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ፤ ትምህርተ ውግዘት፤ 1999 ዓ.ም


23 comments:

Anonymous said...

ቸር ወሬ ያሰማን!!!! ቸር ወሬ ሰማን!!!!!!!!!ለዛሬ "ያ" ይነሳልን::
እልልልል ግልግል ነው እንበል ወይንስ እንደ አቤ ቶክቻው አሸወይና/ጣመን ደገመን /እንበል ገና ነዋ ግማቱ ካናቱ ከፖፖው አይደል:: ጃማይካው ወንድሜ ያ ማን !!! አለኝ ደስ ብሎት እኮ ነው::
እኔም አለ ገና አለ ገና ብያለሁ::
ቸር ወሬ ሰማን!!!!!!!

Ewunet tenagari said...

Memihir Yeshitila, can you please tell us what 'metades'/'tehadiso' means according to the 'mezigebe qalat' you referred to explain the word 'mawugez'/'mewegez'? What if those 'wuguzan' come under the name' 'miruqan' and try to continue their covert heretic teachings? Are we going to say to the laity, 'watch out for those 'miruqan'? Or ‘wuguzan’? MK is doing a good job in following and exposing those heretics, but the stubbornness of some of its leaders and members is creating confusion for us. In matters of faith if anything got wrong, it should either be corrected or repented. It cannot be let continue as it is if proved to be wrong. The use of the word 'tehadiso' to refer to 'menafikan' is deadly wrong terminology and need to be corrected. Because our Church will inevitably undertake tehadiso as the Coptic Church has done so. Not its dogma, basic canon and teachings, but overall approaches and reach out strategies to disseminating the teachings of the Church to others and to descendants of Ethiopians scattered all over the globe. I am a fierce anti heretic son of Tewahedo; thus, I do not want to see those 'kelebat' be called with a name they do not deserve.

Anonymous said...

aba welidetinisay man nachew yetewegezut yet new yeminorut?

Anonymous said...

እነዚ ሰዎች በጥፋታቸው መውገዛቸው ኤግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስ የሚል ዜና ነው ነገር ግን ከዚ ቀደም የተውገዙ ጳጳሳት አሉ የነዝ ስዎች ውግዘታቸው ሳይነሳ እርቅ እየትባለ ይገኛል አናንተም አቡነ ጳውሎስ እምቢ አሉ ብላችሁ ትስፋቺሁል ታድያ የነዝ ውግዘት ከቀደሙት በምን ይለያል ይሄ ነገር እንዲታሰብበት ለማለት ነው ወስብሐት ለእግዚአብሔር::

Moges Dessale said...

It is very impressive and informative piece of writing.

Anonymous said...

እልልልልልልልልልልል ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክ አበዊነ! ይሄ ማለት ዲያብሎስ አርፎ ይተኛል ማለት ስላልሆነ ቀጣይ ቀሳጮችን ተከታትሎ ለሲኖዶስ የማቅረብ ስራችሁን ይበልጥ አጠንክሩ፣ለዚህም አምላከ ናቡቴ ይርዳችሁ!!!!

Anonymous said...

እልልልልልልልልልል ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክ አበዊነ!!!

ይህ ማለት ግን ዲያብሎስ አርፎ ይተኛል ማለት ስላልሆነ ቀጣይ ቀሳጮችን ተከታትሎ ለሲኖዶስ ማቀረብን በርቱ ለዚህም አምላከ ናቡቴ ይርዳችሁ!!!

Anonymous said...

ENDE ene Begashaw,,miretnesh Aba Serke ... yetalu yetwegezut enante minew selenesum setaweru alenberachehum ende ?? mels felgalhu wegen

Anonymous said...

It will be continue. Thanks the Almight God and His mother.

Anonymous said...

እነ በጋሻው እና "አባ" ሰረቀ "በአባ ሰላማ"ውግዘት ውስጥ ይጠቃለላሉ

lele said...

TAMASEGANE..........
yaortodox lejoche adara tsome tsaloto enedayekorate.

galela said...

YAMAYASAFERE AMELAKE ALANE
gena enezameralane/2/
eneda maleketo berehanen labesane
gena enezameralane
esekaza yatanekerane

lelr said...

elelelelelelelelelelele
elelelelelelelelelelele
elelelelelelelelelelele

Anonymous said...

"Ewnet Tenagari"

You have given yourself the job of "savior" of "tehadiso" without knowing it, or purposefully and with knowledge! You must know by know that you are fighting our Tewahedo Church while you still claim to be a "a fiece anti-heretic son" of Our Tewahedo Church. But your continued advocacy of "saving" the word "tehadiso" to mean what it doesn't mean according to the teachings of the EOTC, puts you outside the teachings of Our Church, to say it mildly!

Indeed the same has been claimed by all those condemned and yet to be condemned and excommunicated from Our EOTC. But the facts are different!

Here you ask Dn. Yeshitila to "explain" to you the dictionay meaning of your theme "tehadiso". That indeed isso strange from someone like you who calls himself
"ewnet tenagari"!

You are trying to reduce our wstruggle to save Our Church from the subversion of "tehadis"-protestantism to a simple squabble over a dictionary definition?!

If there is any Tewahedo vestige left in your soul, we recommend that you stop preaching a doctrine which you defend , but are not even more qualified to "defend" than those on the above condemned list!

Those on the condemned list also pretended to be "sons" of The EOTC while at the same time "advancing" their "tehadiso-ism", with a level of protestant indoctrination and methodology which has caused great havoc in Our Church.

Are you more "qualified" than those on the condemned least to save "tehadiso"-protestantism in the name of "saving the word tehadiso" to "fit" your oown fantasy and imagination ?!

It is such self-elavation which has exposed the pretentions of "tehadiso"-protestants like Begashaw and Co. who tried to eliminate the name of EgziAbHier and Silassie from our liturgy and prayers. Such is the sinful hight of little knowledge!

It is advisable for you to stop your provocations and start to learn about Our Tewahedo faith without debating in matters of Church Dogma and Doctinal issues about which you are neither qualified nor, at least as of know, shoe the readiness to strat to learn quietly!

Your claim to be "anti-heretic son of Tewahedo" is not being validated by your continued "self-elevation" to "save" "tehadiso" which is condemned and rejected by Our Qidus Sinodos. Where do you find yourself in the face of this position of Our Qidus Sinodos?! To conclude Please don't drag the Coptic Church in matters concerning Our EOTC. It is neither necessary nor benefitial for the cause of advancing "tehadiso-ism" which is protestantism.

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

ብላቴናዋ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች እንደምን ከረማችሁ ደስየሚል ዜና ነው ያሰማችሁን ታዲያ ምነው የጀርመን ሀገሩን መናፍቅ ያቶገዳሙ ደምሳቨ ጉዳይ ከግብሮአበሮቹ ጋር ቢታይልን ሰውየው የዋዛደፋር እንዳይመስላችሁ በሀሰት ሰውንሰድቦኛል በማለት እስከ 5000 ኦይሮ ካሳ የጠየቀነው ለዚያውም የጀርመኑን አስተዳዳሪ ተብየ ቄስመራዊን እና የፍራንክፈርት ማርያም አስተዳዳሪ አባሲራክ \አባ ሀይለመለኮትን)ለመሰደቡ ምስክር እንደሚሆኑት ጠቅሶ እናም በግዜ ወደጉዋደኞቹ ብትቀላቅሉልን ለነጉማ የሀገረ ስብከቱ ፓፓስ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉበትሁኔታነው ያለው እናም እባከችሁ መፍትሄ ፈልጉልን የቤተክርስቲያን አምላክ ሰላሙን ያድለን አሜን

ጉዳይ

Ewunet tenagari said...

Samuelzeasebot, I think you need to take some philosophy courses/lessons to understand this issue of assigning a name to something or somebody. You can call anything by any name as long as there is consent by a given society that uses that specific language. And that something is identified by a name assigned to be called. If heretics had been called Samuelzeasebot, they would have been known by it and we would now call them Smuelzeasebot or the heretic; but this name now is used as a pen name by you my brother who blindly deny and is so stubborn to accept that you are wrong. According to our Church teachings and fathers, those people who teach different and new meanings of the Apostles’ teachings about Jesus Christ, those who oppose the grace of intercession of the Holy Virgin Mary and the Saints and the Angles are called Menafikan. Our Church has been undergoing Tehadiso for centuries to get where it is now, and it needs to undertake Tehadiso now and in the future. Since Tehadiso means something positive to advance the journey of Christianity, it has always been there. Besides administrative reforms needed for efficient and advanced services, which I mentioned in my previous comments, for instance, the order of ordination, the requirements to become a priest or a deacon has been reformed formally and informally. That is how so many of our ‘grown up friends’ have become deacons and priests and even bishops. The order of holy marriage /matrimony has been reformed at least as it is carried out nowadays, the observance of holydays and the Sabbath, establishment of Churches, and so on all have undergone reformation formally or informally. You people out there, particularly MK blind followers, adhere only to what MK says even if it is deadly wrong as it is the case in this issue of the use of the word Tehadiso. The undercover heretics in our Church at this time of lawlessness and failed leadership of the church are caring out the same heretic duty of their forefathers who attempted to divide the church, but to no avail. What is going on in our church is heresy, not Tehadiso. They come under the word which is acceptable by the Church and the laity as they used to come saying WENGELAWEAN, EYESUSAWEAN,Etc but our Church always called them-Menafikan since wengelawean are its theologians, priests and all other members of the clergy. Since when did we start using this terminology and why? In my view, it is first used by the heretics themselves to create confusion among true followers of the church. But, sadly, MK is also trapped in their intrigue and now blindly defends its wrong association of the good word Tehadiso to menafikan. Finally, I would say to you my brother- Lemetades yabikah!

Anonymous said...

"ewnet tenagari"

Your claim to be "anti-heretic son of Tewahedo" is not being validated by your continued "self-elevation" to "save" "tehadiso" which is condemned and rejected by Our Qidus Sinodos. Where do you find yourself in the face of this position of Our Qidus Sinodos?!

You are now coming out slowly, but surey to deliver a picture of your true self through your unwaranted, and as ever the typical slander of "tehadiso"-protestants against Mahibere Qidusan!

Isnb't that the same jective of the "gubie ardiete" that the "tehadiso" protestants are now hatching?! What will be your destiny in this emerging constilation?!

As you keep on with your assault, and the camouflage receds to the background, we are destined to discover the true features of of a "tehadiso" protestant!

Anonymous said...

Lots of debate

Ewunt tenagari said...

You guys think you are the only children of the Church and the rest of us are alien. You are laughing creatures. This is hypocritical! Our Church matters are also our concerns, not just a bunch of ignorant self acclaimed pseudo 'kidusan'. You pretend as if you stand for the Church only when your advantages are at risk. Yes, we equally have rights to forward our opinion and correct erroneous terminologies and approaches of MK. The holy Synod excommunicated heretics, not Tehadiso. It will undertake tehadiso when it deems necessary to do so regarding various areas of the Church. Our Church is not a back ward institution as your think. It has passed through ups and downs thanks to our brilliant, farsighted, righteous fathers. What is now a big deal to you, confusion creators, had been there since the time of The Apostles. You lost the argument and you are WRONG!

Anonymous said...

"ewnet Tenagari"
Yor postion as a ptotagonist of protstantism is becoming ever more clearer.

Your obstinate indulgence in not only to give a definitional cover for the protestant subversion. You are openly campaigning not only against your most hated target, Mahibere Qidusan, but also against Qidus Sinodos of the EOTC through your claim of knowing better than Our Church Fathers!

Others have peddled the your ideas
and failed. Some have now been condemned by Our Qidus Sinodos; and others will follow soon! We are determined to free ourselves from protestant subversion.

There is no doubt it is such elements like you who are now being recruited into the so called "gubaie ardiete" to hijack and "destroy" the EOTC. THIS WILL NEVER HAPPEN!

Definitely, you are here in the wrong company. No true son and daughter of Our Tewahedo Church will fall into your sugary traps
of the snake.

It must be more than obvious to you by now, that we have rejected your "preachings" which are alien to Our Tewhedo Doctrine and Tewfit. You have claimed for yourself unabashedly the "position" of "teacher" against the teachings of Our Tewahedo Church.

Your views are very close to those of abba paulos,abba gerima and abba fanuel.It is because of them that you are openly waging such an open "tehadiso"-protestant war against Our Tewahedo Faith and Church under the cover of claiming to be an "anti-heretic son of Tewahedo". Others had also worn that garb until they were exposed and thrown out of Our Church.

You are outside the teachings of Our Tewahedo Fathers. And you adamntly want to bring us the worn-out schismatic "teachings" of Luther and his legewon.

However "sweet" you are trying
to make it sound, Tehadiso-ism
is condemned to failure and has
no place in Tewahedo-Ethiopia!

All your efforts will fail under the Mighty Hand of Medhanie Alem Kristos and Dingil Mariam!

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

@Ewunet tenagari

There is a saying "Do not argue with an idiot. He will drag you down to his level and beat you with experience." These people are one of the most narrow minded people, with a category of their own. It’s a pity to know these are the people that represent our church.

Anonymous said...

"ewnet tenagari"
You are now bruised and exposed. What remains of your "all knowing"
bravado is indulgence in slander
and name callings!
"በመከራዬ፡ደስ፡የሚላቸው፡ይፈሩ፥
በአንድነትም፡ይጎስቁሉ፤
በእኔ፡ላይ፡የሚታበዩ፡እፍረትንና፡ጉስቁ
ልናን፡ይልበሱ።
ጽድቄን፡የሚወድዷት፡ደስ፡ይበላቸው፡ሐ
ሴትንም፡ያድርጉ፤"
መዝሙር፡ 34 ከቁ.26-27
Medhanie Alem Kristos will not let Tewahedo-Ethiopia down. Those whos curse against us and attack us will in the end harvest the bitter fruits of their unworthy campaigns!

It must be more than obvious to you by now,that alien"preachings" have no place amongst the true sons and daughters of our Tewahedo Church!

Your views are very close to those of abba paulos,abba gerima and abba fanuel.It is because of them that you are openly waging such an open "tehadiso"-protestant war against Our Tewahedo Faith and Church under the cover of claiming to be an "anti-heretic son of Tewahedo". Others had also worn that garb until they were exposed and thrown out of Our Church.

Your "tehadiso"-protestant cover has now been totally exposed and your are now in your phase of spewing slander. We are neither surprised nor shocked by this, your metamorphosis.

You will be neither the first not the last in this hideous campaign against The EOTC. There is no doubt that you appeared here to dessiminate the poisonous views of your like minds at "aba selama".

You came "tall and pompous"; but now you are shrunk to your own real size! You are battered by the Mighty Hand of Medhanie Alem Kristos and Dingil Mariam!

It is time for you now to declare your evil mission dead. The tewahedo firewall has not permitted you to move an inch. We fought against your false "teachings" on our territory not on yours. You came to infuse us with the sugar-coated poison of "tehadiso"-protestantism.

ተዋሕዶን፡ለመገሰጽ፡ቃጥቶህ፡እንደ፡"አንበስ"እያ
ገሳህ"መሃከላችን፡ዘልቀህ፡የተናገርከው፡ሁሉ፡ለተዋ
ሕዶ"ልጆች፡ከፍተኛ፡ነቀት፡እንዳለህ፡ተገነዘብን፡
"ላስተምራችሁ"እንጂ፡ከተዋሕዶ፡አልማርም፡ብለ
ህ፡አመፅህን፡አወጅህ።አሁን፡ግን፡አልቆልሃልና፡ስ
ድብህን፡አስከተልክ።

አውሬውስ፡በመጨረሻ፡"የስድብ፡አፍ፡"እንደሚሰ
ጠው፡መጽሐፍ፡ያስተምረን፡ስለ፡ቅድስት፡ሃይማኖ
ታችን፡መስክረናል፤ወደፊትም፡እንመሰክራለን።አ
ባቶቻችን፡የጣሉልንን፡ድንበር፡አናስገፋም፤አናስደ
ፍርም፡ብለን፡ተቋቋመንሃል፤ሰብእናህን፡አልነካን
ም፤ሐሰተኛውን፡ትምህርትህን፡ግን፡ታግለናል፡፡

The rejection and exposure of your alien " teaching" is now beyond repair! It is time for you to declare your mission dead and call the quits!
እኛ፡እንደ፡ቀደሙት፡አባቶቻችን፡ወደ፡ንስሐ፡እን
ጠራልን፡እንጂ፡እንደ፡አሮጌ፡ዕቃ፡በመድኃኔ፡ዓለም፡
ክርስቶስ፡ስም፡የተጠመቀን"ታደስ"አንልም።ይህ፡
የሚስዮኖች፡የተሳሳተ፡ትምህርት፡ነው!

በተዋሕዶ፡እምነታችን፣ትምህርታችንና፡ትውፊታ
ችን፡የእግዚአብሔር፡ጥሪ፡ነስሐ፡በመግባት፡ወደ፡እ
ርሱ፡እንድንመለስ፡እንደሆነ፡እናምናለን!!!

"የትዕቢት፡እግር፡አይምጣብኝ፥
የኃጢአተኞችም፡እጅ፡አያውከኝ።
ዓምፃን፡የሚያደርጉ፡ሁሉ፡ከዚያ፡ወደቁ፤
ወድቀዋል፥መቆምም፡አይችሉም።"
መዝሙር፡35 ከቁጥር 11-12

ትዕቢት፡ዓመፃ፡ከእኛ፡ይራቁ

ድንግል፡ማርያም፡ትዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ጠብቂ!

እግዚአብሔር፡ለንስሐ፡ያብቃን።አሜን።


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

Ashu wenetetagn ayegeta agelegay new ke'ennet ga min guday alew esu eko getawen megelet becha new seraw bekerana sedet endehone amlakum tekbelotal bech besemayawi sefera gen esu keber alew yenate seyami ke'derejetawi neger ayalefem . Ashuye tsegawen yabesaleh begeta yebereta hun.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)