June 2, 2012

ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።


በአሜሪካን አገር “ዋይት ሐውስ ነው የምሠራው” በሚለው ማታለያው ከሲ.አይ.ኤ ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል የዋሆች በማስፈራራት እና “የኢህአዴግ አባል ነኝ” በሚል ብዙዎችን ለማሳቀቅ እና ከእምነታቸውና ከቤተ ክርስቲን አገልግሎታቸው እንዲንራተቱ ለማድረግ በመጣር ላይ የሚገኘው ይኸው ግለሰብ አያሌ ሊቃውንት ባሉባቸው አህጉረ ስብከት የበላያቸው ሆኖ እንደፈቀደው እንዲፏንን እንደተለቀቀ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ እጅግ ሊያስመሰግነው በሚችል መልኩ በተሐድሶ ድርጅቶች እና አራማጆች ላይ የውግዘት ቃሉን ባስተላለፈ ማግሥት ቅዱስነታቸው ቀንደኛውን ተሐድሶ በአሜሪካ የሾሙበት ምክንያት የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ቅስም ለመስበር እንዲሁም ወደ ውጪ አገር ሰው በመላክ ሰበብ የሚያጋብሱትን ገንዘብ በታማኛቸው አማካኝነት ለማካሔድ በማሰብ መሆኑን ምንጮች አብራርተዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ አቡነ ፋኑኤል የቀረቡት አቤቱታዎች በአጀንዳነት እንዳይያዙ፣ በመካከሉም በሚነሡበት ወቅት እልባት እንዳያገኙ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የከረሙት ፓትርያርኩ ይባስ ብለው ኃ/ጊዮርጊስን መላካቸው በሰሜን አሜሪካ የተጀመረውን ተቃውሞ የበለጠ ያጎላው ካልሆነ በስተቀር የሚፈይደው አንዳች ፋይዳ እንደማይኖር ይታወቃል።
ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ
በአሜሪካ ሦስት አህጉረ ስብከት ሲኖሩ የዋሺንግተን ዲሲው በዋና ፀሐፊው  በቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ የኒውዮርኩ በመ/ገነት ቆሞስ አባ ዘርዓ ዳዊት በርኼ፣ የካሊፎርኒያና አካባቢው ደግሞ በሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ ሥራ አስኪያጅነት ሲመራ ቆይቷል።

ር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡23 comments:

Anonymous said...

You know guys, I know this guy. He was my batch when we were at Addis Ababa University. Tsom enkuan Yemaytsom sew eko new...

well said...

እሱ አቶ ኃ/ ጊዮርጊስ በመጣበት እግሩ እንደሚመለስ አትጠራጠሩ እግዚአብሔር ሥራ ይሰራል ለመሆን የአባ መላኩ( አባ ፋኑኤልስ ጉዳይ እንዴት ሆነ? እሳቸው ተመልስው ወደ አሜሪካን የሚሄዱ ከሆነ የዚያን ጊዜ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በውጪ ያለችው ከፍተኛ ግጭት መከፋፈልና የማይገባ ተግባር ይፈጸማል የሚል አለ እና ለቋሚው ሲኖዶስ እንዲያስቡበት በጥብቅ ማሳሰብ ተገቢ ነው በጣም የማይሆን ጉዳይ ነው አባ ጳውሎስ እንደሆነ " እኔ ከሞትኮ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው እንስሳ ነው የሚያስቡት የተዋህዶ እምነት ባሕሏ በአጠቃልያይ ታሪኳ እንዲጠፋ ነው የሚፈልጉት ሲሆን መካሪ የላቸውም እንጂ በስታኢርጅና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ለጣሉት እጅግ መጥፎ ጠባሳ ንስሐ ገብተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ቢጠይቁ እግዚአብሔር ይቀበላቸዋል የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

galela said...

yaletadalo abate

lamelame europe said...

yamaderegoten ayawekom ena yeker balachawe

Talem said...

DS: Thank u for the report. Keep It up.
But you can be sure of one thing, he will not set foot in any church in the West America hagere sibket. Everyone knows who he is and there is no way he would even dare. Ofcourse, if the leaders (of some of the churches) are "in bed" with Aba Paulos, that might be something. but the members have to fight and chase his "arse" out of America.
May God bless our Church and the true servants.

Talem
West America

Anonymous said...

ደጀ ሰላምዊያን ዜናውን ስላቀረባችሁልን እናመሰግናለን
ፓትርያርኩ ከዚህም የባሰ ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይሉም
እኛ የሰንበት ተማሪዎች ግን ለሃይማኖታችን ህይወታችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል
አሁን የሚያነጋግረን ፖለቲካ አይደለም፣ዘርም አይደለም፣የጥቅም ጉዳይ አይደለም፣የበላይነት ወይም የበታችነት አይደለም የሃይማኖት ጉዳይ እንጂ

Anonymous said...

+++

ምዕመናን አጥቢያችሁን ከተሃድሶ ጠብቁ:: ጭቅላቱ መናፍቅ ቢሆንም መሰረቱን መጠበቅ እንችላለንና ተግተን እንጠብቅ::
ቅዱሳን አባቶች የተጋደሉላት ሃይማኖታችን መናፍቃን በግልጽ እያየን አይቀልዱባትም:: የሰንበት ት/ቤት አንድነት ና ማቅ አሜሪካ አስቡበት:: አደራ
እግዚአብሔር ይርዳን::

Anonymous said...

So what surprises you ? do not accept his authority and make him functionless . You are not like us (in Ethiopia) where you can be intemediated by the federal police or governement security agents loyal to the patriarch. You better die than sureendering to such kind of people.

Anonymous said...

Egziabeher meftihe alewu. Shih zemen yinoru mesluachewu "Patriyarku" bibetebitum sirachewu sayitalem yetefeta sayitegeber yetewegeze newu. Tewahido nitsigit natina be"Patriyariku" sira atimezenim.

EW said...

የምለው ስለሌለኝ ምን ልበል አይረቡም

Anonymous said...

+++
ቅዱሳን አባቶቻችን በተጋድሎ ያቆዩንን ንጽት የሆነች ተዋህዶ ሃይማኖታችን የመናፍቃን መፈንጫ አትሆንም:: በአጥቢያው ያላችሁ የቁርጥ ልጆች አደራ አለባችሁ::

ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

Patriarkun tewachewu essachew yealem abiyate kirstiyanat president nachew Silezih yemiyasasibachew orthodoxin betehadiso bemacheq kealem abiyatekristiyanat gar and madreg new. Bezi lay Yealem yehaymanotoch mikir bet president nachew. Bezih lay tinish tirit meyaz alebachew

Anonymous said...

Ere lenehe sewye leb yestacheu belen tselot enyzelachew beewenet almachew menem legbagen alchalem . O! amlake dawit tselotachinen seman amen.

Anonymous said...

ደጀሰላሞች ለምን በግለሰብ ላይ ታተኩራላችሁ? ስለምትሉት ሁላ በማስረጃ ልታረጋግጡልን ትችላላቹ?

Anonymous said...

Min Ayinetu Anony new Yihe Degmo. Kezih belay Endet bale Masreja Yokreb.

Anonymous said...

H/Giorgies, I know you will read this and you definitely understand it.
ዲቁናህን ጥለሀው ነበር፣
ባህር ዳር ጊዮን ማኅሌት ስታድር፣
አሁንስ ምን ሠርተህ ይሆን፣
ለወደቀው ዲቁናህ ተተካልህ ሊቀስዩማን∷

I will have a lot to say about you, as we know very well each other. Eske meche betekrstianin tasadidataleh???????

Anonymous said...

ለምን ጳጳስ አያደርጉትም? ለምን ጵጵስና ሰጥተው አንዱን ሀገረ ስብከት አይሰጡትም?!

Anonymous said...

I wonder if Dejeselamawian don't utter any word about Abebe Gellaw's appearance in Saint Gebriel church in seatle.I want to see ur reaction

mekonnen said...

Hi Dejeselam It is obvious that everybody know him as Tehadiso. So why call him Diakon?

Anonymous said...

ወይ አንተ ሌባ እንደው የሚያዘልቅህ ይመስልሃል? እግዚአብሄር ይበቀልሃል። የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች እንዳሏት እንዳትረሳ። እኔ የሚገርመኝ አንተም ሆንክ ሿሚዎችህ ለምን ቤተክርስቲያንን የሙጥኝ ብላችሁ እንደ መዥገር መመጥመጥ መረጣችሁ? አይነቃብንም ከሆነ ነቅተናል ስለዚህ እግዚአብሄርም እኛም አንተዋችሁም።

Anonymous said...

I said this so many times. I repeat again. Unless we act against this ungodly so cold patriarch, more and more of such decisions will come. if we just sit and accept because we can't question it. As you see the holly synod is either tied, ineffetive or down right bought. We can't just sit and wait for mena to fall of the sky.

All our brothers and sisters above say same thing. THE, I say THE, source of our problem is the Patriarch and his cronies.

If we foolishly and stubbornly defend, the hierarchy of the church, like Mahbere kidusan and others did, we are going down drain. I don't question good intention of organizations like mahbere kidusan or others who defend oneness and hierarchy of the church. They mean well. These are dedicated and faithful brother. But it is not the time. "LEHULUM GIZE ALEWU" says wise SOLOMON. However, blindly following the church hierarchy will only push more political, destructive and divisive decisions to our locals (Atbias). The solutions is temporarily resort to congregational church structure lead by guba'es elected by priests and lay people. We follow our church dogmas, but, will not allow greedy and politically motivated pope and his cronies funnel their decisions down to us. We should realize by now the so called fathers are out to fulfill their greedy and politically motivated wishes. Peace

Anonymous said...

ስለ ዋልድባ መዘገቡን አትርሱ እነዚህ ፔንጤዎቹ ለጥፋት የተመደቡ ስለሆነ ተዋቸው መጨረሻቸው የመጥፊያቸው ጊዜ አጭር ነው ይልቁንስ አንዳንድ ዳዎናት/አውተር/ ነን የሚሉ በዋልድባ ዙሪያ መርዶውን አርድተውን ጠፉሳ:: እናንተ ተግታችሁ ተከታተሉ አሁን የጎንደር ህዝብ የሞራልና የማቴርያል እርዳታ የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ ነው ዋልድባን አላስነካም ዓላስደፋርም ብሎ ከትግራይ ነፃአውጭ ጋር ትንንቅ ላይ ናቸው :: በመሆኑም የቤተክርስቲያናችን ታሪክ ናውና በዚያ ዙሪያ ዘገባ ያስፈልጋል::
ቸር ወሬ ያሰማችሁና እኛንም ቸር ወሬ አሰሙን

lamelame europe said...

pls deieselamoche YATALATACHENEH photo badanebe asayone,

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)