June 29, 2012

አጀንዳችን አንድ ነው - ሃይማኖታችን እና ቤተ ክርስቲያናችን ብቻ!!!!!!

To Read, Print & share, click HERE (PDF).
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 13/ 2011)፦  ላለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናሳስብ እንደቆየነው ቤተ ክርስቲያናችንን ከፊት ከኋላ፣ ከግራ ከቀኝ እና ከውስጥ ጠፍንገው የያዟት ችግሮች የበለጠ እየተገለጡ፣ ፈተና የሆኑባት ግለሰቦችም የበለጠ እየታወቁ፣ በሕዝቡ ዘንድ ይፈጥሩ የነበሩትም ብዥታና ግርታ የበለጠ እየጠራ በመምጣት ላይ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጪም ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት ቢሆንም ከውስጥ ተቀምጠው፣ እንጀራዋን እየበሉ ተረካዛቸውን የሚያነሱባት ግን ፋታ የሚሰጧት አልሆኑም። እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና የተሰጣቸውን አደራ አራካሾች ሳናሰልስ ተግባራቸውን በመቃወምና ለምእመኑም ለማሳወቅ በመጣር ላይ እንገኛለን። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች የተንጠለጠሉበት ካስማ ደግሞ ሁለት ነው። አንደኛው ሙስና፣ ሁለተኛው ኑፋቄ። ደጀ ሰላምም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሰፈነውን ሙስና ትቃወማለች፣ ሰርገው የገቡትን መናፍቃን እና የሚዘሩትን ኑፋቄ ትጸየፋለች። ምን ማለታችን እንደሆነ እናብራራው።

June 28, 2012

ርዕሰ አንቀጽ፡- የሀገሪቱን ሰላም ለማስከበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላም ማስከበር

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 2/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከትችውን አስተዋጽዖ መዘርዘር ለቀባሪው እንደማርዳት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ሕግና ሥርዓትን አውጥታ፤ ካህናትና ምዕመናን በአንድነትና በመከባበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓተ እምነት፤ ዶግማና ቀኖና እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ፤ በልማትና በማኅበራዊ ጉዳዮች በሕብረተሰቡ ዘንድ መረዳዳትና መቻቻል እንዲኖር አድርጋለች፣ በማድረግም ላይ ትገኛለች። ይህም ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል።

ቤተ ክርስቲያን “ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ” በሚለው ወይም በ“ያ ትውልድ” ቁጥጥር ሥር፦ የዳላስ ተሞክሮ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 20/2010)፦ ይህ ጽሑፍ በቅርቡ በተከታታይ ስናስነብባችሁ እና በዩ-ቲዩብም ስናሳያችሁ የቆየነው “የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ተከታታይ” ሳይሆን ከዳላሱ ጉዳይ በመነሣት የቀረበ አጠቃላይ ምልከታ ነው። ርዕሱን የበለጠ ለመረዳት ግን ሁለት መሠረታዊ አባባሎችን መገንዘብ ያስፈልጋል። እነዚህም “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” እና “ያ ትውልድ” የሚሉት ሐረጎች ናቸው። እነዚህ ሁለት ወካይ ሐረጎች አሁን ኢትዮጵያን በመምራት ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ እና የኢህአፓ መታወቂያዎች ናቸው። ኢሕአዴግ ስለ ራሱ ገድል ያወጣቸው የነበሩት (የነተስፋዬ ገብረ አብ) መጻሕፍት የሚታወቁት “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በሚል ሲሆን ስለ ኢሕአፓ ታሪክ በሰፊው ያተተው የፓርቲው መሥራች ክፍሉ ታደሰ የጻፋቸው መጻሕፍት ደግሞ “ያ ትውልድ” ይባላሉ። ይህ ጽሑፍ እነዚህ ሁለት ትውልዶች ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን እስካላነሱ ድረስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነጻነት እንደሌላት ለማጠየቅ ይሞክራል።

June 23, 2012

በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ


·         የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአስተዳዳሪው ላይ ያቀረበው የሙስና ክስ በመጣራት ላይ ነበር::
·         ወርቅ፣ የውጭ ምንዛሬና የሌሎች ነዋያት ግምት ሳይጨምር በጥሬ ብር ከ200,000 በላይ መዝብረዋል::
·         የአስተዳዳሪውን ሹመት በማስፈጸም የእጅጋየሁ በየነ ሚና አለበት::
·         የሀ/ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ለዐመፅ ለማዘጋጀት አባ ጳውሎስ ያሰቡት ዕቅድ አካል ይኾን?
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- ሰባኬ ወንጌል ከነበሩበት የመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን  ብቻ ነው ያስቆጠሩት - አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ፡፡ በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትን ጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢ የመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነት አስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይ አደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።

June 22, 2012

በጀርመን የቅ/ሚካኤል በዓለ ንግሥ በመናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ


(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ሆን ብለው ከረፈደ በቦታው በተገኙት መናፍቁ «ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ። በሀገረ ጀርመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኑፋቄያቸው ምክንያት በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቁጣን እያስነሱ ያሉት መናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ “ከልካይ የለኝም” በሚል መንፈስ በአካባቢያቸው የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን በአውቶብስ ጭነው ከአካባቢያቸው ወጥተው በአገልግሎት እንዳይስተፉ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የጣሉባቸውን እግድ በመተላለፍ እሑድ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።

June 19, 2012

አቡነ ጳውሎስ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘ ቡድን እያደራጁ ነው


አርእስተ ጉዳዮች፡- (READ THIS ARTICLE IN PDF)
  • ·    አቡነ ጳውሎስ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መናጋቱ የተረጋገጠውን የዐምባገነንት ሥልጣናቸውን ያድሱልኛል ያሏቸውን ሦስት ቡድኖችን አቋቁመዋል፤ “ጉባኤ አርድእት” አንዱ ነው።
  • ·         የ”ጉባኤ አርድእት” መተዳደርያ ደንብ ከሰሞኑ በአቡነ ጳውሎስ ፊርማ እንደሚጸድቅ እየተነገረ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ቢሮ ተሰጥቶታል፤ ምንጩ ያልታወቀ በጀትም ተመድቦለታል፤ 25 መሥራች አባላት እና 180 ተባባሪ አባላት እንዳሉት ተገልጧል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሂደቱን በትኩረት እየተከታተሉት ነው።
  • ·       ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንን ጨምሮ በአእመረ አሸብር፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ እና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራ ነው የተባለው “ጉባኤ አርድእት” የአቡነ ጳውሎስን የጠቅላይነት ሥልጣን የሚያጠናክር የሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹ማሻሻያ› ረቂቅ አዘጋጅቷል፤

June 16, 2012

ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ

·         መናፍቃ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም
·         የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ
·         መናፍቃ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ
·         ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል
·         ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
·         “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡

June 15, 2012

የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት፣ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በ”ችግር ፈጣሪው” አስተዳዳሪ አባ ሚካኤል ታደሰ ታውከዋል READ THIS ARTICLE IN PDF.
·        በአስተዳዳሪነት የተሾሙት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ ዐዋዲውን በመጣስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመኾናቸው ማዕርገ ክህነታቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከተወገዙ በኋላ ነው።
·         ሀ/ስብከቱ የሀብት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ ዘረፋን ያበረታታሉ።
·        ሰንበት ት/ቤቱን ‹ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው› በሚል አገልግሎቱን የሚያደናቅፉ ርምጃዎች ወስደዋል።
·        አስተዳዳሪው ከአባ ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስ ሢመት ተስፈኞች አንዱ ናቸው።

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 8/2004 ዓ.ም፤ ጁን 15/ 2012/) በማዕርገ ዲቁናቸው በእቲሳ ደብረ ጽላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በዐቃቢነት አገልግለዋል፡፡ ያን ጊዜ ስማቸው ዲያቆን ሙሉነህ ታደሰ ይባል ነበር፡፡ በገዳሙ ማዕርገ ምንኵስና ሲቀበሉ ስማቸው አባ ኀይለ ኢየሱስ ታደሰ መባሉን የገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 79/05/98 በቀን 16/05/1998 ዓ.ም የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የግለሰቡን ማንነት አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

June 8, 2012

እውን የማኅበረ ቅዱሳንና የኦርቶዶክስ "ተሐድሶ" ፍልሚያ ወይስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ?


(አዲሱ ተስፋዬ/ READ IN PDF):- ከትላልቆቹ ያገራችን ባለስልጣናት ጀምሮ ታች እስካለው ሕዝብ ድረስ  ማኅበረ ቅዱሳን  የበርካቶች መነጋገርያ ከሆነ ከራርሟል:: የሰሞኑን ግን ለየት የሚያደርገው ራሱን " ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” " በማለት የሚጠራው ድርጅት በማኅበሩና በተዋሕዶ እምነታቸው ላይ ጽኑ አቋም ባላቸው  ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ላይ ለማንበብ የሚዘገንኑ (character assassinating) ጽሑፎችን እያስነበበ ነው ከዚህም አልፎ  የ”ተሐድሶ”  ቡድኖች አቡነ ጳውሎስን የተቃወሙ አባቶች ላይ ስማቸውን የሚያጠፋ በርካታ መጽሀፍት እስከመታተም ተደርሷል (አቡነ ሳሙአልን አቡነ አብርሃምን አቡነ ሚካኤል እና ሌሎች ጳጳሳትን ስም እያጠፉ የወጡት መጻህፍትን ያስታወሷል) አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸውና የድረገጻቸውን traffic rank ከመጨመር የዘለለ አርቀው ማሰብ የተሳናቸው የፖለቲካ ዌብሳይቶችም እነዚህኑ ጽሑፎች በየድረ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ለብዙዎች አስነብበዋል

ስለ ደብረ ይድራስ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንና ስለ ፖሊስ ጉዳይ ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር


(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 1/2004 ዓ.ም፤ ጁን 8/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በፖሊስ እና በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ በርካታ የአዲስ አበባ ፖሊሶችና ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ቁጥራቸው ከ70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣትና ዐዋቂ ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ወዴት እንደተወሰዱም ለማወቅ አልተቻለም፤ ከፖሊሶቹ ከራሳቸው÷ በዐይን ምስክሮች አነጋገር ደግሞ በቦታው ላይ አመራር ይሰጡ ከነበሩት አመራሮች በአንዱ÷ በተተኰሰ ጥይት እንደሞተ በሚነገረው የወረዳው ፖሊስ አባል ሳቢያ የታሰሩት ወጣቶች ለከፋ ጉዳት እንዳይዳረጉ ብዙዎች ስጋታቸውን በመግለጽም ላይ ናቸው፡፡

June 6, 2012

በደብረ ይድራስ ቅ/ጊዮርጊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን የተሰማራው ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ይዞ ቤተ መቅደስ ገባ


·        በአስለቃሽ ጢሱ ጸሎተ ቅዳሴው ታጉሏል፤ ሕፃናት፣ ምእመናንና አገልጋዮች ታፍነዋል::
·        ለውዝግቡ መፍትሔ ያፈላልጋል የተባለ ጥምር ኮሚቴ ተቋቁሟል::
·        ከ70 - 80 የሚደርሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን እንደታሰሩ ናቸው::
·        ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሊቀ ጳጳሱን በስልክ አነጋግረዋል::

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 29/2004 ዓ.ም፤ ጁን 6/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ትናንት፣ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ ስድስት ፖሊሶችና በርካታ ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ብዙዎቹን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላትንና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ በቁጥር ከ70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣት እና አዛውንት ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡

“በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ” (ኢሳት)

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 28/2004 ዓ.ም፤ ጁን 5/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ” ሰዎች መገደላቸውን ኢሳት ዜና ዘገበ። የኢሳት የመረጃ ምንጮችን የጠቀሰው የኢሳት ዜና “ግጭቱ የተከሰተው ቤተ ክርስቲያኑዋ ለትምህርት የምትገለገልበትን ቦታ መስተዳድሩ ለመንጠቅ ሙከራ” በማድረጉ መሆኑን ጠቅሶ “ምእመናኑ የመንግሥትን እርምጃ መቃወማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ አንድ ፖሊስ መሞቱም ታውቋል” ብሏል። “ግጭቱን ተከትሎም በርካታ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያኑዋ ቅጥር ግቢ እንዳይወጡ በፌደራል ፖሊስ ታግተው ነበር። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችም” መታሰራቸውን ዜናው ጨምሮ ዘግቧል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።
 ር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡ 

June 2, 2012

ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።

June 1, 2012

"የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ተቀየረ" (Mahibere Kidusan)


(Mahibere Kidusan):- ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ሊካሔድ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ በታቀደለት  መሠረት ሊከናወን ባለመቻሉ መርሐ ግብሩ እሑድ ጠዋት ከ 3፡00 ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በድምቀት ይከበራል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)