May 21, 2012

WHAT WE WROTE LAST YEAR


“ነጻው ሚዲያ” ስለ ቤተ ክርስቲያን ባለው አመለካከት “ነጻ” መሆኑን ያሳይ
  • ኦርቶዶክሳዊ ፀሐፊዎች እየመሰሉ፣ በመግቢያቸው “ወያኔ ይውደም” የሚል ማባበያ ቃል እየጨመሩ ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን ትውደም” የሚለውን ግብ ያነገቡ ጽሑፎች በየዕለቱ ማንበብ ይዘናል።
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 26/2011፤ ጥር 18/2003 ዓ.ም)፦በተለምዶ “ነጻ ሚዲያ” እየተባለ የሚጠራው ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆነውና በተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚንቀሳቀሰው ሚዲያ ነው። “ሚዲያ” ያልነውን ራሱን ከለተመለከትነው ደግሞ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ጋዜጣና መጽሔቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ማለትም ሬዲዮና ቴሌቪዥኑን፣ እንዲሁም ድረ ገጾችን ሁሉ ያጠቃልላል። እነዚህን ሁሉ ጠቅልሎ በማጥናት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያስተላልፉትን ለመመልከት ብዙ ጊዜ እና የሰው ኃይል እንዲሁም ገንዘብ የሚጠይቅ ቢሆንም በመጠነኛ የወፍ በረር (Birds Eye-view) ቅኝት ያገኘነውን ሐሳብ መነሻ አድርገን ትዝብታችንን ለመጠቆም እንደማይከለክለን እንረዳለን።

ድረ ገጾችን በተመለከተ ያለውን ስብጥር ቀረብ ብሎ ለተመለከተ ሰው አብዛኞቹ ኢትዮጰያውያውን ድረ ገጾች ዋና አትኩሮታቸው ፖለቲካ ነው። ይህም እጅግ ጽንፈኝት ያለበት፣ የአንድ ወገን ደጋፊነት ብቻ የሚንጸባረቅበት ነው ማለት ይቻላል። በአንድ ወገን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አምርሮ የሚጠላ ሚዲያ (ከ www.ethiopianreview.com/ እስከ www.quatero.net/)፣ በሌላ በኩል ደግም መንግሥትን እንደ ነፍሱ የሚወድ (ከ www.ethiopiafirst.com/ እስከ www.aigaforum.com/) ሚዲያ ነው። ዜናዎቹና ሐተታዎቹ፣ ርዕሰ አንቀጾቹ እና ትንታኔዎቹም በዚሁ መልክ የተቀረፁ ናቸው። ወይ ደጋፊ ሆነው የሚያጸድቁ አሊያም ደግሞ ነቃፊ ሆነው የሚያሰየጥኑ (ሰይጣን የሚያደርጉ)። በሁለቱ መካከል ያለ ኢትዮጵያዊ ሚዲያ እና ድረ ገጽ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳለው “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን?” የሚል ጥያቄ ያለበት ጊዜ ነው።

ዋናው ትኩረታችን ስለነዚህ ድረ ገጾች ፖለቲካዊ አቋም መገምገም ባይሆንም “በፖለቲካቸው ውስጥ” ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትነሣበት መንገድ ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ ወደሆነ ደረጃ እያዘገመ በመሆኑ የራሳችንን ሐሳብ ማካፈል ግድ ስላለን ነው።  በነዚህ ሁለት ወገን ጽንፈኛ የአገራችን ድረ ገጾች ግምገማ ቤተ ክርስቲያን ከአንዱ ወገ ትፈረጃለች። አባቶችም ጭምር። በሀገር ቤት ያለው ቤተ ክህነት እስከ ግሳንግሱ “የወያኔ ነው”፤ በውጪ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት እና አባቶች ደግሞ ከነግሳንግሳቸው “የተቃዋሚዎች ናቸው” የሚል ድምዳሜ ላይ የተደረሰ ይመስላል።

ይህ ስሌት ፖለቲካዊ ስሌት ስለሆነ ተቃውሞውም ፖለቲካዊ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም “የወያኔ” የተባለውን ቤተ ክህነት “ለማጥቃት እና ወያኔን ለመጉዳት” የሚፈልገው ከአገር ውጪ ያለው ሚዲያ ከፖለቲካዊ ሐተታ በዘለለ ኦርቶዶክሳዊቱን የተዋሕዶ እምነት በይፋ ከሚቀናቀኑ ወገኖች እና ፀሐፊዎች ጋር በመቆም ላይ ይገኛል።

ሚዲያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች መጠቀሚያ የሆኑት አብዛኞቹ በሥልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ ለመቀናቀን ካላቸው ፍላጎት ነው። የሚዲያው ባለቤቶች ስለ ነገረ ሃይማኖት ያላቸው ዕውቀት ውሱንነት ለእምነታቸው በጎ ያደረጉ እየመሰላቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጎዱ እያደረጋቸው ነው። ኦርቶዶክሳዊ ፀሐፊዎች እየመሰሉ፣ በመግቢያቸው “ወያኔ ይውደም” የሚል ማባበያ ቃል እየጨመሩ ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን ትውደም” የሚለውን ግብ ያነገቡ ጽሑፎች በየዕለቱ ማንበብ ይዘናል። በፕሮቴስታንታዊ ቅኝት የሚዘፍኑ የተሐድሶ ቡድኖች ወይም ለኢትዮጵያ ድህነት ታሪካዊ ምክንያት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት የሚለው ታሪካዊ ማስረጃ የጎደለው ጥራዝ ነጠቅ አመለካከት አራማጅ ፀረ ተዋሕዶ ፀሐፊዎች ሚዲያዎቹን እንደፈለጉት በመጠቀም ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ መንግሥት በእምነት ውስጥ ጣልቃ ገብቷል ብለው የሚከሱ ወገኖች ያውም ቤተ ክርስቲያኒቱ ስለ ትምህርተ ሃይማኖቷ መልስ እንድትሰጥ ዕድል ባልተሰጣት ሁኔታ ለተቃዋሚዎቿ ብቻ በር በመክፈት የአጽራረ ተዋሕዶ ዒላማ ማድረግ በየትኛውም መመዘኛ ቢሆን ሚዛናዊ አይሆንም። መንግሥትን በሚከሱበት ጉዳይ እነርሱም ተጠያቂዎች ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ መንግሥት አዲስ አበባ እነርሱ በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ መቀመጣቸው ነው።

ከዚህ በፊት በአንድ መልእክታችን እንዳልነው ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ የሚለው የኢሕአዴግ ቡድንም ሆነ “ያ ትውልድ” የሚባለው የኢሕአፓ፣ የመኢሶን፣ የኢሰፓ ወይም በየብሔሩ የተደራጀው ፓርቲ በሙሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የጫነውን እጁን ማንሣት አለበት። ሚዲያዎችም ቤተ ክርስቲያኒቱን መዋጋታቸውን ማቆም አለባቸው። አቡነ ጳውሎስን ለመቃወም ቅዱስ ሲኖዶስን መቃወም የለባቸውም፣ ኢሕአዴግን ለመቃወም በጠቅላላው ቤተ ክህነቱን መቃወም የለባቸውም። አንዱን ጳጳስ ለመቃወም ጵጵስናን በሙሉ መዋጋት የለባቸውም።

ከነዚህ ድረ ገጾች መካከል በተለይ አቡጊዳን፣ ቋጠሮን፣ ኢትዮጵያን ሪቪውን ብንጠቅስ በአብዛኛው በነገረ ማርያም ላይ ለሚነሡ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ተቃውሞዎች ዋነኛ መጠቀሚያ በመሆናቸው ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውን እንዲፈትሹ እንጠይቃለን። ወይም ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያብጠለጥል ጽሑፍ የሚያወጡ ከሆነ ለዚያ መልስ የሚሆን ነገር ከሚመለከታቸው ሊቃውንት መጠየቅ ይኖርባቸዋል። የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር የሚያዘው ይህንን ነው። ወይም “በእምነት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለባቸውም” የሚባለውን  መተግበር አለባቸው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

7 comments:

Anonymous said...

ግሩም አስተያት ነው እኔ በመጀመሪያ በፊት እነዚህ ዌብ ሳይቶችን በጣም አዘውትሬ እከታተል ነበር አሁን አሁን ግን የውጭውን ሲኖዶስ መደገፍ ብቻ ሳይሆን የተሃድሶንና፤ማናፍቃን ወሬ የሚያወጡ ከሆነ በኋላ እዲያውም የማውቀውን ነገር ብዙ ውሸት
ደባልቀው ጥቄት እውነት እሚያስመስል ነገር ስለሚጽፉ ድረ ገጾችን መክፈት ጊዜ ማባከን ነው በማለት አቁሜአለሁ።ደጀ ሰላማውያን ጥሩ ምክር አዘል ጽሁፍ በመጻፋችሁ ምን አልባት ሥህተታቸውን ያርሙ ይሆናል ምነው የሲኖዱሱ ጉዳይ ጸጥ አለ?

Anonymous said...

dejselamoch endew egzehabher yakeberachu awo be poltika bemasaseb zare betkerstyanen lemwegate yetnsu bezochu endehonu eyayene eyesemane new amelake kidusan yastageselen enge yeflguten betrku bezu abatochachen pepsenaw menkusenaw kehntu astemarentu yemtyebachew yemenbebebachew bezu abatoch alune yehnene degmo atebekew lerdu yegebale egzehabher sew alew bewededew seat hulune mastekakel yemechel newena lersu enstew.

Anonymous said...

ene yemilew mk abba pawlos andegifim sinodosun endegifalen malet min malet new??? ene yemigebagn hawariyatin enkebelalen Geta Eyesusin Anikebelim Malet Eko new Ebakachiw Aszewulu

Anonymous said...

Deje Selam Girum Asiteyayt & Ababal new Tikikil Nachihu Enantem Kezih temaru Zare Bete Kirsityann Sedibo Lesedab yesetse Manew ?Bemeweyayet -bemenegger- Benisiha - bewsane yemistekakeln neger Adebabay mawtsat Min Yibalal/
Poletikegoch yihichin megibiya agigitew Sedebu Awaredu Keledu
Semonun yeteyazew neger Mindinew ?Deje Selam Endezegebew eyalu yerasachewn neger menager yejemeru Yelum ? Alu Deje Selam degimo Mahibere Kidusan newna poletikega asbalut mahibere Kidusan degimo poletikega ayidelem Zare melkam tenagrachihal betu enantem Abune Ekele endih nachew maletn tew adera

ድሉ ዘእግዚአብሔር said...

ቤተ ክህነትን ፥ ጵጵስናን ፥ ፓትርያርክነትን መቃዎምና ስሙን እንጅ ግብሩን የማይከተሉትን መቃወም አንድ አይደለም። ሥልጣኑ እና በሥልጣኑ የሚነግዱበት ሰዎች አንድ ኣይደሉምና። አንድ ተቋም የሚመራው ከተቋሙ መሠረታዊ መርሆ ውጭ በሆነ መንገድ የሚመራ ከሆነ ያ ተቋም እንደተቋም መነቀፉ የማይቀር ነው። ተቋሙ የተቋቋመበትን መሰረታዊ መርሆ ጠብቆ እንዲሄድ ከተፈለገ ለተቋሙ ሕግ በሚገዙ መሪዎች መመራት አለበት። ታድያ እንዴት ሁኖ ነው በአባ ጳውሎስ የሚመራውን ሲኖዶስ መተቸት እንደ ፀረ ሲኖዶስ ፥ እርሳቸው በሚሾሟቸው ''የቤተ ክህነት መሪዎች''የሚመራን ጊዜአዊ አመራር ቋሚ የሆነውን የቤተ ክህነት ተቋም እንደ መተችት ወይም እንደ መንቀፍ ሁኖ ሊታይ የሚገባው? ተቋማቱ እየደረሰባቸው ያለው ነቅፋ ምክንያቶቹ እስካልተወገዱ ድረስ መነቀፋቸው አይቀሬ ነው። እስቲ ደጀሰላማውያን አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ? ቤተክህነት ከቤተ መንግስት ነፃ የሆነችበት ነበረ ? ዛሬስ በተግባር አለ ? ይህ እንግዲህ ሞራላችሁን የሚፈታተን ጥያቄ ነው ። አዎ እኔ ያለሁት በነፃው ዓለም ነው እናንተ ደግሞ ነፃ ባልሆነ አገር በጨለማ ውስጥ ስለምትኖሩ በነፃነት ሁሉንም ነገር እንደ ሁኔታው ትነግሩን አላችሁ ብየ አልጠብቅም። እንዲያም በከፊልም ቢሆን በአንበሳ መንጋጋ ውስጥ ሁናችሁ ለመግልጥ መሞከራችሁ በተግባር ከእኔ ትበልጣላችሁ። የምታደርጉትን መንፈሳዊም ሆነ አገራዊ ጥረትም እያደነቁ ከመጡት መፃተኞች አንዱ ነኝ። እና በርቱ ነው የምለው።

Anonymous said...

Deje selam, enanate ye selam bet nachehu. As the article mentioned especially Ethiopian review is publishing such anti-orthodox notes. We advised him in group to not to publish such notes any more and if he continues we planned to stop our monthly contribution and and interest on the website. We will respect him when he respect our belief. Especially, the so called "Mulugeta w/gebriel" is using the website to insult the chruch and its holy members. Seyitan Mulugeta is anti-orthodox, his every thing is protestnat , so he is free to go to Protestant church but why he bother us by pretending as if he is orthodox. He call him self deacon but I don't think so???????

Anonymous said...

Excellent view may GOD bless u

ግሩም አስተያት ነው እኔ በመጀመሪያ በፊት እነዚህ ዌብ ሳይቶችን በጣም አዘውትሬ እከታተል ነበር አሁን አሁን ግን የውጭውን ሲኖዶስ መደገፍ ብቻ ሳይሆን የተሃድሶንና፤ማናፍቃን ወሬ የሚያወጡ ከሆነ በኋላ እዲያውም የማውቀውን ነገር ብዙ ውሸት
ደባልቀው ጥቄት እውነት እሚያስመስል ነገር ስለሚጽፉ ድረ ገጾችን መክፈት ጊዜ ማባከን ነው በማለት አቁሜአለሁ።ደጀ ሰላማውያን ጥሩ ምክር አዘል ጽሁፍ በመጻፋችሁ ምን አልባት ሥህተታቸውን ያርሙ ይሆናል ምነው የሲኖዱሱ ጉዳይ ጸጥ አለ?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)