May 14, 2012

"ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፍርድ እና ውሳኔ እንዲሰጠኝ" ቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ


ቀን   ግንቦት 5 ቀን 2004 ዓ.ም  ቁጥር  EOTCDC/135/2004
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን                                                                                                                   ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

ጉዳዩ ፦    ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ  ጉባኤ  ፍርድ እና ውሳኔ ንዲሰጠኝ ስለመጠየቅ  

በቅድሚያ የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት የሆናችሁ አባቶቼ  ሁሉ  ቡራኬያችሁ  ይድረሰኝ እያልኩኝ ፤ ለቀደሙት አባቶቻችን  እውነተኛ የሃይማኖትን ገድል እንዲፈጽሙ ጽናትንና ትእግሥትን የሰጠ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር እናንተንም  በተቀመጣችሁበት ሐዋርያት መንበር  ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ዘላቂ ሰላም   የሚጠቅም   እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ለገጠማትን  ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሔ ለመስጠት እንድትችሉ እግዚአብሔር ይርዳችሁ እላለሁ :፡
 
ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደድኩት  የቤተ ክርስቲያናችን  የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ከሆነው  ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  ውሳኔ እና ፍርድ  እንድጠይቅ የሚያስገድድ ጉዳይ ስለገጠመኝ ነው ። እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያንን እምነት ሥርዓትና  መዋቅር መጠበቅና ማስጠበቅ የሁላችን ግዴታ በመሆኑ ፤እኔም በምኖርበት በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በተሰጠኝ ኃላፊነት መሰረት የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በመጠበቅ በጽናት የቆሙ የአብያተ ክርስቲያን አቋም እንዲገለጽ በማድረጌ  እና ይህንንም መዋቅር ለማፍረስ የተነሱት አቡነ ፋኑኤል የሚያከናውኑት  ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን  የወጣ ተግባራቸው ጋር ተባባሪ ባለመሆኔ የተነሳ  በክፋትና በጥላቻ መንፈስ ተይዘው ስም ለማጥፋትና ባይሳካላቸውም በቱሩፋት የማከናውነውን የቤተ ክርስቲያን  አገልግሎት ለማደናቀፍ ደብዳቤ እስከመጻፍ ደርሰዋል ። ይህ የጥላቻ ተግባራቸው በዚህ አልበቃ ብሎ ለዚህ የክፋት ተግባራቸው ተባባሪ ከሆነው   ከኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን  እና ከዜና ቤተ ክርስቲያን  አዘጋጆች ጋር በመሆን   ቤተ ክርስቲያን መሪና ተቆጣጣሪ የሌላት የጥቂት ግለሰቦች መፈንጫ የሆነች በሚያስመስል መልኩ  በዜና ቤተ ክርስቲያን  እኔን በተመለከተ የተሳሳተ እና በሀሰት ላይ የተመሰረተ ዘገባ እና  የስም ማጥፋት ተግባር ተፈጽሟል። 

ደሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ታላቅ መንፈሳዊ አደራ  የተሰጣችሁ አባቶች   ለዚህ ችግር በመንፈሳዊ አግባቡ  ከእናንተ የበለጠ መፍትሔ ሊሰጥ የሚችል አካል የለምና ፤ ይህንን የተፈጸመውን በደል ማለትም ሀሰትን መሰረት አድርጎ  በአቡነ ፋኑኤል የተጻፈብኝን ደብዳቤ  እና  አቡነ ፋኑኤልና  ኃይለ ጊዮርጊስ  ጥላሁን  በዜና ቤተ ክርስቲያን  እንዲወጣ ያደረጉት ዘገባ  በመመልከት  ቅን ፍርድ እንዲሰጠኝ ይህንን አቤቱታ አቀርባለሁ። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በትክክል ጉዳዩን ከመረመረው አቡነ ፋኑኤል  በተደጋጋሚ በፈጸሙት  ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን  የመተላላፍ ተግባር  በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጭምር እየተነገራቸው የባሰ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም የሚያናጋ ተግባር ውስጥ መገኘታቸው  ቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ንቀት የሚያመላክት ነው ።  

ስለዚህ የቤተ ክርስቲያንን ኃላፊነት ለመወጣት ባደረኩት ጥረት የተነሳ ለተፈጸመብኝ በደል አቡነ ፋኑኤል፤                                                                                                                            ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ፤የዜና ቤተ ክርስቲያን አዘጋጆች እና  ከጀርባ ሆነው ይህ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረጉ ሁሉ  በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲጠየቁና ለተፈጸመብኝ በደል  በመንፈሳዊ አግባቡ ተገቢው  ውሳኔ እንዲሰጠኝ ሃይማኖታቸው በቀና  በኒቅያ በተሰበሰቡ በ318 ሊቃውንት  ስም ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ ሰማዕትነትን በከፈሉ በኢትዮጵያን ቅዱሳን ስም  እጠይቃለሁ ። 

ቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ
የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት  ጸሐፊ

ግልባጭ
ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት                                                                                                                                           ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)