May 14, 2012

በጀርመን የሚገኙ ምእመናን በአካባቢው በሚገኝ መናፍቅ ቄስ ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት አሁንም ምላሽ እየጠበቁ ነው


 (ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 6/2004 ዓ.ም፤ May 14/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ለረጅም ዓመታት በጀርመን በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን አቤቱታ ሲቀርብበት የነበረው ከመናፍቅነት “ተመልሻለሁ” የሚለው የ”ቀሲስ” ገዳሙ ደምሳሽ ጉዳይ  እስካሁን ድረስ መፍትሄ አለማግኘቱ በአካባቢው ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን እያስነሣ ይገኛል። ሕዝበ ክርስቲያኑ ቅሬታቸውን ምንም እንኳን በተደጋጋሚ በጀርመን ካለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ኃላፊ አንስቶ ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ ቢያሰሙም የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት አስገብቶ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጣቸው የቻለ አንድም አካል አለማግኘታቸው እንዳሳዘናቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያስረዳል።


የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በነሐሴ ወር ፳፻፫ ዓ/ም  እኚህኑ ግለሰብ ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ በአጥቢያቸው ብቻ እንዲወሰኑ እገዳ ጥለውባቸው ከሄዱ በኋላ ግለሰቡ ምእመናንን የማሰናከል ሥራቸው እየከፋ ከመሄዱ በፊት በአስቸኳይ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ በጀርመን የሚገኘው የምእመናን ኅብረት የአቤቱታ ደብዳቤ በጥቅምት ለዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በብፁዕነታቸው በኩል ቢያቀርብም የሚጠበቀው ውሳኔ የውኃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል።

በወርኃ ታኅሣሥ ፳፻፬ ዓ/ም የቅዱስ ገብርኤል በዓል በሙኒክ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሚከበርበት ጊዜ ምእመናን በድጋሚ ጥያቄውን ከሌሎች በጀርመን ከሚገኙ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት አስተዳደራዊ ችግሮች ጋር አንድ ላይ አድርገው ቢያነሱም “ጊዜ ስጡን” ከሚል ምላሽ ውጭ ተግባራዊ ነገር አለማየታቸው ወደ ተስፋ መቁረጡ እያስገባቸው እንደሆነ ጠቁመውናል። በሙኒክ በነበረው ንግግር ጉዳዩ በምእመናኑ በኩል በሰፊው የተነሳ ሲሆን ሊቀ ጳጳሱ የምእመናኑን ችግር ለማዳመጥ መድረክ መስጠታቸው ከጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ እና ከፍራንክፈርት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በኩል ቅሬታን የፈጠረ ሲሆን በተለይ ከፍራንክፈርት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ከአባ ሲራክ ወልደሥላሴ ከአንድ የሃይማኖት አባት የማይጠበቁ ከሥርዓት ውጪ የሆኑ ንግግሮች እንዲሰሙ ምክንያት ሆኗል።

ሊቀ ጳጳሱን በምእመናኑ ፊት የዘለፉት አባ ሲራክ በአጥቢያቸው “ሰበካ ጉባዔው እንዳይጠናከር፤ ስብከተ ወንጌልም ተዳክሞ እንዲቆይ፤ የሰንበት ትምህርት ቤቱም በአግባቡ እንዳይሠራ፤ ህጻናት ልጆቻችንም ተገቢውን መንፈሳዊ ትምህርት እየተማሩ እንዳያድጉ” ምክንያት ሆነዋል የሚል አቤቱታ ቀርቦባቸው ሳለ መናፍቁን ቄስ መከላከሉ ላይ መግባታቸው፣ ከማዕረገ ክህነታቸው ወደ ላይ ከፍ ብለውም ሊቀ ጳጳሱን መናገራቸው በብዙዎች ዘንድ ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል።  በሌላ በኩል በዋዜማው ዕለት የምእመናኑን ሮሮ ካዳመጡ በኋላ “በምትፈልጉት ጊዜ መጥቼ አብረን እንነጋገራለን” ብለው የነበሩት ሊቀ ጳጳሱ በበነጋታው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ አሳባቸውን መቀየራቸው በጉዳዩ ጠንካራ አቋም መያዝ አለመቻላቸውን ከማሳየቱም በላይ በጀርመን ባሉት ኃላፊ እየደረሰባቸው ያለውን ተፅዕኖ ያመላከተ አጋጣሚም ነበረ።

የሊቀ ጳጳሱን እገዳ ከቁብም ያልቆጠሩት ኃላፊውን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙት አንዳንድ ካህናት ከሁለት ሳምንታት በፊት በሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም መናፍቁ ቄስ በአጥቢያቸው ባከበሩት የንግሥ በዓል ላይ መገኘታቸው ታውቋል። ሊቀ ጳጳሱ እገዳውን ያስተላለፉት ግለሰቡ በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ምእመናንን በኑፋቄ ትምህርታቸው እንዳያሰናክሉ መሆኑ እየታወቀ ግለሰቡ በሚገኙበት ቦታ ምእመናንን አስተባብሮ ለመሄድ መሞከሩ ይህን ያደረጉት ካህናት ለሃይማኖት ጉዳይ ያለ ቸልተኝነተን ያሳየ ነው። በዕለቱ የተገኙት በጣም ጥቂት ምእመናን ሲሆኑ በዑደት ጊዜ ታቦቱን እንዲያጅቡ ከውጡት ሥዕላት ውስጥ የእመቤታችን ሥዕል አለመውጣቱን በቦታው ተገኝተው የነበሩ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “መጻሕፍትን መርምሩ፤ በእልቅና ካባ ፓስተር መቅደስ ገባ?” በሚል ርዕስ በዛው በጀርመን በሚገኝ የካስል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመምህር ኅሩይ ኤርምያስ ተዘጋጅቶ በኅዳር ወር ፳፻፬ ዓ/ም ታትሞ ለአንባቢዎች የቀረበውና በ”ቄስ” ገዳሙ ደምሳሽ ለተፃፉት ሦስት መጻሕፍተ ኑፋቄ ሰፊ እና ጥልቅ የሆነ ምላሽ የሰጠው መጽሐፍ ራሳቸውን የቤተ ክርስትያናችን አባት ነኝ ብለው የዋህ ምእመናንን በማሰናከል ላይ ያሉትን የ”ቀሲስ” ገዳሙን ማንነት በማጋለጥ ደረጃ ትልቅ አስዋጽኦ እንዳለው መጽሐፉን አንብበው አስተያየታቸውን የሰጡን ምእመናን ገልጸውልናል።

በመጽሐፍ የገባን ኑፋቄ በመጽሐፍ መመለስ እንዲገባ ተረድተው ምላሹን ያቀረቡት መምህር ኅሩይ ልክ እንደቀደሙት ሊቃውንት ማለትም ኰኵሐ ሃይማኖትን እና መድሎተ አሚንን እንዳቀረቡልን እንደ ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ “መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና”ን እንዳስነበቡን ዓይናማው ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ በሚጥም አንደበት የነሱን ፈለግ ተከትለው ያዘጋጁት መጽሐፍ ምላሽ ብቻ ሳይሆን ራሱን የቻለ ትምህርት ነው ሲሉ መጽሐፉን ያነበቡ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ በምላሽ መጽሐፉ አቀራርብ እና ጥልቀት በጣም እንደተደሰቱ ቢያሳውቁንም በአንጻሩ የሊቃውንት እጥረት በሌለባት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የዋህ ምእመናን እንደ “ቀሲስ” ገዳሙ ላሉ የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች ተላልፈው መሰጠታቸው እጅጉን እንዳሳዘናቸው፤ ጉዳዩ በሚመለከታቸው በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ኃላፊዎች ዝምታና ቸለተኝነትም  ቅር መሰኘታቸውን ጨምረው ገልጸውልናል።

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ባሉ ኢትዮጵያውያን ምእመናን እየተነበበ ያለውና 219 ገጾች ያሉት ይኸው መጽሐፍ “ቀሲስ” ገዳሙ ደምሳሽ በሦስቱ መጽሐፎቻቸው ያቀረቡትን ኢኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ነቅሶ በማውጣት በቀደሙ አባቶች ለዛ እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረውን ትምህርት ያሳየ ሲሆን ምእመናንም ይኽንን የምላሽ መጽሐፍ በማንበብ አባቶቻችን መምህራን የሃይማኖት ቅንጣትን በዘሩበት በወንጌል እርሻቸው ላይ ሐሰተኛ መምህራን የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንዳይዘሩባቸው፤ ራሳቸውን እና ቤተ ክርስቲያናቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ ያሳስባል።

በጀርመን ሀገር በቪዝባደን ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት “ቀሲስ” ገዳሙ ደምሳሽ በ1997 ዓ.ም “ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቀደመች ቤተ ክርስቲያናቸው ተመልሰዋል” ከመባላቸው በፊት በይፋ በፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያገለግሉ የነበሩና በአጠቃላይ አራት የኑፋቄ መጻሕፍትን የጻፉ ሰው ናቸው። ሁለቱን ቀደም ብለው ቀሪ ሁለቱን ደግሞ “ተመልሰዋል”  ከተባሉ በኋላ ያቀረቡ  ሲሆን ከአራቱ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ የሚያተኩሩት ሁለቱ አንዱ ከአንድኛው በይዘት ካለመለያየታቸውም በተጨማሪ በመጨረሻ የወጣው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሁለተኛ ክፍል ቀድሞ በመናፍቃኑ ጎራ በግላጭ እያሉ በጻፉት በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ የነበረውን ሕጸጽ አርሞ ያልወጣ ይልቁንም ያንኑ ስህተት አጠናክሮ ይዞ የቀረበ ነው።

ግለሰቡ ከሚያስተዳድሩት ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው እየኮበለሉ ወደመናፍቃን አዳራሽ የሚነጉዱት ምእመናን ቁጥር ያሳሰባቸው፤ ይህም ሲሆን እያየ ምንም ዓይነት ርምጃ ሊወስድ ያልቻለውን በጀርመን ሀገር ያለውን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የተቃወሙ በጀርመን ሀገር የሚገኙ ምእመናን በጥቅምት 2004 ዓ.ም ቅ/ሲኖዶስ እኚህኑ ግለሰብና ያለውን የአስተዳደር ችግር በተመለከተ ፊርማቸውን ያሰፈሩበት አቤቱታ ከመረጃዎች ጋር ለመንበረ ፓትርያርክ ውጪ ጉዳይ መምሪያ እና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ያስገቡ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምላሽ አለማግኘታቸው ይታወቃል። የዝግጅት ክፍላችን ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ ላይ የዘገበ ሲሆን በቀጣይም ሁኔታውን እየተከታተለ ላንባቢዎች የሚያሳውቅ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናሳውቃለን። ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ዘገባ ለመመልከት እዚህ ጋር  http://www.dejeselam.org/2011/10/blog-post_19.html ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

18 comments:

galela said...

batame yegaremale eska ahone ''kase''gadamo alo manafeke mahonachawen holome yawekalo.yazare wayem yatekeme godaye nawe enje.

lelr said...

I know ''kase''gedamo,he is manafek

Anonymous said...

dejeselam akerabewache tabbarako

Anonymous said...

I know him very well,since i was a kid....menafk new.

Anonymous said...

መናፍቅን ወደ ቤተ መቅደስ ይዞ የገባና ያስገባስ?

Anonymous said...

እንዲያው ገዳሙን እንላለን እንጂ በጀርመን ለብዙ ዓመታት ቤተክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የኖሩት ዶክተር መራዊ ተበጀስ
ምን ሊባሉ ይሆን ከማይመስሉን የመናፍቃን ድርጅቶች ጋር በጥምቀት አንድ ነን ብለው የተፈራረሙት?

Anonymous said...

Slehulume Egzio Egzio Egzio Yasegale. Yefelegewn Gize wosedo KIDUS SINODOSU Melse Mestet Yalebet wokedt new. Lezhume Yemiazen Lubona Yestelen. Ere besentu twotern Amlkachen Ebakehe Siman. Gorohen Ende kedemut Abatoch Ahunem Seman. Dengle Tamalden. AMEN.

Anonymous said...

Deje selamwech egzabhe yestelen yezeh yemenafeg gwday gena ewnetw becha yewetal lemanegawem ersu becha sayhwen menafek Dr.Merhawy menafek new selezeh enezehen kebetekrestanachen maswtat aleben egzabher yerdan

Anonymous said...

dejselamochen bekdmeya eymesgenku bezeh techmares yersus ande leytoletale aberwen yaltuen abatoch ,..men enbelachew wengel endaysete senbet temhert bet endaynore memenane endaysebsebu felagote yelelachewen tadya men enbelchew dejselamochen kesafachu layker yehulunem betdasesu teru new betleye ye FRANKFURTEN guday

Anonymous said...

Can you mention just one issue that would label Reverend Gedamu " Menafiq?". If you were to stand for the truth and the church, you would have done that. For all what we know, this is the work of Mahbre " Kidusan", and their desperate move to terrorize the faithful and the church. But let me tell you this, you are now dying, a shameful death indeed...

Anonymous said...

awo zarem betam asasabe cheger weste engegalen betkerstyanwa sew endaynorat eydargu yegegale lesmu new docter,aba yetbalute enrsu yechegrachew ye euro gedaye enge lela aydelem gen wedet enhed betley Germane yalen memenane cheger west new yalnew ena betchale meten beslotachu asebune

Anonymous said...

For the one who asked about Gedamu's "nufaqe" (written in English). Please read the above mentioned book if you can read amharic; otherwise let others read to you.

Nahom said...

ወጊድ የጀርመኑ ይሁዳ!
ናሆም/ከጀርመን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“ክብርት ናት ብንል የምንናገረው የእርሷን ክብርትነት ብቻ ሳይሆን ያከበራት የጌታንም ቸርነት ጭምር ነው።ቅድስት ናት ብለን ብንመሰክር የምንመሰክረው የእርሷን ቅድስና ብቻ ሳይሆን የቀደሳት የጌታንም ታላቅነት ነው።ክብሯን ንቀን አቃለን ብንገኝ ግን እርሷን ብቻ ያይደለ ያከበራት ክርስቶስ እየሱስንም ንቀናል አቃለናል።አብና መንፈስ ቅዱስም የሉንም። “አሁንም የሚክድ መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁን እግዚያብሄርን እንጂ ሰውን የካደ አይደለም እንዳለ ጳውሎስ 1ኛ ተሰ4፡8`` መጻህፍትን መርምሩ በእልቅና ካባ ፓስተር መቅደስ ገባ? መፅሃፍ ገፅ 182.
ከላይ እንደ መግቢያ የተጠቀምኩበትን ጥቅስ ማጣቀሴ የፅሁፌን አጠቃላይ መንፈስ በደንብ ስለሚገልፀው ነው።
የዚህ ፅሁፍ ዓላማም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ቅዱስ አባታችን አቡነ ጳውሎስ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አገረስብከት በሚተዳደረው የጀርመን ቪዝባደን ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፓስተር ገዳሙ ደምሳሽ አፅራረ-ቤተክርስቲያናችን እንቅስቃሴ መላው ምዕመን ልቡ መድማቱን ልብ ያለው ልብ እንዲል ለማስገንዘብ ነው።
በስም ተጠቃሹ ግለሰብ(ፓስተር ገዳሙ ደምሳሽ) ከዚህ ቀደም ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ክደው ወደ መናፍቃን ከሄዱ በሁዋላ የተለያዩ መፃህፍትን በመፃፍና ቤተክርስቲያንን እስኪበቃቸው ሰድበው ለሰዳቢ በመስጠት ከቆዩ በሁዋላ “ይቅርታ“ ብለው ተመልሰዋል በሚል በምዕመንነታቸው መቀጠል ሲገባቸው ማን እንደሾማቸው ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ተመልሰው ጭራሽ የአንድ ቤተክርሲቲያን አስተዳዳሪ ሆነው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
በቤተክርስቲያናችን ህግ መሰረት ከሰባቱ ሚስጥራት መካከል ጥምቀት፣ሜሮን፣ክህነትና ተክሊል ለአንድ ጊዜ ብቻ ያለመደጋገም ቁርባን፣ንስሃና ቀንዲል ግን ተደጋግመው የሚፈፀሙ መሆናቸው በግልፅ ሰፍሮ ክህነቱን በአደባባይ ያፈረሰው ፓስተር ተመልሶ አለቃ ሆኗል።ለምን?ህጋችንን ማን አፈረሰው ለሚለውም እስካሁን እከሌ የሚል አልተገኘም።
ይህንንም በማየት ህዝበ ክርስቲያኑ በተደጋጋሚ ቅሬታውን ቢያቀርብምና አቤቱታውን እስከ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ዘንድ ቢያደርስም እጅግ በጣም በሚገርም ሁኔታ ለበርካታ ዓመታት ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቷል።
ጉዳዩ ይባስ ብሎ “ተመልሷል“ በተባለባት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሆኖ የውስጥ ለውስጥ ሸፍጡ ሳያንስ ፀረ-ቤተክርስቲያን የሆነ መፅሃፍ- በመናፍቃን ጎራው እያለ ከፃፋቸው ጋር ተመሳሳይ የሆነ መፅሃፍ አሳትሞ ማሰራጨት ሲጀምር በምዕመኑ ከፍተኛ ተጋድሎ ሳይስፋፋ ቀርቷል። ይህ ባይሳካለትም ፀረ-ቅድስት ድንግል እግዚእትነ ማርያም መፅሃፍቱን በመሸጥ ላይ የሚገኘው መፅሃፍቱ ለቆመለት የመናፍቃን ሃይማኖት መደብሮችና የእነዚህኑ የክህደት ትምህርት በሚያስተላልፉ የኢንተርኔት መረጃ መረቦች ላይ ሆኗል።
ይህ ግለሰብ በሚሰጠው ኑፋቄ ትምህርትም በተለይም ከግለሰቡ ጋር ቅርበት ያላቸው የቤተክርስቲያን አገልጋዮች (የሰበካ ጉባኤ አባላት)ቅዱስ ቁርባናቸውን ሳይቀር አፍርሰው ወደ መናፍቃን ጎራ ገብተዋል ክደዋል።በአንድ ወቅትም ምነው እርሶ በዛች ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከሆኑ በሁዋላ ምዕመናን ክህደት አበዙ ይህ ይሰማዎታል ወይ ?ተብለው በህዝብ ፊት ተጠይቀው አንድ ተራ ሰው ሄደና ምን ጉዳት አለው አይነት መልስ ሰጥተዋል።የሚሰጡት ትምህርት ሁሉ መድሃኒያለም በሚያውቀው ፀረ-እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነው።ይህን ለተመለከተ ቤተክርስቲያኗን እውነት የሚመራት አካል የለም እንዴ ያስብላል።
አንባብያን በጣም ልባችንን የጎዳውን ነገር አሁን እነግራችሁዋለሁ።ብታምኑም ባታምኑም ግለሰቡ በሚያስተዳድራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል አይወጣም።እውነት ስለሌለ ነው ወይስ ግለሰቡ በመፃህፍቱ እንደሚነግረን እመቤታችንን ስለሚጠላት?ይሄ ሳያንስ በዓመታዊ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል ላይ ከሌላ ቤተክርስቲያን እንኳን የእመቤታችንን ስዕል ተውሶ ምዕመኑን ላለማስቆጣት አልሞከረም።በማን አለብኝ ስሜት ያለእመቤታችን ስዕል ታቦት ወጥቷል።ይሄ ደግሞ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን አምናም ጭምር ነው።ለምን ቢባል ሰውየው ደረቱን ነፍቶ ስለሌለ ነው የሚል ምላሽ የሰጠ ደፋር ነው።ህዝበ ክርስቲያኑም ስርዓቱን ላለመረበሽ በሚል እስካሁን ሲያልፍ ቆይቷል።
ቀጣዩን ክፍል በሚቀጥለው ክፍል ይመልከቱ !

Nahom said...

ከቅድሙ የቀጠለ ነው።መልካም ንባብ-

ለመሆኑ በየትኛው ስርዓትና ቀኖና ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ያለ-ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም የተሰበከው? ለመሆኑ ከእመቤታችን ውጭ ኦርቶዶክስነት አለ እንዴ?
ሌላው ቢቀር የሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ፊት ሳይቀር በመላ ትምህርቱ ለማስመሰል ካልሆነ በቀር የእመቤታችንን ስም አይጠራም።በታላላቅ ክብረ-በዓላት ሳይቀር የእመቤታችንንና የመላዕክትን ስም መጥራት ግድ ሲሆንበት እንኳን የሚተናነቀው ሰው ነው።ለነገሩ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ ስሟን ጠርተው የሚድኑ ሚሊዮኖች ናቸውና የሚደንቅ አይሆንም።ግን አባቶች እያሉን እንደሌሉን ነው የሆነው።
ይህንን ጉዳይ በአካባቢው ያሉ ሁሉም አባቶች ያውቁታል።ነገር ግን በተለይ በጀርመን አገር በአገልግሎት የቆዩት አባቶች አሁን አሁን እያሳሰባቸው ያለው ጉዳይ የግል ጓደኝነታቸው እንጂ የቤተክርስቲያኗ ባለመሆኑ አብዛኞቻችን ምዕመናን እምነት እያጣንባቸው ነው።እሱም የልብ ልብ የተሰማው አንዳንዶቹ የሱን ሃሳብ የሚጋሩ መሆናቸውን ማወቁ ነው።በዚህም መሰረት በርካታ ምዕመናን ሳይፈልጉ በሌሎች አገሮች ኦርቶዶክሳዊ አብያተ-ክርስቲያናት ለመገልገል እየተገደዱ ነው።
እንደ እኔ እምነት ግለሰቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመናፍቃን ተወካይና የክህደት እንቅስቃሴዎች መሪ ሆኖ በማገልገል ላይ የተሰማራ በበግ ለምድ የተሸፈነ ተኩላዊ-ይሁዳ ነው!
ብሎ ብሎ አሁን አደገኛ አካሄድን መርጦ ምዕመኑን ለመከፋፈል የዘር ፖለቲካ ጀምሯል።ኑፋቄ ትምህርቱን የተቃወመውን ሁሉ ይሄ እኮ ፀረ-እከሌ ብሄር ስለሆነ ነው አይነት ቅስቀሳ ላይ ተጠምዷል።እዛ በአገር ቤት የለመደውን ክፉኛ መርዙን በመርጨት ዋናውን ጉዳይ ለማስረሳትና አቅጣጫ ለማስቀየር የሚያደርገውን ጥረት ደግነቱ ምዕመኑ ቀድሞ በመገንዘብ እየተከላከለው ነው እንጂ ለእድሜ ማራዘሚያው ግን ተጠቅሞበታል።
በአጠቃላይ የግል ጓደኝነት ወይስ ቅድስት እመቤታችን? አፋጣኝ ምላሽ ወይስ እመቤታችን በተካደችበት ግለሰብ የሚመራ ቀጣይ ቤተክርስቲያን? ፀረ-እመቤታችን የክህደት ትምህርት የሚሰጥ አንድ ግለሰብ ወይስ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ቀናዒ አመለካከት ያለው ህዝበ ክርስቲያን?
እርግጥ ነው ዋናውን መልስ የምጠብቀው ከራሱ ከአምላካችን ከቅዱስ መድሃኒተዓለም ቢሆንም በተደጋጋሚ ህዝበ ክርስቲያኑ ለሚያነሳው ጥያቄ መልስ ያለመሰጠቱ “ጌታዋን የተማመነች ፍየል……“አይነት ብሂሉን እንዳስብና ከበላይ አካልም ይህንኑ የክህደት አስተማሪ መሳይ መናፍቃኑ ተወካይ አላቸው ብሎ ለመጠርጠር አስደፍሮኛል።ይህ ከሆነ ደግሞ በእመቤታችን እገዛ በመድሃንያለም ፈቃድ ከላይ እስከታች መናዱ አይቀርም! ወሳኙን ሚና ደግሞ አባቶቻችን የማትወጡ ከሆነ እኛው የጉዳዩ ባለቤቶች በእግዚያብሄር ፈቃድ ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እንድታውቁት በትህትና መግለፁ ተገቢ ይመስለኛል።
ይህንን ጉዳይ ወደ ሚዲያ ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን መዋቅር መኬድ ያለበት ድረስ የተሄደና እስካሁን ተጨባጭ መልስ ባለመገኘቱ ምዕመኑ ጠንከር ያለና የማያዳግም እርምጃ ከመውሰዱ በፊት አባቶቻችን ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡት በድፍረትም ቢቆጠርብኝ ለማሳሰብ ነው።ይህ ካልሆነ ግን የሚሰማው አባት እንደሌለው አውቆ ሃላፊነቱን ምዕመኑ ወስዶ ለቤተክርስቲያናችን የሚበጀውን እንደሚያደርግ መገመት አያዳግትም።
ውድ ምዕመናን “በአባቶች ፋንታ ልጆች“ እንደሚባለው በጀርመን የምንገኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ሃይማኖታችንን ለመታደግ በህብረት አንድ ሆነን የእስካሁኑ ይበቃል ማለት አለብን።የግለሰቡ ጉዳይ በጣም ቀላል ነው ይቅርና ወደ ሃይማኖታችን ተመልሷል ከተባለ በሁዋላ የፈፀመው ክህደት በህጋችን መፍረስ ብቻ ክህነት አንዴ ነው በሚለው ብቻ መፅሃፍትን መመርመር፣ ታሪክ ማጣቀስ፣ ፎቶ ማገላበጥ፣ ቪዲዮ መመልከት ሳያስፈልግ ግለሰቡን የማገድ እርምጃ ለመውሰድ ቆራጥነት ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ምዕመናን ታዛዥ የምንሆነው የሚሰማን አባት እንዳለን እስካመንን ብቻ ነው!
አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈፀመኝ አምላክ ምስጋናው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ ይሁንልኝ።ቅዱስ እግዚያብሄር አፅራረ-ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን! ለአባቶቻችንም በቤተክርስቲያናችን ላይ ከመደራደር ታቅበው ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲሰጡን ይዘዝልን አሜን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር! አሜን!!!

Hagos said...

sorry for writing this message again and again. we are so ashamed on our religious fathers. because they do not want to address our historical questions. anyways, we urge our religious fathers to give us a quick response for our real and tangible question in this manner. indeed, gedamu demsash is a pastor who hates our Saint Virgin Mary, our Orthodox Church, and its Dogma! so,if our religious fathers do not want to give us a very best decision regarding this issue. we(all Ethiopian Orthodox Tewahedo followers) will going to take a fruitful action. May God bless us and our beloved Orthodox religion.

here is the Germany`s translation.

sorry für das Schreiben dieser Nachricht wieder und wieder. wir sind so beschämt auf unsere religiösen Väter. weil sie nicht wollen, um unsere historische Fragen zu behandeln. Wie auch immer, bitten wir unsere religiösen Väter, um uns eine schnelle Reaktion für unsere echten und greifbaren Frage in dieser Weise. In der Tat ist gedamu demsash ein Pastor, der unsere Heiligen Jungfrau Maria, unsere orthodoxe Kirche und ihre Dogmen hasst! ja, wenn unsere religiösen Väter nicht wollen, um uns ein sehr beste Entscheidung in dieser Frage errichen. wir (alle Äthiopisch-orthodoxen Tewahedo Anhänger) gehen wird, um eine fruchtbare Maßnahmen zu ergreifen. Gott segne uns und unseren geliebten orthodoxen Religion.

Demesew from Cologne/Germany said...

እኔ በምን ቋንቋ እንደምናገረው አላውቅም።ናሆም የተባለው ሰው ጀርመን ውስጥ ያለውን ችግር ቁልጭ አድርጎ በፅሁፉ አስፍሮታል።መናፍቁ ፓስተር በእውነት ወጊድ ሊባል የሚገባው ይሁዳ ነው።እኔ ምንም አይነት ቃላት ብጨምር ናሆም ካለው ውጭ መናገር ስለማልችል እባካችሁ ደጀሰላማውያን የናሆምን ፅሁፍ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ለሚገኙት አባቶች ብታደርሱልን ችግራችንን እንዳቃለላችሁልን እቆጥረዋለሁ!እግዚአብሄር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ይባርክልን!ከፀረዎቿም ይጠብቅልን።አሜን

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን በቅድሚያ እግዚአብሔር ይስጥልን የጀርመንን ቤ ክ ችግር በመዳሰሳችሁ ገዳሙም ሆነ ዶክተሩ ሁለቱም መናፍቅ ናቸው ነገር ግን ደፍሮ ዶክተሩን እንዲህ ኖት የሚላቸው ስለጠፋ ነው እንጂ እኔንስ እየገረመኝ ያለው የጳጳሱ ነው  መናፍቅ ስለ መሆኑ ከምዕመናን ተቃውሞ እንደቀረበበት እያወቁና  እየሰሙ መጋቢ ሀዲስ ብለው የማይገባውን ማዕረግ መስጠታቸውና በቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ላይ እርሳቸው ቁጭ ባሉበት መናፍቁ ካሰለጠናቸው የሴት ሐዋርያ አንዲቱ ተነስታ በዓውደ ምህረት ስታስተምር እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት በሌላውም አጥቢያ  እንዲለመድ ማበረታታቸው ብቻ ነው

Anonymous said...

ችግሩ ያለው ቄስ መራዊ ጋር ነው ከ 30 አመት በፈት አብረው የሚያካሂዱት ተግባር ነው እስቲ ስለ እርሱ ወይም ስላለው ሁኔታ ይናገሩ ፦ መስመር ላይ ይገናኛሏ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)