May 8, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ተካሄደ


Photo: Courtesy of  Anke Wagner 
  •  “የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና መጠበቅ ነው፤ ስለ ሃይማኖት መጠበቅና ስለ ምእመናን ሕይወት መጽናት የማይነጋገር ሲኖዶስ ከተራ የመንደር ስብሰባ ተለይቶ አይታይም” /ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ/ 
  • ፓትርያሪኩ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱና በልማት ኮሚሽኑ ስም በተንቀሳቃሽ እና በቁጠባ ሒሳብ የተመዘገቡ የባንክ ሒሳብ አንቀሳቃሾችን በተመለከተ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ያስተላለፉት ጥያቄ ከጉባኤው አነጋጋሪ አጀንዳዎች አንዱ እንደሚኾን ይጠበቃል

·         የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቅዱስ ሲኖዶስ ለኮሚሽኑ በሰጠው መምሪያ መሠረት የፓትርያሪኩን ጥያቄ ያገዱ ሲኾን ፓትርያሪኩ በበኩላቸው ብፁዕነታቸው “የቀደመው ዐይነት [የ2001ዱ] ሁከት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሱ ነው” የሚል ክስ ለመንግሥት መጻፋቸው ተሰምቷል
·         ቅዱስ ሲኖዶስ በገዳማት ይዞታና በመነኰሳት መብት መከበር ላይ ቤተ ክርስቲያን ያላትን አቋም እንዲገልጽ ተጠይቋል
·         የዋሽግንተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ልኡካን “ቃለ ዐዋዲው ይከበር፤ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ” በሚል አቡነ ፋኑኤልን የተመለከቱ አቤቱታዎችን ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል
·         ማኅበረ ቅዱሳን በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ዋና ሓላፊ ላይ የተወሰደውን ሕገ ወጥ ርምጃ ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ እንዲወስንበት ጠይቋል፤ ማኅበሩ በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾመው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ጋራ ለመሥራት እንደሚቸገር ገልጧል
 (ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 30/2004 ዓ.ም፤ May 8/2012)፦ ፍትሕ መንፈሳዊ በአምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በሚያዝዘው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳል፡፡ የመጀመሪያው ጉባኤ በየዓመቱ ጥቅምት 12 ቀን ሲኾን የሁለተኛው ጉባኤ ደግሞ ትንሣኤ በዋለ በ25ው ቀን /በርክበ ካህናት/ የሚካሄደው ነው፡፡ የዘንድሮው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት ዛሬ፣ ሚያዝያ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል፡፡
የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብሩን አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስን ጨምሮ 26 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዐቱ ተከናውኗል፡፡
መርሐ ግብሩ የጸሎቱን ሥነ ሥርዐት በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይገልጸዋል፡-
ሀ. ዳዊት
ለ. ውዳሴ ማርያም ይደገማል፤
ሐ. አድኅነነ ሕዝበከ ይባላል፤
መ. መልክአ ማርያም ደርሶ እግዝእትነ በዜማ ይሰማል፤
ሠ. መልክአ ኢየሱስ ተደግሞ ኢትግድፈነ የሚለው በዜማ ይደርሳል፤
ረ. መስተብቍዕና ሊጦን ዘሠርክ አምላክነ ዘዲበ ኪሩቤል ትነብር የሚለው ይዜማል፤
ሰ. ዘበእንቲአሃ ለቤተ ክርስቲያን ተጸፋዕከ በውስተ ዐውድ የሚለው ደርሶ መሐረነ አብ ተብሎ አጭር እግዚኦታ ይደርሳል፤
ሸ. ምስባክና የወንጌል ምንባብ ከተሰማ በኋላ በአራራይ ዜማ ቅዱስ ተብሎ የሠርክ ኪዳን ይደርሳል፡፡

የመክፈቻ ጸሎቱ በተጠቀሰው ቅደም ተከተል ከተከናወነ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ቃለ ምዕዳን አሰምተው ቡራኬ እንደሚሰጡ የተገለጸ ቢኾንም ትምህርቱ የተሰጠው በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ - ሰላሌ እና የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡ 
ብፁዕነታቸው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ቁ. 18 ላይ በተመሠረተውና ለዕለቱ መርሐ ግብር ተስማሚ አድርገው ባቀረቡት ትምህርታቸው “ልዑል እግዚአብሔር በማይወሰን ቸርነቱ ለዚህ ዕለትና ሰዓት ካደረሰን ዘንድ የምናስተላልፈው መልእክት÷ አባቶቻችን ሐዋርያት፣ ሠለስቱ ምእት፣ ሊቃውንትና መምህራን እንዳስተማሩን የምንከተለው የቀናውን የሃይማኖት መንገድ ነው” የሚል እንደ ኾነ አመልክተዋል፡፡ ከዚህም ጋራ በማያያዝ ምሥጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ጥምቀትን፣ ምሥጢረ ቍርባንንና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን ለሁሉ በሚረዳው ፍሰትና ትይይዝ እያብራሩ አቅርበዋል፡፡ በተለይም የምሥጢራት ሁሉ ጉልላት በኾነው የምሥጢረ ሥጋዌው ክፍል “ወልደ እግዚአብሔር፣ ቃለ እግዚአብሔር በተለየ አካሉ በተወላዲነት ግብሩ ንጽሐ ጠባይዕ ካላደፈባት ንጽሕት ድንግል እመቤታችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተወልዶ ሰው ኾነ፤ በዚህም የሥጋ ገንዘብ ለቃል፣ የቃል ገንዘብ ለሥጋ ኾነ” በሚል አጽንዖት የሰጡባቸው ኀይለ ቃላት ወቅታዊም መልእክት እንዳላቸው ብዙዎች የተግባቡባቸው ናቸው፡፡
ብፁዕነታቸው ዕለቱን አስመልክቶ ሲያስረዱ “ሲኖዶስ ማለት የኤጲስ ቆጶሳት፣ የጳጳሳት ጉባኤ ነው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና መጠበቅ” እንደ ኾነ ገልጸዋል፡፡ የዘላለም ሕይወት፣ ድኅነት የሚገኝባትን የቀናችውን ሃይማኖት የመጠበቅ ሓላፊነት ከእግዚአብሔር የተሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ከሌላው ተለይቶ ቅዱስ የሚባለው ከእግዚአብሔር በተቀበለው አደራ ሃይማኖት የሚጸናበትን፣ የሰው ልጆች ሕይወት ወደ እግዚአብሔር የሚቀናበትን፣ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት የሚሰፋበትን ሥራ በጥንቃቄ መፈጸም ስለሚገባው መኾኑን አስረድተዋል፡፡ በተፃራሪው ስለ ሃይማኖት መጠበቅና ስለ ምእመናን ሕይወት መጽናት የማይነጋገር ሲኖዶስ ከተራ የመንደር ስብሰባ ተለይቶ እንደማይታይ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል - “ቅዱስ ሲኖዶስ በተሰበሰበ ቁጥር አጀንዳ ቀርጾ፣ ርእስ አድርጎ የሚነጋገረው የሃይማኖት ነገር፣ የምእመናን ሕይወት ያለበት ጉዳይ በመኾኑ ያስጨንቀዋል፡፡ ይህን ችላ ካለ ግን ቅዱስ አይደለም፡፡”
ብፁዕነታቸው በመጨረሻም ዛሬ አባቶችም ምእመናንም ተሰብስበን “ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ” ያልነው ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን አደራ ለመፈጸም በጸሎት መጠየቅ አስፈላጊ መኾኑን በማስታወስ “ጉባኤውን ፍጻሜውን ያሳምርልን፤ ሥራችንን የተቃና እንያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን” በማለት ትምህርታቸውን አጠቃለዋል፡፡
በነገው ዕለት የምልአተ ጉባኤውን የመወያያ አጀንዳዎች አርቅቀው የሚያቀርቡ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ኮሚቴ በመሠየም ሥራውን የሚጀምረው የቅዱስ ሲኖዶሱ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች አፈጻጸም ይቀርቡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከእኒህም መካከል የቃለ ዐዋዲው ማሻሻያ ሐሳቦች፣ የቤተ ክህነቱ መዋቅር ጥናት፣ በአባ ሰረቀ እምነት ሕጸጽ፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅነት መረጃ የቀረበባቸው ግለሰቦች እና ማኅበራትን አስመልክቶ የተቋቋሙት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አጣሪ ኮሚቴ እና የሊቃውንት ጉባኤ ሪፖርቶችና የውሳኔ ሐሳቦች ይገኙባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የቤተ ክህነቱ ምንጮች በምልአተ ጉባኤው አነጋጋሪ ኾነው ሊነሡ ይችላሉ ያሏቸውን ሌሎች አጀንዳዎች ጠቁመዋል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

17 comments:

Anonymous said...

ከዚይ ስብሰባ ለቅድስት ቤተክርስቲያን እና ለእውነተኛ ልጆቿ ምንም አልጠብቅም በበኩሌ። ቅዱስ ሲኖዶስ ጥርስ የሌለው አንበሳ ከሆነ ቆይቷል። ውሳኔ አያስተላልፍ ቢያስተላልፍም ተፈጻሚነቱን በውል አይገመግምም። አምላክ ሆይ ስለቸርነትህ ብለህ ተዋህዶን አስባት።

Anonymous said...

I do not expect anything at all from this corrupt Fathers 00000000000000000000000000000 this is how much i expect from them. They are a descrace for our church and for our country

Anonymous said...

Please guys don't frustrate, we should consistently pray and I believe God will not let us down.

Anonymous said...

zero*zero. Whenever the Patriarchate is not deliver himself before the Holy Spirit, no new resolution and decision is expected. We expect a miracle, only if God in His Mercy and Love for His Holy Church intervene and soften the heart of Aba Paul and his group. May God the Father, the Son and the Holy Spirit give all the power and wisdom to His non-corrupted servants, few members of the Holy Synod and protect the Holy Church from the wicked wishes of all adversaries and heretics including those attending the council.

Anonymous said...

Lets see what will they say about the patriarich's statue after they passed the verdict to demolish it.

lamelame europe said...

ara tasefa anekorate ewenatone ahone abatoche yalayote yemaselangale.
YAEWENATE AMELAKE EWENATE ENDENAGARO ANEDABATE SETACHAWE.
AMEN

Gofa Geberal said...

we were expecting to much from them, always disapointment, always always, so this time I don't expect any thing, how come Ye Waldeba gedame issue is not one of the topics, isn't it very urgent matter. Every thing else should wait until the waldeba issue is over, those fricken idiots are destroying the gedame, and abussing the fathers, some of the pops are even lived theres, can't they ask the holy sinode to do somthing, wooooooo, why talking about money corruption, forget that please save our gedam and kedusane from this suffering, if any father who is not be able stand for this historical gedam, we shouldn't call him father. what is the point, how come they can sleep peacfully, when some one is destroying the gedam at this time. Please the senodos ajenda should be only to save our gedam and fathers.

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

ይህ ወቅት ለቤተ ክርስቲያናችን ህልዉና መከበር አስፈላጊዉ ምላሽ የሚሰጥበት ወሳኝ ወቅት ነዉ። ቅዱስ ሲኖዶስ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቅድሚያ መስጠት ያለበት አጀንዳ ቢኖረዉም የምእመናንን ጥያቄ መመለስ አለበት እላለሁ። እርሱም በቤተ ክህነት አካባቢ ያለዉ ሙስና ዘረፋ እና የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ነዉ። ጥርት ባለ መልኩ መጽዳት ያለበት። ምእመኑ ለሃይማኖቱ በወኔ በተንቀሳቀሰበት ወቅት በምእመኑ ሕይወት ላይ ወኃ መቸለስ ተገቢ አይሆንም። በእግዚአብሔርም ዘንድ ያስጠይቃል። አሁን የምንጠብቀዉ የአባ ጳዉሎስ፣የአቡነ ገሪማ እና የአቡነ ፋኑኤል ብሎም የመሰሎቻቸዉ የጨለማ ሥራ መወገድ እንደሚገባዉ ነዉ። ቅዱስ ስኖዶስ ከትላንት ተሞክሮዉ ተምሮ አባ ጳዉሎስ እንደ ልማዳቸዉ በማግሥቱ ዉዥንብር እንዳይነዙ አፍ ተልብ ሆኖ ሊከታተላቸዉ ይገባል።

Anonymous said...

Don't say like that you don't have that much moral to call our Fathers WE respect our Fathers and there meeting. They are the highest position to protect our church and follower. God bless our church, our fathers and us.

galela said...

alawekem battame gera yagabale

lele said...

katachale dejeselamoche yatakafaloten abatoche asayone

Anonymous said...

Am stil gone say 00000000000000, i do not expect anything from them they just sit and play poker on the believers mind.i do not only blame Abune Paulos,it is all of them, the reason they don't say anything is,cause they are part of the corrupt group, i mean all papasat.how come one can not spoke about the truth until noe? amazing....

Anonymous said...

+++
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በአንድ ልብ እንዲያስቡ በአንድ ቃል እንዲናገሩ በኃይልህ እርዳቸው::

አሜን

danf said...

BESEW SEWEGNAW AGEMAMETE KE SINODOS SIBSEBA MINIM YEREBA NEGER LEBETEKRSTIAN ALTEBIKIM HONOM NEGER BE IGZIABHER CHERNET LAWUNET YEKOMU ABATOCH AND LAWUT YAMETALU BIYE TESFA ADERGALAW

Anonymous said...

You said " Am stil gone say 00000000000000, i do not expect anything from them they just sit and play poker..."
መጀመሪያ የእምነቱን ምንእነት ማወቅና መረዳት አለብህ(ሽ)። አባቶች የሚያገለግሉ እግዚአብሔርን ነው፤ እንደ ፍርድ ቤት ዳኛ አንተ የፈለግዅውን አይፈጽሙም።

asbet dngl said...

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በአንድ ልብ እንዲያስቡ በአንድ ቃል እንዲናገሩ በኃይልህ እርዳቸው::ይህ አባባል መልካም ነው::ከመልካም አባባል ጥሩ መንፈስ አለ ብየ አምናለሁ::ምንም እንኳን የምናየው የምንሰማው ሁሉ ትእግስት አስጨራሽ ቤመስልም "ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም "ይባላል:: ደግሞም እስኪ ጥንታዊ የሚባሉት የክርስትያን አገሮች እንመልከት ዘንድር የትኛው አገር ነው በሰላም የሚንቀሳቀስ ያለ:: አባቶች ሲበረቱ ምእመን᎓ ምእመን ሲበረታ አባቶች ሲል በዚህም በዚያ ትርምሱ የኛ አገር ብቻ ሳይሆን የአለም ነው ማለት ይቻላል:: ይህም ስል እናንተ ሳታውቁት ቀርቶ ስለግብፅ ወይም ስለሮም በተክርስትያን ችግር ላትት ፈልጊ ሳይሆን"ችግር አለ ችግር የለም አይባልም ነገር ግን ችግሩ ችግር ይፈታዋል" አይዞ ችሁ:: ለማለት ነው::
የድንግ ልጅ ᎒ የቀራንዮው ንጉሥ ፀሐይና ጨረቃ ይስጠን:: አሜን

Anonymous said...

EGIZIABHER MELKAM ENA EWNET ENDIASASIBACHEW YADERGLEN. YEGEDAMACHINNEN HUNETA EGIZIABHER YETEBEKELEN. LETARIK YAKOILEN .EMEBETACHEN TIRDAN AMEN.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)