May 15, 2012

የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣን ጽሑፎች የሚመረምር ኮሚቴ ተቋቋመ


·        አባ ጳውሎስ በጉባኤው ላይ እንዲቀርቡ ለተጠሩት አዘጋጆች በተፈለጉበት ጉዳይ ዙሪያ ሲመክሩና ነገር ሲያስጠኑ አምሽተዋል፤ አዘጋጆቹን አቅርቦ ለመጠየቅ የነበረው ዕቅድ ተሰርዞ እንዳይገቡ ተደርገዋል::
·        “እኔ የግል ቤት የለኝም፤ መኪና የለኝም፤ ሲኖዶሱ መወሰንና ርምጃ መውሰድ አለበት” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)
·        “ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው፤ መወሰን አለብን” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 7/2004 ዓ.ም፤ May 15/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ዛሬም ለተከታታይ ሁለተኛና ሙሉ ቀን በዜና ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ላይ ሲወያይ የዋለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ
የጽሑፎቹን ይዘት ከሕግ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር መርምሮ ውሳኔ የሚያቀርብ ሰባት አባላት ያሉት የምሁራን፣ ባለያዎችና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ አቋቋሟል፡፡ የኮሚቴው አባላት ኾነው የተመረጡት ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው፡፡ የሕግ ባለያዎቹና ምሁራኑ ደግሞ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ ዶ/ር ተክለ ሃይማኖት አንተነህ፣ አቶ ፊልጶስ ዓይናለም እና አቶ በፍርዱ መሠረት ናቸው፡፡


ኮሚቴው የጋዜጣውን ጽሑፎች ከደረሰለት ለዐርብ አልያም እስከ ቅዳሜ፣ ግንቦት 10/11 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡


ተጨማሪ ዜናዎችን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

8 comments:

Gebre Z Cape said...

አምላክ ይህ ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ እየራቀው ነውና አንተ አትለየው:: በየጊዜው የምንሰማው የአባቶቻችን ክርክር: ንትርክ አንገት የሚያስደፋ ሆናል::

ከሁለት ቀን በፊት ከወጣው ዘገባ ጋር የማይጣጣም ኮሚቴ የተዋቀረ ይመስለኛል:: ምናልባት ሌላ የማላውቀው ነገር ከሌለ እንጂ:: እንደ እኔ ከሆነ ግን: አቡነ ማርቆስ በኮሚቴው ውስጥ መግባት ነበረባቸው:: (መንፈስ ቅዱስ እርቆን ካልሆነ በስተቀር)::

"ከሻሂ ዕረፍት መልስ ጋዜጣው ምን እንደጻፈ፣ ስለምን እንደጻፈ ሊያውቅና ሲቆጣጠርም ይገባ የነበረው የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ስለ ጋዜጣው ዝግጅት ምንም እንደማያውቁና ሌሎች አጀንዳዎች ወደ ኋላ ቀርተው ምልአተ ጉባኤው በዚሁ ጉዳይ እንዲነጋገር ይጠይቃሉ፡፡" Dejeselam May 13, 2012


አምላክ እባክህን አትለየን:: ለእያንዳንዳችን አስተዋይ ልቦና ስጠን::

Anonymous said...

What is going on? Ere yegud new. Lemin hezebe christianu ayewetamina yih neger yekum yemil meleeket ayetelalefem. Ere beza, ere beaza, egziooooo. Koy men eskimeta new yemitebekew? Manes new yemitebekew? Shemagelochun letasfegu new ende, enga yalabat enkir? seweyew eko libe tenesetuachewal ayesemum, egna enewetaena yasfegun. Deje Selamawian, please let the laity come out of his living quarter and gather in Arat Killo to die with the good shepherds for the Holy Church of Christ the Lord! yemin metashet new. MK debedabe lemen yetsatsafal, there is no need to send a reply to that letter of heretic. Just write a letter to all concerned to come out for a demonstration. beka, mefetehew yehe becha new!

Anonymous said...

ሰላም ደጀ ሰላሞች፣እንደምን አላችሁ? ቤተ ክርስቲያናችንን ለመታደግ ብላቹ ለመታደርጉት ጥረት ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ፣ለወደፊቱም ብርታቱና ያድላቸሁ እያልኩ:አምላከ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከመጠን በላይ ከፍቶ ከመጣ መከራና ስቃይ እንዲታደግልን በአባትነት ርህራሄው በቃቹ ይበለን::

ደጀ ሰላሞች, ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን እየፈረሰች እያየ ቀኑ ቢያልቅ ማራዘም አይችልም እንዴ ፣ምነው የአባቶቻችን ጉባኤያት/በ 325 ዓም የተደረገውን ጉባኤ ኒቂያ፣ በ 381 ዓም የተደረገውን ጉባኤ ቁስጥንጥንያ እና በ 431 የተደረገውን ጉባኤ ኤፌሶን/ከዚህ ይተናነሳል አሁን ያጋጠማት? እነሱስ እስከ መጨራሻ አልሞቱላትም፣..... ቀኑን አርዝመው ቤተክርስቲያናችንን አይታደጔትም አባቶቻችን? ፓትሪያርኩና የግብር ልጆቻቸው እቅዳችውን እንዲያሳኩ ይኅው እያልናቸው አይደለም? አላማቸውን እኮ አሳኩ፣!!!!!!

እባካችሁ በዚህ ዙሪያ ሃሳብ አካፍሉን.........

እግዚአብሔር አምላክ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን፣ለናንተም ብርታቱን ያድላቸሁ::አሜን::

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

If you are Christians, please respect the word of God which says, "negerachihu Ewnet bihon ewnet...".
You are tryng to tell us the conspirators behind the "Zena Betechristain" news are - Abune Fanuel & his followers...

How on earth do you think us belive you on this?? The writing is fully against him when it comes to his properties & nationalities as both issues are the focus of the news.
Yenante degafi Papasatoch endene Aba Abrham yalut tikm sileteneka bich - beAbune Fanuel malakek Hatyat new. Ewnetawn yemitakut yimeslegnal.
Kudos to Megabe-Mistir WeldeRufael for bringing the very important issue to the forefront!! Hige-beteChristianu kalteshashale, yichi betechristian benegede papasatna bene MK balu poletikegna mahberat metfatwa new.
Egziabher betun Yitebik!!

Anonymous said...

Wanaw meftegna yehe sayhon YE TEHADESOHAWUYAN GUDAY NEWu. Aktacha bemaskeyer ena bembtebet ye 2001dun medgem yeflegalu. Ewnut Teretalech!

Anonymous said...

Aye guddddd...muslimochi mebtachewin taglew bemetenu weynen astenefesut.... Egna meche yihon sile-haymanotachin yeminikom. Ayeeee

Anonymous said...

Ye abune pawlosen ymotqn msmat nafqn yesachwe erft aymeslgnme mot new erftma le kedusan new

Anonymous said...

Ye abune pawlosen ymotqn msmat nafqn yesachwe erft aymeslgnme mot new erftma le kedusan new

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)