May 23, 2012

የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 15/2004 ዓ.ም፤ May 23/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያካሒድ የሰነበተውን ጉባኤ ባለ አሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ። ዝርዝሩን እንመለስበታለን።

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!!
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡ 

22 comments:

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን ምን እንላለን ዋጋችሁን በሰማይ ነው የምታገኙት ባላችሁበት እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ ኪዳነምህረት ትርዳችሁ
መቼም ዘንድሮ ለየት ያለ ነበር የተሃድሶና የመናፍቃኑ ጦርነት ቀላል አልነበረም እስቲ ይሁን። የዕርገት በዓልም በሰላም ለማክበር ያብቃን ሁላችንም በቤተ መቅደሱ እንድንቆይ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን።

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን

yeaquame megelechawe yewetawe sebesebawe kemalequ befite newe endea?

melese beasechekuaye efelegalehu

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ። እንዴት ነው በመግለጫው አባይ ተነስቶ ዋልድባ የተረሳው? ወይንስ ቅዱስ ሲኖዳሱ የዋልድባ ጉዳይ አይመለከተውም? ነው እኔ ሳላየው አለፍኩት? አይመስለኝም። እስኪ ደጀ ሰላሞች በጉዳዩ አንድ በሉበት። በቅድሚ አመሰግናለሁ።

Anonymous said...

temesgen esey elelelelelele. enbayem eyewerede new. Abatochachin rejim edme yistilin amen

Alemayehu said...

Amlak hoy endahunu hulu ewnetegna abatochachinen abertalin

Anonymous said...

The news has lately become source of unhappiness and depression. It refreshing to get this kind of ones every now and then.

It is my prayers that God will bless us with more of this kind of news in the future. Amen.

Anonymous said...

same old same old!

Anonymous said...

Dear Brothers/sisters (dejeselam)

Many thanks for all your efforts. What you have been doing is an examplary work that demonstrates how the true sons/and daughters can do to the church who seek the help of her children. God Bless you more and let the intercession of our mother and saints be with you. Please keep it up. The higher the challenge to the church is the more it needs our support.

Anonymous said...

Dear Brothers/Sisters,

Have you noticed the declaration ? it s dated ginbot 10 while the end of the holy synod meeting is to day (ginbot 15). What does this mean ? We need answer.

And the other point why is the guy's " the patriarch" put under the declaration ? probably because he drafted and declared it in the name of the holy synod even before the end of the meeting ? This is funny.

Anonymous said...

For me it is prepature end ! Many decisions are made but, their implementaion is not always there as long as the stambling block the so called patriarch and his advisor Elizabel are there. Hence, I feel that the holy synod must have discussed about implementaion problem encountered so far including demolition of the statue, reckless involvement of the guy on every church affair beyond his mandate. And the cover he gives to the so called " tehadiso".He had to be given a warning letter/statent.

The holy synod has underweighed the role of "aba" Serqe in his role as a pivot or axis of " Tahadiso" in the church.

Most of the people who are condemened us Menafiq and declared to be outcasted are already known and that is not a big success unless the gain in making it official. The holy synod had to give due attentions to the mites 'qinqin' who windowdress like memebrs of the church but are brain children of the decayed protestant.

The north America dioces and the gang group memeber " Aba Fanuel" and his accessory " Hailegiorgis" had to be discussed. And I feel that the north American christains must stand firmer than before against this guy and his club. The church has no place for these kinds of pigs and blood sucking leeches.

I am not clear if the holy synod has decided to reinstate Aba Hiruy or not !? I know there was an idea but I could not understand the final.

If enqubahir is there, I take it as the holy synod rescued MK but made the vast sunday schools vulnerable to weak leadership of the guy. And I suggest the sunday school youth must unite and defend the fact that the sunday school department is not waste bin or garbage spot for incapable and corupt menafiks like enqubahiri.And mk must not stop struggling for the betterment of the sunday scholl department that is expected to lead millions of church youth.

I am sorry that the holy synod never discussed about waldiba while it is the at most church monastry and is under difficult situation !!!

Thanks to the information you provided to us, if you ask me if about the success of the holy synod meeting.

The most important thing is that the Our fathers have demonstrated their unity on the church affairs except Guys like " patriarch, aba Gerima, aba fanuel" the latter two blind supporters and corrupt members of the gang club led by the former.

I was wondering why "Aba Gerima" was in every committee established !Just as informer of the " Patriarch " on what shall go in each committee. If I were " aba gerima" I prefer death rather than playing this role.


Finally, I thank you dear brothers/sisters. And please keep it up. God be with u.

YeAwarew said...

Dear DS:
thank you for the report. Big fan. Remember to stay focused on the truth and true reporting. nothing more, nothing less.
The footing from MK, Sound is OK but very poor video. The recording person must be given basic Video Recording lesson, b/c this is really not good, not to be mean.

Cher yaseman,
yeAwarew

Anonymous said...

መግለጫው፡የአባ፡ጳውሎስን፡አድብቶ፡የማጥቃት
ና፡የማዳከም፡ዘዴ፡እንደገና፡አረጋግጧል።አድበስ
ብሶ፡ማለፍ፡ማለት፡እንዲህ፡ነው።ያለ፡ጥርጥር፡አ
ባ፡ገሪማና፡አድመኛው፡ወራሪ፡ቡድን፡አሁንም፡አ
ጥፊ፡ሥራውን፡እየሠራ፡ነው።

አባቶች፡በዘንድሮው፡ጉባኤ፡ያደረጋችሁት፡ተጋድ
ሎ፡ቀላል፡አይደለም።ሙሉ፡መፍትሔ፡አግኝተና
ል፡ባንልም፣በፅኑ፡ትኩረት፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ለመ
ታደግ፡ባደረጋችሁት፡ጥረት፡ከወደቅንበት፡በመነ
ሳት፡ላይ፡ነን።

ልንቆም፡ነው፡ስንል፣በአባ፡ጳውሎስ፡በተሰጠው፡የተ
ጋድሏችንን፡ውጤት፡የማያንጸባርቅ፡መግለጫ፡እና
ዝናለን!

በአባ፡ጳውሎስ፡የተሰጠው፡መግለጫ፡የእርሳቸው፡
የግል፡ዓላማ፡መግለጫ፡እንጂ፣በቅዱስ፡ሲኖዶስ፡ተ
ፈርሞ፡ያልወጣ፡በመሆኑ፡በምዕመናን፡ዘንድ፡ተቀ
ባይነት፡ሊኖረው፡አይችልም!

መግለጫው፡የቀስ፡በቀስ፡ግደለው፡ዓይነት፡መርዝ፡
እንጂ፡በኢኦተቤክ፡"ቅዱስ፡ሲኖዶስ፡"ስም፡ሊወጣ፡
የማይገባውና፡የዘንድሮውንም፡ሲኖዶስ፡ተጋድሎ፡የ
ማያንጸባርቅ፡መሆኑ፡ግልጽ፡ነው!

ሰውዬው፡ወርደው፡ወርደው፡የበጋሻውን፡ደብዳቤ፡
ማንበባቸው፡የሚያሳፍር፡እና፡የእራሳቸው፡ጉዳይ፡
መሁኑ፡በግልጽ፡እንዲታይ፡አስችሏል።

ሲኖዶስ፡በጌታቸው፡ዶኒ፣አባ፡ሰረቀ፡እና፡በጋሻው፡ላ
ይ፡ቆራጥና፡ወሳኝ፡አቋም፡ባለመውሰዱ፡እናዝናለን።
በቀጠሮ፡ያደረው፡ማስረጃ፡ጠፍቶ፡ወይስ፡አንሶ?እነ
ዚህ፡ሦስቱ፡ከነስጦታው፡የሚለዩት፡የጣዖቱን፡ድንጋ
ይ፡ያቆሙና፡በጣዖቶ፡የታቀፉ፡በመሆናቸው፡ለመሆ
ኑ፡አንዳችም፡ጥርጣሬ፡የለንም።

ዋናው፡የ"ተአብሶ"አራማጅ፡አባ፡ጳውሎስ፡በመሆና
ቸው፣ይህም፡ከፍተኛ፡የሃይማኖት፡ሕፀጽ፡አላንዳች፡
ተገቢ፡ውሳኔ፡በነካ፡ነካ፡ብቻ፡ተድበስብሶ፡ታለፈ!

የአባ፡ሰረቅም፡ቀና፤ደፋ፡ማለት፡ከዚሁ፡እከከኝ፡ልከ
ክህ፡ጋራ፡የተያያዘ፡ለመሆኑ፡በቂ፡ማስረጃዎች፡አሉ!
አባ፡ሰረቀ፡"ጳጳስ"ሆኖ፡ለመሾም፡ያላደርጉትና፡ወደ
ፊትም፡የማያደርጉት፡ጉድ፡የለም!

ውንጀላውና፡አሳልፎ፡የመስጠቱ፡ክስ፡ሁሉ፡ከዚሁ፡የ
ተሐድሶ፡መናፍቃን፡መፈንቅል፡ጋር፡የተሳሰረ፡እን
ደሆነ፡እናውቃለን!ለዚህም፡ነው፡እስካሁን፡ድረስ፡አ
ባ፡ሰረቀ፡ቤተ፡ክህነት፡መሽገው፡ተዋሕዶን፡እንዲዋ
ጉ፡በበላይ፡አይዞህ፡ባያቸው፡የሚደገፉት!

መግለጫው፡በሲኖዶሱ፡ጽሕፈት፡ቤት፡መሰጠት፡
ነበረበት!ይህ፡ሆኖ፡ቢሆን፡ኖሮ፣ዋልድባ፤ዝቋላ፡አ
ቦና፡ደብረ፡አሰቦት፡በዋነኛነት፡ይዳሰሱ፡ነበር!ሌሎ
ችም፡እንደ፡ስልጢው፡የቅድስት፡አርሴማ፡መቃጠ
ል፡ጉዳይ፡ውሳኔ፡ይሰጥባቸው፡ነበር!

በእነ፡አባ፡መላኩ፡በኩል፡በዜና፡ቤተ፡ክርስቲያን፡አ
ማካኝነት፡የተፈጸመው፡ወንጀል፡በሚገባ፡ሳይወገዝ፡
በአባ፡ጳውሎስ፡መግለጫ፡ጠለላ፡ሊታለፍ፡ቻለ!

በግፍ፡በሲኖዶስ፡ከተሰጣቸው፡የሰንበት፡ት/ቤቶች፡
መምሪያ፡የተባረሩት፡መልአከ፡ጽዮን፡አባ፡ኅሩይ፡
ጉዳይና፣ሲኖዶስ፡የማያውቀው፡መናፍቁ፡ዕንቁ፡
ባሕርይ፡ጉዳይም፣የአድመኞቹን፡ጉድ፡የሚያጋል
ጥ፡በመሆኑ፡በመግለጫው፡ሳየጠቀስ፡ተድበስብሶ፡
ታለፈ!

ዕንቁ፡ባሕርይ፡በሕገ፡ወጥ፡መንገድ፡ከያዘው፡ቦታ፡
እንዲወገድ፡አጥብቀን፡እንጠይቃለን!

አባ፡ኅሩይ፡በግፍ፡ወደ፡ተነጠቁት፡መምርያ፡እን
ዲመለሱና፡ቅን፡አገልግሎታቸውን፡እንዲያበረክ
ቱ፡በደሉም፡እንዲታረም፡አጥብቀን፡እንጠይቃለን!

የቀሲስ፡ዶ/ር፡መስፍን፡ተገኝ፡አቤቱታም፡የአባ፡መ
ላኩን፡ወንጀል፡የሚያጋልጥ፡በመሆኑ፡አላንዳች፡ው
ሳኔ፣በመግለጫውም፡ሳይጠቀስ፡ተድበስብሶ፡ታለፈ!

ችግሩን፡ጠንቆል፡ጠንቆል፡አደረግነው፡እንጂ፡ጠ
ራርጎ፡የመጣሉ፡ተጋድሏችን፡ገና፡አልተሳካልንም!
ጥሩ፡እርምጃዎችን፡ተራምደናል።የአባቶች፡ውሳኔ
ዎች፡ሥራ፡ላይ፡እንዲውሉ፡አሁንም፡በተጋድሏች
ን፡እንጽና!ፋታ፡መስጠት፡አይገባንም!

እስከ፡መጪው፡ጥቅምት፡ድረስ፡የአባ፡ጳውሎስ-አባ፡ገሪማና-አባ፡መላኩ፡ሰዎች፡አፍራሽ፡ሥራቸው
ን፡እንደሚገፉበት፡ጥርጥር፡የለንም!

እኒህ፡የችግሮቻችን፡ሁሉ፡ምክንያቶች፡እስካልተወ
ገዱ፡ድረስ፣ቤተ፡ክርስቲያናችን፡በታላቅ፡የጥፋት፡
ወጥመድ፡ተቆፍድዳ፡ትንገዳገዳለች...!

ብጹአን፡አባቶቻችን፡በዘንድሮው፡ተጋድሏችሁ፡አ
ብረን፡በመቆም፡የደስታችሁም፡ሆነ፡የሐዘናችሁ፡ተ
ካፋዮች፡ነን።ብዙ፡ጠቃሚ፡ጉዳዮችን፡ፈር፡ለማስያ
ዝ፡ባደረጋችሁት፡ጥረት፡ረክተናል።

ሆኖም፣በጠላፊዎች፡የተከበበችውን፡ቅድስት፡ቤተ፡
ክርስቲያናችንን፡ስንመለከት፣እጅግ፡እናዝናለን!
በየገዳማቱ፡የሚደርስብንን፡በደል፡ስንመለከት፡እ
ጅጉን፡እናዝናለን!በዋልድባ፡ቅዱሳን፡አባቶች፡ላ
ይ፡በመፈጸም፡ያለውን፡ግፍ፡ስናስተውል፡እጅግ፡እ
ናዝናለን!በዝቋላና፡በደብረ፡አሰቦት፡የተፈጸመውን፡ጥፋት፡ሁሉ፡ስናስተውል፡እጅጉን፡እናዝናለን!

ይህ፡በመነኮሳት፡ጉባኤ፡"ስም፡"የተሰጠው፡የአባ፡ጳ
ውሎስ፡መግለጫ፣በመነኮሳትና፡በገዳማት፡ላይ፡ስለ
ሚፈጸመው፡የማውደም፡ጥፋት፡አንዳችም፡ቃል፡አ
ለመሰንዘሩን፡ስናስተውል፡እጅጉን፡እናዝናለን!

የአባታችን፡የተክለ፡ሃይማኖት፡አምላክ፡ይፍረደን!
በተጋድሎ፡የጸናችሁትን፡አባቶችም፡ይጠብቅልን!
መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ተዋሕዶ፡ቤታችንን፡ከመ
ናፍቃኑ፡ወረርሺኝ፡ያጽዳልን፤ይፈውሰን!በእናታች
ን፡ቅድስት፡ወንጽሕት፡ድንግል፡ማርያም፡ስም፡እን
ማልዳለን!አሜን!አሜን!አሜን!!!

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Dn hailemichael said...

ፈተና ብበዛም እግዚአብሔር አምላክ በአባቶቻችን አድሮ መልካም ውሳኔዎችን እያስወሰነልን ነው::
ስለተደረገልን ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር አምላካችን ስም ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በፍጥረቱ ሁሉ የተመሰገነ ይሁን::
የእግዚአብሔር ቸርነቱ የእመ አምላክ አማላጅነቱዋ የቅዱሳን ጸሎትና ተራዳእነት ከእኛ ስላልተለየ ነው ይህ የተደረገልን::
ግን አሁንም በዚህ እግዚአብሔርን ከማመሰገን ባለፈ ብዙ በመደሰት መዘናጋት የለብንም:: ማስተዋል ያለብን ቤተክርስቲያናችን ኢጥሙቃንን በማጥመቅ ከበረቱዋ የወጡትን በመመለስ ለመናፍቃን የሐሰት ትምህርት መልስ በመሰጠትና ለሕዝቡ ተደራሽ በማድረግ ዕርቃኑን በማስቀረት በሕዝቡ በማኅበራዊ ሕይወት በሰፊው በመሳተፍ በኢኮኖሚ ችግርና በተለያየ ምክንያት በሞራሉ እየላሸቀ ያለውን ኅብረተሰብእ በመታደግ ወዘተርፈ መገስገስ ስገባት በአስተዳደር ችግርና አንቀዋት በያዙአት የተሐዲሶ መናፍቃን ሴራ እስካሁን በተከላካይ መስመር ላይ መሆኑዋን ነው:: ተከላካይ ደግሞ ብበዛ ግብ እንዳይገባበት ቢያደርግ እንጂ የማግባት እድል የለውም:: ሙከራው ስደጋገምም መግባቱ አይቀርም:: መናፍቃን የምዕራባውያን ባህል አሕዛብ በተቁዋሙዋና በምእመናኑዋ በተደጋጋሚ ጥቃት ብፈጽሙም ተቅዋሙዋ ከውስጥ ባለባት ችግር ምክንያት ዘመኑን የዋጀ ተመጣጣኝ ምለሽ ለመስጠት አለተነሳችም::
እኛ ምእመናን እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ቸርነቱ ሳይለየን ይህን በመሰለ ፈተና ውስጥ በአባቶቻችን አድሮ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ውሳኔ ካስወሰነልን በፈቃደ እግዚአብሔር በምክረ ካህን በመኖር በአካን ምክንያት ወደ እስራኤል ጉባዔ የገባውን ርኩሰት ኢያሱ እንዳራቀ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጭ እንዲንኖር የሚያደርጉንን ነገሮች ማስወገድ ይገባናል :: ያን ጊዜ እኛ ዝም እንላለን ::በአጽራረ ቤተክርስቲያን አድሮ እረፍት የሚነሳትን ዲያብሎስን እግዚአብሔር ያስታገስልናል ፡እኛንም በጸጋ በምሕረት ይጎበኘናል ፡፡በቤቱ ለማገልገልም ጸጋችንን በትክክል እንረዳለን አገልግሎታችንም ፍሬያማ ይሆናል፡፡
ቤተክርስቲያናችን በደራሽ ጉዳዮች ከመወጠር በረጅም ጊዜ እቅድ እንድትጉዋዝ ወደ ቀደመ ክብሩዋ እንድትመለስ የኛ የምእመናን ተሳትፎ ወሳኝ ነው ፡፡
የአሁኑም ሆነ የወደፊት ዋነኛ የቤተክርስቲያናችን ፈተና የተሐዲሶ መናፍቃን ናቸው፡፡ ተሐዲሶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈልና ይዞታዎቹዋን ለመናፍቃን ለማስረከብ በሚያደርገው ሴራ ከውስጥ ጳጳስ ቄስ ዲያቆን ለመምሰል ስሠራ ወጥኑን ስጨርስ ለመክፈል ከማናፍቃን እንኩዋን በሰበካ ጉባኤ ከማሰመዝገብ ወደ ኋላ አይልም፡፡ አያምጠውና ፍርድ ቤት ብንቆም እንኩዋን መናፍቃንን አግበስብሶ አምጥቶ ይህን ያህል ተከታዮች አሉኝ ከማለት ወደ ኋላ አይልም ፡፡ይህንንመ በባለፈው የጥቅምት ስኖዶስ የበጋሻው ደጋፊ ነን እያሉ በአንገታቸው ማተብ እንድታይ አድርገው ከሀዋሳ ከመጡት መናፍቃን መረዳት ይቻላል፡፡ለተሐዲሶ መናፍቃን ዘላቂ መፍትሔው ከላይ እንደተጠቀሰው ከእኛ የሃይማኖት ጽናት ከምግባር ቅናት በተጨማሪ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ሲባል ሕጉዋን ሥርዓቱዋን አስተምህሮዋን ትውፊቱዋን ማወቅ ፡ማንንም ብሆን ከዚህ ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ሕግ ትውፊት አስተምህሮ አንጻር መመዘን የምንችልበት ደረጃ መድረስ እኔ… የኤገሌ ነኝ ከማለት እኔ የቤተክርስቲያን ነኝ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ሥራ እየሠራ ያለው ማን ነው ማለት መቻል ቅዱስ ስኖዶስ በየጊዜው የሚወስናቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ �እንደሆኑ መከታተል ከሰበካ ጉባዔ አባልነት በተጨማሪ በምደረጉ ምርጫዎች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ወዘተርፈ፡፡�
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል ወይትባረክ ስመ ስብሐትሁ ቅዱስ ወይምላዕ ስብሐትሁ ኩሎ ምድረ ለይኩን ለይኩን፡፡ ወያርእየነ ትንሣኤሃ ለቤተክርስቲያን ወለሀገሪትነ ኢትዮጵያ�::

Anonymous said...

Wendeme ataferm? Ateshemaqeqem? Betsuan abatochen baletegeba shumet meterat tegebi new? Wedatalehu yemetelat beate kerstiyan yehanen tewfit endematastemrhe eregetegna negn. Yemetewedew maheber gen bel lilhe yechelal. Sema manem yale Egziabeher feqad memeret, meshom, ketom menor enkuan endemaychel atawqem? Antena maheberh ye wededachehut sihon tsedq yehonal, E/r yefeqedw sihone degmo tesadebalachehu. Ere be Fetari men eye honen new? Geata yastekaklen. Amen!

Anonymous said...

God Blues you ! you speake for many of us Samuel the Asebot.
it is all true.

lele said...

yeha egane ayasarefanem talatochachenen awekanale bezo maserate alaben.

Anonymous said...

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁ መልካም ነው...ነገር ግን አንድም ቁምነገር አለየዉበትም;; ስንት አንገብጋቢ ነገሮች እያሉ ተራ በሆኑ አሉባልታዎች አባቶች ጊዜያቸውን ማጥፋታቸው በጣም ያሳዝናል። የታዩት ችግሮች በጥቂቱ
1. መግለጫው የወጣበትና አባ ጳውሎስ የፈረሙበት ቀን አለመገናኘት...
2. በሰሜን አሜሪካ ስላለው የቤተክርስቲያን ችግሮች መፍትሔ አልመስጠት...
3. የቤተክርስቲያን ችግሮች በርካታ ሆኖ ሳሉ ሁሌም ለፖለቲካ ቅድሚያ መስጠት...
4. የአባ ጳውሎስ ሐውልት ተደንቅሮ መቅረት....
5. ጉባኤው ከተጀመረ ጀምሮ አባቶች ሲታገሉበት ሌላ ሆኖ ሳለ የወጣው መግለጫ ግን ልላ ነበር....
ከቅዱስ ሲኖዶስ ብዙ ብዙ የተሸለ ነገሮችን እንጠብቃለን...

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን

ተመስገን አምላካችን ቸር ወሬ ያሰማን

ብጹአን አባቶች የእመቤታችን የድንግል ማርያም በረከትና ረድኤት አይለያችሁ!

ከእምነት በላይ ምን አለ?

ተኩላ የበግ ለምድ ለብሶ በበጎች መካከል እንደሚገባ ሁሉ ስማቸውን ቀይረው ቦታ ለውጠው የዋህ ምእመናንን እንዳያስቱ በስም የተዘረዘሩትን የተሃድሶ መናፍቃንን ፎቶአቸውን ጭምር ብታወጡልን እና ብናውቃቸው ጥሩ ነው

በአባ ጳውሎስ ፕትርክና ዘመን:
- ስንቱ ቤተክርስቲያን እና ምእመን በመንግሥት ታጣቂዎች ሳይቀር ተደፈረ?
- ስንቱ ገዳማት እና አድባራት ተቃጠሉ?
- ስንቱ ንዋዬ ቅድሳት ተዘረፈ?
- ስንቱ ምእመን እና ካህናት ተሰየፉ?
- ስንቱ ብጹአን አባቶች እና ሊቃውንት ተሰደዱ?
- ስንቱስ በስውር ተገደሉ?
- ስንቱ ምእመንስ በተኩላዎች ተነጠቀ?

አባቶች ሆይ

የጠፉትን በጎች የመፈለግ: ቤተክርስቲያናችንን እና ምእመኗን የመጠበቅ መንፈሳዊ የአባትነት ግዴታ አለባችሁና የጠፉትን ለመመለስ: እንዲሁም ቤተክርስቲያናችንን ለመታደግ የተሃድሶያውያኑ መመኪያ እና አለኝታ የሆኑትን የተኩላውን አውራ ራሳቸውን አባ ጳውሎስንም ፈትሻችሁ ብታወግዙ ቤተክርስቲያናችን ከገባችበት ማጥ ትወጣ:አሰተዳደሯም ሰላምና እፎይታን ያገኝ: የጠፉት በጎችም ይመለሱ ነበር::

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን

ተመስገን አምላካችን ቸር ወሬ ያሰማን

ብጹአን አባቶች የእመቤታችን የድንግል ማርያም በረከትና ረድኤት አይለያችሁ!

ከእምነት በላይ ምን አለ?

ተኩላ የበግ ለምድ ለብሶ በበጎች መካከል እንደሚገባ ሁሉ ስማቸውን ቀይረው ቦታ ለውጠው የዋህ ምእመናንን እንዳያስቱ በስም የተዘረዘሩትን የተሃድሶ መናፍቃንን ፎቶአቸውን ጭምር ብታወጡልን እና ብናውቃቸው ጥሩ ነው

በአባ ጳውሎስ ፕትርክና ዘመን:
- ስንቱ ቤተክርስቲያን እና ምእመን በመንግሥት ታጣቂዎች ሳይቀር ተደፈረ?
- ስንቱ ገዳማት እና አድባራት ተቃጠሉ?
- ስንቱ ንዋዬ ቅድሳት ተዘረፈ?
- ስንቱ ምእመን እና ካህናት ተሰየፉ?
- ስንቱ ብጹአን አባቶች እና ሊቃውንት ተሰደዱ?
- ስንቱስ በስውር ተገደሉ?
- ስንቱ ምእመንስ በተኩላዎች ተነጠቀ?

አባቶች ሆይ

የጠፉትን በጎች የመፈለግ: ቤተክርስቲያናችንን እና ምእመኗን የመጠበቅ መንፈሳዊ የአባትነት ግዴታ አለባችሁና የጠፉትን ለመመለስ: እንዲሁም ቤተክርስቲያናችንን ለመታደግ የተሃድሶያውያኑ መመኪያ እና አለኝታ የሆኑትን የተኩላውን አውራ ራሳቸውን አባ ጳውሎስንም ፈትሻችሁ ብታወግዙ ቤተክርስቲያናችን ከገባችበት ማጥ ትወጣ:አሰተዳደሯም ሰላምና እፎይታን ያገኝ: የጠፉት በጎችም ይመለሱ ነበር::

Anonymous said...

Thank you dejeSelam for your report timely and genuinely.We thank Our fathers for their unity and stand to condemn the so-called tehadiso. But I am sorry because they did't say about
1. the sever attaches on Waldiba and other monasteries
2. "ye chelema Budin" gungsters , like Aba Paulos, Aba Fanuel, Hailegiorgis, Aba Gerima,....
3. your firm stand on Begashaw, Aba sereke and Getachew Doni was recognised. I think, you are expected to do the same next congress including the overthrow of the "Tehadiso " leader Aba Paulos.

Anonymous said...

our brothers and sisters above say samething. THE , I say THE, source of our problem is the Patriarch and his cronies.

If we foolishly and stubornly defend, the hierarchy of the church, like Mahbere kidusan and others did, we are going down drain. I don't question good intention of organizatioins like mahbere kidusan or others who defend oneness and hierarchy of the church. They mean well. This are dedicated and faithful brother. But It is not the time. "LEHULUM GIZE ALEWU" says wise SOLOMON. However, blindly following the church hierarcy will only push more political, distructive and divisive decisions to our locals(Atbias). The solutions is temporarly resort to congregartionla church structure lead by guba'es elected by priests and lay people. we follow our church dogmas, But, will not allow greedy and politically motivated pope and his cronies funnel their decisions down to us. We should realize by now the so called fathers are out to fulfil their greedy and politically motivated wishes. Peace

Anonymous said...

ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ ዉሳኔዉ እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ይህችን ቤተ ክርስቲያን እንደማይተዋት ያረጋገጠ ነዉ፡፡ አባቶቻችን አኮሩን፣ እድሜያችሁን ያርዝምልን፤አሜን፡፡ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ ዉሳኔዉ እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ይህችን ቤተ ክርስቲያን እንደማይተዋት ያረጋገጠ ነዉ፡፡ አባቶቻችን አኮሩን፣ እድሜያችሁን ያርዝምልን፤አሜን፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)