May 17, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ (አርእስተ ጉዳይ)


/ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳመጠ
 (ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 8/2004 ዓ.ም፤ May 16/ 2012/ READ this news IN PDF)፦
·        ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል

·        “ሃይማኖቴ እንደ አባቶቼ ነው” ያሉት የአባ ሰረቀ እና “የቅን ልቦና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎትን ያቋቋምኹት ልጆቼን የማበላቸው ስለተቸገርኹ ነው” ያሉት የ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ጉዳይ ያለውሳኔ ሐሳብ ለምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀርቧል
·        አባ ጳውሎስ ከጥንተ አብሶ ጋራ በተያያዘ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና እንዲመሰክሩ ሊጠየቁ ይችላሉ
·        ሊቃውንት ጉባኤው ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጎለት ያልቀረበው በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት የሊቃውንት ጉባኤውን ሰብሳቢ በእጅጋየሁ በየነ አማላጅነት ሲለማመጥ ታይቷል፤ ሊቃውንት ጉባኤው “በአንድ ወቅት በራስ ቅል ኮረብታ ላይ ኢየሱስና ዲያቢሎስ ቁማር ተጫወቱ . . . ዲያቢሎስም በጨበጣ ገባ” የሚለውና ሌሎቹም ጥንቃቄ የጎደላቸው ንግግሮቹ ፍጹም ውግዘት የሚገባቸው እንደኾኑ አመልክቷል
·        የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አመራርና መዋቅር ይሻሻላል፤ በጠቅላላ ጉባኤና በቦርድ ይመራል፤ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እንደሚኾኑ ተጠቁሟል
·        የማኅበራት መመሪያ ረቂቅ ለውይይት ቀርቧል፤ አሁን ባሉበት አኳኋን ከቀጠሉ “ሌላ ሲኖዶስ ይኾናሉ፤ የፖቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ይኾናሉ፤ በቀኝ ዘመምና ግራ ዘመም አቋም ቤተ ክርስቲያኒቷን ይውጣሉ/ይከፍላሉ” የሚል ስጋት የቀረበባቸው ማኅበራት ንብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተጠቃልሎ እንዲተዳደር ሐሳብ ቀርቧል፤ የመመሪያውን ረቂቅ በጥንቃቄ የተመለከቱት የምልአተ ጉባኤው አባላት ጉዳዩ በይደር እንዲታይ አድርገዋል

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

9 comments:

Anonymous said...

ከጽጌ ስጦታው ፤ ግርማ በቀለ እና ከልኡለ ቃል የ2 ወር ኮርስ ወስጄላለው፡ በተለይ ጽጌ ስጦታው በተሳዳቢነቱ፤ ቤተክስቲይንን እንዴት ይንቅ እንደ ነበር ከ14 ኣመት በዋላ እንኳን ትዝ ይለኛል። በቤተ ክርስቲያ ደመወዝ እየተቖረጠለት፤ ታማኝነቱና አገልግሎቱ ለፕሮቴስታንቶች፡ ነበር።የስድብ፡ መንፈስ፡የተሞላ፡ፍጥረት፡ነው።

Anonymous said...

ከጽጌ ስጦታው ፤ ግርማ በቀለ እና ከልኡለ ቃል የ2 ወር ኮርስ ወስጄላለው፡ በተለይ ጽጌ ስጦታው በተሳዳቢነቱ፤ ቤተክስቲይንን እንዴት ይንቅ እንደ ነበር ከ14 ኣመት በዋላ እንኳን ትዝ ይለኛል። በቤተ ክርስቲያ ደመወዝ እየተቖረጠለት፤ ታማኝነቱና አገልግሎቱ ለፕሮቴስታንቶች፡ ነበር።የስድብ፡ መንፈስ፡የተሞላ፡ፍጥረት፡ነው።

haile michael zedebretsige said...

የቅድሰት ቤተክርስቲያን የመጨረሻው የላዕላይ ሥልጣን ያለው ቅዱስ ስኖደስ እንደሆነ ይታወቃል :: ይህ ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቤተክርስቲያን የሚበጁ እንደሆነ ተግባራዊም መደረግ እነዳሉበት እሙን ነው::ነገር ግን ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በፓትርያርኩ እምብተኝነት በመንግሥት ከለላ ሰጭነት ተግባራዊ መደረግ ከተተው ቆይቶአል፡፡ ቅዱስ ስኖደስም ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖአል ማለት ይቻላል፡፡ይህን በማየታችንም የቅድሰት ቤተክርስቲያን ልጆች በቁጭት ከመብገን ባለፈ መፍትሔ ማምጣት አልቻልንም፡፡ይልቁንም መፍትሔ ማማጣት ያለባቸው አባቶች ጳጳሳት ብቻ እንደሆኑ በማመን በአባቶች ላይ ያለንን ተስፋ እስከ መቁረጥ የደረስንም አለን፡፡ ይህንንም በደጀ ሰላም በአንድ አድርገን የጡመራ መድረኮች ከምሰጡ አስተያያቶች መረዳት ይቻላል፡፡ስጀምር ስለ ቤተክርስቲያን ችግር እንደየሚናችን ሁላችንንም እንደሚያገባን መረዳት አለብን ፡፡አባቶች ድቁና ቅስና ልሾሙ እኛ ምእመናን የሚንመሰክርበት አሠራር መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው ሊያሥር ልፈታ ልያጠምቅ ቀድሶ ልያቆርብ አንድ ሰው የግድ ቅስናና ከዚያ በላይ የክህነት ደረጃ ልኖረው ግድ ይለዋል ፡፡ ግን አንድ ሰው ካህን ስላልሆነ በአስተዳደር በገንዘብ አያያዝ ጉዳይ ወዘተረፈ አያገባውም ማለት አይደለም ፡፡በእርግጥ አባቶች መሔድ ያለባቸውን ደረጃ እስከመጨረሻ ሔደዋል የሚል ድምዳሜ ባይኖረኝም ከአቅማቸው በላይ የሆነ ጉዳይ ያለ ይመስለኛል:: እንደ እኔ እምነት አብዘኞቹ አባቶች ስለቤተክርስቲያን ነፍሳቸውን እንኩዋን አሳልፈው ልሰጡ የተዘጋጁ ናቸው::ነገር ግን ነፍሳቸው አልፋ ሥራ መሠረት አለበት ::የደርግ መንግሥት ብሆን ገድሎ ስለምፎክር አባቶች ለሃይማኖታቸው ስሞቱ ምእመኑ ይሰማል ወደ ቀጣይ እርምጃም የሔዳል: አሁን ባለው ሁኔታ ግን ገና ከማሰባቸው ልገደሉ ይችላሉ:: በሌላ ምክንያት እንደ ሞቱም የውሸት ወሬ ወዲያው ይቀነባበራል ፡፡ስለዚህ አባቶች ሥራ የማይሠራበት ለምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ጥብዐት የማይጨምር ከንቱ ሞት ከምሆን ጊዜ ከመጠበቅ ወጭ ምንም ማድረግ አይችሉም፡ ታፍነዋል፡፡መፍትሔው ያለው በምእመናን እጅ ነው፡፡

1)ምእመናን በአንድነት መንግሥት በሃይማኖታችን ጠልቃ መግባቱን እንዲያቆም ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም ከሚሠራው ግልጽና ስውር ሤራ እንዲታቀብ መጠየቅ ፡፡ይህንን በግንባር ቀደምትነት በማስተባበር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ ፡፡ ምቹ ሁኔታ ያላቸውም እነርሱ ናቸውና ::

2)በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሁሉም ምእመን እንደሚያገበው መረዳት

3)በየትኛው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማን መሳተፍ እንደሚችል ግልጽ ግንዛቤ መያዝ

4)ሕግጋተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ማወቅ

ከላይ ከ2-4 የተጠቀሱትን ለማሳወቅ መምህራነ ቤተክርስቲያን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የሰማን በማሰማትና በማስረዳት ዛሬ ነገ ሳንል መሥራት ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከእጃችን ወደ መውጣት እየተቃረበ ነው፡፡

ፓትርያርኩ ከውስጥ የተሐዲሶ መናፍቃን አርበኞችን ሲያደራጁ መንግሥት ከውጭ የሃይማኖት ነጻነት በሚል በፍርድ ቤት ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል እየቁዋመጠ ነው፡፡

መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ከመጀመሪያው አጀንዳ እንደ ነበረው ከዚህ በፊት በሰፊው ማንበባችንና ማስነበባችን ይታወሳል፡፡

ይህ ስባል “እግዚአብሔር ያውቃል መጸለይ ብቻ……” የሚትሉትን ረስቼ አይደለም:: ግን እግዚአብሔር በሰው አድሮ እንደሚሠራ መረዳት ያለብን ይመስለኛል :: በእርግጥ ሁሉም በጎ ሥራ በጸሎትና በእግዚአብሔር ኃይል ነው የሚሠራው፡፡

የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ከእጃችን ሳይወጣ ዛሬ ነገ ሳንል እንታደግ ፡፡

ማላሰብያ ፡ምን አልባት ከዚህ በፊት ለብዙዎቻችን የሚመስለን የመንግሥት የመረጃ ደኅንነት ኤጄንሲ ማን ከማን ጋር ምን እንዳወራ ለመከታተል የሚችለው ስልክ ስንደዋወል ብቻ ነበር::

ተንቀሳቃሽ ስልካችሁን አጥፍታችሁ ባትሪዉን ካላወጣችሁ ወይም ከስልካችሁ ተለይታችሁ ካላወራችሁ ባስተቀር ሳትደዋወሉ ተሰብስባችሁ ከማን ጋር ምን እንዳወራችሁ በቀላሉ የመንግሥት ደኅንነት መረጃ ቁዋት ውስጥ ልገባ ይችላል::

ጾዳቤ(Email) ስትጠቀሙም ከስማችሁ ጋር ግኑኙነት የሌለውን account በመክፈትና password በመጠቀም አንድ ቦታ ወይም የግል ኮምፒዩተር ሳይሆን በተለያየ ቦታ ወይም ብዙ ሰው በሚጠቀምበት በመላላክ ስለ ቤተክርስቲያን መወያየት ትችላላችሁ፡፡

Anonymous said...

ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ !!!
ADAMETU ! BEMADAMET BIZAT JOORO'ACHI SEBTOWAL INNA INAANTEM SINOODOSOCH KATOOLIK SATIHOONUU ATIQERUM BIYEE EGEMTALEHU.WAANNAWUN ABBA PAUL CATHOLIC SATAWEGZUU BE EOTC BETE K/N LAYI YEE POLETICA NAA YEE ZERENYINET HAWUULT AQUMOO LIYASEGIIDEEN DEFAQENA YEMIL AYQEDIMIMI NEBER. "AYAAYAZUUN AYITEHI CHIBITOOWUN QEMMA"EG/Z YASIBEN YASIBISH EOTC.

Anonymous said...

የኔ ጥያቄዎች 1. ኑፋቄ የሚዘራ ፀረ-ተዋሕዶ ስለተቅለሰለሰ. . . Ah ልጆቼን ምን ላብላ?! መቼም ቢሆን ሊሸጠን ከተዘጋጀ ለምን መከራችንን እናበዛለን? ዼንጤ የሀይማኖት እንጂ የብር ችግር የለበት! ስለዚህ መናፍቃን ለምንድነው የማይወገዙት? 2. Someone was telling us abt "operation FINHAS". One im not clear why such a secrete could leak out if at all operable. Two if again thought abt it, z immediate and long effects on z church analysed? Third it is a crime and there could be perpetual cycles of killings coz z patriarch has formed 'mafia group' which wont sleep. Fourth z govt will quote zis site as 'terrorist agent' and those writing Fifth will it bring us what we need or just replacement therapy? So im so confused abt this "operation" stuff. 3. Tell us how a mobile phone with out calling and not switched of can be hacked? The science is not clear for me coz im ignorant abt it. But i could understand abt using internet. Good plz plz tell me! Have a nice day.

Anonymous said...

uuuuuuuuuuu


betame yemigereme newe atadafiwe gudaye yetsegea..girma...ayedelem..enesuma ke 1990 gedema yewetu nachewe!!!!

AHUNE ASASABIWE GUDAYE BETEKIHENETE YETESEGESEGUTE MENAFEQANE TETERAREGEWE MEWETATE ALEBACHE...BETECHEMARIME..GETACHEWE DONI...SEREQE...AGURAZELELE SEBAKINA ZEMARI MALETEA YEMENAFEQAN ARAMAJOCHE YEHONUTE...BEGASHAWE.....TIZITAWE..


ERE ABATOCHACHEN BE POLETIKA MEZEWERE EYEZORU MESELEGNE BETEKIRSTIYANENEN BIYADENUTE YESHALALE KEZA MEMENU YERASUN AQUAM ABATOCHUNE TEKETELO YEWESEDALE ...EGIZIO MAHERENA KIRSITOS EGIZIABEHERE BETEKRESTIYANENEN YETEBEQELENE

Anonymous said...

wondime Hailemichael, ke abaatoch Akim Belay yehon nege ale maletih indene sihitet now. Be Korstos tsinat Eske semaa'itinet now. simech bichaa aydelem!!

asbet dngl said...

ሃይለ ምካኤል እጕዚአብሔራ ይባርክህ:: እንግዲህ ምእመን ይሄው ወንድማችን ያለው ነው የሜያስፈልገው:: አባቶችን ወደኋላ እናቆይና እኛው እንሰለፍ::መንግሥት በጀርባ አለ የሜባለው ማስፈራራያ ለኔህ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ለማያምኑ አባት ሲል ምእመንን ይጕዳል የሜል እምነቱም የለኝም::ይሁን ካለም በግዜው ይታያል:: ቁም ነገሩ "ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም" ግዚው አሁን ስለሆነ ስለበተክርስቴያን ጉዳይ እንነሳ::
አባት ሆይ ሃይማኖታችንንና አገራችንን ጠብቅ:: አሜን

Anonymous said...

pray for eotc

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)