May 19, 2012

በብዙ ጫና ውስጥ ያለው ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢ ስለሚገነባቸው ፕሮጄክቶች ሪፖርቱን አቀረበ


  •    ሪፖርቱ የጠ/ቤተ ክህነት ሓላፊዎች “አቀረብን” ካሉት በይዘትም በተአማኒነትም የተሻለ ነው።
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 10/2004 ዓ.ም፤ May 18/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢው ሊሠራው ስላቀደው ግዙፍ ሮጄክት “አጠናሁት” ያለውን ሪፖርት አቀረበ፤ ከመንግሥት ጋር መነጋገሩንም ገለጸ። ዛሬ ይፋ የተደገው የማኅበሩ ሪፖርት የቤተ ክህነቱ አዳዲስ ተሿሚዎች ማኅበሩን በዋልድባ ጉዳይ በከሰሱ ማግስት የቀረበ ሲሆን ለእነርሱ ክስ የተሰጠ አፋጣኝ ምላሽ ይሁን አይሁን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።


አዲስ የተሾሙት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ኃላፊ መምህር ዕንቁ ባሕርይ ተከስተ “በዋልድባ አካባቢ መንግሥት ሊሠራ ያቀደውን ግዙፍ የስኳር ፋብሪካን በማስመልከት በዋልድባ ይዞታ ላይ ያደረሰው ተጽእኖ መኖር አለመኖሩን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተፈላጊውን የማጣራት ሥራ አከናውኖ” ከተመለሰ በኋላ “ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱና … የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጠኞች መከታተላቸው መሣተፋቸውና የሚፈልጉትን ጥያቄ በይፋ አቅርበው ምላሽ መሰጠቱ”ን ጠቅሰው “ማንኛውም ጋዜጠኛ በተለይም ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሣን የሆነው የማኅበሩ ጋዜጣና መጽሔት መረጃ ከወሰደ በኋላ መግለጫውን አለማውጣቱ አግባብነት የሌለው ከመሆኑም በላይ የሚዲያ ሥነ ምግባርንም ያልተከተለ ስለሆነ” ጽሑፉ ያልወጣበትን ምክንያት ማኅበሩ በጽሑፍ ይገልጽ ዘንድ ከሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መታዘዛቸውን እንዳብራሩ መዘገባችን ይታወሳል።

የመምሪያው ደብዳቤ “ጋዜጣዊ መግለጫውን በሚዲያ ለማውጣት ተስማምታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ከወሰናችሁ በኋላ ዘገባው የቀረበት ምክንያት በጽሑፍ ለማደራጃ መምሪያው” እንዲመለስ እንደሚጠብቅ በመግለጽ “ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎትና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን” ግልባጭ ተደርጓል። ደጀ ሰላምም “የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ እና ሕግ አገልግሎት መምሪያ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ስለሆነ በቀጥታም ባይሆን ጉዳዩ ሊያገባቸው ይችላል። ከላይ ስማቸው የተዘረዘሩት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምን አግባብ ነው ስለ አንድ ማኅበር፣ ያውም በአንድ መምሪያ ሥር ስላለ አካል ግልባጭ የሚደረግላቸው? መንግስታዊ መሥሪያ ቤቶቹ ከሚዲያ ጋር የተገናኙ እንኳን ቢሆኑ በግድምድሞሽ “ግንኙነት አላቸው” ይባል ይሆናል። ፌዴራል ጉዳዮች፣ ደኅንነት፣ ፖሊስ … መጠቀሳቸው ለምን ያስፈልጋል? እሰሩልን፣ ግደሉልን፣ ቀፍዱድልን ለማለት ካልሆነ” ማለቷ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበሩ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የዋልድባ አጥኚ ቡድን ሪፖርት እጥር ምጥን አድርጎ አቅርቧል። ከመንግሥት ከቤተ ክህነትም መልስ ለሚፈልጉ ሰዎች የየድርሻቸውን በመስጠት ከነገሩ ጦም እደሩ ለማለት ሞክሯል። ከሀ-ሠ በተዘረዘሩ ዐበይት ዐዕማድ ርዕሶች የተዘረዘረው ሪፖርቱ ከአጠቃላይ ዳራ (Background) በመጀመር በማጠቃለያ ይፈጽማል። እነዚህም ሀ “ዳራ”፣ ለ “ዋልድባ ገዳምና አካባቢ ከመንፈሳውያት ተቋማት አንጻር” ፣ ሐ “በቅዱሱ ቦታ ድንበርና አካባቢ ስለሚገነባው ፕሮጄክት አጠቃላይ ዳሰሳ”፣ መ “ፕሮጄክቱ ላይ ገዳማውያኑ ያነሡአቸው ጥያቄዎችና የልዑካኑ ዕይታ”፣ ሠ “ማጠቃለያ” ናቸው።

ማኅበሩ በመንደርደሪያው ጉዳዩ ብዙ ወገኖችን ያነጋገረ፣ ያከራከረ መሆኑን ጠቅሶ “የጉዳዩን ምንጭ እና መፍትሔ ነጣጥሎ ማየት እስከሚከብድ ድረስ በሰው ልቡና ሲመላለስ ቆይቷል” ይላል። ምንጩን እና መፍትሔውን ለምን ለያይቶ ማየት እንደሚያስፈልግ አላብራራም። መፍትሔው የሚመጣው ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት ከሚደረግ ጥረት መሆኑን (የcause and effect ግንኙነት) የዘነጋው ይመስላል።

ቀጥሎም “ከመጋቢት 25-30 ቀን 2004 ዓ.ም አምስት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ወደቦታው” ተልኮ እንደነበር፤ “በቦታው በመገኘት ሁሉንም አካላት ማለትም የገዳሙን አባቶች፣ የፕሮጄክቱን ሓላፊዎች፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በማነጋገር ያገኘውን ምላሽ ከልዑካኑ ዕይታ ጋር በመጨመር ሰፋ ያለ ሪፖርት ይዞ” መመለሱን ጠቅሶ የማኅበሩ አመራር አካልም ሪፖርቱን “ከሰማ በኋላ፣ ከልዩ ልዩ አቅጣጫዎችና ተጨማሪ መረጃዎች ጋር በመመርመር” እንዳጸደቀው ይተርካል።

የማኅበሩ አመራር የቀረበለትን መረጃ “ከልዩ ልዩ አቅጣጫዎች” ማየቱ መልካም ቢሆንም  ከጠ/ሚኒስትሩ ንግግር እስከ መምህር ዕንቁ ባሕርይ ደብዳቤ ድረስ ማኅበሩ ከባድ ጫና ውስጥ መግባቱን ለሚያውቅ ማንኛውም ወገን ማለትም በመንግሥት ዘንድ “ሞገስ ያገኙት” ተሐድሶዎች እና ብሎጎቻቸው በተደጋጋሚ ሲሉት እንደነበረው መንግሥት በዋልድባ ዙሪያ የሚያካሒደውን “ፕሮጄክት” ለመቃወም በመላው ዓለም የተነሣው እንቅስቃሴ መሪ “ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ” ተደርጎ መዘገቡ፣ ከአቦይ ስብሐት ጀምሮ ሌሎች የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ጣታቸውን በማኅበሩ ላይ መቀሰራቸውን ለሚገነዘብ ሁሉ ሪፖርቱ በነጻነት የተዘጋጀ ነው ለማለት ይከብዳል። ለዚህም ፍንጭ የሚሰጠው በማጠቃለያው ላይ “ማኅበሩ በወልቃይት እየተገነባ በሚገኘው የስኳር ፕሮጄክትና በግድቡ ዙሪያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አጥንቶ ያዘጋጀውን ሪፖርት ከሚመለከተው ከፍተኛ የመንግሥት አካል ጋር ውይይት አድርጎ ነበር” የሚለው ዐቢይ ዐረፍተ ነገር ነው።

ጥናቱ በገዳሙ እና በመንግሥት መካከል ያለውን አለመግባባት ተመርኩዞ የተደረገ እስከሆነ ድረስ፣ ማኅበሩም በገለልተኝነት እና በሃይማኖታዊ ተቆርቋሪነት ነጻ እና ሙያዊ ትንተና ለመስጠት የፈለገ ከመሆኑ አንጻር ሪፖርቱን ሚዛናዊና ነጻ በሆነ መልክ ይፋ ከማድረጉ በፊት ለአለመግባባቱ አንድ አካል ማለትም ለመንግሥት “ከፍተኛ አካል” ቀድሞ ካቀረበ ምኑን “ነጻ ሪፖርት” ሆነው? “ከፍተኛ አካል” የሚለው በራሱ ከፍተኛነቱ ከትከሻ እስከ ራስ ድረስ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ግልጽ ባይሆንም ሪፖርት አቅራቢው ክፍል ይህንን ሁሉ “ከፍተኛነት” ተቋቁሞ ለማለፍ አቅሙ እስከምን እንደሆነ ለማወቅ ይቸግራል።

የከፍተኛ ባለሥልጣኖችን አስፈሪ ግርማ ተቋቁሞ እውነቱን ብቻ በመናገር በኩል የቤተ ክርስቲያናችን መሪዎች ተፈትነው እንደወደቁ እናውቃለን። ከፓትርያርኩ እስከ ሌሎች አባቶች ድረስ ባለሥልጣናቱን ከመላእክት ባልተናነሰ እንደሚያከብሯቸው እና እንደሚፈሯቸው እናውቃለን። የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት አቅራቢዎችና አመራር አካላት ይህንን የባለሥልጣናት “ግርማ” እና ውስጠ-ዘ መመሪያ ተቋቁመው “ነጻ ሪፖርት” ለማቅረብ ችለው ይሆን? ሪፖርቱ “ሐሰት” እንደሌለበት ብናምንም “ከእውነታው ላለመቆንጸሉ” ግን እርግጠኞች አይደለንም። ስለዚህም ይህ ሪፖርት ምን አዲስ ነገር ነገረን ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። “አዲስ ነገር” ካልነገረን ደግሞ የቀረ ነገር መኖሩን እንጠረጥራለን። ያ የቀረው ነገር ምንድነው? ይዋል ይደር እንጂ መውጣቱ አይቀርም።

በጎ ጎኑን ከተመለከትን ሪፖርቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሓላፊዎች “አቀረብን” ካሉት በይዘትም በተአማኒነትም የተሻለ ነው። ለውይይት ጥሩ መነሻ  ይሆናል። መንግሥት ያዘጋጀውን ጥናት በአጭሩ ማቅረቡም ጥሩ ነው። የገዳሙን ታሪክ እና ማን ምን እንደሆነ ማብራራቱም በዋልድባ ጉዳይ የሚኖረን ውይይታችን መሠረት ያለው እንዲሆን ይረዳል። ፎቶዎቹ፣ ካርታዎቹ እና ዳሰሳዎቹ ጥሩ “ዳራ” ይሰጣሉ። ከዚህ የሚቀረው ፈረንጆቹ (reading between the lines) እንደሚሉት ከተጻፈው የማኅበሩ ሪፖርት ላይ በመመርኮዝ ያልተጻፈውን፣ አጠይሞ ያለፈውን እና ሳይናገረው በጥቅሻ ብቻ ያለፈውን ማብራራት ነው። እንዳለመታደል ሆኖ “ነጻ አስተያየት” የሚሰጡ አካላት የሚደቆሱበት አገር ስለሆነ ከማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በላይ መጠበቅ “ግፍ” ሊሆን ይችላል። ጭራሹኑ “እሳት ውስጥ” ግቡልን እኛ ዳር ቆመን እናያለን ከማለት እንዳይቆጠርብን፣ ያንንም ለማለት “ሞራላዊ ብቃታችን” ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ በሪፖርቱ ባንረካም “መቸስ ምን ይደረግ፣ አገሩ ኢትዮጵያ ሆነ” ከማለት ውጪ።

በጠቅላላው ሪፖርቱ አዲስ የውይይት በር ከመክፈት በስተቀር የተከፈተውን የተቃውሞ እና የውይይት በር የሚዘጋ እና እልባት የሚሰጥ ሊሆን አይችልም። ተቃውሞውም ይቀጥላል፤ ውይይቱም ይቀጥላል። አጭሩ መፍትሔ መንግሥት የጀመረውን ነገር ማቆም ብቻ ነው። ይዋል ይደር እንጂ መቆሙ ግን አይቀርም። ያለ ሕዝብ ተቀባይነት የሚጀመር ነገር መረሻው ምን እንሆነ በታሪክ እናውቃለን፤ በአገራችንም አይተነዋል። ደርግ መንደር ምሥረታ አለ፣ ልማት አለ፣ ገበሬውን ሰበሰበ … ለውድቀቱ ምክንያት ሆነ፣ መንደሩም ተበተነ፣ ልማቱም እንደቆመ ቀረ። ይኼኛውስ ምን የተለየ ያደርገዋል?

READ THE REPORT IN PDF

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን


16 comments:

Anonymous said...

The report is up to our expectation. Only God and the study team know the truth. We may not hear about Waldeba any more except the intervention of God's mighty hand. Men yaderegu, chegerun kemetekom belay lela men malet yechelalu? Manes yesemachewal. Gize yefetaw. Amlake Kidusan ersu serawen yesera. lenegeru balebetun kedewet yele, min yedenkal. Aye Aba Paulos Egeziabher yeyelewot, letsedk abenet honew limerun sigeba enkefat honuben. Amlake Tekelhaimanot lebunawoten yemeleselewot. Gen seweranu yegedamatuena yekedusat mekanatu tebakewoch yet hedu? Hulum tewen malet new? Bewenu mekeberiya ena mekebera mekan, mekari wemegesets yehone abat yemaygegnebet zemen lay deresen malet new. Enkyas ho belo weteto memot yeshalenal, men albat alemotenem kalen.

Anonymous said...

Well done Mk, it seems there was a comunication break down b/n the gov and the the church fathers at the walidba.From what i read is the bigger problem is the issue b/n the fathers at the walidba that creats a bigger information breakdown,one says it's ok the other say's no. so if you ask me the problem is in those fathers that is self centered,have their own agenda.

The bigger issue is our church fathers preach we are 1 GOD creation but in their deeds they are separated by tribe what a shame.

Anonymous said...

bravo Enkubahriy go for it

Anonymous said...

+++
በእውነት ሚዛናዌ ሪፖርት ነው:: እንደ መጀመሪያ አጥኒ ከዚህ በላይ ሊሉ አይችሉም:: ገዳሙ ተደፍሮአል:: መንግስት ቢያቆመው የተቫለ ነው:: ለሪፖርት አቅራቢዎች እግዚአሔር ይስጣችሁ:: ሌሎች አጥኒዎች ደግሞ ቀጥሉ በአካል ባይቻልዘመን ባፈራውመሳሪያ ተጠቅሞ::

Anonymous said...

ይዋል ይደር እንጂ መቆሙ ግን አይቀርም

Anonymous said...

Mahbere Kidusan’s report is good but the conclusion is not appropriate. Even the monks and nuns in Waldba do not have the authority to suggest an exchange of 16.6 hectares of blessed land (blessed and trodden by the Christ and His Mother our Queen the Blessed Virgin Mary). Waldba is God’s own real-estate; not man’s. The report is also a little short on the environmental and urbanization threats Waldba encounters as a result of this invasion. It is, however, understandable that Mahber Kidusan is in an extremely difficult situation to report beyond what it already has given it is under such immense threats from the EPRDF.

Anonymous said...

ማህበሩ እኮ እንደ አጥኚ ቡድን እውነታውን አውጥቷል:: ግድቡ ከ 40 በመቶ በላይ ገዳሙን እንደሚያጥለቀልቅ ማስረጃ ሰጥቷል:: ከዚህ በኋላ የሚቀረው ድርሻ እንደ ማንኛውም ምዕመን መፍትሄው ላይ መንቀሳቀስ ነው:: ስለዚህ በተጽዕኖ ውስጥም ቢሆን በ ሰከነ አቀራረብ እዉነታውን ቁልጭ አድርጎ አቅርቧል ብዬ አምናለሁ::

Gofa Geberal said...

Mahbere Kidusan’s report is well done especially the first part, that project needs to stop.But the conclusion is not right at all. "The exchange of blessed land", to give another land to the gedam, our fathers didn't want to take another land or give what they have. Offcourse it is easy for the goverment to give another land for exchange. But no way, no one should accept or suggest that, we don't have land issue, but this is our blessed holy land. So even with any pressure, it shouldn't be written as conclusion. This will confuse people's understanding of the issue. We need to fight to keep what waldeba already have no new land or no giving land. We should keep as we received from our fathers to the next generation. No new land, no gving away the gedam property.Mahbere Kidusan our brotthrs sisters we all knows in what kind of pressure, and even secrifies you are going through. From insiders, from outsiders but be strong, we only live one time in this world. For the church you all love the most do as much as u can and tell the truth as you always do. Let God's will be with our gedam and Ethiopia

lamelame europe said...

mk yakedosane amelake yeredachohe

Ewunet Tenagari said...

እንዳለመታደል ሆኖ “ነጻ አስተያየት” የሚሰጡ አካላት የሚደቆሱበት አገር ስለሆነ ከማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በላይ መጠበቅ “ግፍ” ሊሆን ይችላል። ጭራሹኑ “እሳት ውስጥ” ግቡልን እኛ ዳር ቆመን እናያለን ከማለት እንዳይቆጠርብን፣ ያንንም ለማለት “ሞራላዊ ብቃታችን” ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ በሪፖርቱ ባንረካም “መቸስ ምን ይደረግ፣ አገሩ ኢትዮጵያ ሆነ” ከማለት ውጪ።
They are called after 'kidusan' to be martyrs, to be persecuted, to be jailed, to be burned, ETC.... They have to only speak the truth, not to be diplomatic or politically correct. If they fear those who can jail or kill them, they should change their name. 'kidusan ' were not and are not smart Christians. They did not pretend to have been conservative Christians, but lived Christianity enduring all trials and tribulations they faced. MK is hero against Begashaw, so called 'tehadiso' and those who commented against its wrong doings and suggested the way forward regarding its mission??? If you fear you have to pave the way for others who are ready to be martyrs to their Church and to their religion. But, in my judgment, it not only fears rather your under cover loyalty to the 'government' in the palace is implied in your response. You are trying to play a game; but Christianity is not a game. You either live it or leave it!

Anonymous said...

+++
ደጀ ሰላሞች፦ አምላክ መቼም በጊዜው ያስነሳቸሁ ናቸሁ ።ከንጹሕ የተገኘ ንጹሕ ምንጭ ነውና ። አሁንም አምላከ ጥበቡን ዕውቀቱን
ትጋቱን ያድላችሁ፦ ለወንድሞቻቸንም ባለቤቱ አንደበት ይሁናቸው በዕውነት የቅዱሳን አምላክ።

Orthodoxawi said...

ደጀሰላም ለሚዛናዊ ዘገባችሁ እጅግ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። አንዳንዶች በማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት እንዳልተደሰቱ አይቻለሁ። እኔም እንዲሁ። ነገር ግን ወደ እውነታው ስንመጣ ጉዳዩ በጥንቃቄ ካልተያዘ መስዋእትነት የሚያስከፍል ነው። እኔ አሁን በውጭ ሀገር ከኪችን (ማዕድ ቤት) ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብዬ አስተያየት እንደምጽፈው አይደለም። ስለዚህ ሪፖርቱን አንብቦ እንደሚገባ በመተርጎም ዋልድባን ለማዳን ተገቢውን እርምጃ መውሰድ የእያንዳንዳችን ድርሻ ይሆናል።

ማኅበረ ቅዱሳን ለአሁኑ ዘገባ እግዜር ይስጥልን። ለወደፊትም እውነታውን ሳትሸራርፉ ለማቅረብ ሞክሩ ... ምንም እንኳ በእሳት ተከባችሁ እንደምትሰሩ ባውቅም። በአሁኑ ዘገባም ቢሆን በቻላችሁት አቅም መንግስትንም ቅዱስ ሲኖዶስንም ጨዋነት በተሞላበት አጻጻፍ ተችታችኋል ... ጆሮ ያለው ይስማ! አገር ቤት ከሚንቀሳቀስ ማኅበር ከዚህ በላይ መጠበቅ ይሉኝታ ማጣት ይሆንብኛል።

በተረፈ ግን ወደዚህኛው ጉዳይ ብቻ አተኩራችሁ የሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ገዳማት እና የአብነት ት/ቤቶች ክትትል፥ እርዳታ እና የፕሮጀክት ትግበራ እንዳይዘነጋ። ቤተክርስቲያናችንን ከመናፍቃን ሴራ በተለይ ከተሐድሶ ፕሮቴስታንት መከላከሉን ቀጥሉበት። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን።

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክህነቱም፥ ለቤተ መንግስቱም ልቦና ይስጥልን። ቅዱሳት መካናትን ሁሉ ይጠብቅልን። አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን። አሜን!

Anonymous said...

We done MK I am always proud of you, but the conclusion should not even cosidered with Waldba holy land. All we wanted is the truth. The rest is leave it to people. We will fight to our death no matter what is the outcome.

Anonymous said...

Melkam new yaqerebachut Egeziabeher yesetachu
Amen.....

Anonymous said...

Dear Dejeselamoch,
Do you think guys u r doing the right way? r u following the 10 commandments? or r u guys pointing the way that ur enemies to come to u? or is the must or a prophet to these all stuffs.....
better to think twice before going a head but I appreciate also ur dedications!!

Anonymous said...

God reveal himself through men. We need people who stand for the truth. As we all know Mahbere kidusan claim that it stands to defend the EOC and this is the time to speak out their mind with all expected harassment, torture, and intimidations. That’s what makes them different from ordinary citizen. We all have sympathy to waldiba and our country in general. The advantage of being organized is to defend yours and others right. This is the time mahberkidusan to be tested. Get lesson from our Muslim brothers.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)