May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰባተኛ ቀን ውሎ ሪፖርታዥ


·         አባ ጳውሎስ በእመቤታችን ንጽሕና ላይ እምነታቸውን እንዲገልጡ ቢጠየቁ አንደበታቸው ተሳሰረ፤ ለጥያቄው መነሻ የኾነው ፓትርያርኩ በአባ ሰረቀ ‹መጽሐፍ› ላይ ስለተጠቀሰው የዶክትሬት ጽሑፋቸው ዝምታን በመምረጣቸውና ኮሚቴውም የእርሳቸውን ምላሽ ወይም አቋም አለመመርመሩ ነው - “አባ ሰረቀ ጽሑፍዎን ጠቅሰው መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ ለምን ዝም አሏቸው? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም? ይሉኝታ ነው ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው?” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም - ነደ ‹ተሐድሶ›/
·         አባ ጳውሎስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ “አልቀበልም፤ ኮሚቴው በትክክልና በጥራት አልሠራም” በሚል ያመጡትን ተለዋጭ ሐሳብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውድቅ በማድረግ ሪፖርቱ ተባዝቶ እንዲደርሰው አዝዟል፤ ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል

·         አባ ጳውሎስ የቅዱስ ያሬድን በዓል ለማክበር በሚል ሰበብ የቅዱስ ሲኖዶሱን ስብሰባ አቋርጠው ዛሬ ወደ አኵስም ለማምራት ያሰቡትን ጉዞ ምልአተ ጉባኤው ተቃውሟል - “በሐዋርያት ቃል፣ በሐዋርያት ቃል÷ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ይህ አጀንዳ ሳምንትም ቢፈጅብን እርስ በርሳችን ሳንፈታተሽ አንድ ሰው እንዳይሄድ!” /ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እንዳስጠነቀቁት/
·         በማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ ዝግጅት ላይ በ”ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች የተጠና ነው” የተባለው ሰነድ በምልአተ ጉባኤው አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፤ ጥናቱ በልዩ ኹኔታ ማኅበረ ቅዱሳንን እንደሚመለከት አባ ጳውሎስ ግልጽ ቢያደርጉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አርቅቀንና አጽድቀን ሰጥተናል፤ ይህ ጥናት አይመለከተውም፤ ለሌሎቹም ቢኾን ሰነዱን በጥንቃቄ መርምረን ፈትሸን ነው የምንወስነው” በማለት 15 ገጾች ያሉት ጥናት ተባዝቶ እንዲደርሳቸው አዝዘዋል፡፡
·         በመንፈሳውን ማኅበራት ምሥረታ ላይ የተደረገው ጥናት በዋናነት የማኅበራትን አፍራሽ ገጽታ በማጉላት “አሁን ባላቸው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያም ይኹን በጥንታውያን አኀት አብያተ ክርስቲያን ታሪክ ያልተለመደ በመኾኑ ሊስተካከል ይገባዋል፤ ቤተ ክርስቲያን በቃለ ዐዋዲው የተዘረዘሩ መዋቅሮቿን በማጠናከር ምእመናን ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይገባል፤” ብሏል፡፡ ማኅበር የሚለው ስያሜ የማይለወጥ የቤተ ክርስቲያን መገለጫ በመኾኑ አሁን በማኅበራት መልክ ለተደራጁትና ለሚደራጁት አካላት “ኮሚቴ፣ ክበብ” የሚል ስያሜ ብቻ እንዲሰጣቸው ሐሳብ ያቀርባል፡፡
·         በሲዳሞ /ሐዋሳ/ ሀገረ ስብከት “ሊቀ ጳጳሱ ሁሉንም አካላት አቅፈው ለመምራት አልቻሉም፤ ለማኅበረ ቅዱሳን ያደላሉ” በሚል ጥቅመኞችና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች “ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የኾነ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዲቋቋምላቸው በአባ ጳውሎስ የቀረበውን ሐሳብ ምልአተ ጉባኤው “የተሐድሶ መንፈስ እንዲህ አድርጎ ቤተ ክርስቲያኒቱን መገነጣጠል ነው፤” በሚል ውድቅ አድርጎታል፡፡ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስነታቸው ለሁሉም ማእከላዊ አባት ኾነው እንዲመሩ፣ ጥያቄ አቅራቢዎቹም ለሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲገዙ እንጂ ለማንም ተብሎ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደማይሻሻል ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል፡፡
·         ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ወጥ መንገድ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ ኾኖ የተሾመው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ “መምሪያውን ለመምራት ብቃት የለውም” በሚል በአስቸኳይ ተነሥቶ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው እንዲመለሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፤ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ የተነሡበት መንገድ “ሽፍትነትን በቤቱ ያነገሠ” በማለት ባላመኑበት ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ መገደዳቸውን አጥብቆ ኮንኗል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ስለተጻፈው ደብዳቤም “ሁልጊዜ ይኼን ማኅበር ምክንያት እየፈለጉ በፖቲካና በአስተዳደር መክሰስ፣ ማሳደድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? መቼስ ነው የሚቆመው? ማኅበሩን ማዳከም ቤተ ክርስቲያንን በድጅኖ የማፍረስ ያህል ነው፤ የመናፍቃን መቀለጃና መጫወቻ ለማድረግ ነው፤” በሚል ክፉኛ አብጠልጥሎታል፡፡
·         የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ፊት ቀርበው ከመምሪያው ዋና ሓላፊ በሕገ ወጥ መንገድ መነሣትና በእርሳቸው ምትክ በሽፍትነት ከተሾመው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ጋራ በተያያዙና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የገጠማቸውን ችግር እንደሚያስረዱ ተነግሯል፡፡ ተወካዮቹ አባ ጳውሎስ ሠርቶ ከማሠራት ይልቅ በአንድ በኩል ማኅበሩን በተለያየ መንገድ እያጠቁና አገልግሎቱ በየምክንያቱ እንዲዳከም በመጣር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅር በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠላቶች እንዲወረር የሚያደርጉበት አካሄድ ከቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ህልውና አኳያ ስለሚያደርሰው ጉዳት አቋማቸውን ገልጠው ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
·         አባ ጳውሎስ በሌላቸው ሥልጣን በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ የጣሉት የፊርማ እገዳ ተነሥቶ የኮሚሽኑ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሒሳቦች በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደ ቀድሞው እንዲንቀሳቀስ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ አባ ጳውሎስ የኮሚሽኑን ሊቀ ጳጳስ ለምን እንዳገዱ በቤቱ ሲጠየቁ “አልፈርምም፤ አልታዘዝም እያለ፤ በሲኖዶስ እየፈከረ” በሚል ከስሰዋል፡፡ ብፁዕነታቸውም “አዎ! ሕግ ስለተጣሰ፣ ጥያቄው አግባብ ስላልኾነ አልፈርምም ብዬአለኹ፤ በገንዘብ እጦት ከመቶ በላይ ሠራተኞችን በትነናል፤ ኮሚሽኑ የፕሮጀክት ብር ብቻ እንጂ ሌላ ገንዘብ የለውም፤ የፕሮጀክት ብር ደግሞ ለፕሮጀክት ብቻ ነው የሚውለው፤ የፋይናንስ መምሪያ ሓላፊውን ጠይቄ ይህንኑ አረጋግጦልኛል፤ ኮሚሽኑን ከጥፋት ለማዳን ነው ይህን ያደረግኹት፤ ይህ ጉባኤ ገንዘቡ ይውጣ ካለ አይደለም አቶ ወይዘሮም መጥታ ትፈርም! በሕጉ መሠረት ግን ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ ኾነን እኔና የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ነው የምንፈርመው፤” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አባ ጳውሎስ እገዳው ለጊዜው ያስተላለፉት እንደኾነ ቢናገሩም “ለጊዜውም ቢኾን ቅዱስ ሲኖዶስ የሾመውን ሊቀ ጳጳስ እርስዎ ሊያግዱ አይችሉም፤ አሠራሩ ባለበት ይቀጥል” በማለት የፊርማ ስረዛ ጥያቄ ላቀረቡባቸው ባንኮች ሁሉ የጻፉት ደብዳቤ በሌላ ደብዳቤ ተሸሮ አሠራሩ በነበረበት እንዲቀጥል ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
·         አባ ጳውሎስ ግፊት በአኵስም ሀገረ ስብከት ከሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ጋራ ስለተፈጠረው ችግር የአኵስም ጽዮን ማርያም ንቡረ እድ በቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ቀርበው ያስረዳሉ፤ አባ ጳውሎስ “በላሊበላ ጉዳይ ላይ የተያዘው አጀንዳ ከማኅበራት ማቋቋሚያ ጥናት ጋራ ተያይዞ ይታይልኝ፤” በሚል “ማኅበረ ቅዱሳን ሕገ ወጥ ጉባኤ አካሂዷል” ብለው ለመክሰስ አሸምቀዋል፡፡ በስደት ላይ የሚገኙት አባቶች ተወካይ በዕርቀ ሰላም ንግግሩ ሂደት ላይ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ሪፖርት አቅርበዋል፤ ንግግሩን በሚያደናቅፉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተዋል፤ በሪፖርቱ ላይ የሚካሄደው ውይይት ዛሬ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 10/2004 ዓ.ም፤ May 18/ 2012)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ዘጠኝ ቀን ሰባተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ስብሰባውን የጀመረው ቀደም ሲል በንባብ ባዳመጠው ባለ60 ገጽ የሃይማኖት ሕጸጽ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበለት ሪፖርት ላይ በመወያየት የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ነበር፡፡

ይኹንና ኮሚቴው በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ በየደረጃው ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ የተናነቃቸው ርእሰ መንበሩ አባ ጳውሎስ ያንን በመገልበጥ ሌላ የውሳኔ ሐሳብ ይዘው በመቅረብ ያነባሉ፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም አባ ጳውሎስ ያነበቡት ትናንት ካዳመጡት የሚለይባቸውን ነጥቦች በመጥቀስ ቀደም ሲል በቀረበው ወደ ውሳኔ መሄዱ የተሻለ መኾኑን ይናገራሉ፡፡ አባ ጳውሎስ ግን የኮሚቴውን አባላት ሌሎች ተናጋሪዎችን “እናንተ ባቀረባችኹት አላምንበትም፤ ኮሚቴው በትክክል እና በጥራት አልሠራም፤ ሪፖርቱ ችግር አለበት፤ አልቀበለውም” በማለት ፍርጥም ይላሉ፡፡

ይህን ጊዜ ነበር ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተነሥተው “አዎ፣ ችግር አለ፤” አሉ “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ አባ ሰረቀ ያሳተሙትን መጽሐፍ መሰል ጥራዝ በማስታወስ ንግግራቸውን ሲጀምሩ፤ “አዎ ችግር አለ፤ ዝምድና ነው፣ ይሉኝታ ነው፣ ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው ኮሚቴው እርስዎን ያልጠየቀው? አባ ሰረቀ ከእርዎ ጽሑፍ በመጥቀስ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት እንደሚሉ አውጥተዋል፤ እውነት ይህ ቃልዎ ነው? እንዲህ ብለዋል? መጽሐፉ ከወጣስ በኋላ ለምን በዝምታ አለፉት? ትክክል ነው ብዬአለኹ፤ ካላሉ ደግሞ አላልኹም ብለው ለምን አልተናገሩም? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም?” የሚል ጠንካራ ጥያቄ አንሥተዋል፡፡

የብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥያቄ ሰበቡ የአባ ሰረቀ “እውነትና ንጋት” ይኹን እንጂ አባ ጳውሎስ በፕሪንስተን ቴዎሎጂ ኮሌጅ “Filsata: The Feast of the Assumption of the Virgin Mary and the Mariological Tradition of the Ethiopian Othodox Tewahedo Church” በሚል ርእስ እ.አ.አ በ1988 በነገረ ማርያም ላይ የሠሩት የነገረ መለኰት ዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ከቀድሞው ጀምሮ ውስጥ ለውስጥ ሲነሣ የቆየ ነው፡፡

በነገረ ማርያም ላይ የኢኩሜኒዝም አንድነት(Ecumenical Unity) ለማምጣት በሚል ዓላማ የተሠራው ይኸው ጥናት በአቀራረቡ ንጽጽራዊ ሲኾን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን (ከገጽ 45 - 306)፣ የሮም ካቶሊክን (ከገጽ 307 - 320)፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስን (ከገጽ 333 - 348) እና የፕሮቴስታንት አብያተ እምነትን (ከገጽ 321 - 332) የነገረ ማርያም አስተምህሮ የራሱና በንጽጽር የቀረበበት ነው፡፡ ለዚህም በታሪክ የተደረገ የንግግር ጥረቶችን በማስታወስ በቀጣም በክርስትናው ዓለም አንድ የተዋሐደ የነገረ ክርስቶስ አስተምህሮ መደረስ እንደሚቻል ይመክራል፡፡

አባ ሰረቀ በመጽሐፍ መሰል የዶሴ ጥራዛቸው የጠቀሱት ከገጽ 336 - 338 ያለውን የጥናቱን ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል ግን አባ ጳውሎስ በተለይም የምሥራቅ ኦርቶዶክስን (መለካውያን) የነገረ ማርያም አስተምህሮ ታሪክና ምንነት የዘረዘሩበት ነው፡፡ አባ ሰረቀ እንደነ ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ነገረ ማርያም ከሌሎች ጋራ ለመቀየጥ ካልፈለጉ በቀር አባ ጳውሎስ የኢትዮጵያን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ባቀረቡበት ክፍል ከአንድ በላይ አስረጅዎችን ለመጥቀስ በቻሉ ነበር፡፡

በዚህ ክፍል (በተለይ ከገጽ 45 - 141) ፓትርያርኩ ነገረ ማርያምን በቅዱስ ያሬድ፣ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ድርሳናት ውስጥ ደኅና አድርገው የተነተኑትን ያህል በአንዳንድ መሠረታዊ ጉዳዮች ግን “የአስተምህሮ አንድነት አመጣበታለኹ” ለሚለው አካዳሚያዊ ፕሮጀክታቸው ይመስላል ከኢትዮጵያ ምንጮች የማያገኙትን አስተምህሮ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይትበሃል ካልቃኑት ምንጮች ሲጠቅሱ እናገኛቸዋለን፡፡

ለአብነት ያህል በዚሁ ክፍል አባ ጳውሎስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነፍስዋም በሥጋዋም ንጽሕት (በሁለት ወገን ድንግል) የኾነችና በክርስቶስ የማዳን ሥራ ያልተለየች ብትኾንም ከውርስ ኀጢአት ግን ነጻ እንዳልነበረች የጻፉት የቅብጦችን ምንጭ ጠቅሰው ነው፡፡ አባ ጳውሎስ በጥናታቸው ምንጩን ጠሰው እንዲህ ይላሉ፡-
For the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church the Virgin Mary is the example par excellence of obedience and faithfulness to God. She is two-fold virgin; i.e, virgin both in body and soul, who, though not “immaculate” or free from original sin, yet was all-holy, pure, chose to actively participate in the saving work of God, His Incarnation. (p.306) (Amba Alexander, “The Assumption in the Liturgy of the Church of Alexanderia;” Eastern Churches Quarterly, 9 (1951)

በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና (በ1986 ዓ.ም) በቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፈቃድ በተሰበሰቡ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና 11 ሊቃውንት “ወኢረኵሰት በኢምንትኒ እምዘፈጠራ፤ ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ርኵስ ነገር አልተገኘባትም፤ በነፍስም በሥጋም ሁልጊዜም ንጽሕት ናት፤” (ሃይ. አበ 53) በማለት በቅዱሳን አበው የተመዘገበውን መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዐተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት” መጽሐፍ ግን ስለ እመቤታችን ክብር፣ ንጽሕናና ቅድስና የሚለው የሚከተለውን ነው፡-
“ቤተ ክርስቲያናችን የምታምነውና የምታስተምረው፡- አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት፣ መርገመ ሥጋ፣ መርገመ ነፍስ የሌለባት፣ ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች፣ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ ሐሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች፣ ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት፡፡”

አባ ጳውሎስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞተች ስለተባለ “የበደል ውርስ አለባት” ብለው ከሚያምኑ ጸሐፊዎች ጋራም ተባብረዋል፡፡ እነ ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌም የሚሉት እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህም ከአበው ድርሳናት ምስክርነት ቢያጡ የጠቀሱት ከቅብጦቹ ምንጭ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፡-
Like all daughters and sons of Adam, the holy Virgin Mary died as a result of Adam’s sin. “Mary sprung from Adam, died on consequence of original sin; Adam died in consequence of sin, and the flesh of the Lord, sprung from Mary, died to destroy sin.” (p.302) (Malaty, T.Y. St. Mary in the Orthodox Concept, 1978)

ይህን ሐሳብ በተመለከተ አባ ሰረቀን ጨምሮ እነ ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌና ሌሎችም “ስሜን (ሥራዎቼን) በመጥቀስ ማታለያ አድርገውኛል” ያሉት ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ግለሰቦቹ እሳቸውን በእነርሱ የኑፋቄ ሐሳብ ውስጥ እንዳይጨምሯቸው፣ ለራሳቸው እንዲመለሱና እንዲታገሡ በመከሩበት “ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ” በሚል ርእስ ባዘጋጁት የመጨረሻ መጽሐፋቸው፡-
“እነ ቄስ አስተርኣየ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞተች ስለተባለ የበደል ውርስ እንዳለባት አድርገው ሊቈጥት ሞክረዋል፡፡ ክሕደቱ፣ በደሉ ካልቀረ ሰው የኾነ አምላክ ልጇም የመስቀልን ሞት ተቀብሏልና ከአይሁድ ጋራ ቆመው የጲላጦስን ምስክርነት ቢያስተባብሉ ይሻላል፡፡ ከአበዱ ወዲያ በመንገዱ መሄድ መስነፍ ነው ይባል የለ?
በማለት ተችተዋል፡፡

እንግዲህ ትናንት አባ ጳውሎስ በእመቤታችን ክብር፣ ንጽሕናና ቅድስና ላይ “እምነትዎን ይግለጡ፤ ይመኑ ወይም ያስተባብሉ” ሲባሉ ወዲያና ወዲህ በሚላጉ ንግግሮች አንደበታቸው መተሳሰሩ ነው የተዘገበው፡፡ ከዚህ በኋላ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት 60 ገጽ ያለው የኮሚቴው ሰነድ በቁጥራቸው ልክ ተባዝቶ እንዲደርሳቸውና እያንዳንዱን የውሳኔ ሐሳብ በጥንቃቄ እየተመለከቱ ለመወሰን ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ግንቦት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የሚከበረውን የማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ “ወደ አኵስም እሄዳለኹ” የሚለው የፓትርያርኩ ሐሳብ ያሰጋቸው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በይደር የተያዘው አጀንዳ በውሳኔ ሳይታሰር እንዳይቀር የሚያስጠነቅቅ ማሳሰቢያ ተናግረዋል - “በሐዋርያት ቃል፣ በሐዋርያት ቃል÷ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ይህ አጀንዳ ሳምንትም ቢፈጅብን እርስ በርሳችን ሳንፈታተሽ አንድ ሰው እንዳይሄድ!”

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ!!!

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

29 comments:

Anonymous said...

egiziabehere yemesegene!!!abatochachenene egiziabehere endihe yatsenalene!!!!!


uhhhhhhhhhhhhhhhuuuuuuuuuuuuuuuuuwwwwwwwwwwwweeeeeeeeeeeeeeeeeeyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyeeeeeeeeeeeeeeeeeee!!!!!


egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!egiziabehere yemesegene!!!

asbet dngl said...

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን:: ይህ የአባቶች የሰሞኑ ስብሰባ ከጥቄቶቹ ባሻገር በጣም ሃይማኖታዌና ሞራል ያለው ነው የሜመስል:: ምእመን የኛ ድርሻሽ ምን ይሁን??? እንዴት ባለ መልኩ እንሄን አባቶች እንርዳ ? ውሳኔያቸው እንዴከበር: ጥያቄያቸው በአክብሮት እንዴመለስ ወዘተ የኛ የምእመናት ድጋፍ ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ:: እባካችሁ ወቅቱ አሁን ነው :: መላ እንበል:: ዝም ካልን :አባባ ጳውሎስ :: በተክርስትያን ለመክፈል:አባቶችን ለጥሮታ :ማህበረ ቅዱሳን ለማፍረስ: ከዚያም አልፈው አለኝ ለሜሉት መንግሥት ጠንቅ ለመሆን ሰልት በማያውቀው ግትርነታቸው ታጥቀው የተነሱ ይመስላሉ:: አንድ ቅኖና ፈርሶ በተክርስትያንና ምእመን ቤተርፍ በጐ አይሆንም ትላላችሁ?
የድንግል ማርያም ልጅ ጌታ ሆይ እባክህ እርዳን:: አሜን

well said...

አሜን አባቶቻችን እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ዝናር ያስታጥቅልን በርቱ እና ልጆቻችሁ አለን መናፍቃኑን ጠርጋችሁ አውጡ ከቤተ ክርስቲያናችን ገና ብዙ አሉ እንጀራዋን እየበሉ ተመልሰው የሚበሏት ለሆዳቸው ያደሩ አሉ ገና ይወጣለሁ እናተ ብቻ ብርቱልን ከአባቶቻችሁ የተረከባችሁን የቀናችውን ሐይማኖት ሳትከለስ አስረክቡን መጨረሻውን ያሳምርልን

Anonymous said...

አግዚአብሔር ለአባቶቻቺን በርታት ያድላቸው:: አሁን ከጎበዙ ቢያንሰ ባለፈው ዓመት አንደአደረጉት የተልፈሰፈሰ አቁአም ሳይዙ ጠንካራ አርምጃ መውሰድ

ይቺላሉ ::አባ ፓዉሎስ ልክ አንደአባታቸው ወያኔ ሌላ ዘዴ ቀይረው ወደ አክሱም ሊሄዱ ሞከሩ: አልተሳካም :: ነገ ደግሞ አመመኘ ይሉና ስብሰባው አንድበተን ያደርጋሉ ::

ስለዚህ አባቶች አባካቺሁ በርቱ:: የህ ሁሉ ነገሮችን የማስቀየሻ የአረጀ ዘደአችው ነው:: በንህ ሰውዬ ላይ አንድ ውሳኔ ሳትሰጡ አባካቺሁ አትሌያዩ!! አለበለዚያ

ገታቸን በመንገድ ላይ መስቀል ተሸክሞ የምሰቀልልኝ አጣሁ አንዳይላቺሁ አፈራለሁ:: ደግሞም አምና በቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፉት ውሳኔዎች ለምን ተግባራዊ

አልተደረጉም? አሁንስ የሚወሰኑትን ነገሮች ማን ተግባራዊ ያደርጋቸዋል? ለምሳሌ የሃውልቱ ጉዳይ ? ሰውየው አንደሆኑ አናንተ ወደ በአታቺሁ ሳትመለሱ

የወሳኔ መሻርያ ደብዳቤ መበተን ይጀምራሉ :: አባካቺሁ አባቶች ዝም ብላቸሁ ወስናቺሁ አትሌያዩ:: ስብሰባው አንድ ወር ቢፈጅባቺሁም በርቱ::


አዲስ የተሾመው የመምርያ ኃላፊ ለምን አንደተመደበ አናውቃለን!!

ከዛሬ ፩፪ አና ፩፫ ዓመት በፊት ድአቆን ነኘ በሚልበት ጊዜ ጀምሮ ማህበረ ቅዱሳንን በየአጋጣሚው ሁሉ ሲቃወም የነበረ ሆድ አደር ነው ::

ለነገሩ አርሱ ወሬ ስለቃቅም ማህበረ ቅዱሳን በአግዚአብሔር ቸርነትና ፈቃድ : በገዛ ገንዘቡና ጊዜው የተዘጉ ገዳማትንና አድባራትን አየረዳ አዚህ ደርሶአል::

weldamanuel said...

Abotachachen YEKIDUSAN abotachachen selotachewe Eskemecherschawe Kenante gare yehun Ahunem beyalachuebet tseneatun bertatun yestachu

Unknown said...

የተከበራችሁ አባቶች እውነት ነው የፈጀውን ቀን ይፍጅ ቤተክርስቲያንን ታደጓት፡፡ በተስፋ እንጠብቃለን
“በሐዋርያት ቃል፣ በሐዋርያት ቃል÷ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ይህ አጀንዳ ሳምንትም ቢፈጅብን እርስ በርሳችን ሳንፈታተሽ አንድ ሰው እንዳይሄድ!”

አሉን ዶክተሮች ሁለት፣
አፕሬሽን አድርገው የሚያወጡ አንጀት፡፡
ካወጡ በኋላ ክዘረገፉ፣
መልሰው የማይሰፉ፡፡
ይህንን ግም ከ 10 አመት በፊት ነበረ የሰማሁት/የማውቀው/ አሁን ገና ገባኝ በአባ ጳውሎስ እና በአባ ገሪማ አንጀቱ ያረረው ቀሲስ ነበር የገተጠመው
“ሁልጊዜ ይኼን ማኅበር ምክንያት እየፈለጉ በፖለቲካና በአስተዳደር መክሰስ፣ ማሳደድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? መቼስ ነው የሚቆመው? ማኅበሩን ማዳከም ቤተ ክርስቲያንን በድጅኖ የማፍረስ ያህል ነው፤ የመናፍቃን መቀለጃና መጫወቻ ለማድረግ ነው፤” በሚል ክፉኛ አብጠልጥሎታል፡፡ ድሮስ አላማው ይህ አይደል?
አባ ጳውሎስ በእመቤታችን ንጽሕና ላይ እምነታቸውን እንዲገልጡ ቢጠየቁ አንደበታቸው ተሳሰረ ምነው ለምን ጀግና አይደሉም እንዴ? አዎ እምነት የሌለው ስሟን ለመጥራት እንኳን አይችልም፡፡ እርስዎ ለሌላው ነው የሚበረቱት ስለ ሃይማ ኖቱማ ምን ገዶት? ካወቁት ይህ የንስሃ ጊዜዎ ነው ይጠቀሙበት፡፡

Anonymous said...

Amen!Amen!EGZIABHER kibir misgana yigbaw!Betam des yilal abatochachin menfes kidus kewunetegnoch gar newuna bertulin egnam yemitebikibinin lemesirate Egziabher endefekede kegnachihu nen::

lamelame europe said...

endawe tasefa korecha bazanekobate geza yehenen yasamage AMELAKE YEMASEGANE.
elelelele elelelelel elelelelel

Anonymous said...

abatocacen bertu emebetacen alec engam kgonachu nnen

galela said...

DEJESELAMEWACHE MANEGESTE SAMAYATTEN YAWERESACHOHE////

Anonymous said...

ABA paulos sile emebetachin kidisina memesker kakatachew tinte abso yelebatim belew be andebetacw sinageru kalsemanachew how come we call his name in the kidse and how come we can recive burake from his hand NO WAY Emetachin Eko nech bezih keld ale ende?
Abatoch And Belu emebetachin tirdachu

Anonymous said...

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን:: ይህ የአባቶች የሰሞኑ ስብሰባ ከጥቄቶቹ ባሻገር በጣም ሃይማኖታዌና ሞራል ያለው ነው የሜመስል:: ምእመን የኛ ድርሻሽ ምን ይሁን??? እንዴት ባለ መልኩ እንሄን አባቶች እንርዳ ? ውሳኔያቸው እንዴከበር: ጥያቄያቸው በአክብሮት እንዴመለስ ወዘተ የኛ የምእመናት ድጋፍ ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ:: እባካችሁ ወቅቱ አሁን ነው :: መላ እንበል:: ዝም ካልን :አባባ ጳውሎስ :: በተክርስትያን ለመክፈል:አባቶችን ለጥሮታ :ማህበረ ቅዱሳን ለማፍረስ: ከዚያም አልፈው አለኝ ለሜሉት መንግሥት ጠንቅ ለመሆን ሰልት በማያውቀው ግትርነታቸው ታጥቀው የተነሱ ይመስላሉ:: አንድ ቅኖና ፈርሶ በተክርስትያንና ምእመን ቤተርፍ በጐ አይሆንም ትላላችሁ?
የድንግል ማርያም ልጅ ጌታ ሆይ እባክህ እርዳን:: አሜን

asbet dngl said...

ወንድሞች እህቶች መልካም ነው አባቶችን ማበረታታት ::ነጥቡ ግን ያ አይመስለኝም አባቶች ሃውሉቱ ይነሳ ካሉ የአባቶች ትእዛዝ መፈጸም ያለበት በመጀመሪያ በአባ ጳውሎስ አልያም በእኛ ልጆቻቸው ነው::ሌላው እስኪ እሩቅ አንሄድ እስላም ወገኖቻችንን እንመልከት እንዴት ነው? እስከመቸ የወረቀት አርበኛ ይኮናል::

የድንግል ማርያም ልጅ አባትሆይ እባክህ እርዳን:: አሜን

Anonymous said...

Yewusanewoch ategebaber lay wuyiyit yidereg yalebeleziya enante adisabeban sitilequ yefelegachewun sira mesrat yijemiralu.

Min liyadergu newu wede aksum yemihedut yetsidk sira endemisera sew. Elzabel mekrachewu new !!! Kehedum abatochachin teteki abat kenante mehal temerto gubaewu yiqetil.

Ahunm mahbere kidusan, yeadis abeba senbet timhirt betoch ena christiyanoch bemola leabatochachin tegebiwun tibeqa madreg yitebeqibinal keegziabher gar.

Anonymous said...

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ደጀ ሰላሞች ይኽው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን የተጋረጠባት ፈተና እና እውተኞች አባቶች እከፈሉት ያለው ተጋድሎ አቅርባችሁልናል እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታችሁን ይባርክላችሁ:: ሆኖም ግን ቤተክርስቲያናችን ከከበቧት ፈተናዎች: ከአባቶቻችን ጎን በመሆን እንደ ቤተክርቲያን ልጅነታችን ማድረግ ስለሚጠቅብ ነገር የተጠቆመ ነገር የለም “ ከእኛ ምን ይጠበቃል” ከሚል ጥቆማ ውጪ
ስለዚህ ደጀ ሰላሞች የአባቶቻችን ተጋድሎ ውጤታማ እንዲሆን ሁላችንም የቤተክርቲያን ልጆች በጸሎት ከአባቶቻችን ጎን በመቆም ደጀን እንሁን ቤተክርቲያናችን አሁን ካልታድግናት ችግሩ እየከፋ ነው የሚሄደው ደጀ ሰላሞችም ከምታቀርቡት ሪፖርት ጎን ለጎን ይህንን የጸሎት መርሃግብር እና ሌሎች ከምእመኑ የሚተበቅብንን ነገር ብጠቁሙን
ቸር ዜና ያሰማን

Anonymous said...

ስብሰባው ከተጀመረ ዕለት አንስቶ ፣ ዛሬ ገና ሃይማኖት ነክ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደ ተወያዩ አነበብን ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሁለትና ሦስት ሊያደርጋት የሚችለው የሃይማኖት ህጸጽ እንጅ የቤትና የመኪና ክፍፍል አይደለም ፡፡ ደሃ ስለሆንን ብቻ ሁሉም የህዝብ መኰርኰሪያቸውን ገንዘብና ዳቦ አድርገውት አረፉ ፡፡ ጽድቃችንም በብር የሚገዛ ይመስል ፣ ውይይቱ ሃብትና ንብረት ነክ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኰረ ፡፡

አፍሬ የነበርኩትም ሰው ዛሬ ገና አባት አለን ብዬ ፣ ትንሽ አንገቴን ቀና ማድረግ ልጀምር ነው ፡፡ በብዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መወያየት ፣ መፈተሽና መወሰን ቢገባቸውም ፣ ቀዳሚ ማድረግ ያለባቸውና ትኩረት ሰጥተው መከራከር የሚገባቸው ፣ የዶግማና ቀኖናን ጥሰትን በሚፈጥሩት አባባሎች ላይ ነው ፤ ለማስተካከልም የሚረዳውን አቋማቸውን ግልጽ አድርገው ለምእመን ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

Anonymous said...

Hello Fathers. Thank you, it looks like you are on the path.
What about the relation b/n Aba Paulos and R & B superstar Beyonce, don't he should be asked to explain? What was the spiritual messages that he gave her? Did he baptise and christening her? Isn't she a temptations and sins of our time that he condemns in his daily sermons.Yes, I see you are going to say: Jesus said unto them, "He that is without sin among you, let him first cast a stone at her." Then Jesus said unto her, "Neither do I condemn thee: go, and sin no more." Did Aba Paulos follows Christ in saying "go, and sin no more"?

Anonymous said...

ጉ ድ ድ ድ ድ እእእእእእእእእእ ሁለቱ አምባገነን ጳውሎስ ና መለስ በ አዲስ አበባ ና ዲሲ በዓንድ ቀን ተዋረዱ ። አምላኬ ተመስገን ፤፤ ቀላል ምን ጊዘም የትም ይቀላል ፤፤ አመበቴ አደራ ጠላቶችን አትልቀቂ አደራ ......

Anonymous said...

የቤተክርስትያን ሰላም እንደመንግስተ ሰማያት ውርስ በጉጉት ለምትናፍቁ ውድ የተዋህዶ ልጆች እንኳን የአባቶችን ቆራጥነት የሚያሳይ መልእክት ለማንበብ አበቃችሁ አበቃን። እንግዲህ እንደምታውቁት ምንም እንኳ የቤተክርስትያናችን ሀዘን የማይሰማቸው የእግዚአብሔር ክብር የማያስጨንቃቸው ከውጭ እስከቤተክህነት እንዳሉ ግልፅ ቢሆንም የቤተክርስትያንን ሐዘን የማይወዱ እንባዋን ሊያብሱ ሰላሟን ሊፈልጉ ጠላቶቿን ሊዋጉ እግዚአብሔርን ከሐይማኖታዊ ምግባር ጋር ሊያገለግሉ የቆሙ አባቶችም እነዳሉ አንክድም። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ባለፉትም የሲኖዶስ ስብሰባዎች ላይ በተለያየ መልኩ ከሐሳብ ጀምሮ እስከ ውሳኔ ያሳለፏቸውን ነጥቦች እናውቃለን (ፍፃሜው ባያረካም) ። ዛሬ ግን ከኛ ከሰነፎቹ ከፈራጆቹ ውጭ ቆመን መስማትን ከምንመርጥ ብዙ ሥራዎች ይጠበቅብናል። አሁን ባለንበት ዘመን ህጻናትን ማታለልና ማባበል በማይቻልበት ዘመን እንዴት የጠለቀና የሰፋ እውቀት ለበስ የሆነችውን ብዙ ቅዱሳንን ያፈራች ቤተክርስትያናችንን ንቀው ሲጫወቱብን ዝም እንላለን። ዛሬ እነዳለፉት አባቶች መስዋዕት በመሆን ያሰለፉትን ውሳኔዎች ሳይፈፀም አይተን እንደቀልድ የምናልፍ እንዳይመስላቸው። አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ለሚያሳልፉት ውሳኔ ሁሉ ፈፃሚ አካል ለመሆን ቆርጠን መነሳት አለብን። ተነስተናልም። ለኔ ሐይማኖቴ ክብሬም ሀብቴም ሰላሜም ከአምላኬ የምገናኝበት መሰላሌም ናትና እስከዛሬ ሰሚ ለሆኑኩበት ሁሉ አምላክ በቸርነቱ ይቅር እንዲለኝ እየለመንኩ ዳግም እናዳልከሰስ የጥፋት ተባባሪ ላለመሆን ቆርጫለሁ። በሰው ላይ አድሮ መልካምን የሚሰራ አምላክ በሁላችንም ላይ ስራውን ይስራ። ከሁላችንም በላይ ስለቤተመቅደሱ አምላክ ይቁምላት። አሜን!!!

መላኩ said...

የእግዚአብሔር ሰላምታ ለሁላችን ይድረስ!

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የበደል ውርስ በተመለከተ፡ ላለፉት ሀያ ዓመታት ከጳጳሱ ጋር ውይይት አልተካሄደምን? ይህን መሰሉን በጣም የተሳሳተ አመለካከት ይዘው እንዴትስ ለሃያ ዓመታት ያህል ጵጵስናውን ሊገፉበት ቻሉ?

መላኩ said...

ወንድሞች እህቶች፡ ለምንድን ነው የአማርኛችንን ፊደላት በመጠቀም ጽሑፎቻችሁን የማታቀርቡት? ምንድን ነው ምክኒያቱ? ምንም ምክኒያት፣ ሰበብ ሊኖር አይገባም። ባካችሁ ባካችሁ የሚያኮሩንንና የራሳችን የሆኑትን ፊደላት ካልተጠቀማችሁ መንፈሳዊ ስለሆነ ነገር በላቲን ፊደል ጽሁፍ ለማቅረብ አትሞክሩ።

Anonymous said...

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ብየ ተመስገን እንደምልህ አላውቅም ግን በትንሽ ቃል ምስጋና ይግባህ አባቶቻችን እንዲህ እንዲነቁ ያደረክ:: አሁን ተስፋዬ ሁሉ በጣም ለመለመ አሁንም ፈጣሪዬ እኔን እንኳን ችላ ብትለኝ በስራዬ ነው ግን ቤትህን ጠብቅ

Areaya GEtachew said...

ግድየለም እግዚአብሔር ቤቱን አንደ ቀን ማጥራቱ አይቀርምና ተስፋ አንቁረጥ

Anonymous said...

TEMESGEN AMLAKIE CHER WARE YASEMAHEGN

Anonymous said...

Original sin is nothing else but the inclination to sin in the teaching of Our Church. We all know that Our Lady the Virgin Mary has no inclination to sin at all: bemeserat becha aydelem, bemayet, bemashetet, bemedases, bemesemat, yehen bemesaselew hulu. keenatua Mahetsen gemiro leyu netsehit adergo leenatenet merto yasegegnat ersu aydel ende;lenegeru hulet baheri, kebat wezetu belew kalu selewers hatyat endih aynet hasab benorachew ayegeremem. Be 1987 wede and gedam hegde neberena and aregawi abat Aba paulos tewahedo nachew belew teyekewegn endeneber astawesalehu. lekas...tadya Adam gena benefisu aldanem malet newa! Kidus paul men belo yehon, woy enen mesel woy simen meles alalachew yehon?

Wolde Kirkos said...

So, what makes Tewahedo different than Catholicism? The facts are twisted and people seem to be moved by emotions than facts. How could one claim that Tewahedo faith different than than the Oreantal dogma? Please read below that was extracted from the Malaranka website our sister Church on this issue. Also read Pope Shenauda's book titled "Comparative Theology".

What are the differences between the Catholic Church and the Oriental Orthodox Churches?

What are the differences between the Catholic Church and the Oriental Orthodox Churches? a. Regarding the place of St. Peter

According to the Catholic Church, St. Peter is the foundation stone of the Church. Therefore, Peter has authority over the whole Church. The Orthodox Churches believe the authority is given to all Apostles whoare called by Jesus – not to just one Apostle (Ephesians 2:20). The teaching of the Orthodox Churches regarding the foundation stone (Matthew 16:18) and the keys of the kingdom of heaven (Matthew 16:19) are synoptically given below:

a) The Foundation Stone:

Christ is the real Rock: “…the Rock was Christ” (1Corinthians 10:4).

1

2 Peter declared the faith of the Apostles; and the rock is their faith, upon which the Church is built. 3 Peter believed and confessed his faith, signifying the Church is built upof true believers, who are the rock.

b) The Keys of the Kingdom of Heaven: The Keys represent the authority to bind and loose or to forgive sins (Matthew 16:19). Jesus gave the authority ‘to bind and loose’ to all disciples (Matthew 18:18; John 20:23) b. Regarding the position of the Bishop of Rome The Catholic Church teaches that the Bishop of Rome is the ambassador of Christ, the head of the whole visible church of Peter, and is the symbol of unity of the Church. It teaches not only that the Pope has the supreme authority but also that he is infallible. The Orthodox Churches teach that all Priests are ambassadors of Christ, and that Peter does not have any special authority over the Church. Because all Apostles are equal as far as priestly rights are concerned, there is no need for a visible head for the whole church except Christ, and that the Holy Synods are the symbol of unity of the visible Church. They affirm that the supreme authority of Peter and the infallibility of the Pope are not in line with Christian principles. c. Divine and human natures in Christ In accordance with the Chalcedon Council, the Catholic Church gives emphasis to the separate divine and human natures in Jesus Christ. The Oriental Orthodox Churches, rejecting the decision of the Chalcedon Council, teach the unity of the divine-human nature in Jesus Christ. d. Number of Universal Synods The Roman Catholic Church recognises 21 Universal Synods while the Oriental Orthodox Churches recognise only the first three synods of Nicea, Constantinople and Ephesus. e. Addition of Filioque clause The Catholic Church altered the Nicene Creed regarding the Holy Spirit (Filioque) by adding proceeding “from the Son also”, which the Orthodox Churches reject. f. Immaculate conception of St. Mary The Catholic Church teaches that Virgin Mary was born sinless. The Orthodox Churches believe that Christ died for humanity, including St. Mary. And she was made holy for the incarnation of the Son of God, with the annunciation of Gabriel. g.Transubstantiation The Catholic Church teaches the dogma of Transubstantiation, which means the Bread and Wine in the Holy Eucharist undergoes a change of substance literally into the Body and Blood of Christ, without change of appearance. The Orthodox Churches believe in the real presence of the Body and Blood of Christ in the Holy Eucharist, without change of substance. The Orthodox dogma is called Consubstantiation.

Anonymous said...

Sewuyew edasebut tinfash lemewused Axum hedew yehon?

Anani zefasiledes said...

Begit Amarigna tetekime lewedefitu etsifalehu.. Gim yimesgen mechem sitegeber binayewu tiru newu.Elay andiwondime endalut Abbatochachin lerasachewu sira tegzi honewu ahunim yewesenutin wusane asifetsimewu newu meleyayet yalebachewu alebelezia gin minim tikim yelewum Sewuyewu lib yelachewum. Eski esachewum yimekeru yikiritam yideregilachewal, poleticawiunimyisiru minim chigir yelewum, gin betechristianin lekek adirigo beras eminet yaramidu.
Abo amlake endegena eyen, asazinenih newuji endezih andersim neber.

Anonymous said...

we should to have a courage to say Aba Paulos go! Aba Paulos go! Aba Paulos go! .
that's the only solution i guess.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)