May 11, 2012

የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ሁለተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎ

·         አጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴው 20 ጉዳዮችን በረቂቅነት አቅርቧል
·         ከአቡነ ፋኑኤል ጋራ በተያያዘ በዋሽንግተን የተፈጠረው ችግር በአጀንዳዎቹ ዝርዝር ውስጥ ራሱን ችሎ አልተመለከተም
·         ፓትርያርኩ የዕርቀ ሰላም ንግግር አጀንዳን ተቃውመዋል፤ በተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አጀንዳ አቋማቸው ጸንተዋል

·         “በእኛ ዘመን የተከፈለች ቤተ ክርስቲያን ለቀጣዩ ትውልድ አናስረክብም፤ ሹመቱ ዕርቀ ሰላሙን የሚያደናቅፍ በመኾኑ ወቅቱ አይደለም /ብዙኀኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት/
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 2/2004 ዓ.ም፤ May 10/ 2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በትናንትናው ዕለት በቋሚ ሲኖዶስ የቀረቡለትን 15 የመነጋገርያ አጀንዳዎች የተመለከተውና በምልአተ ጉባኤው የተሠየመው ስምንት አባላት የሚገኙበት አጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴ 20 የመነጋገርያ ጉዳዮችን ዛሬ ጠዋት ለምልአተ ጉባኤው አቅርቧል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቲያስን በሊቀ መንበርነት፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስን በጸሐፊነት በመምረጥ ሥራውን የቀጠለው ኮሚቴው÷ ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ ተቀርጾ በቀረበው አጀንዳ ላይ በስፋት በመወያየት ዘመኑን የዋጁና ወቅቱን የተመለከቱ የ20 አጀንዳዎችን ዝርዝር ለምልአተ ጉባኤው አቅርቧል፡፡

እኒህም በተቀመጡበት ቅደም ተከተል መሠረት፡- 1) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የመክፈቻ ንግግር፤ 2) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ዓመታዊ ሪፖርት፤ 3) ስለ ቤቶችና ሕንጻዎች ጉዳይ፤ 4) በላሊበላ የሰባት ወይራ ሆቴል መመለስ እና ወደ ማእከል ስለሚመጣበት ጉዳይ፤ 5) ስለ ማኅበራት ጉዳይ፤ 6) ማእከልን ጠብቆ አለመሥራት እያስከተለ ስለ አለው ችግር፤ 7) ስለ ሰላም ጉዳይ፤ 8)በላሊበላ ስለተፈጠረው ችግር፤ 9) ስለ ቃለ ዐዋዲው መሻሻል፤ 10) ስለ ልማት ኮሚሽን፤ 11) ስለ ሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ፤ 12)በአኲስም ሀገረ ስብከቱና በርእሰ ገዳማት ወአድባራት መካከል ስለ አለው ችግር፤ 13) ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ በኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርት መስማትና መወሰን፤ 14) ስለ ሲዳማ ሀገረ ስብከት ጉዳይ፤ 15) ስለ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ፤ 16) ስለ ስብከተ ወንጌል ጉዳይ፤ 17) ስለ አብነት መምህራን ፍለሰት ጉዳይ፤ 18) ስለ ተጀመረው የአሜሪካው ዕርቅ ጉዳይ ሪፖርት መስማት፤ 19) ልዩ ልዩ ጉዳዮችን በተመለከተ፤ 20) የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ምርጫ የሚሉ ናቸው፡፡

አጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴው ዝርዝሩን ለምልአተ ጉባኤው ካቀረበ በኋላ ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በተራ ቁጥር 18 ላይ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙ አባቶች ጋራ የተጀመረው ዕርቅ ጉዳይ በአጀንዳነት መያዙን ተቃውመዋል፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት “ፖሊቲከኞች ናቸው” በሚልም በዕርቀ ሰላሙ ሂደት መቀጠል ላይ እንደማያምኑበት ተናግረዋል፤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ተወክለው ከሄዱት ልኡካን መካከል አንዱን አባል በስም በመጥቀስ “ወደኋላ ቀርተው ከእነርሱ ጋራ ነገር ሲሸርቡብኝ ነበር” በማለት ወቅሰዋል፡፡

በአንጻሩ ፓትርያርኩ በዕርግና እና በሞተ ዕረፍት የተለዩ አባቶችን በመቁጠር ተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት መሾም እንዳለባቸው ከዚህ ቀደም በያዙት አቋም ጸንተዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሚያንጸባርቋቸው አብዛኛዎቹ አቋሞች የብፁዕ አቡነ ገሪማን፣ የብፁዕ አቡነ ማርቆስን፣ የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስንና የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ድጋፍ ያገኙ ቢኾንም ከብዙኀኑ የመደበኛው ጉባኤ አባላት ግን ጠንካራ ተቃውሞ ነው የገጠማቸው፡፡

አቡነ ጳውሎስ በሰሜን አሜሪካው የዕርቅ አጀንዳ ላይ ስለሰነዘሩት ተቃውሞ ሐሳባቸውን የሰጡ አባቶች÷ “በእኛ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፍላ አትቀርም፤ ለቀጣዩ ትውልድ ለሁለት የተከፈለች ቤተ ክርስቲያን ማስረከብ አንሻም፤ የዕርቅ ሂደቱ መቀጠሉ ግድ ነው፤ በእግራችንም ቢኾን እዚያው ሄደን እናሳካዋለን” የሚሉ ጠንካራ ምልልሶችን ከፓትርያርኩ ጋራ መለዋወጣቸው ተዘግቧል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በአጀንዳው እንደተመለከተው የመንበረ ፓትርያርኩ ልኡካንና በስደት የሚገኙት አባቶች ተወካዮች በየካቲት ወር ተደርጎ በነበረው ውይይት ላይ የሚያቀርቡትን ሪፖርት እንደሚያዳምጥ የስብሰባው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

አቡነ ጳውሎስ ያለማሳለስ እየተሟገቱበት ያለውንና በብዙዎች ዘንድ “የፓትርያርኩ አዳዲስ የዓላማና ጥቅም ወዳጆች ማፍሪያ ነው” የሚባለውን የተጨማሪ ኤጴስ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይንም “ለጊዜው ያለነው እንበቃለን፤ ከተጀመረው ዕርቅ አንጻር ወቅቱን የጠበቀ አይደለም፤ የዕርቁን ሂደት ያደናቅፋል፤ ያለውንም ችግር ያባብሳል” በሚል በሚበዙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመካከል የወዲያውንም የወዲሁንም ሐሳብ በመዳኘት ለመሸምገል የሞከሩ ብፁዓን አባቶች የነበሩ ቢኾንም ምልአተ ጉባኤው ቀትር ላይ የተነሣው የሚጠቀስ መግባባት ላይ ሳይደረስ ነው፡፡

ከስብሰባው ጋራ በተያያዘ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ገና ባልተወሰነባቸው አጀንዳዎች ሳይቀር መሠረት የሌላቸው አሉባልታዎች እያናፈሱ ይገኛሉ፡፡ ከእኒህም አንዱ በአጀንዳ ተራ ቁጥር 13 “ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ በኮሚቴው የሚቀርበውን ሪፖርት መስማትና መወሰን” በሚል የተመለከተው ሲኾን÷ ሊቃውንት ጉባኤው የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተመርቶለት በጥቅምትና ኅዳር ወራት በመረመራቸው ማስረጃዎች “መወገዝ ያለባቸው፣ ከዕውቀት ማነስ የተሳሳቱና ወደ ት/ቤት መግባት ያለባቸው፣ መመከር የሚገባቸው” በሚል የከፈላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና አቀንቃኞች መኖራቸው ተዘግቧል፡፡ እንዲህ ዐይነት አሉባልታዎች የሚናፈሱት ምናልባትም ሊቃውንት ጉባኤው የውሳኔ ሐሳቡን ለሊቃነ ጳጳሳቱ ኮሚቴ ከመራ በኋላ በክትትል ማነስ የተፈጠሩ ክፍተቶችን በመበዝበዝ ጠንካራ አቋም በያዙቱ ላይ ጫና ለመፍጠር፣ ጉዳዩን የሚከታተለውን ቀናዒ አገልጋይና ምእመን አስተያየትንም በማዛባት ተስፋ ለማስቆረጥ ከመቋመጥ አያልፍም፡፡

ከቀትር በኋላ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወደ አጀንዳው በመግባት መወያየቱን እንደሚቀጥል የጉዳዩ ተከታታዮች ተስፋ አድርገዋል፡፡


ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

16 comments:

Anonymous said...

yemenafequ dehere getsoche bemulu werea bemanafese laye nachew...yetelemede qesetachewen lematenakere endimechachewe

well said...

አባ ፋኑኤል ተመልሰው ወደ ሰሜን አሜሪካ ከሄዱ በሰሜን አሜሪካ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የበለጠ ትከፋፈላለች ከፍተኛ የሆነ ችግር ይፈጠራል እባካችሁ ይህ የምታነቡ ወገኖች ሁላችሁ ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ እንዳይቀር ለምናውቃቸው የስብሰባው ተካፋዮች እናሳስብ ሰውየውን ጥላቻ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሲባል ነው እውቀት ወይም ችሎታ ያለው አባት ይላክልን ካልሆነ ስለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውድቀት ዘላለም ስናለቅስ ነው የምንኖረው እባካችሁ አደራ አሳስቡ

Anonymous said...

teqetere welowe mene endemimesele betolo astawequn!!!!

egiziabeher betekerstiyanene yetebeqelen

Anonymous said...

Antew EgiZiAbHer Fitaw engi endiaw ke ae'emero belay new hulum neger

Anonymous said...

The holy synod looks more powerless now probably they are intemediated by...., The only solution is to remove the guy the so called " patriarch". And the holy synod is not going to do this. Therefore, we have to take it to our hands. Like the muslims we have to revolt against the patriarch and his gang club members. You may say this is not Godly, but God needs people to do his job and we are the ones to do that. After all, he is not some one anointed by the holy sprit, He is brought to patriarchate position by.... So if the holy synod fail to remove him, we will remove him in any way....you have to know that the Muslims are going to have the people whom they elect. How about us. The holy synod members look afraid. Otherwise, they could have considered the following agendas

1) failure to implement earlier decisions made by the holy synod. This is totaly because of the guy.
2) The issue of north America dioce, the truble maker and the member of the gang club, "aba" Fanuel.

galela said...

EGA BATSALOTE ENEREDACHAWE.
YALETADALO ABATE

Anonymous said...

chere wore yaseman (Hg)

Anonymous said...

ቅዱስ ሲኖዶስ መቼም ቢሆን ቅድስናዉን አያጣም።የሚያኮሩ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ዉሎ ዓላማ በትክክል የሚተረጉሙ አባቶች አሉን። ስለዚህ ወዳጄ በዚህ ስጋት አይግባህ።አሁን ተኩላዉ ከመንጋዉ ተለይቷል። እርቅ፣ ሰላምና ፍቅር የክርስትና መሠረታዊ አስተምህሮዎች ናቸዉ። እርቅና ሰላም የማይወድ ዲያብሎስ ብቻ ነዉ። በዚህ ደግሞ አቡነ ጳዉሎስና ግብረ አበሮቻቸዉ አቡነ ገሪማ፣አቡነ ማርቆስ፣አቡነ ፋኑኤል፣ ወዘተ በይፋ ማንነታቸዉ ታዉቋል። ስለሆነም ከአሁን በኋላ እንደ ባለፉት ጊዜያት በእዉነተኞቹ አባቶቻችን ሕይወት መቀለድ አይሞከርም። አባ ጳዉሎስና ግብረ አበሮቻቸዉ የያዙትን የመስቀል ምስጢር፣የተጎናጸፉትን የክብር አስኬማ ደግመዉ ሊማሩ በሕይወታቸዉ ሊመረምሩት ይገባል።ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ህልዉና ሳይሆን እየኖሩ ለሌሉት ኣባቶቼ ለአባ ጳዉሎስና ወዳጆቻቸዉ አዘንኩ። "በጨዋ አነጋገር" ሳይገባቸዉ ለተገባቸዉ ማዕረግ አዘንኩ። ብዕሩ ዘ-አትላንታ

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

ቅዱስ ሲኖዶስ መቼም ቢሆን ቅድስናዉን አያጣም።የሚያኮሩ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ዉሎ ዓላማ በትክክል የሚተረጉሙ አባቶች አሉን። ስለዚህ ወዳጄ በዚህ ስጋት አይግባህ።አሁን ተኩላዉ ከመንጋዉ ተለይቷል። እርቅ፣ ሰላምና ፍቅር የክርስትና መሠረታዊ አስተምህሮዎች ናቸዉ። እርቅና ሰላም የማይወድ ዲያብሎስ ብቻ ነዉ። በዚህ ደግሞ አቡነ ጳዉሎስና ግብረ አበሮቻቸዉ አቡነ ገሪማ፣አቡነ ማርቆስ፣አቡነ ፋኑኤል፣ ወዘተ በይፋ ማንነታቸዉ ታዉቋል። ስለሆነም ከአሁን በኋላ እንደ ባለፉት ጊዜያት በእዉነተኞቹ አባቶቻችን ሕይወት መቀለድ አይሞከርም። አባ ጳዉሎስና ግብረ አበሮቻቸዉ የያዙትን የመስቀል ምስጢር፣የተጎናጸፉትን የክብር አስኬማ ደግመዉ ሊማሩ በሕይወታቸዉ ሊመረምሩት ይገባል።ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ህልዉና ሳይሆን እየኖሩ ለሌሉት ኣባቶቼ ለአባ ጳዉሎስና ወዳጆቻቸዉ አዘንኩ። "በጨዋ አነጋገር" ሳይገባቸዉ ለተገባቸዉ ማዕረግ አዘንኩ። ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

sile WALIDIBA guday adjenda aleteyazem eindae?.yigermalu... tesfa besoch nachew!!!!! hodamoch !!!!

Anonymous said...

ከአጀንዳዎቹ መካከል የዋልድባ ገዳም ጉዳይን የሚመለከት አጀንዳ አለመኖሩ በጣም አሳዛኝ ነው ።ሕዝቡ በየሀገሩ በየደብሩ ስለገዳሙ እያለቀሰ፣ መገናኛ ብዙኃኑ ሰፊ የአየር ጊዜ ሰጥተው ያለውን ችግር እያሳዩ፣ የገዳሙ መነኮሳት የሰሚ ያለህ እያሉ እንባቸውን ወደ ሰማይ እየረጩ ባለበት በዚህ ወቅት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ሲኖዶስ በቀዳሚ አጀንዳነት መፍትሔ ሊሻለት ሲገባ ምን አገባኝ በሚል መንፈስ በዝምታ ለማለፍ መሞከሩ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስፈርዳል ።
መንፈሳዊነትን ከማን እንማር?????? እባካችሁ አባቶቻቸን ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ለእውነትና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልዕልና ስሩ፥ በፍርድ ቀን እያንዳንዱ ስለ ሃላፊነቱ እንደሚጠየቅ ምንጊዜም አትርሱ ።ቀና ብዬ በእድሜና በመንፈሳዊ ጸጋ የምትበልጡ አባቶቼን ለመምከር በሞከርኩ ይቅር በሉኝ ማሩኝ። ግራ ገብቶኝ እኮ ነው።

Anonymous said...

what about Waldeba????? Zikuala???? Asebot????.... My God!!! and I was hoping to hear their names, well I am proven wrong.

Anonymous said...

GOD keep Ethiopian Orthodox church! We want removal of paulos.

Anonymous said...

የሁሉም የቤ/ክ ችግር መሰረቱ ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ሰውየው ከመንፈሳዊነት ይልቅ ፓለቲካዊ አካሄድን የሚጠቀሙ ስለሆነ ሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶች ምንም ሊያደርጓቸው አይችሉም፡፡
በጣም የሚያሳዝነውም ሁሉም ችግራቸውን እያወቀ በሳቸው ፖለቲካዊ አካሄድ መሸንገሉ ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳንም ቢሆን ለስሙ ከሳቸው ጋር ይመስላል እንጅ ልቡ ከፓትርያርኩ ጋር እንዳልሆነና ችግራቸውንም ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ግልጽ ነው፡፡ ግን የሚገርመው ማህበሩም ያ ዲን ዳንኤል እንዳለው ህልውናውን ብቻ ስለሚፈልግ ደፍሮ እሳቸውን መጋፋት አይፈልግም፡፡ እሳቸውም ደስ ሲላቸው በፖለቲካዊው ንግግራቸው “ልጆቼ “ እያሉ ያሞኙታል፡፡ በርግጥ እሳቸውም ማህበሩ ድራሹ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፡፡ ግን ማጥፋት ስለማይችሉ እያታለሉ ይዘውታል፡፡
ፓትርያርክ አባታችን አትሟቸው፤ ስማቸውን አታንሱ እያለ ሲከራከር የነበረ ሁሉ አሁን ወደተሳዳቢነት ነው የተቀየረው ሌላ ምን አተረፈ፡፡ ሌሎች ቀድመው ተሳደቡ ሌላው ደግሞ ዘግይቶ ተቀላቀለ፡፡ በዚህ ሰዓት ከተራ ምእመን እስከ ገዳማዊያን ፓትርያርኩ ስማቸው ሲነሳ የሚያመው ነው የሞላው፡፡ ታድያ ሰውየውን በቅድሴዉም ለስሙ ስማቸው ያጠራል እንጅ ማን ከልቡ ጸለየላቸው፡፡ እኛም ወይ በጽድቃችንና በጸሎታችን መፍትሄ አላመጣን ካልሆነም ደግሞ ጨክነን በሥጋዊው መንገድ ተጉዘን መፍትሄ አላመጣን ፡ ከሁለት ያጣ ጎመን!!!
አምላክም የእኛን ክፋት አይቶ ራሳቸው እንዳሉት /“እናንተ ደግ ብትሆኑ ደግ አባት ይሰጣችሁ አልነበረም” /እንዳሉት ይችን ቤ/ክን ለተሃድሶዎች እስኪያስረክቡ ወይም ደግሞ ተአምሩን ከላከላቸው ለንስሃ እድሜ እየሰጣቸው ነው፡፡
አሁን የሚያስፈልገው እንደ ሙስሊም ወገኖቻችን ”የቅዱስ ሲኖዶስ ስልጣን ይከበር፤ ፓትርያርኩ አይወክሉንም” ብሎ መጋፈጥ ብቻ !!!
ዘጊዮርጊስ

Anonymous said...

ወንድሞች አይ ብዙ ነገር አልተረዳንም


ፈርኦንም እስኪጠፋ ድርስ ህዝበ እስራኤልን ለ40 ዓመት አስጨንቋል።

አሁንም አባ ጳውሎስም 20 ጨርሰዋል ገና 20 ዓመት ይቀራቸዋል።

አትድከሙ

Anonymous said...

All our brothers and sisters above say samething. THE , I say THE, source of our problem is the Patriarch and his cronies.

If we foolishly and stubornly defend, the hierarchy of the church, like Mahbere kidusan and others did, we are going down drain. I don't question good intention of organizatioins like mahbere kidusan or others who defend oneness and hierarchy of the church. They mean well. This are dedicated and faithful brother. But It is not the time. "LEHULUM GIZE ALEWU" says wise SOLOMON. However, blindly following the church hierarcy will only push more political, distructive and divisive decisions to our locals(Atbias). The solutions is temporarly resort to congregartionla church structure lead by guba'es elected by priests and lay people. we follow our church dogmas, But, will not allow greedy and politically motivated pope and his cronies funnel their decisions down to us. We should realize by now the so called fathers are out to fulfil their greedy and politically motivated wishes. Peace

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)