May 14, 2012

ከዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዝግጅት ጀርባ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 5/2004 ዓ.ም፤ May 13/ 2012/ READ this article IN PDF)፦ በ56ኛ ዓመት ቁጥር 126፣ ሚያዝያ ግንቦት 2004 ዓ.ም ታትሞ በወጣው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጋለጥ” በሚል ርእስ ስለ ሰፈረው ርእሰ አንቀጽ፣ “ቤተ ክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ” በሚል ርእስ ስለተዘጋጀው ሐተታ አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ “እኔ ማንንም አልፈራም፤ ጽሑፉ አያስጠይቀኝም እንጂ ብጠየቅበት አልፈራም፤ በይዘቱ አዲስ አይደለም፤ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው አቀራረብ ሲጽፉት የቆዩት ነው፤ እኔ ለመጻፍ የሞከርኹት የቤተ ክርስቲያን ህልውና እየተነካ ነው ብዬ በማምንበት ስለ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ነበር፤ አባ ጳውሎስ ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይሻሻል አሉ፤ እውነቱን ለመናገር ግን ጽሑፉ ከውጭ የመጣ እንጂ በዝግጅት ክፍሉ የተጻፈ አይደለም፤ በስሜ እየተነገደብኝ ነው፤” ብለዋል፡፡


ዋና አዘጋጁ ጽሑፉ ከውጭ ተዘጋጅቶ እንደመጣ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ አዘጋጁን አካል ለማወቅ በተደረገ ጥረት÷ “አባ ጳውሎስን ደግፋችኹ ከጻፋችኹ ማንም አይነካችኹ፤ ከተነካችኹም እኛ አለንላችኹ፤ ሁሉም ወንጀለኛ ነው” በሚል የጥቅም ማበረታቻ የተቀበሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ሓላፊ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና እንደ ቀበሮዋ ዘለው ዘለው የሻቱትን ማዕርገ ጵጵስና ቢያጡት የተሾሙትን አባቶች ማሸማቀቅ የመረጡት አባ ሰረቀ፤ ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ የሰጡት አባ ፋኑኤልና ዦቢራው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን መኾናቸው እየተነገረ ነው የአባ ጳውሎስ አይዟችኹ ባይነት (ቡራኬ) ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡ ይኹንና የዝግጅት ክፍሉም በጽሑፉ ላይ ማሻሻያ በማድረግና እንዲታተም በመፍቀድ፣ ምናልባትም የጥቅሙም ተካፋይ በመኾን መጠየቁ እንደማይቀር ግልጽ ነው፡፡
ከአቡነ ፋኑኤል ቤቶች አንዱ
በጋዜጣው ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች “ጋዜጣው የደገፈውንና የነቀፈውን አያውቅም፤ ለምሳሌ አባ ፋኑኤል ስለ ራሳቸው እያወሩና ቀሲስ ዶ/ር መስፍንን ከስሰው የከበሩ ቢመስላቸውም በውስጥ ገጽ በተጻፈው ጽሑፍ ደግሞ ‹በእግዚአብሔር ገንዘብ የግል ቪላ ገንብተው ያከራያሉ፤ እንደ ዓለማዊ ሰው ለአባት የማይገቡ ዘመናዊና ከፍተኛ ዋጋ ያለው መኪና ገዝተው ያሽከረክራሉ፤ ሌላም፣ ሌላም ተብለው የተወነጀሉት ዋነኛው ራሳቸው ናቸው፤” በማለት ተችተዋል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

9 comments:

Anonymous said...

የለንም ሞተናል
ሥርዓታችን ሲፈርስ ሃይማኖት ሲሰደብ:፦
መሳለቂያ ስንሆን ከቶ ያለገደብ፦
አስመሳይ ተኩላዎች እንድህ ሲቀልዱ፦
ሃይ የሚል ሰው ጠፍቶ ዝምታን መውደዱ፦
በቃ ኦርቶዶክሶች ለካ ተንቀናል፦
የቆምን እንዳይመስለን የለንም ሞተናል።
ቅኔና መዝሙሩ በዘፈን ሲቀየር፦
ተኩላ ሲመላለስ በቤተ መቅደስ በር፦
የእምነት ወረራ ግፍ ሲፈጸምብን፦
መናፍቅ ሲመረጥ ሲታጭ ለስልጣን፦
እስከመቸ ድረስ ዝምታ እንመርጣለን፦
ተነስ የተዋህዶ ልጅ ዛሬ ነው ቁርጥ ቀን።
አንዱ በር ሲዘጋ ባንዱ እየሾለኩ፦
የመናፍቅ ትምህርት በይፋ ሲሰብኩ፦
በአውደ ምህረት ላይ ዘፈንን ሲያዜሙ፦
ቤተክርስቲያንን ሲያቆስሉ ሲያደ ሙ፦
ስድብን የተሞላ መግለጫ ሲያወጡ፦
ሆድ ይፍጀው እያሉ እንድህ መ ቀመጡ፦
አይገባኝም ለኔ ትእግስቴ ገንፍሏል፦
ያለን እንዳይመስለን የለንም ሞ ተናል።
ስለዚህ ወገኔ ተነስ ተነቃነቅ፦

Anonymous said...

የለንም ሞተናል
ሥርዓታችን ሲፈርስ ሃይማኖት ሲሰደብ:፦
መሳለቂያ ስንሆን ከቶ ያለገደብ፦
አስመሳይ ተኩላዎች እንድህ ሲቀልዱ፦
ሃይ የሚል ሰው ጠፍቶ ዝምታን መውደዱ፦
በቃ ኦርቶዶክሶች ለካ ተንቀናል፦
የቆምን እንዳይመስለን የለንም ሞተናል።
ቅኔና መዝሙሩ በዘፈን ሲቀየር፦
ተኩላ ሲመላለስ በቤተ መቅደስ በር፦
የእምነት ወረራ ግፍ ሲፈጸምብን፦
መናፍቅ ሲመረጥ ሲታጭ ለስልጣን፦
እስከመቸ ድረስ ዝምታ እንመርጣለን፦
ተነስ የተዋህዶ ልጅ ዛሬ ነው ቁርጥ ቀን።
አንዱ በር ሲዘጋ ባንዱ እየሾለኩ፦
የመናፍቅ ትምህርት በይፋ ሲሰብኩ፦
በአውደ ምህረት ላይ ዘፈንን ሲያዜሙ፦
ቤተክርስቲያንን ሲያቆስሉ ሲያደ ሙ፦
ስድብን የተሞላ መግለጫ ሲያወጡ፦
ሆድ ይፍጀው እያሉ እንድህ መ ቀመጡ፦
አይገባኝም ለኔ ትእግስቴ ገንፍሏል፦
ያለን እንዳይመስለን የለንም ሞ ተናል።
ስለዚህ ወገኔ ተነስ ተነቃነቅ፦
source Misganaw

Anonymous said...

ይህ ቤት በአቡነ ፋኑኤል ስም ስለመመዝገቡ ትክክለኛ መረጃ ልትሰጡን ትችላላችሁ?

ለምሳሌ: የቤት ካርታ ወይም በእርሳቸው ስም የተመዘገበበት የመዝገብ ቁጥር ወይም መንኛውንም የባለቤትነት ማረጋገጫ የሚያሳይ::

አለበለዚያ ስም ለማጥፋት ያደረጋችሁ ስለሚያስመስ ከሚል እሳቤ ነው ይህንን አስተያየት የጻፍኩኝ::

በዚህ አጋጣሚ ግን ሰዎቹ ደጀሰላም መጦመሪያን የሚፈሩትን ያህል እግዚአብሔርን ቢፈሩ ምንኛ በተደሰትን ነበረ::

galela said...

yaletadalo 'abate'ABONA'....................

Anonymous said...

Lewnet Ykomachehu Kirstian Yetewhido Lijoch, MK, Yesenbet Temairwoch, Yetemeket Bal Commeettee, Yandenet Gubaye, Tekelala Yeketemam Nuariewoch Ena Lelochem Bewichem Bemelaw Alem Newariwoch HULACHINEM YEMIAQUARET SELAMAWY SELF ENEWTA. BEWNEt kezieh behuala lELAA Meftihe anagegnem Yehennen Edelem Anagegnem. KeAba Pawlos Mefthie Enagegenalen malet zebet New. Abatoch Yegemerut Tenkara Aquam Endilezebe Egena Beselamawy Selfe Ena Berhab Adma Dejen Enhunachew. Lezhime Embetachenen Amalage Yezen. Tsadkan Semetaten meketa adregen. Endegna Sira Sayhone Yegiziabheren Chereneten Blebe Mulenet Tesfa Adregen.

lamelame europe said...

feredone egame enesete bayalanebate enekawame.yechalale balafawe ena kamenorebate wata yaleakatama dn bagashawe yematale tabelo ande kale honane lamakawame tanagagerane yaabatoche tselote yezote kara.YABATOCHEN LAABATOCHE YAEGEANE EGAENESERA

galela said...

ENA TTEGESETA ALEKOLE YAMECHELAWEN LAMARAGEZEGEGO NAGE

Anonymous said...

derose nke pastor paulosen pastor fanuel mene yetebeqale!!!!!

andnet said...

መላው የኦርቶዶክስ ተከታዮች በምነታችን እመጣውን አደጋ በዝምታ ውይንም በፍራቻ ማለፍ ለመጭው ትውልድ ታሪክን ቅርስ እምነትና ፍልስፍና ማስጣት በመሆኑ በትክክል ለዚህች የታሪክ መሰረታችን የሆነችውን እናት ቤተክርስትያን ለማዳን የማንነሳ ከሆንን ለስም የምንጥራባት እንጂ የእምነታችን ማእገር እንዳልሆነች ልንጋለጥ እንድሆንን እያስመሰከርን በመሆናችን ፕሮተስታቶች በማህላችን ገብተው እንዳዳከሙንና እኛም እንድተሸነፍን እያስመሰከርን ለመሆናችን አንዱ መገለጫችን የአሰቦት የዝቋላ በሳት መቃጠል የዋልድባን መታረስ የሚያሳየው እኛን ኦርቶዶክስ ልጆች ውርደት በመሆኑ በአንድነት ገዳሞቻችንና እምነታችንን ለማስከበር በጽናት ለመቆም መሰባሰብ ለማዳን በእግዚአብሔር ስም እማጸናለሁ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)