May 13, 2012

(UPDATED AGAIN) የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ሦስተኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎ

አቡነ ጳውሎስ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ጋራ ማበራቸውን የቅ/ሲኖዶስ አባላት ገለጹ  

·         ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣይ ለሚኖረው አመራር የመላው ካህናትና ምእመናን ጸሎትና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ተጠይቋል
·         በአባ ጳውሎስ፣ አባ ፋኑኤልና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ምክርና ኮሚሽን አድራጊነት የተጻፈው የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ርእሰ አንቀጽ እና ዘገባ በፈጠረው ቁጣ ሳቢያ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተቋረጠ
·         ጋዜጣው በስብሰባ መካከል መሰራጨቱና ባተኮረበት ይዘት ብፁዓን አባቶችን ለማሸማቀቅ ተብሎ መዘጋጀቱን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተናግረዋል

·         የጋዜጣው ርእሰ አንቀጽና ዘገባዎች አባ ጳውሎስ በስብሰባው እንዲያዙላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች ከአባ ጳውሎስ “የፓትርያርክነት ዐምባገነንነት” ፍላጎት አንጻር የማብራራት ግብዝነት የሚታይበት ነው
·         አባ ጳውሎስን ከፓትርያርክነት ማዕርጋቸው በሚያወርዷቸው የቃለ መሐላ ጥሰትና የታማኝነት መታጣት ጉዳዮች ዙሪያ ጠንካራ ውይይት ተጀምሯል
·         የአባ ጳውሎስ ግብረ በላዎች ንት ማምሻውንና ዛሬ ቀን በአባቶች ማረፊያ ቤት እየተዘዋወሩ በማስፈራራት ጽናታቸውንና አንድነታቸውን ለማላላት እየሞከሩ ነው፤ እጅጋየሁ በየነ፣ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንና ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሱ ግለሰቦች ይገኙባቸዋል
·         መደበኛ ስብሰባው ነገ ሰኞ ይቀጥላል
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 5/2004 ዓ.ም፤ May 13/ 2012)፦ ንት፣ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በፊት በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ርእሰ መንበሩ አባ ጳውሎስ በምልአተ ጉባኤው ስምምነት የተደረሰባቸውን አጀንዳዎች ባለመቀበል ኾነ ብለው በያዙት ግትርነት የተነሣ ብዙኀኑ አባላት ከቀትር በኋላ ሌላ ሰብሳቢ መርጠው ውይይታቸውን ለመቀጠል ወስነው ነበር የተነሡት፡፡

በዚህ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ከቀትር በኋላ ስብሰባውን ለመቀጠል ወደ አዳራሹ ሲገቡ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በየመቀመጫቸው አንጻር ተቀምጦ ያገኛሉ፤ ፓትርያርኩም በኮሚቴው የተዘጋጁትን አጀንዳዎች እንደሚቀበሉ መስለው ተላስልሰው በመቅረባቸው ምልአተ ጉባኤው በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እየተመራ በተ.ቁ (2) ላይ የተመለከተውን የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ሪፖርት አዳመጠ፤ እግረ መንገዳቸውንም ጋዜጣውን እንደ ዋዛ መመልከታቸውን አላቆሙም ነበር፡፡

ሪፖርቱ በንባብ ተሰምቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ውይይት ከመጀመሩ በፊት ለሻሂ ዕረፍት የተነሡት አባቶች ግን ጋዜጣው በያዘው ‹ቁም ነገር› ላይ መመካከር ያዙ፤ ምክክሩም አቡነ ጳውሎስ ከስብሰባው ቀደም ብለው ከዋሽንግተን ወደ አገር ቤት ከመጡት አባ ፋኑኤል እና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ጋራ በማበር የጋዜጣውን አዘጋጆች እና ጋዜጣው በሚዘጋጅበት መምሪያ ውስጥ በሓላፊነት የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችን በቅጥረኝነት በመጠቀም የሠሩት መኾኑን ይደርሱበታል፡፡

ከሻ ዕረፍት መልስ ጋዜጣው ምን እንደጻፈ፣ ስለምን እንደጻፈ ሊያውቅና ሲቆጣጠርም ይገባ የነበረው  የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ስለ ጋዜጣው ዝግጅት ምንም እንደማያውቁና ሌሎች አጀንዳዎች ወደ ኋላ ቀርተው ምልአተ ጉባኤው በዚሁ ጉዳይ እንዲነጋገር ይጠይቃሉ፡፡ ከዚህ በኋላ በቤቱ የነበረው ድባብ በፓትርያርኩ እና በአባ ፋኑኤል ላይ ባነጣጠረ የተግሣጽ መአት የተሞላ ነበር፡፡ አባ ጳውሎስም ይኹኑ አባ ፋኑኤል የሠሩትን ያውቃሉና አንገታቸውን አቀርቅረው ተግሣጻቸውን ከመቀበል ውጭ ትንፍሽ ያሉት ነገር አልነበረም፡፡

በተግሣጹ አባ ጳውሎስ ከተሐድሶ መናፍቃን ጋራ በግልጽ በማበር አባቶች በወቅታዊ ጉዳዮች በተቀረጹት አጀንዳዎች ዙሪያ ያላቸውን አንድነት እና የዓላማ ጽናት በመሸርሸር ለማሸማቀቅ (በግብር የሚመስሏቸው የመፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች እንደሚያደርጉት) አስበው እንዲፈጸም በማዘዝ እጃቸው እንዳለበት ተነግሯቸዋል፤ አባ ፋኑኤልም “መወገዝ ያለብኽ ሕገ ወጡ አንተ ነኽ፤ በሌላው ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከት ገብተኽ ክህነት የምትሰጥ፤ አንተ ብሎ ክህነት ያዥ¡” በሚሉና ሌሎችም ኀይለ ቃላት የድርሻቸውን አግኝተዋል፡፡

56 ዓመት ቁጥር 126 ሚያዝያ ግንቦት 2004 . ታትሞ በወጣው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ‹‹የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጋለጥ›› በሚል ርእስ ስለ ሰፈረው ርእሰ አንቀጽ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ›› በሚል ርእስ ስለተዘጋጀው ሐተታ አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ‹‹እኔ ማንንም አልፈራም፤ ጽሑፉ አያስጠይቀኝም እንጂ ብጠየቅበት አልፈራም፤ በይዘቱ አዲስ አይደለም፤ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው አቀራረብ ሲጽፉት የቆዩት ነው፤ እኔ ለመጻፍ የሞከርኹት የቤተ ክርስቲያን ህልውና እየተነካ ነው ብዬ በማምንበት ስለ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ነበር፤ አባ ጳውሎስ ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይሻሻል አሉ፤ እውነቱን ለመናገር  ጽሑፉ ከውጭ የመጣ እንጂ በዝግጅት ክፍሉ የተጻፈ አይደለም፤ በስሜ እየተነገደብኝ ነው፤›› ብለዋል፡፡

እስክንድር ገብረ ክርስቶስ
ዋና አዘጋጁ ጽሑፉ ከውጭ ተዘጋጅቶ እንደመጣ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ አዘጋጁን አካል ለማወቅ በተደረገ ጥረት÷ ‹‹አባ ጳውሎስን ደግፋችኹ ከጻፋችኹ ማንም አይነካችኹ፤ ከተነካችኹም እኛ አለንላችኹ፤ ሁሉም ወንጀለኛ ነው›› በሚል የጥቅም ማበረታቻ የተቀበሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ሓላፊ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ፣ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ባለው ሥልጣን ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያንን ከመድረክ እያገለለና በየአህጉረ ስብከቱ በመዞር ከፕሮቴንታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና አቀንቃኞች ጋራ ያለውን ግንኙነት እያጠናከረ የሚገኘው አእመረ አሸብር፣ እንደ ቀበሮዋ ዘለው ዘለው የሻቱትን ማዕርገ ጵጵስና ቢያጡት የተሾሙትን አባቶች በማሸማቀቅና አንገት በማስደፋት ለመሾም የቋመጡት አባ ሰረቀ፤ ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ የሰጡት አባ ፋኑኤልና ዦቢራው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን መኾናቸው እየተነገረ ነው፤ የአባ ጳውሎስ አይዟችኹ ባይነት (ቡራኬ) ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡ ይኹንና የዝግጅት ክፍሉም በጽሑፉ ላይ ማሻሻያ በማድረግና እንዲታተም በመፍቀድ፣ ምናልባትም የጥቅሙም ተካፋይ በመኾን መጠየቁ እንደማይቀር ግልጽ ነው፡፡

ሰኞ በሚቀጥለው ስብሰባ ቀዳሚው አጀንዳ የጋዜጣው አዘጋጆች ተጠርተው የሚጠየቁበት እና ለዝግጅቱ ሓላፊነት የሚወስደው አካል ተለይቶ አስፈላጊው ውሳኔ የሚሰጥበት እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡ ጋዜጣው ከመሰራጨት እንዲታገድ፣ አባ ጳውሎስን ጨምሮ አዘጋጆቹና ተባባሪዎቻቸው በቅዱስ ሲኖዶስና በሕግ አግባብ የሚጠየቁበትም ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

        የጋዜጣው ዝግጅት ቤተ ክህነቱ በአባ ጳውሎስ ዙሪያ በተሰበሰቡ ጥቅመኞች እና የተሐድሶ መናፍቃን ለመወረሩ ማስረጃ እንደ ኾነ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ገልጸዋል፡፡ ‹‹ትልቁ ቁም ነገር የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ቤተ ክህነቱ በተሐድሶዎችና ጥቅመኞች ለመወረሩና በእነርሱ ተጽዕኖ ሥር ለመውደቁ ከዚህ በላይ ማስረጃ አያስፈልገንም፤›› ብለዋል አንድ አባት፡፡ ስብሰባው በጋዜጣው ሳቢያ ያለሰዓቱ መቋረጡን ተከትሎ ሁሉም አባቶች በየማረፊያ ቤታቸው ትላንት ማምሻውንና ዛሬ ቀን እርስ በርስ መመካከራቸውን ቀጥለዋል፡፡

          ‹‹በአባቶች መካከል በተፈጠረው አንድነትም ይኹን በግቢው የአባ ጳውሎስ ግብረ በላዎች በሚያደርጉት መራወጥ 2001 . የነበረው ኹኔታ ተመልሶ የመጣ ይመስላል፤›› ያሉ አስተያየት ሰጭዎች ብፁዓን አባቶች የቅዱስ ሲኖዶሱን ሥልጣን በመጠቀም በስብሰባዎች ላይ አባ ጳውሎስ የሚፈጥሯቸውን የማዘናጊያ አካሄዶች ወጊድ እያሉ ጉዳዮች በሚገባቸው ጥልቀት እየተብላሉና በውሳኔ እየታሰሩ መሄዳቸውን እንዲያረጋግጡ መክረዋል፡፡

ጋዜጣው ርእሰ አንቀጽ እና ዜና ዘገባ የሚከተሉትን ዋና ዋና ሐሳቦችለማንሣት ይሞክራል፦
·    አባ ጳውሎስ በሌላቸው ሃይማኖትና ምግባረ ጽድቅ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን በማሻሻል የፓትርያሪክነት ዐምባገነንነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሹ በጉልሕ ያሳያል፡፡ ለዚህም ርእሰ አንቀጹ ‹‹በ1991 ዓ.ም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን . . .አልፎ ተርፎ የቤተ ክርስቲኒቱን ርእስ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩን መብት የሚጋፋ ነው፤›› የሚለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ኧረ እንዲያው ለመኾኑ አባ ጳውሎስ ራሳቸውን በአምሳለ ንጉሥ እስኪመለከቱ ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት እንዳሻቸው እያባከኑ ባሉበት ኹኔታ የትኛው መብታቸው ነው የተገፋው? ወይስ በጣዖትነት መመለክ አማራቸው?
·         በብፁዓን አባቶች ላይ ደግሞ በሥርዐተ ሢመት (ምርጫ፣ ዕድሜ፣ የትምህርት ደረጃ)፣ በሀብት ክምችትና ውርስ እንዲሁም በውጭ ዜግነት ከጊዜው በጣም የዘገየ፣ አባ ጳውሎስን ከተመሳሳይ ወቀሳ ነጻ ያደረገ የጩኸቴን ቀሙኝ ክስና ግብዝነት የተሞላበት ጽሑፍ አቅርቧል፡፡
·      የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ፕሮጀክት መንገድ ጠራጊ የኾነው “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” ተብዬ ከቃለ ዐዋዲውና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ጋራ የሚፃረር መዋቅር በመኾኑ እንዲዘጋ ያሳለፈውን ውሳኔ በመናቅ ነውረኛውን ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን “በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ባለሙሉ ሥልጣን ዋና ሓላፊ” በማለት ይጠራዋል (በጋዜጣው የፊት ገጽ የወጣውንና አባ ፋኑኤልና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ‹በአጭር ጊዜ ስላሳዩት የሥራ ፍሬ› የሚናገር ‹ዜና› ራሱ እንዳረቀቀው ይነገራል፡፡)
·         ከግማሽ ምእት በላይ በሰሜን አሜሪካ ሲከናወን የቆየውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመዘንጋት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ተላልፈው በሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት አህጉረ ስብከት ክህነት በመስጠትና ማእከላዊ አሠራርን በመናድ የሚታወቁትን አባ ፋኑኤልን “በሰሜን አሜሪካ ሥራ አሁን ገና ሥራ እንደተጀመረ እና የታሪክ እመርታ እንደታየ” በመተረክ ይቀጥፋል፡፡
·     የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት wana የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ “በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ ሲሠሩ ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው እንደተባረሩ” በመጥቀስ ‹ክስና ማስረጃው› የማይገናኝ ውንጀላ ይናገራል፤ አያይዞም በቤተ ክህነቱ ሠራተኞች አገላለጽ አባ ጳውሎስና ግብረ በላዎቻቸው መጥምጠው እንዳዳከሙት ለተገለጸው ኮሚሽን “የተሳሳተ መረጃ ለለጋሽ ድርጅቶች በመስጠት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ እንዲዘጋ ያስደረጉት ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ናቸው፤” በሚል ክሱን ይቀጥላል፤ ሊቀ ጳጳሱ በሌላቸው ሥልጣን በቀሲስ ዶ/ር መስፍን ላይ አስተላልፌዋለኹ ለሚሉት ከንቱ ‹ውግዘት›ም አጽድቆት ይሰጣል፡፡
·     በጋዜጣው ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ‹‹ጋዜጣው የደገፈውንና የነቀፈውን አያውቅም፤ ለምሳሌ አባ ፋኑኤል ስለ ራሳቸው እያወሩና ቀሲስ ዶ/ር መስፍንን ከስሰው የከበሩ ቢመስላቸውም በውስጥ ገጽ በተጻፈው ጽሑፍ ደግሞ ‹በእግዚአብሔር ገንዘብ የግል ቪላ ገንብተው ያከራያሉ፤ እንደ ዓለማዊ ሰው ለአባት የማይገቡ ዘመናዊና ከፍተኛ ዋጋ ያለው መኪና ገዝተው ያሽከረክራሉ፤ ሌላም፣ ሌላም ተብለው የተወነጀሉት ዋነኛው ራሳቸው ናቸው፤›› በማለት ተችተዋል፡፡


በአጠቃላይ ጋዜጣው በአቡነ ፋኑኤል ጉቦ እንደተዘጋጀ ምንም አላጠራጠረም። በተግሳጽ መዶሻ ሲወቀሩ ያመሹት አቡነ ፋኑኤልም አልካዱም። ጥያቄው ፓትርያርኩ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ሊፈቅዱ ቻሉ የሚለው ተመሳሳይ ጥያቄ ነው። ራሳቸው የሚመሯቸውን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጎን በጋዜጣ ማስደብደብ ምን የሚሉት “ፓትርያርክነት” ነው? ፓትርያርክነታቸውስ ለማን ነው? በ2001 ዓ.ም በቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ የተቃወሟቸው አባቶች ቤታቸው በሌሊት ከመሰባበበሩ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ይህ ሕገ ወጥ ጋዜጣ አዘገጃጀት ግልጽ አያደርገውምን?

ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶሱን ባለመስማት ካመጹ ቆይተዋል። የዚህ ሕገ ወጥነታቸው ምልክት ደግሞ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የተደነቀረው ሀውልታቸው ነው። ቅ/ሲኖዶስ እንዲነሣ ቢወስንም በርሳቸው አምባገነንነት ይኸው እንደተገተረ አለ። ውሳኔያቸውን በተግባር ለመግለጽ ምንም አቅም ያጡት አባቶች ከዚህ በኋላ ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑ ይፈረድባቸዋልን? የወሰኑትን ውሳኔ ቤተ ክህነቱ ለማስፈጸም የማይፈልግ ከሆነ ምእመናን ሊያግዟቸው አይገባምን? ይህንን ጣዖት መሰል ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሀውልት ምእመናን ነቃቅለው ሊጥሉ፣ አባቶቻቸውን ሊያጠቋቸው ከሚመጡ ወንበዴዎች እና “ዶላር-አምላኩ” የዲሲ ጆቢራዎች ሊከላከል አይገባውምን?

ደጀ ሰላም ባለፉት ዓመታት ስታደርግ እንደቆየችው ሁሉ በዚህ ዓመትም ስብሰባዎቹን “እንደወረደ” ሪፖርት ታደርጋለች። ይህንን የምታደርገው ግን እገሌ እንዲህ አሉ፣ እገሌ እንዲህ ሠሩ” በሚለው እንድንዝናና ሳይሆን የሰማነውን ሰምተን ፣ ማድረግ ያለብንን ደግሞ እንድናደርግ ነው። ጎራው ለይቷል። ቤተ ክርስቲያን አፍራሾቹ፣ ጉበኞቹ፣ ዘራፊዎች እና የቤተ ክርስቲያን አጥፊዎቹን በግልጽ አውቀናቸዋል። ስለነርሱም ብዙ ብዙ ብለናል። አሁን ግን ይበቃናል። አባቶቻችን እየያዙት መጡትን አቋም በመደገፍ “አይዟችሁ” ልንላቸው ይገባል። ጎናቸውም እንቆማለን። መንግሥትም ቢሆን ይህንን ሕገ ወጥነት በመደገፍ ፖሊሱን እና ወታደሩን፣ ጥይቱንና ዱላውን የሚልክ ከሆነ ምእመናን ለሃይማኖታቸው መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጁ መሆኑንም ማሳየት ይገባቸዋል። ቅ/ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ እንዳስተማረን “ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም” (1፥29)። እናምናለን፣ ስለ ማመናችን የሚመጣብንን መከራም በጸጋ እንቀበላለን። ከአባቶቻችን ጋር በመቆም ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደጋለን። እግዚአብሔር ይርዳን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

40 comments:

Anonymous said...

menafeqanena paster paulos ezihe ga bibeqachewe melekame yemeselegnale!!!!


egiziabehere hayemanotachenene tewahidone yitebeqelene

Anonymous said...

ይሔ ደጀ ሰላም ሳይሆን ደጀ መዓት ነው ይህ የመናፍቃን ብሎግ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ ሁሌ ሰላምን የሚያውክ ነገር እንዳወራችሁ ዓላማችሁ ታውቃል ለቤተ ክርስተያን የቆማችሁ መስላችሁ መዓትን ዝሩ እስኪ ኃይማኖተኛ ከሆናችሁ ለሰማዕትነት እራሳችሁን ግልጽ አድርጉ እውነት ለቤተ ክርስትያን ከቆማችሁ ምንድነው ተደብቆ ነገር ማጫጫስ

Anonymous said...

ይሔ ደጀ ሰላም ሳይሆን ደጀ መዓት ነው ይህ የመናፍቃን ብሎግ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ ሁሌ ሰላምን የሚያውክ ነገር እንዳወራችሁ ዓላማችሁ ታውቃል ለቤተ ክርስተያን የቆማችሁ መስላችሁ መዓትን ዝሩ እስኪ ኃይማኖተኛ ከሆናችሁ ለሰማዕትነት እራሳችሁን ግልጽ አድርጉ እውነት ለቤተ ክርስትያን ከቆማችሁ ምንድነው ተደብቆ ነገር ማጫጫስ

Million said...

Egziabher amlak yekir yebelen. yehe hulu fetena bebetekrestiyan lay yemetaw begna hatiyat mekniyat new. ahun ye Dengil maryam lij like kahnat Eyesus Kirstos yekir yebka yebelen. lebetekrestiyan ena lelijochwa selamin yestelin. Dejeselamoch Egziabher yestilin yabertalin.

Anonymous said...

ሰውዬው አሁንም ምን ያህል ፖለቲከኛ እንደሆኑና ፖለቲካዊ አካሄድ እንደሚጠቀሙ በድጋሜ ያሣዩበት አጋጣሚ ነው፡፡ እንዴት አድርገው አጀንዳ ማስቀየር እንደሚችሉ እንዴት ማዘናጋት እንደሚችሉ ጠንቅቀው ያውቁበታል፡፡

አሁን ጉባኤው መንፈሳዊ የሲኖዶስ ጉባኤ ቀርቶ እኛ አባት ያሉት የመንደር ስብሰባስ መች ሆነ?? አለም አቀፋዊት የሆነችን ተቋም የሚመራ ጉባኤ ያውም እግዚአብሄርን አጋዥ ያደረገ ጉባኤ እንዴት በጎረምሳና በባልቴት አጀንዳ ስራ ይፍታ!!!

እኚህ ሰው እኮ በግልጥ በቃሁ መባል ካለባቸው ጊዜ በጣም አልፈዋል፡፡ የቤ/ክን ቀኖና ሁሉ ከሚጣስ አንድ ፓትርያርክን በማውረድ የሚጣስ ቀኖናስ ካለ ቢጣስስ ምኑ ነው ችግሩ የቤ/ክንን መሰረት ፈጽሞ ከማናጋታቸው በፊት አንድ እርሳቸውን ይብቃሁ ብሎ ማሳረፍ ያስፈልጋል፡፡
ደጀ ሰላምም የዜና ስራ ብቻ ሳይሆን ጠንከር ያለ የማስተባበበር ስራ ትስራ! ከምእመናን ምን ይጠበቃል የሚለውን ልክ እንደዛሬው ትጠቁም፡፡ ይህን ዜና ለማግኘት የምትቆፍሩትን ያህል አባቶችን እንዴት እናግዛችሁ ብላችሁም ጠይቁና አሳውቁን፡፡
ምን ይደረግ!!! እኛም ያለቦታችንና የእነርሱ ድፍረት እኛንም ደፋር አድርጎን ሲኖዶስን መካሪ አደረገን! ወይ የተገላቢጦሽ ዘመን!!! ያን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለኝን ፍርሃትና ግምት አሳጥተሁ ይህን ያስጻፍኩኝ አባ ጳውሎስ ሆይ እባክዎት መንበሩን አስረክበሁ እኛም የምናከብረው እርሱም የሚያከብረን አባትና ቅዱስ ጉባኤ እንዲኖረን ይተባባሩን !!!


ዘጊዮርጊስ

getachew said...

betam des yilal abatochachin bekalachihu yatinachihu gudegnawun leytachihu awutut
egziabher yimesigen................

Anonymous said...

Dejeselam, thank you for your devotion in following and reporting the current issues occurring in our church.

It is just today the Ethiopian Christians to put the dictator and protestant Ato Paulos and his followers in jail for the frequent crimes made on Kidist Tewahido. All Sunday school attendants and MK must take the responsibility to organize the march against the criminals. The march must be conducted on Monday morning. Please, pass all such messages to all.

Anonymous said...

yebekanal,we are loosing our identity. lets pray strongly

Teshome zedallas said...

Dejeselamoch lemitaderigut Yebetekiristiyan Wuleta Egziabher amlak wagachihun yikifelachihu.
Ebakachihu scan adirigachihu Ye zena betekiristianin mulu zegeba post arigut,please,please,please,please.....

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጥልኝ ደጀሰላማዊያን ከቀደም አስተያየቴና ጽኑ እምነቴ ጋር ባልተየ የመልካም አቋም ማሳሳቢያ በማስቀመጣችሁ ምስጋናየ የበዛ ነዉ፡፡ በተረፈ የደጀሰላም ታዳሚዎች የምናነበዉ ለወሬ ሳይሆን ወደ ተግባራዊ ሥራ እንድንሸጋገር ነዉ፡፡ ከወዲሁ ለቅዱስ አባቶቻችን አጋርነታችንን ልንገልጽ ያስፈልጋል፡፡ ከማንኛዉም የዉንብድና ጥቃት ለመከላከል እራሳችንን ብንቃት ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ መረጃዎችን ለምእመናን የማድረስ ተግባር በፍጥነት መከናወን አለበት፡፡ በቤተክርስቲያንና በህዝብ ላይ ያለዉ ንቀት ለአንዴና ለመጨረሻ ሊቆም ይገባዋል፡፡ ጎራዉ ለይቶአል ጠላታችንንና ወዳጃችንን ለይተናል ከዚህ በኋላ የምንጠብቀዉ ነገር የለም በቃ በቃ በቃ!!!
እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክርስቲያን ለመቆም ጽናቱን ይስጠን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ከመጣባት መከራ ይታደጋት አሜን!

ወ/ሓዋሪያት

Anonymous said...

Bemejemeria ledejeselamoch masasebia, Endene kezare jemiro patriarch tebiyewun ena ye Americawun wenbede "Abune " "Kidusnetachew" " Btsuentachewe" eyalachihu metirat aqumu. Hizbu Benezih sewoch lay endaynesana ewunetegna abatochun endayikelakel gira yemitagabut enante nachihu Bemayigebachewe maereg eyeterachihu. Enkwan yihe maereg yeminkusna simim ayigebachewum. Silehonem menafiqinetachwunan wunbdinachewun yemiyasay sim wotolachw hulum blogoch bezih enditeruachewu madreg yasfeligal. Lemisal "Ye elzabel paulos" ena "Jobirawe melaku".

Egna ye adis abeba wetatoch leqidus sinodosu yalenin tazajinet hawultun bmeneqaqel engeltsalen. Yih yebete kirstiyan guday new mengistin ayagebawum. Miknyatum yebetekiristiyanua yebelay akal qidus sinodosu wusane silesete.

Ewunetegna Abatochachin lay enkwan dibdeba qerto yemayigeba qal yetenagere yejun wediyawu yagegnatal.

Egziabhere betun kewenbedewoch matirat yifeligal egnam wenbedewochin lemaswetat tezegajitenal.

Yefera yimeles,

YE GEDEON SERAWIT

Anonymous said...

aye gud....aye "aba" pawlos...minale keto bimot....aye amlake..

Haile leul said...

በእውነት አባ ዻውሎስ እጅግ ነውረኛ ናቸው:: ቤተክርስቲያናችንን እንደታይታኒክ ወደ ጥልቁ እያሠጠሟት. . . እያወቅን. . . ገዳይ ዝምታ እስከመቼ? "ሥጋም ፍርሃቱን አበዛው ከታረደ በሗላ ምን አንቀጠቀጠው?". . . (ሲዘለዘል)

Anonymous said...

Get rid of him now!!! If we stand together he is just an old man!

sis said...

Bertu abatochachen atferu yebekal eyteshemakekachehu menoru yebkachehu eskemecha teshemakachehu eskmechase enfer be abatochachen egam anefer enatem atshemakeku beka belu EGTHIABEHARE kenantega new ewnet yethachehu mefrat aywatam gethaw acher new semen letarik teto malef melkam new .Manem Yebatekrestyan guday yagebagal yemil lethieh guday theb mekom alebet bewechiem bewestem yalew hulu menkat alebet

sis said...

Bertu abatochachen atferu yebekal eyteshemakekachehu menoru yebkachehu eskemecha teshemakachehu eskmechase enfer be abatochachen egam anefer enatem atshemakeku beka belu EGTHIABEHARE kenantega new ewnet yethachehu mefrat aywatam gethaw acher new semen letarik teto malef melkam new .Manem Yebatekrestyan guday yagebagal yemil lethieh guday theb mekom alebet bewechiem bewestem yalew hulu menkat alebet

Anonymous said...

Abatochachin Ebakachihu yemiwesdewun Gize wesdachihu Ajendawochun cherisu, Patriyark tebiyewu ende goromsa yemirbishut yenanten gize bemabaken bewesagn gudayoch lay satinegageru endtihedu new. Adera

yetewahido lij said...

memar yeneberebin kabatochachin neber gin yalemetadel honena alihonem enigidih yetewahido lij kitet musilim wegenochihun temeliket yslemesiwatinet yemigegn tirif wuridet bicha newu enih sewech aligebanachewumi aliyam aligebunim megibabiyawu kuwanikuwa mebitin betigil masikeber newuna fitsum kirisitiyanawi ametsin amitsen bekachihu enibelachewu sile ewunet lebetekirisitiyan enikum !!!

Anonymous said...

einanite eirasachihu ketewahido hayimanot akuwamina alama wechi eiyewetachihu yimesilal ababtochin yaleminim mafer sitizelifu kekirisitina anisar bizu yetedaferachihu ayimesilachihum ? amilak hulachininim yikir yibelen

Anonymous said...

መቼምበዚህ ድርጊት ጥርጥርበሌለውመልኩ ተዋናይ ይሆኑ የግቢው ሰዎች አሉ።
፩ በዋናነት የአባትነትለዛ የሌለውና የጵሮቴስታንት ተህድሶ መሪና የገንዝብ ምንጭ በሆነችው በአሰገደች መሪነት እየተንቀሳቀስ የሚገኝው አባ ሳይሆንአባ ነኝብሎ የሚማገትው ሰርቀ ከብዙ ችግሩና እንክኑ ጋርእንዱ ነው።
፪ ቀደም ሲል በተሀድሶነቱ ተወግዞ በደብረ ሊበኖስ ቀኖና የውስድውና ነገርግንከግብሩ ያልተመለስው እሁን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳንየሆነውን ስብከተ ወንጌሉንእንዲመራ በቅድስና ስፍራ ርኩሰትን የሚያደርገው የእውሬው ተከታይ የሾመው እይመረ አሽብር ነው። ይህ ሰው በቢሮ ከተመደበ ጊዝጀምሮ በርካተ የተሀድሶ አበላትየነበሩና ከቤተ ከርስቲየን አገለግሎት ተገልለው የነበሩ ሰዎች ለምሳሌ ጽጌ ስጦታው፤ ኤልያስ ዘቂርቆስ፤ ኃ/ጊዮርጊስ አሁንበአሜሪካ ያለው ፓስተር አሰግድ ሳህሌና ወይዘሮ ፐስትራይት አሰገደች/ይችሴትየሰረቀ አመራር ሰጭና ከአስግድ ጋር በቤተ ክህነት ግቢ በመገኝት የቀድሞው የሙሉ ወንጌል ትራክት በታኝ የ አሁኑ የቤተ ክህነቱ መዝገብ ቤትና የፓትርያሪኩ ዘመድ ጋር ከሆነችው አጸደ ጋር ከፍተኛ የተህድሶ ዘምቻ የምተድርግናት/ ጋርስብሰባ መቀመጥ ከጀመሩ የስነባብቱ ሲሆን በአፋጥኝ እልባትካተስጠችው ጉዳዩ አሳሳቢ ነው

Anonymous said...

Ahun Gezie tesatu honalena Ebakachehu Hulachenem Tegeten Entselie Enalkese. Menem Enquan Yetensaye wokete behonem Entsome Entselie Enalkes adera kabatochachen gone enekume Alenachehu Enbelachew. Adera Yadis Ababa krstianoch Abrachehu hunu Attitegnue. Birtu Abatoch Yehe woket Yemechershaw mehone Alebet. Egna Angetachen koslo Aemeroachen teblashto Sele Ewnetegeoch Abatoch Yet Tefuben Eyalen Eylkesen new Yekeremene Ena Adera kefesame Aderuslen. Eme Amlake Woladite Amelak Atleyen Lewsanawme Abra trdane. Amen .

Anonymous said...

Deje Selamoch Egziabher Hulunem Amaleto Yestachehu, Yebarkachehu. Biance biance Begenzeb bredachew keleb des yelegne neber. Mikniatume Enante ken kelet betegat hinen hulu keale hiwote seemetasemun Egziabher Kalehiwot lenantem Yasemachehu. Yehonew Hono Abatochachen Adera Yemelew Yetyazute agendawach Sayalku Menem aynet askefe Agenda enquan bemeta Sebsebaw Endiquate Ader Abatoch Amlake Egziabher Yerdachehu.(Ande worem befeje adera SIBSEBAW ENDIBETEN. ADERA ADERA ADERA...)

Anonymous said...

የተዋህዶ አምላክ ልባችንን ለከበረ ሰማዕትነት አጽና ! የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ልባችንን ለንጹህ ሰማዕትነት አበርታ! የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ አምላክ ልባችንን ለታላቅ ሰማዕትነት አበርታልን !ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ በከበረ ደምህ የመሰረትካት፣ቅዱሳን ሰማዕታት በጽኑ ተጋድሎ የሞቱላት፥ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመናፍቃን ተወራለችና፣ መቅደስህም ገንዘብን በማፍቀር በተፈለፈሉ ወንበዴዎች ተደፍሯልና፣ አቤቱ ለቅድስት ቤተክርሰቲያን የከበረ ሞት እንድንሞት አንተ አጽናን! ከፊት ምራን ከኋላም ተከተለን አሜን አሜን አሜን!

Anonymous said...

ንጽህት እምነት እንከን የለሽ
ተዋህዶ የተቀደስሽ
በንጹህ የአምላክ ደም የከበርሽ
የዘላለም ህይወት ማግኛ
ቀጥ ያልሽ መንገድ እውነተኛ
ተዋህዶ ተከበሪ ዛሬም በእኛ
ተዋህዶ ተከበሪ ዛሬም በእኛ
ተዋህዶ ተከበሪ ዛሬም በእኛ!

Anonymous said...

ደጀ ሰላምም የዜና ስራ ብቻ ሳይሆን ጠንከር ያለ የማስተባበበር ስራ ትስራ! ከምእመናን ምን ይጠበቃል የሚለውን ልክ እንደዛሬው ትጠቁም፡፡ ይህን ዜና ለማግኘት የምትቆፍሩትን ያህል አባቶችን እንዴት እናግዛችሁ ብላችሁም ጠይቁና አሳውቁን፡፡

galela said...

EGA KAABATOCHE GARE MAKOMACHENEN BAMENE ENEGELASE????????????????????????????????????KATSALOTE LELA

ሰጠችኝማርያ said...

የመጀመሪያው አስተያየት ሰጭ ጭፍን ጥላቻ ያለብህ ይመስላል አንተማንበብ ካልፈለክ ማን አስገደደህ እኛ ግንስለቤተክርስቲያናችን ማወቅ እንፈልጋለን የእነሱን ማንነት ለማወቅ ከመጣር ያንተን ስምመለጠፍ ይቅደም

Anonymous said...

Ebakewo aba pawelose hoye chegere sayefeteru beselame seletanewoten aserekebu.

sila tsion zim alilim said...

YEKIDUSAN AMLAK IGZIABHER YIRDAN BEWUNET ABATOCHACHIN ANGETACHININ KEDEFANIBAT KENA INDINIL SILAREGACHUN BELUIL IGZIABHER SIM INAMESEGINALEN. IGNAM BARIYAWOCH TENESTEN INISERALEN YESEMAY AMLAK IGZIABHER YAKENAWUNILINAL

tazabi said...

I am afraid that we are on a very dangerous junction now. Before everything else, what's needed now is prayer. Yemihila tselot. I have no clue how that can be achieved without the fathers issuing it, but that's what is necessary.

If God is with us, he could change everyone's heart; yepatriyarikun bemamraratim hone yelelochun qoraT bemadreg.

Dejeselam, give this priority.

yedingil baria said...

What a disgrace he is doing against the holy Church and the holy synod!, now it`s the right time to say enough is enough to the so called patriarch aba pawlos! let` stand and act right now!!!!! so help us God and Dingil Mariam!!!Amen!

Beka! said...

Ere gobez ... tewu yihnie eninesa .... abatochachin bewerobeloch ena beduryewoch tekebewu yigegnalu ena ... kereb bilen betekrstiyanin enaskebr.

Beka! Beka! Beka!

Anonymous said...

ደጀሰላሞች እግዚአብሄር ይስጥልን ከሁሉም አስቀድሜ ለአባቶቻችን ጳጳሳት ይህን የሚያስደንቅ ጽናት እና መንፈሱ ለሰጣቸው አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው። እኛ ልጆችቻቸ ሁሌም ከነሱ ጎን እንደምንቆም ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን በዚህ ጉዳይ ምመናኑ ነቅቶ እንዲከታተለ ኢንፎርሜሽን የማስተላለፍ ሃላፊነት የሚዲያዎች ታላቅ ድርሻ ነው

Anonymous said...

ደጀሰላሞች እግዚአብሄር ይስጥልን ከሁሉም አስቀድሜ ለአባቶቻችን ጳጳሳት ይህን የሚያስደንቅ ጽናት እና መንፈሱ ለሰጣቸው አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው። እኛ ልጆችቻቸ ሁሌም ከነሱ ጎን እንደምንቆም ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን በዚህ ጉዳይ ምመናኑ ነቅቶ እንዲከታተለ ኢንፎርሜሽን የማስተላለፍ ሃላፊነት የሚዲያዎች ታላቅ ድርሻ ነው

GebreZemaryam said...

ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እየተላለፉ ሳይፈጸሙ መቅረታቸው የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በመገናኛ ብዙሃን እንደምናየዉ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰኑ ውሳኔዎች አለመፈጸማቸውን በመንቀፍ እና ውሳኔዎቹ እንዲፈጸሙ ከመሻት በስተቀር ብዙም አጥጋቢ ስራ አልሰራንም::

በመጀመሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኗ የበላይ ጠባቂና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚነሱ ቀኖናዊ ጉዳዮችን እየተመለከተ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ውሳኔዎችን የሚያስተላለፍ ነው:: እነዚህ የተወሰኑት ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ደግሞ ያልተፈጸሙትን እንዲፈጸሙ ማድረግ በተዋረድ የተቀመጡ ሃላፊዎችና የምእመናን ድርሻ ነው:: አለበለዚያ በዓመት 2 ጊዜ የሚሰበሰብን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ውሳኔዎችን እንዲያስፈጽም መሻት የዋህነት ነው::
አሁንም አባቶች-- በታሪክ አጋጣሚ በእጃችሁ የወደቀውን የቤተክርስቲያነ አደራ እንትወጡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ እያልን፤ ከዚህ በፊት ተወስነው ሳይፈጸሙ በቀሩ ውሳኔዎች ተስፋ ሳትቆርጡ በመንፈሳዊ ሃይልና ጥባት ተሞልታችሁ ከፊት ለፊታችን የተጋረጠውን የሰይጣን ፈተና በተሰጣችሁ ሃይል ገስጻችሁ ቁርጥ ውሳኔ እንድታስተላልፉና ውሳኔውንም በማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን እንድታሳውቁን አደራ እንላለን::
እኛም እግዚአብሔር ቢፈቅድ አባቶች በእግዚአብሔር ቸርነት ከሰማይና ከምድር የተጣለባቸው አደራ ቢወጡና ጠንከር ያለ ውሳኔ ቢያስተላልፉ እኛም ከዚህ በሃላ ውሳኔውን የማስፈጸሙ ድርሻ የእኛ መሆኑን ተረድተን በጸሎትና በትጋት በጥባት እንከታተል::

Anonymous said...

ለዚህ፡ያደረሰን፡እግዚአብሔር፡ይመስገን!አሁን፡የ
ጥፋት፡ርኩሰት፡ከነግብስብሱ፡ስለተጋለጠ፤የተዋሕ
ዶ፡ልጆች፡በሙሉ፡ለታልቅ፡ሃይማኖታዊ፡ሰማዕትነ
ት፡እንዘጋጅ!

የተዋሕዶን፡አባቶች፡ቆራስጥነት፡በመደገፍ፡በየአጥ
ቢያችን፡የሚፈለጉትን፡ግዳጆች፡ለመፈጸም፡እንዘጋጅ!

በአባ፡ጳውሎስና፡ግብረ፤መናፍቃን፡አበሮቻቸው፡የ
ሚካሄደው፡መፈንቅለ፡ተዋሕዶ፡መሆኑን፡በማወቅ፡
ተንግዲህ፡መለማመጡን፡አርግፈን፡ትተን፡ቤተ፡
ክርስቲያናችንን፡ከወራሪዎች፡ለማጽዳት፡እንንቀሳ
ቀስ!

አባቶች፡አባ፡ጳውሎስ፡የማይታረሙና፡በውስጣቸ
ው፡የሰረፀው፡የጥፋት፡ርኩሰት፡ለመጥፊያችን፡የተ
ሰጠን፡መለኮታዊ፡ምልክት፡መሆኑን፡በመገንዘብ፡

1ኛ፣ አባ፡ጳውሎስን፡ከፓትርያርክነት፡በአስቸኳዋ
ይ፡አስወግዱልን!

2ኛ፣አባ፡ጳውሎስ፡ደግመው፡ደጋግመው፡በሥራቸ
ው፡እንዳሳዩን፡የትዋሕዶ፡ምእመንና፡አገልጋይ፡አ
ይደሉምና፡ጵጵስናቸውን፡በውግዘት፡አንስታችሁ፡
ከኢትዮጵያ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡አሰናብቱልን!

3ኛ፣ግብረ፡አበሮቻቸው፡ጌታቸው፡ዶኒ፣አባ፡ሰረቀ፣አ
ባ፡ፋኑኤልና፡ቤተ፡ክህነት፡ውስጥ፡በየዘርፉ፡የተሰገሰ
ጉትን፡መናፍቃን፡በሙሉ፡መንጥራችሁ፡አሰናብቱ
ልን!መጡብን፡እንጂ፡እኛ፡ከነ፡እሳቸው፡ምን፡ያገና
ኘናል?!

ብጹአን፡አባቶቻችን፡-
ያሁኑ፡ጉባኤያችሁ፡የሐዋርያዊ፡ቆራጥነት፡ወቅት፡
ስለሆነ፡የጀመራችሁት፡ተጋድሎ፡በተዋሕዶ፡ድል፡
አድራጊነት፡እንዲፈጸም፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያ፡አ
ብረናችሁ፡ቆመናል!ተእዛዛችሁን፡እንጠባበቃለን!

ይህ፡ወሳኝ፡ወቅት፡በእንዲሁ፡እንዲሁ፡በእነ፡አባ፡
ጳውሎስ፡የተለመደ፡ማጭበርበር፡ካለፈ፣የቤተ፡ክር
ስቲያናችን፡ዕጣ፡ፈንታ፡በራዕየ፡ዮሐንስ፡እንደተገለ
ጠው፡የሰባቱ፡ቤተ፡ክርስቲያናት፡መውደም፡መሆኑ፡
አይቀሬ፡ነው!አሁን፡ለመዳን፡ጊዜ፡አለን።ጊዜውን፡
እንጠቀምበት፣እንሥራበት!

የአቡነ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡አምላክ፡አይዘንብን!

ዲያቢሎስ፡ሊውጠን፡እየታገለን፡መሆኑን፡አውቀን፣
የጥፋት፡ርኩሰትን፡በተዋሕዶ፡እምነታችን፡ረትተ
ን፡ሂድ፡ውጣ፡ብለን፡ቤታችንን፡ከአጽራረ፡ቤተክር
ስቲያን፡የማጽጃው፡ወቅት፡አሁን፡ነው!ተንግዲህ፡
ይዋል፡ይደር፡ማለት፡የሚያጓራው፡ጠላታችን፡ይዋ
ጠን፡ብሎ፡እጅእንደ፡መስጠት፡እንዳይሆን፡ይህን፡
ወቅት፣ይህን፡ጊዜ፡ዋጁት!

የነቢያትና፡ሐዋርያት፡አምላክ፡ይርዳን!
የቅዱሳና፡አባቶቻችን፡አምላክ፡ይርዳን!
የጻድቃንና፡ሰማዕታት፡አምላክ፡ይርዳን!
እመ፡ብርሃን፡የተዋሕዶን፡ነገር፡አደራሽን!

አሜን።አሜን።ወአሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

The time for tselot minamin is over! what the AddisAban miemen need and must do is action. For how long are we going to stand on the side while the thugs led by Aba Paulos destroys eotc as we know her? For how long are we going to be spectators when our fathers are beaten and humiliated by the thugs and cronies of Aba Paulos? When are you AddisAbans going to say enough is enough like the Gondares did against the government's plan to dismantle our sacred monastery, Waldiba? May be the Synod should convene elsewhere like Gondar or Bahirdar or Nazret or even Axum or Mekelle. The AddisAban m'emenan have so far done nothing to protect the church from the onslaught of the Aba Paulos Gange. They have even ereted a Haulit which the Synod found heretic and approved its removal. Is AddisAba a city of Muslims and Pentes only? I absolutely agree with Deje Selams call to stand behind our fathers and implement their decisions. We should start by destroying Aba Paulos's Tawult in front of our Church. No more praying, fasting, crying blah blah. We have tried that for years and nothing has happened excepting multiplying our problems. God wants us to take matters into our hands, and that is exactly what we have to do. The church is ours! She is not the property of the corrupt patriarch nor his criminal gang.

My apology for talking like this. honestly, i am not a religious man, but i have so much respect and love for my church, the church of my ancestors. The church is even where i learned ha hu and my Ethiopian personality. We must fight to save her from the men who takes for a cash cow. I don't even believe Aba Paulos believe in God let alone by the power of the synod.

መላኩ said...

የእግዚአብሔር ሰላምታ ለሁላችን ይድረስ።

ወንድሙን የሚያንቋሽሽ የሚሳደብ ጨለማ ውስጥ ነው የሚኖረው፡ በማለት ቅዱስ መጽሐፉ ያስተምረናል። መሪዎቻችን ከኛ ወጥተው እኛን ለማገልገል የተመረጡ እንደመሆኖቻቸው የኛኑን ማንነት ነው የሚያንጸባርቀው፡ ነገሮችን ፊት ለፊት ተጋፍጠን በራሳችን ላይ ያለውን ጉድፈት ማስወገድ ይኖርብናል። ፓትርያርኩን አንዴ ፕሮቴስታንት አንዴ ካቶሊክ ናቸው እያሉ መጥራት ዋጋ የለውም። ገበሬውም፣ ተማሪውም፣ዶክተሩም መንፈሳዊ መሪውም ሁሉ አገሩን ለቆ አሜሪካና አውሮፓ መኖር ይፈልጋል፡ ፈረንጆቹ ደግሞ በነጻ የመጣላቸውን ስጦታ በረቀቀ መልክ በደስታ በመቀብል ከ20 ወይም 30 ዓመታት በኋላ የሜመጣውን ትውልድ እንደ ፍላጎታቸው ለመግዛት ያመቻቸው ዘንድ እነዚህኑ ዶክተሮች እና የሃይማኖት መሪዎች ይጠቀሙባቸዋል። አባ ጳውሎስ ላይ የሚታየውም ይኽው ነው። በነገራችን ላይ የዶክተርነት ማዕረግ ካውሬው ምልክቶች ውስጥ አንዱን ይገልጽልናል። ጥሩውን ከመጥፎው ለመለየት እድሉ የተሰጠን ካለን ማድረግ ያለብን በሃዘን ለነዚህ ወንድሞቻችን ጸሎት ማድረስ መቻል ነው። ለመሆኑ፡ ተሃድሶ ነን ከሚሉት መካከል ወደ ተዋህዶ ተመልሰናል፡ ተሳስተን ነበር፡ አሁን ንስሃ ገብተናል ለማለት የበቁ ወገኖች አሉን?

Gebre Z Cape said...

Thanks DJ for the article. Can you please scan and upload the newspaper of "zena betekiristian" It is good we also have a good look at the material. It is also a clue or proof of what you analyse in your blog.

Finally I would like to stay, we Orthodox Christian, this is the time to stay united. Let us stop supporting groups. Let us just fight for the truth, not for aba, or deacon or whoever it is. Let us fight so that everyone follows the rules of the church.

Amilak yaberitan.

Anonymous said...

Let us pray!! Our father's mothers gave our mother church as healing as it is. We this generation have responsibility to pass the church for the next generation. Please let us pray to fight the evil sprit surrounds us and trying to destroy the mother church.
mahiber kudusanoch please be strong and protect our church from this evil spirit. Please let us fast and pray together (subae) .for sure we all will die for our religion .let us stand together and say enough is enough

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)