May 12, 2012

(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ


·         የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል
·         ለምልአተ ጉባኤው ሐሳብ ተገዥ ባልኾነው የፓትርያ አቋም ስብሰባው እግዳት ውስጥ ገብቷል
·         ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል (መንግሥት) ጣልቃ ይግባ” (አንድ አባት)
·         ሦስተኛ አካል ጣልቃ አይገባም፤ በተለይም የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ሳናጠራ እርስዎ ያነሷቸውን አጀንዳዎች አናይም፤ ሲኖዶሱ በራሱ ወስኖ ኹኔታውን ለሚዲያና ለሕዝቡ ይፋ ያደርጋል” (ሌላ አባት)

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 4/2004 ዓ.ም፤ May 12/ 2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ንት ዐርብ፣ ግንቦት 3 ቀን 2004 . ጠዋት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ መነጋገርያ አጀንዳዎች ላይ የተጀመረው ውዝግብ ከቀትር በኋላም ቀጥሎ የዋለ ሲኾን ዛሬ፣ ግንቦት 4 ቀን 2004 . ከቀትር በፊት በነበረው የምልአተ ጉባኤው ውሎም እንደቀጠለ መኾኑ ተሰምቷል፡፡


በዛሬ ጠዋቱ ስብሰባየእርስዎ ዕውቀት ይህ ስብሰባ የገጠመውን ችግር እንደምን መፍታት ይሳነዋልበሚል ተማኅፅኖ ሳይቀር በብፁዓን አባቶች እየተለመኑ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስየእኔን አጀንዳ ካልተቀበላችኹ የእናንተንም አልቀበለምእስከ ማለት መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ይልቁንም በሰሜን አሜሪካው ዕርቀ ሰላም ሂደት ቀጣይነት፣ በተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመትና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻ አጀንዳዎች መካተት ላይ የያዙትን አቋም እያከረሩና አልፎ አልፎም እያለሳለሱ የስብሰባን ሂደት እግዳት ውስጥ አስገብተውታል፤ እያደር በሚታየው አሰላለፍም ፓትርያርኩ በአንድ ወገን የተቀሩት የምልአተ ጉባኤ አባላት በሌላ ወገን ጎራ ለይተው መቆማቸው ነው እየተነገረ ያለው፡፡

ዛሬ ቀትር ላይ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው÷ ከፓትርያርኩ በቀር ብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ መደበኛ ስብሰባውን ከቀትር በኋላ ለመቀጠል ወስነው ለምሳ ዕረፍት ተነሥተው ነበር፡፡ ምልአተ ጉባኤው እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከዚህ ቀደም መንግሥት ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ እንዲገባ የቀረበውን ሐሳብ የሚያስታውሱ አስተያየቶች ተነሥተው እንደነበር የጉባኤው ምንጮች ተናግረዋል፤ ከእርስዎ ጋራ መነጋገር አልቻልንም፤ ወደ አጀንዳ ሳንገባ በየቀኑ ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል ይግባ፤ ከዚህ በፊትም መንግሥት ይግባ ብለናል ብለዋል አንድ በፓትርያርኩ ግትርነት የተማረሩ አንድ አባት፡፡ ይኹንና ሐሳቡ ወዲያው ነበር ተቃውሞ የገጠመው፡፡

አሁን ጎራ ለይቷል፤ በአንድ በኩል ቅዱስነትዎ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፤ ስለዚህ የቀረቡትን አጀንዳዎች ለተቀበሉት አብዛኛው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ድም ተገዥ እየኾኑ አይደለም፤ ያሉት ሌላ ብፁዕ አባት ሦስተኛ ወገን የሚባል አካል አይገባም፤ አያስፈልገንም፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጭ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈጻሚ ነው፤ ስለዚህ አጀንዳዎቹን አጽድቆ መወያየቱን መቀጠል ይኖርበታል፤በማለት አንገብጋቢ የኾኑ አጀንዳዎችን በመለየት ዘርዝረዋል፡፡ በእኚህ ብፁዕ አባት ሐሳብ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ሀገረ ስብከት አላቸው፤ በአባትነት የሚመሩት ምእመን አላቸው፤ ስብሰባውን አቋርጠን ወደየ አህጉረ ስብከታችን ተመልሰን የእርስዎን እንቢታ እናስረዳለን፤በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ሐሳብ ጋራ የሚጣጣም ተጨማሪ አስተያየት የሰጡ ሌላ አባ ስብሰባውን ማቋረጥ ብቻ ሳይኾን ይህ ምልአተ ጉባኤ የሚለያየው ስለ ኹኔታው ለሚዲያ መግለጫ በመስጠት ጭምር ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የስብሰባው ምንጮች እንደሚያስረዱት ፓትርያርኩ የኋላ ኋላ በአቡነ ፋኑኤል በድጋሚ መጠቀሱ የተነገረውን ሦስተኛ ወገን (የመንግሥት አካል) ጣልቃ ገብቶ ያነጋግረን የሚለውን ሐሳብ የተቀበሉ ቢኾንም ከዚህ በፊት ተደብድበን ምን የመጣ ነገር አለ፤ በሃይማኖት፣ በአስተዳደር ጉዳይ ሲኖዶሱ የመወሰን ሙሉ ሥልጣን አለው፤ በሚል ተቃውሞ ሐሳቡ ተቀባይነት ገኝ ቀርቷል፡፡ በመጨረሻም ከፓትርያርኩ በቀር የምልአተ ጉባኤው አባላትስብሰባውን አናቋርጥም፤ ወደየ ሀገረ ስብከታችንም አንሄድም፤ ሌላ ሰብሳቢ መርጠን እንቀጥላለንበሚል ውሳኔ ከቀትር በኋላ ለመገናኘት ቆርጠው መነሣታቸው ተመልክቷል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የማጽደቅና እንደ አስፈላጊነቱም የማሻሻል፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የመወሰን ሥልጣን እንዳለው ተደንግጓል፡፡

ፓትርያርኩ በብቸኝነት ከሚሟገቱላቸው ሦስቱ አጀንዳዎች ይልቅ ለስብሰባው ከተቀረጹት መነጋገርያ አጀንዳዎች መካከል በተ. (2) ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ዓመታዊ ሪፖርት፣ በተ. (6) ማእከልን ጠብቆ አለመሥራት ስላስከተለው ችግር፣ በተ. (10) ስለ ልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ በተ. (13) ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ በኮሚቴው የሚቀርበውን ሪፖርት መስማትና መወሰን፣ በተ. (18) በሰሜን አሜሪካው ዕርቅ ጉዳይ ሪፖርት ስለ መስማት የሚሉት አጀንዳዎች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጧቸው እንደ ኾኑ ብዙኀኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚያንጸባርቋቸው አቋሞች ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከእኒህም ሁሉ በላይና በፊት ደግሞ በዛሬው የቀትር በፊት የስብሰባው ውሎ ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ የተጠናቀረው ሪፖርት አጀንዳ አንገብጋቢ እንደኾነ በብዙዎቹ የስብሰባው ተሳታፊዎች አጽንዖት የተሰጠበት ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

ይልቁንም በሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ ከታየ በኋላ ሪፖርቱ ገና ወደ ምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ ውሳኔ ሳይሰጠበት የተወሰኑ ግለሰቦች ከሕጸጽ ነጻ መኾናቸው እንደተረጋገጠ በመፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች የተነዛው አሉባልታ ብዙዎቹን አባቶች ክፉኛ አስቆጥቷ የሚቀርበውን ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም ከወዲሁ አነቃቅቷቸዋል፡፡ አሉባልታውን ከሚያናፍሱት ብሎጎች የአንዳንዶቹ ጸሐፊዎች ሃይማኖታቸው እንዲመረመር ውሳኔ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል እንደሚገኙበት ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተለው የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መርበብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስለ ቅዱሳን ሲኖዶስ ቀጣይ ውይይቶች እና የዛሬ ፍጻሜ የምናዘጋጀውን ሪፖርታዥ እንተጠናቀቀልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

31 comments:

Anonymous said...

abatochachin bertu!!!.ye AdissAbeba chirstyan le abatoch zeb yikum. eindaydebedebuubin.

Anonymous said...

abatochachen endihe sitenekeru newe enji yelebe yemiyadersewe lelama mene waga alewe!!!!

egiziabehere hayimanotachenen yitebeqelene!!!!!

Anonymous said...

I think there is a need to be steadfast from the laity side. Apart from prayers, we should show readiness for any undesirable pressure from the patriarchate or from the government, if any. This is the season to say enough is enough. Kenfer memtetena endihu mawerat metechet ayibekam. Haimanot beminimmlilewot ayichilim. Abatoch sidebedebu zim bilo yemiay gin beybotaw yemiawera Christian ayidelem yemiasefeligew. Dejen yemihon ena yagebagnal yemil new enji. Engdih wede Anwar Megid mayet yasfelig yihon ende! Limid lemekisem. Zemene Susinious ayibekanimin?

Anonymous said...

+++
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን የእናንተ የአባቶች ቁርጥ ዉሳኔ ያስፈልጋል: ጌታ ሆይ ከቅዱሳን አባቶቻችን ጋር እንደነበርክ አሁንም አብረሃቸው ሁን::
አሜን::

galela said...

kebere mesegana yegabawale

Anonymous said...

Abotochachin bertu, Bertu Bertu Bertu ye'ewunet amlak kenante gar new. Mengist yigba yemilewun neger aqumu. Mengist man honena. Esachewun endih agura zelel endihonu yaderegachewu man honenan. Sitidebedebu, abatochachin adis ababa metew bemekina adegana baltaweqe mikniyat simotu mikniyatun matarat sigebawu shefafno yeqebere manhonena ? Sewuyew lezih belew aydel bekdus sinodosu sibsba lay sint menfesawi guday lay nigigir madreg sigebachew sile abay gidib yeminagerut. Ye'adis abeba christiyanoch bemulu, yesenbet timhirt bet woetatoch, yebetechristiyan lijoch bezih wesagn gize keabatochachin gar lemeqom mereja melewawet alebin. Bezih guba'e patriyarch tebiyewu yemiyasayut agura zelel tebay lezih halafinet yemaybequ mhonachewun yemiyasay silehone lela bota yifelegilachew. Erfun chebitachihuwal wedehuwala atbelu.

Egnam ende musulimochu haymanotachinin lemaskeber gizewu ahun new yih degmo ke kidus sinodosu mejemeru higawi new. egnam kenante gar nen. kehulum belay egziabher kenante gar new.

Anonymous said...

መልካም ! አሁን ከእያንዳንዳችን ስለ ቅድስተ ቤተክርስቲያን የበለጠ ጸሎት ይጠበቃል። ከአዳም ጀምሮ መንፈሳዊያንን በመዋጋት ላይ ያለው ብርቱ ጠላት፥ ጌታችንንም ሊፈትን በገዳመ ቆሮንቶስ የተገኘ ብርቱ ጠላት ፥በተዋህዶ ላይ ሠራዊቱን በውስጥና በውጭ በብዛትና በዓይነት አሰልፎብናልና እንግዲህ ነፍሳችንን ማዳን የምንሻ ከሆነ ይህቺ በምድርና በሰማይ ያለች፥ የሰማይ ደጅም የተባለች እውነተኛ ሃይማኖት እንዳትበረዝ፣ እንዳትከለስ፣ በቅዱሳን አበው በተወገዙ የስህተት ትምህርቶችም እንዳትጥለቀለቅ የተዋህዶን አምላክ በአንድነት ተዋህዶን ጠብቅልን ብለን እንማጸን አደራ አደራ አደራ ...

Anonymous said...

Awo Endalefew gize Lehimanotachen Yemiwadekuten Abatoch tebikulen tenkebakebulen Yeaddis Abeba chirstyanoch Adera Adera Adera. Endenese behone Yememegebuten megebem chimer tetenkekew yemegebu tehdiso christianoch yemiaderguten aywkumena. EGZIABHER AMLAK EWNETEGNOCH ABATOCHEN BEMEDHANITEM YEHONE BMENEM SIGAWY HIWOTACHEWN BIATFUM HULEM MENFESAWE HIWOTACHEW KEGNA GARA NEW. LELAW DEGEMO EGIZIABHER KEMITEBEKUTE BELAY YEHONEWN YASNESALENAL. LEABATOCH EWNET LEMENEGAGER YABKALEN. AMEN.

Anonymous said...

Ye haymanot hitsets guday patriyarch tebiyewun mechemer alebet
1) Ye phd timihirtachew lay sile tinteabso yanesut.

2) ke qidus sinodos ewuqina wuchi ke katolikoch gar sibseba bemadregachewna.
3) Beziya sibseba lay haymanotawi guba'eyatin bemananaq yetenageruwachwu nigigiroch.
4) Be migibare bilishunet, be fet galemota mikir (be Elizabel) bete egziabherin lememrat yemifeligu bemehonachew.
5) Yeqidus sinodos wusan endayifetsem be madreg hige betekirstiyanin bemetelalefachwu.
6) Be ersachewu menber behonewu yeqidusan abatoch maderiya be abatoch lay dibideba tsifetsem awuqewu endalawequ bememsel behuwalam gudayu endayitara bemadreg abatochin bemasferarat hige bete kiristiyanan lemelewet tiret madiregachew.
7) Qenona betechristiyanin bemetelalef hawultachwun masqomachewuna endayfersim bemekelakelachew.

Endihum yeqidus sinodosun sibseba memrat yemaychilu bemehonachewu.

Yih hulu

Anonymous said...

ye addis abeba christiyanoch leabatochachin tibeqa enadirg.

Le abatochachin tibeqa tibeqa tibeqa yiderg.

Gubaewu yale patriyarchu yiqetil.

lamelame europe said...

macherashawen yasamerelen

Anonymous said...

ውድ ደጀሰላሞችና መላው የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ ነገሩን ሁላችንም በጥንቃቄ እንድንከታተልና ከአባቶች ጎን በንቃት እንድንቆም አሳስባለሁ:: ከዚህ በፊት በአባቶች ላይ የደረሰውን ድብደባና ማስፈራራት በማስታውስ አባቶቻችንን ሊያሸማቅቋቸው ይችላሉ:: ይህ ደግሞ የነፍሳችን ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም ለማንኛውም መስዋእትነት ዝግጁ በመሆን ከአባቶች ጎን እንሁን:: የደጀሰላም ሪፖርት አዘጋጆችና መላው ክርስቲያኖች እባካችሁ እንደዚህ አይነቱን መልእክት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በማዳረስ ሃላፊነታችንን እነወጣ:: በኛ ዘመን ቤተክርስቲያንን ለመናፍቃን አሳልፈን አንሰጥም:: በህይወት እያለን ተሃድሶ የሆነው አባ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ላይ የሚጫወትባት እዚህ ላይ መቆም አለበት:: ለዚህ ደግሞ ሁሉም ክርስቲያን ነፍሳችንን እስከመስጠት ለሚያደርስ መስዋእትነት ዝግጁ እንሁን:: ከዚህ በኋላ አባቶቻችንን በማስፈራራት እንኳን ቢበታትኗቸው መላው ህዝበ ክርስቲያን ግን በአንድነት ለፍጹም መስዋእትነት ዝግጁ እንድንሆን አሳስባለሁ:: እባካችሁ ሁላችሁም በምትችሉበት መንገድ ሁሉ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናሳስብ:: ሁሉ ግን እናዳባቶቻችን በስርአት ይሁን:: ኢትዮጵያ በስርአት የሚንቀሳቀስ እንደሚደበደብና እንደሚገደል እናውቃለን ቢሆንም ግን እኛ እስከወዲያኛው ድረስ ስርአት በጠበቀ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ስርአት የማስከበር መንፈሳዊና ሃገራዊ ግዴታ አላብን:: እነሱ እንደለመዱት ይደብድቡን ይግደሉን:: እኛ ግን ነስፍንና ስጋን ጭምር ሊገድል የሚችለውን እንጂ ስጋን ቢቻ ሊገድል የሚችልን ማንኛውንም ወገን አንፈራም ዮሐ. ራእይ 2:10...ለህግ ግን መቼም መች ሁሌም ተገዢዎች ነን::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
H/Mariam

Anonymous said...

ውድ ደጀሰላሞችና መላው የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ ነገሩን ሁላችንም በጥንቃቄ እንድንከታተልና ከአባቶች ጎን በንቃት እንድንቆም አሳስባለሁ:: ከዚህ በፊት በአባቶች ላይ የደረሰውን ድብደባና ማስፈራራት በማስታውስ አባቶቻችንን ሊያሸማቅቋቸው ይችላሉ:: ይህ ደግሞ የነፍሳችን ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም ለማንኛውም መስዋእትነት ዝግጁ በመሆን ከአባቶች ጎን እንሁን:: የደጀሰላም ሪፖርት አዘጋጆችና መላው ክርስቲያኖች እባካችሁ እንደዚህ አይነቱን መልእክት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በማዳረስ ሃላፊነታችንን እነወጣ:: በኛ ዘመን ቤተክርስቲያንን ለመናፍቃን አሳልፈን አንሰጥም:: በህይወት እያለን ተሃድሶ የሆነው አባ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ላይ የሚጫወትባት እዚህ ላይ መቆም አለበት:: ለዚህ ደግሞ ሁሉም ክርስቲያን ነፍሳችንን እስከመስጠት ለሚያደርስ መስዋእትነት ዝግጁ እንሁን:: ከዚህ በኋላ አባቶቻችንን በማስፈራራት እንኳን ቢበታትኗቸው መላው ህዝበ ክርስቲያን ግን በአንድነት ለፍጹም መስዋእትነት ዝግጁ እንድንሆን አሳስባለሁ:: እባካችሁ ሁላችሁም በምትችሉበት መንገድ ሁሉ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናሳስብ:: ሁሉ ግን እናዳባቶቻችን በስርአት ይሁን:: ኢትዮጵያ በስርአት የሚንቀሳቀስ እንደሚደበደብና እንደሚገደል እናውቃለን ቢሆንም ግን እኛ እስከወዲያኛው ድረስ ስርአት በጠበቀ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ስርአት የማስከበር መንፈሳዊና ሃገራዊ ግዴታ አላብን:: እነሱ እንደለመዱት ይደብድቡን ይግደሉን:: እኛ ግን ነስፍንና ስጋን ጭምር ሊገድል የሚችለውን እንጂ ስጋን ቢቻ ሊገድል የሚችልን ማንኛውንም ወገን አንፈራም ዮሐ. ራእይ 2:10...ለህግ ግን መቼም መች ሁሌም ተገዢዎች ነን::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
H/Mariam

123... said...

MENGIST QIDUS SINODOS GUDAY WIST MEGBAT YELEBETM. MENGIST POLITICA NEW YIZO YEMIMETAW. LIFETA YEMAYCHIL MEQEMEQ WIST NEW GUDAYU YEMIGEBAW.KEWISTACHEW EKO MENGIST ALE.ENA HAYMANOTAWI QORAT ENA SIRATE BETE CHRSTYANN YETEKETELE WISANE ABATOCH BE ABUNE PAWLOS LAY MESTET ALEBACHEW.

Orthodoxawi said...

ውድ አባቶቻችን - በርቱ ቀጥሉበት። እንደ 2001 ዓ.ም. የድብደባ ወንጀል እንዳይፈጸምባችሁ ጠባቂው እግዚአበሔር ቢሆንም እናንተም ራሳችሁን ጠብቁ። ለሚመለከታቸው አካላትም አሳውቁ።

የአዲስ አበባ ምእመናን አባቶቻችንን ለወሮበሎች አሳልፋችሁ እንዳትሰጡ። አደራ። አባቶቻችን የሚችሉትን እያደረጉ ነው...እኛም የሚጠበቅብንን መስዋእትነት መክፈል አለብን።

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክርስቲያን የሚቆሙ አባቶችን አያሳጣን። አሜን።

ኢትዮጵያ said...

ለካስ አባቶቻችን ተቸግረዉ ነዉ እንጂ የችግሩን ምንጭ አላጡትም!! እነሱም እየተብከነከኑ 'እህ' እያሉ ነዉ እየኖሩ ያሉት። ቢያንስ ግን የሚጠበቅባቸዉን በማድረግ ለሃይማኖታቸዉ ሰማዕታት ከሆኑ ሌላዉን የቅዱሳን አምላክ ለእግዚአብሔር ይፈጽምልናል። ያን ጊዜ ነዉ በሰማይም በምድርም ከመጠየቅ የምድኑት!!

እዉነተኞቹ አባቶች እግዚአብሔርን ይዘዉ፤ እኛኛዉ ሰዉን ይዞ ነዉና የተሰለፉት አይዞአችሁ፤ የባሰ አያምጣ እንጂ ያሁኑ ችግር በጊዜ ሂደት (ዕድሜ ለሰጠዉ ሰዉ የሚታይ) የሚፈታ ነዉ። ዋናዉ ጸንቶ መቆሙ ላይ ነዉ። እግዚአብሔር አምላክ ለአባቶቻችን ጽናቱን ይስጣቸዉ። እኛም 'ለካስ አባቶች አሉን' እንድንል ያድርገን፤ አሜን።

lele said...

neseha gebo.....

sis said...

Abatoche bertu echi alem alafi mehonuan atzengu tarik sel betekrestian sel ewnet serto malef telek neger new Egthiabehar kenantega yehun Manegawem hezb kerestyan lezieh guday zeb mekom alebet gedatam new

sis said...

Abatochachen Bertu tegest gedeb alew yebekal betarik tetyaki kemehone memote yeshalal ahunn enante kedmachehu hethbun masketel albachehu

Anonymous said...

ayezochohe bareto abatochachen

Anonymous said...

tesfa kemekuret yadnun esti. hayimanotachinin tebko yemiastebik abat atan

Anonymous said...

አባቶች በእውነት አቋማችሁ እጅግ የሚበረታ ነው:: በርቱ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን::

Anonymous said...

አባቶች በእውነት አቋማችሁ እጅግ የሚበረታ ነው:: በርቱ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን::

Anonymous said...

አባቶች እባካችሁ በርቱ አብረን ሰማእት ሆነን ሃይማኖታችን እናስከብር።

ለመጪው ትውልድ ይህ ሁኔታ አናውርስ እባካችሁ።

እኛም ከጎናችሁ ነን። ህዝቡ እኮ የእናንተን ውሳኔ ነው የሚጠብቀው። ካልሆነ ከሁለቱም ሳትሆኑ በመሃል ትቀራላችሁ።
ማለትም ከህዝብም ሳትሆኑ የቤተክርስቲያንም ስርዓት ሳታስከብሩ የፈጣሪያችሁንም ትእዛዝ ሳትጠብቁ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉ ተጠንቀቁ የሚለውንም አትርሱ።


እመአምላክ ከእናንተ ትሁን።

Anonymous said...

Lela Sebsabi Malet mIn malet new 3 Patiryark Malet new ? yikebdal Abune Merkorewos weredu bilen yetekefafelnew anso Degimo Abune Pawlos Liwerdu new ? Yigermal Minale egizabher Bigelagilen ahunis bezabin Ahun Sinodosu Manin wekele ? Maninis Mertse Hulum Ayhonum eko Abune Samueil Or Abune Abirham Or Abune Fanueil Or Abune Matewos Bihonu melkam yimesilal

Anonymous said...

Dear Dejeselam

We very thank for the valuable and highly expected news you provide. This is the right strategy our fathers(The Holly Synod) follow. We appreciate their genuine decisions. But this struggle must be backed by the Ethiopian people,(especially Sunday schools, MK, and all Christians in general) must involve in the process.

By no means,Abune Paulos must seize power because he is still standing against the rules and regulations of the church. Our fathers, we all Ethiopians are eagerly expecting your genuine decisions.

Anonymous said...

በእውነት ሰው ለሰው የስጋ ረፍትን/ሞትን አይመኝም ግን እግዚአብሔር የዚህችን ቤተከርስቲያን ፈተና በቃ ቢላት ጥሩ ነበር:: በአንድ ሰው እንዴት ትታምስ?

Anonymous said...

deje selamoche Egizabehare yesetachohe.
endawe katachala kabatochachen gaer yameneganagebate nagare benore?

ቸር ያሰማን said...

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን የእናንተ የአባቶች ቁርጥ ዉሳኔ ያስፈልጋል: ጌታ ሆይ ከቅዱሳን አባቶቻችን ጋር እንደነበርክ አሁንም አብረሃቸው ሁን::
አሜን:

ምስጋናው said...

የለንም ሞተናል
ሥርዓታችን ሲፈርስ ሃይማኖት ሲሰደብ:፦
መሳለቂያ ስንሆን ከቶ ያለገደብ፦
አስመሳይ ተኩላዎች እንድህ ሲቀልዱ፦
ሃይ የሚል ሰው ጠፍቶ ዝምታን መውደዱ፦
በቃ ኦርቶዶክሶች ለካ ተንቀናል፦
የቆምን እንዳይመስለን የለንም ሞተናል።
ቅኔና መዝሙሩ በዘፈን ሲቀየር፦
ተኩላ ሲመላለስ በቤተ መቅደስ በር፦
የእምነት ወረራ ግፍ ሲፈጸምብን፦
መናፍቅ ሲመረጥ ሲታጭ ለስልጣን፦
እስከመቸ ድረስ ዝምታ እንመርጣለን፦
ተነስ የተዋህዶ ልጅ ዛሬ ነው ቁርጥ ቀን።
አንዱ በር ሲዘጋ ባንዱ እየሾለኩ፦
የመናፍቅ ትምህርት በይፋ ሲሰብኩ፦
በአውደ ምህረት ላይ ዘፈንን ሲያዜሙ፦
ቤተክርስቲያንን ሲያቆስሉ ሲያደ ሙ፦
ስድብን የተሞላ መግለጫ ሲያወጡ፦
ሆድ ይፍጀው እያሉ እንድህ መ ቀመጡ፦
አይገባኝም ለኔ ትእግስቴ ገንፍሏል፦
ያለን እንዳይመስለን የለንም ሞ ተናል።
ስለዚህ ወገኔ ተነስ ተነቃነቅ፦

ምስጋናው said...

የለንም ሞተናል
ሥርዓታችን ሲፈርስ ሃይማኖት ሲሰደብ:፦
መሳለቂያ ስንሆን ከቶ ያለገደብ፦
አስመሳይ ተኩላዎች እንድህ ሲቀልዱ፦
ሃይ የሚል ሰው ጠፍቶ ዝምታን መውደዱ፦
በቃ ኦርቶዶክሶች ለካ ተንቀናል፦
የቆምን እንዳይመስለን የለንም ሞተናል።
ቅኔና መዝሙሩ በዘፈን ሲቀየር፦
ተኩላ ሲመላለስ በቤተ መቅደስ በር፦
የእምነት ወረራ ግፍ ሲፈጸምብን፦
መናፍቅ ሲመረጥ ሲታጭ ለስልጣን፦
እስከመቸ ድረስ ዝምታ እንመርጣለን፦
ተነስ የተዋህዶ ልጅ ዛሬ ነው ቁርጥ ቀን።
አንዱ በር ሲዘጋ ባንዱ እየሾለኩ፦
የመናፍቅ ትምህርት በይፋ ሲሰብኩ፦
በአውደ ምህረት ላይ ዘፈንን ሲያዜሙ፦
ቤተክርስቲያንን ሲያቆስሉ ሲያደ ሙ፦
ስድብን የተሞላ መግለጫ ሲያወጡ፦
ሆድ ይፍጀው እያሉ እንድህ መ ቀመጡ፦
አይገባኝም ለኔ ትእግስቴ ገንፍሏል፦
ያለን እንዳይመስለን የለንም ሞ ተናል።
ስለዚህ ወገኔ ተነስ ተነቃነቅ፦

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)