May 7, 2012

(ሰበር ዜና) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ከሓላፊነታቸው ተነሡ


·         የዋና ሓላፊው መነሣት በቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን የተቀነባበረ ነው፤ የአቡነ ጳውሎስ ስውር ትእዛዝና የአቡነ ገሪማ የተለመደ አድርባይነት እንዳለበትም ተረጋግጧል
·         የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” በማለት ርምጃውን ተቃውመዋል
·         “ተግባሩ በቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው አሳሳቢ ኹኔታ መገለጫ ነው” /ማኅበረ ቅዱሳን/
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 29/2004 ዓ.ም፤ May 7/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ከአሿሿማቸው እና ከተሾሙበት ጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም አንሥቶ መነጋገርያ የኾኑት በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው ተሰማ፤
የመምሪያው ምክትል ሓላፊ የኾኑት መ/ር ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ በቦታቸው የተተኩ ሲኾን የመምሪያው ጸሐፊ የኾኑት መ/ር መኰንን ወልደ ትንሣኤ ደግሞ የመምሪያ ምክትል ሓላፊ ኾነዋል፡፡ ከዋና ሓላፊነት የተነሡት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞችና በፓትርያሪኩ ሳይቀር “መጋዘን” እየተባለ ወደሚጠራው መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አባል ኾነው እንዲሠሩ ተዘዋውረዋል፡፡
መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ከሓላፊነታቸው ለመነሣት ያበቃቸው በቀድሞው ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ አማካይነት ሲገፋ ለቆየው÷ ማኅበረ ቅዱሳንንና ሰንበት ት/ቤቶችን አሽመድምዶ በማዳከምና በመቆጣጠር የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን ፕሮጀክት ለማሳከት፣ የግልንና የቡድን ጥቅምን ለማስፈን ምቹ ኹኔታ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ለሚገኘው የቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን ሤራ አልመች፣ አልታዘዝ በማለታቸው እንደ ኾነ ተዘግቧል፡፡
የጨለማ ቡድኑ ዋነኛ መሪዎች ለረጅም ጊዜ የመምሪያው ም/ሓላፊ ኾኖ ሲሠራ የነበረውና የግል ጥቅሙን በማሳደድ የሚታወቀው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ፣ ከቀድሞው ዋና ሓላፊ በሚሰጠው ጥቅምና ተስፋ ሥጋዊ ኑሮውን ሲያደላድል የቆየው የመምሪያው ጸሐፊ መኰንን ወልደ ትንሣኤ እና አንዴ ‹ኢሕአዴግ ነኝ፤ ተሰሚነት አለኝ› ሌላ ጊዜ ‹የሲ.አይ.ኤ አባል ነኝ፤ ከዲፕሎማቶች ጋራ እገናኛለሁ› እያለ የሚያጭበርበረው የአቡነ ፋኑኤል ተስፈኛ ይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ናቸው፡፡
ካለፈው ሳምንት ዐርብ ምሽት ጀምሮ የጨለማ ቡድኑ ሲያካሂድ የቆየውንና ዛሬ ጠዋት ገሃድ የኾነውን አስከፊ ማፊያ ተግባር የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ዋና ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” የሚል ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገልጧል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሚያዝያ 24 ቀን 2004 ዓ.ም “ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪዎች” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ የጨለማ ቡድኑን አባላት “ጆቢራዎች እና ወሮበሎች” በማለት የገለጻቸው ሲኾን ድርጊቱም “በቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው አሳሳቢ ኹኔታ መገለጫ ነው” ሲል ማጋለጡ ይታወሳል፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም እንደገለጹት በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር የፓትርያሪኩ አቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ እንዳለበት ያመለከቱ ሲኾን ጸሐፊያቸው አቡነ ገሪማ ከጨለማ ቡድኑ አባላት ጋራ ኾነው እንዲያስፈጽሙም ማዘዛቸው ተረጋግጧል፡፡
በአሁኑ ወቅት የጨለማ ቡድኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪዎች ጋራ በመደመር በፓርላማ የተናገሩትን ውንጀላ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም መስከረም 12 ቀን 2002 ዓ.ም ከቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ከማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ በሚጋጭ አኳኋን የተላለፉ ውሳኔዎችን ለማስፈጸም እየጣረ መኾኑ ተገልጧል፡፡ በሌላም በኩል ኹኔታውን ፓትርያሪኩ በቅርቡ በሚጀመረው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከገዳማት ህልውና እና ክብር መጠበቅ ጋራ ተያይዞ ለሚነሡባቸው አጀንዳዎች እንደ ትኩረት ማስቀየሻ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡

ከዜናው ጋራ የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን እንደ ደረሰን እናቀርባለን፡፡  

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

26 comments:

lele said...

yaletadalo abatoche...

Anonymous said...

እኔ የምለው እንዲህ አይን ያወጣ ግፍ በአደባባይ ሲፈጸም እንዴት ነው ዝም የምንለው፣ መጪው ትውልድ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርም በጣም የሚያዝንብን ይመስለናል:: አቡነ ጳዎሎስ ይቺን ቤተክርስቲያን አይወክሉም፣ እየገደሏት፣ ለአውሬዎች አሳልፈው እየሰጧት ነው:: በፍጥነት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ህዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ ሊተባበር ይገባል:: ምን እስኪሆን ነው የምንጠብቀው???? እባካችሁ ተባብረን አንድ ነገር እናድርግ::
በአገር ውስጥም፣ በውጪ ያለን ሁላችን አባ ጳውሎስን እንደማይወክሉን በተለያየ ምክንያት ተጽዕኖ በማድረግ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ እናድርግ::
ከተጽዕኖዎቹ በጥቂቶቹ
_እሳቸው በሚገኙበት የቅዳሴ እና የክበረ በዓል ማንም ሰው እንዳይገኝ
_ ለአብያተ ክርስቲያን ከንዋየ ቅድሳት በስተቀር ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠት
_ ስማቸው በየትኛውም አብያተ ክርስቲያን እንዳይጠራ ማድረግ
የቤተክርስቲያን ልጆች ደግሞ ከኔ የተሻለ ሃሳብ እንደምታመጡ ተስፋ አደርጋለሁ

ግን እባካችሁ ዝም ብለን አንይ፣ ይቺ ቤተክርስቲያን ሊያጠፏት ነው

Anonymous said...

Yeabatochachin Amlak Egziabhere wedet aleh? Ere betekhinet wedet eyehede new yalew? Min Yeshalal?

Anonymous said...

ebakachehu dejeselamoch lemind new mahebre kidusan eko ewenet eyesera new belachehu batekerakeru mikeneyatum mahebru yemeyesedebu tikit yemayebalu werbeloch aluna bewechem behager westem yanin matsedat alebachehu bay negn

Anonymous said...

ውድ ወገኖቼ አሁን ማልቀሰ አለብን! የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ እጅ ከወደቀ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ በመናፍቃን እጅ ገባች ማለት ነው! እንግዲህ ቁርጣችንን እንወቅ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ድምጹ ብቻ (ሲያዜም ስትሰሙት) የተዋህዶ ሲሆን ውስጡ ግን ከተዋህዶ እጅጉን የራቀ ነው። እንግዲህ እውነት እንነጋገር አንድ ጉዳይ ላጫውታቸሁና እርማችንን እናወጣ መቼም ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ይህንን ታሪክ ሲያነበው እንዴት እንደሚደነግጥ ! ይህውላችሁ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የከምባታ ሀዲያና ጉራጌ ሀገረ ሰብከት ሃላፊ እያሉ (ጵጵስና ሳይሰጣቸው ያንጊዜ ስማቸው ቆሞስ አባ ኃይለ ኢየሱሰ ነበር) ዕንቍ ባሕርይ ተከሥ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ተወክሎ ለስብሰባ ሆሳዕና ከተማ መጥቶ ነበር ከዚያም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ወዳዎቸ በሙሉ ሊቃነ ካህናትና የስብከተ ወንጌል ሃላፊዎቸ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ተጠርተው ሁሉ ታድሞ ነበር። ስብሰባው ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ውስጥ ነበር (ታስታውሳለህ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ? ) ከዚያም መድረኩ ለዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ተለቀቀ አዜመው አዜመው አዜመው ድምጹ ማራኪ ነበር በኋላ ንግግር ሲጀምር ግን ነገር መጣ የሚያወያየን በመናፍቃን ጉዳይ ነበር በመሀል ከቦርሳው ሁለት መጽሔት አወጣ ከፍ አድርጎ ለተሰበሳቢው እያሳየ እነዚህን መጽሔቶች ታውቃላችሁ ብሎ ጠየቀ መጽሔቶቹ ሐመርና መለከት ነበሩ አብዛኛው አዎ አለ እርሱም በሉ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሚያዘጋጁቸው ናቸው እና እንዳትገዙ እንዳታነቡ ሌላም ሌላም ሌላም አለ በእውነት ብዙዎች ደነገጡ ስለእርሱ ልቤ የተሰበረው ያን ጊዜ ነው። ታስታውሳለህ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ? እናም ከብዙ ዘመን በኋላ ያሰበውን የሚያደርግበት ሥልጣን አገኘ አላችሁን ወይኔ ተዋህዶ ወይኔ እናቴ ወይኔ ተዋህዶ ወይኔ የጎርጎሪ ድካም ወይኔ

Anonymous said...

ውድ ወገኖቼ አሁን ማልቀሰ አለብን! የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ እጅ ከወደቀ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ በመናፍቃን እጅ ገባች ማለት ነው! እንግዲህ ቁርጣችንን እንወቅ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ድምጹ ብቻ (ሲያዜም ስትሰሙት) የተዋህዶ ሲሆን ውስጡ ግን ከተዋህዶ እጅጉን የራቀ ነው። እንግዲህ እውነት እንነጋገር አንድ ጉዳይ ላጫውታቸሁና እርማችንን እናወጣ መቼም ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ይህንን ታሪክ ሲያነበው እንዴት እንደሚደነግጥ ! ይህውላችሁ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የከምባታ ሀዲያና ጉራጌ ሀገረ ሰብከት ሃላፊ እያሉ (ጵጵስና ሳይሰጣቸው ያንጊዜ ስማቸው ቆሞስ አባ ኃይለ ኢየሱሰ ነበር) ዕንቍ ባሕርይ ተከሥ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ተወክሎ ለስብሰባ ሆሳዕና ከተማ መጥቶ ነበር ከዚያም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ወዳዎቸ በሙሉ ሊቃነ ካህናትና የስብከተ ወንጌል ሃላፊዎቸ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ተጠርተው ሁሉ ታድሞ ነበር። ስብሰባው ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ውስጥ ነበር (ታስታውሳለህ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ? ) ከዚያም መድረኩ ለዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ተለቀቀ አዜመው አዜመው አዜመው ድምጹ ማራኪ ነበር በኋላ ንግግር ሲጀምር ግን ነገር መጣ የሚያወያየን በመናፍቃን ጉዳይ ነበር በመሀል ከቦርሳው ሁለት መጽሔት አወጣ ከፍ አድርጎ ለተሰበሳቢው እያሳየ እነዚህን መጽሔቶች ታውቃላችሁ ብሎ ጠየቀ መጽሔቶቹ ሐመርና መለከት ነበሩ አብዛኛው አዎ አለ እርሱም በሉ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሚያዘጋጁቸው ናቸው እና እንዳትገዙ እንዳታነቡ ሌላም ሌላም ሌላም አለ በእውነት ብዙዎች ደነገጡ ስለእርሱ ልቤ የተሰበረው ያን ጊዜ ነው። ታስታውሳለህ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ? እናም ከብዙ ዘመን በኋላ ያሰበውን የሚያደርግበት ሥልጣን አገኘ አላችሁን ወይኔ ተዋህዶ ወይኔ እናቴ ወይኔ ተዋህዶ ወይኔ የጎርጎሪ ድካም ወይኔ

Tesfa said...

this is totally unacceptable and we should stand against this decision and talk openly in our churches and sundayschools. All Sunday schools and youth group
orthodoxy associations should get together hand in hand and work stragegically to stop this evil work which is against our beloved mother church.

lamelame europe said...

ebakachohe yehanen gode sameto zeme yameale yalame.ema yamenorawe europe nawe.banse yabirr eredata maderage echelalaho.gene leama?

galela said...

yakedosane Amelake yeradanale.yamenechelawen enarege enetsaley enjea anerabashe.

Anonymous said...

Egizabehare seittle enje semata ayetayem.yewadekalo

Anonymous said...

kaga gare yalawe yebaletale.

Anonymous said...

Enezih sewoche drama eyeseru erasachewen yasedestalu ende? YeMayehone negere new Enkubahri.

Anonymous said...

pls let us do the same thing what muslim people against their leaders.let us aganist abune paulos.

Anonymous said...

anonymous on May 7, 2012 8:13 PM, mentioned a lot of good points, but I disagree on not calling his name on kidsse. Because it is the law we have to see. Teseno lemasader, we can stay away from being at the place where he will be or others b/c it is not Dogma or Cannona. But calling the present time patriarch is a rule and law we have to do. It will also open a door to have too many geleltegna kind churchs. Not giving money is also good. Because there are other ways we can help churches, gedamat, adbarat... They are playing with the money, so why give to players.

Adinen said...

Aye Aba Paulos 40 million yemiyahil Orthodox Christian lay endih yale yeseytan sira lemin yiseralu Ye'Teklehaymanot Amlak yihinih gif yimelketew enbachinin yabisilin yerson gin abetu wedelay angaten asalifen setitenal. midirawiw firdima meche ewinet alew.

michael said...

+++
በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሊያተራምሱት ፈልገዋል ማለት ነው::

ጌታ ሆይ እርዳን እባክህ

ከዝዋይ

Anonymous said...

+++
በግንቦቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሊያተራምሱት ፈልገዋል ማለት ነው::

ጌታ ሆይ እርዳን እባክህ

ከዝዋይ

Anonymous said...

አሁን የቁርጥ ቀን ላይ ደርሰናል። ዓይናችን እያዬ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትጠፋ ሞት በቀደመን። አባ ጳዉሎስ ለዚህ ነበር የተሾሙት? አቡነ ገሪማስ? በልጆቻችሁ ሬሳ በቤተ ክርስቲያን ዉድቀት ለመክበር ነበር አክሊለ ሶኩን የተሸለማችሁት? የአቡነ ጴጥሮስ አጽም፣ የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረዳችሁ። አሁንስ በእናንተ አፈርን...አባቶቻችን ብለን እንዳልተኩራራን አንገታችን ደፋን...ዕንቁ ባህርይን በማደራጃ መምሪያዉ መሾማችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለማጥፋት ብላችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል...የምታጠፉት ገዳማቱን ፣የአብነት ትምህርት ቤቶችን፣የሰ/ት/ቤቶችን፤በመጨረሻም ክብራችሁን መሆኑን እወቁ። ሁላችንም እናልፋለን ቤተ ክርስቲያን ግን ትኖራለች።

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

አሁን የቁርጥ ቀን ላይ ደርሰናል። ዓይናችን እያዬ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትጠፋ ሞት በቀደመን። አባ ጳዉሎስ እና አቡነ ገሪማ በልጆቻችሁ ሞት፤ በቤተ ክርስቲያን ዉድቀት ለመክበር ነበር አክሊለ ሶኩን የተሸለማችሁት? የአቡነ ጴጥሮስ አጽም፣ የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረዳችሁ። አሁንስ በእናንተ አፈርን...አባቶቻችን ብለን እንዳልተኩራራን አንገታችን ደፋን...ዕንቁ ባህርይን በማደራጃ መምሪያዉ መሾማችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለማጥፋት ብላችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል...የምታጠፉት ገዳማቱን ፣የአብነት ትምህርት ቤቶችን፣የሰ/ት/ቤቶችን፤በመጨረሻም ክብራችሁን መሆኑን እወቁ። ሁላችንም እናልፋለን ቤተ ክርስቲያን ግን ትኖራለች።

Anonymous said...

ምንም ስጋት አይግባችሁ፤ ይህም ሴራ እንደቀደሙት ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንደ አመጣጡ እንመልሰዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን እኮ ከዚህ በላይ እጅግ የከፉና የሚከብዱ ፈተናዎችን ድል ያደረገች የድል አድራጊው ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ የመድኃኔዓለም ቤት ነች!!! አንድ ቁም ነገር ልንገራችሁ፤ ከቻላችሁ ለጆቢራው ቡድን አባላት በተለይ ደግሞ አሁን ሥልጣን ተሰጠው ተብሎ እንደ ነብር እያያችሁት ላለው ለዕንቁባሕርይ አስነብቡልኝ "ቤተ ክርስቲያን ላይ እጃችሁን ለመጫን በሞከራችሁ ቁጥር እኛ እየተከታተልን የእጃችሁን እንደምንሰጣችሁ አትዘንጉ፤ የምንታዘዛችሁ ላከበረቻችሁ ቤተ ክርስቲያን እስከታዘዛችሁ ድረስ ብቻ ነው፤ እርሷን ከነካችሁ አልቅሳችሁ ለማታባሩበት መከራ ራሳችሁን አሳልፋችሁ እንደሰጣችሁ እወቁ፤ ወትሮም ፈሊጥ የማይገባውን በፍልጥ ይላሉ አበው፤ የተዘጋጀላችሁ ፍልጥ ምን ያህል እንደሚያሳምም ለማወቅ ተገርፋችሁ መፈተን ያለባችሁ አይመስለኝም፤ ዱላው ከተጀመረ ለመፀፀት እንኳን ጊዜ አታገኙምና፤ ስለዚህ ብልህ በባልንጀራው ሞኝ በራሱ ይማራልና ከዚህ ቀጥሎ የምታደርጉት ነገር ሞኝ ወይም ብልህ መሆናችሁን ያሳውቀናል፤ ተጠንቀቁ! ተጠንቀቁ! ተጠንቀቁ!"

Anonymous said...

A generation which can not bring a single solution!Why not we inform laity & go together to ask Holy Synod to make tangible decisions & participate on practicability of decisions ?
"The dogs bark , the camels go their way"
Really we are the dogs who can not stop the camels Patriarch & His group while we have right & ability to stop.
Shit!!!!!!!!!!!!!!
Look the muslims . They have courageous while the will go to hell after their death. But we having hope to go heaven after our death , we are very frustrated.
Please let us take action.
Unless otherwise only reports , with no action is making a bad history.
Please organize!!!!!!!

Anonymous said...

Aye, yewaldiban guday lemadebesebesm yetasebe lihon yichilal. Min addis neger ale!

Anonymous said...

ከሞስሊሞች ልንማር ይገባል!
ጳዎሎስ ይቺን ቤተክርስቲያን አይወክሉም!!!
ከስልጣናቸው ይወገዱ !!
በእድሜያቸው እንጅ በተግባር የሚከበሩ ሰው አይደለም/ሉም::

Anonymous said...

Deje Selam, any I am tired of reading this kind of news and doing nothing? What can we do for a solution? Majority of Ethiopian Orthodox followers are confused and don't know what to do. Please come up with some idea and let us save our church.

lele said...

aende sawe kalaye hasabe siesate enda moselimoche enehone belole.
sereata batakerestain nawaye?
ename yahona nagare marage enedalaben amenalaho.kase honawe yagabote lakase yalanen kebere selawako nawe........
GENE baka abatohe abate kalehoneo/////

Anonymous said...

"Ye'asa gimatu kechinqilatu new" We have to remove the cancer cell of the church and that is "Beyonce's Guider". And we know what caused the cancer, his past unpleasant behavior. He is being threatened by ELIZABET. His shame ful pictures will be posted every where if he refuses to obey the blood sucking ticks feeding on the church.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)