May 6, 2012

"ቤተ ክርስቲያናችንን መጠበቅ ኃላፊነታችን ነው" (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ)


ቤተ ክርስቲያናችንን መጠበቅ  ኃላፊነታችን ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ 
በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ : ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን: በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን:: ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኅይል አትግዙ “ ፩ ጴጥ ፭፥ ፪-፫
 
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጽንዖት  ሰጥታ ከምታስተምረው ትምህርት መካከል አንዱ በሃይማኖት የተሰጠንን ኃላፊነት እንዴት መወጣት አንደሚገባን ነው ። ይህ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የእምነቱን ተከታዮች በሙሉ የሚመለከት ሲሆን ፤ ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ፤በማስተማር ፤ በመዘመር ፤ እውነትን በመመስከር ፤ ለሌሎች ምሳሌ በመሆን ፤የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በመጠበቅና በማስጠበቅ ፤ ደሃ እንዳይበደል ፤ ፍርድ እንዳይጓደል በቅንነት ውሳኔ በመስጠትና  ተመሳሳይ  የሆኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመፈጸም የሚገለጽ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም  “ ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር እንዘ ትሬእዩ ሠናየ ግእዞሙ ወተመሰሉ በሃይማኖቶሙ ፦ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው” ዕብ 13፡7  ያለው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የተወጡ አባቶቻችንን በመመልከት እነርሱንም በሃይማኖት ፤በበጎ ምግባር እና ኃላፊነትን በመወጣት መስለን እንድንገኝ የተሰጠንን አደራ የሚያሳስብ ነው። ለዚህም ነው በሁሉም ቦታ የሚገኙ ክርስቲያኖች ጉዳየ ብለው የቤተ ክርስቲያንን ነገር በመከታተል የቤተ ክርስቲያን አምነት ሥርዓትና መዋቅር በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይፋለስና ሰዎች የሚሰናከሉበት ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ለማድረግ መነሳት የሚገባቸው። ቤተ ክርስቲያን ከውስጥና ከውጭ ችግር ቢገጥማትም ፤ ከባድ የሚሆነው ከውስጥ የሚፈጠር ችግር ነውና በግልጽ እየተነጋገሩ ፤እውነትን  በመያዝ ለተፈጠረውም ችግር ሥር ሳይሰድ መፍትሔ እየሰጡ መሄድ  በተለይም  ቤተ ክርስቲያንን በኃላፊነት ከሚመሩ አባቶች የሚጠበቅ ነው ። 
ይህንን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ለመወጣት የቀደሙት ክርስቲያኖች የከፈሉትን መስዋዕትነት ስንመለከት እራሳችንን እንድንመረምርና አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በምንፈጽመው ስህተት የቱን  ያህል ቤተ ክርስቲያንን  እንደምንጎዳ ፤ ጸጋና በረከት እንደምናጣ ፤እግዚአብሔርንም እንደምናዛዝን  ያስገነዝበናል ። የተሰጣቸውን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ለመወጣት ሲሉ ብዙዎች ሰማዕትነት ከፍለዋል።ሐብትና ንብረታቸውን ለቤተ ክርስቲያን የሰጡ( ሐዋ 2፡45  )፤ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ቀንና ሌሊት ያገለገሉ ፤ እምነት የሌላቸውን ነገሥታትና መኳንንት ጭምር ሳይፈሩ  እውነትን የመሰከሩ ፤ የተገረፉ፤ በሰይፍ የተመተሩ ፤ ለአውሬ የተሰጡ ፤ በድንጋይ የተወገሩ ፤የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞረው ያስተማሩ  ፤ የዓለም ክብር ይቅርብን ብለው በዋሻና በምድረበዳ በጸሎት ተጠምደው የኖሩ  እነዚህ ሁሉ መከራን የተቀበሉት ፤ የቤተ ክርስቲያንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት የሚያስገኘውን ክብር ፤ ችላ ብለው ደግሞ ጊዜያቸውን ቢያሳልፉ የሚጠብቃቸውን ፍርድ በመመልከት ነው ። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ይመለከተኛል ኃላፊነትም አለብኝ ብለን ለእውነተኛ አገልግሎት የምንነሳው በእግዚአብሔር የፍርድ ሚዛን ቀለን እንዳንገኝ ነው ። የኑሮአቸውንም ፍሬ ተመልከቱ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው የሰዎችን ስም  ሳይሆን  ምግባራቸውንና የእምነታቸውን  ፍሬ  ለይተን እና ትክክለኛነቱን አረጋግጠን እንድንከተላቸው ማሳሰቡ ነው ። 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ የተመሰረተውም ይህንን  የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ለመወጣት የሰንበት ት/ቤት አባላት ድርሻቸውን በመረዳት ለቤተ ክርስቲያን መዋቅር እምነትና ሥርዓት  መጠበቅ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ለማበረታታት ነው ። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ከተመሰረተ 12 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ከአኅጉረ ስብከት ጋር አብሮ በመስራት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠናከር፤ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ ፤ገዳማትና አድባራት ያለባቸው ችግር እንዲቃለል ድጋፍ በማድረግ እና በመሳሰሉት መንፈሳዊ አገልግሎቶች እየተሳተፈ ይገኛል። ለአብነትም ያህል በምዕራብ ጎጃም ዞን የዋሻ አምባ ቅ/ተ/ኃይማኖት ገዳም የወፍጮ ተከላ ፕሮጀክት:በጅማ እና አካባቢው በአክራሪ እስላሞች ጉዳት ለደረሰባቸው አብያተክርስቲያናት እና ምዕመናን መልሶ ማቋቋሚያ $11,000 (አስራ አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር)፤ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የፅርሃ ጽዮን ማህበር ጋር በመተባበር በጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ሰባክያንን በቋንቋቸው ለማሰልጠን የተነደፈውን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ በመሸፈን፤ በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በሆሳዕና ከተማ የሚገኘውን የንባብ እና የቅዳሴ ት/ቤት ፕሮጄክት በማስፈጸም፤ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙት ሶስቱ አኀጉረ ስብከቶች መካከል  የዋሽንግተን ዲሲ እና የካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከትን ለማጠናከር በሚደረገው እንቅስቃሴ በገንዘብ እና በሌሎች አስፈላጊ ነገሮች በማገዝ፤ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ካከናወናቸው መልካም ስራዎች ከፊሎቹ ናቸው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚተዳደርበትን ደንብ  በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አህጉረ ስብከት ታይቶ የጸደቀ ሲሆን በየጊዜው የሚያደርገውንም እንቅስቃሴ ለብፁዓን አባቶች እና ለአህጉረ ስብከት ጽ/ቤት በመግለጽ  ለአሠራር የሚጠቅሙ ሀሳቦችንም በመቀበል ሲሠራ ቆይቷል።በተለያየ ጊዜ ከቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው ከመጡ ብፁዓን አባቶች ጋር  እና ከሚመሯቸው አኅጉረ ስብከት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት   በርካታ ዓመታትን አሳልፏል።
ካለፉት 6 ወራት ማለትም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና የካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተመደቡ ወዲህ ያሉትን ነገሮች ስንመለከት ግን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ኅብረት : ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ : ለምዕመናን ፍቅርና ሰላም የሚደክሙትን ሁሉ ግራ የሚያጋቡ ነገሮችን እየተመለከትን መጥተናል ። ለመጥቀስም ያህል ላለፉት 12 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኘውን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ አላውቀውም የማለት ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር መጠበቅ የማያመላክቱ ሹመቶችን ሲሰጡ ማየት ፤ ለቤተ ክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ የሚሰጠውንና ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረት የሚቀንሱ ደብዳቤዎችንና  ፤ ያለ አግባብና ያለ ሥርዓት ሥልጣነ ክህነትን ለመያዝ የሚደረጉ ሙከራዎችን በማየታችን የበለጠ ግራ እየተጋባን እንድንሄድ  በማድረጉ ለቤተ ክርስቲያን  መዋቅር እና ለሥልጣነ ክህነት የተሰጠው ክብር  እያነሰ መጥቷል የሚል አመለካከት አሳድሮብናል ።
 በተለይም በአባቶች የተፈረሙ ደብዳቤዎች የቅዱሳን ክብር በሚዋረድበት አባ ሰላማ በተባለ ብሎግ (የመጻጻፊያ መድረክ) ላይ በተደጋጋሚ ሲወጣ ማየታችን  ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሮብናል፤እንዴት ይህ ሊከሰት ቻለ ? የሚል ጥያቄ አሳድሮብናል።  የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት  የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት በስልክና በደብዳቤ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል ።
በአጠቃላይ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ  አሁን የምንመለከተው ችግር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገንዝበናል ። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅርና ሥርዓት የሚያዳክሙ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ተገቢ አለመሆናቸውንና የመናገር መንፈሳዊ ኃላፊነት  እንዳለብን በመገንዘብ ብዙዎቻችንን ግራ እያጋባ ያለው አካሄድ በአስቸኳይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሔ መስጠት እንዳለበት አናምናለን ። በዚህም መሰረት ፦
1.              ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜን አሜሪካ የቤተ ክርስቲያን መዋቅርን ጠብቆ ስለመሥራት  ግልጽ  የሆነ መመሪያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን
2.             ከዚህ በፊት የነበሩት ብጹዓን አባቶች ያደርጉት እንደነበረው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓትን የበለጠ እንዲጠናከር የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚጠናከርበት መንገድ እንዲመቻችልን
3.             የቤተ ክርስቲያንን ደረጃ ያልጠበቁ ፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን  ተጽዕኖ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ ደብዳቤዎችና አሠራሮች ሥርዓት እንዲይዙ እንዲደረግ  እንጠይቃለን።
4.             በቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች የሚጻፉ ደብዳቤዎች የቅዱሳን ክብር በሚነቀፍበት ብሎግ እንዳይወጣና የቤተ ክርስቲያንን እና አባቶችን ክብር ዝቅ እንዳያደርግ  ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን
                                        ሚያዝያ 23 2004 ዓ. ም            
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ስራ አመራር
ሰሜን አሜሪካ
ግልባጭ:
·                     ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ፣
·                     ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት 
·                     ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት  
·                     በሰሜን አሜሪካ ላሉ ሶስቱም አህጉረ ስብከት
·                     ለሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በያሉበት ፣11 comments:

Unknown said...

Very nice article...
I recall a proverb in the Holly Bible
"be'abatoch fenta lijoch tetekulish"
please hand over this great mettel to the next generetion!

The EOTC Sheep said...

በጐችን በትኖ ፍየልን መጠበቅ
===================
ይድረስ ለብጹአን ወቅዱሳን ጳጳሳት የቅዱስ ሴኖዶስ አባላት።

ውድ አባቶቻችን።

ለመሆኑ ይህን አውቃችኋል፧ የላካችሁልን አባት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በጐችን በትነው ፍየል ጥበቃን እንደተያያዙት ታውቃላችሁን፧ በጐች አንበተንም እረኛችን እርስዎ ነዎት ኑ ይጠብቁንዕ ብለው ቢጠይቁ ክቃለ አዋዲ ውጭ በሆነ የብዕርና ወረቀት ዱላ አወረዱባቸው። ይህን እየተደረገ ያለውን ድርጊት እንዳልፈረሰው የፓትርያረኩ የቁም ምስል ቀላል አድርጋችሁ አትዩት የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና እና መዋቅር እየተሸረሸረ ነው።

ላለፉት ስድስት ወራት የሃገረ ስብክታችን አስተዳዳሪ ማለትም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና የካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በቅዱስ ሴኖዶስ ተመድበው ከተላኩበት ቀን ወዲህ ያሉትን ነገሮች በዚሁ በተመደቡበት ሃገረ ስብከት ውስጥ ሆነን ስንመለከት ግን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ኅብረት ፥ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ፥ ለምዕመናን ፍቅርና ሰላም የሚደክሙትን ሁሉ ግራ የሚያጋቡ ነገሮችን እየተመለከትን ነው። ለመጥቀስም ያህል በአሜሪካ ምድር ሃገረ ስብከት የለም ማለት ፤ በቃለ አዋዲ የምትመራ ቤተ ክርስቲታን የለችም ማለት ፤ ካህናትን ቅስናችሁን እይዛለሁ እያሉ ማንገራገርና በተግባርም መተርጎም ፤ ላለፉት ፩፪ ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኘውን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ አላውቀውም የማለት ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር መጠበቅ የማያመላክቱ ሹመቶችን ሲሰጡ ማየት ፤ ለቤተ ክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ የሚሰጠውንና ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረት የሚቀንሱ ደብዳቤዎችንና ፤ ያለ አግባብ የቤተ ክርቲያኗን የቀኖና ሥርዓት መጣስ የሚደረጉ ሙከራዎችን በማየታችን የበለጠ ግራ እየተጋባን እንድንሄድ በማድረጉ ለቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ለሥልጣነ ክህነት የተሰጠው ክብር እያነሰ መጥቷል የሚል አመለካከት አሳድሮብናል ።
በተለይም በአባቶች የተፈረሙ በጣም በጣም የሚገርም እና የሚያሳዝነው ደገሞ ፤ ከፓትርያኩ የተላኩ ደብዳቤዎች የቅዱሳን ክብር በሚዋረድበት አባ ሰላማ http://www.abaselama.org በተባለ ብሎግ (የመጻጻፊያ መድረክ) ላይ በተደጋጋሚ ሲወጣ ማየታችን ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሮብናል፤ እንዴት ይህ ሊከሰት ቻለ የሚል ጥያቄ አሳድሮብናል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና አንዳንድ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት እንደጠቀሱት ፤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት በስልክና በደብዳቤ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል ።
ውድ ኣአባቶቻችን እባካችሁ የበጐችን እረኛ ላኩልን፤ እባካችሁ በጐችን የሚበትን ሳይሆን የጠፋቸዋን በግ የሚፈልገውን የክርስቶስን ባለሟል ላኩልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ። አሜን ።

Anonymous said...

አወ "ውድ አባቶቻችን እባካችሁ የበጐችን እረኛ ላኩልን፤ እባካችሁ በጐችን የሚበትን ሳይሆን የጠፋቸዋን በግ የሚፈልገውን የክርስቶስን ባለሟል ላኩልን።"

lamelame europe said...

ebakachohe ega ande mahonen kaUSA enemare

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

መልካም ሥራ ነዉ። በአሜሪካ እየተዛመተ ያለዉን ሥርዓተ አልበኝነትንና የተሀድሶ መናፍቃንን ሕዋስ ከቤተ ክርስቲያን ቅጽር ለማስወገድ የወጣቱ ተሳትፎ ራኢ ለአላት ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊና ወሳኝ ነዉ። የህሊና ህግ የማይዳኛቸዉ ህገወጥ ዳኞች ተበራክተዋልና በርትተን እንሥራ። የዚህ ክፍለ ዘመን የሃይማኖት አርበኞች እንሁን። አሉባልታና ወሬ ሳይበግረን ጠንክረን እንሥራ በርቱ ከጎናችሁ ነን።

Anonymous said...

ኧረ ደጀ ሰላሞች እባካቹ እስቲ አንድ ጊዜ ወደ ጀርመን ጎራ ብላችሁ እዩን በምንፍቅና ምዕመናን እያለቀን ነው።

ስለ እመአምላክ ብላችሁ። አደራ በሰማይ በምድር


ከዚህ በፊት የጀርመን ቤተክርስቲያን በተመለከተ መዘገባቹ የሚታወስ ነው።

ታድያ በዚያ ሰዓት የዘገባቹት በፓስተር ገዳሙ ጉዳይ ነበር።

የአሁኑ ግን እጅግ የከፋ ነው!!!!!!!!!!!!!!!

የዓሣ ግማቱ ከአናቱ እንደሚባለው ሁሉ የጀርመን ቤተክርስቲያን ለቀ ካህን ተብየው ዶር መርሐዊ ተበጀ የተባለ እንኳን ዶር ሊባል ምንም አይገባውም።
አሁንስ አለቅን ድረሱልን።

ሰሞኑ በፋሲካ የኢየሩሳሌም ጉብኝት በሴቶች ልማድ ካይ ሆኖ ቅዱስ ቁርባን መቁረብ፤
አሳማ የማንበላው ኢትዮጵያን ስለሆንን ነው እንጂ ኃጢአት አይደለም
ሴቶች ወንጌል ማንበብ ይችላሉ በማለት አስተምሮ ሲጨርስ ለሚስቱ አንብቢ በማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነ ክፍል አውጥቶ ሰጥቶ አንብባለች።

እኔ ተቃጠልኩኝ አሁን ከቤተክርስቲያን መጥቼ ተጓዦች ነግረውኝ አልቅሼ አልወጣ አለኝ።

ምን እናድርግ ?

lele said...

YALETADALACHOHE ABATE.....

Anonymous said...

Beyederejaw yalachihu Abatochachen ebakachihu selebetekrstian Amlak belachihu ewunetegna meri,mekari astedadari abat lakulen. Egna Aba Fanuaelen ayidelem yemenekawemew/yemenetelaw yilkunem sirachewun alamachewun enji. Enen yemidenkegn keteleyaye bota tekawumo getemuachew noro America le mukera/lebelete tifat melakachew new. Yih hulu hono sale egna gin Abatachin belen aberen lemeserat betedegagami tiyake benakerbelachewum alawukachihum yemelaetachew neger yasazenal, kemanew yemayitebek sihetet! Meche yihun yemimelesut? Amlak hoy tenesh leben setelen rub ken enquan yemitsetsetubet. Abatoch ere Abat lakulen,,,,

መላኩ said...

የዲያብሎስ አበጋዞች ቱርክ ሙስሊሞች የቁስጥንጥንያን በር ጦር ይዘው ለማንኳኳት ሲሰጋጁ የቁስጥንጥንያ ክርስቲያኖች የምላዕክት የዓይን ቀለም ጥቁር ወይስ ሰማያዊ በማለት እየተነታረኩ እራሳቸውን አደከሙ። ከዚያ አያ ጅቦ መጥቶ ሁሉንም በላቸው፡ ቁስጥንጥንያንም ኢስታንቡል ብለው ጠሯት። እኛም የሰሜን አሜሪካ ያገር ቤት ሲኖዶስ፡ የአለቃ ገበየሁ ንግግር፡ የአባ እንትና ኃውልት ቅብርጥሴ ስንል ጥገኞቹ የዲያብሎስ ልጆች ከነነፍሳችን ሊበሉን እየተዘጋጁ ነው። ሁሉ ነገር ቁልጭ ብሎ በሚታይበት ዘምን ለምን ይሆን ነገሮችን ማየት የተሳነን?

Anonymous said...

Hasabu Melkam Nebere yetemala neger gin yelewim Abune Fanueil Yeserut Melkam neger Metsekes neberebet Sewn Sinkawem Dekama gonun bicha sayihon Tsenakara Gonun menager alebin
Lemehonu Yesenbet Timhirt bet Andinet Gubae Malet Min Malet new ?Debdabew Mamalat yemgebaw neger nebere And Sew ( Anid Mahiber) tenesito Hulunim yewkele memisel yelebetim Andinet Gubae Malet Min Malet New ? Ahun Min Andinet Ale ?
Abune Fanueil yemdegifachewm bizu Mehonun mawek yasfelgal Enkawmalen yemilu Degimo Simachewn -Debrachewn -Maninetachew
Megilets Alebachew Ahun Yemimesilew yetelemedew Ya Mahiber Tekawimo new
Min Andinet Ale ? ye Abune Pawlos -Ye Abune Merkorewos-Geleltega-Yeshew-yegonder-yetsgiray- yeoromo Church tebilo tekefafilo Andinet Gubae Malet min malet New

Anonymous said...

የአንድንቱ አባላትም ሆናቹህ የሌሎች ሰንበት ት/ቤት አባላት ሁላችሁ ስራችሁን እግዚአብሔር ይባርክ፤ በርቱ።

እየጸለይን እግዚአብሔር በሰጠን አቅምና ችሎታ ሁሉ እየተባበርን ቤተ ክርስቲያናችንን እናሳድግ/እናስፋፋ/ነቅተንም እንጠብቅ።


ከአቡነ-ተክለሃይማኖት ወአቡነ አረጋዊ/ዳላስ.ቴክሳስ/ምዕመን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)