May 3, 2012

በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከፈታል" መባሉን ምዕመናን ተቃወሙት በሚል በደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ለቀረበው ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ


(ፍሰሐ ተስፋዬ)              
 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከፈታል" መባሉን ምዕመናን ተቃወሙት በሚል በደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ለቀረበው ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ

መግቢያ
አለመታደል ሆነና ዛሬ አውላላ ሜዳ ላይ ቆሜ የማስነብባችሁ ነገር ከላይ በጠቀስኩት ብሎግ ላይ ስማችንን ለማጉደፍ የፈለጉ አንድ ግለሰብ በእኔ በአቡነ ኤልያስና በአባ ኒቆዲሞስ ላይ የጻፉትን የሐሰት ውንጀላ ለማስተባበልና እውነቱን ለማሳየት እፊታችሁ ወጣሁ። ራሴን አስተዋውቄ ዝርዝር ነገሩን በመጠኑ አስረዳለሁ።
 
እኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ስሜ ፍሰሐ ተስፋዬ ይባላል። የምኖረው በስቶክሆልም ስዊድን ነው። በክህነት ደረጃዬ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ካህን ነኝ። ድቁና በ1976 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ ዘከፋ ጂማ ተቀብያለሁ። ቅስና በ1985 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ሊቀ ጳጳስ ዘአርባምንጭ ተቀብያለሁ። በደብር አስተዳዳሪነት ደግሞ በዳውሮ ዋካ ደብረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከ10 ዓመት በላይ አገልግያለሁ። በዘምናዊው ትምህርት ደግሞ የትምህርት ባለሙያ ስሆን  በመምህርነት፤ በርዕሰ መምህርነትና በትምህርት ባለሙያነትና በኃላፊነት ወደ ሃያ ዓመት ያህል  አገልግያለሁ። በመምህራን ኮሌጅና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርቴን ተከታትያለሁ። በከፍተኛ የትምህርት ባለሙያነት አገልግያለሁ።
እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሀገሬን በጣም እወዳለሁ። በሀገራችን ያለውን የወያኔ ህወሃት ገዢ ቡድንን ከልቤ እቃወማለሁ።በዚህ የተነሳ ማንኛውንም ሀገራዊና ጸረ ወያኔያዊ እንቅስቃሴን የቻልኩትን ያህል እደግፋለሁ። ገዢውን መንግሥት ትቃወማለህ፤ ህዝብን በመንግሥት ላይ አነሳስተሃል ተቃዋሚን ወክለህ በምርጫ ተሳተፈህ አሸንፈሃል፤ ነፍጠኛ ነህ በሚልና በየሰበብ አስባቡ በወያኔ የተለያዩ ጊዜያት እየታሰርኩ ስጉላላ የቆየሁ ነኝ። የእኔን የሀገር ቤት ማንነት የሚገልጽ በቂ አድራሻና ሰፊ ህዝብ የሚያውቀኝ ሰው ነኝ። ስለራሴ በዚሁ ላብቃ።
ይህንን የዘረዘርኩት ያለምክንያት አይደለም። ወይም ራሴን ማስተዋወቅ ፈልጌም አይደለም። በእኔ ላይ አንድ ግለሰብ ላደረሰብኝ የሐሰት ስም ማጥፋት ጽሑፍ ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት እንዲያመቸኝ ራሴን ማስተዋወቄ ነው። ጸሓፊውን መቼም አንቱ ልበላቸውና ስማቸውን ሳይጠቅሱት ትተውታል። እኔ ግን እንደሳቸው ስሜን በመደበቅ መዋሸት አያስፈልገኝም። ውሸታም ደፋር አይደለም እንጂ ወደፊት ደፍረው ከወጡና እውነተኛ ከሁኑ በፊትለፊት ስንገጥም ታውቋቸው ይሆናል።
ጸሓፊው በስዊድን “አዲስ ቤተክርስቲያን ይከፈታል” መባሉን ምዕመናን ተቃወሙ በሚል መንደርደሪያ ርዕስ የእኔን ስም ለማጥፋት ሞክሯል። የእኔስ ግድ የለም በተለይ የብፁዕ አቡነ ኤልያስ ስም ያላግባብ መጠቀሱ ያሳዝነኛል።   
እኔን ጸሐፊው በንጉሠ ነገስቱ ወይም በደርግ ኢሠፓ አሊያም በወያኔ ዘመን ከፍተኛ ባለስልጣን ወይም ሚ/ር ሆኖ ጓደኞቹን ወይም በርካታ ንጹሃንን በቀይ ወይም በነጭ ሽብር ወይም በሌላ አስገድሎና ገድሎ በዚህ ዉለታው ሳቢያ ተሹሞ ካገር የወጣ ሰው ነበር ባለማለታቸው አመሰግናቸዋለሁ። ሌላ የፈለጉትንና የሚሹትን ወይም የቀድሞ የራሳቸው ወንጀል ጨምረው የእሱ ነው ያለማለታቸው ደስ ይለኛል።  
ላለፉት ወይም አሁን ላለው የወያኔ ሥርዓት  እንዲያገለግል አምባሳደር ሆኖ  ተሹሞ ተሸልሞ ወደ ውጭ አገር የተላከና ሀገሩን የከዳ ከሃዲ ነው ቢሉኝ እታዘባቸው ነበር። እኔ ግን ከወያኔ ጋር ነፃነትን ሽጦና የባርነት ቀንበርን ተሸክሞ ከመኖር ይልቅ ተሰድጄ ካገሬ መውጣትና መኖር ነበረብኝና ነው የተሰደድኩት። ሌሎች እኔነቴን የሚያሳዩትን መረጃዎች ሲያስፈልጉ ወደፊት እመለስበታለሁ።
በስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ በአንድ ቤተክርስቲያን ባልሆነ የግል ማህበር ውስጥ የሕዝብ ቤተክርስቲያን መስሎኝ ለተወሰኑ ዓመታት ሳገለግል ቆይቻለሁ። ከዚያም በእኛ በካህናትና በቤተክርስቲያኗ ባለቤቶች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት እያደገ መጣ። የደበቁንን መረጃ አግኝተን እኛንም ሆነ የስቶክሆልምን ምዕመናን ይቅርታ እንዲጠይቁ የመክረናቸውን ምክር ባለመቀበላቸው ምክንያት ትተንላቸው ልንወጣ ችለናል እንጂ ጸሓፊው እንደቀባጠሩት ጸቡ የተፈጠረው በዋናነት በቀኖና ጉዳይ እንጂ በፖለቲካ አመለካከት ብቻ አይደለም።
                     
              ወደ ዝርዝር ጉዳዩ ልውሰዳችሁ።
ጸሐፊው ፖለቲከኛ፤ ሰነፍ፤ ምግባረ ብልሹ ወዘት በማለት ወርፈውኛል። በመሠረቱ በዚህ ባለንበት የስደት ዓለም እንኳንና ሳይሰሩ ቀን ከሌሊት ተሰርቶም ራስንና ቤተሰብን መምራት የሚከብድበት ዓለም መሆኑን በውጪው ዓለም ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይገነዘባል። ይህች “”የሥነ ምግባር ብልሹነት”  የምትባል የወያኔ ታፔላ የሆነች ቃል ከኮከበ ጽባህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ጀርባ ተነስታ ማነህ ባለሳምንት ብላ በደጀ ሰላም አልፋ እውጭ ሀገር ተሰድዳ መጥታ ስታበቃ እኔ ላይ ከየት እንደመጣችና ማን እንደለጠፈብኝ ለማወቅ አልከበደኝም። ለዚህ ማስረጃ አሁን ምን እንደምሰራና የሚከፈለኝን እዚህ ላይ ማውራት አያስፈልገኝም። ተጧሪ ነው ከዘራ ይዞ ይዞራል አለማለታቸው ይመሰገናሉ።
ጸሓፊው የአቡነ አረጋዊ ታቦት በስቶክሆልም መ/ጸ/ቅ/ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ መሆኑን እያወቅን ለጨረታ በሚመስል መልኩ እኛ ሌላ ታቦት እንዳስመጣን አስመስለው ጽፈዋል። ይህ ሓሳብ በመሰረቱ ለስቶክሆልም ምዕመናን በተለይ ለተጠቀሰው ደብር ማህበረ ምዕመናን የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህንን ልንል የቻልንበት ምክንያት በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ የተባለው ታቦት መቼ እንደመጣና መቼ ይነግሳል እንደተባለ የተከበሩት የደብሩ ካህን እውነቱን እንደሚናገሩ አልጠረጠርም። እርስዎ ያሉት ውሸት ነው። ስቶክሆልም ብዙ እውነተኞች እንደሚኖሩ ስለማምን እውነቱን እንዲናገሩ በቅ/ሥላሴ ስም አደራ እላለሁ።
የዱብ እዳውን ታቦተ አቡነ አረጋዊ ጉዳይ የደብሩ ምዕመናንንም ሆነ መላው የስቶክሆልም ህዝብ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ማለት አልፈልግም። እውነቱን እግዚአብሄር ያውቃልና ለእሱ ልተው።
በዚሁ አጋጣሚ የብዙ ዓመት ጥያቄያችሁ የተመለሰላችሁ የደብሩ አፍቃሬ አቡነ አረጋዊ የሆናችሁ ምዕመናን የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ! ”ሊሁሉም ጊዜ አለው እላለሁ። 
በካህናትና በማርያም “ቤተክርስቲያን” ባለቤቶች መካከል የተፈጠርው
   ያለመግባባት ምክንያቱ ምንድነው?
ዋናው ልዩነቱ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ይከበር እንላለን እኛ። አይ እኛ የቤተክርስቲያኗ ባለቤቶች ያልነው ይሆናል ይደረጋል በሚሉት የቤተክርስቲያንዋ ባለቤቶች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው። የቤተክርስያንዋ ባለቤቶች ደግሞ መቀደስ እንጂ ካህን ሌላ ምንም ጥያቄ ለማንሳት አይችልም ባዮች ናቸው። አንኳር አንኳር የሆኑትን የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ግድፈቶች አሉ። ሊስተካከሉ ይገባል። ሊጣሱ አይገባም ብለናል።
         
የተጣሱትን የቤተህርስቲያን ሥርዓቶችንና ቀኖናዎችን እንመልከት
ቀደም ብለው ከአገር በመውጣታቸውና በመሰደዳቸው ምክንያት አብዛኛው ወገኖቻችን ቤተክርስቲያን መስርተው አባቶች ካህናትን ለአገልግሎት በማምጣት የቤተክርስቲያን ሥርዓት እንዲከበር፤ ምዕመናን እንዲበዙ፤ በስደት የሚወለዱ ህፃናት የአገራቸውን ሐይማኖት ባህል ቋንቋ እንዲያውቁ ከፍተኛ ጥረት በማድረጋቸው ሊመሰገኑና ሊኮሩ ይገባል።
ሆኖም አንዳንዶች የቤተክርስቲያን ትርጉም ያልገባቸው ከማን አንሼዎች የቤተክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖናዋን በመጣስ ለአገልግሎት ያመጡትን ካህናት እንድግል የቤት ሠራተኛ በመቁጠር ተገቢውን ክብር አጉድለው ሊያሰሯቸው ሲሞክሩ ይስተዋላል።
ይህንን ባለመገንዘብ ለካህናት አባቶች መቀደስን፣መባረክን፣ክርስትና ማንሳትን፣ማጥማቅን፣ብቻ የስራ ድርሻ አድርገው ሲሰጡ የቤተክርስቲያን አመራርና አስተዳደር ካህናት አባቶችን እንደማይመለከት ቆጥረው ከፍትሐ ነገሥት መጽሐፍ ገጽና አንቀጽ ሲጠቅሱ ቃለአዋዲውን ሳያነቡት ዘንግተውት ነው የቤተክርስቲያንን አመራርን ለካህናትና  ለሌላው ባለተራ ላለመስጠት የሚዋደቁት ብዬ ራሴን አላታልልም።  
1.     ሥልጣነ ክህነት የሌለው ሰው ከታቦት ቁልፍና ከታቦተ ህግ ጋር ግንኙነት የለውም። ታቦተ ህጉን ማንም ይይዘው ዘንድ አይገባም። ታቦተ ህግ የሚገኝበት ቤተ መቅደስ ቁልፍ ማለት ታቦተ ህግ ማለት ነው። ታቦተ ህግ ደግሞ ከሌሎች ንዋየ ቅድሳት ጋር መያዝ ያለበት በካህን እጅ ብቻ ሊሆን እንደሚገባ በቃለ ዓዋዲው ገጽ 30 አንቀጽ 25  በቁጥር 1 ላይ ተመልክቷል። ክህነት የሌለው ምዕመን ታቦተ ህጉን መያዝ እንደሚገባው አልተፈቀደም። ስለዚህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ደንብና መመሪያ መሰረት ታቦተ ህጉ አሁን ከያዘው ምዕመን እጅ ወጥቶ በካህን እጅ እንዲቀመጥ ይደረግ ብለናል።
2.    . የቤተክርስቲያኗ የመተዳደሪያ ደንብ ገጽ 3 ተራ ቁጥር 2 የመተዳደሪያ ደንብ ለውጥ በሚለው ሥር የሚከተለው ሃሳብ ሰፍሯል።ማኅበሩ እንዲፈርስ በሚደረግበት ጊዜ የሚገኘው ንብረት የቤተ ክርስቲያኑን መንፈስ የሚከተል የበጎ አድራጎት ዓላማ ላለው ማኅበር እንዲተላለፍ ይደረግይላል። ማርያም ቤተክርስቲያን ናት ወይስ ማህበር? በሚል ጠይቀናል። ስንፈልግ ቤተክርስቲያን ናት እንላለን ካልሆነም ማህበራችን ናት ደስ ያለን ቀን እናፈርሳታለን ነበር መልሱ። ታዲያ ማህበር ከሆነ የጽዋ ወይም የሰንበቴ ካልሆነም የአክስዮን እንጂ ቤተክርስቲያን አለን እያሉ ማጭበርበር ተገቢ ነው አንባብያን?  ከዚህ ጥዬ መውጣቴ እስካሁን ምን ትሰራ ነበር? ለምን ዘገየህ? ልባል እችላለሁ። መልሴ ቤተክርስቲያን መስሎኝ ሳላውቀው ደንባቸውን ሸሽገውኝ ነው። ደንባቸውን ባለፈው ህዳር ወር መግቢያ ላይ ሰው አሳይቶኝ ደንግጬ ባነንኩ ወገኖቼ። እውነቱ ይህ ነው። የማህበሩን ደንብ እዚህ ላይ ተጭነው ይመልከቱት። ገጽ 3 ላይ የማህበሩ ደንብ ማሻሻያ ጊዜ በሚለው ስር ተራ ቁጥር 2 ላይ ይመልከቱና ማርያም ማህበር እንጂ ቤተክርስቲያን ያለመሆንዋን አረጋግጡ። በአጭሩ ተጭበርብሬ ነው። እናንተ ከእኔ ተማሩ።
3.    ከቀኖና ቤተክርስቲያን አንጻር ሴት ልጅ ካህናት አባቶችን ለመምራት አትችልም። ትመራም ዘንድ አይፈቀድም። እንደፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ቆጥረውት አንዲት ሴት እንደ ኢትዮጵያዊ ካህን መቅደሱን ተቆጣጥራ፤ሊቀ ካህንና የደብር አስተዳዳሪ ሆና የምትመራው ቤተክርስቲያን በእውነት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ነው? አሁን የቤተመቅደሱ መሪ ሴት አይደለችም? ይህ ጉዳይ እንዲቀየር ካህናት ቢጠይቁ ታዲያ ስህተቱ ምንድነው?  ስለዚህ ወ/ሮዋ ከቤተክርስቲያን የበላይ አመራርነታቸው ተገቢ ነው? ሴት ቤተ እግዚአብሄርን ልትመራ ይገባል? በተለይ ከእኛ ቀደም አገልግሎታቸውን ትተው የሄዱት ካህን ይህን ጥያቄ በግልጽ ማቅረባቸው ይታወሳል። መልሱ ይህ ኢትዮጵያ አይደለም ተብለዋል። ታዲያ ከrስቲያን ህዝብ ሆይ ይህ የቤተክርስቲያናችንን ቀኖና አያፈርስም? ይህ ልክ ነው ጸሓፈው?
4.    ህዝበ ክርስቲያኑ በተለያየ የሥራና የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ላይ እንዲሳተፍ በሩ ክፍት ይሁን። ቤተ ክርስቲያን የህዝብ በምትደረግበት ጊዜ ታድጋለች፤ ትሰፋለች፤ ወደሚቀጥለው ትውልድ ለመሸጋገር አያዳግታትም። ይህ ካልሆነ ግን ከፍተኛ የተሳትፎ ድርሻውን የያዘ ግለሰብ ወይም ቡድን ሲያልፍ አገልግሎትዋና እንደ ቤተክርስቲያን መቀጠልዋ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። ስለዚህ ቤተክርስቲያኗ እስከወዲያኛው ዘመን እንድትቀጥል  ለህብረተሰቡ የአመራር ተሳትፎ እንዲኖረው አድርጉ አላልኳችሁም? በንግግር ሳይሆን በተግባር እንቢ ማህበራችን ውስጥ ማንም አይገባም አላላችሁም?
5.    የማህበሩ ደንብ የቤተ ክርስቲያኑ የሥራ አስኪያጅ አካል ለአንድ ዓመት የሚመረጡ አምስት አባሎችና ሁለት ተለዋጮች ይኖሩታል ይላል። እነሆ እነርሱ ሰባት ዓመታቸው አልፏል። ሥልጣን ልቀቁ። ለተረኛ አስረክቡ። ወጣቱ ትውልድ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ ያገልግል። በሩን ልቀቁት ነው ያልኩት።
 ይህንና ይህን የመሳሰሉትን በርካታ መስተካከል የሚገባቸውን ቁልፍ ነገሮች በዝርዝር ጽፌ ማሻሻያ እንዲያደርጉበት አቅርቤላቸዋለሁ። ባለፈው አገልግሎቱን አቋርጦ የሄደው ሌላው ካህን እባካችሁ ቤተክርስቲያንን አትዳፈሩ ብለዋቸው መክረዋቸው ነበር። አርፈው ይቀድሱ እንቢ ካሉ በረንዳ ይወድቃሉ የሚል መልስ ተሰጧቸው በመጨረሻም እንዴት እንዳደረጉዋቸውና እንዴት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ የስቶክሆልም ህዝብ ያውቀዋልና ይቅር።
እኔን እንደቀደሙት ካህን ወደ ሀገር ቤት ችለው የሚያስባርሩኝ ባለመሆኔ የተያዘው መንገድ በስድብ ስሜን ማጥፋት ነው ተብሎ በብዕር ስም እየተሰደብኩ ነው። ቆሞስ አባ ኒቆዲሞአ ላይ ደግሞ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ የተደረገው ሙከራ ሁሉ በእግዚአብሄር ኃይል ከሽፎባቸው ተበሳጭተው አሁን ወደ ተራ ስድብ አምርተዋል። እርሳቸው ምናልባት ወደፊት ስለራሳቸው የሚሉት ይኖራቸው ይሆናል።
                    
 ለአዲስ ቤተክርስቲያን ምሥረታ መነሻው ምክንያት ምንድነው?
የዚህ ቤተ ክርስቲያን መሥራቾች በዋናነት እኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ቀሲስ ፍሰሐ ስፋዬ እና ቆሞስ አባ ኒቆዲሞስ አስፋው ከሌሎች ሦስት ዲያቆናት ጋር ሆነን ነው። ሌሎች የዚህ ቤተክርስቲያን መስራቾችም ቀደም ሲል እኛ ስናገለግል በነበረበት በአንድ የግል ቤተክርስቲያን ውስጥ ተገልጋይ የነበሩ ምዕመናንና ሌሎች የኢ////ክርስቲያም አባላት ናቸው።
በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በግል ሀብታቸውና ገንዘባቸው እንዲሁም በፈቃዳቸው ቤተክርስቲያን አሠርተው ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስቻሉ አሁን በሕይወት ያሉም ሆነ ያለፉ በርካታ የእምነታችን አባላት እንዳሉና እንደነበሩ ይታወቃል።  
እነርሱም ቤተክርስቲያን አቋቁመው ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለገልበት አስረክበዋል። ህዝበ ክርስቲያኑም ቤተክርስቲያኑን በብጿአን አባቶች ወይም በቆሞሳት አስባርኮ፤ ካህናትን ቀጥሮ ቤተክርስቲያኑ የጋራ ንብረታችን ነው ብሎ አምኖ ማስገልገልና ማገልገል ይጀምራል።
ካለፉት አባቶቻችን ታሪክ የምንማረው ግለሰብም ሆነ አንድ ቡድን ቤተክርስቲያን የሚያሳንጸውና አገልግሎቱ እንዲቀጥል የአቅሙን ያህል የሚያደርገው/ እናንተም እንደምታደርጉት ማለት ነው/፤የእግዚአብሔር ክብር መገለጫና አምላካዊ ፀጋና በረከት ማግኛ፤ እንዲሁም የሰማያዊውን ሕይወት በማሰብ እንጂ የገንዘብ ገቢ ማግኛ ወይም የግላዊ ክብር መግለጫ ሥፍራ በመፈለግ አይደለም።
ይሁን እንጂ ቅሉ በማንኛውም መንገድ ቤተክርስቲያን ቢመሠረትና በአበው ህግ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሠረት የሚመራ ቢሆን አይጠላም ነበር። በስዊድን በአገልግሎት የቆየንበት እንዲሁም በአንዳንድ በአውሮፓና በአሜሪካ ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አመሠራረት ከላይ በጠቀስነው ተቃራኒ በሆነ መልኩ ከአንድ የግል ካምፓኒ ወይም አክስዮን ማህበር ጋር ተመሳሳይነት ባለው ህግ የተመሠረቱና የሚመሩ ናቸው።
ሥልጣነ ክህነት የሌለው ምዕመን ታቦተ ህጉን እንደግል ንብረት በማሰብ እንደ ቄሰ ገበዝ ራሱን ቆጥሮ ታቦተ ህጉንም ሆነ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ይቆልፍበታል። ከግል ንብረት ምንም ልዩነት በሌለው መልኩ በርካታ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ወጣ ያሉ ድርጊቶች ይፈጸማሉ። በካህናት አባቶች እጅ ክብሩ ሳይጓደል ታቦተ ሕጉ የሚቀመጥበትን መንገድ ለማመቻቸት ብዙ ሞክረናል፤አስተምረናል፤ መክረናል፤ደክመናል።
የደከምነው ድካም ዉጤት ሊያመጣ ባለማቻሉ በጣም ብናዝንም የህዝብ ንብረት ባልሆነና በቀኖና ቤተክርስቲያን መሠረት ባልተመሠረተ የግል ተቋም ላይ ማዘኑ ተገቢ አለመሆኑን አመንን። አቤቱታ ሊቀርብ የሚችልበት መንፈሳዊም ሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር የለም።  የመተዳደሪያ ደንቡም ይህንኑ  የግለሰቦችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ነው።
ማህበረ ምዕመናኑ ኢትዮጵያዊ ነው። እምነታችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው።ካህናት፤ ንዋየ ቅድሳት እንዲሁም የአገልግሎቱን ሥርዓት ከኢትዮጵያ አምጥተን ቤተክርስቲያን አቋቁመን ስናበqa የቋቋምነውን ቤ/ክርስቲያን በስደት በምንኖርበት አገር ቤተክርስቲያን ደንብ እንመራዋለን ካልን እንቸገራለን።
ሴቶች እናቶቻችን በርካታ ቅድስና ያላቸውን ሥራዎች ማከናወናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት ያከበርነውን የጌታችንን ትንሳኤ ቀድመው በማየት ያበሰሩት ሴቶች ናቸው። የአይሁድን ልቅሶ ዋይታ ሐዘን ወደ ደስታ የለወጠችው አስቴር እናታችን ሴት ናት።መጽ፣አስቴ፥ 4 3 ጀምሮ ያለ ታሪክ ነው።
በሰለጠነው የምዕራባዊያን ዓለም ሴቶች ቤተክርስቲያን ይመራሉ፤ ክህነት ይቀበላሉ፤ ክህነት ይሰጣሉ፤ ሊቀ ካህን ይሆናሉ። ይህንን ህግ ተቀብለን በኢ/////ያን ተግባራዊ እናድርግ ብንል እንቸገራለን። ክህነት ለሴቶች እህቶቻችን አይሰጥም። ሊቀካህን ሆነው ቤተክርስቲያን ሊመሩ አይችሉም። ይህ ህግ አባቶቻችን ያስቀመጡት ነው። ዛሬ እንለውጥህ ብንለው ከድፍረት ውጭ ሊሆን አይችልም። የኢ/////ያን የምትመራው አባቶቻችን ባኖሩልን የቤተክርስቲያናችን ህግ መሠረት ብቻ መሆኑን ለአፍታም ልንዘነጋው አይገባም። 
ለወደፊት ለእኛም አገልግሎት ሆነ ለተገልጋዩ ምዕመናን ቀጣይ የአምልኮ ዘመን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ፤ የአባቶችንም ሆነ የአገልጋይ ካህናትንና የተገልጋይ ምዕመናንን መብት ሊጠብቅና ሊያስጠብቅ፤ ሊያከብርና ሊያስከብር የሚችል፤ ንብረትነቱና ባለቤትነቱ በስዊድን ስቶክሆልም የሚኖር የመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ህዝበ ክርስቲያን ሀብት የሆነ፤ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ያላፈነገጠና በብፁዓን አባቶች የሚመራ፤ ግለሰብ እንዳሻው የማይመራው፤ ለቤተክርስቲያን የሥልጣነ ክህነት የማዕረግ ልዩነት ክብርና ትኩረት የሚሰጥ ቤተክርስቲያን መመሥረትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሳይበረዝ ለትውልድ የማስተላለፍ ሃዋሪያዊና ታሪካዊ የሆነ አደራ እንዳለብን በማመን ለተግባራዊነቱ ተነሳን። እነርሱም ለህገ ቤተክርስቲያን አንገዛም አሉን። ምን ማድረግ እንዳለብን ወስነን ተለየናቸው።
ታዲያ ቤተክርስቲያን አስፈቅደን ከፍተን ለህዝብ ከማገልገል ወዲያ ካህንና መነኩሴ በስደት ዓለም ምን እንዲሰሩ እንቬስተሮቹ እንደሚፈልጉ አልገባንምና ጠይቁልን። ታዲያ አባቶች መነኮሳት ቤተክርስቲያንን መስርተው በስደት ያለውን ምዕመን ካላገለገሉ ቆብና ቀሚሳቸውን ጥለው ምን እንዲሰሩ እንድሚፈልጉ አልገባኝ።
                              
                              ይህን እስቲ ማን ይጠየቅ፟?
  አንባብያን በስቶክሆልም ስዊድን የቅ/ሥላሴ ቤ/ክርስቲያንና የማርያም ማህበር ሲመሰረቱ በቂ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል አገልጋይ ካህን ቀርቶ ለሁለት አንድ እንኳን ካህን አልነበራቸውም። ይህንን እኔም አውቃለሁ። እኔ ስመጣ ሁለቱም ካህን አልነበራቸውም። ተመልከቱ! ካህን ያልተረከበው ታቦት፤ ካህን የሌለው ማዕጠንት፤ ካህን የሌለው ቤተክርስቲያን ተመሰረተ። ማን ከማን ያንሳል የሚል የእልህ ቤተክርስቲያን መሆናቸው ነው። ከሥላሴ ምሥረታ በኋላ ሌላ ቤተክርስቲያን መመስረት ሳያስፈልግ በጋራ መስራት የማይቻል አልነበረም። ሥላሴ በቶሎ ወደ ሥርዓተ ቤ/ክርስቲያን ሲመለስ ሌላው በማህበርነት ቀጠለ።   
ለምን ቤተክርስቲያን መሰረታችሁ? ያላቸው የለም። ብፁዕ አባታችንም የዚያኔ ቡድንተኞቹ ከመድሐኔዓለም ሲለዩ መለየታቸው ተገቢ እንዳይደለ አስተምረው መክረው ደክመው ስላልሰሟቸው ተዉአቸው። አሁን አንዱ በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ይተዳደራል። አንዱ ደግሞ የቤተክርስቲያኑ ባለቤት በሆነ ግለሰብ ይተዳደራል።
እነርሱ ጥቂት ምዕመናን ተሰባስበው በግላቸው ያለ ሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ ቤተክርስቲያን ሲከፍቱ ትክክል ነን ብለው ካመኑ ታዲያ ዛሬ ካህናት በህብረት ሆነው በህግ ሊቃጳጳሱን አስፈቅደው አዲስ ቤተክርስቲያን ሲያቋቁሙ ምነው ተበሳጩ? ምነው በካህናቱ ላይ ተራ የስድብ ናዳ አወረዱ? ብፁዕነታቸው ምን አድርገው ነው ይህ ወቀሳና ማስፈራሪያ የሚሰነዘርባቸው? እውነት አሁን የእምነታቸው ጉዳይ አሳስቧቸው ነው እኚህ ጸሓፊ? አይደለም።
እኔ ራሴ አቡነ ኤልያስ ስር ሆነን በውጭው ሲኖዶስ ውስጥ እንታቀፍ ብዬ ጥያቄ አቅርቤ የቤተክርስቲያንዋ ባለቤት አቡነ ኤልያስ ቤተክርስቲያኔ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለመሳለም ሊመጡ ይችሉ ይሆናል እንጂ በሌላ ሁኒታማ አይሆንም ብለውኝ አልነበረም እንዴ ትናንት? ምነው ዛሬ ቤተክርስቲያን አስከፈቱብን የሚል ጫጫታ መጣ? የስዊድን ሀገር አብያተ ክርስቲያናት የተመሠረቱት በሁለት መንገድ ነው። የመጀመሪያውና አንጋፋው የመድሃኔዓለም መንበረ ጵጵስና በአንድ የተከበሩ ታላቅ መንፈሳዊ አባት የበላይነት የሚመራ ሲሆን ንብረትነቱና ሀብትነቱም  በስዊድን ሀገር የሚገኝ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው።
ሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የተመሠረቱት የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ከመድሃኔዓለም / ክርስቲያን ተገንጥለው የወጡ ጥቂት ግለሰቦች የመሰረቷቸው ናቸው። ከሁለቱ አንዱ በሀገርቤቱ ሲኖዶስ የሚመራ ሲሆን ሌላኛዋ አንዷ ደግሞ የግል ንብረት ብጤ በመሆንዋ የምትመራው ባለቤትዋ በሆነ ግለሰብ ነው።
የገረመኝ ነገር  ቤተክርስቲያን መክፈት ትተን ካህናቱ ጣሪያው ላይ ያስቀመጥነውን መስቀል አውርደን ጨረቃ ወይም ኮከብ ማድረግ ነበረብን?እንዲህ ቢሆን ምን ያህላችን እንቆረቆር ነበር? እውነት አሁን ጸሓፊው ለእምነታቸው ተቆርቁረው ነው? ከተቆረቆሩ እስቲ አሉ ከሚሏቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸመውንና ካህናት ተቃውመዉት ለማስተካከል ጉልበት ያጡበትን ተመልከትና ለዚያ መስተካከል ብትታገል ያምርብሃል እላለሁ። ግን ጸሐፊው አድራጊው ሆንክ እንጂ።
ሊቀጳጳስ ቤተክርስቲያን እንዲመሰረት ተገቢ ነው ብሎ መፍቀድ ወይም ያለመፍቀድ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ነው። ጸሓፊው ካህናቱን መዝለፋቸው አያስገርምም። እርሳቸው ቤተክርስቲያኔ  እያሉ የሚያጭበረብሩ ናቸውና ስራቸውን የሚጋራና ገቢያቸውን የሚቀንስ የመጣ እየመሰላቸው እየደንገጡ ስለሆነ ስድባቸው አይገርመኝም። የገረመኝ ከደረጃቸው በላይ ሊቀጳጳሱን ቤተክርስቲያን ለምን እንዲከፈት ፈቀድክ የሚል ድፍረታቸውና ማስፈራሪያቸው ነው።
እነርሱ ቤተክርስቲያን የዛሬ ሰባት ዓመት የከፈቱት ማንን አስፈቅደውና ማንን የቤተክርስቲያን ስያሜ አስመርጠው ነው? ራሳቸው አይደሉም እንዴ  የሰየሙት? ታዲያ እነርሱ ሲሰሩ ልክ የነበረው ምነው ዛሬ ሌላው የተሻለ ሲሰራው መንጫጫታቸውሊቀጳጳስ ሳያስፈቅዱ ቤተክርስቲያን መክፈታቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ እነርሱ ራሳቸው ፍቃድ ለሌላው መስጠት ወይም መንሳት መከጀላቸው ያሳዝናል። እናንተ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሳያግዳችሁ የግል ቤተክርስቲያን ስትከፍቱ ልክ ነበራችሁ ዛሬ ካህናት ብፁዕ አባታችንን አስፈቅደው አዲስ ቤተክርስቲያን መክፈታቸው ምነው አበሳጫችሁ? ሀገሩ ስዊድን ነው የሚገዛውም ወያኔ አይደለም። ይህንን አትርሱ።
ያንን ጽሑፍ የጻፉት ወይም ያስጻፉት ግለሰብ፤ ምናልባት በስቶክሆልም ስዊድን ማርያም የምትባል የግል ቤተክርስቲያን አለችን የሚሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ወይም ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ አንዱ ይሆናሉ ብዬ እገምታለሁ። አሊያም ጓደኞቻቸው ከሆኑት የሌላኛው ደብር ጥቂት አመራሮች መካከል ሊሆን እንደሚችል ከቀረበው ጽሑፍ መገመት ይቻላል።
የለመታደል ሆኖ ዞሮ ዞሮ ትግሉ ማንነቱን ከደበቀ፤ የኢትዮጵያዊያን መሰባሰብ የሚያበሳጨው፤ ሁሉን ነገር እኔ ካልተቆጣጠርኩት ከሚለው፤ ሆን ብሎ ዓይኑን ካንሸዋረረ ወያኔ አይደለሁም ገለልተኛ ነኝ ከሚል ጋር መሆኑ ያሳዝናል። ኢትዮጵያዊያንን ሊያሰባስብ ይችላል ይህ አዲሱ ቤተክርስቲያንና ብፁዕ አባታችንን አትተባበሯቸው እንበላቸው እናስፈራራቸው ብለውት አረፉት።አቡነ ኤልያስ አይፈሩም። ማህበር ፈርሶ ቤተክርስቲያን ሲመሰረት ይደሰታሉ እንጂ ጸሐፊው ምን አስፈራቸው ብለህ ነው?
እና ደግሞ ለጸሓፊው የምለው ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ ዘስቶክሆልም ወያኔ ካባውን እየቀያየረ በፈለገው አቅጣጫ ቢመጣ ያውቁታልና እረፍ እልሃለሁ። እውነተኛ ከሆንክ ራስህን ኧገሌ ነኝ ብለህ እንድ እኔ በግልጽ ቅረብና በግንባር ከኢትዮጵያዊው አባት እግር ሥር ወድቀህ ንስሓ ግባ እልሃለሁ።ውሾቹ ቢጮሁም ግመሉ በፍጥነት ከማጓዝ አይገታምና በከንቱ አትድከሙ። መስላችሁ ከመኖር ሁኑና ኑሩ። ክርስትና በመሆን የሚኖርበት ህይወት እንጂ በመምሰል የሚኖርበት አይደለም።
                 ቀጥታ ምላሾች
ጸሓፊው ለብፁዕ አቡነ ኤልያስ በሰጡት ማሳሰቢያ የተለያዩ ሃሳቦችዎን ሰንዝረዋል።
1.      በገጽ 2 ቁጥር 3 ላይ አዲስ የተመሰረተው ቤተክርስቲያን ወደፊት ይወርዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም በእጅጉ ጎጂ መሆኑን በማስረዳት ራሳቸውን እንዲያገሉ ጠይቀዋል።
         በመሠረቱ የዚህ ጽንሰ ሃሳብ የሥጋት መነሻ መንደር የት አካባቢ እንደሆነ በግሌ አውቀዋለሁ።ነገር ግን ብፁዕ አቡነ ኤልያስም ይሁኑ የሌሎች ወንድሞቻቸው የሆኑት ብፁዓን አባቶች አቋም ጸሓፊው እንደቀባጠሩት ሳይሆን ወጥ በሆነ ብሄራዊ እርቀ ሰላም ወርዶ በማንኛውም ሁኔታ ከሀገራቸው ተሰደው የወጡ ኢትዮጵያውያን ፍጹም ሰላምና ምህረት ተደርጎ ወደ ሀገራቸው መውጣትና መግባት ሲችሉ፤ የተጣሰው ቀኖና ቤተክርስትያን ሲስተካከል እንጂ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በቤተክርስቲያን ስም ሲነግድ ደርሰውበት ትክክለኛን ፍትሃዊ የሆነ እርምጃ በመውሰዳቸው ምክንያት እርቀ ሰላሙ ይስተጓጎላል ብለህ አትስጋ።
እዚህ በሚደረገው የቤተክርስቲያን ምስረታ ላይ ሲሆን ይቃወሙ ካልቻሉም ግን እንዳይተባበሩ የጠቅኽው፤ ጸሓፊ ሆይ! ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በዋልድባው ገዳም የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ላይ እንደ ብፁዕ አቡነ ኤልሳ ገዳም ፈርሶ በምትኩ የስኳር ፋብሪካ እንዲመሰረት እንዲተባበሩ ነው የምትፈልገው ወይስ በገዳማቱ ቃጠሎና ዘረፋ?
ይልቅ ባለፈው ሰሞን በተደረገው የአባቶች የእርቅ ድርድር ላይ አዲስ ቤተክርስቲያን እንዲቋቋም ለምን ፈቀዱ ያልካቸውና የወቀስካቸው ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ ከወያኔ ተልከው ለመጡት አባቶች እነርሱ የሚኖሩትን የተንደላቀቀ ኑሮና የሚጠቀሙበትንና የሚገዛላቸውን የመኪና ዓይነት ጠቅሰው ከምንኩስና ህይወት ጋር አዛምደው ምድራዊ ድሎት ሰማያዊውን ስራቸውን ምን ያህል እንደጎዳው ጭምር አስተምረዋቸው መላካቸውን እኔ ልንገርዎት። እርስዎ ይህ እውነት መሆኑን ከሀገር ቤት አባቶችዎ ጠይቀው ይረዱ። ምናልባት ገለልተኛ ነኝ የሚለው ጨዋታ የተበላ እቁብ ነውና ይተዉት የሚታለል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል እውነቱን።
2.    ጸሃፊው ለአንድ ከተማ አንድ ዓይነት ታቦት በቂ ነው ወደሚል ድምዳሜ ደርሰው ተጨማሪ ተመሳሳይ ታቦት አያስፈልግም በሚል ብፁዕነታቸውን ኮንነዋል።  ይህ ውሳኔ በመሠረቱ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተፈጸመ ሳይሆን በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ገብተው እውነተኛ የማርያም ቤተክርስትያን መስሏቸው ሲወናበዱ የነበሩ የካህናትና የማህበረ ምዕመናኑ የጋራ ውሳኔ ነው።
3.    ጸሓፊው አያይዘው በአንድ ፌርማታ ርቀት አዲሱ ቤተክርስቲያን እንደተመሰረተ ጽፈዋል።  ብፁዕ አቡነ ኤልያስን ለመኮነን ካልሆነና ከስዊድን ውጭ የሚኖርን ሕዝብ ለማታለል ካልሆነ በቀር ከሱንድቢይበሪ እስከ ሶለንቱና ድረስ ያለው ርቀት እውነት አንድ ፌርማታ ነው? በማንኛውም ዓለም ያላችሁ አንባብያን ጎግል ማፕ ውስጥ ገብታችሁ ስቶክሆልም ከተማ ከሱንድቢይበሪ እስከ ሶሌንቱና ከእግር ጉዞ ባሻገር ያለውን የፌርማታ ብዛት ተመልከቱ። ነጭ ዉሸት ነው። እውነቱን ግን እኔ ልዘርዝረው/Sundbyberg, kalbery, Solna, Ulriksdal, Hellenelund, Sollentuna / የሚባሉ ፌርማታዎች አሉ። ቤተክርስቲያን መፍቀዱ ችግር ይፈጥራል ያሉት ችግር ለመፍጠር ሞካሪው እርስዎና መሰሎችዎ ናችሁ እንጂ ሌላ ችግር የለም።
4.    ጸሓፊው ሆይ! የብፁዕነታቸውን የቀኖና አርበኝነት ተርከውልናል። አልተሳሳቱም ልክ ነዎት። ብፁዕነታቸው ሰባት ዓመት ሙሉ የታገሉለት ቀኖና ቤተክርስቲያን ዛሬ ትግላቸው ፍሬ አፍርቶ ጸሎታቸው ሰምሮ የግል ድርጅቱ ፈርሶ በምትኩ እውነታኛይቱ በስቶክሆልም ሶሌንቱና የደብረ ቅዱሳን ምክሓ ስዱዳን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለመመስረት በቅታለች።
                      
             ይህንን ጽሑፍ የምታነቡ ካህናት አባቶች ሆይ!

ጸሓፊ ሆይ! ለካህናት አባቶችም ጭምር ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እዚህ ላይ በከንቱ ደክመዋል። ምናልባት እንደግል ድርጅትዎ አሠራር በቧገታ ወይም በሸመታ ካህናት ከለንደንና ከአንዳንድ ሀገሮች ነጋዴና አትራፊ ካህናት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለማስገልገል ታስቦ የተቋቋመች ሳትሆን በሙሉ ሰሞነኛ ብቃት ባለው አደረጃጀት በሰፊ የማህበረ ምዕመናን ተሳትፎ አገልግሎት እንድትሰጥ ሆና የተመሰረተች ቤተክርስቲያን መሆኗን ሊያውቁ ይገባል።

ጸሓፊ ሆይ! እንደእርስዎ ቅስቀሳ ካህናት አባቶችን ከእኛ ከወንድሞቻቸው እንዲርቁ ለማድረግም ሞክረዋል። በካህናት ወንድሞቻችን አዕምሮ የሚመላለሰው እውነታ ግን ከዚህ የተለየ መሆኑን ልግገርዎት። በአሁነ ሰዓት በውጭው ዓለም በስደት የሚገኙ አብዛኛዎቹ አባቶች በእርስዎና በእርስዎ መሰል ቤተክርስቲያን ብጤ የግል ማህበር ውስጥ እውነኛይቱን ቤተክርስቲያንን እያገለገሉ ያሉ መስሏቸው ወይም አማራጭ አጥተው የእለት ኑሯቸውን ለመግፋት ሲሉ የእጅ አዙር ሎሌነት ውስጥ ገብተው መከራ በሚያዩበት የውጪው ዓለም የእኛ ቤትክርስቲያን መመስረት ለአባቶች ካህናት ታላቅ ይድል ብስራት ሆኖ የሚያስደስታቸው እንጂ ከእኛ የሚያሸሻቸው ስራ ያልሰራን በመሆኑ ሊኮሩ ይገባል ብለን እናምናለን። እውነታውም ይህ ነው።

            በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አማኞች በሙሉ
በተለይ ስቶክሆልም!
የተጻፈው ነገር ሁሉ ውሸት ነው። ካህናትን እናንት ምንም አትናገሩ። ቀኖና ዶግማ ምናምን አትበሉ። ብቻ ቀድሱልን ነው የተባልነው። እኛ እንመራችኋለንብቻ ቀድሱ እናንተ። የሚመራው ቤተክርስቲያን ነው። የሚመራው ምዕመን ድቁና እንኳን የሌለው ነው። ተው እኛ እንምራው ቃለዓዋዲው ለእኛ ይፈቅዳል መምራቱን አልን እንቢ አሉን።ታዲያ ይቅር ሞክሩት ብለን ወጣን ሌላ ምን እናድርግ? እግዚአብሔር ያሳያችሁ! የግል ድርጅት ማለትየግል ቤት ነው።
ጸሓፊ ሆይ! “ይሉሽን ባልሰማስ ገበያም ባልወጣሽ” እንዲሉ በስቶክሆልም ከተማ ውስጥ በሚቋቋሙ ማህበራዊም ሆነ ሐይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ እየገባ ህዝቡን ሲያበጣብጥ የኖረ ማን መሆኑን እርስዎም ያውቃሉ የስቶክሆልም ህዝብ ያውቀዋል። የቤተክርስቲያን ማሊያ ለብሰን አክስዮን የምናጫውት ጥቅም ፈላጊዎች ።  አንሆንም ግድ የሎትም
እኛ የመሠረትነው ቤተክርስቲያን  ለወደፊት  ለእኛም አገልግሎት ሆነ ለተገልጋዩ ምዕመናን ቀጣይ የአምልኮ ዘመን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ፤ የአባቶችንም ሆነ የአገልጋይ ካህናትንና የተገልጋይ ምዕመናንን መብት ሊጠብቅና ሊያስጠብቅ፤ ሊያከብርና ሊያስከብር የሚችል፤ ንብረትነቱና ባለቤትነቱ በስዊድን ስቶክሆልም የሚኖር የመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ህዝበ ክርስቲያን ሀብት የሆነ፤ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ያላፈነገጠና በብፁዓን አባቶች የሚመራ፤ ግለሰብ እንዳሻው የማይመራው፤ ለቤተክርስቲያን የሥልጣነ ክህነት የማዕረግ ልዩነት ክብርና ትኩረት የሚሰጥ ቤተክርስቲያን መመሥረትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሳይበረዝ ለትውልድ የማስተላለፍ ሃዋሪያዊና ታሪካዊ የሆነ አደራ መወጣታችንን እወቁልን።

                      መልዕክት
አንዳንድ ካህናት በሚኖሩበት አገር ያሉትን ስደተኞች በማጽናናትና በማስተማር ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።ልጆቻቸውን ቃለ እግዚአብሄር ይመግባሉ። ቀኖና ቤተክርስቲያንን ያስተምራሉ ህይወታቸውን ይለውጣሉ። አንዳንዶች ካህናት ደግሞ በተቃራኒው ሲሰሩ ማየት የተለመደ ነው። የሚከተለውን ስናገር ውስጤ ከፍተኛ ሓዘን ይሰማዋል።
አንድ ካህን ምንም አስገዳጅ የሆነ ሁኔታ ሳይኖር፤ ጦርነት በሌለበትና ሰላም ባለበት አገር ምዕመን ከሊቀጳጳስ ጋር በመጣላቱ ብቻ ምዕመኑን ለማስደሰት በሚል ካህን ቀርቶ ዲያቆን በሌለበት ሥፍራ ታቦትን የመሰለ ክቡር ነገር አጓጉዞ አምጥቶ ለምዕመን በእጅ መስጠት ተገቢ ነው ወገኖቼ? ይህንን እያደረገ ያለ ካህን ምን እየሥራ ነው ይባላል? እምነቱን እያስፋፋ ነው ወይስ ሰው እያስደሰተ? ታቦቱን ማምጣቱ ስህተት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ታቦት ካህን በደብሩ ከሌለ ካህን ወዳለበት ደብር ተወስድ ይዳበላል እንጂ ምን አድርግ ተብሎ ነው ለምዕመን በእጁ የሚሰጠው? በእጁ ይዞ የለመደ ምዕመን ሥልጣነ ክህነት እንዳለው ካህን ራሱን ቆጥሮ እኔስ ምን ሆኛለሁ ማለት ጀምሮ ሲያበቃ ማላቀቅ ችግር ሆነ። ኧረ እባካችሁ የአባቶችን ሥርዓት እናስጠብቅ።
ምዕመናንም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ በሥር ዓተ ቤተክርስቲያን ላይ በድፍረት በሚያላግጡት ላይ ጫና በማሳረፍ በማውገዝ ወደ ትክክለኛ ህጋዊ አቅጣጫ ለመመለስ በጋራ መትጋት አለብን።
እንግዲህ አበቃሁ። የጸሐፊዬን ማንነት ካወቅሁ ወይም እኔ ነኝ ሲል ብቅ ብሎ ራሱን ካስተዋወቀ ከተጨማሪ መረጃ ጋር እመለሳለሁ። በነገራችን ላይ ይህ በክፋትና በምቀኝነት በመነሳሳት በስም ማጥፋት ዘመቻ የዳከረ ጸሓፊ ራሴን በአግባቡ እንድገልጽ፤ ስለቤተክርስቲያኑ አመሰራረትና የነበረውን ቅድመ ሁኔታ እንዳሳውቅ ስለረዳኝ ምስጋና ለማቅረብ ባልፈቅድም ፈጣሪ ሆይ”ጸላዕትየ እኩየ ይቤሉ ላዕሌየ፡ ማእዜ ይመውት ወይሰዐር ስሙ” ቢሉኝም እኔ  ጠላቴን ከፊቴ አጥፋ የማይወዱኝን ሁሉ አርቅ ብዬ አንጸልይበትም።፡ቸር ያክርመን።

    


    
                                                                                                    

19 comments:

Anonymous said...

Kesis Endemin Alu? betsam Melkam yehone Mels new zemenu kifu new-yefetena zemen new-Andand Alawaki yehonu kirstyan mesayoch bebete kirstiyan lay seltsinew kekahinu belay -kepapasu belay honew metayet yifelgalu beki yehone melsina timihirit newna Yibertu Egizabher yirdawot
Beteley Ke Mahibere Kidusan Gar Mesratot melkam new Mahobere Kidusan le sirate bete kirsitiyan yiredal ahunim Mahiberu kegoniwot yikomalna yibertu

Anonymous said...

ኤውነት የሚናገር የጠፋበት ዘመን። ቀሲስ ምርት እና ገለባው ሲልይ እርሶ እንደሚሉት ምንም ጥፋት ያላጠፉ ጻድቅ፤ የሰሩት ሁሉ ሰማያዊ.... እረ እናስተውል። በድብዳቤ ድሪቶ የሰውን መግዛት ይቻል ይሆናል የመድኃንያለምንስ?

Unknown said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አህዱ አምላከ አሜን
በተሰጠው መልስ በጣም ተደስቻለሁ ከአንድ የሃይማኖት አባት የሚጠበቅ አባታዊ ምላሽ ሆኖ አግኝቸዋልሁ እንደነሱ ወርደው ተራ ስድብ ባለመጻፈወ ኮርቸብዎታለሁ ቀሲስ ይህ የለውጥ መንፍስም በሌሎች አብያተ ክርስትያናት በቅርብ ቀናት እንደምናይ ተስፋ አደርጋለሁ እንደዚህ የሃሰት ወሬ በመንዛት ቤተክርስትያንን ለሚያምሱ ሃሳበ ድውያን እግዚአብሔር ልቦናውን ይስጣቸው እላለሁ ሰላምና አንድነት ለቤተክርስቲያናችን አሜን

Unknown said...

Endenezih Yalu kehanat binoru betkrstiyanachin ahun kalechibet chigr balgebach neber tadiya min yadergal hulum lehodu eyadere techeger eko bertu elalehu kesis kegonwet nen egziabher sirawotn yibark amen

Geta hoy temesgen said...

Betam des yilal tsihufu! Anbesa yehonu kahnat nachew. Enersu yebelay honew kahnatun ketach adrigew sirate bietekrstiyanacn lay yichawetalu! Egziabhier yifredbachew! Min aynet yeteregeme sew new endew yexafebachew!
Esti weta bileh ene negn yexafkubachew belenina yeqerewun negerhin yingerun ebakih?

KeStockholm said...

ለቀሲስ ፍሰሐ -
"ታዲያ ዛሬ ካህናት በህብረት ሆነው በህግ ሊቃጳጳሱን አስፈቅደው አዲስ ቤተክርስቲያን ሲያቋቁሙ ምነው ተበሳጩ?" ብለው ለጻፉት ---

አቡነ ኤሊያስ እኮ የእናንተን ቤተክርስቲያን አልባረኩም። የዚያን እለት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ነበሩ። ለምን በእርሳቸው ስም ለመጠቀም ይሞክራሉ? ቢስማሙ ኖሮማ መጥተው ይባርኩላችሁ ነበር። እርሳቸው እንደሚገኙ አስመስላችሁ የጻፋችሁትም የሐሰት ኤስ.ኤም.ኤስ (SMS) ሊያሳፍራችሁ ይገባል። ለምን በእኒህ አረጋዊ አባት ስም ይነገዳል? ስለዚህ እናንተም "የከፈታችሁት" ሌላ ገለልተኛ "ቤተክርስቲያን" ነው! "አልሸሹም ዞር አሉ!"

Anonymous said...

Selam Kesis
Excellent response

Ke Mahibere Kidusan Gar Mesratot melkam new Mahobere Kidusan le sirate bete kirsitiyan yiredal ahunim Mahiberu kegoniwot yikomalna yibertu.

May God bless u and ur family

Anonymous said...

ለዚህ አስተያየት ሰጭ:-
Anonymous said...

ቀን:- May 5, 2012 8:41 PM
”Mahiberu kegoniwot yikomalna yibertu”

እባክዎ እንዲህ ብለው የጻፉ ሰው እግዚአብሔርን ይፍሩ። ማኅበረ ቅዱሳን ስለራሱ የሚናገርባቸው የራሱ የመገናኛ ብዙኀን አገልግሎቶች አሉት። በተጻፈው ጽሑፍ ውስጥ ምንም እርስዎ ከጻፉት አስተያየት ጋር የሚገናኝ ነገር እንደሌለ እያወቁ ለምን እንዲህ ብለው በማኅበሩ ስም እንደጻፉ አላውቅም። ስለዚህ እባክዎ ራስዎን ብቻ ወክለው ይጻፉ።

Kinfe Michael said...

Kesis Fisseha, that is a nicely detailed explanation. The same thing is also happening here in the United States as well. Many "Churches" which are practically under the absolute command of a "board" are notoriously resistant to follow the "Kal-awadi." Because of this, it is not uncommon to witness the establishment of new Churches departing from "board" adminstrations. From your explanation, I agree that your decision was correct and in good terms with the rules and regulations of our Church. You have done what is right and shouldn't bother about rumors. God be with us.

Unknown said...

To be honest, i am really delighted to read this article. It was posted at ethiopiazare.com and i read it there... I was the one whom i quarrel with somebody in comments in the previous article posted here in dejeselam...
I am against all the church in Sweden...since they are out of Kale awadi. Kesis! Let me tell you the truth! Silassie church is also under the name of the "association" and it is not under the umbrella of Mother Church! Only calling Ababa Pawlose's name, will by no means bring the church to the system. The same "ownership" problem is also occurred in Silassie church! Some people still consider themselves as "owners" .. Knowingly or unknowingly! May God forgive me if i misscouted any body in Christ! But the truth is this!

Anonymous said...

KeStockholm በከንቱ አትድከም ወንድሜ/እህቴ ኢትዮጵያውስጥ ያለውን ወደ 38 ሺህ ገደማ ቤተክርስቲያን ሁሉ ብጿአን አባቶች ራሳቸው በአካል እየተገኙ የባረኩ ይመስለሃል? አይደለም! እርሳቸው ፈቅደው የሚመለከተውን መባረክ የሚያስችል ሹመት ያለውን ቆሞስ ልከው ያስባርካሉ። የሆነው ይሄ ነው። እርሳቸው ቀድሞውንም በአካል እንደማይመጡ ይታወቃል፤ ውይይት ተደርጎ በብፁዕነታቸው መልካም ፈቃድ የተወከሉት ቆሞስ አባት እንዲባርኩት ተደርጓል። እሳቸው የፈቀዱት ነው አይደለም ታያለህ ምን አስቸኮለህ?
አትበሳጭ በተባለው ቡድን ውስጥ እርግጠኛ ነኝ አንተ ያለህበት አይመስለኝም! አይደል? "ዉሾችም ይጮሃሉ ግመሉም ይሄዳል" ማለት ይህ ነው።

Anonymous said...

KeStockholm በከንቱ አትድከም ወንድሜ/እህቴ ኢትዮጵያውስጥ ያለውን ወደ 38 ሺህ ገደማ ቤተክርስቲያን ሁሉ ብጿአን አባቶች ራሳቸው በአካል እየተገኙ የባረኩ ይመስለሃል? አይደለም! እርሳቸው ፈቅደው የሚመለከተውን መባረክ የሚያስችል ሹመት ያለውን ቆሞስ ልከው ያስባርካሉ። የሆነው ይሄ ነው። እርሳቸው ቀድሞውንም በአካል እንደማይመጡ ይታወቃል፤ ውይይት ተደርጎ በብፁዕነታቸው መልካም ፈቃድ የተወከሉት ቆሞስ አባት እንዲባርኩት ተደርጓል። እሳቸው የፈቀዱት ነው አይደለም ታያለህ ምን አስቸኮለህ?
አትበሳጭ በተባለው ቡድን ውስጥ እርግጠኛ ነኝ አንተ ያለህበት አይመስለኝም! አይደል? "ዉሾችም ይጮሃሉ ግመሉም ይሄዳል" ማለት ይህ ነው።

Tigist said...

ከትግስት ተሻለ
ከዚህ ጽሁፍ የምረዳው ቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ላይ መሆንዋን ነው፡፡እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው፤
የይቅርታ አምላክ ነው፤፤ በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ ብለን እንድንጸልይ ነው
ጌታችን መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምረን፤፤ ከሃይማኖት አባት ይህንን ትምህርትና ምሳሌ ነው የምንጠብቀው፤፤ሌላውንማ
አለም ታስተምረናለች፤፤ የቄሱ ጽሁፍ ይህንን የመሰለ አላየሁበትም፤፤ በቂም በቀልና በክፋት በቁጠአ የተሞላ ነው፤፤
የራሳቸውን ንፅህና ለመግለጽ ብቻ ነው የሞከሩት፤፤ ቤተ ክርስቲያናችንን መቀለጃ ላደረግዋት ግን ወዮላቸው፡የእውነት አምላክ መፍረዱ አይቅርም፤ምናልባት ይዘገያል፤፤ ፍቅርን፤ይቅርታን፤ ሰላምን፤ትግስትን፤ስምምነትንና፤አብሮ መኖርን የማያስተምረንን፤ማንንም ቄስ መቀበል የለብንም፤፤ አምላካችን እንዳስተማረን፤በስራቸው የእሱ መሆናቸውን እናውቃቸዋለን፤፤ስለዚህ ማንም እንዳያስተን እናስተውል፤፤
አምላክ ይርዳን፤፤አሜን

Anonymous said...

ዉድ አንባቢያን በቅድሚያ ይህን ተገንዘቡልኝ --- እውነተኛ ካህን እጅግ የማከብረውን ያክል በክህነት ያለአግባብ የሚጠቀሙትንም እቃወማለሁ። ቤተክርስቲያንም በካህናት መመራት እንዳለባት ጽኑ እምነት አለኝ።

ለ Anonymous (May 6, 2012 5:23 PM) said... አስተያየት ሰጪ ---
1. በማስታወቂያችሁ ----- ”በዕለቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፤ የአቡነ ተክለሐይማኖትንና የአቡነ አረጋዊን የቃል ኪዲን ታቦታት አካትቶ የያዘ አዲስ ቤተክርስቲያን የፊታችን ሚያዝያ 21/ 2004 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ. ኤፕሪሌ 29/ 2012፤ እሁድ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ጸሎትና ቡራኬ ተመርቆ ይከፈታል”
ብለው ሲያበቁ--- እርሳቸው ለምን እንዳልተገኙ እያወቅነው ለምን ከእውነት የራቀ ነገር ይጽፋሉ? መቸም አቡነ ኤልያስ አያነቡት ብለው ነው ፈቅደዋል የሚሉን? ፕሪንት እየተደረገ እኮ ይሰጣቸዋል።
2. ለምንስ የሐሰት SMS በተናችሁ?
3. ደግሞም ፍትሐ ነገስት የሚለው ”ሊቀ ጳጳሱ መገኘት ካልቻለ በሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ ቆሞሱ ይባርካል” ነው። እዚሁ ከተማ ውስጥ እያሉ ወደ እናንተ ያልመጡት የምእመናን ተቃውሞ በማየሉ : እርሳቸውም ስላልተስማሙበት ነው። ይሄ ዓይናችሁን ጨፍኑ እና ላሞኛችሁ አያስኬድም። የጽሑፍ ብዛት እኮ ስህተትን ትክክል: ሐሰትንም እውነት አያደርገውም። ምናልባት ኢትዮጵያ እና ከስዊድን ውጭ ያሉ ምእመናን ያምኑዎት ይሆናል እዚህ ላለኖቹ ግን አይሳካልዎትም።
4. ሌላው ልናገረው የማልወድ ግን እርስዎ ስላነሱት የማላልፈው ጉዳይ ---
”ታቦትን የመሰለ ክቡር ነገር አጓጉዞ አምጥቶ ለምዕመን በእጅ መስጠት ተገቢ ነው ወገኖቼ? ይህንን እያደረገ ያለ ካህን ምን እየሥራ ነው ይባላል?” ብለዋል::

ይህን የደረገ ካህን ሥርዓት ጥሷል:: ነገር ግን እርስዎስ የሠሩት ሥራ ምን ይባላል? ከአንድም ሦስት ጽላቶችን ከየት እና በየትኛው ካህን እጅ ይሆን አጓጉዘው ያመጧቸው? ያኔ ተሰደው ሲመጡ ይዘዋቸው እንዳልመጡ በቂ ማስረጃ አለን። አቡነ ኤልያስ ሰጡኝ ብለው ለመሸፋፈን እንዳይሞክሩ አደራ ... እርሳቸው ይህን እንዳላደረጉ ስለምናውቅ። ----- እስኪ ለአሁኑ በዚሁ ይብቃኝ::

ለስርዓተ ቤተክርስቲያን መጠበቅ ብየ አስተያየት ስጽፍ በስህተት የምበድለው ሰው እንዳይኖር አምላኬን እለምናለሁ።

Tigist said...

ከትግስት ተሻለ
ከዚህ ጽሁፍ የምረዳው ቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ላይ መሆንዋን ነው፡፡እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው፤
የይቅርታ አምላክ ነው፤፤ በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ ብለን እንድንጸልይ ነው
ጌታችን መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምረን፤፤ ከሃይማኖት አባት ይህንን ትምህርትና ምሳሌ ነው የምንጠብቀው፤፤ሌላውንማ
አለም ታስተምረናለች፤፤ የቄሱ ጽሁፍ ይህንን የመሰለ አላየሁበትም፤፤ በቂም በቀልና በክፋት በቁጠአ የተሞላ ነው፤፤
የራሳቸውን ንፅህና ለመግለጽ ብቻ ነው የሞከሩት፤፤ ቤተ ክርስቲያናችንን መቀለጃ ላደረግዋት ግን ወዮላቸው፡የእውነት አምላክ መፍረዱ አይቅርም፤ምናልባት ይዘገያል፤፤ ፍቅርን፤ይቅርታን፤ ሰላምን፤ትግስትን፤ስምምነትንና፤አብሮ መኖርን የማያስተምረንን፤ማንንም ቄስ መቀበል የለብንም፤፤ አምላካችን እንዳስተማረን፤በስራቸው የእሱ መሆናቸውን እናውቃቸዋለን፤፤ስለዚህ ማንም እንዳያስተን እናስተውል፤፤
አምላክ ይርዳን፤፤አሜን

Uke said...

1. በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ጸሎትና ቡራኬ ተመርቆ ይከፈታል”
ብለው ሲያበቁ--- እርሳቸው ለምን እንዳልተገኙ እያወቅነው ለምን ከእውነት የራቀ ነገር ይጽፋሉ?
2.እርሳቸውም ስላልተስማሙበት ነው። ይሄ ዓይናችሁን ጨፍኑ እና ላሞኛችሁ አያስኬድም።
3.የጽሑፍ ብዛት እኮ ስህተትን ትክክል: ሐሰትንም እውነት አያደርገውም።
4.ጽላቶችን ከየት እና በየትኛው ካህን እጅ ይሆን አጓጉዘው ያመጧቸው? ያኔ ተሰደው ሲመጡ ይዘዋቸው እንዳልመጡ በቂ ማስረጃ አለን። ከላይ ይህን አስተያየት ለሰጡት አንባቢ ዝርዝር ነገሩን ባላውቅም ትንሽ ፍንጭ ልስጥዎት።
መልስ ከሆንዎት
1. ለምን እንዳልመጡ ወደፊት እርሳቸው የሚገልጹበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚኖርና እዚያው ተገኝተው ቡራኬ እንደሚሰጡ አረጋግጥልዎታለሁ።
2. ተስማምተው ፈቅደው ለካህኑ ደብዳቤ ጽፈው ቤተክርስቲያን እንዲከፈት አረጋግጠው መፍቀዳቸውን በምረቃው ዕለት በቤተክርስቲያኑ የተገኙ ምዕመናን ደብዳቤ በሚገባ አይተን አረጋግጠናል። እርስዎ በጨበጣ ነው የሚያወሩትና ከስህተትዎ ይመለሱ እልዎታለሁ።
3. የጽሑፉን ብዛት ተችተዋል። ለምን ከቻሉ ካህኑ ያስቀመጡትን ጭብጥ የምእመን ድፍረትና ብልግና እያነሱ ነጥብ በነጥብ ይህ ዉሸት ነው ልክ አይደለም አይሉም። እውነተኛ ከሆኑ ካህኑ እንዳሉት እኔ ኧገሌ ነኝ ብለው ወጣ ብለው ያስረዱን። አለበለዚያ ካህኑ እውነት ስላላቸው ነው ደፍረው ለመናገር ያልፈለጉትን ነካክታችሁ ያናገራችሁዋቸውና የጓረ ወሬ ተዉ ጌታዬ።
4. ጽላቶቹን እንዴት አስመጡ እርስዎ? ያሉት ካህኑ እንዴት አድርጎ ማስመጣት እንዳለባቸው እንዲነግርዎት ፈልገው ነው? ነገ እኔ ነኝ ያመጣሁት የሚል አባት ያመጣበትን ደብዳቤ ይዞ ብቅ ቢል እንዳያፍሩ። ሁለትና ሦስት ወር ያህል ጠብቁ ጌታዬ ያዩታል። ይልቅ ሌላ ብዙ ጉድ ካህኑ የሚነግሩን ነገር ነበራቸው። እመለሳለሁ እኔ ነኝ ባይ ከተገኘ ብለዋልና የፈረደብህ እኔ ነኝ በልና ቀጣዩን የደበቁትን ይንገሩን። ዓለም ይማርበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ለማጠቃለል ካህኑ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት መከበር መስዋዕትነት ለመክፈል የቆሙ፤ ጠንካራ እውነተኛና ደፋር፤ ሀገራቸውን የሚወዱ ስለሚመስሉኝ ሌሎችም ካህናት ብዙ ሊማሩበት ይገባል። እምነታችን ጠንካራ መምህራንና ካናት የሚያስፈልጋት ሰዓት አሁን ነው። ኢትዮጵያም ጠንካራና እውነተኛ ልጅ የሚያስፈልጋት ሰዓት አሁን ነው። ከዚህ ካህን ብዙ መማር ችዬአለሁ።

ከወለተ ገብርኤል ዘዋደራ said...

አቡነ ኤልያስ አዲስ ቤተክርስትያን ለመሰረቱት ካህናት እውቅና/ፈቃድ አልሰጡም እያላችሁ የበሬ ወለደ ወሬያችሁን ትታችሁ debrekidusan.se በመግባት በሬው እንዳልወለደ ተመልከቱ፣ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ አውነቱ አንድ ቀን እንደ ጥዋት ጸሃይ ፍንትው ብሎ ሲታያችሁ ለሰራችሁት ስተት ንስሃ ትገባላችሁ ብለን እንጠብቃለን የይቅርታ አምላክ ደግሞ ይቅር ይላችሖል.... የዛ ሰው ይበለን
ለአባ ኒቆዲሞስና ለቀሲስ ፍስሃ የያዛችሁት ስራ በርቱ የሚያሰኝ ነውና በርቱ እላለሁ የአባታችን የእምነቱ ገበሬ አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት ከናንተ ጋር ይሁን አሜን

ከወለተ ገብርኤል ዘዋደራ

Anonymous said...

ዉድ "Uke" በቅንንነት በመነሳት ስለሰጡኝ መልስ አመሰግናለሁ። ነገር ግን ከመለሱ አይቀር ሙሉዉን ነው። ነገር ግን ቀሪዎቹ ጥያቄዎች እንዲመለሱልኝ አልሻም። እኔ የምፈልገው ካህኑ ከአሁን በኋላም ቢሆን አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ ለማድረግ ነው። እንጂ እኮ የማውቀዉን ሁሉ አልተናገርኩም----ያንጻል ብዬ ስለማላምን። ለምሳሌ የጽላቶቹን ሁኔታ ከየት እና በማን በኩል መጡ ብየ ያቆምኩት --- ካህኑ የሠሩት እንደሚታወቅ ተረድተው እንዲታረሙ በማሰብ ነው።

አየህ ወንድሜ ካህን የሁሉ አባት ሊሆን ይገባል--- ለክፉውም ለደጉም: ለእገሌ ፓርቲ ደጋፊም ተቃዋሚም:: በሰንበት እየቀደሱ በአዘቦት እና በምሽት ፓልቶክ ላይ ቁጭ ብሎ የፖለቲካ ሥራ መሥራት ለካህን ተገቢ ነው ትላለህ? በፖለቲካ ሥራ አንዱን ማወደስ አንዱን መርገም ይኖራል እንደምታውቀዉ:: ይህ ግን ለቄስ አይስማማምውም:: ይልቁንም ዘር እና ፖለቲካ ሳይወስነው ሁሉን በአባትነት ማገልገል አለበት። የሁሉ መዳን ሊያሳስበን ይገባል--- እንደ ክርስቲያን እንደ ሃይማኖተኛ ሰው:: በዚህ አጋጣሚ ጊዜያቸውን ሰዉተው ስለሀገር የሚታገሉትን መቃወሜ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት በስደት ሆነንም ልናስከብር አደራ አለብን።

Anonymous said...

Mehret Bemenet

"Ebakachu Band Amelake Seme Yjachhalhu"!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Haymanot mekelegeya aydelem!!! Ande abate yeker tbabelu belo yastarkal enge endet yehe hulu weregbejie ysnzeral? Yehe hulu yemekefafel qalatoch HAYMANOTEN YAWARDAL, EGZEABHEREN YASAZNAL!!!! Meles belen
RASACHENEN ENETYEK??? MANE YDESETAL? SEYTAN!!! BEZEHE ANDBET YTNAGER SEWE ENDETE SEGAWOU DEMU
Mehret Bemenet

YFTETAL????????? MEGEMEREYA MRKDES KMDEFERU BEFIT RASEN AWEKO "NESHA MEGEBATNA LE TEWESEN GEZE BE TSELOT METAGED ALEBET" KALBLZIAMA YE HAYMANOTACHEN SERAT "TEDEFRAL" MALET NEWE!!! ESTEY HULACHENEM BE HBECHA LAYE YE METAWEN...... TETEN BE ANDE EJELEJ TYAYZEN BE ANDE LEBE MEKREN BESELAM BE SWEDEN HGERE LE MENOR YE AMELAKEN SEME BEANDENT ENETRA!!!!!!!!!!!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)